Detecting...

Please whitelist dirzon to continue.

or subscribe for ad-free contenct.

dirzon
  • Convert to Pdf
  • Reading List
  • Summary
  • Audiobook
  • Search
  • Upload
  • myzon
  • Log in
  • Register
English  አማርኛ  Français  العربية
Book of the day

ወንጀልና ቅጣት 2.pdf


  • word cloud

ወንጀልና ቅጣት 2.pdf
  • Extraction Summary

ሲል ጠየቀ እመቤቷ ከሆነች ያም ተስፋ ነው። የእ ራስኮልኒኮቭ የሆነ ነገር እየሰራሁ ነው በማለት ያለውዴታው በቅሬታ ተናገረ የቀ አሁን ማን ይሙት ይህ ኮስማና ፈረስ ሁላችንን በየቤታችን የሚያደርስ ነው። ሚኮልካ ዛሬ ምን ነክቶሀል።እያለ ጮኽኸ ይህች አሮጌ ፈረስ ልቤን ነው ያቆሰለችው ገና ድሮ መገላገል ነበረብኝ እርሷን ማቆየት ዋጋ የለውም ሁላችሁም ተሳፈሩ እያዘለልኩ ነው የማሮጣት። መንገዱን ሁሉ ሊያሮጣት ነው።አለ ምን አገባህ። ምን ነክቶኝ ነው። ምን አይነት ፍሬ ከርስኪ ነው። አንድ ሰአት ተኩል መሆኑ ነው። ብሎ አሰበ አለመረበሽ ነው።

  • Cosine Similarity

እኔ ራሴ ተስፋ ቆርጩ ነበር በወቅቱ ሁኔታውን እኔ ራሴም ቢሆን አልደረስኩበትም ነበር ዳንያ አብራ እየኖረች የእነርሱን ልጆች እንድታስተምር በተቀጠረች ጊዜ በየወሩ የምትከፍለው የአንድ መቶ ሩብል የቅድሚያ ክፍያ ስላገኘች እዳዋን ከፍላ ሳትጨርስ ስራውን መተው አልቻለችም የቅድሚያ ክፍያ የወሰደችውም ተወዳጅ ሮዲ አሁን ሁሉንም ነገር ልገልፅልህ እችላለህ በወቅቱ በጣም ያስፈለገህንና ባለፈው አመት የደረሰህን ስልሳ ሩብል ለመላክ ስትል ነበር በጊዜው ሁኔታውን ሳንገልፅልህ አታለንሀል የነገርንህ ገንዘቡ ከዳንያ ተቀማጭ ሂሳብ የተገኝ አድርገን ነበር ሁኔታው ግን እንዲያ አልነበረም አሁን ግን ሁሉንም ሳልደብቅ እነግርሀለሁ ምክንያቱም ለአምላክ ምስጋና ይግባውና ሁኔታው በአጋጣሚ ስለተለወጠ ነው ዳንያ የቱን ያህል እንደምትወድህና ምን አይነት ብሩህ ልብ እንዳሳት እንድታውቅ ስለምፈልግ ነውመጀመሪያ ላይ ሚስተር ስቪድሪጋሉቭ ዳንያን ያዋርዳትና ለገበታም ቀርባ ጠያፍ አባባሎችን ይሰነዝርባት እንደነበር አይታበልም አሁን ሁሉም ነገር ካለቀለት በኋላ ስለሁኔታው አንስቶ አንተን መረበሹ አስፈላጊ ስሳልሆነ ስለነዚህ አሳዛኝ ዝርዝሮች መግለፅ አልፈልግም በአጭሩ ለማስቀመጥ ያህል የስቪድሪጋሎቭ ሚስትና የተቀረው ቤተሰብ ዳንያን በበጎ አይን ቢመለከቱም በተለይ ሚስተር ስቪድሪጋሎቭ የአልኮል መጠጥ በቀማሰ ቁጥር ዳንያ አይመቻትም ነበር ግና ይህ አይነቱን የሚወገዝ ጠባይ ያሳየበት አውነተኛ ምክንያት የታወቀው እያደር ነበር አይገርምህም። ምን አይነት ብልህና ጎበዝ ልጃገረድ እንደሆነች አሳምረህ ታውቃለህ ዳንያ በጣም ቻይ ነች በቀውጢ ወቅት እንኳን በልቧ ርህራሄ ሳይለያት በፅናት መቆም ትችችሳለች ሳይታሰብ ግን ሁኔታው ወሳኝ ደረጃ ላይ ደረሰ በአትክልት መናፈሻው ላይ ስቪድሪጋሉቭ ዳንያን ሲያባብል ሚስትዬው በአጋጣሚ ሰምታ ኖሮ ከተሳሳተ መደምደሚያ በመድረስ ዳንያን ተወቃሽ አደረገቻት በመናፈሻው ውስጥም በመካከሳቸው አስቀያሚ ሁኔታ ተፈጠረ የስቪድሪጋሎቭ ሚስት አልፋ ተርፋ ዳንያን ደበደበቻት ሰው የሚላትን ሳትሰማ አንድ ሰአት ሙሉ ሰደበቻት በመጨረሻም ዳንያ በተራ ጋሪ ተጭና ወደእኔ እንድትላክ ቀጭን ትእዛዚን አስተላለፈች ልብሶቿንና ጨርቆቿን በወግ ሳይሰበስቡና ሳይቋጥሩ ያገኙትን ሁሉ ከጋሪው ላይ ጫኑት ወዲያውኑም አህያ የማይቸለው ዝናብ መጣል ጀመረ ዳንያ ተዋርዳና ክብሯን ተነጥቃ ለአስራ ሁለት ማይል ርቀት ያህል ሌጣዋን በጋሪ ለመጓዝ ተገደደች ተወዳጁ ልጄ። በማግስቱም ሰንበት ስለነበር ወደቤተክርስቲያን ሄዳ ከእመቤታችን ስዕል ስር ተንበርክካ ለሰራችው ህጢአት ምህረት እየጠየቀች በለቅሶ ተማፀነቻት ከቤተክርስቲያን መልስ ደግሞ ለማንም ሳትናገር ወደእኛ መጣች ተፀዕታ በጣም እያለቀሰች የሆነውን ሁሉ አጫወተችን ዳንያን አቅፋ ምህረት ጠየቀቻት የዚያኑ ጠዋት ጊዜ ሳታባክን በየመንደሩ ወዳሉት ቤቶች ሄደች ክፉኛ መሙ ሥጋ ጨሙጮጋሙጨሥሥሥዘዘዘዘዘበበባዘ በ ዝዘ እያለቀሰች የዳንያን መልካም ጠባይ በታሳቅ ከበሬታ በመግለፅ መወቀስ እንደሌለባት ተናገረች ከሁሉም በላይ ደግሞ ዳንያ ለሚስተር ስቪድሪጋሎቭ የፃፈችውን ደብዳቤ ለሰው ሁሉ እያሳየች አነበበችሳቸው ደብዳቤውን በፅሁፍ እንዲገለብጡትም አደረገች ህ እንኳን ሁኔታውን ማጋነኗ መሰለኝ ሁሉንም በእኩል አይን ሳታይ አንዱን ከሌላው አበላልጣለች የሚል ስሞታ ስለተሰማባትም ሰውን ሁሉ እየጠራች ለአያሌ ቀናት በመንደሩ መቆየት ነበረባት እያንዳንዱ ሰው ደብዳቤው መቼ እንደሚነበብለት በቅድሚያ እንዲያውት ከአደረገች በኋላ በየቤታቸው ወይም በየጎረቤታቸው የተነበበሳቸው ሰዎች በብዛት በተገኙበት ደብዳቤው በንባብ ተሰማ ይህ ሁሉ እንኳን አስፈላጊ አልነበረም ይሁንና እንዲህ አይነት ሴት ነች ያም ሆነ ይሀ በሕብረተሰቡ ዘንድ የዳንያ ክብር ሙሉ በሙሉ እንዲታደስ አደረገች ለዚህ ወራዳ ተግባር ባሏ በቀጥታ ተጠያቂ ስለሆነ ተወቀሰበት አፍር ከበሥች ዘንድ መቅረብ ስለማይችል አሳዘነኝ እንዲሀ ማለቴም በቅሌቱ የደረሰበት ቅጣት ከልክ በላይ እንደሆነ ስለተሰማኝ ነው ወዲያውኑም በግለሰቦች ቤት እንድታስተምር ለዳንያ ብዙ ጥያቂ ቀረበላት እርሷ ግን ጥያቄውን አልተቀበለችውም በአጠቃላይ ለመናገር ያህል ሁሉም ሰው ከመቅፅበት ተለውጦ እርሷን በከበሬታ አይን ማየት ጀመረ የወደፊቱን ትልማችንን ሙሉ በሙሉ የለወጡ ሁኔታዎች ሳይታሰብ ለመቀየራቸው ዋናው ምክንያቱ ይህ ነበር ተወዳጁ ሮዲ ዳንያ የጋብቻ ጥያቄ እንደቀረበላትና እርሷም ፈቃደኛ እንደሆነች ለአንተ መንገር አለብኝ በጥድፊያ የማሳውቅህም ይሄንኑ ነው ምንም እንኳን ይህ ሁሉ የተወጠነው የአንተ ሀሳብ ሳይጠየቅ ቢሆንም እኔን ወይም እህትህን እንደማትቃወመን እርግጠኛ ነኝ ከአንተ መልስ እስከሚመጣልን ድረስ የዳንያን ምላሽ ማዘግየት አለመቻሉን እንደምትረዳልኝ ተስፋ አደርጋለሁና ከዚህም በተጨማሪ አንተ ራስህ ወደ እዚህ እስካልመጣህ ድረስ ለመወሰን ትችላለህ ብዬ አልገምትም ዝርዝር ሁኔታውም እንደሚከተለው ነው በአማካሪነት ደረጃ ያለ የመንግስት ሰራተኛ ነው ስሙም ፒተር ለዚን ነው የስሺድሪጋሎቭ ሚስት የሩቅ ዘመድ ሲሆን ነገሩን ያቀነባበረችው እርሷው ራሷ ነች ከእኛ ጋር ለመተዋወቅ እንደሚፈልግ ለመጀመሪያ ጊዜ የገለፀው በእርሷ በኩል ነበር እኛም ደስ ብሎን ተዋወቅነው አብረን ቡና ጠጣን በማግስቱም ዳንያን ማግባት እንደሚፈልግና ቁርጥ ያለ መልስ እንዲደርሰው በታላቅ ትህትና የጠየቀበት ደብዳቤው ደረሰን የስራ ሰው ነው ስራም ይበዛበታል። በአሁኑ ሰአት ወደ ፒተርስቡርግ ለመሄድ እየተጣደፈ ስለሆነ እያንዳን ደቂቃ ወርቃማ ጊዜ ነች ይሄ ሁሉ ሳናስበው በጥድፊያ የተደረገ በመሆኑ መጀመሪያ ላይ በጣም ተገርመን ነበር የዚያን እለት ጉዳዩን ስናወጣና ስናወርድ የትኛው አማራጭ እንደሚሻል ስናሰላስል ዋልን በጣም አስተማማኝ ሰው ነው ሁለት መደበኛ ስራ አለው ባለገንዘብም ነው እድሜው አርባ አምስት አመት ቢሆንም መልከ መልካም ነው በአሁኑ ደረጃው ቁመናው ሴቶችን ይስባል ብዬ መናገር እችላለሁ ትንሸ ቁጡና እኔ ያልኩት ብቻ ይሁን ከማለቱ በስተቀር በጣም የተከበረ ሰው ነው ይሁንና ሰዎች ለመጀመሪያ ጊዜ ሲቀርቡት እንደዚያ መስሎ ሊታይ ይችላል ተወዳጁ ሮዲ ምናልባትም በቅርቡ ፒተርስቡርግ ከተገናኛችሁ ተናደህ በችኮላ ግምት እንዳትወስድበት እጠይቅሀለሁ በመጀመሪያ ላይ የማያስደስት ነገር ካየህበት ግምት ትወስድበታለህ ብዬ ስለሰጋሁ ነው ይሄን የምጠይቅህ ተወዳጁ ልጄ። እንዲህ የምልህ ለምናልባቱ ብዬ እንጂ በሰውዬው እንደምትደሰት እርግጠኛ ነኝ ከዚህ በተጨማሪ ዘ ቨ ዘ ኽ ስሀተትንና አጉል አስተሳሰብን ማስቀረት የሚቻለው አንድን ሰው ቀስ በቀስና በጥንቃቄ ገምግሞ ማወቅ ሲቻል ብቻ ነው ከአለፈ በኋላ ግን ስህተትንና አጉል አስተሳሰብን ማረምና ማስወገድ በጣም ያዳግታል ከብዙ ሁኔታዎች መገመት እንደሚቻለው ሚስተር ሉዚን በጣም የተከበረ ጨዋ ሰው ነው የስራ ሰው እንደሆነ «የወጣቱን ትውልድ አሳማ» እንደሚከተልና አጉል አስተሳሰቦችን እንደሚዋጋ መጀመሪያ የተገናኘን እለት ነግሮናል ሌላም ሌላም ብሎናል ትንሽ ጉረኛ ከመምሰሉም በላይ ሴሎች ብቻ እንዲያዳምጡት ይፈልጋል ይህ ግን ይሄን ያህል ድክመት አይደለም ሰወዬውን በጥልቀት ባልረዳም በጣም ባይማርም ስልጡንና ደግ ሰው ነው በማለት ዳንያ ነግራኛለች ሮዲ እህትህ እንዴት አይነት እንደሆነች ታውቃለህ ከልምድ አሳምሬ እንደማውቀው ምንም እንኳ በስሜቷ የምትመራ ብትሆንም ጎበዝ አስተዋይ ታጋሽና ደግ የሆነች ልጃገረድ ነች በእርሷም ሆነ በእርሱ በኩል የሚታይ የተለየ ፍቅር የለም ይሁንና ዳንያ ብልህና ብሩክ ልጃገረድ ነች ባሏን የማስደሰት ግዴታ እንዳለባት ትገነዘባለች እርሱም ቢሆን እርሷን ለማስደሰት የሚቻለውን ሁሉ ያደርግ ይሆናል ምንም እንኳ ሁሉም ነገር በጥድፊያ የተከናወነ ቢሆንም ይህን ለመጠራጠር በቂ ምክንያት የለንም ከዚህም በላይ በጣም አስተዋይ ሰው ነው ዳንያን ባስደሰታት ቁጥር የእርሱ የጋብቻ ሕይወት ደስታን እንደሚሳበሰ ይገነዘባል የወደፊቱ ግንኙነታቸው በቅንነት ላይ እስከተመሰረተ ድረስ ነገሮችን በመቋቋም ችሎታዋ ስለምትተማመን የተወሰነ የጠባይ ጉድለት የቆየ ልማድና የሀሳብ ልዩነት ከተዋጣለት ጋብቻ የማይጠፉ ቢሆንም ዳሩ ግን የሚያሳስቡ እንዳልሆኑ ራሷ ዳንያ አጫውታኛለች ለምሳሌ ያህል መጀመሪያ ላይ ግብዝ ሰው መስሎኝ ነበር እንዲህ የመሰለኝ ግን በግልፅ በመናገሩ መሆን አለበት የዳንያ ፍቃደኛነት ከተነገረው በኋላ ለሁለተኛ ጊዜ እንደተገናኘን ግን ሀብት የሌሳትን ችግር የቀመሰች ጨዋ ልጃገረድ የማግባት ፍላጎት ዳንያን ከመተዋወቁ ቀደም ብሎ እንደነበረው በጨዋታችን ሳላይ ገለፀልን ሚስት ባሏን እንደ አጋዥ አድርጋ ብትቆጥር ስለሚሻል ባል ለጥቅም ብሎ ከሚስቱ ጋር ግዴታ መግባት ጭራሽ እንደማይኖርበት ነገረን በትክክል ያላቸውን ቃላት ዘንግቼው አጠቃላይ ሀሳቡን ብቻ ስለማስታውስ ያህል እንጂ እርሱ ግን የተናገረው እኔ ከገለፅኩት በበለጠ መልኩ በተለሳለሰና ትህትናን በተላበሰ መንገድ ነበር ይሄን የተናገረው ደግሞ ሆን ብሎ አይደለም ድንገት ከአፉ አምልጦት የወጣ ቃል ነው ስለሆነም ራሱን ለማረምና ቃሉን ለማስተካከል ሞክሮ ነበር ይሁንና ለዳንያ በኋሳ እንደነገርኳት ሁሉ አባባሉ ትንሽ የሚከብድ መስሎ ነው የተሰማኝ ዳንያ ግን «ንግግርና ስራ ለየቅል ነው» በማለት አልተቀበለችኝም ደግሞም ትክክል ነች ዳንያ ለሚስተር ለዚን የእሺታ መልስ ለመስጠት ከመወሰኗ በፊት ሌሊቱን ሙሉ እንቅልፍ አልተኛችም እኔ የተኛሁ መስሏት ከአልጋ ተነስታ በክፍሉ ውስጥ ሳይ ታች ስትል ነበር በመጨረሻም ከአንድ የተቀደሰ ስእል ስር ተንበርክካ ለረጅም ጊዜ በተመስጦ ፀሎት አደረሰች ሲነጋም ሰውየውን ለማየት መወሰኗን ነገረችኝ ሚስተር ሉሌዚን ወደፒተርስቡርግ እንደሚሄድ የገለፅኩልህ ይመስለኛል የሚያከናውነው ከፍተኛ ስራ አለው በፒተርስቡርግ የሕግ አገልግሎት የሚሰጥ ቤት ለማቋቋም እቅድ ይዞአል ለብዙ አመታት የሕግ ስራ ሲያከናውን ቆይቷል በቀደም እለት ኣንድ ከፍተኛ ሙግት ለመርታት በቅቷል በአሁኑ ጊዜ በከፍተኛው ፍቤት የሚከታተለው ትልቅ ገዳይ ስላለው በፒተርስቡርግ መገኘት አለበት ስለሆነም በብዙ መንገድ አንተንም ሊጠቅምህ ይችላል ዳንያና እኔማ ስራ እንደጀመርክና የወደፊቱ እድልህም እንደተቃና አድርገን ቆጥረነዋል ምኞታችን ከሰመረ አንተ በጣም ስለምትጠቀም የአምላክ ፀጋ አድርገን ነው የምንቀበለው ዳንያ በአእምሮዋ የምታሰሳስለው ይሄንኑ ብቻ ነው እንዲያውም ስለጉዳዩ አንስተን ለሚስተር ሌዚን ጠቆም አድርገነዋል የግድ ፀሀፊ እንደሚያስፈልገወና ለማያውቀው ሰው ደመወዝ ከመክፈል ለዘመድ መክፈል እንደሚሻለው ከገለፀ በኋላ ዋናው ገዳይ ለስራው ብቁ ሆኖ መገኝት ነው በማለት አንተ ብቃት የማይኖርህ ይመስል። ተጠራጥሮ መልሶልናል ወዲያውኑም የዩኒቨርስቲ ትምህርትህ ለቢሮው ስራ ጊዜ ሳይሰጥህ ይችላል የሚል ሥጋት እንዳለው ተናግሯል እንግዲህ እስካሁን ድረስ ጉዳዩ ይህን ይመስላል ዳንያ ግን የምታሰላስለው ይህንኑ ብቻ ነው ባለፉት ጥቂት ቀናት ጉጉቷ ከፍተኛ ደረጃ ላይ በመድረሱ የተነሳ አንተ የሕግ ተማሪ እንደመሆንህ መጠን የሚስተር ሉዚን ረዳት እየቆየ ሲሄድ ደግሞ ሸሪክ የምትሆንበትን እቅድ አውጥታ ነበር ሮዲ እኔ ከእርሷ ጋር ሙሉ በሙሉ እስማማለሁ የእቅልና የተስፋዋም ደጋፊ ነኝ እቅሷና ተስፋዋ ተግባራዊ የማይሆነብት ምክንያት አይታየኝም ሚስተር ለዚን አንተን ገና ባለማወቁ በጥርጣሬ አይን ቢመለከትህም ቅሉ ዳንያ በወደፊቱ ባሏ ሳይ በምታሳድረው መልካም ተፅእኖ የተነሳ ሁሉንም ነገር እንደምታስተካክለው ፅኑ እምነት አላት እርግጠኛ ነች ስለዚህ የሩቅ እቅዳችን በተለይም አንተ ሸሪክ ስለመሆንህ ጉዳይ ለሚስተር ሉዚን ያልነው ነገር የለም የስራ ሰው እንደመሆኑ መጠን ብዙም ሳይጥመው ይችላል ሀሉም ነገር ላም አለኝ በሰማይ እንደሚሉት አይነት መስሎ ሊታየው ስለሚችል ነው ለዩኒቨርስቲ ትምህርትህ የሚሆን ገንዘብ እንዲሰጥህ ዳንያም ሆነች እኔ ያልነው ምንም ነገር የለም ምክንያቱም ወደፊት የሚሆን ጉዳይ ስለሆነና ሃሳቡ ከእርሱ ከራሱ ወዲያው ሊመነጭ ስለሚችል ነው ለዳንያ እምቢ ይላታል ብዬ አልገምትም አንተስ ትገምታለሀ። በተለይም ደግሞ አንተ ራስህ በቢሮው ውስጥ ቀኝ እጁ ልትሆን ስለምትችልና ይህ ገንዘብ በዳረጎት መልክ የሚሰጥህ ሳይሆን ለፍተህ ያገኘኸው ስለሚሆን የእምቢታ ነገር አይኖርም ባይ ነን ዳንያ ነገሮቹን ለማቀናጀት ያሰበችው በእንዲህ አይነት መልኩ ነው እኔም ከእርሷ ጋር ሙሉ በሙሉ እስማማለሁ በሁለተኛ ደረጃ ስለሁኔታው ምንም ያልገለፅንለት በቅርቡ ስትገናኙ ራስህን ዝቅ ሳታደርግ በእኩል ደረጃ እንድታነጋግረው በተለይ እኔ ስለፈለግሁ ነው ዳንያ ስለአንተ አንስታ በከፍተኛ ስሜት ስትነግረው ስለሰው ማለት የሚቻለው በቅርብ ሲያውቁት እንደሆነና አንተን በአካል ከአገኘ በኋላ የራሱን አቋም እንደሚወስድ ገልፆ መልስ ሰጥቷታል ተወዳጁ ሮዲ አሁን እንደማደርገው ሁሉ ከሰርጋቸው በኋላም ለብቻዬ ብኖር ይሻላል ከልጄ እንዳልለይ በማለት አብሬአቸው እንድኖር እርሱ ራሱ እንደሚጠይቀኝ እርግጠኛ ነኝ እስካሁን ድረስ በዚህ ጉዳይ ላይ ምንም ያልተናገረው የተለየ ሃሳብ ስለሌለው ነው እኔ ግን እሺ አልልም እናቶች ጅ ከልጆቻቸው ባሎች ጋር እንደማይስማሙ በሕይወቴ ብዙ ጊዜ አጋጥሞኛል የሰው ሸክም መሆን የምጠላ መሆኔ ብቻ ሳይሆን ለመተዳደሪያ የሚሆን ትንሽ ነገር እስካላጣሁና አንተንና ዳንያን የመሳሰሉ ልጆች እስካሉኝ ድረስ ራሴን ችዬ መኖር እፈልጋለሁህ የሚቻል ከሆነ ጨ ሁለታችሁ ከምትኖሩበት አካባቢ እኖራለሁ ሮዲ እጅግ አስደሳች የሆነውን ዜና ወደደብዳቤዬ ማብቂያ ላይ ሳነሳው ነው ከሶስት አመታት መለየት በኋላ ሶስታችንም ሦ «ዩ መክ። ለጊዜው የፃፈችልህ ምንም ነገር የለም ነገር ግን ብዙ የምትነግርህ ጉዳይ ስላሳት ራሷን ማወክ ካልሆነ በስተቀር በጥቂት መስመር ሀሳቧን መግለዕ ያቅታታልና ብእሯን ለማንሳት አለመድፈሯን እንድነግርህ ጠይቃኛለች በጣም አድርጋ ሰላም ብላሃለች ምንም እንኳ በቅርቡ የምንገናኝ ቢሆንም የምችለውን ያሀል ገንዘብ በአንድ ወይም በሁለት ቀን ውስጥ እልክልሀለሁ ከሚስተር ለዚን ጋር ዳንያ የምታደርገው ጋብቻ ወሬው በመሳ መንደሩ ስለተሰማ እዳዬን በሚመለከት የነበረው ሁኔታ ሳይታሰብ ተሻሸኋል የጡረታ አበሌን በመያዝ ሚስተር ቫክሩሺን ሰባ አምስት ሩብል ለማበደር ወደኋሳ እንደማይል እርግጠኛ ነኝ ሃያ አምስት ወይም ከዚያ በላይ ሰላሳ ሩብል ልልክልህ እችላለሁ ለመጓጓዣ ገንዘብ ያጥረናል ብዬ በመስጋት እንጂ ከዚህም የበለጠ ገንዘብ ለመላክ በቻልኩ ነበር ምንም እንኳ ለጓዝ ማንሻ የሚያስፈልገንን ወጪ ራሱ ሚስተር ሉዚን የቨፈነልን ቢሆንም ፒተርስበርግ እንደደረስን ለመጀመሪያዎቹ ጥቂት ቀናት የሚሆን ትንሽ ገንዘብ መያዝ አለብን ዳንያና እኔ ሁሉንም ነገር በጥንቃቄ አስልተነዋል የጉዞው ወጪ ይሄን ያህል እንደማይሆን ደርሰንበታል ከእኛ መንደር እስከባቡር ጣቢያው ድረስ ያለው ርቀት ስልሳ ማይል ብቻ ነው ለምናልባቴም ብለን ወደዚያው በጋሪ ከሚያደርሰን አርሶ አደር ጋር ተዋውለናል ከዚያም ዳንያና እኔ የሶስተኛ ማእረግ የባቡር ቲኬት እናስቆርጣለን በጉዞው በጣም እንደምንደሰት እርግጠኛ ነኝ ስለሆነም ከዚያም ከዚህ ብዬ ሰላሳ ሩብል ልልክልህ እሞክራለሁ በሁለቱም ገፆች ላይ ጥቅጥቅ አድርጌ ስለፃፍኩ ቀሪ የመፃፊያ ቦታ ያለ አይመስለኝም ጠቅላላ ሕይወታችን ይህን ይመስላል። እቅፍ አድርጌ ደጋግሜ እስምሀለሁ እስከመቃብር ድረስ ያንተው እናት ራስኮልኒኮቭቨ ደብዳቤውን ማንበብ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ፊቱ በእንባ ታጠበ ደብዳቤውን አንብቦ እንደጨረሰ ግን ፊቱ ገረጣ ተጨማደደ የሀዘን ስሜት ወረረው የአረጀ ትራሱን ተንተርሶ ለረጅም ጊዜ ሲያሰላስል ቆየ የልቡ ምት እየጨመረ ሄደ አስተሳሰቡም የተምታታ ነበር በመጨረሻም ቁምሳጥን እንጂ ቤት በማትመስለው በዚያች ጠባብ ክፍል ውስጥ ኩርምት ብሎ ቀረ አይኖቹ ከዚያ ተላቀው ሰፋ ያለ ቦታ ለመቃኘት ፈለጉ ባርኔጣውን ይዞ ከቤት ወጣ ደረጃው ላይ ሰው መኖር አለመኖሩ ደንታ አልሰጠውም ሁሉንም ረስቶታል አጣዳፊ ስራ ያለበት ይመስል መንገዱን ይዞ ቀጠለ አልፎ መንገደኛው እስኪገረምና ሰከሯል ብሎ እስኪገምተው ድረስ እያጉረመረመና አንዳንዴም እየለፈለፈ ሲጓዝ እንደተለመደው ሁሉ ወዴት እንደሚሄድ አያውቅም ነበር የእናቱ ደብዳቤ ክፉኛ ረበሸው መሰረታዊ ነጥቡን በተመለከተ ግን ገና ደብዳቤውን እያነበበ በነበረበት ጊዜ እንኳ ስለሚሰጠው ፈጣን መልስ ጥርጣሬ አላደረበትም። ዳንያ ሊሆን አይችልም። እያለ ከራሱ ጋር ጦፈ ነደደ እናቴ «ስለወጣቱ ትውልድ» ለማውሳት መፈለጓም የሚገርም ነው በእርሷ ቤት ሚስተር ሉዚን ምን አይነት ሰው እንደሆነ መግለጺ ነው። እንዴት አይነት ብልጥ ሴት ነች። ስሜቱ በጣም እየተለዋወጠ ስለሄደ ሚስተር ሉዚንን በዛች ደቂቃ ቢያጋጥመው ኖሮ ምናልባትም ህይወቱን በእጁ ባሳለፋት ነበር ሆኖም እንደሸማኔ መወርወሪያ የሚመላለሰውን ሀሳቡን እያፍተለተለ አንድ ሰው «ምን እንደሚመስል ለማወቅ ቀስ በቀስና በጥንቃቄ መገምገም» ያለበት መሆኑ ትክክል ይመስለኛል አለ ሚስተር ሉዚን ምን አይነት ሰው እንደሆነ ለማወቅ ግን ይህን ያህል አያዳግትም ዋናው ነገር «ልበ ቀና የቢዝነስ ሰው» መሆኑ ነው እስቲ ይታያችሁ በራሱ ወጪ የቤት ዕቃቸውን ለማጓጓዝ ለመላክ ሀሳብ አቅርባል። በተማሪ ስብሰባ ውይይት ወይም ጨዋታ ላይ አይገኝም ራሱን ሳያዝናና አጥብቆ ያጠናል በዚህ ከበሬታ ቢያተርፍም ማንም ሰው አልወደደውም መናጢ ድሃ ቢሆንም የሚመካበት ያለው ይመስል ከሌላው የተቫልኩ ነኝ ብሎ የሚኩራራና ሰው የሚንቅ ነበር አንዳንድ ተማሪዎችማ በአጠቃላይ እድገት እውቀትና አላማ በጣም ርቋቸው ስለሄደ የእነርሱን አሳማና ፍላጎት አሳንሶ የሚመለከትና እነርሱን እንደሕፃን የሚቆጥራቸው አድርገው ይገምቱ ነበር በጣም ጓደኛ ባይሆኑም በተወሰነ ምክንያት ከራዙምኪን ጋር ተቀራረቡ ራስኮልኒኮቭ ግልፅ ሆኖ በይበልጥ እየተግባባው ሄደ ደስተኛ ተግባቢና ጣጣ የለሽ ከሆነው ራዙምኪን ጋር እያደር ለመወዳጀት በቃ ዩን ኣንጂ ጣጣ አያበዛም ሲባል ክብሩን ይጥሳል ማለት አልነበረም የቅርብ ጓደኞቹ ይህን ባህሪውን ከመገንዘባቸውም በሳይ በሁሉም ሰው ዘንድ ተወዳጅ ሆኖ ቆይቷል አንዳንድ ጊዜ ራሱን በመጠኑ ቢጥልም ደደብ አልነበረም ረጅምና ቀጭን ጢሙን በደንብ የማይሳጭ ፀጉረ ጥቁር ነው አንዳንድ ጊዜ ከቁጥጥር ውጭ ልቅ ይሆናል የከፍተኛ የአካል ጥንካሬ ባለቤት ነው የሚል ዝናም አትርፎአል ከሌሎች ተማሪዎች ጋር ሆኖ በአንድ ምሽት ላይ ይዝናና በነበረበት ወቅት ስድስት ጫማ ርዝመት የነበረውን ፖሊስ በአንድ ምት ከመሬት ላይ ዘርሮታል። ያስታወሰው ረሀብ ተሰምቶት በአንድ ምግብ ቤት በኩል ማለፉን ነበር ወደምግብ ቤቱ ገባ ብሎም አንድ ብርጭቆ አረቄ ጠጣ ቁራጭ ኬክ ገመጠ ኬኩን መንገድ ላይ እየተጓዘ በልቶ ጨርሶ ወይን ጠጅን እንጂ አረቄን ከጠጣ ረጅም ጊዜ ስሳስቆጠረ አረቄው ቶሎ ወደአናቱ ወጣ ከመቅፅበት ቋንጃው ተያያዘና እንቅልፍ አሰኘው እንደምንም ብሎ የቤቱን አቅጥጫ ይዞ ከተጓዘ በኋላ ፍፁም ተዳከመ መንገዱን ጥሎ ወደጫካ በመግባት ከሳር ላይ ተዘረረ ወዲያውኑም አሸለበ ሰዎች ጤናቸው ሲታወክ የሚታያቸው ሕልም ጉልህ ቁልጭ ያለና ህያው የመምሰል ባህሪ አለው አንዳንድ ጊዜ ጠቅሳላ ስእሉ አስፈሪ ይሆናል ነገር ግን ሁሉም ነገር ከእነአቀራረቡ ጭምር ተአማኒነት ስለሚኖረው ዝርዝር ነገሮቹ ሁሉ የስነጥበብ ሕግን ተከትለው በግሩም ሁኔታ ስለሚቀረፁ አላሚው የፔሽኪንን ያህል ታላቅ ሰው ቢሆን እንኳ በዝዱ አለም ውስጥ ሆኖ ይህ አይነቱን ስእል ጭራሽ ሊፈጥረው አይችልም እንዲህ አይነቱ ህልም የማያስደስት ህልም ከታየ በኋላ ደግሞ ለረጅም ጊዜ ከአእምሮ አይጠፋም በሰውየው የተዛባ አካል ሳይ ከፍተኛ ስሜት ያሳድራል ራስኮልኒኮቭ ሕፃን ሆኖ በገጠር በኖረበት ጊዜ አንድ አስከፊ ህልም አየ የሰባት አመት ልጅ ሳለ በአንድ አመት በዐል ቀን ከሰዓት በኋላ ላይ ከአባቱ ጋር በመሆን ገጠር ውስጥ ይዘዋወራሉ ጭር ባለ ሞቃት ቀን የሚዘዋወሩበት ስፍራ ልክ በፊት እንደሚያውቀው ነው አካባቢው ጨርሶም አልተለወጠም በገላጣ መስክ ላይ የተቆረቆረችው ትንሺ መንደር ፍንትው ብላ ትታያቸዋለች እይታቸውን የሚጋርድ አንድም ዛፍ የለም ከአድማሱ ባቫገር ብቻ የተሰበጣጠረ ጥቁር ደን ይታያቸዋል በመንደሩ ካለው የመጨረሻው የአትክልት ስፍራ አጠገብ የመሸታ ቤት አለ የማይወደውና ከአባቱ ጋር በዚያ በኩል ባለፉ ቁጥር የሚያስፈራው መሸታ ቤት ነው በአስከፊ ሁኔታ እያጓሩ የሚጮሁ የሚያሽካኩ የሚሳደቡና የሚዘምሩ ሰዎች ከመሸታ ቤቱ አይጠፉም ብዙውን ጊዜም እርስ በርሳቸው ግብ ግብ ይገጥማሉ ከመሸታ ቤቱ አጠገብ ጥንቢራቸው እስኪዞር ድረስ የሰከሩ ሰዎች ስለሚገጥሟቸው እነርሱን ባየ ቁጥር እየተርበተበተ ከአባቱ ጉያ ይሸጎጣል ከመሸታ ቤቱ ብዙም ሳይርቅ ኮረኮንች መንገድ ተዘርግቷል ከመንገዱ ላይ የሚነሳው አቧራ ምን ጊዜም ጥቀርሻ እንደመሰለ ነው አቧራው እየተጠማዘዘ በርቀት ይጓዛል ሶስት መቶ ሜትር ያህል ከተጓዘ በኋላም ወደቀኝ ታጥፎ የመንደሩን መካነ መቃብር ይከባል ከመካነ መቃብሩ መሀል ላይ አረንጓዴ ጣራ ያለው ከድንጋይ የተሰራ ቤተክርስቲያን ቆሟል አይቷቸው የማያውቀውንና ቀደም ሲል ያረፉትን የሴት አያቱን ለማሰብ በአመት ሁለት ጊዜ ዝክር ሲደረግ ወደቤተክርስቲያኑ ይሄዳል በዝክሩ ላይ ሲገኙ ከነጭ ዝርግ ሰሀን ሳይ ሆኖ በነጭ ወረቀት የተሸፈነ ልዩ ምግብ ይዘው ይሄዳሉ ምግቡ ጣፋጭ ሩዝ ሆኖ በላዩ ላይ በመስቀል መልክ የተቀረፀ ዘቢብ ጣል ጣል ይደረግበታል ጥንታዊ ስእሎችና ጭንቅሳታቸውን የሚነቀንቁ ሽማግሌ ቄስ የሚገኝበትን ያን ቤተክርስቲያን ይወደዋል ሐውልት ከተሰራለት ከሴት አያቱ መቃብር አጠገብ የማያውቀውና የማያስታውሰው በመንፈቅ እድሜው የሞተ ሽ ወንድሙ አነስተኛ መቃብር አለ ይሁንና ትንሽ ወንድም እንደነበረው ስለተነገረው ወደመካነ መቃብሩ በሄደ ቁጥር የወንድሙን መቃብር ጎንበስ ብሎ በክብር ይሳለማል በህልሙ ያየው አባቴና እርሱ በኮረኮንቹ መንገድ አድርገው ወደመካነ መቃብሩ ሲሄዱና በመሸታ ቤቱ በኩል ሲያልፉ ነው የአባቱን እጅ ይዞ የመሸታ ቤቱን በፍርሀት ትክ ብሎ ይመለከታል የነበረው ልዩ ሁኔታ ትኩረት አሳደረበት የባለእጆች ሚስቶች የአማሩ ልብሶቻቸውን ለብሰው ሴት አርሶ አደሮች ከነባሎቻቸው እንዲሁም የተናቁት የህብረተሰብ ክፍሎች ሁሉ ተኮልኩለዋል ሁሉም የስካር መንፈስ ተጭኖአቸው ይዘፍናሉ ከመሸታ ቤቱ ደጃፍ አጠገብ በትላልቅ ፈረሶች የሚጎተት የጭነት ማጓጓዣ ጋሪ ቆሟል። ሌሳም ሰው ስለሚልኩ ራስሽ ለመወሰን ትችያለሸ አንድ ብርጭቆ ሻይ አዘጋጅቼ እጠብቅሻለሁአለች የነጋዴው ሚስት ሊሳቬታ ፈራ ተባ እያለች ይሁን እሺ እመጣለሁ ብላ በዝግታ እየተራመደች ገዞዋን ቀጠለች ራስኮልኒኮቭ ተጨማሪ ንግግር ሳይሰማ ወዲያውኑ አካባቢውን ለቀቀ እያንዳንዷን ቃል ለማሰላሰል አየሞከረ ሳይታይ ቀስ ብሎ እብስ አለ እንሸርት ውሃው የፈሰሰ ይመስል አድሮበት የነበረው የመገረም ስሜት ቀስ በቀስ ወደመሸበር ስሜት እየተለወጠ ሄደ በማግስቱ አንድ ሰዓት ላይ የአሮጊቷ እህት የሆነችውና አብራት የምትኖረው ብቸኛ ሰው ከዚያ ቤት የማትኖር መሆኗን ሳያስበው በድንገት ደረሰበት እናም አሮጊቷ ልክ አንድ ሰዓት ሲሆን ቤት ውስጥ ብቻዋን ትጎለታለች ከቤቱ አቅራቢያ ነበር ወደ ክፍሉ ሲገባ የሞት ቅጣት የተወሰነበት ሰው ይመስል ነበር ስለምንም አላሰበም ማሰብም አልቻለም ከመቅፅበት ሁሉም ነገር በማያሻማ መልኩ በውስጡ ስለተወሰነ ከእንግዲህ የማሰላሰል አቅም እንደሌለው ተሰማው እቅዱን ተግባራዊ ለማድረግ አንዴ እስከቆረጠ ድረስ አመቺ ሁኔታ ለአመታት ያህል ቢጠብቅ እንኳን በአጋጣሚ ከተገኘው ከአሁን ሁኔታ የተሻለ ዕድል እንደማይኖር እርግጠኛ ሆነ ከእንግዲህ ለአደጋ ሳይጋለጥና ከፍተኛ ክትትል ሳያደርግ የመግደል ሙከራ የሚፈፀምባት ሴት ነገ በዚህ ሰዓት ብቻዋን ከቤቷ እንደምትገኝ እርግጠኛ ሆነ ይህን ምሥጢር በትላንትናው እለት ቢሆን ኖሮ ጭራሽ ለማወቅ ባልቻለ ነበር ሪ ነጋዴዋና ሚስቱ ሊሳቬታን የቀጠሩበትን ምክንያት ራስኮልኒኮቭ በኋላ ተገነዘበ ምንም የተለየ ነገር ለሊለው ተራ ቢዝነስ ነበር የቀጠሯት ወደፒተርስቡርግ ለመኖር የመጡና ቀን የጣላቸው ቤተሰቦች የሴት ልብሶች ለመሸጥ አስበው ገበያ አውጥተው በርካሹ ከሚጥሏቸው ይልቅ በሰው በኩል ለመሸጥ ደሳሳ ፈልገዋል ሊሳቬታ ደግሞ ይህ አይነቱን ቢዝነስ ትሰራለች የሳልቫጅ ልብሶችን እየገዛች ትሸጣለች ከታማኝነቷ በላይ የምትሸጠው በዝቅተኛ ዋጋ ስለሆነ ብዙ ደንበኞች አትርፋለች የምትጠይቀው ዋጋ ሁሉ ተቀባይነት ያገኛል ከዚህም በተጨማሪ በፊት እንደተባለው ሁሉ ታዛዥና ፈሪ ሴት ስለነበረች ለፍልፋ ተናግራ ሰው አታስቀይምም ራስኮልኒኮቭ ከአለፈው ወር አካባቢ ጀምሮ አጉል እምነት ተጠናውቶታል። ለዚህም ማረጋገጫው ብዙ ወንዶችን የምትስብ ሆና መገኘቷ ነው ጭምት ቢጤ ነች ጨዋ አይን አፋርና እሺ ባይ ነች ለተጠየቀችው ሁሉ መልሷ እሺ ነው ግሩም ፈገግታ ደግሞ አላት ማራኪ ሆና አግኝተሀታል ማለት ነውአለና መኮንኑ ሳቀ አዎ የምትገርም ፍጡር ስለሆነች እወዳታለሁ አንድ ነገር ላጫውትህ ያቺን የተረገመች አሮጊት ገድዬ ያላትን ሁሉ እዘርፋለሁ ይሄን የማደርገው ደግሞ ያለአንዳች ሀዘኒታ እንደሆነ አረጋግጥልሀለሁሲል ተማሪው በስሜት ተገፋፍቶ ነበር የተናገረው መኮንኑ በድጋሚ ቢስቅም ራስኮልኒኮቭ ግን በሁኔታው ተገረመ እሰቲ ይታይህ አንድ አቢይ ጥያቄ ልጠይቅህ በርግጥ መቀለዴ ቢሆንም ሁኔታውን በዚህ መልኩ ተመልከተው በአንድ በኩል ደደብ ርካሽ እርጉም ደቃቃ አሮጊት ማንንም ሳትጠቅም ሀሉንም የምትጎዳ ከይሲ ለምን እንደምትኖር የማታወቅና ወጣም ወረደ በቅርቡ የምትሞት ፍጡር ነች። ካፖርቱ በጣም ሰፊ ስለነበረም እጁን በኪሱ ውስጥ ከትቶ የያዘው ነገር ያለ አያስመስልም ሲባነውን የማንጠልጠል ሀሳብ የመጣለትም ከሁለት ሳምንት በፊት ነበር የክፍሉን የግራ ጥግ ይዞ ከተዘረጋውና ለደቂቃ ያህል ሲመነቃቅረው ከቆየው ከቱርክ ፎቴ በስተጀርባ ወደነበረው የተሰነጣጠቀ ግድግዳ እጁን ሰደደ ከረጅም ጊዜ በፊት አዘጋጅቶት በዚያው የደበቀውን ለመበደሪያ የሚውል የማስያዣ ዕቃ አወጣ እቃው ግን አስይዘውት ብድር የሚያስገኝ አይደለም ከብር በተሰራ የሲጋራ ማስቀመጫ መጠን የተዘጋጀ የተላገ እንጨት ነበር የሆነ ዐውደ ተግባር ይካሄድበት በነበረ አካባቢ ሲዘዋወር ያገኘው እንጨት እንጂ ሌላም አይደል በዚያኑ ወቅት ከመንገድ ያገኘውን የብረት ቁራጭ በተላገው እንጨት ላይ አስቀምጦ ሁለቱንም በመስቀል ቅርፅ ጥፍር አድርጎ አሰረ ከዚያም በንፁሕ ነጭ ወረቀት በጥንቃቄ ጠቀለሳቸውና በቀጭን ሪበን አሁንም በመስቀል ቅርፅ አይነት አሰረ አስተሳሰሩ ግን ለመፍታት ጊዜ በሚወስድ አይነት የተደረገ ነበር ይህን ያደረገውም አሮጊቷ ለመፍታት በምትታገልበት ጊዜ እርሱ በቂ ጊዜ እንዲያገኝና እርሷም እንዳታተኩርበት በማሰብ ነበር የብረቱ ቁራጭ የተጨመረው ለክብደት ሲባል ነው ይህ ከሆነ ዕቃው ከእንጨት የተሰራ መሆኑን አሮጊቷ መገመት አትችልም እንደዚህ አድርጎ ያዘጋጀው ዕቃ ነበር ከፎቴው በስተጀርባ በስውር የተቀመጠው ዕቃውን በእጁ እንዳስገባም አስራ ሁለት ሰአት ከአለፈ ቆየ እኮ። ይህ ከሆነ በርግጥ ጥርጣሬ የሚያስነሳና ለጥርጣሬም ምክንያት ሊሆን የሚችል ነገር ነው ይሁንና እነዚህ ሁሉ አጥብቆ ያላሰበባቸው ዝርዝር ነገሮች ነበሩ ከዚህም በተጨማሪ ስለእነርሱ እያወጣና እያወረደ ጭንቅላቱን የሚረብሽበት ጊዜ አልነበረውም ዋናው ነጥብ ነበር አእምሮውን ሲያስጨንቀው የቆየው እርሱ ራሱ ስለሁሉም ነገር እርግጠኛ እስከሚሆን ድረስም ስለ ጥቃቅን ነገሮችን ላለማሰላሰል ወሰነ ስለሁሉም ነገር እርግጠኛ መሆን ፍፁም የማይቻል መስሎ ታየው ለምሳሌ ያህል ተነስቶ ወዲያውኑ ወደዚያ መሄዱን ማሰብ የሚተወበት ጊዜ ይመጣል ብሉ አልገመተም በቅርቡ ወደ አሮጊቷ በመሄድ ዙሪያውን ቃኝቶ ያደረገው ልምምድ እንኳን ድርጊቱን ስለመፈፀሙ ቆርጦ የተነሳበት ጉዳይ አልነበረም። በልቡ ግን አሁንም ራሱን ዝግጁ አድርጎ አልቆጠረም ወደዚያ የሄደውም ሌላ ሰው ገፋፍቶትና አስገድዶት ይመስል እያመነታ ነበር ይሁን እንጂ በዚህ የመጨረሻ ቀን ሳይ ሳይጠበቅ ሁሉንም ነዢ በመወሰን ራሱን ከመቅዕበት ለወጠ የካፖርቱ ጫፍ በመኪና ቸርኪዎ ውስጥ ተሰግስነ እርሱንም ጎትቶ ያስገባው ይመስል ነበር የሆነ ሰው በእጁ ይዞ እየጎተተው ሳያመነታ እንዲከተለው የተደረገ አይነት ሆኖ ተሰማው ከሞላ ጎደል ሁሉም ወንጀል ለምን በቀሳሉ ይፈፀማል። ሲል አማረረ በድንገት አይኑን ወደ አንድ ሱቅ ሲያነጣጥር በግድግዳው ላይ የተሰቀለ ሰዓት አይቶ አንድ ሰዓት ከአስር ደቂቃ መሆኑን ተመለከተ በቤቱ ጀርባ በኩል ዞሮ ለመግባት ተጣደፈ ከዚህ በፊት ሁኔታውን ሲያወጣና ሲያወርድ አስከፊ ጭንቀት ይገጥመኛል ብሎ ያስብ ነበር አሁን ግን እንኳን ሊጨነቅ ቀርቶ ቅንጣት ያህል እንኳን አልፈራም በዚያን ጊዜ አእምሮው ከአሁኑ ድርጊት ጋር ያልተያያዙ ዝባዝንኬ አስተሳሰቦችን አስተናግኗል በአቅራቢያው የነበረውን የመናፈሻ ስፍራ አልፎ ሲሄድ አካባቢውን ወደላይ በሚለቀቅ ውሃ በማየቱ የማሻሻሉ ጉዳይ ክፉኛ መሰጠው ይህ ከሆነ የአደባባዩ አየር ግሩም መአዛ ይኖረዋል ብሎ አሰበ የአትክልት ስፍራዎች ከተስፋፉ ከተማው በግሩም ሁኔታ ያሸበርቃል ከሚል መደምደሚያ ደረሰ ወዲያውኑም ሌላ ሀሳብ መጣለት በትላልቅ ከተሞች ውስጥ ያሉ ሰዎች የሚሰባሰቡት አትክልትና የሚለቀቅ ውሃ ባለበት አካባቢ ሳይሆን ቆሻሻ ሽታና ክርፋት በተንሰራፉበት አካባቢ መሆኑ አስገርሞት ምክንያቱን ጠየቀ ራሱም ቆሻሻ በበዛበት የገበያ ስፍራ ያደረገውን ጉዞ ከአስታወሰ በኋላ እንደመንቃት ብሉ ምን አይነት ፍሬ ከርስኪ ነው።

  • N.B. This Summary is Very Experimental!! based on the following scripts from:
    • https://github.com/millzon/textSummarizer-am
    • https://github.com/icoxfog417/awesome-text-summarization#motivation
Download Searchable PDF Download PDF

Comments:


memezon

Download options | Convert to Pdf | Book of the day

© dirzon | Terms of Service | Privacy | About | Services | Contact