Detecting...

Please whitelist dirzon to continue.

or subscribe for ad-free contenct.

dirzon
  • Convert to Pdf
  • Reading List
  • Summary
  • Audiobook
  • Search
  • Upload
  • myzon
  • Log in
  • Register
English  አማርኛ  Français  العربية
Book of the day

መልክእ ምንድን ነው.pdf


  • word cloud

መልክእ ምንድን ነው.pdf
  • Extraction Summary

መልክእ መልክእ ምንድን ነው። አንድ ሰው በየወሩ ከደመወዙ ወይም ከገቢው ላይ ተምኖ በወር ይኸን ያህል እሰጣለሁ ማለት ይችላል ሳይተምንም እንዲሁ በትሩፋት መስጠ ት ይችላል ነጋዴና ገበሬ አሥራት የሚያወጡት እንዴት ነው። ስለ ወርኃዊና ዓመታዊ አስተዋጽኦ በቃለ ዓዋዲው «አንቀጽ ቁጥር ሀ «ገቢ ያለው ካህንም ሆነ ምእመን ለሰበካው ቤተ ክርስቲያን አስተዋጽኦ አሥራት ብር ከአንድ ብር እስከ ሃያ አራት ብሩን ከከፈለ በኋላ ለቤተ እግዚአብሔር ከዚያም በላይ ማድረግ አለብኝ ብሎ ካደረገ ትሩፋት ነው አሥራት የሚከፈለው ለሰበካ ጉባኤ በደረሰኝ ብቻ ነው። ይህን ጥያቄ ከመመለሳችን በፊት ልንገነዘበው የሚገባ ጉዳይ አለ ሕዝቡ የባሕል ግጭት አለበት ችግሩ የባሕል ግጭቱን ማስታረቅ አለመቻላችን ነው የባሕል ግጭቱ ምንድ ነው።

  • Cosine Similarity

ይህ ፍቺ በብዙ የቤተ ክርስቲያንም ሆነ ዘመናዊ ሊቃውንት ተቀባይነት ያገኘ ነው አለቃ አያሌው ታመሩ እነዚህ ግጥሞች የባለመልክኡን መልክ ከስሙ በመጀመር ከራስ ፀጉሩ እስከ እግር ጥፍሩ ድረስ በቅደም ተከተል በስንኝ የሚያመሰግኑ ናቸው ይላሉ እንደ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ የአለቃ አያሌውም ፍቺ የመልክእን ዋና ዋና ባሕርያት ማለት ገላጭ መሆኑን የሰውነት አካላትን መዘርዘሩን ምስጋና መሆኑንና በስንኝ መጻፉን ይጠቅሳሉ በነዚህ ሁለት ፍቺዎች መካከል ያለው ልዩነት የመልክእን የምስጋና መጀመሪያ ክፍል በመጥቀስና ባለመጥቀስ ነው ፖላንዳዊው ምሁር አሌክሳንደር ፌሬንክ መልክእን ሲፈታው «የባለመልክኡን የተለያዩ የሰውነት አካላት በአብዛኛው ከራስ ጀምሮ እስከ እግር ድረስ የሚያመሰግን ገላጭ ግጥም ነው» ይላል ይህ የፌሬንክ ፍቺም ከላይ ከጠቀስናቸው የቤተ ክህነት ሊቃውንት ፍቺዎች ጋር የተመሳሰለ ነው ከጥቂት ልዩነቶች በቀር ፌሬንክ መልክእ የሚጀምረው ከራስ ነው በማለት ስምንና ፀጉርን ሳይጠቅስ ያልፋቸዋል ሌላው ሀርደን የተባለ ምሁር «መልክአ የእያንዳንዱን ቅዱስ የሰውነት አካል እየዘረዘረ በአንዳንድ አርኬ የሚመሰገንበት መዝሙር ነው» ይላል ይህ ፍቺ የሰውነት አካላት በቅደም ተከተል ስለመመስገናቸው አይናገርም እርግጥ ብዙ አርኬዎች ያሉት መሆኑን ይጠቅሳል አንድ አርኬ ለአንድ የሰውነት ክፍል በማለት ቢሳሳትም በተጨማሪም መልክእ የሚጻፍላቸው ቅዱሳን ብቻ እንደሆኑ ያስመስላል ከዚህ በላይ የተጠቀሱት የመልክእ ፍቺዎች በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ባለ መልክኦቹ የተለያዩ ብልቶች ያላቸው ግዙፍ አካል እንደሆኑ ይጠቅሳሉ ግዙፍ አካላት የሌላቸው መልክእ የተጻፈላቸው አሉ ከእነዚህ ግዙፍ አካል ሳይኖራቸው መልክእ ከተጻፈላቸው ውስጥ ንዋያተ ቅድሳት የጸሎት መጻሕፍትና ልዑል እግዚአብሔር ይገኙበታል ለምሳሌ ያህል ጠቢበ ጠቢባንን መልክአ መስቀልን መልክአ ሰንበትን መልክአ አንቀጸ ብርሃንን መጥቀስ ይቻላል ስለዚህ መልክእ ማለት የባለመልኩን የሰውነት አካላት እናወይም ሌሎች ነገሮችን በማመስገን ምሕረትን የሚለምን ባለብዙ አርኬዎች የምስጋና ግጥም ነው መልክአ መልክእ የተጀመረበትና የቆመበት ዘመን መልክአ መልክእ መጻፍ የተጀመረበትን ጊዜ በእርግጠኛነት መናገር አይቻልም እኔ እስከማውቀው ድረስም ይህንኑ በእርግጠኛነት የተናገረ ተመራማሪ የለም መልክአ መልክእ መድረስ የጀመሩበትን ሳይሆን በስፋት የተጻፉበትን ዘመን ኛው ምእተ ዓመት የሚያደርጉ አሉ ፌሬንክ ዓለማየሁ ሞገስ ወደ ኛ ምእተ ዓመት ይወስዱታል እንደ ፔደርሰን ያሉት ደግሞ መልክእ እስከ ኛ ምእተ ዓመት ድረስ እንዳልተጀመረ ይናገራሉ የዚህ ሁሉ ልዩነት መነሻው ድርሰቶቹ በተጻፉበት ብራና ላይ ጊዜን የሚጠ ቁም ምንም ነገር አለመገኘቱ ነው «እግዚአብሔር መልክ አለው ወይስ የለውም» የሚለው ጉዳይ በአፄ ዘርዐ ያዕቆብ ጊዜ ያወዛገበ ነገር ነበር ሩንግሬን ደቀ እስጢፋ የተባሉ የድንግል ማርያምን የመላእክትን የቅዱሳንንና የጻድቃንን ከእግዚአብሔር የማማለድ ጉዳይን ያልተቀበሉት በዚያው ዘመን የተነሥ ነበሩ እነዚሁ ሰዎች ለቅዱሳንና ለሥዕለ አድኅኖ ክብር የሚሰጠውን ስግደትም ይቃወሙ ነበር ይህ የደቀ እስጢፋ እንቅስቃሴ በቤተ ክርስቲያን ኑፋቄ ነው ተብሎ በንጉሠ ፍርድ የከፋ ቅጣት ተፈጽሞባቸዋል ይህ ውዝግብ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንትን የምልጃን ኃይልና ለቅዱሳንና ለሥዕሎቻቸው መስገድን የሚያረጋግጠበትን አዲስ የግእዝ ግጥም ስልት እንዲያስገኙ ግፊት የሆናቸው ይመስላል ይህ መላምት እውነት የሚመስለው በዚያ ዘመን ይህን ኑፋቄ የሚቃወሙ ብዙ ሃይማኖታዊ ጽሑፎች በመውጣታቸው ነው የሚከተለው አርኬ የዚህን ኑፋቄ ችግር ያነሣል ሰላም ሰላም ለመልክአ ሥዕልኪ ኩሉ እምነ ፀሐይ ወወርኅ ዘያበርህ ሥነ ፀዳሉ ወበእንተዝ ማርያም ሰብአ ቤትኪ ይብሉ ስብሐት ወክብር ወሰጊድ ለመንግሥት ይደሉ ማርያም በረከትኪ ምስሌነ የሀሉ መልክአ ሥዕል አርኬ ይህ አርኬ ለቅድስት ድንግል ማርያም መስገድ ተገቢ መሆኑን ይናገራል የሚከተለውም ስንኝ ይህንኑ ኑፋቄ በቀጥታ ያወግዛል ሰላም ለማርያም ዐጽፈ ወልድ ዋሕድ ወመንበረ ሕያው ነድ ለድንግልናሃ ይደሉ ሰጊድ ለማርያም ዘይቤ ኢይስግድ ሞጸፈ መብረቅ በሊኀ በርእሱ ለይረድ መልክአ ሥዕል ዳግሚት አርኬ ከዚህ በላይ የጠቀስኳቸው ሁለት አርኬዎች የስግደትን ተገቢነትና ስግደትን መቃወም ኑፋቄ እንደሆነ የሚያስረዱ ናቸው ሌላው ይህን መላምት የሚደግፈው በየገድላቱ መጨረሻ ወይም መጀመሪያ መልክእን መጨመር ልማድ መሆኑ ነው ገድላት በአፄ ዘርዐ ያዕቆብ ዘመነ መንግሥት መጻፍ እንደተጀመሩ ይነገራል አምሳሉ ስለዚህ መልክእም በዚያው ጊዜ መገጠም ጀመሮ ሊሆን ይችላል የሆነው ሆኖ ይህ ጉዳይ የብራናዎቹን ጥልቅ ጥናት የሚሻና የባለመልክኦቹን ታሪክ ማጥናትን የሚጠይቅ የምርምር መስክ ነው ደራሲ የሁሉም መልክአ መልክእ ደራሲዎች በአብዛኛው አይታወቁም እያንዳንዱ የመልክእ ደራሲ በድርሰቱ ውስጥ የራሱን የተለየ የአጻጻፍ ስልት ስለማይጠቀም ይህ ጉዳይ ብዙም ችግር አይሆንም የሥነ ቃል ደራሲው አይታወቅም ደራሲያቸውን ልዩ ስልት ሳይጠቀሙ ራሳቸውን ሆን ብለው ያልጠቀሱ በመሆናቸው ነው የመልክአ መልክእ ደራስያን እንደ ባለቅኔዎች አካባቢን በመከታተልና በምናብ ምጥቀት አይታወቁም አያሌው አንደ ተማረና ጥሩ መናገር መጻፍ እንደሚችል ሰው እንጂ የመልክአ ክብሩ በደራሲው ታላቅነት ሳይሆን በባለመልክኡ ታላቅነት ነው በመልክአ መልክእ ውስጥ የሠፉሩት የአንድ ሰው ስሜትን የያዙ ሳይሆኑ ለሁሉም ሰው የሚሆኑ ምስጋና ኑዛዜ ምሕረትና ልመናን የያዙ ናቸው የመልክአ መልክእ ደራስያን የአጻጻፍ ልማድን ተከትለው የሜጽፉ ናቸው ደራስያኑ የሚጽፉበት ርእሰ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የአጻጻፍ ስልቱም የሚይዙት ስሜትም ተወስኖ የተሰጣቸው ነው አንድ ጊዜ የአጻጻፍ ስልቱ ካደገ በኋላ የመልክእ ቅር እንደ ሕግ ተይዞ ተከታዮቹ እንዲከተሉት ሆኗል ስለዚህም ግላዊ የሆነው ስሜታቸው በሚጽፉት መልክእ ውስጥ ሊገለጽ አይችልም ዋና ጉዳያቸው ያጻጻፍ ሥርዓቱን ተከትለው መጻፍ ነው በአጠቃላይ መልክአ መልክእ ግልጽ የአጻጻፍ ስልት ያለው የአካላት ገለጻ ነው ስለዚህም ሊነበቡ የሚገባቸው በማስተዋል ነው መልክአ መልክእ ለጸሎትነት የሚያገለግሉ ግጥሞች ናቸው ምሕረትን የሚለምኑትም ደራሲዎቹ ብቻ ሳይሆኑ ጸሎተኛው ራሱን በደራሲው ቦታ ተክቶ እኔ አያለ ይናገራል ይህ ራስን በደራሲው ቦታ ማስቀመጥ ደራሲውን ከአንባቢው አእምሮ ያርቀዋልፈ ይህም ጸሎተኛው የሚያቀርበው የምስጋናና የልመና ጸሎት የራሱ አድርጎ እንዲቆጥር ያደርገዋል ይህን የሚያስረዳ ምሳሌ ልስጥ ማኅበረ ምእመናን ወምእመናት እለኪያከ ተአመኑ ለነሚአ ሥጋከ ወትረ ኀበ ተዐየኑ ወልደ አብ ክርስቶስ ዘኢትትፈለጥ እም ሕፅኑ እሰብክ ሎሙ ሕማመከ ወመስቀልከ እዜኑ ጸጋ መንፈስ ቅዱስ ሊተ እምሰማይ ፈኑ መልክአ ቁርባን አርኬ ይህ ግጥም የሚደገመው በካህናት ሲሆን ካህኑ ሁሉ ራሱን በደራሲው ቦታ እንዲተካ የሚያደርግ ነው ባለመልክእ ባለመልክኦቹን በሚመለከት እስካሁን የተጻፉት መልክአ መልክእ በአራት ይከፈላሉ ሀ እግዚአብሔር ለእግዚአብሔር ሥላሴ የተጻፉ መልክአ መልክእ አሉ ለምሳሌ መልክአ እግዚአብሔር አብ ጠቢበ ጠ ቢባን መልክአ ጳራቅሊጦስና መልክአ ሥላሴ ይጠቀሳሉ ለ መላእክት ለመላእክት የተጻፉ ብዙ መልክአ መልክእ አሉ እነዚህን ለሁለት መክፈል እንችላለን በወል ስም የተጻፉና ለእኔ ባይ የተጻፉ የወል ስም ለተሰጣቸው መላእክት የተጻፉ እንደ መልክአ ዑቃቤ መልአክ እና መልክአ መላእክት ያለ እኔ ባይ ሊሆኑ የተጸውኦ ስም ላላቸው መላእክትም በስማቸው መልክአ መልክእ የተደረሰላቸው ሲሆን ለምሳሌም መልክአ ሚካኤልንና መልክአ ገብርኤልን መጥቀስ ይቻላል ሐ የሰው ልጆች ለቅዱሳን ለሰማዕታትና ለጻድቃን የተጻፉ ብዙ መልክአ መልክእ አሉ እነዚህንም እንደላይኛው ለሁለት መክፈል እንችላለን የወል ስም ያላቸው እንደ መልክአ ሰማዕታት መልክአ ነቢያት መልክአ ጻድቃን መልክአ ሠለስቱ ምእትና የመሳሰሉት ናቸው እኔ ባይ የተጸውኦ ስም ለተሰጣቸው የተጻፉ አሉ መልክአ ጊዮርጊስ መልክአ አዳም ከዚህም በተጨማሪ በቤተ ክርስቲያን ጻድቅ ናቸው ተብለው ላልተከበሩ ነገሥታትም መልክእ ተደርሶላቸዋል መልክአ አፄ ተዎድሮስ መልክአ አፄ ዮሐንስ መልክአ አፄ ምኒልክና የመሳሰሉት መ ረቂቅና ሕያው ያልሆኑ ለረቂቅ ሐሳቦችና ሕያው ላልሆኑ ግዑዝ ነገሮች መልክአ መልክአ ተጽፎ አእናገኛለን ረቂቅ ሐሳቦች ማለት እንደ ፍቅር ባሕርይና ጠባይ ሲሆኑ ለነዚህ መልክአ ፍቅር መልክአ ባሕርይ መልክአ ጠባይ መልክአ ሰንበት የሚሉ መልክአ መልክአ ተጽፈውላቸዋል ሕያው ያልሆኑ ነገሮች ያልኳቸውም ንዋያተ ቅድሳት የጸሎት መጻሕፍትና የመሳሰሉት ሲሆኑ በዚህ ክፍል መልክአ አንቀጸ ብርሃን መልክአ ሥዕልና መልክአ ቤተ ክርስቲያንን በምሳሌነት መጥቀስ ይቻላል አንዳንድ ባለመልክእ ግዙፍ አካልና ሰብአዊ መልክእ ባይኖራቸውም እንዳላቸው ተደርጎ በሰውኛ ተጽፎላቸዋል ለምሳሌ መልክአ ቤተ ክርስቲያን መልክአ ፍቅር እና መልክአ ሰንበት ሰብአዊ አካል እንዳላቸው ተደርጎ ተጽፎላቸዋል በቤተ ክርስቲያን በልዩ ክብር የሚታዩ አንዳንድ ባለመልክአ መልክእ በስማቸው የተለያዩ ብዙ መልክአ መልክእ ተደርሶላቸዋል ለምሳሌ የባለመልክኡን ልዩ በዓላት በማሰብ መልክአ መልክአ ይጻፋል ለምሳሌ ለኢየሱስ ክርስቶስና ለድንግል ማርያም የተደረሱትን እንመልከት መልክአ መልክእና ቅዳሴ ለኢየሱስ ክርስቶስ ለድንግል ማርያም መልክአ ኢየሱስ መልክአ ማርያም መልክአ ዐማኑኤል መልክአ ኤዶም መልክአ መድኃኔዓለም መልክአ ፍልሰታ ለማርያም መልክአ መድኃኔዓለም እሰግድ መልክአ ቁስቋም መልክአ ቁርባን መልክአ ሥዕል ሐጅ ጠጠ መጭ መልክአ መስቀል መልክአ ኪዳነ ምሕረት ልሳነ ሰብእ መልክአ ልደታ ለማርያም መልክአ ቅንዋት መልክአ ልደታ ለማርያም ዳግሚት መልክአ ማኅየዊ መልክአ ማርያም ካልእ መልክአ ማርያም ሣልሲት መልክአ ድንግል መልክአ ጎልጎታ መልክአ በኣታ ውቻ ቅዳሴ መሥዋዕት ጸሎትና የቤተ ክርስቲያን ምሥጢራት የሚከናወነበት ሥርዓተ ጸሉት ነው ሥጋ ወደሙን ካህናት ለምእመናን ከማቀበላቸው በፊትና በኋላ መልክአ ቁርባንን ይዘምሩታል መልክአ ቁርባን የክርስቶስን ሥጋና ደም የሚያከብር መልክእ ነው ከቅዳሴ በኋላ በየዕለቱ ከሚደገሙ ጸሎታት ውስጥ ከውዳሴ ማርያም ጋር የሚጸለዩት መልክአ ማርያምና መልክአ ኢየሱስ ይገኙበታል እነዚህ መልክአ መልክእ በካህናቱ ይደገማሉ ይህ ጸሎት የሚካሄደው መልክኡ እስኪፈጸም ድረስ በቅደም ተከተል ለካህናቱና ለሊቃውንቱ አንዳንድ አርኬ በማደል ነው ማደሉ የሚካሄደው በዲያቆናት ወይም በሌሎች የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ሲሆን የሚጠቅሱት እያንዳንዱ አርኬ የሚያመሰግኑትን የመጀመሪያውን የሰውነት አካል ወይም ሌላ ቃል ነው ከዚህ በተጨማሪም ዕለቱ መታሰቢያው የሆነ ጻድቅ ሰማዕት መልአክ ወይም ሌላ በዕለቱ ከተጠቀሱት መልክአ መልክእ በተጨማሪ የእርሱ መልክእም ይደገማል ቤተ ክርስቲያኑ የሚታሰብበትን ስም የያዘው መልክእ ወይም ጻድቅ ስምም በዚያ ቤተ ክርስቲያን መልክኡ በየዕለቱ ይደገማል ለምሳሌ በላሊበላ መልክእ ላሊበላ እና በሳማ ሰንበት ደግሞ መልክአ ሰንበት በየቀኑ ይደገማሉ መልክአ መልክእ በዜማ ሊዘመሩ ይችላሉ የሚዘመሩትም ከመልክኡ ውስጥ ተመርጠው የወጡ ጥቁት ስንኞች ናቸው የሚከበረው ዕለት የሚታሰብበት መልክእ ወይም ጻድቅ በዓመታዊ ክብሩ ዕለት ከመልክእ ውስጥ ጥቂት ስንኞች ተመርጠው በጸናጽል በከበሮ ይዘመራሉ ለምሳሌ ለልደት በዓል ከመልክአ ኢየሱስ ሁለት አርኬዎች ይዘመራሉ አርኬ እና አርኬ መልክእ እንደ ጸሎት መጽሐፍ ከማገልገሉ በተጨማሪ የማስተማር ተግባርንም ያከናውናል የባለመልክኡን ሕይወትና ተአምራት ከጸሎተኛው ጋር ያስተዋውቃልፁ ይህን የሚያደርገውም መልክአ የተመሠረተው በባለመልክኡ ታሪክ ላይ በመሆኑ ነው ስለዚህም መልክአ መልክእን ለመረዳት የባለ መልክኡን ታሪክና ትምህርተ ሃይማኖት ማወቅ አስፈላጊ ነው ሰላም ለዝክረ ስምከ ስመ መሐላ ዘኢይሔሱ ዘአንበረ ቅድመ እግዚአብሔር በአትሮንሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ለዳዊት ባሕርየ ከርሥ አክሊለ ስምከ እንዘ ይትቀጸል በርእሱ አህጉረ ጸር ወረሰ ኢያሱ መልክአ ኢየሱስ አርኬ ይህን አርኬ ለመረዳት የመስፍነ እስራኤል ኢያሱን ታሪክ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ትውልድና ምሥጢረ ሥጋዌ ማወቅ ያሻል የኢየሱስና የኢያሱና የስም አንድነት ማወቅም አስፈላጊ ነው ኢያሱ የተስፋይቱን ምድር የመውረሱ ታሪክና የጌታችንን ከዳዊት ዘር መወለድንም ማወቅ አስፈላጊ ነው እያንዳንዱ እንደየወቅቱ መጠን የዚህን አርኬ ትርጓሜ እያሰፋና ጥልቀት እየሰጠ መቀጠል ይችላል አስነኛኘት ነ አስነኛኘት የተባለው የግጥሙን ውጫዊ ገጽታ የሚያሳዩትን ቤት ምትና አርኬን ነው ቤት በመልክአ መልክእ የስንኞቹ የመጨረሻ ቤት መምቻ ሁልጊዜ አንድ ዓይነት ሆሄ ነው መልክአ መልክእ ሁልጊዜም በአንድ ዓይነት ሆሄ ቤት የሚመቱ ባለ አምስት ስንኝ አርኬዎች ያሏቸው ናቸው ሰላም ለአዕይንቲከ ከመ ምሉዕ ምዕቃለ ማይ እለ ይትረአይ ወትረ በመንበረ መጽሔት ርሱይ ያጌጠ ኢየሱስ ክርስቶስ መስተሥርየ ኩሉ ጌጋይ ንዝኃኒ እግዚኦ በአዛብከ ሠናይ ወአጻዕድወኒ እም በረድ ጽሩይ መልክአ ኢየሱስ አርኬ ከዚህ በላይ በተጠቀሰው አርኬ ውስጥ ያሉት ስንኞች ቤት የሚመቱት «ይ» በተባለው ሆኖ ነው የዚህ ቤት መምታት ፋይዳ ስንኞቹ በሚዜሙበት ጊዜ የዜማው አካሄድ እንዲጠበቅ ያደርጋሉ ምት ቀለም ዓለማየሁ ሞገስ የግእዝ ሥነ ግጥምን አስነኛኘት ሲያብራሩ የግእዝን ሥነ ግጥም ዜማ የሚወስኑት የሚቆጠሩ ድምፆች ሆሄያት እና የአነባብ ሥርዓት ተነሽ ወዳቂ ሰያፍ ናቸው እንደ አቶ ዓለማየሁ ሞገስ ጥናት በአንድ አርኬ ውስጥ የሚገኙ ስንኞች የተለያዩ መጠን የቀለም ያላቸው ሊሆኑ ይችላሉ በዚህም በአንድ አርኬ ወስጥ ያሉ ስንኞች የቀለም መጠናቸው የተለያየ ነው የሚከተሉት አራት አርኬዎች ቀለም እንደሚያሳየው መልክአ መልክአ አንድ ዓይነት የቀለም መጠን የላቸውም። ርስታቸው እግዚአብሔር ነው ርስታቸው ሕዝቡ ነው በእርሻ ወይም በሌላ ሥራ እንዲተዳደሩ ሳይሆን ከሕዝብ በሚያገኙት አሥራት እንዲተዳደሩ ርስታቸው ጉልታቸው አሥራት እንዲሆን ሥራቸው በቤተ እግዚአብሔር አገልግሉት እንዲሆን ተብሎ ተወስኗል ዘጉልኮ ስለዚህ ለቤተ እግዚአብሔር የሚሰጠው ነገር ሁሉ ለካህናትም ነው የሚሰጠው የካህናት ማደሪያ ነው ለቤተ እግዝአብሔር የሚሰጠው ለካህንም ስለሆነ ለካህን ለብቻው የሚሰጥ የለም ለቤተ እግዚአብሔር መስጠትን ለካህን ከመስጠት ነጥሎ ማየት አይቻልም እንዲህም ሆኖ ግን ካህናቱም ቢሆኑ የአሥራት አሥራት ይከፍላሉ እንዲያውም ፈሪሳውያን ከቅመማ ቅመም ሳይቀር ይከፍሉ ነበር ማቴኮ እነሱ ለቤተ እግዚአብሔር የሚሰጠውን አሥራት ይቀበላሉ ለቤተ እግዚአብሔር መሥዋዕት የሚሆነውን የሚያስፈልገውን ሁሉ ካወጡ በኋላ የተረፈው የካህናቱ የዕለት ተዕለት መተዳደሪያቸው ይሆናል ስለዚህ ለቤተ እግዚአብሔር የተሰጠ አሥራት ለካህንም ተሰጠ ማለት ነው አሥራት የተሠራው በብሉይ ኪዳን ነው ለድሀ ተብሎ አይደለም ለቤተ እግዚአብሔር ተብሉ ነው የቤተ እግዚአብሔር አገልግሎት የተሟላ እንዲሆን ቤተ እግዚአብሔርን የሚያገለግሉ ካህናት ተቸግረው አገልግሎቱ እንዳይጓደል ካህናቱ በሌላ የመተዳደሪያ ሥራ ተሠማርተው አገልግሉቱን እንዳያስተጓጉሉ ወይም እንዳያጓድሉ ለእነሱ ማደሪያ የሚሰጥ እንጂ ለድሀ ተብሎ አይደለም አሥራት የተፈቀደው መጀመሪያ ሥርዓቱ የወጣው ለቤተ እግዚአብሔር ነው ለድሀ የሚሰጠው ለቤተ እግዚአብሔር ከሚሰጠ ው አሥራት የተለየ ነው ነገር ግን ከዚህ ውጪ ለድሆች የተለየ ነገር አለ ለምሳሌ በኦሪቱ ድሆች ምርት በሚሰበሰብበት ጊዜ ቃርሚያ እንዲለቅሙ በአጨዳ ጊዜ የወደቀ ነዶ እንዳይነሣ ይደረጋል በማሳም ሆነ በውድማ ላይ የረገፈ እህል የወደቀ ነዶ የሚተወው ለድሆች ነበር በብሉይ ኪዳን ጊዜ ዋርሣ መውረስ የሟች ወንድም ሚሜስት መውረስ ሕግ ስለ ነበረ ችግረኛ ቤተሰብ ላይኖር ይችላል ለምሳሌ አሁን በሐዲስ ኪዳን ቤተ ክርስቲያን ዘወትር ድሀ አደጐችንና ባሎቻቸው የሞቱባቸውን መበለቶች አደራ በማለት አጠንክራ ታሳስባለች በኦሪቱ ግን በሐዲስ ኪዳን ያለው ዓይነት ችግር የለም ዋርሣ መውረስ ስላለ ባሎቻቸው የሞቱባቸው ሴቶች የባሎቻቸው ወንድም ስለሚያገቧቸው እና ልጆቻቸውን ስለሚያሳድጉላቸውና በሐዲስ ኪዳን የሚታየው ዓይነት ችግር በዚያን ጊዜ አልነበረም በሐዲስ ኪዳን ግን ዋርሣ መውረስ ስለሌለ ባሎቻቸው የሞቱባቸው ሴቶችና ድሀ አደግ ልጆችን አደራ የሚባለው ለዚህ ነው ስለዚህ ለቤተ እግዚአብሔር የሚሰጠው አሥራት ለድሆች የሚሰጠው ደግሞ ምጽዋት ይባላል ከአጥቢያው ቤተ ክርስቲያን ውጪ ለሌሎች የተቸገሩ የገጠር አብያተ ክርስቲያናት መስጠት አሥራት እንደማውጣት አይቆጠርም። ለሌላ ቤተ ክርስቲያን የሚሰጠው ነገር መባዕ ነው የሚባለው አንድ ምእመን ለፈለገው ቤተ ክርስቲያን መባዕ መስጠት ይችላል ምእመናን ከሚያወጡት አሥራት የተወሰነው የንስሐ አባት ድርሻ ነው በማለት ለንስሐ አባታቸው የሚሰጡ አለ የሚል ሐሳብ ተነሥቷል እንግዲህ ደመወዝ በሌለበት ቤተ ክርስቲያን እያንዳንዱ የነፍስ ልጅ የንስሐ ልጅ ለንስሐ አባቱ ይሰጣል በደመወዝ የሚተዳደሩ ካህናት ከሆኑ ግን ለአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን የሚሰጠው አሥራትና መባዕ ለንስሐ አባትም ማለት ለካህናቱ ሆነ ማለት ነው እንደውም በተጨማሪ በምእመናን ላይ እንዲከብዱ አያስፈልግም ለካህናቱ ደመወዝ ከአጥቢያ ቤተ ክርስቲያኑ እየተከፈለ እንደገና ደግሞ ሌላ ተጨማሪ ደመወዝ ከምእመናን መቀበል አያስፈልግም ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በጣም የተጠነቀቀውና እንደ ትልቅ ነገር የሚያየው ለምእመናን አለመክበድን ነው ሐዋርያ የምእመናን አባት ሆኖ ለምእመናን መክበድ እንደማይገባ አስተምሯል በተግባር አሳይቷል ካህናት በምእመናን ላይ ከከበዱ ትልቅ ችግር ያስከትላል ምእመኑ ሲከብደው ሸክሙ የሚቃለልበት ሌላ አማራጭ ይፈልጋል ከቤተ ክርስቲያን መራቅና መሸሽም ይፈልጋል ካህናት በምእመናን ላይ ሳይከብዱ በጣም ተጠንቅቆ በአግባቡ መያዝ ያስፈልጋል በእርግጥ ደመወዝ ሳያገኙ ሳያርሱ ሳይነግዱ ቤተ ክርስቲያንን የሚያገለግሉ ካህናት ከሆኑ ራሳቸውንም ሆነ ቤተሰባቸውን ማስተዳደር ስላለባቸው ምእመናን ሊረዷቸው ይገባል አለበለዚያ ካህናቱ ከምእመናን ካላገኙ በስተቀር ቤተሰባቸውን ለማስተዳደር በሌላ ሥራ ሳይ ከተሠማሩ የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ይጓደላል ስለዚህ ሌላው ምአመን አርሶ ነግዶ ሠርቶ ከሚያገኘው ቤተ እግዚአብሔርን ለሚያገለግሉት ካህናት የሚገባውን መክፈል አለበት ይኸም በሰበካ ጉባኤ አማካኝነት ለቤተ ክርስቲያን መገልገያና ለካህናት ደመወዝ ይሰጣል ደመወዝ የሌለው ካህን ከተገኘ ለሚያገለግለው ካህን እያንዳንዱ ምእመን አቅም ያለው በገንዘቡ በመደጉም በሌላም ነገር የሜረዳ አለ ለምሳሌ በገጠሪቱ ኢትዮጵያ ካህናቱ ደመወዝ ስለሌላቸው ምእመኑ የንስሐ ልጁ እርሻውን አረሙን አጨዳውን ሌላውንም ሥራ በመሥራት የንስሐ አባቱን ይረዳል አንዳንድ ጊዜ ለምሳሌ በጐጃም በዓመት አንድ ጊዜ በደብረ ዘይት ዕለት ስብሰባ ይደረጋል በንስሐ አባት ቤት ጠበል ጸዲቅ ይዘጋጅና በዚያ የሚሰበሰበው የንስሐ ልጅ የተቻለውን ስጦታ ያደርጋል በጎንደር በበጌምድር ስንሄድ የንስሐ ልጁ ካህኑን የንስሐ አባቱን በእርሻ በአረም በአጨዳ በጉልበቱ ይረዳዋል እንጂ ካህኑ ከንስሐ ልጁ ገንዘብ አይጠብቅም ምእመኑ ካህኑን በሚችለው አቅሙ ያገለግለዋል ምእመኑ ለካህኑ ምንም ባያደርግለትም እንኳን ቄሱ የነፍስ አባት ነውና የንስሐ አባት ወይም መምህረ ንስሐ አልሆንህም አይለውም ይህ ሊሆን አይችልም ምክንያቱም ካህን ሥዩመ እግዚአብሔር ነው ምንደኛ አይደለም ካህን ሹመቱ ከእግዚአብሔር የተሰጠው ስለሆነ በከንቱ ያገኘውን በከንቱ በጸጋ ያገኘውን በጸጋ የመስጠት ግዴታ አለበት በሌላ በኩል እናትና አባት የሞቱባቸውን ችግረኛ ልጆች ማሳደግ የተቸገሩ ሰዎችን መርዳት አሥራት እንደ ማውጣት ሳይሆን የሚቆጠረው ብጽአት ነው የሚባለው ለቤተ እግዚአብሔር የሚሰጠው ራሱን የቻለ ነገር ነው ከዚያ በተረፈ አንድ ሰው ለድሆች በየወሩ ወይም እንደተገኘ በሆነው ጊዜ መስጠት አለበት በየቦታው እንደሚታወቀው ሕዝቡ ለድሆች ይሰጣል አሥራትን ደግሞ ለሰበካ ጉባኤ ለብቻ ይከፍላል ለተቸገሩ ሰዎች ይረዳል ይመጸውታል አሥራቴን ለቤተ ክርስቲያን ሰበካ ጉባኤ ከፍያለሁ ብሎ የሚለምነውን ድሀ ዝም ብሎት አያልፍም የሚችለውን ያህል ይሰጣል ለድሆች የሚሰጠው የተለየ ነው አንድ ሰው በየወሩ ከደመወዙ ወይም ከገቢው ላይ ለድሆች ይኸን ያህል እሰጣለሁ ብሎ ለይቶ መስጠት ወይም መክፈል ይችላል ከአሥራቱ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም ለብቻ ማስቀመጥ ይችላል ሕዝቡ ይህንን አሁንም እያደረገው ይገኛሉ ድሀን ያበላል ያጠጣል ያለብሳል ለተቸገረ ይሰጣል ስለዚህ ከሰበካ ጉባኤ ውጪ ወይም ለቤተ እግዚአብሔር ከሚከፍለው ሌላ ለድሆች የተወሰነ ከገቢው ላይ ተምኖ በወር ይኸን ያህል እሰጣለሁ ማለት ይችላል ሳይተምንም እንዲሁ በትሩፋት መስጠ ት ይችላል ነጋዴና ገበሬ አሥራት የሚያወጡት እንዴት ነው። የሚሉና ሌሎችም ጥያቄዎች ይነሣሉ ብዙ ጊዜ አሥራት በኩራት ቀዳምያት ተብሎ ሲወጣ የኦሪት ሕግ ነው በአጭሩ ከላይ እንደተገለጠው የወንጌል ሕግ ከዚህ በላይ ማድረግ ነው የወንጌል ሕግ ደግሞ የተወሰነ ነገር አይሆንም እንደውም በወንጌል አንድ ሰው ያለውን ሁሉንም ንብረት ሽጦ ገንዘቡን ለድሀ ሰጥቶ መመነንም አለ የወንጌል ሕግ የተለየ ነው በዚያን ጊዜ ለነጋዴ ግልጽ ሆኖ የተቀመጠ ነገር የለም የሆነው ሆኖ ግን ወደ ወንጌል ስንመጣ ነጋዴዎች ትርፋቸውን ቆጥረው ሂሳቡን አስልተው ተምነው አሥራት መስጠት ብቻ ሳይሆን ለቤተ እግዚአብሔር የሚገባውን ከሰጡ በኋላ በመባዕ ከዚያ በላይ መስጠት አለባቸው ገንዘባቸውን ቆጥረውና አስልተው ይኸን ያህል ገንዘብ ዕዳ አለብኝ ብሎ መክፈል አይደለም በወንጌል ይህን ያህል ገንዘብ የእግዚአብሔር ዕዳ አለብኝ ይህን ዕዳ ልክፈል አይባልም ትሩፋት ነው መሠራት ያለበት ቤተ ክርስቲያንን ያሠራል ይሠራል ድሆችን ይረዳል የፈለገውን መልካም ነገር ያደርጋል ለካህናትም የተቻለውን ሁሉ ያደርጋል ባለው ገንዘብ ትሩፋት መሥራት አለበት እንጂ የተወሰነ ገንዘብ ቆጥሮ ይኸን ያህል የቤተ እግዚአብሔር ዕዳ አለብኝ ልክፈል አይባልም ቆሮኮ ቆሮኮ ስለዚህ በነጋዴው በኩል እግዚአብሔር ከሰጠው ገንዘብ ሳይ በፈቃዱ መክፈል አለበት እንጂ ይህን ያህል ገንዘብ አለብኝ ልክፈል ማለት አይደለም እግዚአብሔር የሚሰጠን ጸጋ ያልተወሰነ ነው እኛ ደግሞ እግዚአብሔር ከሜሰጠን ያልተወሰነ ጸጋ ወስነን አይደለም መስጠት ያለብን ከተሰጠን ሀብት ላይ ለእግዚአብሔር ባልተወሰነ ሒሳብ ወይም ተመን ትሩፋት መሥራት አለብን ዕዳዬ ይኸን ያህል ነው በማለት ተምኖ መክፈል የለበትም ወንጌል የትሩፋት ሕግ ነው ወደ ገበሬው ስንሄድ በኦሪቱ ሕግ አሥራት በኩራት ቀዳምያት ማውጣት አለበት በተመረተው እህል የመጀመሪያው ሥፍር ቀዳምያት ይባላል ያ የእግዚአብሔር ነው ከዚያ በኋላ የሚሠፈረው አሥር በሞላ ቁጥር አንድ ሥፍር ለቤተ እግዚአብሔር ይሰጣል አሥራት ነው በኩራት የሚባለው ደግሞ ከእንስሳት ሲወለድ የመጀመሪያው ለቤተ እግዚአብሔር ይሰጣል በእንስሳቱ በኩል በመጽሐፍ ቅዱስ ንጹሕ የሆነ ርከኤ እና ንጹሕ ያልሆነ ህክርርበር አለ ንጹሕ ያልሆኑ ከሚባሉት እንስሳት የጋማ ከብቶች የሚወለደው የመጀመሪያው እንዳለ ተወስዶ ለቤተ እግዚአብሔር አይሰጥም። በገንዘብ ይዋጀውና ገበሬው ገንዘቡን ወስዶ ለቤተ እግዚአብሔር ይሰጣል ንጹሕ ሀክርርከ ወይም ቅዱስ የሚባሉት የተፈቀዱና የሚበሉት እንስሳት የመጀመሪያው ሲወለድ ለቤተ እግዚአብሔር ይሰጣል ቀዳምያት አሥራት በኩራት የሚባሉት ሦስቱን የሚመለከተው በኦሪት ሲሆን ገበሬውን ነበር በዚያን ጊዜ ሕዝቡም ኑሮው ግብርና ስለነበረ ነው ያን ጊዜ ሕዝቡ ማለት ገበሬው ነው ስለዚህ የገበሬው ሕግ ነው ወደ ሐዲስ ኪዳን ስንመጣ ግን አሥራቱ እንዳለ ተወስኗልር ቀዳምያትና በኩራት የሚባሉት የሉም በዘመነ ሐዋርያት ሁሉም ያለውን ሀብቱን እየሸጠ ወደ ቤተ እግዚአብሔር ገቢ እያደረገ በአንድነት መኖር የሚል ነገር ተጀምሮ ነበር በመጀመርያይቱ ቤተ ክርስቲያን ሀብቱን ሁሉ ሸጦ ለቤተ እግዝአብሔር አስገብቶ አብሮ መኖር ነበር ያ ሁኔታ አልዘለቀም በዚያው ተበትኗልጹ ምክንያቱም ሕዝቡ እየበዛ ማኅበሩ እየሰፋ ሲሄድ ወደ ዐዐዐ ሲደርስ ችግር ተፈጠረ ማኅበሩም ተበተነ እናም ዋናው ትልቁ ነገር ለቤተ እግዚአብሔር ክፍያ የሚገባውን አሥራት መባዕ መክፈል ይገባል በሌላው አገር ስንሄድ የቤተ እግዚአብሔር ክፍያ የሚሰጠው በአብዛኛው በሙዳየ ምጽዋት ነው ሁልጊዜ በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት በሚሰጥበት ጊዜ የሙዳየ ምጽዋት ስጦታ አለ በየዕለቱ አገልግሉት የሚሰጥ የስእለት ስጦታም አለ በተለይ ከአሥር አንድ የሚለውን ስንመለከተው በሌላው አገር የለም እኛ አገር ግን አለ ምክንያቱም ኢትዮጵያ ብቻ የብሉይ ኪዳንን ባሕሉን ትውፊቱን ይዛ ቆይታለች ሌላው ከአረማዊነት ወደ ክርስትና ሕይወት ነው የመጣው ባሕሉም የሌለውም ለቤተ እግዚአብሔር ትሩፋት የሚሰጡ ብቻቸውን ቤተ ክርስቲያን የሚያሠሩ ብቻቸውን የቤተ ክርስቲያንን ዓመታዊ በጀት የሚሸፍኑ ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ በተለያየ መንገድ ገንዘባቸውን በመባዕ በትሩፋት ይሰጣሉ እንጂ በርስት መልክ ይኸን ያህል መክፈል አለብኝ የሚለው ሁኔታ የለም ከላይ እንደተጠቀሰው እነሱ ከአረማውነት ወደ ክርስትና ስለ መጡ የኦሪቱ ባሕል የላቸውም። በተለይ በቀጥታ አሥራት የሚለው ነገር በመጽሐፍ ቢኖርም በተግባር በተለይም በገጠሪቱ ኢትዮጵያ እንዲሁም በከተማው አልታየም ሕዝቡ ለቤተ ክርስቲያን በጣም ብዙ ነገር ያደርጋል በአሥራት መልክ ለሰበካ ጉባኤ እንዲከፍል ሲጠየቅ ግን እንደ ትልቅ ዕዳ አድርጐ ይመለከተዋል በግድ ነው የሚከፍለው ምክንያቱም ልምዱ ከሥር ጀምሮ እየዳበረ ስላልመጣ ነው ይሁን እንጂ ሕዝቡ ለቤተ ክርስቲያን ከአሥራ ሁለት ብር እና ከሃያ አራት ብር በላይ የበለጠ ብዙ ያደርጋል ይህችኛዋ አዲስ ሕግ ሆኖ ስለ መጣችባቸው እንደ ትልቅ ዕዳ ይቆጥሯታል ለቤተ ክርስቲያን ሲረዱ ንዋያተ ቅድሳቱን ሲያሟሉ አዲስ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ሲሠሩ የፈረሰውን ሲጠግኑ ድሀ ሲረዱ ሲዘክሩ ሲጋብዙ ሲያለብሱ እጅግ ብዙ ነገር ሲያደርጉ አሥራት ከሚከፍሉት በላይ ያወጣሉ ነገር ግን በዓመት የተወሰነውን አሥራት መክፈል ይከብዳቸዋል አሁን ከጊዜ በኋላ የከተማው ሰው እየለመደው የመጣ ይመስላል በአብዛኛው የገጠሩ ሕዝብ ግን በባሕለ ማርያም ባርኪ ተብሎ በየውድማው የመሪጌታ ይከፍላል የገበዝ ይከፍላል የዓመት መቀደሻ ይከፍላል በተለይ በጉራጌ ማኅበረሰብ በአካባቢው ደብር የሚቀደሰው የዓመቱ በዓል ምን ያህል ጊዜ እንደሆነ ተለይቶ የሰበካው ሕዝብ አዋጥቶ የዓመት አስተዋጽኦ ይሰጣል ከዚያ በተረፈ ደግሞ ራሱ እያወጣ መዝበዐሪያ ይሰጣል ይኸን እያደረገ አሥራት ለብቻ ክፈል ይባላል ያንን ሁሉ እያደረገ አሥራት ክፈል መባል የለበትም ለማርያም ባርኪኝ ለመሪጌታ ለገበዝ ለመቀደሻ ወዘተ በእህል መልክ የሚሰጠውን በሰበካ ጉባኤ ሒሳብ በአሥራት መልክ መያዝ ይቻላል ከዚያ በኋላ በተለያየ ምክንያት መጠየቅ የለበትም የተሰበሰበውን ለሜፈለገው ነገር በአግባቡ በሥርዓት እያወጡ መመደብ በሚገባ መጠቀም ይቻላል ሕዝቡ የተሰበሰበው እህል በሰበካ ጉባኤ ገቢ ተይዞ በሚገባ ለቤተ ክርስቲያን ጥቅም ላይ ሲውል ማየት አለበት በገጠር ገበሬው በየዓመቱ ምርቱን በውድማ በሚሰበስብበት ጊዜ የሚሠፈረው በቃለ ዓዋዲው እንደ አሥራት የሰበካ ጉባኤ ክፍያ ሆኖ ሊመዘገብለት ይገባል ደንቡ የሚለው ይኸንን ነው በገጠሪቱ ኢትዮጵያ ይህንን በአግባቡ ተግባራዊ የሚያደርገው ስለሌለ ግጭት ሲፈጥር ይታያል ይህንን ለማስተካከል ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ በየሀገረ ስብከቱና በየወረዳው በሴሚናር መልክ በማስረዳት ግንዛቤ እንዲፈጠር እንደተደረገው ሁሉ ወደፊትም በተጠናከረ ሁኔታ መቀጠል ይኖርበታል ስብከተ ወንጌልም ተጠናክሮ ከተስፋፋ ምእመናን አሥራታቸውን ለምንና እንዴት ማውጣት እንዳለባቸው እየተረዱት ከእነሱ የሚጠበቅባቸውን በጊዜው ለማድረግ ይነሣል ማጠቃለያ በየትኛውም ዓለም የሚኖረው የኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ምእመን ሁሉ ከአጥቢያ ጀምሮ እስከ ማዕከል ያለችውን ቤተ ክርስቲያን አንድ አድርጐ ማየት ይገባዋል የገጠሪቱ ቤተ ክርስቲያን አለመኖር ማለት ማዕከላዊው የቤተ ክርስቲያን አካል አለመኖር ማለት ነው ዳሩ ሲፈታ መሐሉ ዳር ይሆናል ይባላል በእኛ በቤተ ክህነትም በምእመናንም ዘንድ ይህንን ተረድተንና አምነንበት የገጠሯ ወይም በጠረፍ ያለችው ቤተ ክርስቲያን ስትዘጋ በዝምታ ማየት የለብንም ያቺ ከዳር ያለችው የገጠር ቤተ ክርስቲያን ስትዘጋ መሐሉም ዳር እንደሚሆን አውቀን በጠቅላላው ምንም ገቢ የሌላቸውን አብያተ ክርስቲያናት በችግር ምክንያት እንዳይዘኑ ማድረግ አለብን ለዚህ የተሻለው መፍትሔ የቤተ ክርስቲያንን ገቢ በማዕከላዊ ሁኔታ አደራጅቶ በሥርዓት በአግባቡ መምራትና ማስተዳደር ነው ሌሎች አገሮች የሚያደርጉት እንደዚህ ነው በአንዱ ገቢ ነው ሌላው አነስተኛ ገቢ ያለው አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን የሚተዳደረው በአንዱ አጥቢያ ያለ ምእመናን ቁጥራቸው አነስተኛ ሆኖ በሌላው አጥቢያ ብዙ ሺሕ ምእመናን ሊኖሩ ይችላሉ ለምሳሌ በጠረፍ አካባቢ ሃያና ሠላሳ ምእመናን ይኖራሉ እነዚያ በአነስተኛ አቅማቸው ካህን ቀጥረው መገልገልና ማስገልገል ስለሚያቅታቸው ቤተ ክርስቲያኑም ይዘጋል እነርሱም ወደ አረማዊነት ይመለሳሉ በአንዱ አጥቢያ እጅግ የተትረፈረፈ ሀብት በአንድ በኩል ደግሞ ባዶ ሆኖ ይታያል ይህን አስተካክለን በገጠሯ ቤተ ክርስቲያን ጭምር አገልግሉቱ ሳይጓደል የሚሰጥበት ሁኔታ ቢኖር መልካም ነው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ይህንን ለማድረግ አቅሙም ችሉታውም አላት ያጣነው ዘዴ ብቻ ነው መቀናጀት ያስፈልጋል ምእመናን ካህናትና በየደረጃው ያሉ የቤተ ክርስቲያን አካላት በቅንጅት በመወያየትና በጋራ በመሥራት የቤተ ክርስቲያናችንን የተጠናከረ አሠራር እግዚአብሔር እንዲያሳየን እንመኛለን።

  • N.B. This Summary is Very Experimental!! based on the following scripts from:
    • https://github.com/millzon/textSummarizer-am
    • https://github.com/icoxfog417/awesome-text-summarization#motivation
Download Searchable PDF Download PDF

Comments:


memezon

Download options | Convert to Pdf | Book of the day

© dirzon | Terms of Service | Privacy | About | Services | Contact