Detecting...

Please whitelist dirzon to continue.

or subscribe for ad-free contenct.

dirzon
  • Convert to Pdf
  • Reading List
  • Summary
  • Audiobook
  • Search
  • Upload
  • myzon
  • Log in
  • Register
English  አማርኛ  Français  العربية
Book of the day

• ህልም አለኝ በማርቲን ሉተር ኪንግ.pdf


  • word cloud

• ህልም አለኝ በማርቲን ሉተር ኪንግ.pdf
  • Extraction Summary

ወያ ዳታ ፖፆሪኘፇው ም«ጀሂን ታሃረ ሷቃፇ መዳኀፍ ጭሩ ዖረበዐያሦ ሮያው ጽሥፉ ያምምሦመሪ ሐውፇታ ሪፇያ ሐም» ዕረ ቦያአታሰ ኖሃሦጨማሪም የ ደደሁሃዖ ያረትሂረኝኛ መራረር ምሳረ ዜዖፇ ለመሠሥሯራሪሦ ይዘሳዳኋ የጥቁሮች መገለልና ተከትሎት የመጣው የዘር ልዩነት ከፖለቲካ ከኢኮኖሚና ማህበራዊ ኑሮ የተሸመደመዱ ጥቁር ወጣቶችን ከቤታቸው ስምንት ሺህ ማይል አርቀን በደቡብ ምዕራብ ጆርጂያ አና ምሥራቅ ሀርለሞ ያላገኙትን ነጻነት በደቡብ ምሥራቅ ኤስያ እንዲያረጋግጡ ስንልካቸው ነበር በዚሁ መሠረት የኔግሮ ልጆችና የነጮች ልጆች ጎን ለጎን ቁጭ ብለው መማር አይችሉም የድሆችን ቤቶችና መንደሮች በጭካኔ የማቃጠል ተግባር ላይ ሲደጋገፉ ተመልክተናል ነገር ግን አንዲታወቅልን የምንፈልገው ሰው ለመሆን ቆርጠን መነሳታችንን ብቻ ነው። ህዝብ ለመሆን ቆርጠናል እኛም የእግዚአብሔር ልጆችን የሚመለከት ነው ይህን ለመፈጸም ዝግጁ ካልሆናችሁ እኛም ልንከተለው የሚገባን አቅጣጫ ስላለ አስቀድማቸሁ ንገሩን የኛ አጀንዳ ለናንተ የምናደርገውን ኢኮኖሚያዊ ድጋፍ ማቋረጥ ነው። ዎንደር ዳቦ አዎ መጠጥም እንዳይገዙ ንገሩአቸው ሌላኛው የዳቦ ኩባንያ ማን ነበር። ጀሲ ነው። የሚል መሆን ይኖርበታል ከዛሬ ምሽት ጀምሮ በላቀ ዝግጁነት እንንቀሳቀስ በቁርጠኝነት እንነሳ በነዚህ ወሳኝና ታሪካዊ ቀናት ውስጥ አሜሪካን ከሚገባት ደረጃ ላይ ለማድረስ እንንቀሳቀስ አሜሪካን የተሻለች አገር ለማድረግ ዕድሉ በአጃቾችን ውስጥ ይገኛል ከናንተ ጋር በዚህ ሥፍራ እንድገናኝ ስለረዳኝ በድጋሚ አግዚአብሔርን አመሰግናለሁ ከብዙ ዓመታት በፊት ኒውዮርከ ውስጥ ከዕለታት በአንደኛው ቀን ለመጀመሪያ ጊዜ በጻፍኩት መጽሐፍ ላይ ስሜን እየፈረምኩ ነበር ተቀምጩ መጽሐፉ ላይ አፈርም በነበረበት ቦታ አንዲት የአፅምሮ ችግር ያለባት ጥቁር ሴት መጣች ከሷ የሰማሁት አንድ ጥያቄ አንተ ማርቲን ሊተር ኪንግ ነህ የሚል ነበር አቅርቅሬ እየፈረምኩ አዎን አልኳት ቀጥሎ የሆነ ነገር ደረቴን ሲመታው ተሰማኝ ሳላስበው በዚች በከፉ መንፈስ በተያዘች ሴት ተወጋሁ በአስቸኳይ ወደ ሀርለሞ ሆስፒታል ተወሰድኩ መጥፎ እሁድ ነበር የተነሳሁት ራጅ እንዳመለከተው የተወጋሁበት ስለት ጫፍ በደረቴ ዘልቆ ትልቁ የደም ቧንቧ ከተሸነቆረ በራስ ደም ውስጥ መዋኘት ነው ይህ ማለት የህይወት መጨረሻው ምዕራፍ ላይ መድረስ ማለት ነው በዚያ ሰዓት ድንገት አስነጥሶኝ ቢሆን ኖሮ ሞቼ አንደነበር በነጋታው በወጣው ኒውዮርክ ታይም ላይ ታትሞ ወጣ ደረቴን ዘልቆ የገባውን ስለት በቀዶ ህከምና ካወጡ ከአራት ቀናት በኋላ በሆስፒታሉ ተንቀሳቃሽ ወንበር ተቀምጩ አቤት ውስጥ እንድዘዋወር ተፈቀደልኝ ከመላው ዓለምና ዩናይትድ ስቴትስ ከተላኩልኝ ደብዳቤዎች ውስጥ የተወሰኑትን አይቻለሁ ከደብዳቤዎቹ ውስጥ ያነብብኩት ጥቂቶችን ብቻ ቢሆንም አንዱን ግን አልረሳውም ፕሬዝዳንቱና ምከትላቸውም ደብዳቤ ልከውልኛል አነዚያ ቴሌግራሞች ምን አንደሚሉ አሁን ረስቻለሁ ይሁን እንጂ አንድ ደብዳቤ ከአንዲት ትንሽ ልጅ ደርሶኝ ነበር ደብዳቤው የተላከው ዋይት ፕሌንስ ሁለተኛ ደረጃ ትቤት ከምትማር ትንሸ ልጅ ነበር ይህን ደብዳቤ መቼውም አልረሳውም ባጭሩ እንዲህ ይላል የተከበሩ ዶር ኪንግ።

  • Cosine Similarity

ዞ ወደ ጋንዲ አረ የኃይል አልባ ትግል ማህበራዊ መዋቅር የአቅጣጫ ለውጥ ወደ ኃይል አልባ ትግል ንቃተ ማንነት የነጻነት ጊዜ ደርሷል ከበርሚንጋም አሥር ቤት የተላከ ደብዳቤ ህልም አለኝ የኖቤል ሽልማት ሲቀበል ያደረገው ንግግር ርሑ ሓ ር ርክ ከፍል ህልሙ ተራዘመ ለተሰዉ ህጻናት መታሰቢያ አምላካችን በሥራ ላይ ነው ኃይል አልባ ስልት ወደ ነጻነት ብቸኛው መንገድ የዝምታ ጊዜ ይብቃ። በማለት ቬትናም ውስጥ ስለሚካሄደው ጦርነት አና ጦረኝነት የሚያስከትለውን አደጋ የተቃወመባቸው ጽሁፎች ይገኙበታል ዶር ኪንግ እኔነት በሚል ርዕስ ሥር ልቆ ስለ መገኘት በጥልቀት በማብራራት እሱ ከጻፈበት ጊዜ ይልቅ ዛሬ በአጅጉ አስፈላጊ የሆኑ ልማዶችን ወይም እሴቶችን በዝርዝር አቅርቧልከዚህ ወዴት ሄ እንሄዳለን የሚለው ጽሁፉ ደግሞ ለዓለም ያለውን ራዕይ ያመላከተበት ነው እነዚህና ሌሎች ባጠቃላይ በዚህ መድበል የተካተቱት ሃያ ጽሁፎች የዶር ማርቲን ሉተር ኪንግን አስተሳሰቦች ከማንጸባረቅ አልፈው ላሳተማቸው መጽሐፎቹ እንደ መግቢያ ናሙና የሚያገለግሉ ናቸው ዶር ኪንግ የሚታወቀው አነቃቂና ስሜት ቀስቃሽ በሆኑ ንግግሮቹ ቢሆንም በዚህ መድበል ገጾች ላይ የተጻፉት ቃላት ያዘሏቸው መልዕከቶች በሥራ ተተርጉመዋል ዶር ኪንግ አንደበተ ርቱዕ ብቻ ሳይሆን ለዲሞከራሲ የተገባውን ቃል ፅውን ለማድረግ ህይወቱን አደጋ ላይ እስኪጥል ድረስ የታገለ ጀግና አሜሪካዊ ነው በዚህ መድበል ውስጥ ለተካተቱት ጽሁፎችና ሌሎች ሥራዎቹ ቀዳሚ ምንጮች አትላንታ ጆርጅያ በሚገኘው የማርቲን ሉተር ኪንግ ትንሹ ቤተ መጻህፍትና የሰላማዊ ትግል ማዕከል ውስጥ ይገኛሉ ይህ ልዩና ታሪካዊ ማዕከል በዓመት ከአምስት ሺህ በላይ ለሆኑ አንባቢዎችና ተመራማሪዎች አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን የባለቤቴን ንግግሮች ስብከቶች የግል ማስታወሻዎችና ሌሎች ጽሁፎችን ጨምሮ ከሁለት ሚሊዮን በላይ ከአሜሪካን ሲቪል መብቶች እንቅስቃሴዎች ጋር የተያያዙ ሰነዶችን ይዚል ጄምስ ዋሸንግተን በዚህ መድበል ውስጥ የተካተቱት ጽሁፎች እንደየሚገልጹት ድርጊት ቅደም ተከተል ተቀናብረው እንዲቀርቡ በማድረግ ረገድ ትልቅ ሥራ ሰርቷል ይህ መድበል የተረጋጋች ዓለምን ለመፍጠር ማርቲን ሊተር ኪንግ የተከተለውን ፍልስፍናና ሥራ ላይ ያዋላቸውን የሰላማዊ ትግል ዘዴዎች ለማጥናት ያበረታታል ብዬ አምናለሁ ህቨ ለአንባቢያን የማርቲን ሱተር ኪንግ ትንሹን ንግግሮችና ጽሁፎች ማንበብ ዶር ኪንግ ወገኖቹን ማህበራዊ ፍትህ ለማጎናጸፍ የነበረውን ፍላጎት ጥንካሬና ቆራጥነት እንድናደንቅ ይረዳናል ስሜቱን ለመግለጽ የተጠቀመባቸውን ቃላት ጥንካሬና በቀደሙት ዘመናት የተፈጸሙ ስህተቶችን ግዝፈትም ያስገነዝበናል እሱ ሲናገራት የነበረችው አሜሪካ ዛሬ ካለችው አሜሪካ በእጅጉ የተለየች ናት የያኔዋ አሜሪካ በዘር ላይ የተመሠረተ ጭቆና ኢፍትሀዊ በሆኑ ህጎች የተደገፈባት ነበረች አፍሪካዊ ዝርያ ያላቸው አሜሪካውያን ተለይተው እየተነጣጠረባቸው የበታችነታቸውን እንዲያስቀጥል ተደርጎ የተዋቀረውን ሥርዓት መራዘም ለመቀበል የተገደዱባት ነበረች ማርቲን ሉተር ኪንግ ይህን ሁኔታ በመቃወም በወቅቱ የነበረውን ተሰሚነትና የማሳመን ችሎታውን ተጠቅሞ ጥቁር አሜሪካውያን ማንነታቸውን ተረድተው የትግሉ ተሳታፊ እንዲሆኑ አድርጓል እርሱ ራሱ አርአያ በመሆን ጨቋኝ ሥርዓትን አሽቀንጥሮ መጣል እንደሚቻል ሊያሳምናቸው ሞከሯል ሰብዓዊ መብታቸውን ለማስከበር ከሱ ጋር መሰለፍ ብቻ በቂ እንደሆነም አሳምኗቸዋል ማርቲን ሉተር ኪንግ በዚህ ድርጊቱ የሃያኛው ከፍለ ዘመን ታዋቂ የሲቪል መብት ንቅናቄ መሪ ለመሆንም በቅቷል ይህንን ተከትሎ ጥቁር አሜሪካውያን ከምንጊዜውም በላይ ተነሳስተው በዘር ላይ የተመሠረተ አድሎን በመቃወም ለመብታቸው ታግለዋል ከዎቹ አጋማሽ ጀምሮ እስከ ዎቹ መጨረሻ ድረስ ባካሄዷቸው ትላልቅ ሰላማዊ ሰልፎች ጥቁር አሜሪካውያን ከነጮች አኩል ማህበራዊ አገልግሎት የማግኘት በምርጫ የመሳተፍና ሰብዓዊ ከብር የማግኘት መብቶችን ተጎናጽፈዋል ህ የመሪዎች ምርጫ በ የአፍሪካ አሜሪካውያን የሲቪል መብት ጉዳይ ህልም እንጂ ዕውን ሊሆን የሚችል ተደርጎ አይታሰብም ነበር በደቡቡ ክፍል ዘረኝነት ሀጋዊ ነበር ይህ ህግ ነበር አንድ የአላባማ ሞንትጎመሪ የአውቶቡስ ሾፌር ሮዛ ፓርከስ የተባለች አንዲት የአርባ ሁለት ዓመት ልብስ ሰፊ የነበረችን ጥቁር ሴት ለአንድ ነጭ መቀመጫዋን አልለቅም በማለቷ አሥር ቤት አንዲያስወረውራት ያስቻለው ይህ ዜና የባለ ቀለም ህዝቦች ብሔራዊ ማህበር ባቀህብማ ተብሎ ለሚጠራ የሲቪል መብት ተከራካሪ ድርጅት ሲደርስ የድርጅቱ ፕሬዝዳንት ወዲያውኑ የአካባቢውን ማህበረሰብ መሪዎች ሰበሰቡ ጥቁር አሜሪካውያን ከዚህ በላይ መታገስ እንደማይችሉ ለማሳየት አውቶቡስ ላለመሳፈር የሚያድሙበት ጊዜም ደረሰ ለታህሳስ ቀን ለአንድ ቀን ብቻ ታቅዶ የነበረው አውቶቡስ ያለመሳፈር አድማ ለረጅም ጊዜ በመራዘሙ ትግሉ ጠንካራ ድርጅትና መሪ አንደሚያስፈልገው ግልጽ አደረገ በዚሁ መሠረት የሲቪል መብት ድርጅት መሪዎች በመስፈርቶች ላይ ውይይት አካሄዱ በመሪነት የሚታጨው ሰው ወጣት አቅም ያለው የተማረ ቆራጥና አንደበተ ርቱዕ መሆን አንዳለበትም ተስማሙ ለዚህ ኃላፊነት ብቃት ያለው ሰው ሲፈለግ መንፈሳዊ ብርታትና ጥንካሬ ስትሰጣቸው የነበረችው የጥቁሮች ቤተከርስቲያን አገልጋይ ተመራጭ ሆኖ ተገኘ አዎን በባቀህብማ ፕሬዝዳንት አዕምሮ ውስጥ መስፈርቱን የሚያሟላ አንድ ሰው ነበር ወጣት በቂ ሥልጠና ያለው አዲስ ኃይል በዚሁ መሠረት ፕሬዝዳንቱ ማርቲን ሉተር ኪንግን በእጩነት ሲያቀርቡ ሁሉም ተቀበለው መጀመሪያ ላይ ኪንግ ጥሩ አማራጭ ስለመሆኑ አጠራጥሮ ነበር ምክንያቱም በነጻነት ትግሉ ውስጥ ታዋቂ ሰው አልነበረም የፓስተር ልጅና የልጅ ልጅ እንደመሆኑ መጠን ድሎት እንጂ ችግርን አያውቅም ዘረኝነት የሚያመጣው ጣጣ ፈንጣጣም ነከቶት አያውቅም አላባማ ጆርጅያ ውስጥ አድጎ በአሥራ አምስት ዓመቱ ጎበዝ ተማሪ በመሆን ጥቁሮች በሚማሩበት ሞርሀውስ ኮሌጅ ገባ በኋላ ደግሞ ነጮች በሚበዙበት ከሮዘር መንፈሳዊ ሴሚነሪ ተምሮ አንደኛ በመሆን ተመረቀ በ ከቦስተን ዩኒቨርስቲ የዶከትሬት ድግሪ ትምህርቱን ሳያጠናቅቅ ወደ ደቡብ ተመልሶ ሞንትጎመሪ ውስጥ ዴክከስተር ጎዳና ላይ በምትገኘው የመጥምቃውያን ቤተክርስቲያን ፓስተር ሆነ የቤተክርስቲያኒቱ ምዕመናን ጥቂት ቢሆኑም ተጽዕኖ ፈጣሪዎች አንቱ የተባሉ ባለሙያዎችና ኪንግ በቀላሉ ሊለማመዳቸውና ሊግባባቸው የሚችሉ ዓይነት ነበሩ ስለዚህ ስኬታማ ነበር በዚህ አዲስ ወጣት አገልጋይ ፊት ተጋርጦ የነበረው ብቸኛ መሰናከል ሞንትጎመሪ ውስጥ ተንሠራፍቶ የነበረው ዘረኝነት ነበር አውቶቡስ ላለመሳፈር ለተደረገው አድማ መነሻ የሆነው ሰበብ ከመፈጠሩ በፊትም ቢሆን ኪንግ የዘረኝነትን መኖር አጥብቆ ይጠላ ነበር የሮዛ ፓርከስን መታሰር እንደሰማ ደግሞ ጥቁር አሜሪካውያን ስለ ዘር መድሎ አንድ ነገር ማድረግ እንዳለባቸው ተረዳ ስለዚህ እንዲመራቸው ሲጠየቅ ያለማቅማማት ተፃዋበለ የዘረኝነት መዘዞችን መጋፈጥ ታህሳስ የተጀመረውን አውቶቡስ ያለመሳፈር አድማ የመምራቱ ኃላፊነት መሻሻል ለሞንትጎመሪ መሞ የተሰኘውን አዲስ ድርጅት እንዲመራ በተመረጠው የሃያ ስድስት ዓመቱ ፓስተር ትከሻ ላይ ወደቀ የዚህ አድማ ዓላማ ጥቁር አሜሪካውያን ከነጮች እኩል በአውቶቡስ ውስጥ በመጀመሪያዎቹ ረድፎች አንዳይቀመጡ የሚከለከለው ህግ እንዲለወጥ ለማድረግ ነበር የከተማዬዩቱ ነጭ ባለሥልጣናት ይህን ባለመቀበላቸው አድማው ለ ቀናት ቀጠሰ በዚህ አድማ ወቅት ዘጠና በመቶ ጥቁሮች አውቶቡስ ላለመሳፈር አሻፈረኝ ብለዋል ይህን አድማ ተከትሎ የአውቶቡስ ኩባንያ ገቢ በስልሳ አምስት በመቶ አሽቆልቁሏል በመጨረሻም የአሜሪካ ጠቅላይ ፍቤት ከዚህ ቀደም የሞንትጎመሪ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍቤት የሰጠውን ውሳኔ አጸደቀ ሶስት ዳኞች የተሰየሙበት የሞንትጎመሪው የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍቤት በአውቶቡሶች ውስጥ የዘር ልዩነትን የሚፈቅደው የአላባማ ግዛት ህግ የዩናይትድ ስቴትስን ህገ መንግሥት ስለሚጻረር ተፈጻሚነት የለውም በማለት ውሳኔ ሰጥቶ ነበር ይህ ውሳኔ ጥቁር አሜሪካውያን ለመብታቸው ባደረጉት ትግል ውስጥ የአዲስ ጅማሮ አሳት አቀጣጠለ የነጻነት ብርሃንም ፈነጠቀ ከዚሁ ጋር ተያይዞ የደቡብን ኢፍትሃዊ ህጎች በሰላማዊ መንገድ መቃወምን በማስተዋወቅ ማርቲን ሉተር ኪንግ በአሜሪካና በመላው ዓለም የዘር አኩልነት ተምሳሌት ሆኖ ታዋቂነትን አገኘ አንደ ደቡብ ከርስቲያን አመራር ምቤት ደከአም መሪም የዘረኝነት ደጋፊዎችን በግልጽ በመቃወም ዘመቻ ከፈተ ኪንግ ጥቁር አሜሪካውያን የሚገኙበት ሁኔታ ሲለወጥ የሚችለው በማያቋርጥ ሰላማዊ ትግል ብቻ ነው ብሎ አመነ ይህ የሰላማዊ ትግል ስልት ሞንትጎመሪ ውስጥ ተቀጣጥሎ በተማሪዎች የመቀመጥ አድማ ተሻሸሎ በታላላቅ ሰልፎች ዳብሮ በነጻነት ተጓዥች ዕውን እስከ መሆን ደረሰ በመጨረሻም በወጣውና ጥቁር አሜሪካውያንንና ነጮችን አኩል መብት ባጎናጸፈው የምርጫ ህግ ተደምድሟል ህያው ከብር በኪንግ አመራር ሥር አፍሪካዊ ዝርያ ያላቸው አሜሪካውያን ህገ መንግሥቱ የሰጣቸውን መብቶች ለማስከበር ከምንጊዜውም የበለጠ ተነሳሽነት አሳይተዋል በዚህ መድበል የተካተቱ ንግግሮቹና ጽሁፎቹም ይህንኑ ታሪከ ያመለከታሉ ፍትሀዊ የሆኑ ህጎች እንዲወጡ በወቅቱ የተጫወተውን ሚና እንድናስታውስም ያግዙናል ንግግሮቹ እንዳሉ መወሰድ አለባቸው ለማለት ባይቻልም እሱ የቀሰቀሰው ለራስ ህሊና ታማኝ የመሆን ስሜት ግን መቼም ሊዘነጋ አይችልም ጽሁፎቹና ንግግሮቹ ማርቲን ሉተር ኪንግ የቆመላቸውና የተሟገተላቸው አሴቶች ገላጭ ብቻ ሳይሆኑ የራሱ የግል ታሪከ መዛግብትም ጭምር ናቸው ኣ ከነዚህ አሴቶች ውስጥ አንዱ አገሪቱ በአሜሪካ ኑሮና ህግ ውስጥ ዘር ሥፍራ የለውም በማለት ለህዝቦቿ የገባችውን ቃል ዕውን ታድርገው የሚል ነው ኪንግ በመጨረሻዎቹ የህይወቱ ዘመናት አካባቢ ዘረኝነት ድህነትና ቬትናም ውስጥ የሚካሄደው ጦርነት ተያያዥነት አንዳላቸውና ተቀባይነትም የሌላቸው ከመሆን አልፎ አሜሪካን የሚያዳከሙ ናቸው የሚል እምነት ላይ ደርሶ ነበር ስለዚህ ከፊቱ ላለው በዋሸንግተን የድሀ ህዝቦች ሰልፍ በሚል ስያሜ ላቀደው ትዕይንት ዝግጅት ማድረግ ጀመረ ኪንግ ሚያዝያ ቀን ባደረገው ንግግር አጋጣሚውን ከ ጀምሮ የሲቪል መብቶችን ለማስከበር የተደረጉ ትግሎችን በማስታወስ በትግሉ የተሳተፉትን ሁሉ ለማመስገን ተጠቅሞበታል በንግግሩ ውስጥ እኔ የአግዚአብሔርን ፈቃድ ብቻ ለመፈጸም አፈልጋለሁ በማለት መንፈሳዊ ተልዕኮ እንዳለው ገልዷል ቀጥሎም አግዚአብሔር ወደ ተራራ አወጣኝ እኔም አሻግሬ ተመለከትኩ ከዚያም የተስፋዩቱን አገር አየሁ አኔ በዛሬው ምሸት በዚህ ደስ ተሰኝቻለሁ ስለ ምንም ነገር አልሰጋም ማንንም አልፈራም አይኖቼ የጌታን መምጣት አይተዋል ሲል ደምድሟል ይህ ማርቲን ሉተር ኪንግ አስከ መጨረሻው የህይወት ዘመኑ የደከመለት ራዕይ ነው ዋረን ጄ ሀሊበርተን ጸሐፊና መምህር የአር መግቢ ማርቲን ሉተር ኪንግ ዛሬ በህይወት ቢኖር ኖሮ እንዲህ ብዬ እጠይቀው ነበር ነሐሴ ያኔ ህልም አለኝ የተሰኘውን ንግግር ለማድረግ ስትሰናዳ ምን ይሰማህ ነበርፇ እነዚያ ያንተን ንግግር ለማዳመጥ በዋሸንግተን ዲሲ ሊንከን አደባባይ የተሰበሰቡ ከሁለት መቶ ሺህ በላይ ነጮችንና ጥቁሮችን ስትመለከት አስገርሞህ ነበር አንድ የሰላሳ አራት ዓመት ጥቁር ጎልማሳ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዴት ወደ አሜሪካ የታሪከ ምህዋር አንደገባ ስታስብ አስደንቆህ ነበርፇ ይህን ህልምህን ለመላው ዓለም ለመንገር ስትነሳ የተፈጠረብህ የፍርሃት ስሜት ነበረፇ ዳሩ ምን ያደርጋል የፈሪዎች ግድያ እነዚህን ጥያቄዎች ለዕውቁ የሃያኛው ከፍለ ዘመን አሜሪካዊ ነብይ እንዳናቀርብ ዕድል ነፍጎናል ዶር ኪንግን አግኝተን መጠየቅ ስለማንችል የማርቲን ሉተር ኪንግ ጎልያድ በነበረው የጂም ከሮው አስከሬን ላይ የታሪክ ምርመራ አድርጌ አቅርብላችኋለሁ ይህ ጂም ከሮው የተባለ ፍጡር የተፈጠረው ከዘረኝነት ሲሆን ራሱን ዲሞክራሲያዊ ብሎ በሚጠራ አገር ውስጥ አንኳን ብርቱ አምባገነን ነበር ስረ መሠረቱና ተጽዕኖው ደግሞ ከዩናይትድ ስቴትስ አልፎ ድንበር ተሻግሮ ባህር አቋርጦ ተንሠራፍቷል እንደዚያም ሆኖ ለብዙ አሜሪካውያን በግልጽ የሚታይ አልነበረም አንዳንድ ጊዜ ግን ውድቀቶች በተለይ ደግሞ ዓለማቀፍ ይዘት ሲኖራቸው ያንቀላፉትን እንኳን የመቀስቀስ ኃይል አላቸው በ ማርቲን ሉተር ኪንግ ትንሹ ከመካከለኛ ጥቁር አሜሪካውያን የወንጌል አገልጋዮች ቤተሰብ አትላንታ ጆርጅያ ውስጥ ሲወለድ ዓለም ወደ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ቀውስ አያመራች መሆኗን ብዙ ሰው አልተገነዘበም ነበር ኪንግ በተወለደ በአሥር ወሩ የምዕራቡ ዓለም ራሱ በፈጠረው ኢኮኖሚያዊ ድቀት ተመታ ነገር ግን በጥቁሩ ማህበረሰብ ላይ ይደርስ የነበረው ኢኮኖሚያዊ ድቀት ሌሎች ላይ ይደርስ ከነበረው የከፋና ተደጋጋሚነት ያለው ነበር እነዚህ ህዝቦች ሰብዓዊ ከብርና መተዳደሪያ ፍለጋ ወደ ሌሎቹ የዩናይትድ ስቴትስ ግዛቶች ይሰደዱ ነበር እንደዚያም ሆኖ የከተማ ህይወት መሻሻልና የኢንዱስትሪ መስፋፋት ለነዚህ ጥቁሮች አንዳች ፋይዳ ሳይሰጥ ጥሏቸው ሄዴል ማርቲን ሉተር ኪንግ ትንሹ ከመካከለኛ ቤተሰብ በመወለዱ ተነሳ ከሌሎቹ የጥቁሮች ልጆች የተሻለ ዕድሰኛ ነበር ነገር ግን በኢኮኖሚ ተሽሎ መገኘት ብዙሀን ነጮች ልዩ ልዩ ቀለም ያላቸውን ህዝቦች በበታችነት በሚመለከቱበት አገር ውስጥ በአፍሪካዊ አሜሪካውያን ላይ የሚፈጸመውን አድልኦ ለማስቀረት አልቻለም በዘረኝነት የሚያምኑ ሰዎች ከፍተኛ የህዝብ ገንዘብ ወጪ እያደረጉ አሜሪካ ውስጥ ጥቁሮች የበታች መሆናቸውን ሲያስተምሩ ይውላሉ ባተሌ ጥቁር ጎልማሶች የልጆቻቸው ዕድል እንዲሻሻል ሲታትሩ ልጆቻቸው ደግሞ የተለየ ነገን ያልማሉ አንደ ማንኛውም ሰው ሁሉ የማርቲን ሉተር ኪንግ የህልም ዓለም ወደ ንቃት ጉዞ የጀመረው ጥር ቀን ከልደቱ ዕለት ጀምሮ ነበር ነገር ግን የነጭ ዘረኞች ጫጫታ የወጣት ጥቁሮች አካሄድ ባልታሰበ ፍጥነት አንዲጓዝ አደረገ ግንቦት ቀን ቴነሲ ውስጥ አንድ ጥቁር ታዳጊ በነጮች ተደብድቦ ሲገደል ማርቲን ገና የአራት ወር ጨቅላ ነበር ሐምሌ ቀን ደግሞ በፕሪንሰስ ኣን ሜሪላንድ ነጮችና ጥቁሮች ተጋጠመ ወር ሳይሞላ ነሐሴ ቀን ነጮችና ጥቁሮች እንደገና በኒውዮርክ ጎዳና ላይ በአደባባይ ተፋለሙ ከአሥራ ሁለት ቀን በኋላ ባልቲሞር ሜሪላንድ ውስጥ በዘር ምከንያት በተቀሰቀሰ ጠብ ሃያ ሰዎች ጉዳት ደረሰባቸው የአንዲህ ዓይነቶቹ ግጭቶች መንስኤ ብዙ ጊዜ ግልጽ አልነበረም ነገር ግን ግጭቶቹ ሥር የሰደደ ጥላቻ መኖሩን ያመለከታሉ ከአሥራ ስድስተኛው ከፍለ ዘመን የአዲሱ ኮሎኒያሊዝም ከስተት ጀምሮ በተለያዩ ዘሮች መካከል ጥላቻ መታየቱ የተለመደ እየሆነ መጥቷል በዶር ኪንግ የጎልማሳነት ዘመን በዓለም ላይ የተከናወኑ ድርጊቶችንና በተለያዩ ዘሮች መካከል የተካሄዱ መራራ ተቃውሞዎችን አንስቶ ማየት የኪንግን ህልም አስፈላጊነትና አፈጣጠር እንድንገነዘብ ይረዳናል አሃ አውሮፓውያን ፍላጎቶቻቸውን በቀላሉ ለማሟላት ሲሉ ራቅ ብለው በሚገኙ አገሮች ውስጥ የቅኝ አገዛዝ አስተሳሰባቸውንና ድርጊታቸውን ለማስረጽ ደፋ ቀና ይሉ ነበር ቀስ በቀስም ድርጊታቸውን ዛሬ ጉዲፈቻ ብለን የምንጠራውን ስም በማላበስ ትክከለኛነቱን ለማሳመን ጥረት ያደርጉ ጀመር የጉዲፈቻ አስተሳሰብ መሠረቱ የሰው ልጅ ማህበራዊ ግንኙነት በአብዛኛው በመረዳዳት ላይ የተመሠረተ ነው የሚል ነው አውሮፓውያን ከርስቲያናዊ ልግስና የሚል አስተሳሰብ ተመርኩዘው ስዎች ከራሳቸው ለሚያንሱ ሌሎች ሰዎች ድጋፍ ሊያደርጉ ይገባል የሚል አምነት ነበራቸው ተረጂዎች ደግሞ ለተደረገላቸው ዕርዳታ ቢወዱም ባይወዱም በጉልበት ዋጋውን መከፈል ነበረባቸው በዚህ ዓይነት መንገድ ምዕራብ አውሮፓውያን የነበራቸውን ዕውቀትና ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ተጠቅመው ልዩ ልዩ ዝርያና ባህል የነበራቸውን ቀደምት ህዝቦች በልማት ስም ሲበዘብዚቸው ነበር እነዚህ ዘመናዊ አስተዳዳሪዎች ራሳቸውን የነዚያ ነባር ህዝቦች ተጠሪዎች አድርገው ይቆጥሩ ጀመር ምጽዋቱ ለጥቁሮች ብቻ አልነበረም ሴቶች ህንዶች ባጠቃላይ አውሮፓዊ ያልሆኑ ህዝቦች ሁሉ የዚህ አንዳንዶች የነጭ ወንዶች የበላይነት በሚሉት ድርጊት ተጠቁዎች ነበሩ በአሥራ ሰባተኛው ከፍለ ዘመን አጋማሸ ላይ የተካሄደው የእንግሊዝ የእርስ በርስ ጦርነት ድሃ በሆኑ ነጭ ወንዶችም ላይ ፍትሃዊ ያልሆነ የመደብ መድሎ መኖሩን ግልጽ አደረገ በመደቦች መካከል ያለውን ድንበር መሻገር እየከበደ በመጣ ቁጥር ከነጭ ቅኝ ገዥ አመራሮች አንዳንዶቹ በተለይም በሰሜን አሜሪካ የእንግሊዝ ቅኝ ገዥዎች ይህን ማህበራዊና ፖለቲካዊ አለመመጣጠን መቃወም ጀመሩ ለምሳሌ ከነዚህ ውስጥ አንዱ የሆኑት አሜሪካዊው ቶም ፔን ቅኝ ገዥዎች ግብዝነት ውስጥ እንዳይዘፈቁ ሰዎች ሁሉ በአኩልነት መታየት አለባቸው የሚል አመለካከት ነበራቸው ይህ ማህበራዊ ልዩነት ወይም መበላለጥ አሜሪካ በ ከብርታኒያ ነጻነቷን ካገኘችበት ጊዜ ጀምሮ የህዝቦቿን ኑሮ ቀፍድዶ ይዞ ይገኛል ኗሃ የዘረኝነት ችግር ከጥንታዊው ሰው የጎሰኝነት አጀማመር ጋር እኩል ዕድሜ ያስቆጠረ ቢሆንም በተግባር ልዩ ወደ ሆነ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተቋም የተሸጋገረው በኛው መቶ ክፍለ ዘመን ነበር በዚያን ጊዜ ነበር በአሜሪካና በፈረንሳይ አብዮቶች ተፈልፍለው የነጭን የበላይነት የሚያንጸባርቁ ህጎች እንደተፈጥሮአዊ ህጎች ተቆጥረው በአዳዲሶቹ ሪፓብሊኮች ማህበራዊና ፖለቲካዊ ህይወት ውስጥ በሚያሳዝን ሁኔታ ዕውቅና ያገኙት የዩናይትድ ስቴትስ ህገ መንግሥት አሜሪካ በአፍሪካ የባሪያ ንግድ ውስጥ ያላትን ተሳትፎ እንድታቆም በ የደነገገ ቢሆንም ንግዱ በተለይም በምዕራቡ ከፍል አስከ አሥራ ዘጠነኛው ከፍለ ዘመን ማገባደጃ ድረስ ቀጥሎ ነበር በዓለማቀፍ ደረጃ የባሪያዎች አቅርቦት እንዲቀንስ መደረጉ በአገር ውስጥ የነበረውን የባሪያ ንግድ አላስቆመም ባሪያዎቹ ተዋልደው መበራከታቸውም አልቀረም በ በተደረገው የህዝብ ቆጠራ ከሰላሳ ሁለት ሚሊዮን የአሜሪካ ህዝብ ውስጥ አራት ሚሊዮን የሚሆኑት በመጠኑ የተሻሻለ ነገር ግን አፍሪካዊነቱን ጨርሶ ያልለቀቀ ባህል ያላቸው ባሪያዎች ነበሩ አገሪቱ አንድነቷን ለማጠናከርና የኔግሮዎችን የወደፊት ባህልና ፖለቲካ ፅጣ ፈንታ ለመወሰን በቅድሚያ የርስ በርስ ጦርነት ማካሄድ አንዳለባት ውሳኔ ላይ ደረሰች ፕሬዝዳንት አብርሃም ሊንከን ሚያዝያ ቀን ባደረጉት የሁለተኛ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ንግግራቸው እንደገለጹት ካገሪቱ ህዝብ ውስጥ አንድ ስምንተኛውን የያዙት ልዩ ልዩ ቀለም ያላቸው ባሪያዎች ሲሆኑ አነሱም በመላ አገሪቱ ተሠራጭተው ሳይሆን በደቡብ ከፍል ብቻ ተከማችተው ይገኛሉ እነዚህ ባሪያዎች የራሳቸው የሆኑ ፍላጎቶችና ጠንካራ ባህሎች አሏቸው የጦርነት መንስኤ የሆነው ይህ የነሱ ፍላጎት አለመሟላት እንደሆነ ሁሉም ይገነዘባል ብለው ነበር በዚህ ከ እስከ በተካሄደ ጦርነት ወቅት ነበር ፕሬዝዳንት ሊንከን የነጻነት አዋጅ የተባለውን ፕሬዝዳንታዊ ትዕዛዝ ያስተላለፉት ኣባ ሊንከን መጋቢት ቀን ባደረጉት የመጀመሪያ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ንግግራቸው የባርነት ተቋማት ባሉባቸው ግዛቶች ውስጥ ስለ ጉዳያቸው በማናቸውም መልኩ ጣልቃ ልገባ አልሻም ቢሉም የጦርነቱ መራዘምና አሱን ተከትሎ የመጣው መሰላቸት ከሌሎች ምከንያቶች ጋር ተዳምረው ሃሳባቸውን እንዲቀይሩ አስገድዷቸዋል የነጻነት አዋጁ ያገሪቱን አንድነት ጥያቄ ከባሪያዎች ነጻ መውጣት ጋር አቆራኘው ህዳር ቀን ጌትስበርግ ውስጥ ባደረጉት ሁለተኛው የፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ንግግራቸው እሜሪካ ውስጥ ማህበራዊ አኩልነት ህልም አንጂ ፅውን እየሆነ አይደለም ሲሉ በይፋ ተናገሩ ጆን ዊልከስ ቡዝ በ ሊንከንን ሲገድል ታላቁን የኛው ከፍለ ዘመን የአሜሪካ ፕሬዝዳንት መግደል ብቻ ሳይሆን ሊንከን ተስፋ ያደረጉትን አዲስ የዘር እኩልነት ዘመን እስከ ሞት ለማቁሰል ችሷል ከ እስከ የተሃድሶ ዘመን ተብሎ በሚጠራው አጭር ጊዜ ውስጥ አሜሪካ አፍሪካዊ ዝርያ ላላቸው አሜሪካውያን የማንኛውም ፖለቲካ ድርጅት ተባባሪ አባላት እንዲሆኑ ፈቅዳላቸው ነበር ነገር ግን በታዋቂ ምሁራንና የሃይማኖት መሪዎች ሸርና ደባ ምከንያት የቀድሞ ህጎች ታድሰው ሥራ ላይ በመዋላቸው በዘሮች መካከል ዲሞከራሲን ለማስፈን የተወጠነው ታሪካዊ ሙከራ ተደናቀቆፈ ይህ የማዕከላዊው መንግሥት መስፋፋት የፈጠረው ስጋት የፌደራሉ ግዛቶች ጉዳይ እንደገና እንዲጤን አደረገ ይህ አስተሳሰብ በኋላ ላይ የግዛቶች መብት የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል ሆኖም ግን የየግዛቱ መንግስታት ለከልላዊ ፍረጃ ተጋላጭ ስለነበሩ ከተሃድሶ ዘመን ሙከራ በኋላ ነጻ የወጡት ባሪያዎች መልሰው መብታቸውን እንዲያጡ ተደርገዋል ከ እስከ ባሉት ጊዜያት መካከል የዘር ልዩነት ህጋዊነት አግኝቶ የአሜሪካን ህይወት ተቆጣጠረው የአሜሪካ ምከር ቤት በ የሲቪል መብቶች ህግ ቢያወጣም ጠቅላይ ፍቤቱ ህጉ ህገ መንግሥቱን ይጻረራል በሣለት በ ውድቅ አድርጎታል ዘረኛ ሃ ነጮች ጂም ከሮው በመባል የሚታወቁ ዘረኛ ማህበራዊ ከንዋኔዎችና ህጎችን ሥራ ላይ በማዋል አፍሪካውያንን አይሁዶችንና ብዙ የአሜሪካ ካቶሊኮችን በተለየ ትቤት እንዲማሩና በተለየ የመኖሪያ ሰፈር ተገልለው እንዲኖሩ አደረጉ ከዚህ የተነሳ እስከ ሃያኛው ከፍለ ዘመን መጨረሻ ድረስ በነበሩት ጊዜያት ሁሉ በተለያዩ ዘሮች መካከል የሚከናወን ጋብቻና ግንኙነት አደገኛና መሳቂያ መሳለቂያ እስከመሆን ደረሰ በአፍሪካ አሜሪካውያንና በአይሁዶች ላይ የሚሰነዘረው ጥላቻ ውስጥ ውስጡን በህዝቡ ዘንድ ተቀባይነት አግኝቶ ነጭ አሸባሪዎች በቡድን እየተደራጁ አስገድዶ በመድፈር በድብደባ በግድያና ቤት በማቃጠል አገር አንዲያምሱ አበረታታቸው የነጮች ዘረኝነት ሌላ መልከም ነበረው በዘረኝነት ላይ የተመሠረተ ሥርዓት አሜሪካ ውስጥ አቆጠዋቁጠ ነጭ ነጋዴዎች ለጥቁሮች የተለየ የአገልግሎት ሥፍራ አዘጋጁ ከዚህ የተነሳ ኔግሮዎች ደረጃው ዝቅተኛ ለሆነ አገልግሎት አኩል ወይም ከፍ ያለ ዋጋ ለመክፈል ተገደዱ በመላ አገሪቱ ለጥቁሮች የተለዩ መዝናኛ ቤቶች ሆስፒታሎች የቀበር ሥፍራዎች የህዝብ ማመላለሻዎች መጸዳጃ ቤቶች መጻህፍት ቤቶች ሆቴሎች ምግብ ቤቶች ቲያትር ቤቶችና ትቤቶች ተመደቡ እነዚህ ድርጊቶች በደቡብ የአገሪቱ ከፍል በጣም የተስፋፉ ሲሆን በሌሉች ግዛቶችም ተግባራዊ ሆነዋል ድርጊቶቹ በተለይም ትምህርትን በተመለከተ ጠቅላይ ፍቤቱ በፕሌስና ፈርጉሰን መዝገብ ላይ በ በሰጠው ውሳኔ ህጋዋነትን አገኙ በዚህ በቱ ውሳኔ መሠረት ለህዝብ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት አገልግሎታቸውን ለጥቁርና ነጭ አኩል ነገር ግን ለየብቻ ሊሰጡ ይችላሉ ይህ ድርጊት የአሜሪካ መንግሥት በማንኛውም ደረጃ ጥቁር አሜሪካውያን በሚከፍሉት ገንዘብ ለነጮች የተሻለ አገልግሎት ለጥቁሮች ደግሞ ከደረጃ በታች የሆነ አገልግሎት እንዲሰጥ አስቻለው ይህ የዘረኝነት አሠራር ሁለት እኩል ያልሆኑና የተለያየ ባህል ያላቸው ማህበረሰቦችን ፈጠረ ታዋቂው ጥቁር አሜሪካዊ ገጣሚ ፓል ሎሬንስ ኗሃ ዳንባር ስለዚህ ሁኔታ በጽሁፉ ውስጥ በለሆሳስ ሸፍነው ደበቁን በማለት ገልጾታል የጂ ም ከሮው ዘመን ዘረኝነትን እንዳቀፈ የጥቁር አሜሪካውያንን መንፈስና አዕምሮ ከቱ የተሀድሶ ዘመን መጨረሻ አንስቶ ግንቦት ቀን ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ በብራውንና ቶፔካ ትምህርት ቦርድ መዝገብ ላይ እስከሰጠው ታሪካዊ ውሳኔ ድረስ ለሰማኒያ ዓመታት ተንሰራፍቶ እንዲቆይ አደረገ በዝነኛው ጥቁር አሜሪካዊ ታሪከ ጸሐፊ ጆን ሆፕ ፍራንከሊን ግምት መሠረት ከ እስከ አንደኛው የዓለም ጦርነት መጀመሪያ ድረስ ሶስት ሺህ ስድስት መቶ አፍሪካዊ አሜሪካውያን ተደብድበው ተገድለዋል ይህ ቁጥር ነጮች በጥቁር ወንድና ሴቶች ላይ የፈጸሟቸውን የአስገድዶ መድፈር ወንጀሎችና በማይፈለጉበት አገር ውስጥ ለመኖር ደፋ ቀና የሚሉ አፍሪካዊ ዝርያ ባላቸው አሜሪካውያን ላይ የተደረጉ ተቆጥረው የማያልቁ አስነዋሪ ተግባሮችን አያካትትም የአሜሪካን አሳዛኝ የዘረኝነት ታሪከ እንቆቅልሽ የሚያደርገው የዲሞከራሲ መርሆችን መመሪያዋ ባደረገች አገር ውስጥ መከናወኑ ነው ማርቲን ሉተር ኪንግ የተወለደው ዘረኝነት ሃይማኖታዊና ዲሞከራሲያዊ እሴቶችን እያጠፋ መሆኑን ለአገሪቱ ለማስታወስ ጥረት እየተደረገ ባለበት ወቅት ነበር ነገር ግን የታሪከ ማዕበል ይህን ሃሳብ የሚያራምዱ ሰዎች ከሚጓዙበት አቅጣጫ በተቃራኒው የሚሄድ ይመስላል ኪንግ ከመወለዱ በፊት ደብልዩኢዲ ቡዋን የመሳሰሉ ምሁራን ዘረኝነት ዓለማቀፋዊ ከስተት ነው በማለት ለረጅም ዓመታት ሲከራከሩ ቆይተዋል ይሁን እንጂ ዘረኝነትን ቀላልና ከፋት የለሽ አድርጎ መውሰድ ከባድ አደጋ እንደሚያስከትል ከሁለተኛው የዓለም ጦርነትና ከናዚ ፍጅት ተምረናል በ ማርቲን ሉተር ኪንግ ትንሹ የአንደኛ ከፍል ትምህርቱን ሊጀምር በሚዘጋጅበት ወቅት አዶልፍ ሂትለር ስለ አርያን ዘር የበላይነት የነበረው የተዛባ አመለካከትና የኮሚኒዝም ስጋት የተገጣጠመበት ወቅት ነበር ጀርመን ውስጥ የዌይማር ዲሞከራሲያዊ ሪፓብሊክ ተገልብጦ ኛ ሪኸ አ በኃይልና በሸፍጥ ተመሠረተ እሱን ተከትሎ ጎሰኝነት ጀርመንን ቀስፎ ያዛት በመላው ዓለም የተከሰተው የኢኮኖሚ አለመረጋጋት እየከፋ በሄደ ቁጥር ፈላጭ ቆራጭ መንግሥታት በአገሮቻቸው ውስጥ ለየት ያሉ የፖለቲካ አስተሳሰቦች አንዳይራመዱ በህግ አገዱ እነዚህ ሥርዓቶች በጀርመን በጣሲያን በሶቭየት ህብረትና በጃፓን አቆጠቆጡ በትውልደ አፍሪካዊ አሜሪካውያን ላይ የደረሰው በደል ናዚ ጀርመን በአይሁዳውያን ላይ ካደረሰቸው ግፍ የሚስተካከል ባይሆንም የደረሰባቸው ስነ ልቦናዊ ተጽዕኖ ግን ተመሳሳይነት ነበረው አያደር የኩ ከላከስ ክላን አንደገና ማንሠራራት እንዲሁም አባ ቻርለስ ኢ ኩግሊን በኋላ ደግሞ እነ ቄስ ጄራልድ ኬ ስሚዝን የመሳሰሉ የቀኝ ዘመም የቤተከርስቲያን መሪዎች ዘረኛና ፋሽስታዊ አመለካከት ለአሜሪካ ዲሞክራሲ ውርደት መሆኑን ብዙ አሜሪካውያን ተረዱኑ በዚህ መሃል የተለያየ ዘር ሃይማኖትና የፖለቲካ አመለካከት ያላቸው ቅን ዜጎች ተሰባስበው ይህን ድርጊት ለመቃወም እጅ ለእጅ ተያያዙ ሚያዝያ ቀን ማርቲን ሉተር ኪንግ ትንሹ አንደኛ ዓመት ልደቱን ካከበረ ጥቂት ሳምንታት በኋላ ደግሞ ከዘረኝነት ነጻ የሆነች ዓለም ማየት የሚፈልጉ ዜጎች በህንዳዊው ማህተማ ጋንዲ ቆራጥነት መመሰጥ ጀመሩ ጋንዲ የእንግሊዝ መንግሥት በህንድ ጨው ላይ ቀረጥ ለማስከፈል የማቀዷን ድፍረት በመቃወም በጋምቤይ ሰርጥ ላይ የጨው ተቃውሞ ሰልፍ እንዲካሄድ አደረገ በወቅቱ በጦር ኃይል ጠንካራ የነበረውን የእንግሊዝ ሠራዊት ህንዳውያን በሰላማዊ የትግል ስልት እንዲቋቋሙት ጋንዲ ህዝቡን አስተማረ ይህን የትግል ስልት ጋንዲ ራሱ ወጣት ጠበቃ በነበረበት ወቅት ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ማህበራዊ ለውጥ ለማምጣት በሙከራ ደረጃ ተጠቅሞበታል ይሁን እንጂ የአፍሪካ አሜሪካውያን ማህበረሰብም የነጮችን የበላይነት በመታገል ረገድ የራሱ ታሪክ አለው ይህ የትግል ባህል አምስት መልክ ነበረው እነሱም የባህል ተቃውሞ ተቋማዊና ድርጅታዊ አምቢተኝነት ከርክር ወይም ሙግት ዕቀባና ህዝባዊ አመጽ ናቸው የትውልደ አፍሪካዊ አሜሪካውያን ባህል ልዩና የራሱ ባህሪያት ያሉት ቢሆንም ኗጂ በምዕራባውያን ባህል ውስጥ ስላለው ድርሻ ዕውቅና ለማግኘት ከባድ ፈተና ነበረበት የው የሀርለም ተሃድሶ ለአካዳሚ ለስነ ጽሁፍና አርት ትግል ስኬት እንደ መመዘኛ ይወሰዳል የዚህ ፍሬ መጎምራት የሃያኛው ከፍለ ዘመን የሲቪል መብት ተቆርቋሪዎችን መንፈስ ለማደስ በእጅጉ ረድቷል በኛው ከፍለ ዘመን መጨረሻ ላይ ከተመሠረቱበት ጊዜ አንስቶ የጥቁር አሜሪካውያን አብያተ ከርስቲያናት የመረዳጃ ማህበራትና ሌሎች የጥቁር ተቋማት የነጮችን የበላይነት ሲታገሉ ኖረዋል እነዚህ ማህበራት ኋላ ላይ ለተደረጉት ትግሎች ሁሉ መሠረት ሆነዋል በየወቅቱ የተነሱት ተቃውሞዎች ከ ባሉት ጊዜያት ውስጥ በዓመት አንዴ ይሰበሰብ የነበረው የኔግሮ ብሔራዊ ህብረት ኔብህ የመሳሰሉ ድርጅቶች እንዲፈጠሩ ምከንያት ሆነዋል ነገር ግን በ እና በ በቅደም ተከተል እንደተመሠረቱት የባቀህብማ እና የከተሞች ብሔራዊ ሲግ ከብሊ የተሳካለት የለም ያካሄዳቸው ውጤታማ ሙማቶችና ያሳትም የነበረው ከራይሲስ የተባለ መጽሄቱ ባቀህብማን ስኬታማ የጥቁር አሜሪካውያን የሲቪል መብት ተከራካሪ ድርጅት አድርገው ስሙን አገነኑት ቻርለስ ሂዩስተንና ታርጉድ ማርሻልን በመሳሰሉ ዕውቅ ጥቁር አሜሪካውያን ጠበቆች አማካኝነት በተራቀቀ የከርከር ስልት በብራውንና ቶፔካ መዝገብ በጠቅላይ ፍቤት ሲካሄድ የነበረውን ሙሣት በ ባቀህብማ ሰመርታት በቃ ከብሊ በበኩሉ ዲፕሎማሲያዊ ጥበብን ሳይንሳዊ የመረጃ አሰባሰብ ዘዴና የከተማ ጮሌነትን በመጠቀም ስለ ጥቁር አሜሪካውያን የሚነዛውን የሃሰት ወሬ ከሥሩ መንግሎ ለመጣል ቸሷል ይሁን እንጂ ሁለቱም ቡድኖች በየግዛቶቹ በርካታ ቅርንጫፎች ቢኖሯቸውም መላውን የጥቁር ማህበረሰብ ለማንቀሳቀስ ግን አልተቻላቸውም የአፍሪካ አሜሪካውያን የሃይማኖት እንቅስቃሴዎች አብዛኛውን የጥቁሩን ህዝብ አስተያየት ተቀብሎ ሥራ ላይ በማዋል ረገድ ጥሩ ተሞከሮ ኣ አላቸው ራንዳል ኬ ባርኬት ጋርቬይዝም እንደ ሃይማኖት ንቅናቄ በተሰኘ መጽሐፍ ውስጥ በማርከስ ጋርቬይ የተመሠረተውን የኔግሮ መሻሻል አጠቃላይ ማህበርን ኔመአማ እንደ ሃይማኖት ንቅናቄ እንደሚመለከተው አጥብቆ ተከራክሯል በዎቹ ውስጥ ጋርቬይ ነጮች በጥቁሮች ባህልና ፖለቲካ ላይ የሚሰነዝሩትን ትችት ችላ እንዲሉት ትውልደ አፍሪካዊ አሜሪካውያንን ይገፋፋ ነበር ነገር ግን ያም ሆኖ የፌደራል መንግሥቱ ጋርቬይን መልዕከት በማምታታት ወንጀል ከሶ ፍርድ ቤት ሊገትረው ችሏል ይህ ድርጊት የጥቁሮችን በራስ የመኩራት ስሜት አልቀነሰውም ይልቁንም እንቅስቃሴው ሌላ መልክ ያዘ ለምሳሌ ጆርጅ አለከሳንደር ማከጉሪ ዊሊያም ያንሲ ቤል እና የቺካጎ መጥምቃውያን ቤተከርስቲያን ፓስተር ጁኒየስ ሲዛር ኦስቲን የመሳሰሉ የሃይማኖት ሰዎች የጋርቬይ ቅርብ ጓደኞች ለመሆን በቅተዋል ፓስተር ኦስቲን በ ዕቃና አገልግሎታቸውን ለጥቁሮች ለሚሸጡ ግን ጥቁሮችን ከማይቀጥሩ ድርጅቶች ምንም ነገር ያለመግዛት አድማ እንዲመቱ ጥቁሮችን አስተባብሯል የሥራ ዕድል ለጥቁሮች የተባለው ይህ እንቅስቃሴ እስከ ከሊቭላንድና ኒውዮርክ ድረስ ተስፋፍቶ ነበር በጥቅምት አሜሪካን የመታው ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ብዙ አሜሪካውያን በተለይም አፍሪካውያኑ የአብርሃም ሊንከንን ግራንድ ኦል ፓርቲ በመተው ወደ ዲሞከራቱ ፕሬዝዳንት ፍራንክሊን ዲላኖ ሩዝቨልት የአዲስ ስምምነት ፕሮግራም ፊታቸውን እንዲያዞሩ አደረገ ፕሬዝዳንት ሩዝቨልት ከወሰዷቸው ዋና ዋና አርምጃዎች ውስጥ አንዱ በ በፕሬዚዳንታዊ ትዕዛዝ ቁጥር እንዲቋቋም ያደረጉት የፍትሃዊ ቅጥር ኮሚሽን ነው በዚህ ወቅት የተሸከርካሪ ኩባንያ ሠራተኞች ፕሬዝዳንት የነበሩት ኤ ፊሊፕ ራንዶፍ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ከተጀመረ አንስቶ የጦር መሳሪያ አያቀረበ ባለው የመከላከያ ኢንዱስትሪ ውስጥ ሩዝቨልት የዘር ልዩነትን የማያስቆሙ ከሆነ በዋሽንግተን ሰላማዊ ሰልፍ እናካሂዳለን በማለት አስጠንቅቀው ነበር አ። ዶር ኪንግ ከሌሎች አባሪዎች ጋር ከሞንትጎመሪው የአውቶቡስ ዕቀባ ጋር ተያይዞ እውነትነት ለሌለው ነገር የንግድ ሥራን ለማስተጓጎል ተስማምታችኋል ተብለው ተከሰሱ ሪዕ ፊ የፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍቤት በከተማ አውቶቡስ ውስጥ የዘር ልዩነት ማድረግ ህገመንግሥታዊ አይደለም ሲል ወሰነ ሪ ዶር ኪንግ ባቀህብማ ሳንፍራንሲስኮ ውስጥ በጠራው ስብሰባ ላይ በአንግድነት ተገኝቶ ንግግር አደረገ ጆባ ሯመረ ሶስት ዳኞች የተሰየሙበት የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍቤት በአላባማ ግዛት ውስጥ በዘር ላይ የተመሠረተው ትራንስፖርት ህግ ኢህገመንግሥታዊ መሆኑን የሰጠውን ውሳኔ የአሜሪካ ጠቅላይ ፍቤት አጸደቀው ታቃሀጎ በአውቶቡስ ውስጥ የሚደረግ የዘር ልዩነት አንዲቆም ለሞንትጎመሪ ከተማ የአውቶቡስ ድርጅት መሪዎች ከፌደራል መንግሥት ትዕዛዝ ተላለፈ ትፅዛዙ ለመንግሥት ባለሥልጣናትም ደረሰ ታፅዕ በሞንትጎመሪ አውቶቡሶች ውስጥ የዘር ልዩነት አበቃ ጥረያልፈነዳ ቦምብ በዶር ኪንግ በረንዳ ላይ ተገኘ ረ የደቡብ ከርስቲያን አመራር ምቤት ደከአም አትንላታ ውስጥ በአቤኔዘር መጥምቃውያን ቤተከርስቲያን ውስጥ ተመሠረተ ዶር ኪንግ ፕሬዝዳንት ሆኖ ተመረጠ ያትካድራፖ ታይም መጽሔት በፊት ገጹ ላይ የዶር ኪንግን ፎቶግራፍ ይዞ ወጣ መጎለረም ፕሬዝዳንት አይዘናወር አርካንሳስ የሚገኘው የፌደራል ከብር ዘብ ዘጠኝ ጥቁር ተማሪዎችን ነጮች ብቻ ወደሚማሩበት ሊትል ሮክ ኛ ደረጃ ትቤት አጅበው አንዲያመላልሱ ትዕዛዝ አስተላለፈ መጎረምየአሜሪካ ኮንግረንስ የመጀመሪያውን የሲቪል መብቶች ህግ አጸደቀ በፍትህ መምሪያ ሥር አጸህሃ የሲቪል መብት ኮሚሽን እና የሲቪል መብት ቅርንጫፍ ከፈተ መጎሰረም ጉዞ ወደ ነጻነትየሞንትጎመሪው ታሪከ የተባለው የዶር ኪንግ መጽሐፍ ታተመ መፅስረም ኢዞላ ኬሪ የተባለች የአርባ ሁለት ዓመት ሴት ዶር ኪንግን ደረቱ ላይ በስለት ወጋችው የአዕምሮ በሽተኛ ናት ተባለች ዶር ኪንግ የተወጋው ሀርለም ከተማ ውስጥ ሲሆን በወቅቱ ባሳተመው መጽሐፍ ላይ ስሙን እየፈረመ ሳለ ነበር በመጥፎ ሁኔታ ውስጥ እንዳለ እና ለህይወቱ ግን አስጊ አንዳልሆነ ተገለጸ ያካሯዎ ለሰዖ መጋቧ ገዐ ዶር ኪንግና ባለቤቱ የጠቅላይ ሚኒስትር ኔህሩ አንግዳ ሆነው የሰላማዊ ትግል ስልቶችን እያጠኑ ህንድን ጎበኙ ፐር የማርቲን ሉተር ኪንግ ቤተሰብ ጓዙን ጠቅልሎ አትላንታ ገባ ዶር ኪንግ በአቤኔዘር የመጥምቃውያን ቤተክርስቲያን የአባቱ ረዳት ፓስተር ሆነ ዖነጓድዶፆ በምግብ ቤቶች ውስጥ ያለውን የዘር ልዩነት በመቃወም በሰሜን ካሮላይና የግሪንስቦሮ ተማሪዎች በምግብ ቤቶች ውስጥ ፖምጦ ጎመኦጎፖ አድማ አካሄዱ ሚሰጋረዖ የሰላማዊ ትግል አራማጅ ተማሪዎች አስተባባሪ ኮሚቴ ለጊዜው የተማሪዎችን ተቃውሞ ለማስተባበር በሰሜን ካሮላይና ዩኒቨርስቲ ሾው ውስጥ ተመሠረተ ጥቅምት ውስጥ ቋሚ ሆነ በማህበሩ ምስረታ ላይ ዶር ኪንግና ጀምስ ሎውሰን ዋነኛዎቹ አህ ተናጋሪዎች ነበሩ ፓምሥቻ ዶር ኪንግ ከመቀመጥ አድማ ጋር ተያይዞ ህግ በመተላለፍ ወንጀል ተከሶ ታሰረ ጥምቻታ የአትላንታ ከሱ ተነሳለት ሁሉም ሰልፈኞች ሲለቀቁ ዶር ኪንግ ግን ከትራፊክ ጉዳይ ጋር በተያያዘ በአሥር እንዲቆይ ተደረገ ዶር ኪንግ ወደ ዲካልብ ዲካቱር ጆርጅያ በኋላ ደግሞ ወደ ሬድቪል የመንግሥት አሥር ቤት ተዘዋወረ ከዚያ አሥር ቤት ሁለት ሺህ ዶላር አስይዞ ተለቀቀ ግዐቻ አገር አቋራጭ አውቶቡሶችን ማቀላቀል ዓላማ ያደረገው የመጀመሪያው ያዕዳኑዮዶ ዶ ቡድን በግሬይሃውንድ አውቶቡስ ከዋሸንግተን ዲሲ ተነሳ ይህ ቡድን የዘሮች እኩልነት ምክከር ቤት ዘአም በተሰኘ ድርጅት የተሰባሰበ ሲሆን የተንቀሳቀሰው የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ በአገር አቋራጭ አውቶቡሶች ውስጥ የነበረው ዘረኝነት ኢህገመንግሥታዊ መሆኑን እንደወሰነ ነበር አውቶቡሱ ግንቦት አኒስተን ድንበር ላይ አላባማ ውስጥ ተቃጠለ ተጓዥቹ በርሚንጋም ሲደርሱ በሁከተኞች ተደበደቡ አነዚህ ተጓፐች ጃከሰን ሚሲሲፒ ውስጥ በቁጥጥር ሥር ውለው ከአርባ እስከ ስልሳ ቀናት ያህል በፓችማን አሥር ቤት ቆዩ መጎለፅረም ጀምስ ሜሬዲዝ የተባለ ጥቁር አሜሪካዊ በሚሲሲፒ ዩኒቨርስቲ ተመዝግቦ ለመማር የመጀመሪያውን ሙከራ አደረገ የተመዘገበው ጥቅምት በጠቅላይ ፍቤት ትዕዛዝ ሲሆን ወደ ኦከስፎርድ ሚሲሲፒ ግቢ ሲሄድ በአሜሪካ ሰላም አስከባሪዎች ጀአ አየታጀበ ነበር መጋ ሟዖሂሮ በምግብ ቤቶች የሚፈጸመውን ዘረኝነት በመቃወም መቀመጫ ይዞ ያለመነሳት አድማ ተደረገ ሰልፍ ላይ ዶር ኪንግ በቁጥጥር ሥር ዋለ ሟያጃያ ኪንግ አዚያ ሆኖ ከበርሚንጋም እሥር ቤት የተላከ ደብዳቤ የተሰኘ መልዕከት ጻፈ ግም የበርሚንጋም የጸጥታ ሃላፊ ዩገን ቡል ኮነር በወጣት ጎልማሶችና ህጻናት ሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ የፖሊስ ውሾችና ውኃ እንዲለቀቅባቸው ትዕዛዝ ሰጠ ግጋ። ወያ ዳታ ፖፆሪኘፇው ም«ጀሂን ታሃረ ሷቃፇ መዳኀፍ ጭሩ ዖረበዐያሦ ሮያው ጽሥፉ ያምምሦመሪ ሐውፇታ ሪፇያ ሐም» ዕረ ቦያአታሰ ኖሃሦጨማሪም የ ደደሁሃዖ ያረትሂረኝኛ መራረር ምሳረ ዜዖፇ ለመሠሥሯራሪሦ ይዘሳዳኋ የጥቁሮች መገለልና ተከትሎት የመጣው የዘር ልዩነት የተንሥራፋው ጥቁሮች የበታች ናቸው በሚለው በራሳቸው በጥቁሮችና በአብዛኛው ነጮች መሀል በተስፋፋው አመለካከት ምክንያት ነው ከአፍሪካዊ ባህላችን በግድ በመቆራረጣችን በባርነት በድህነት የምንፈልገውን ሁሉ በማጣታችን ምክንያት ብዙ ጥቁሮች ከብራችንን አጥተናል ነጮች ከጥቁሮች ጋር ባላቸው ግንኙነት ጥቁሮቹ የግብረ ገባዊ ሙያቸውን መሠረት ማጣታቸውን ተረድተዋል ከውስጣቸው ተሟጦ የቀረውን ትንሽ የአኔነት ስሜት በመቋቋም ከራሳቸው ጋር በሰላም ለመኖር አለመቻላችውንም አውቀዋል እነዚህ ከሰው በታች ሆነው የኖሩት ዕድለ ቢስ ጥቁሮች ሰላማቸውን መልሰው ለማግኘት ሁለተኛ ዜጋ መሆን ራሱ በቂያቸው ነው እነሱም ይደሰቱበታል በማለት ለመጽናናት ሞከረዋል በተጨማሪም ጥቁር አሁን የሚገኝበት ዝቅተኛ የማህበራዊ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ደረጃ ለሱ መልካም ነው ብለው ይከራከራሉ ጥቁር ከተወሰነ ደረጃ አልፎ ሊሄድ ስለማይችል የማይችለውን ነገር እንዲሞከር ባይመከሩት ደስ ይለዋል የተጨቆነው ከፍ ያለ ባህል ባለው የሰለጠነ ህዝብ ነው የጌቶች ዘር እስከተወሰነ ደረጃ ድረስ ጥቁሩን ሊያሰለጥኑ የሚችሉት አሁን ያለበትን የበታችነት ሥፍራ የተቀበለው አንደሆነ ብቻ ነው ይላሉ የደቡብ ባህልና ተቋሞቻቸው በሙሉ ይህን አስተሳሰብ ለማራመድ የተደራጁ መሆናቸውን ነጮቹ ዘንግተውታል እያዩት ያለው የበላይነትና የበታችነት እንዲሁም አሁን የምንገኝበት ማህበራዊ ምስቅልቅል እነርሱ የፈጠሩት ሳይሆን በትከከል ይህን የጥቁሮች ትውልድ ማንነት የሚያመለከት መሰላቸው ከጊዜ ብዛት የተነሳ ብዙ ጥቁሮች በራስ የመተማመን ስሜታቸው ሟሽሾ ራሳቸው የሆኑትን ሳይሆን ነጮች ስለነሱ የነገሯቸውን ማለትም ከሰው በታች መሆናቸውን ማመን ጀመሩ ይህን ማንነታቸውን አሜን ብለው እስከተቀበሉ ድረስ በተለያዩ ዘሮች መካከል ሰላም ይሰፍናል ነገር ግን ይህ ሰላም በቀላሉ የሚገኝ ሰላም አይደለም ይህ ሰላም ጥቁሮች ኢ ፍትሀዊነትን ውርደትን ግፍንና ጭቆናን በትዕግስት እንዲቀበሉ የተገደዱበት ነበር ቀስ በቀስ በደቡብ የሚገኙ ብዙ ጥቁሮች መለስ ብለው ራሳቸውን ማየትና መገምገም ጀመሩ ይህ አካሄድ የጥቁሩን ማህበረሰብ አስተሳሰብ አና የደቡብን ማህበራዊ አሰላለፍ ለመቀየር ችሷል ከብራችንን ከራሳችን ላይ አሽቀንጥረን አንዳልጣልን ተገንዝበናል ለገዛ ራስ ክብር ሳይሰጡ ከራስ ጋር በሰላም መኖር እንደማይቻልም ተገነዘብን በዚህ አዲስ አስተሳሰብ ምከንያት በተፈጠረው መደፋፈርና ጥቁሮች ተደራጅተው ለመንቀሳቀስ ዕለት ተለት ባሳዩት ዝግጁነት በደቡብ ሰፍኖ የነበረው ሰላም ችግር ውስጥ ገባ የደቡብ ነጮች በቀደመው ሥርዓታቸው ሙጥኝ ባሉ መጠን ግጭቶችና ብጥብጦች አየተበራከቱ ሄዱ ዛሬ በነጮችና በጥቁሮች መካከል ስፍኖ የሚገኘው ውጥረት መንስኤው ጥቁሮች ራሳቸውን እንደገና መልሰው መገምገም መጀመራቸው ስለ ወደ ፊት ዕጣ ፈንታቸው ማሰብ መጀመራቸው ለፍትህ ለመታገል ቆርጠው መነሳታቸው ነው እኛ ጥቁሮች ለራስ ማዘንን ለራስ ከብር በመስጠት ራስን ዝቅ ማድረግን ደግሞ በራስ መተማመንን ተከተናል ሮዛ ፓርከስ ያች ጥቁር ልብስ ሰፊ ያች የሞንትጎመሪን ሰላማዊ ትግል ያቀጣጠለችው ሴት ለምን ወንበሯን ለቃ ሄዳ ከኋላ አንዳልተቀመጠች ተጠይቃ እንዲህ ነበር ያለችው ይህ የከብር ጉዳይ ነው እነሱ አንዳሉኝ ባደርግ ኖሮ በራሴም ፊት በህዝቤም ፊት አንገቴን ቀና አድርጌ መራመድ አልችልም ነበር አዲሱ ኔግሮ ብዙዎቹ ጥቁሮች ተቃውሞውን የተቀላቀሉት በርግጥ ይሳካልናል ብለው በማሰብ አልነበረም ለምን ተብለው ሲጠየቁ ከነዚህ ሶስት ምከንያቶች አንዱን ይሰጣሉ ጥቁሮች እንደዚህ ጠንከረው ይገፉበታል ብዩ አላሰብኩም ነበር ወይም እኛ ጥቁሮች እንዲህ ዓይነት ቆራጥነት አለን ብዬ አላመንኩም ነበር ወይም ከነጮች የሚሰነዘረው አጸፋ ትግሉን ገና ሳንጀምረው ያኮላሽብናል ብዬ ሰግቼ ነበር የሚሉ ናቸው ከዚህ አንጻር ስንመለከተው ሞንትጎመሪ ውስጥ በሰላማዊ መንገድ ያደረግነው ተቃውሞ አስፈላጊ ነበር ምክንያቱም ከሰሜን እስከ ደቡብ የሚገኙ ጥቁሮች ስለ ራሳቸውና ስለ ሌሎች ጥቁሮች የነበራቸው አስተሳሰብ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን እንደተገነዘቡ አሳይቷል ሞንትጎመሪ ያን አሮጌ አመለካከት በመስበር የጥቁሮችን ማንነት በትክከል የሚገልጽ አዲስ አስተሳሰብና ተግባር ለማሳየት ችሷል ከሞንትጎመሪ የሚከተሉትን ትምህርቶችንም ለመቅሰም ችለናል በህብረት መቆም እንችላለን በሞንትጎመሪ ከታህሳስ ጀምሮ አርባ ሁለት ሺዎቻችን የዘር መድልኦ የሚያራምዱ የከተማዬቱ አውቶብሶችን ከመሳፈር ታዓቅበናል ብዙዎቻችን በየቀኑ የአሥራ አራት ማይል ወይም ሃያ ሶስት ኪሎ ሜትር ጉዞ በእግራችን ተጉዘናል መሪዎቻችን ሊደለሉ አይገባም አብዛኛዎቻችን ተከሰናል ታስረናል ተደብድበናል ይሁንና በየሳምንቱ ሰኞና ሀሙስ ምሸት ለአምልኮ ስንሰበሰብ በጥቁር ምዕመናን ፊት ቆመን ደጋግመን ለእውነተኛ ዓላማ መታሰር ከብር ነው በማለት እንፈከር ነበር በበቂ የነቁ እና ሰላማዊ ታጋዮችን ዛቻና ድብደባ ወደ ኋላ አይመልሳቸውም የሁለት ወገኖቻችን ቤቶች በቦምብ መደብደባቸው ይበልጥ አንድንጠናከር አደረገን በነጭ ዜጎች ምከር ቤት ስብሰባ ላይ ጥቁሮች በጠመንጃ በቀስት በወንጭፍና በሰይፍ መወገድ አለባቸው የሚል ጽሁፍ ሲበተን ከወትሮው በላቀ ጀግንነት ተቋቁመናቸዋል ቤተክርስቲያናችን ታጋይ እየሆነች ነው በሞንትጎመሪ ሃያ አራት አገልጋዮች ታስረው ነበር አስፈላጊ ከሆነ ሁሉም በድጋሚ ተመልሰው ለመታሰር ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል ወደ ኢየሱስ ኑ የሚለውን የወንጌል ቃል ለመስማት ያልፈለጉ የላይኛው መደብ ጥቁሮች እንኳን አሁን ባለው አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ቤተከርስቲያን ማህበራዊ ለውጥ ለማምጣት ሰላማዊ ትግል ከማፋፋም ውጭ ሌላ አማራጭ እንደሌላት ተረድተዋል ሃያ ሺህ ጥቁር ሠራተኞችን ተማሪዎችን ህጻናትን አና ሴቶችን የሚያመላልሱ ተሸከርካሪዎችን ለመከራየት የዋለውን ሰላሳ ሺህ ዶላር ያሰባሰብነው በቤተክርስቲያን ውስጥ ነው አብያተ ክርስቲያናት ነጻ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚጠብቁ ወገኖቻችን የሚሰበሰቡባቸው ሥፍራዎቸም ነበሩ በራሳችን እንተማመናለን ዛሬ ሞንትጎመሪ ውስጥ በልዩ ሁኔታ አንራመዳለን በአስገራሚ ሁኔታ አንገታችንን ቀና አድርገን እንሄዳለን በሞንትጎመሪ የተሰበሰቡ ጥቁር ዘጋቢዎች እንኳን ለኛ የተለየ አመለካከት አላቸው በሥራ ሲደክም ውሎ በአንድ የበርሚንጋም ምሳ ግብዣ ላይ በመገኘት ስለ ሞንትጎመሪ አስተያየት አንዲሰጥ የተጠየቀ አንድ ዘጋቢ ተነስቶ ቆሞ ጥቂት ካሰበ በኋላ አንዲህ አለ ሞንትጎመሪ ጥቁር በመሆኔ እንድኮራ አድርጋኛለች ኢኮኖሚ የትግላችን አካል ነው የሞንትጎመሪ ነጭ ነጋዴዎች የአውቶቡስ ኩባንያውንና የከተማ ባለሥልጣናትን ለማሳመን እየሞከሩ አንደሆነ ሰምተናል ጥቁሮች ወደ መሀል ከተማ ወጥተው ከነጮች ጋር መገበያየት ስላልተመቻቸው ትናንሽ የጥቁሮች ሱቆች መጠናከራቸውን አይተናል ይህ ተቃውሞ ከተጀመረ ወዲህ የነጮች ሱቆች መስተንግዶም ተሻሸሷል ለምናወጣው እያንዳንዱ ዶላር ክብር እያገኘን ነው አዲስና ጠንካራ መሳሪያ አገኘን ኃይል አልባ የትግል ስልት ማህበራዊ ለውጥ ለማምጣት ህግ አስፈላጊ ቢሆንም አዲስ የሚወጡ ህጎችን ሥራ ላይ ለማዋል የሚደረግ ጥረት መልሶ ውጥረትና ሁከት የሚፈጥርበት ጊዜ አለ ትግላችንን ሳናቋርጥ የተፈጠረውን ችግር አየቀረፍን የምንጓዝበትን ዘዴ ስናፈላልግ ነበር አሁን መልሱን አግኝተናል አስፈላጊ ከሆነ ኃይልን አትፍራ ነገር ግን በኃይል ምላሽ አትስጥ ባላንጣዎቻችንን ብናከብር ስለ ሰው ልጆች ግንኙነት አዲስ አይታ ያገኙ ይሆናል አሁን የደቡብ ጥቁር ከፖለቲካዊና ሞራላዊ ዘገምተኝነት መውጣቱን አውቀናል ሞንትጎመሪ ከትግል ወደ ኋላ እንዳናፈገፍግ አስተምሮናል ስለዚህ ለአኩልነት የሚደረገውን ዘመቻ እንደግፋለን ከጥቂት ዓመታት በፊት የነበረውን የወጣት ጥቁሮች አስተሳሰብ በሚቀጥለው ዓረፍተ ነገር አጠቃለን ማስቀመጥ እንችላለን የአላባማ አገረ ገዥ ከመሆን ይልቅ በሀርለም ጎዳና ላይ የመብራት ምሰሶ መሆን ይሻላል ዛሬ ግን በቤተክርስቲያኖቻችን በትቤቶች በምግብ ቤቶችና በመኖሪያ ቤቶች ውስጥ የሚገለጸው ሃሳብ ወንድሜ ባለህበት ሥፍራ ሆነህ በሰላማዊ መንገድ ታገል ምከንያቱም እንዲያስቆጡህ ካልፈቀድከላቸው በስተቀር ታሸንፋለህ የሚል ነው የመሻሻል ለሞንትጎመሪ ታዋቂ መፈከርም ኃይል ሳይጠቀሙ የራስ መብት ማስከበር የሚለው ነው የሞንትጎመሪ ጉዳዮች የቀድሞው ሥርዓት የሞንትጎመሪ ባለሥልጣናት ችግሮችን በውይይት ለመፍታት ዝግጁ አይደሉም ይህም የሆነው ያቋረጥነውን አውቶቡስ ያለመሳፈር አድማ መልሰን ለመጀመር ባስቀመጥነው ቅድመ ሁኔታ ምከንያት አይደለም በአገር አቋራጭ ጉዞ ውስጥ ስላለው መሠረታዊ የዘረኝነት ችግር ጉዳዩ በፍቤት ተይዚል አስከዚያ ድረስ በአትላንታ በሞቢል በቻርልስተንና ብዙ የደቡብ ከተሞች ውስጥ እየተከናወነ ያለው ነገር በመላው ደቡብ ተግባራዊ አንዲሆን እንጠይቃሰለን በዚህ ዘረኛ ሥርዓት ውስጥ የምናነሳው ጥያቄ ከኋላ ተነስቶ ፊት የመቀመጥ ሳይሆን በቅድሚያ የመጣ ሰው ባሻው ቦታ ላይ የመቀመጥ መብት እንዲኖረው ነው በተጨማሪም በክብር የመስተናገድና ጥቁሮች በሚበዙበት የጉዞ መስመር ጥቁር አሸከርካሪዎች አንዲቀጠሩ መጠየቅ ነው አንድ ታዋቂ የቱስካሉዛ ዳኛ ኦትሪን ሉሲ የተባለች ጥቁር ተማሪ አላባማ ዩኒቨርስቲ ለመግባት ባደረገችው ሙከራና በሞንትጎመሪው ኃይል አልባ ተቃውሞ መካከል ግንኙነት እንዳለ ተጠይቆ ነበር ኦትሪን ምን እያደረገች እንዳለች የማታውቅ ምስኪን ልጅ ነች በሞንትጎመሪ የሚኖሩ ጥቁሮች ግን አቅላቸውን ስተው ያበዱ ይመስሉ ነበር ሲል መልሷል ይህ ሰው እንዲህ ሲልም አከሏል በውነቱ ደህና ደህና ጥቁሮች በውጭ ኃይሎች በኮሚኒስቶችና በካድሬዎች ቅስቀሳ ተገፋፍተው ንዴት ውስጥ ገብተዋል ከዚህ የምንረዳው የደቡብ ነጮች ጥቁሮች በራሳቸው ተነሳሽነት እንዲህ ዓይነት ድርጊት ሊፈጽሙ ይችላሉ ብለው ለማመን አሁንም ዝግጁ አለመሆናቸውን ነው የነጭ ባለሥልጣናት ስህተቶች የከተማዬቹ ከንቲባና ሌሎችም ባለሥልጣኖች መለወጣችንን በለመቀበላቸው የሚወስዷቸው እርምጃዎች ሁሉ በጥቁሩ ማህበረሰብ ጦካከል አምቢተኝነትንና አንድነትን አያጠናከሩ ሄቶ ታህሳስ ሞንትጎመሪ ውስጥ ሮዛ ፓርከስ የተባለችን የተከበረች ልብስ ሰፊ አሠሩ ታህሳስ ጥቁሮች የአውቶቡስ ዕቀባ እንዲያደርጉ ጥቂት ሰዎች ጥሪ እያደረጉ መሆናቸውን እንደደረሱበት በጋዜጣ ላይ በማውጣት ጥቁሮችን ለማስፈራራት ሞከሩ ከዚህ የተነሳ ሰላሳ ሺህ የሚደርሱ ጋዜጣውን የሚያነቡ ጥቁሮች ስለ አድማው አንዲሰሙና እንዲደግፉ አደረጉ ታህሳስ ወይዘሮ ርዛ ፓርከስ ለነጭ ተጓዥ ቦታ ባለመልቀቋ ጥፋተኛ ነች ተብሎ የአሥራ አራት ዶላር ቅጣት ተፈረደባት ይህ ድርጊት የአውቶቡስ ፅቀባውን ተሳታፊዎች ቁጥር ከፍ አንዲል አደረገው ታህሳስ መንገደኞችን አስፈራርተሀል በማለት አንድ ጥቁር የኮሌጅ ተማሪ አሠሩ አሱ ግን አንዲት አዛውንት መንገድ እያሻገረ ነበር። ይሆቻታ ይላግሂዳሌር ሥሯ ቱም እኛ በሃያኛው ከፍለ ዘመን ውስጥ የምንኖር ህዝቦች በሰው ልጅ ታሪከ ውስጥ ወሳኝ ወቅት ላይ በመኖራችን ዕድለኞች ነን ይህ ጊዜ በተስፋ የተሞላ ጊዜ ነው ይህ ጊዜ አዲስ ማህበራዊ ሥርዓት እየተወለደ ያለበት ወቅት ነው እነሆ ዛሬ አየሞተ ባለ አሮጌ ዓለምና እየተወለደ ባለ አዲስ ዓለም መሀል ቆመናል በጣም ከፉ በሆነ ዘመን ውስጥ እየኖርን ነው የሚሉ እንዳሉም አውቃለሁ ኤስያ ውስጥ ያለው እርካታ ማጣት አፍሪካ ውስጥ ያለው ንቅናቄ ግብጽ ውስጥ ያለው የብሔር ጥያቄ ሀንጋሪ ውስጥ የሚሰማው የተኩስ ድምፅ አና አሜሪካ ውስጥ የሜታየው የዘር ልየነት ሥልጣአያችንን ከቦ ያለውን አስፈሪ ጨለማ ያመለከታሎ ይላሉ ወደፊት በመሄድ ፈንታ ወደ ኋላ እየተንፋቀቅን አንደሆነም ይናገራሉ ነገር ግን አሁን ያለው ውጥረት ወደ ኋላ የመመለሳችን ምልከት ሳይሆን ሊወለድ ላለ አዲስ ሥርዓት ምጥ ነው ከብዙ ዓመታት በፊት ግሪካዊው ፈላስፋ ሄራክሊተስ ፍትህ ከተቃራኒዎች ፍትጊያ መሀል ትወጣለች ሲል ተናግሮ ነበር ኸግል ደግሞ በአዲሱ ፍልስፍናው ዕድገት በትግል ይገኛል የሚል ሀሳብ ያቀነቅን ነበር ሳይንስም ታሪከም እንደሚያስረዱት ውልደትና ዕድገት ያለ ከባድ ምጥ ሊኖሩ አይችሉም አዲስ ነገር ሊወለድ ሲል አሮጌው እንቅፋት መሆኑ አይቀርም ስለዚህ ዛሬ በዓለም ላይ የምናየው ውጥረት አዲስ ዓለም እየተወለደና አሮጌው ደግሞ ሥፍራ እየለቀቀ መሆኑን ያመለከታል እየሞተ ያለውን አሮጌ ሥርዓት ሁላችንም እናውቀዋለን ለብዙ ዘመናት በውስጡ ኖረናል በዓለም ላይ በቅኝ አገዛዝና በኢምፔሪያሊዝም መልክ አይተነዋል በዓለማቀፍ ደረጃ በግምት ሁለት ቢሊዮን አራት መቶ ሺህ ሰዎች ይኖራሉ ከነዚህ ውስጥ አንድ ቢሊዮን ስድስት መቶ ሺህ የሚሆኑት ነጭ ያልሆኑ ህዝቦች ናቸው ከሃምሳ ዓመታት በፊት ከነዚህ አንድ ቢሊዮን ስድስት መቶ ሺዎቹ ውስጥ አብዛኞቹ በውጭ ኃይሉች አገዛዝ ቀንበር ሥር ነበሩ ቻይናን ብንመለከት ስድስት መቶ ሚሊዮን ህዝቦቿ በእንግሊዝ በዳችና በፈረንሳይ አገዛዝ ቀንበር ሥር መኖራቸውን አናያሰን ህንድና ፓኪስታን ውስጥ አራት መቶ ሚሊዮን ጠያይም ሰዎች በእንግሊዝ አገዛዝ ሥር ወድቀው ይገኛሉ አይናችንን ወደ ኢንዶኔዥያ ብንመልስ መቶ ሚሊዮን ህዝቦች በዳች ጭቆና ሥር ናቸው ወደ አፍሪካ ብናይ ሁለት መቶ ሚሊዮን ጥቁሮች በእአንግሊዝ በዳችና በፈረንሳይ ቀንበር ተጽዕኖ ሥር ይገኛሉ እነዚህ ህዝቦች ሁሉ ለዘመናት በፖለቲካ ተጨቁነዋል ሀብታቸውን ተዘርፈዋል በዘረኝነት ተገልለዋል ውርደት ደርሶባቸዋል ነገር ግን ህዝቦች ይህን ሁሉ መሸከም የማይችሉበት ቀን ይመጣል በጨቋኞች እግር ሥር መረገጥን የማይታገሱበት ጊዜ ይደርሳል ህዝቦች የተስፋ ጭላንጭል ወደማይታይበት ጭው ያለ የብዝበዛ ገደል መወርወርን በቃን የሚሉበት ቀን ይመጣል ከሞቀ ብርሃን ውስጥ ተወርውረው አጥንት በሚቆረጥም ቀዝቃዛ ጨለማ ውስጥ ሰብቻቸው አንዲቆሙ መገደድን አሻፈረኝ የሚሉበት ጊዜ መምጣቱ የግድ ነውለዚህም ነው ጭቁን ህዝቦች በነዚህ ሁሉ ችግሮች ውስጥ ሆነው ለመብታቸው ለመታገል የወሰኑት ዛሬ አንድ ቢሊዮን ሶስት መቶ ሚሊዮን ባለቀለም ህዝቦች በትግላቸው ነጻ ወጥተዋል ዛሬ የራሳቸው መንግሥት የራሳቸው የኢኮኖሚ ሥርዓት እና ራሱን የቻለ የትምህርት ሥርዓት አላቸው ከግብጽ ቅኝ አገዛዝና ኢምፔሪያሊዝም ተላቀው ያንድ ባህል የበላይነት ወደማይንጸባረቅባት የተስፋዬዩቱ ምድር ለመግባት ራስን የማስተካከል ግራ መጋባት ውስጥ ናቸው ዞር ብለው ሲመለከቱ አሮጌው ቅኝ አገዛዝና የኢምፔሪሊዝም ሥርዓት እየተንኮታኮተ አዲሱ የነጻነትና የፍትህ ሥርዓት ደግሞ እየመጣ መሆኑን እያዩ ነው በአገራችን ውስጥ ይህን እየሞተ ያለ ሥርዓት በዘረኝነትና በመድልኦ መልከም እያየን ነው አሜሪካ ውስጥ የዚህን ሥርዓት ረጅም ታሪከ እናውቃለን የተጀመረው በ የኔግሮ ባሮች እግር የዚህን አገር ምድር የረገጠ ዕለት ነበር አነዚህን ባሮች ያመጧቸው ከአፍሪካ ምድር ነው ከአንድ ዓመት በኋላ በፕላይማውዝ በኩል እንደገቡት የሃይማኖት ተጓዞች ሳይሆን እነዚህኛዎቹ የመጡት ያለ ፍላጎታቸው በግድ ነው ኔግሮ ድፍን የባርነት ዘመኑን ከሰው በታች እንደተቆጠረ ነው የኖረው ኔግሮ አንደ ሰው ከብር የሚሰጠው ፍጡር ሳይሆን እንደ ዕቃ የሚገለገሉበት መሳሪያ ነበር ኔግሮ በአንድ ትልቅ እርሻ ማሳ ውስጥ አንደ አንድ ትንሽ ፅቃ ይቆጠር ነበር የቱ የድሬድ ስኮት ውሳኔ የኔግሮን የባርነት ዘመን ሁኔታ ያመለከታል የዚያ የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ ጭብጥ ኔግሮ የዩናይትድ ስቴትስ ዜጋ ሳይሆን ጌታው እንዳሻው ሊያደርገው የሚችለው ንብረት ነው ይላል ከዚያ በኋላ ተከተሰ በዚህ ዓመት ደግሞ ጠቅላይ ፍቤቱ በፕሌሲ እና ፈርጉሰን መዝገብ ላይ በሰጠው ውሳኔ ጥቁሮችና ነጮች አገልግሎትን አኩል ነገር ግን በተለያየ ሥፍራ ማግኘት ይችላሉ የሚለውን ሃሳብ ያገሪቱ ህግ እንዲሆን አደረገው በዚህ ውሳኔ ምከንያት የዘር ልዩነት የህግና የሞራል ድጋፍ አገኘ ይህ ህግ እኩል ለሚለው መርህ ትኩረት ሳይሰጥ የተለያየ የሚለው ብቻ ሥራ ላይ እንዲውል በር ከፈተ ስለዚህ የፕሌሲ ውሳኔ ትልቅ ልዩነት እንዲፈጠርና የከፋ ብዝበዛ እንዲንሠራፋ ምከንያት ሆነ በንዲህ ዓይነት ሁኔታ ውስጥ መኖር ብዙ ኔግሮች በራስ መተማመንን አንዲያጡ አድርጓቸው ነበር እውነትም እኛ ከሰው በታች እንሆን ይሆን። ብለው ቢጠይቁህ ነገ ተነሳሁ ብለህ ልትመልስ የምትችልበት ወቅት ላይ ነን ስለዚህ ይህች ዓለም በአካል አንድ ሆናለች ብሎ ያስረዳል አሁን የሚጠብቀን ተግዳሮት በመንፈስ አንድ ማድረግ ነው ያለንን ችሎታና ዕውቀት ተጠቅመን የዓለም አገሮችን ጎረቤት ለማድረግ በቅተናል መንፈሳዊና ሞራላዊ ችሎታችንን በመጠቀም ደግሞ ወንድማማችነትን መፍጠር ይጠበቅብናል ሁላችን በአንድ ሰልፍ ውስጥ ገብተናል በአንዱ ላይ ተጽዕኖ የሚፈጥር ነገር በተዘዋዋሪ ሁሉም ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል የሰው ልጆችን አስተሳስሮ ባለው ማህበራዊ ገመድ ውስጥ አኛ ቅንጣት አያያዥ ነን አዲሱ ዘመን ያመጣው ሌላው ተግዳሮት በተሰማራንባቸው ማናቸውም ሙያዎች ላይ ተሸሽሎ ስለመገኘት ነው ከዚህ ቀደም ለኛ ክፍት ያልነበሩ በሮች አብዛኞቹ እየተከፈቱልን መሆናችውን ተገንዝበን ለመግባት ዝግጁ መሆን ያስፈልገናል ራልፍ ዋልዶ ኤመርስን በ በጻፈው ጽሁፍ ውስጥ እንደተናገረው አንድ ሰው ከሌላው የተሻለ ጽሁፍ መጻፍ ከቻለ ወይም ከሌላው የተሻለ መስበከ ከቻለ ወይም ጎረቤቱ ከሠራው የአይጥ ወጥመድ የተሻለ መሥራት ከቻለ ቤቱን አርቆ ዱር ውስጥ ቢሠራ እንኳን መንገዶች ሁሉ ወደሱ ቤት ያመራሉ በአዲሱ ዘመን ከሁሉም አገር ህዝቦችና ዘሮች ጋር ለመወዳደር አንገደዳለን ስለዚህ ዓላማችን ጥሩ ኔግሮ መምህራን ጥሩ ኔግሮ ሀኪሞች ጥሩ ኔግሮ አገልጋዮች ጥሩ ኔግሮ ሠራተኞች ለመሆን ብቻ አይደለም ሥራችንን ከየትኛውም ዘር የተገኘ ሰው አሻሸሎ ሊሠራ አንዳይችል አድርገን አሳምረን መሥራት አለብን ሥራህ ምንም ቢሆን ምን አሳምረህ ሥራው ሥራህ ትልቅ ሥራ ከሚባሉት ውስጥ ባይሆንም እንኳን አሳምረህ ሥራው አንድ የኮሌጅ ፕሬዝዳንት በአንድ ወቅት እንደተናገረው ማንኛውም ሰው ሥራውን ሲሠራ ከዚህ በፊት በህይወት የነበረ አሁን በህይወት ያለ ወይም ወደ ፊት የሚወለድ ሰው አሻሸሎት አንዳይሠራው ግሩም አድርጎ መሥራት አለበት ዕድል የሰጠችህ ሥራ ጎዳና ማጽዳት ቢሆን ሚካኤል አንጀሎ አሳምሮ ስዕል እንደሳለው ሼከስፒር አሳምሮ ግጥም እንደገጠመው ቤቶቨን አሳምሮ ሙዚቃ እንደቀመረው አንተም ጎዳናውን አሳምረህ አጽዳው ስታጸዳው የአዳም ዘር ተሰብስቦ እዚያ ቆሞ ጎዳና የሚያጸዳ አንድ ትልቅ ሰው እዚህ ነበር እንደሱ ያለ ከቶ አይገኝም አንዲል አድርገህ አጽዳው ከፊታቸቹን የተጋረጠው ሌላኛው ፈተና አዲሱን ዘመን በቅን ልቦናና በመልካም መንፈስ መቀበል ነው ይህ ማለት ከርስቲያናዊ ባህሪን ፍቅርንና ይቅር መባባልን የህይወታችን መርህ ማድረግ ማለት ነው እኛ ለብዙ ዘመናት በጭቆና ቀንበር ሥር ስንማቅቅ የነበርን ተረግጠን የተበዘበዝን ፍትህ አጥተን ክብራችንን ተገፈን የኖርን ህዝቦች አዲሱን ዘመን በጥላቻና በምሬት ልንቀበለው አንችላለን ነገር ግን እኛም በጥላቻና በምሬት ምላሽ ከሰጠን አዲሱ ዘመን የአሮጌው ዘመን ግልባጭ ከመሆን ያለፈ ትርጉም አይኖረውም የአሮጌውን ዘመን ጥላቻና ኢ ፍትሀዊነት በአዲሱ ዘመን ፍቅርና እኩልነት መርሳት ይገባናል ለዚህ ነው እኔ በኃይል አልባ ትግል ከልቤ የማምነው ኃይል ፍጹም ችግር አይፈታም ይልቁንም አዲስና የተወሳሰበ ችግር ይፈጥራል ለኃይል ትግል ፈተና እጅ ከሰጠን ወደፊት የሚመጣው ትውልድ ከኛ የሚወርሰው ምሬትን ነው ዘመናችንም የትርጉም የለሸ ሁከት ዘመን ሆኖ ሲታወስ ይኖራል አዲስ ፍቅርን ወደ ሥልጣኔያችን የደም ቧንቧ ማፍሰስ የሚችል መልካም ዕድል ከፊታችን አለ ከትውልድ አስከ ትውልድ የሚሰማ ታላቅ ድምፅ አንዲህ አያለ ይጮሃል ጠላቶቻቸሁን ውደዱ የሚረግሟችሁን መርፋቁ በጥላቻ ለሚጠቀሙባችቸሁ ጸልዩ ለሰማዩ አባታቸሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ሥልጣኔያችንን ከጥፋት ሊታደግ የሚችለው ምናልባት ይህ ፍቅር ብቻ ነው ለዚህ ነው ነጻነትና ፍትህ በፍቅር የሚለውን የዚህ ሳምንት መፈከራችንን የምወደው በኃይል አይደለም በጥላቻ አይደለም በዕቀባም አይደለም በፍቅር እንጂ በርግጥ አሜሪካ ውስጥ ለነጻነት ስንታገል አልፎ አልፎ ዕቀባን መጠቀም ይኖርብናል ይሁን እንጂ ዕቀባ በራሱ ግብ እንዳልሆነ መረዳት አለብን ዕቀባ ጨቋኞች በራሳቸው ድርጊት እንዲያፍሩ የማድረጊያና የበላይነታቸውን የመቃወሚያ ስልት ነው ግቡ ግን እርቅ ከከፋት መመለስና ተወዳጅ ህብረተሰብ መፍጠር ነው እንዲህ ዓይነት መንፈስና አንዲህ ዓይነት ፍቅር ነው ጠላትን ወዳጅ የሚያደርገው እንዲህ ዓይነት ቅን ግንዛቤ ነው የትናንትናውን ሀዘን በነገው ደስታ የሚቀይረው ይህ ፍቅር ነው በሰው ልብ ውስጥ ተዓምራትን የሚፈጥረው ስለ ፍቅር ደጋግመን ስናወራ ስሜት ውስጥ እንደምንገባ አውቃለሁ የፍቅር ንግግራችን ተጨባጭ ሊሆን ስለማይችለውና እውነተኛ ስላልሆነ አዲስ ፍቅር እንዳልሆነ ተስፋ አደርጋለሁ የተቃወሟችሁን ውደዱ። ግፉ ቢበረታም ጭቆና ቢያይልም የህልው ምስጢሩ ዋና መዘውሩ በጽልመት ጥላ ሥር ቆሟል አግዚአብሔር እዚህ ሞንትጎመሪ ውስጥ አውቶቡስ ከመሳፈር ታቅበን አሥራ አንድ ወራት በእግራችን ስንኳትን ድካም አልተሰማንም ምከንያቱም በተስፋዩቱ አገራችን በነጻነትና ፍትህ ግቢ ውስጥ እንደምንገናኝ እናውቅ ስለነበር ነው ንግግሬን ከማጠቃለሌ በፊት ሊፈጸም የሚችልን አንድ ስህተት ከወዲሁ ለማስተካከል አፈልጋለሁ ንግግሬን እዚሁ ላይ ከቋጨሁ ምናልባት መልዕከቴን በተሳሳተ መንገድ ተረድታችሁ ትሄዱ ይሆናል በፍጥነት ወደኛ አየገሰገሰ ስላለው አዲስ ዘመን ተናግሬያለሁ አግዚአብሔር አዲስ ነገርን እያመጣ ስለመሆኑም ገልጫለሁ ይህን ከሰማን በኋላ ወደ ቤታችን ተመልሰን አጃችንን አጣጥፈን ቁጭ ብለን የሚመጣውን የምንጠብቅ ከሆነ ይህ ስህተት ነው ሊመጣ ያለው አይቀርም ብሎ መቀመጥ አደጋ አለው ሊመጣ ያለውን ማፋጠን ይጠበቅብናል አሮጌው የዘር መድልኦ ሥርዓት የአልጋ ቁራኛ ሆኗል ማህበራዊ መዋቅሩና የሥርዓቱ ተጠቃሚዎች ግን አንዳይሞት የተቻላቸውን ሁሉ እያደረጉ ነው አሜሪካ ውስጥ ዛሬም መድልኦ አለ ደቡብ ውስጥ አሁንም እንደተጠናከረና እንዳማረበት ከፊታችን ተገትሯል በሰሜን ደግሞ አድብቶ የሌለ መስሎ ተኝቷል ሆኖም ዲሞከራሲ እንዲኖር ከፈለግን መድልኦ መሞት ይኖርበታል መድልኦ የሰውን ልጅ ወደ ዕቃነት ደረጃ ዝቅ ያደርጋል መድልኦ በልዩ ልዩ ድርጊቶች ተሸፍኖ የተደበቀ ባርነት ነው መድልኦ በኢየሱስ ከርስቶስ ያለንን አንድነት ያፈርሳል ስለዚህ በመምጣት ላይ ያለውን አይቀሬ ጉዳይ ለማፋጠን ትግላችንን መቀጠል ይኖርብናል የመምረጥ መብት ለመጎናጸፍ ትግሱን መቀጠል ይገባናል ለችግሮቻችን መፍቻ አንዱ ወሳኝ ቁልፍ የመምረጥ መብት ነው በመምረጥ መብታችን ተጠቅመን የፖለቲካ ሥልጣን ካላገኘን በስተቀር የፖለቲካ ሰዎች መጠቀሚያ ሆነን እንቀራለን በዲሞክራቶች ፓርቲና በሪፓብሊካኖቹ ፓርቲ መዘንጋታችንን በጸጋ መቀበል የለብንም ዲሞከራቶች በደቡቦች አመለካከት ተሸንፈው ሪፓብሊካኖችም በሰሜኖች ትምክተኛና አደናቃፊ ቀኝ መንገደኞች ሃሳብ ተውጠው ከድተውናል የደቡብ ዲሞክራቶችና የሰሜን ሪፓብሊካኖች በምክር ቤት ውስጥ ተባብረው የሲቪል መብት ህጎችን ውድቅ ሲያደርጉ ቆይተዋል ተወካዮቻቸንን መርጠን በመንግሥት መቤቶች ውስጥ ማስገባት አስከንችል ድረስ ይህ ሁኔታ ባለበት ይቀጥላል በመምረጥ መብታችን ተጠቅመን ዕውን ማድረግ ባልቻልንባቸው ቦታዎች ደግሞ ህግና ሞራልን በመጠቀም ችግሩን ከሥሩ መንቀል አለብን ትግላችንን በህግና በህጋዊ አግባብ ብቻ ልንቀጥል ይገባል የዘር መድልኦ ሊጠፋ የሚቸለው በትምህርት ብቻ ነው ምከንያቱም ሞራል በህግ ሊደነገግ አይችልም የሚሉ ወገኖች አሉና እኔም እዚህ ላይ ዲያሌከቲካዊ መሆን አፈልጋለሁራ መድልኦ በትምህርት አይጠፋም በህግም አይወገድም በትምህርትና በህግ እንጂ የሰውን ውስጣዊ ማንነት በህግ ብቻ መለወጥ አይቻልም የሚለውን አስተሳሰብ እኔም አጋራለሁ ግን የህግ ዓላማ ይሄ አይደለም የህግ ዓላማ የሰውን ውስጣዊ ስሜት መቀየር ሳይሆን የሰው ውስጣዊ ስሜት በሰው ላይ የሚያደርሰውን ተጽዕኖ መቆጣጠር ነው ለምሳሌ ህግ አንዱ ሰው ሌላውን አንዲወድ ማድረግ አይቸልም ይህን ማድረግ የሚችሉት ሃይማኖትና ትምህርት ናቸው ነገር ግን ሰው ሰውን ለመግደል የሚያደርገውን ሙከራ ሊቆጣጠር ይችላል ስለዚህ በውስጣችን ካለ ጥላቻ የሚመነጭ ግልጽ ተጽዕኖን ለመቆጣጠር በህግ ተመርኩዘን ልንታገል ይገባል ሌላው ውህደትን ለማፋጠን ልናደርግ የምንችለው ነገር ያለንን ገንዘብ ነጻነታችንን ሊያጎናጽፈን በሚቸል ነገር ላይ ብቻ ማጥፋት ነው ነጻነት ምን ጊዜም ቢሆን ትልቅ ዋጋ የሚያስከፍል ነገር ነው ራስን ሳይከዱና መስዋዕትነት ሳይከፍሉ የሚገኝ ነጻነት አንደሌለ ታሪከ ምስከራችን ነው ስለዚህ ስለ ነጻነት ብዙ ገንዘብ ማፍሰስ ይኖርብናል ካሁን በኋላ ገንዘብ የለኝም የሚለው ማመካኛ ተቀባይነት የለውም የኔግሮዎች ኢኮኖሚ አያደገ መሆኑን መረጃዎች ያመለከታሉ የአሜሪካ ኔግሮዎች ዓመታዊ ገቢ ከአስራ ስድስት ቢሊዮን ዶላር በላይ ደርሷል ይህ ገቢ ከካናዳ ዓመታዊ ገቢ ጋር ተቀራራቢ ነው ቀስ በቀስ በኢኮኖሚ ራሳችንን እየቻልን መሆኑን ከዚህ አንረዳለን በዚህ በሃያኛው ከፍለ ዘመን ኔግሮዎች ለነጻነታቸው በሚጠቅም ነገር ላይ ሳይሆን በመዝናኛ ላይ ገንዘባቸውን ያፈሱ ነበር ብሎ ታሪከ አንድ ቀን ከመሰከረብን በከብራችንና በነጻነታችን ላይ ትልቅ ስህተት ፈጸምን ማለት ነው ዘላለማዊ የሆነውን ነጻነትና ፍትህ ወደ ጎን ትተው አላፊ ጠፊ በሆነው ነገር ላይ ሃብታቸውን ያባከኑ ነበር ልንባል አይገባም መጪውን አዲስ ዘመን ስኬታማ ለማድረግ ከሚጠበቁብን ነገሮች ሌላው ለትግሉ የተሰጠና ጠንካራ አመራር መፍጠር ነው ይህ አሁኑኑ ያስፈልገናል በዚህ የሸግግር ወቅት መፍትሄው ኃይል ነው የሚሉ በአንድ ጫፍ የሚገኙ ያበዱ ጥቁሮችንና ነጮችን ብቻ ለማስደሰት ደፋ ቀና የሚሉ በሌላ ጫፍ ያሉ አድርባይ ጥቁሮችን አንድ ላይ በማምጣት መምራት የሚችሉ የተረጋጉ መሪዎች ያስፈልጉናል አስተዋይ ታማኝ ከገንዘብ ይልቅ የፍትህ ፍቅር ያላቸው የቆሙለትን ዓላማ ከግል ጥቅማቸው የሚያስቀድሙ መሪዎች ያስፈልጉናል ይህን አስመልከቶ ሆላንድ አንዲህ ይላል አባከህ ፈጣሪ መሪዎችን ስጠን በዚህ ወቅት ለኛ ስለሚያስፈልጉን ታላቅ አዕምሮና ማስተዋል ያላቸው ከብርና ዝና ሃብት የማይጥላቸው የከፉዎች ዛቻ የማይበግራቸው ህዝብን የማይዋሹ ከፉ የሚጠየፉ የህይወትን ፈተና በተግባር ያለፉ በመልካም ሥራቸው በያደባባዩ እንዳላማ ሰንደቅ ከሩቅ የሚታዩ በመጨረሻም እየመጣ ያለው አዲስ ዘመን እንዲፋጠን ሁላችንም በህብረት ተነስተን ፍትህ በተጓደለበት ቦታ ሁሉ ትግላችንን ማፋፋም አለብን መድልኦ ባለበት ሥፍራ ሁሉ ተቃውሞአችንን ማሰማት አለብን ይህን ማድረግ ችግርን መቀበልና መስዋዕትነትን አንደሚጠይቅ አውቃለሁ ሊያሳስርም ይችላል ይህም ከሆነ በደቡብ የሚገኙ አሥር ቤቶችን ለመሙላት መዘጋጀት ይገባናል ሞትም ሊኖር ይችላል ነገር ግን አንድ ሰው በአካል ሞቶ ልጆቹን ከቋሚ የስነ ልቦና ሞት ማዳን ከቻለ ከዚያ የበለጠ ክብር የለም ለፍትህ ሲሉ የተሰዉ ሰማዕታት ደማቸው ለነጻነት እንደተዘራ ዘር ይቆጠራል ለፍትህ ስንታገል የሚሰነዘርብንን ጥቃት እና የሚነሳብንን ሁከት አንዴት አድርገን መቋቋም አንቸላለን። » ምድ ዲደፖሥ ያሃህዕሃው ግፍ ውዕፖ ዳዩኦጎው ያጋ ዎ ዳፅታፖ ም ቐያፇ ኖሮ አነሐ ጫፍ ደም ፅሩ ፅጎሜኦገው ያቃጋጠሰቋው ማሀራዊ ዝምም «ፊያ ደረጀ ቂፅ ድረ ማዖ ባሲሷፖ አገር ከመጀመሪያው ጀምሮ የሞንትጎመሪው አውቶቡስ ዕቀባ የተመሠረተበት ፍልስፍና ነበረው የኃይል አልባ ትግል ፍልስፍና ሆኖም ግን ጅማሮው ላይ በብዙ ሰዎች ዘንድ ተቀባይነት ባለማግኘቱ በተፈለገው መጠን ሥራ ላይ ለማዋል አስቸጋሪ ነበር ስለዚህ ፍልስፍናውን ለማያውቁ ሰዎች ለማስተዋወቅ ህዝባዊ ስብሰባዎችን መጠቀም ነበረብን በሳምንት ሁለት ቀን ሰኞና ሀሙስ ስብሰባ ነበረንገ የኃይል አልባ ትግልና ማህበራዊ ለውጥ ኢንስቲትዩትም አቋቁመን ነበር ኃይል አልባ ትግል የፈሪዎች ስልት እንዳልሆነ ማስረዳት ነበረብን ኃይል አልባ ትግል በርግጥ አምቢተኝነት ነው ነገር ግን ፈዛዛ ባለበት የሚረግጥና ባለው ረክቶ የሚቀመጥ አይደለም ሰላማዊ ታጋይ እንደ ማንኛውም ታጋይ ባላንጣውን ይታገላል ግን በኃይል አይደለም ይህ ስልት በአካል ጉልበት አልባ ሲሆን በመንፈስ ግን ጉልበታም ነው ለማዋረድ ሳይሆን ድል ለማግኘት ሌላ ግልጽ ማድረግ የምንፈልገው ጉዳይ ሰላማዊ ታጋይ ተቃዋሚውን ማስተማርና መወዳጀት አንጂ ማንበርከከ ወይም ማዋረድ ዓላማው አንዳልሆነ ነው ዓላማችን ነጮችን ድል ማድረግ ወይም ማዋረድ ሳይሆን ያለፈን ሥርዓት ሲያገለግሉ የነበሩ ሰዎችን ወዳጅነት ማግኘት እንደሆነ ደጋግመን ስንናገር ቆይተናል የኃይል ትግል መደምደሚያ ምሬት ነው የኃይል አልባ ትግል መጨረሻው ግን እርቅና ተወዳጅ ህብረተሰብ መፍጠር ነው ፅቀባ ለራሱ ግብ አይደለም ጨቋኞች በድርጊታቸው እንዲያፍሩና እንዲጸጸቱ የማድረጊያ ስልት ነው ግቡ ግን አርቅ ማውረድና ይቅር መባባል ነው ከዚያ በኋላ የሰላማዊ ታጋዮች ጦርነት ከክፉው ሥርዓት ጋር ነው እንጂ በዚህ ሥርዓት ውስጥ ካሉ ሰዎቸ ጋር እንዳልሆነ ግልጽ ማድረግ ነበረብኝ ለዚህ ነው ደጋግሜ ደቡብ ውስጥ የሚካሄደው ትግል በነጭና በጥቁሩ ማህበረሰብ መካከል ያለ ውጥረት አይደለም የምለው በፍትህና በኢፍትሀዊነት በብርሃን ኃይሎች እና በጨለማ ኃይሎች መካከል የሚደረግ ነው ድልም ቢገኝ የሃምሳ ሺህ ኔግሮዎች ድል ብቻ አይደለም የፍትህ ድል የአኩልነትና የዲሞክራሲ ድል እንጄ ሌላው ልናስተላልፍ የምንፈልገው መልዕከት ኃይል አልባ ትግል የውስጥ ጉዳይም ጭምር መሆኑን ነው የሚታገለው ከውጭ ከሚሰነዝርበት አካላዊ ጥቃት ጋር ብቻ ሳይሆን ከውስጥ ከመንፈሳችን ከሚነሳብን ሁከትም ጋር ነው ስለዚህ የእንቅስቃሴያችን እምብርት የፍቅር ፍልስፍና ነው ሰብዓዊነትን ለመለወጥና ያን የምንመኘውን ህብረተሰብ ለመፍጠር ብቸኛው መንገድ ፍቅርን የህይወታችን አምድ በማድረግ ነው ብለን አናምናለን ከመጀመሪያው አንስቶ ሰዎች ፍቅር ማለት ምን ማለት ነውን የሚቃወሙንንና ሊያጠፉን የሚፈልጉትን ውደዱ እንዴት ትለናለህ አንዴትስ ልንወዳቸው ይቻለናል። ውብ የሆነን ነገር መውደድ የሚቃወሙንን ሰዎች ስለ መውደድ ስናወራ ስለ አሮስ ማውራታችን አንዳልሆነ ይታወቃል የግሪክ ቋንቋ በሰዎች መካከል ስላለ ግላዊ ፍቅር ለመግለጽ ፊሊያ የሚል ቃል አለው ይህ መልካምና ዋጋ ያለው ፍቅር ነው ይሁን እንጂ የሚቃወሙንን ስለ መውደድ ስንናገር አሁንም ስለ አሮስ ወይም ስለ ፊሊያ እያወራን አይደለም የግሪከ ቋንቋ ለዚህ አጋፔ የሚል ቃል አለው አጋፔ ሰውን ሁሉ መረዳትን ይቅር ማለትን መልካም መመኘትን ያካትታል የመጽሐፍ ቅዱስ ተመራማሪዎች አጋፔን በሰው አዕምሮ ውስጥ እየሠራ ያለ የእግዚአብሔር ፍቅር ነው ይሉታል ከማንም ምላሽ የማይሻ ሞልቶ የሚፈስ ፍቅር ነው ይላሉ ወደዚህ የፍቅር ደረጃ ከፍ ስንል ሰዎችን የምንወዳቸው ተወዳጆች ሆነው ወይም መልካምነት ኖሯቸው ሳይሆን እግዚአብሔር ስለሚወዳቸው ነው ስለዚህ ሰውን ወደን ከፉ ተግባሩን ብቻ እንጠላለን ማለት ነው በደቡብ ልናካሂድ የምንፈልገው እንቅስቃሴ በእንዲህ ዓይነት የአጋፔ ፍቅር ላይ የተመሠረተ ነው ዩኒቨርስ ውስጥ ለፍትህ የቆመ ኃይል ከኃይል አልባ ትግል አራማጆች ውስጥ በእግዚአብሔር የማያምኑ እንዳሉ አውቃለሁ ነገር ግን በኃይል አልባ ትግል የሚያምኑ ሁሉ በዩኒቨርስ ውስጥ ትግላቸውን በሆነ መልከ የሚደግፉ አንዳሉ ያምናሉ አንድ የማይታወቅ ኃይል ይበሉት ወይም ራሱ የማይንቀሳቀስ ግን ሁሉን የሚያንቀሳቅስ ኃይል ይበሱት ወይም አግዚአብሔር ይበሱት ብቻ ፍትህን የሚያግዝ ኃይል አለ ሞንትጎመሪ ውስጥ ትግላችንን ስናካሂድ የሚረዳን ኃይል መኖሩ ይሰማን ነበር በዓለም ላይ ያሉ ወንድና ሴት ታጋዮች ከከፉ ሥርዓቶች ጋር ሲታገሉ ፍቅርን በልባቸው ውስጥ ይዘው እንዲታገሱ እግዚአብሔር ይረዳቸዋል ራስን በመግዛት ወይም ራስን በመቆጣጠርና በርጋታ ወደፊት እንድንገፋ አጋፔ ያስገድደናል አሜሪካ ውስጥ ሰው ሁሉ በወንድማማትነትና በሰብዓዊ ከብር የሚኖርባት ታላቅ አገር ለመፍጠር ትልቅ ዕድል አለን ወደዚህ ግብ መጓዝ አለብን አንዳንድ ሰዎች ቀስ ብለን እንድንራመድ አንደሚፈልጉ አውቃለሁ መልካም አመለካከት ወዳላቸው ነጮች ወደ ሰሜኖቹና ኔግሮች ደብዳቤ በመጻፍ እየፈጠናችሁ ነውና ረጋ በሉ በማለት ይመከሯቸዋል አኛንም ለዘብተኛ ፖሊሲ እንድንከተል ይነግሩናል ለዘብተኝነት ማለት በማስተዋል የተሞላ ራስን መግዛትና ምከንያታዊ እርጋታ ከሆነ ይሄ መልካም አስተሳሰብ ያላቸው ሰዎች ሁሉ በውጥረት በተሞላ የሸግግር ወቅት አንዲኖራቸው የሚፈልጉት ሊሆን ይገባል ነገር ግን ለዘብተኝነት ማለት ለፍትህ የሚደረግ ትግልን ማቀዝቀዝ እንዲሁም አሁን ያለው ሁኔታ እንዲቀጥል ለሥርዓቱ ጠባቂዎች እጅ መስጠት ከሆነ ቅን የሚያስብ ሰው ሁሉ ሊያወግዘው የሚገባው መጥፎና አስነዋሪ ጠባይ ነው ስለዚህ ወደፊት መራመድ ይጠበቅብናል ለራሳችን የምንሰጠው ከብር ጥያቄ ውስጥ ነው ከኮሚኒዝም ጋር የምናደርገው የርዕዮተ ዓለም ትግል የሲቪል መብት ጉዳይ የሥልጣኔያችንን የወደፊት ዕጣ ፈንታ ይወስናል ስለዚህ ማስተዋል ላይ በተመረኮዘ ቁጥብነት በፍቅር በመልካም ስነ ምግባር እና በተከበረ አካሄድ ትግላችንን ልንቀጥል ይገባል ከከፋት ጋር አለመላመድ የዘመኑ ሳይኮሎጂ ከሁሉም ቃላት ይበልጥ አብዝቶ ከሚጠቀምባቸው ቃላት ውስጥ መላመድ የሚለው አንዱ ሳይሆን አይቀርም ጭንቀትና ውጥረት ከሰፈነበት ኑሮ ነጻ ለመሆን ሁላችንም ከምንኖርበት አካባቢ ጋር መላመድ ያስፈልገናል ከማህበራዊ የአኗኗር ሥርዓታችን ውስጥ ልላመዳቸው የማልፈልጋቸውና ሴሎችም እንዳይላመዷቸው የምመክራቸው ጉዳዮች ግን አሉ እኔ ዘረኝነትን መላመድ አልፈልግም ከኃይል አገዛዝ ጋርም ልላመድ አልሻም በአካላዊ ኃይልና በመሳሪያ የበላይነት አስገድዶ ሌላውን ከመግዛት ጋር ፈጽሞ ለመላመድ አልፈቅድም እናንተም እነዚህን ከመሳሰሉ ነገሮች ጋር አንዳትላመዱ ጥሪ አደርግላችኋለሁ አሞጽ በዘመኑ በነበረው ኢፍትሀዊነት መሀል ሆኖ ፍትህ አንደ ወንዝ ጽድቅም እንደማይደርቅ ምንጭ ይፍሰስ። መጭው ትውልድ ቢሞከር እንኳን ጋንዲን ሊረሳው አይችልም በማናቸውም መመዘኛ ጋንዲ ከዓለማችን ጥቂት ታላላቅ ሰዎች ውስጥ አንዱ ነው የጋንዲ ተከታዮች አጃቸውን ዘርግተው ስለተቀበሉን ደስ ብሎኛል በሞንትጎመሪ ያካሄድነውን ኃይል አልባ ትግል አድንቀዋል ይህ ስልት በሰለጠነው ደቡብ ውስጥም ተግባራዊ ሊሆን አንደሚችል የተቀበሉ ይመስላሉ ኃይል አልባ የትግል ስልት በጥንቃቄ ከታቀደ በፈላጭ ቆራጭ ሥርዓት ውስጥም ቢሆን ሥራ ላይ ሊውል እንደሚችል ተረድተዋል በዚህ ጉዳይ ላይ ህንድ ውስጥ በመማር ላይ ካሉ አፍሪካውያን ተማሪዎች ጋር በስፋት ተወያይተንበታል እነዚህ ተማሪዎች ኃይል አልባ ትግል ሥራ ላይ ሲውል የሚቸለው ከምንታገላቸው ሰዎች መሀል ይህን ትግል የሚደግፉ ከተገኙ ብቻ ነው ብለው ያስባሉ እነዚህ ተማሪዎች ልክ እንደ ሌሎቹ ሁሉ የዝምታ ትግልን ካለመታገል ለይተው እንደማያዩት ወዲያው ገባን ይህ ስህተት ነው ኃይል አልባ ትግል ማራመድ ለጭቆና አጅ መስጠት ወይም ለክፋት መንበርከክ አይደለም ይልቁንም በፍቅር ኃይል ታግዞ በጀግንነት መጋፈጥ ነው ሰው ላይ ጉዳት ከማድረስ ጉዳትን መቀበል ይሻላል ምከንያቱም ኃይልን መጠቀም የኃይል አጸፋን ይጋብዛል ኃይል አልባ ትግል ግን ኃይልን የተጠቀመው አካል በድርጊቱ አፍሮና ተጸጽቶ ሃሳቡን እንዲቀይር ያደርጋል ኃይል አልባ ትግል ፍቅር ላይ የተመሠረተ ነው ግለሰባዊ ፍቅር ማለት ግን አይደለም አደጋ ሳያደርሱ አደጋን በመቀበል በጋራ እርምጃ የተጣመመውን ማቃናትና የተሳሳተውን ማረም የሚያስችል ፍቅር ነው ለነጻነታቸው የሚታገሉ ጭቁን ህዝቦች ለምን ጉልበት አንደሚጠቀሙ መገንዘብ በአፍሪካ ውስጥ ለሰብዓዊ ከብርና ለነጻነት እየተደረገ ያለው ትግል ጋንዲ በዚህ ከፍለ አህጉር ባስተዋወቀው መንገድ ቢከናወን የበለጠ ውጤታማ መሆኑን ያሳያል ህንድ ብዙ ችግር ያለባት ሰፊ አገር ነች ወደ ደቡብ ወደ ምሥራቅና ምዕራብ ያገሪቱ ከፍሎች በረራ አድርገናል አጫጭር መንገዶችን በባቡር ሌሎች ቦታዎችን ደግሞ በመኪና በመጠቀም አዳርሰናታል። ው ቸፍ ኸማ ጅጋ ር ቸዬን ከአሥር ዓመታት በፊት ገና የመጨረሻ ዓመት ትምህርቴን መጀመሬ ነበር ያኔ ልከ አንደ ማንኛውም የመንፈሳዊ ትምሀርት ተማሪ ልዩ ልዩ መንፈሳዊ ንድፈ ሀሳቦችን በማጥናት ተጠምጄ ነበር ወግ አጥባቂ ባህል ውስጥ በማደጌ የተነሳ ትምህርቴ ውስጥ ለየት ስላሉ አና አንዳንዴም ውስብስብ ስለሆኑ አስተምህሮዎች ሳነብ ድንጋጤ ይወረኝ ነበር ይሁን እንጂ ይህ አካሄድ ሁል ጊዜ አዲስ ነገርን ለማወቅ አንድነሳሳ አና በጥልቀት ተንትፔ ለመመዘን እንድችል ረድቶኛል የሂውምን ጽሁፎች ማንበብ ካንትን እንደረዳው ሁሉ እኔንም ቀደም ሲል የወሰድኩት መንፈሳዊ ሥልጠና አግዞኛል ውስጤ የነበረውን ወግ አጥባቂነት ነቅሎ ጥሎታል በዚህ ደረጃ ጠንካራ ሊብራል ነበርኩ ከሊብራሊዝም የቀሰምኩት ዕውቀት ከፋንዳሜንታሊዝም ከገበየሁት ይበልጥ አስደስቶኝ ነበር ከዚህ ፍልስፍና ፍቅር የተነሳ በሱ ስም የሚመጣ ማናቸውንም ነገር ያለ አንዳች ጥያቄ ወደ መቀበል ወጥመድ ውስጥ አስከመግባት ደርሼ ነበር በተፈጥሮ ሰው መልካም መሆኑንና የሰው ልጅ ነገሮችን ለመገንዘብ ያለው ችሎታ ትልቅ መሆኑን ያለምንም ጥርጥር ተቀበልኩ በአመለካከቴ ላይ መሠረታዊ ለውጥ መምጣት የጀመረው ከሊብራል ቲዮሎጂ ጋር ተዛማጅ በሆኑ አንዳንድ ንድፈ ሃሳቦች ላይ ጥያቄ ማንሳት ስጀምር ነበር ከሊብራሊዝም ሁሌም የምቀበላቸው መልካም ነገሮች አሉ አውነትን አጥብቆ መሻቱ ከፍት የሆነ አዕምሮ መውደዱ እና አሳማኝ የሆነን ምከንያት ችላ ብሎ ያለማለፉ በመጽሐፍ ቅዱስ ፍልስፍናና አጻጻፍ ታሪከ ሂስ ውስጥ የሊብራሊዝም አስተዋጽኦ ከፍተኛ አንደመሆኑ መጠን በሃይማኖታዊ መንፈስና በአዎንታ ሊታይ ይገባዋል ይልቅ ጥያቄ የሆነብኝ ሊብራሊዝም ስለ ሰው የሚከተለው አስተምህሮ ነበር ያለፉትን ዘመናት አሳዛኝ የሰው ልጅ ታሪከ ዞር ብዬ ስመለከት እና የሰው ልጅ በከፉ መንገድ መጓዝን ያለምንም ሃፍረት ለመምረጥ ያለውን ፍላጎት ሳይ የሃጢአት ጥልቀትና ግዝፈት ምን ያህል አንደሆነ እረዳለሁ የሬናልድ ነቡርን መጻህፍት ማንበቤ የሰው ፍላጎት ምን ያህል ውስብስብ አንደሆነና በሰው ኑሮ ማንኛውም ደረጃ ውስጥ ሃጢአት አንዳለ አስገንዝቦኛል በተጨማሪም በማህበራዊ አኗኗር ውስጥ የሰው ተሳትፎ ውስብስብ እንደሆነና ሰዎች በጋራ ሆነው ከፉ መሥራታቸው የታወቀ መሆኑን አንድቀበል አድርጎኛል ሊብራሊዝም በሰው አፈጣጠር ላይ ያለው አመለካከት በስሜት ላይ የተመሠረተና ወደ ሐሰተኛ አይዲያሊዝም ያዘነበለ ሆኖ ተሰማኝ ሊብራሊዝም የሚያምንበት የሰው በጎነት ተስፋ ጥልቀት የሌለው በመሆኑ የሰው ሃጢአት ምከንያታዊነትን ድርጊቱን ለመደበቅ አዕምሮውን ምን ያህል እንደሚጠቀምበት ለማስተዋል ችያለሁ ሊብራሊዝም ያልተገነዘበው አንድ ነገር ቢኖር ምከንያት ራሱ የመከላከያ ሃሳብን ዕውን ከማድረጊያ መሳሪያነት የዘለለ አለመሆኑን ነው በሃይማኖት ታሸቶ ያልነጻ ምክንያት እውነትን ከማጣመምና የራስ ስህተትን ከመደበቅ ነጻ ሊሆን አይችልም ከሊብራሊዝም አስተሳሰቦች አንዳንዶቹን ባልቀበላቸውም ሙሉ በሙሉ ኒዮ ኦርቶዶክስን ወደ መቀበልም አልመጣሁም የኒዮ ኦርቶዶከስ ፍልስፍና የሊብራሊዝምን ጉድለቶች የሚሞላ መሆኑን ባምንም ለሁሉም መሠረታዊ ጥያቄዎች በቂ መልስ ይሰጣል ብዬ ግን አላምንም የሰውን አፈጣጠር አስመልክቶ ሊብራሊዝም በመልካምነቱ ላይ ከፍተኛ ተስፋ ያለው ሲሆን ኒዮ ኦርቶዶክስ ግን ስለ ሰው ያለው አመለካከት ጨለምተኛ ነው በሰው ልጅ ጉዳይ ላይ ብቻ ሳይሆን በሌሎች ወሳኝ ጉዳዮች ላይም ኒዮ ኦርቶዶክስ በወግ አጥባቂነት ከሩቅ ቆሞ ይገኛል ኒዮ ኦርቶዶክስ አግዚአብሔር ከሁሉ የበላይና ድንበር የማይገድበው መሆኑን ለመግለጽ እግዚአብሔር ድብቅ የማይታወቅና ሙሉ ለሙሉ ልዩ ነው አስከ ማለት ሲደርስ ሊብራሊዝም ደግሞ አግዚአብሔር በውስጣችን መኖሩን ያምናልራ ሊብራሎች የሚያምኑበትንና የሚያሞካሹትን ምከንያታዊነት ለመቃወም ሲሉ ኒዮ ኦርቶዶከሳውያን በምከንያት ባለማመን ወይም በኢምከንያታዊነት እና በወግ አጥባቂነት ውስጥ ተዘፍቀው ጠባብና የማይመረመር መለኮታዊ አስተምህሮዎች ይሰብካሉ እንዲህ ዓይነት ትምህርት ለቤተከርስቲያንም ለግል ህይወትም በቂ ሆኖ አይታየኝም ስለሰው ልጅ ለሚነሳ ጥያቄ ከሊብራሊዝም በቂ መልስ ባላገኝም ኒዮ ኦርቶዶክስም አላረካኝም ስለዚህ ስለ ሰው ያለው እውነታ በሁለቱም አስተሳሰቦች ውስጥ እንደማይገኝ ተረዳሁ ሁለቱም ግማሽ አውነታን ብቻ ይወከላሉና የፕሮቴስታንት ሊብራሊዝም በአብዛኛው ሰውን ከበጎ ጎኑ ብቻ ይገልጸዋል ኒዮ ኦርቶዶከስ ደግሞ የሰውን ልጅ ከመጥፎ ጎኑ ብቻ ያየዋል ስለ ሰው በቂ ዕውቀት የሚገኘው ምከንያታዊ ከሆነ የሊብራሊዝም ከርከር ውስጥ ወይም ከምክንያት አልባው የኒዮ ኦርቶዶክስ አስተሳሰብ ውስጥ ሳይሆን በሁለቱም ውስጥ የሚገኝ አውነታን አንድ ላይ አምጥቶ በማስታረቅ ነው ባለፉት አሥር ዓመታት ውስጥ ለሰው ልጅ ግለሰባዊ ባህሪይ ትኩረት የሚሰጠውን የኤግዚስቴንሻሲዝም ፍልስፍናም እስከ መውደድ ደርሼ ነበር ከዚህ ፍልስፍና ጋር መጀመሪያ መተዋወቅ የቻልኩት የኬርከጋርድና የኒቼ መጻህፍትን በማንበብ ነበር በኋላ ወደ ጃሰፐርስ ሄድነገርና ሳትሬ ምርምሮች ዞርኩ እነዚህ ሥራዎች አመለካከቴን በእጅጉ ሞርደውታል በያንዳንዳቸው ላይ ጥያቄዎች ቢኖሩኝም ብዙ ተምሬባቸዋለሁ በመጨረሻም የፖልቲሊችን ሥራዎች በጥንቃቄ ወደ ማጥናት ስመለስ ኤግዚስቴንሻሊዝም ዘመናዊ አመለካከት ቢሆንም ስለ ሰው ሊታለፍ የማይችል መሠረታዊ አውነት ያዘለ መሆኑን አመንኩ ከኤግዚስቴንሻሊዝም አበርክቶዎች ውስጥ ዋንኛው የሰው ልጅ ነጻነት የተገደበ መሆኑን ማመኑ ነው በግል ህይወት እና ማህበራዊ ኑሮ የሚንጸባረቁ ግጭቶችና አለመረጋጋቶች ስለ ወደፊት ህይወታችን አርግጠኛ ካለመሆን ወይም ከአደገኛ ጥርጣሬ የሚመነጩ ናቸው የሚለው አስተሳሰብ በዚህ ዘመን ትርጉም አለው የሚያምኑበት ነገር ያላቸውንም በምንም ነገር የማያምኑትንም እኩል አንድ የሚያደርገው የኤግዚስቴንሻሊዝም ነጥብ የሰው አኗኗር ሁኔታ ከአፈጣጠሩ የተለየ መሆኑን ማመኑ ነው በሄግል ኢሰንሻቫሊዝም ላይ በሚያነሱት ተቃውሞ ኤግዚስቴንሻሊስቶች በሙሉ ዓለም የተከፋፈለች ናት ብለው ይከራከራሉሱ ታሪክ ያልታረቁ ቅራኔዎች ቅደም ተከተል ነው የሰው ህይወት ደግሞ መጪውን ጊዜ በመፍራት በስጋት ትርጉም አልባ ሆኗል የክርስቲያን የመጨረሻው መልስ በኤግዚስቴንሻሊዝም ውስጥ የማይገኝ ሲሆን የሰው ልጅን እውነተኛ ማንነት የሚያጠና የስነ መለኮት ተመራማሪ ግን አያሌ ነገሮችን ያገኝበታል በነዚህ አሥር ዓመታት ውስጥ መደበኛ ጥናቴ የሚያተኩረው በሲስተማቲክ ቲዮሎጂ እና ፍልስፍና ላይ ቢሆንም በየቀኑ ፍላጎቴ ወደ ማህበራዊ ስነ ምግባር እየተሳበ ነበር ስለ ማህበራዊ ችግሮች ያለኝ ተቆርቋሪነት ቀድሞውንም በውስጤ ነበር አትላንታ ውስጥ በነበርኩበት ጊዜ ከልጅነቴ ጀምሮ ስለ ማህበራዊ ኢፍትሀዊነት ያሳስበኝ ነበር ምከንያታዊ ባለመሆኑና በሞራልም ረገድ ተቀባይነት ስለ ሌለው የዘር ልዩነትን እየተጸየፍኩ ነው ያደኩት መቀመጫ ከፊት እያለ ሄዶ ኋላ መቀመጥ ወይንም በባቡር ውስጥ ተለይቶ በተመደበ ቦታ መቀመጥን ህሊናዬ ሊቀበል አልቻለም አንድ ቀን ምግብ በሚሸጥበት አንድ መኪና ውስጥ ከመጋረጃ ጀርባ ሲያስቀምጡኝ ያ መጋረጃ ሁለመናዬን ሸፍኖ የደበቀኝ መስሎ ተሰማኝ የኢኮኖሚ መበላለጥ ከዘር መለያየት ጋር መንትያ መሆናቸውን ተረዳሁ የዘረኝነት ሥርዓት ድሃ ኔግሮችንና ድሃ ነጮችን እንዴት እየበዘበዘ አንዳለ አየሁ ከነዚህ ልማዶች በህዝባችን ውስጥ የተንሠራፋውን ኢፍትሀዊነት እያየሁ ብስለት አያገኘሁ አደግሁ ይሁን እንጂ ወደ መንፈሳዊ ትቤት እስከገባ ድረስ ይሄ ከፉ ሥርዓት እንዴት መወገድ እንዳለበት በቅጡ አስቤበት አላውቅም በኋላ ግን ወዲያውኑ ፊቴን ወደ ማህበራዊ ወንጌል አዞርኩ ወደ ሀምሳዎቹ መጀመሪያ አካባቢ ከርስትናና ማህበራዊ ችግሮች የተባለው የሮሸንቤከ መጽሐፍ ከአዕምሮዬ ውስጥ ሊፋቅ የማይችል አስተሳሰብ ቀርጾ አልፏል በርግጥ ከሮሸንቤከ የምለይባቸው ነጥቦች ነበሩ አይቀሬ ዕድገት በሚለው የአሥራ ዘጠነኛ ከፍለ ዘመን አስተሳሰብ በመወሰዱ ስለ ሰው አፈጣጠር ተጨባጭ ያልሆነ ተስፋ ያለው ይመስላል ከዚህ በተረፈ ደግሞ የእግዚአብሔርን መንግሥት ከተወሰነ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ ጋር ብቻ አስከ ማያያዝ ተቃርቧል ይሁን እንጂ ቤተከርስቲያን ለዚህ ፈተና እጅ መስጠት አይገባትም ሮሽንቤከ እነዚህ ጉድለቶች ቢኖሩትም ለአሜሪካ ፕሮቴስታንት ልታጣ የማይገባትን ህዝባዊ ኃላፊነት ሰጥቷታል ወንጌል ስለ ሁለንተናዊ ሰው ነው ስለ ነፍሱ ብቻ ሳይሆን ስለ ሥጋው ስለ መንፈሳዊ ደህንነት ብቻ ሳይሆን በምድር ላይ ስለሚኖርበት ነገርም ይገደዋል ስለ ሰው ልጆች ነፍስ የሚገደው እና በአንጻሩ ደግሞ ስለሚያስቃያቸው ድህነት ተብትቦ ስለያዛቸው የኢኮኖሚ ሥርዓትና ሽባ ስላደረጋቸው ማህበራዊ ልማድ ደንታ የሌለው ሃይማኖት በመንፈስ ሞቶ ግባተ መሬቱን የሚጠባበቅ ሃይማኖት ነው ሬሽንቤከን አንብቤ ከጨረስኩ በኋላ ማህበራዊ ንድፈ ሃሳቦችንና የታላላቅ ፈላስፎችን ባህሪይ በጥልቀት ወደ መመርመር ዞርኩ በዚያን ወቅት ማህበራዊ ችግሮችን በመፍታት ረገድ ፍቅር በሚኖረው ሚና ላይ ተስፋ ወደ መቁረጥ ደርሼ ነበር አንደኛውን ጉንጭህን ቢመቱህ ሌላኛውን ደግሞ አዙርለት የሚለውና ጠላቶቻችሁን ውደዱ የሚለው ፍልስፍና ተግባራዊ ሊሆን የሚችለው አንድ ሰው ከሌላ ሰው ጋር በሚጋጭበት ጊዜ ነው የተለያዩ ዘሮች ቡድኖች ወይም አገሮች ሲጣሉ ግን ተቀባይነት ያለው ሌላ ዘዴ የሚያስፈልግ መሆኑ ግልጽ ሆነልኝ በኋላ ላይ ከጋንዲ ትምህርት ጋር ተዋወቅሁ ጽሁፎቹን ሳነብ እሱ ያካሄዳቸው ኃይል አልባ ትግሎች በእጅጉ አስገረሙኝ የጋንዲ የሳትያግራሃ አስተሳሰብ ለእኔ ሙሉ በሙሉ ፍትሀዊ ነበር ሳትያ ማለት ከፍቅር እኩል የሆነ እውነት ማለት ነው ግራሃ ማለት ኃይል ሲሆን ሳትያግራሃ ማለት የእውነት ኃይል ወይም የፍቅር ኃይል ማለት ነው ወደ ጋንዲ ፍልስፍና በጥልቀት እየገባሁ ስሄድ በፍቅር ኃይል ላይ የነበረኝ ጥርጣሬ ቀስ በቀስ አየሟሸሸ ሄደ በጋንዲ የኃይል አልባ ትግል ስልት አማካኝነት እየሠራ ያለው ከርስቲያናዊ ፍቅር ለነጻነታቸው እየታገሉ ላሉ ጭቁን ህዝቦች በጃቸው ያለ ዋነኛ መሳሪያ መሆኑን ለመጀመሪያ ጊዜ ተገነዘብኩ ሆኖም ግን ያን ጊዜ ጉዳዩን በጥልቀት ከመገንዘብ ውጪ እንዴት ሥራ ላይ መዋል እንዳለበት ለማቀናጀት ቁርጠኝነቱ አልነበረኝም በ ፓስተር ሆፔ ወደ ሞንትጎመሪ አላባማ ስሄድ አንድ ቀን የኃይል አልባ ትግል ስልት ሥራ ላይ አንዲውል የሚያስገድድ ሁኔታ ይገጥመኛል ብዬ አላስብኩም ነበር ማህበረሰቡ ውስጥ አንድ ዓመት ያህል ከኖርኩ በኋላ የአውቶቡሱ ዕቀባ ተጀመረ የሞንትጎመሪ ኔግሮ ማህበረሰብ አውቶቡሶች ውስጥ የሚደርስባቸው ውርደት ሊታገሱት ከሚችሉት በላይ ስለሆነባቸው ለነጻነት መቁረጣቸውንና በጋራ አምቢ ለማለት መነሳታቸውን አሳዩ እየተዋረድን አውቶቡሶችን ከምንጠቀም ከነከብራችን በአግራችን ብንመላለስ ይሻለናል ሲሉ ወሰኑ በዚህ ሰላማዊ አመጽ መጀመሪያ ላይ ማህበረሰቡ ቃል አቀባይ አንድሆንለት ጥሪ አደረገልኝ ይህን ጥሪ አንደ ተቀበልኩ በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ሃሳቤ ወደ ተራራው ስብከትና ወደ ጋንዲ ኃይል አልባ ትግል ተጓዘ ከጊዜ በኋላ ይህ ሃሳብ የአንቅስቃሴዎቻችን መሪና ብርሃን ለመሆን ቻሰ ከርስቶስ መንፈሱንና ተነሳሽነቱን ጋንዲ ደግሞ ብልሃቱን ሰጠን ከሞንትጎመሪ ያገኘሁት ልምድ ካነበብኳቸው መጻህፍት ሁሉ ይበልጥ ስለ ኃይል አልባ ትግል ያለኝን አመለካከት እንዳስተካከል ረድቶሃናል በየዕለቱ በኃይል አልባ ትግል ሃያልነት ላይ ያለኝ እምነት እየጨመረ መጣ በኃይል አልባ ትግሉ ውስጥ ልምድ እያገኘሁ ስሄድ ኃይል አልባ ትግል በዕውቀት የሚመራ ብቻ ሳይሆን የህይወት መንገድ አካል ሆነልኝ ኃይል አልባ ትግልን በተመለከተ በሃሳብ ደረጃ ግልጽ ያልነበሩ ጉዳዮች በተጨባጭ ትግል ውስጥ ትርጉም እያገኙ መጡ ከጥቂት ወራት በፊት ህንድን የመጎብኘት ፅድል አግኝቼ ነበር ጉብኝቱ በግሌ በብዙ መንገድ ረድቶኛል በኃይል አልባ ትግልም በጽኑ አንዳምን አድርጎኛል የኃይል አልባ ትግልን ውጤት መመልከት ምንኛ ያስደስታል ህንዳውያን ኃይል ሳይጠቀሙ ነጻነታቸውን ለመጎናጸፍ ችለዋል የኃይል ትግልን ተከትሎ የሚመጣ ጥላቻና ምሬት ህንድ ውስጥ የትም አይታይም ዛሬ በጋራ ብልጽግና አገሮች ማህበር ውስጥ በህንድና በአንግሊዝ ህዝቦች መካከል በእኩልነት ላይ የተመሠረተ ወዳጅነት አሰ ኃይል አልባ ትግል በአንድ ምሽት ተአምር ይፈጥራል የሚል አምነት የለኝም ሰዎች በአዕምሮአቸው ውስጥ ለረጅም ጊዜ የቆየን አስተሳሰብ ወዲያው አውጥተው አይጥሉትም የተበደሉት ነጻነታቸውን ሲጠይቁ በዳዮች ደግሞ በኃይል መልስ ይሰጣሉ ጥያቄው በሰላማዊ መንገድ ቢቀርብ እንኳን የመጀመሪያው ምላሽ ያው ተመሳሳይ ነው በሞንትጎመሪና በመላው ደቡብ የሚገኙ ነጭ ወንድሞቻችን ምንም አንኳን የኔግሮ መሪዎች የፍቅርና የኃይል አልባ ትግል መንገድ ቢከተሉም በመሪዎቹ ላይ ጥላቻ ቋጥረው እንዳሉ ይታወቃል ስለዚህ ኃይል አልባ ትግል የጨቋኞችን ልብ ወዲያውኑ የሚቀይር አይደለም በመጀመሪያ ራሳቸውን በሰጡ ሰዎች ልብ ላይ መሥራት ይጀምራል ለራስ ከብር የመስጠት አዲስ ስሜት ያጎናጽፋቸዋል ቀስ በቀስ ራሳቸው አንዳላቸው ያልተገነዘቡትን ጥንካሬና ድፍረት አያገኙ ይሄዳሉ መጨረሻ ላይ ተቃዋሚያቸው ዘንድ ደርሶ ህሊናቸውን በመኮርኮር ወደ ዕርቅ ያመጣቸዋል በነዚህ ቅርብ ወራት ውስጥ በዓለማቀፍ ግንኙነት ውስጥ የኃይል አልባ ስልት አስፈላጊነት ከፍተኛ መሆኑን ተረድቻለሁ ተማሪ በነበርኩበት ወቅት በአንድ አገር ውስጥ ባሉ ቡድኖች መካከል የሚነሳ ግጭትን ለማስወገድ የኃይል አልባ ስልት ከፍተኛ ጉልበት አንዳለው አምኛለሁ በሁለት አገሮች መካከል ያለውን ችግር ለመፍታት ስላለው አቅም ግን አርግጠኛ አልነበርኩም ጦርነት ሙሉ ለሙሉ ጠቃሚ ነው ባይባልም አንድ ከፉ ኃይል እንዳይነሳና አንዳይስፋፋ ለማድረግ የተወሰነ ጥቅም ወይም በጎነት አያጣም ብዬ እስከማመን ደርሼ ነበር በአምባገነን ሥርዓት ከመተዳደር ይልቅ መዋጋት ይሻላል ብዬ አስቤም ነበር ነገር ግን የዘመናዊ መሳሪያዎችን የአውዳሚነት ኃይል ስመለከት ጦርነት ጥቅም ሊኖረው አይቸልም የሚለው ድምዳሜ ላይ ደረስኩ የሰው ልጅ በህይወት የመኖር መብት አለው ካልን ለጦርነት ሌላ አማራጭ መፈለግ አለብን አስኾትኒኮች ሰማይ ላይ እንደ ልባቸው በሚበሩበትና ከምድር ሆነው የሚቆጣጠሯቸው ሚሳይሎች ሞትን ተሸከመው ስትራቶስፈር ውስጥ በሚበሩበት በዚህ ዘመን ማንም በጦርነት ድልን ሊቀዳጅ አይችልም ዛሬ ምርጫችን በኃይል ስልትና በኃይል አልባ ስልት መሀል አይደለም ምርጫችን ኃይል አልባ ስልት ወይም ዕልቂት ነው እኔ ጭፍን ሰላም ፈላጊ አይደለሁም ተግባራዊ ሊሆን የሚችል ሰላማዊነትን ወይም ሰላም ወዳድነትን ለመከተል ሞከሬያለሁ በተጨማሪም እኔ አንድን ሰላም ወዳድ ሰው ሃጢአተኛ አንዳልሆነ ሰው ሳይሆን ከከፉዎች መሀል የተሻለውን ከፋት እንደመረጠ ሰው ነው የማየው ስለዚህ ራሴን አንድን ተራ ከርስቲያን ከሚያጋጥመው የህሊና መዋዝቅ ወይም ማወላወል ነጻ አድርጌ አላይም ነገር ግን የሰው ልጅ በኒውከሌር ዕልቂት ስጋት ተውጦ እየራደ ባለበት ባሁኑ ሰዓት ቤተከርስቲያን ዝም ብላ መቀመጥ የለባትም ብዬ አምናሰሁ ቤተከርስቲያን በርግጥ ጥሪዋን የምታውቅ ከሆነ የጦር መሣሪያ አሽቅድምድም እንዲቆም ጥሪ ማድረግ አለባት ከቅርብ ወራት ወዲህ ስለ ግል አምላከ መኖር ያለኝ እምነት እየጨመረ መጥቷል በርግጥ ምንም ጊዜ በአግዚአብሔር አምናለሁ ነገር ግን ባለፉት ዓመታት የግል አምላከ የሚባለው ሃሳብ ብዙም ከሃሳብ ደረጃ ከፍ ያለ አልነበረም አሁን በዕለት ተለት ኑሮዬ እየተረጋገጠ መጥቷል ምናልባት አየተሳተፍኩበት ካለው አስቸጋሪ ትግል የተነሳ ያለፍኩባቸው አደገኛ የህይወት መንገዶች ወደ አግዚአብሔር አንድቀርብ አድርገውኛል። ዷቦመራ ያቃሥ ማጋታቶሶ ዳራሟጃሦጋ ማቆፅታንም ዳሪጠም ርገ ፇጦጐ ይሟሃንው ጽሥፍ ዶረ ጴፆ ዕያሦምቻ ራኛ ፈሃ ወዌ ራቅ ፈዖሰጾ ያፃ ፀ መሃሃታ ጳርረሃሙ ፇፇዣ ቃያ ሮየፖጋወያነው ኔግሮዎች ራሳቸውን በከብር እንዲመለከቱ ያደረጓቸው ነገሮች ምንድናቸውን በአንደኛ ደረጃ ሊነሳ የሚችለው የህዝቡ ኑሮ ከገጠር ወደ ከተማ ኑሮ መለወጡ ነው ለብዙ ዘመናት አብዛኛዎቹ ኔግሮዎች ኑሮአቸው በገጠሩ እርሻ ላይ የተወሰነ ነበር ከአካባቢያቸው ርቆ ከሚገኘው ዓለም ጋር የነበራቸው ግንኙነት አጅግ በጣም ውስን ነበር ይሁን እንጂ የሁኔታዎች መለዋወጥ ለምሳሌ የተሽከርካሪዎች መስፋፋት የኢኮኖሚ መደንበሽ ሁለቱ የዓለም ጦርነቶች ያስከተሏቸው ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች ቀስ በቀስ ህዝቦች ወደ አዳዲስና ትላልቅ ማዕከሎች አንዲፈልሱ አስፈላጊና አስገዳጅ ሁኔታዎችን ፈጠሩ ይህ ደግሞ አዳዲስ ግንኙነቶችንና ሰፋ ያለ አመለካከትን ለመፍጠር ምከንያት ሆነ ለኔግሮ ንቃት ሁለተኛው ምክንያት የትምህርት መስፋፋት ነው ባለፉት ዓመታት መሀይምነት እየቀነሰ ሄዷል ነጻነታችንን በተጎናጸፍንበት ወቅት የተማሩ ኔግሮዎች ቁጥር አምስት በመቶ ብቻ ነበር ዛሬ ዘጠና አምስት ከመቶ በላይ ተምረዋል በየዓመቱ በርካታ የኔግሮ ተማሪዎች ከኮሌጆችና ከዩኒቨርስቲዎች ትምህርታቸውን አያጠናቀቁ ነው ከአንድ ሺህ ስድስት መቶ በላይ ኔግሮዎች ከአሜሪካ ዩኒቨርስቲዎች ከፍተኛውን የአካዳሚ ድግሪ ተቀብለዋል በትምህርት መግፋታቸው አመለካከታቸው አንዲሰፋ ረድቷቸዋል ትምህርቱ ኔግሮዎች ስለ ዓለም ያላቸው ግንዛቤ አንዲሰፋ መርዳት ብቻ ሳይሆን ስለ ራሳቸውም በጥልቀት አንዲያስቡ አድርጓቸዋል ኔግሮዎች በራሳቸው እንዲኮሩ ካደረጓቸው ምከንያቶች ሶስተኛው የኢኮኖሚ ደረጃቸው እየተሻሻለ መሄዱ ነው በኔግሮ ላይ የሚካሄደው ኢኮኖሚያዊ ዘረፋ ዘግናኝ ቢሆንም የተገኘ መሻሻል ግን አለ የኔግሮዎች ዓመታዊ ገቢ በአሥራ ስምንት ቢሊዮን ዶላር ይገመታል ይህ አሃዝ ከካናዳ ብሔራዊ ገቢና ዩናይትድ ስቴትስ ወደ ውጪ ከምትልካቸው ዕቃዎች ከምታገኘው ገቢ ይበልጣል የኔግሮ የመግዛት አቅም ከፍ ማለት በቂ በሆኑ ቤቶች ውስጥ በመኖር የተሻለ አገልግሎት በማግኘትና ጥሩ የትምሀርት ዕድል በማግኘት በሚገባ ታይቷል እነዚህ ለውጦች መምጣታቸው ኔግሮ በተለየ ዓይን ራሱን እንዲመለከት አድርጎታል በአራተኛ ደረጃ ኔግሮ በራሱ እንዲኮራ ያደረገው ግንቦት ቀን የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በትምህርት ቤቶች ውስጥ ጥቁሮችና ነጮች ተለያይተው እንዲማሩ ጸንቶ የነበረውን ህግ በመሻር ያስተላለፈው ውሳኔ ነው ይህ ቀን በጎ አመለካከት ላለው ማንኛውም ሰው የደስታ ቀንና ዘረኝነት የተወገደበት ፅለት ነው ፍርድ ቤቱ በውሳኔው የተለያዩ ግን አኩል የተባሉት ትምህርት ቤቶች ውስጣቸው እኩል ባለመሆኑ አንድን ልጅ በዘሩ ምከንያት ተለይቶ አንዲማር ማድረግ ህጉ የሰጠውን የእኩል ጥበቃ መብት እንደ መግፈፍ ይቆጠራል ሲል በየነ ይህ ውሳኔ ተዘንግተው ለነበሩ ነጌሮዎች ትልቅ ተስፋ ነበር በወቅቱ ይህ ውሳኔ መንገድ ጠፍቶት ሲዳከር ቆይቶ በድንገት ከዘረኝነት ጨለማ እንደ መውጫ መንገድ ተፃቆጠረ የተስፋ መቁረጥ ድካምን ተስፋ ወደ ሞላበት ጥንካሬም ለወጠው ይህ ውሳኔ ኔግሮው ያለውን ከብርም ከፍ አድርጎታል ኔግሮው ራሱን በክብር እንዲመለከት ካደረጉት ምከንያቶች አምስተኛው የሚያካሂደው ትግል የዓለም አቀፍ ትግል አካል መሆኑን መረዳቱ ነው በኤስያና በአፍሪካ እየተከናወኑ ያሉ ትግሎችን በቅርበት ይከታተላል ከዓለም ህዝብ ሁለት ሶስተኛው በእነዚህ አህጉራት ይኖራል እነዚህ ህዝቦች ሃብታቸው ለዘመናት በውጭ ኃይሎች ተዘርፏል በፖለቲካ ተጨቁነዋል ተረግጠውና ተዋርደው ኖረዋል ከሰላሳ ዓመታት በፊት ሶስት አገሮች ብቻ ላይቤሪያ ኢትዮጵያና ደቡብ አፍሪካ ነጻ ነበሩ በ ነጻ ሀገሮች ስላሳ ደረሱ ይህ ለውጥ በአሜሪካ ኔግሮዎች ላይ ትልቅ የአመለካከት ለውጥን አስከተሰሪ» ለሰው ልጆች መብት የሚያደርጉት ትግል በአንድ ሥፍራ ብቻ የተወሰነ እንዳልሆነም ተረዳ ትግላቸው በዓለም መድረክ ላይ እየታየ ያለ ከንዋኔ መሆኑንና ከሁሉም አህጉራት ተመልካቾችና ደጋፊዎች እንዳሉትም ተገነዘበ ቁርጠኝነትና አምቢተኝነት ኔግሮ ለራሱ የሚሰጠው ከብር ከፍ እያለ መምጣቱ አንደኛ ደረጃ ዜግነትን እስኪያገኝ ድረስ ለመታገልና መስዋዕትነትን ለመከፈል አዲስ ቁርጠኝነትን በውስጡ ፈጠረ ይህንን ዛሬ በደቡብ እያየነው ነው ሁከተኞች ከበው ሲያስፈራሯቸው ሳይደናገጡ በሊትል ሮክ ጎዳና በሚጓዙ ዘጠኝ ጀግና ተማሪዎች ወይም የደከመች ነፍሳቸውን በደከሙ አግሮች በመተካት ቀናት በአግራቸው በተጓዙ ሃምሳ ሺህ የሞንትጎመሪ አላባማ ነዋሪዎች ወይም በቆዳቸው ጥቁረት የተነሳ አንዲገቡ ባልተፈቀደላቸው ምግብ ቤቶች ውስጥ ገብተው አንዳች ሁከት ሳይፈጥሩ መቀመጫ በመያዝ በተቃወሙ ተማሪዎችም ይገለጥ የትግሉ ዓላማ አንድ ነው ኔግሮው የዘር መድልኦን በውርደት ከመቀበል ይልቅ መከራን በከብር ለማስተናገድ ቆርጧል ይህ የኔግሮ ቁርጠኝነት በአንዳንድ ያገሪቱ ከፍሎች በሚኖሩ ህዝቦች ዘንድ ተቀባይነት አላገኘምራ ይባስ ብሎም በብዙ ቦታዎች ተቃውሞ አጋጥሞታል ተቃውሞው ከፍተኛ ደረጃ የሚደርስበት ጊዜም ነበር ጥቂት ያገሪቱ ከፍሎች በድብቅ ሳይሆን ፊት ለፊት ተቃውመውታል በአብዛኛዎቹ የደቡብ ህግ አውጪ ምቤቶች ውስጥ ደግሞ ህጉ ይለወጥ የሚሉ ጩኸቶች ሲሰሙ ይውላሉ አንዳንድ የህዝብ መሪዎች ህጎችን በትከክል ሥራ ላይ ከማዋል ይልቅ ትምህርት ቤቶችን እስከ መዝጋት የሚሄድ አከራሪነት አሳይተዋል የኔግሮን አካሄድ የመቃወሙ ድርጊት በኩ ክላክስ ከላን መልሶ መጠናከርና በነጭ ዜጎች ምክር ቤት መቋቋም ታይቷል በኔግሮ አካሄድ ላይ የሚነሳው ተቃውሞ በግልጽ ብቻ ሳይሆን በስውርና በጥበብ እውነታን በማጣመም ጭምርም ነበር የሰሜንና የደቡብ ሊብራሎችን ድጋፍ ለማግኘት ሲባል የልዩነት ደጋፊዎች ግማሽ አውነታ ያላቸው ሃሳቦችን በብልጠት ያሠራጫሉ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ተመሥርተው የዘሮች መበላለጥና ልዩነት ትክከለኛ መሆኑን ከማሳመን ይልቅ ከርከራቸውን ወደ ባህልና ማህበራዊ ኑሮ ይወስዱታል ኔግሮ ከሌሎች ጋር ለመቀላቀል ዝግጁ አይደለም ምከንያቱም በትምህርትና በባህል ወደ ኋላ ከመቅረቱ የተነሳ ነጭና ጥቁር ተቀላቅለው ቢማሩ ነጮችን ወደ ኋላ ይጎትታሉ በማለት ይሟገታሉ ኔግሮ በባህልና በትምህርት ወደ ኋላ መቅረቱ በመድልኦ ምከንያት መሆኑን መቀበል አይፈልጉም አንድን ችግር ለመፍታት መንስኤውን በቅድሚያ ማወቅ ያስፈልጋል የመድልኦው ውጤት አንዲቀጥል መሟገት ተቀባይነት የለውም ዛሬ አገሪቱን የገጠማት ተግዳሮት ይህን ችግር መፍታትና ዲሞከራሲን ዕውን ማድረግ ነው ይህን ሁኔታ የመቀየሪያ ስልታችን የፖለቲካችንን ጤናማነትና አገራችን አንደ ዋንኛዋ የነጻው ዓለም መሪ ያላትን ከብር ይወስናል አሜሪካ የአገሯን ኔግሮዎች ለመጨቆን አያወጣች ያለችው ወጪ ራሷን ለማጥፋት አያባከነቸው ያለው ሀብት ነው ጊዜው እየሄደ ነው ተነስተን ልንቀይረው ይገባል ከዚህ በፊት ተደጋግሞ እንደተነገረው ዛሬም አንደሚታየው አሜሪካ የዓለም መሪ ሆና ለመቀጠል ከፈለገት ሁለተኛ ደረጃ ዜጎች ሊኖሯት አይገባም አሜሪካ ውስጥ የዘር ልዩነት ማስቀረት ያለብን ኮሚኒዝምን በመፍራት አይደለም ለአፍሪካና ለኤስያ ህዝቦች ብለንም አይደለም ዘረኝነትን ካገራችን መንቀል ያስፈለገን በሞራል ረገድ ትከከል ባለመሆኑ ነው የዘር ልዩነት ከርስቲያናዊ ሃይማኖታዊ ባህላችንን በትክከል በሥራ እንዳንተረጉም ያገደን ዋነኛ በሸታችን ነው የዘር ልዩነት እኔ እና እሱ የሚለውን ግንኙነት እኔ እና ይኹ በሚለው የሚተካ ነው የሰውን ልጅ ወደ ግዑዝነት ደረጃ ዝቅ ያደርጋል ማለት ነው የዘር ልዩነት ያለበት ቦታ ሁሉ በመንፈስ ሙት በሞራልም ሰንካላ ሆኖ እናገኘዋለን ስለዚህ በድፕሎማሲ ቀላል ስለሆነ ሳይሆን በሞራል ረገድ ግዴታ በመሆኑ ዘረኝነት ሊነቀል ይገባል ብሔራዊ ተግዳሮት አሜሪካ ውስጥ የገጠመን የዘር ችግር የአንድ ወገን ችግር ብቻ ሳይሆን የመላ አገሪቱ ነው ባንድ ሥፍራ የሚታይ ኢፍትሀዊነት የትም ቦታ ላለ ፍትሀዊነት ጠንቅ ነው ስለዚህ ማንኛውም ያገሪቱ ዜጋ ዝም ሊል አይችልም ይህ የሁሉንም በር እያንኳኳ ያለ ችግር ነው ይህን ችግር ለመፍታት ከፌደራሉ መንግሥት ጠንካራ አመራርን ይጠይቃል በሰሜን ውስጥ ከምር ነጻ የሆነ በራሱ ማህበረሰብ አልፎም በደቡብ ማህበረሰብ ውስጥ በውህደት የሚያምን ሲብራሊዝም ያስፈልጋል የሚሲሲፒ ኔግሮ ተደብድቦ በሚገደልበት ወቅት በቅንነትና በስሜት ዘሎ የሚነሳ ሊብራል ብቻ ሳይሆን ኔግሮ በአቅራቢያው አንዳይኖር ሲከለከል ወይም በሙያ ማህበራት ወይም በሁሉም የሥራ ዘርፍ ውስጥ ከፍ ያለ ቦታ እንዳያገኝ ሲከለከል ከጎኑ የሚቆም አጋር መሆን አለበት ስለ ውህደት በማውራት ገዜ ልናባክን አይገባም በገቢር ማሳየት አለብን በዚህ ታሪካዊ ወቅት ወሳኝ ሚና መጫወት የሚችሉ አያሴ ድርጅቶችና ቡድኖች አሉ በተለያዩ ዘሮች መካከል ያለው የኢፍትሀዊነት ችግር ከባድና ሰፊ በመሆኑ ለመፍትሄው የብዙ ሰዎችና አካላትን ተሳትፎ ይጠይቃል ትልቅ ኃላፊነት ኔግሮው የአንደኛ ደረጃ ዜግነትን የሚሻ ከሆነ ይህን ዕውን ለማድረግ ደግሞ ራሱ ዋንኛውን ኃላፊነት ሊወስድ ይገባዋል በመጀመሪያ ደረጃ ስለ ዜግነት መብቱ ከራሱ ውጪ የሚቆረቆርለት አካል ያለመኖሩን በግልጽ መገንዘብ ይኖርበታል በዚህ የማህበራዊ ለውጥ ወቅት ኔግሮው በሁለት አቅጣጫዎች በርትቶ ሊሠራ ይገባዋል በአንድ በኩል የመድልኦን ግድግዳ ማፍረሱን መቀጠል አለበት በዘር ላይ የተመሠረተ ኢፍትሀዊነትን በጽኑ መታገል ይገባዋል ይህ ትግልም በታላቅ ስነ ምግባርና ሰብዓዊ ከብር መከናወን ይኖርበታል ወደ ኃይል ትግል ወይም ሁከት ማዝቀጥ አይኖርበትም የተሻለ መንገድ አሰ እንደ ናዝሬቱ ኢየሱስ ትምህርት ረዥም ዘመን ያስቆጠረና እንደ የቅርብ ዘመኑ የጋንዲ የትግል ስልት ስልቱ የደካሞችና የፈሪዎች ሳይሆን የብርቱዎችና የጀግኖች ስልት ነው እንዲህ ዓይነት ትግል በተለያዩ ስሞች ይጠራል ሰላማዊ ትግል ኃይል አልባ ትግል ወይም ክርስቲያናዊ ፍቅር ሊባል ይችላል የኔግሮው የነጻነት ትግል ሥር አየሰደደ በሄደ ቁጥር የኃይል አልባ ትግል ወደ ኔግሮው የበለጠ እየሰረጸ ይሄዳል የሚል ከፍተኛ አምነት አለኝ ከአንድ ዘር እንደተገኘ ህዝብ ደከመን ሰለቸን ሳንል ለአንደኛ ደረጃ ዜግነት መታገል አለብን ነገር ግን በሁለተኛ ደረጃ የትግል ስልት ልንጠቀም አይገባም ዓላማችን ነጮችን ማሸነፍ ወይም ማዋረድ አይደለም ነገር ግን ፍቅራቸውንና ወዳጅነታቸውን ለማግኘት ነው በጥላቻ ተነሳስተን ወይም ለትንኮሳ ተሸንፈን ኃይል ወደ መጠቀም እንዳናመራ ልንጠነቀቅ ይገባናል ይህ ከሆነ ለመጪው ትውልድ መራርነትን አውርሰን እኛም ትርጉም የለሽ በሆነ ሁከት ስንታወስ እንኖራለን እንዲህ ዓይነት ኃይል አልባ የትግል ስልት አስፈላጊ ይመስለኛል ምከንያቱም የተጎዳን ህብረተሰብ መልሶ ለማቋቋም የሚረዳ ብቸኛው ዘዴ ይህ በመሆኑ ነው መንገድ ባለማወቅ በፍርሃትና በትምከህት ተሸብቦ የኖረውን የአያሌ ቅን ሰዎችን ልቦና ኮርኩሮ ፍትሀዊ ህጎችን ሥራ ላይ እንዲያውሉ ሊያነሳሳቸው የሚችል መንገድ ነው የኃይል አልባ ትግል አራማጆች መልዕከታቸውን አሳጥረው አንደሚከተለው ማስቀመጥ ይችትላሉ የትኛውንም ድርጅት ሳንጠብቅ አኛው ራሳችን በኢፍትሀዊነት ላይ ቀጥተኛ እርምጃ እንወስዳለን ኢ ፍትሀዊ ለሆነ ህግ አንገዛም ፍትሀዊ ላልሆኑ ድርጊቶች አጅ አንሰጥም ይህንንም በሰላማዊ መንገድ በግልጽና በደስታ እናደርገዋለን ምከንያቱም ዋነኛ ዓላማችን የሰዎችን አስተሳሰብ መለወጥ ነው ኃይል አልባ ትግል ስልትን የመረጥነው ግባችን ከራሱ ጋራ ሰላም ያለው ማህበረሰብ ለመፍጠር ስለምንሻ ነው በቃሎቻችን ሰዎችን ለመለወጥ እንሞከራለን ነገር ግን በሱ ካልቻልን በድርጊታችን እንሞከራለን ሁልጊዜ ችግሮችን በውይይት መፍታት እንፈልጋለን ነገር ግን አውነት ነው ብለን ላመነው ጉዳይ መከራን መቀበል ካስፈለገ ደግሞ ህይወታችንን ለመስጠት ዝግጁዎች ነን ይህ መንገድ በቸግር የተሞላና መስዋፅትነትን የሚጠይቅ መሆኑን አረዳለሁ ወህኒ ሊያስወርድ ይችላል እንደዚያም ቢሆን በደቡብ የሚገኙ አሥር ቤቶችን ለመሙላት ዝግጁ መሆን አለብን ለሞት ሊዳርግ ይችላል ነገር ግን የአንድ ሰው ሥጋዊ ሞት ልጆቹንና ነጭ ወንድሞቹን ከመንፈሳዊ ሞት ለመታደግ የሚከፈል ዋጋ ከሆነ ከዚህ የተሻለ የተባረከ ድርጊት አይገኝም ይህ መንፈሳዊ ኃይል በጨቋኛቹ አካላዊ ኃይል ላይ ድል ይቀዳጃል ብዬ አምናለሁ ይህ ስልት ከዚህ ቀደም የጭቆና ችግርን ለመፍታት ሥራ ላይ ውሎ ስኬታማ ሆኗል ጋንዲ እውነትን ሰላማዊ ትግልን ጀግንነትንና መንፈሳዊ ኃይልን ብቻ በመጠቀም የብሪቲሸ ኢምፓየርን ግዙፍ ኃይል ተቋቁሞ ህዝቡን ነጻ ሊያወጣ ችሏል ዛሬ በደቡብ ውስጥ ዘረኛ ኃይልን አየታገሉ ያሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎችን በምሳሌነት መውሰድ ይቻላል እነዚህ ወጣት ተማሪዎች የኔግሮውን ማህበረሰብ የዘመናት ለቅሶና ትዕግስት በውስጣቸው ቀምረው በመላው አገሪቱ አውቅናን ወዳገኘው አዲስ የትግል ዘዴ ቀይረዋል ባለፉት ጥቂት ወራት ውስጥ ከራሳቸው አልፈው ለአካባቢያቸው ብርሃንና ሙቀት ለመፍጠር ችለዋል ቀጥተኛ የሰላማዊ ትግል እርምጃ በመውሰድ በሰማኒያ ከተሞች ለጥቁሮች ዝግ የነበሩ ምግብ ቤቶችን ለማስከፈት ችሰለዋል እነዚህ አርምጃዎች ታሪካዊ ናቸው ብንል ሀሰት አይሆንም በዩናይትድ ስቴትስ ግዛት ይህን ያህል ቁጥር ያላቸው ተማሪዎች ይህን ያህል ስፋት ባለው ከልል ላይ ለሰው ልጅ ከብርና ለነጻነት ትግል አካሂደው አያውቁም ታሪከ ጸሐፊዎች አንድ ቀን ይህን የተማሪዎች እንቅስቃሴ ከዚች አገር ትላልቅ ከንዋኔዎች ውስጥ አንደ አንዱ ይጽፉታል የሜል እምነት አለኝ ሌላ በብርቱ ልንሠራበት ስለሚገባን ጉዳይ ማንሳት ይገባኛል አያንዳንዱ ኔግሮ የግል ብቃቱን ከፍ ማድረግ ይጠበቅበታል ከፍርሀትና ካለማወቅ የተነሳ በዝግጁነታችንና በችሎታችን ላይ ጥያቄ ለሚያነሱ ሰዎች ሁሉ ለኋላ ቀርነታችን ምከንያቱ ባርነትና መድልኦ ደካማ ትቤቶች የተገለሉ አሮጌ የመኖሪያ መንደሮችና ላያችን ላይ ተጭኖ የነበረው የሁለተኛ ደረጃ ዜግነት እንጂ በተፈጥሮ ደካሞች በመሆናችን አለመሆኑን ለማሳየት ችለናል የነበረባቸውን ተጽዕኖ ሁሉ ተቋቁመው ኔግሮዎች ለአሜሪካ የአኗኗር ባህል ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን በተግባር በማሳየት ከፊል እውነታ ብቻ ያለውን የነጮች ተረት ተረት ማስተባበል ተችሷል ነገር ግን ብቃታችን ከሚጠበቀው ደረጃ ያለመድረሱን ልንሸሽግ አይቻለንም አራስን ገምግሞ የመውቀስ ደረጃ ላይ መድረስ የብስለት ምልክት ነው ለዘመናት ከኢኮኖሚውና ከማህበራዊው ኑሮ ተገልለን መኖራችን ጉዳት አድርሶብናል አንዳንድ ኔግሮዎቸ በጥላቻና በጥርጣሬ ተሞልተዋል አንዳንዶች ደግሞ ከሥርዓቱ ጋር በመላመዳቸው ተነቃቅተው አዳዲስ ነገሮችን የመፍጠር ችሎታቸውን አጥተዋል ብዙዎች ደግሞ ተጨቁነው መኖራቸውን ለዳተኝነታቸው እንደ ምከንያት ያቀርባሉ ብዙዎቻችን ከአቅማችን በላይ የሆነ ኑሮ እንኖራለን ለማያስፈልግና አልባሌ ለሆነ ነገር ገንዘባችንን እናባከናለን ነገር ግን ጠቃሚ ለሆኑ ጉዳዮች መልካም ሥራ ላይ ለተሰማሩ ድርጅቶችና ፅርዳታ ለሚሹ ትቤቶች እጃችን አይዘረጋም ሃጢአታችን ብዙ ነው ገንቢ ሥራ ስለዚህ ኔግሮዎች ደረጃቸውን እንዲያሻሸሉ የሚረዳቸው ፕሮግራም ከማንኛውም ጊዜ የበለጠ ዛሬ ያስፈልገናል የችግሮቻችንን ማህበራዋና ስነ ልቦናዊ መንስኤ ገምግመን ይህን ችግር የሚያቃልል የግንባታ ፕሮግራም ማውጣት አለብን ወጣቶቻችን ዛሬ ከሚገኙበት ዝቅተኛ ደረጃ ወጥተው በየተሰማሩበት የሙያ መስከ ልቀው እንዲገኙ ማነሳሳትና ማበረታታት ይኖርብናል በፊት ዝግ የነበሩ በሮች መከፈት ጀምረዋል ዛሬ እየገጠመን ያለው ችግር በነዚህ በተከፈቱ በሮች ለመግባት ዝግጁ ሆኖ ያለመገኘት ነው አዳዲስ ዕድሎች እንዲከፈቱ አድርገን ልንጠቀምበት አለመቻልን ያህል አሳዛኝ ነገር የለም ይህ ዘመን የትም ሀገር ከሚገኙ ከማናቸውም ዘር ከተወለዱ ሰዎች ጋር ለመወዳደር የምንገደድበት ዘመን መሆኑን ለወጣቶቻችን ማስተማር ይኖርብናል ጥሩ የኔግሮ መምህር ጥሩ የኔግሮ ሀኪም ወይም ጥሩ የኔግሮ ባለሙያ ለመሆን ማቀድ አይገባንም ከራሳችን ዘር አልሯ የሚሄድ መልካም ሥራ መሥራት ይጠበቅብናል የምንሠራውን ሥራ ማንም ሰው አሻሸሎ ሊሠራው እንዳይችል አድርገን መሥራት አለብን ጥሩ ኔግሮ ብቻ ለመሆን የሚመኝ ኔግሮ ወደ ውህደት ዩኒቨርስቲ የሚያስገባውን ፈተና እንደወደቀ ይቆጠራል ዕቅዳችን ይህ መሆን አለበት የሚያሳስር አንኳን ቢሆን በዘረኝነት ላይ በተመሠረተ ኢፍትሀዊነት ላይ ኃይል አልባ ትግል ማካሄድ አለብን ባርነትና መድልኦ ያደረሱብንን ሞራላዊ ስብራት ለመጠገን ደፋርና ገንቢ አርምጃዎችን መውሰድ ይገባናል የደቡብ ተማሪዎች ያካሄዱት ዓይነት ኃይል አልባ ትግል በጀግንነትና በሰብዓዊ ከብር ሥራ ላይ ብናውል ሞራላዊ ስብራታችንን ለመጠገን ያግዘናል ግን ደግሞ ድላችንን አስተማማኝ የሚያደርገው አግዚአብሔር በህይወት እንድንኖር የሰጠንን መብት በገደቡብን ጉዳዮች በድህነት በበሽታ በማይምነት ላይ ከሁሉ አቅጣጫ የምናካሂደው ዘመቻ ነው ዲሞከራሲያችንና ከርስቲያናዊ ህይወታችን ጤና አንዲያጣ ምከንያት የሆነው የዘረኝነት ነቀርሳ ከፖለቲካ አካላችን ተቆርጦ እንዲወጣ በቁርጠኝነት ልንታገል ይገባል ያን ጊዜ ብቻ ነው የዲሞከራሲ ራዕያችን ፅውን ሊሆን የሚቸችለው አኩል ዕድል የማግኘት ራዕፅይ እኩል መብት የማግኘት ራፅይ ፍትሀዊ የሀብት ከፍፍል ራዕይ የብዙሀን መተዳደሪያ ተነጥቆ የጥቂቶች መንደላቀቂያ የማይሆንበት አገር የማየት ራዕይ የሰው ማንነት የሚወሰነው በቆዳው ቀለም ነው ብለው የማይከራከሩበትን አገር የማየት ራፅይ የተፈጥሮ ስጦታና ሀብት ሁሉ እኛ ብቻ ሳንሆን የሰው ልጆች ሁሉ ሊጠቀሙበት ይገባል የሚባልበት አገር የማየት ራዕይ የሰው ልጆች ሁሉ ለሰብዓዊነት ከብር የሚሰጡበት አገር የመገንባት ራዕይ ይህ ፅውን ሲሆን ሰው በሰው ላይ ካለው አስፈሪ ጭካኔ ወጥተን የእግዚአብሔር ፍጡራን ሁሉ ወደ ነጻነትና ፍትህ አንረማመዳለን የነጻነት ጊዜ ደርሷል ምንያጋጋሪ ዖሃሠፇ ያሰ ሐማቭናስሰረ ፈጳባኔ ዎጮቻ ያሃፈፀ ወጋዶሯ ረሪኝሁፉጋ ሐመቃጋም ፈፉ ልይ ዕሰዶቻን ሃነጠቃቀመዎምሳ ያም። የኔግሮ ህግ ባለሙያዎች ሥራ ከወንጀል ጉዳዮች ጋር ብቻ የተያያዘ ነው ከኑዛዜና ውርስ ከኮርፓሬሽኖች ከታከስና ከመሳሰሉት ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ብዙ ጊዜ ወደ ቢሮአቸው አይመጡም ምከንያቱም ወደነሱ የሚመጡ ደንበኞች ሀብት የማፍራት ዕድል ያላቸው አይደሉም በደቡብ ክፍል አነሱ የሚቀርቡባቸው ችሎቶች የተለዩ ሊሆኑ የሚችሉ መሆናቸው ብቻ ሳይሆን ደንበኞቻቸውም ሆነ አነሱ በሚቀርቡበት ወቅት አቶ አገሌ ተብለው ላይጠሩ ሁሉ ይችላሉ በተጨማሪም ጥቁር ተጠርጣሪዎች ገና ተከሰው ፍቤት እንደቀረቡ እንደሚፈረድባቸው ይታወቃል ለጥቁር ተከራክሮ ነጻ መውጣት የሰማይ ያህል ሩቅ ነው ጠንካራ ዓላማን ይዞ ተምሮ የሚጨርስ የኔግሮ ባለሙያን ከሚያጋጥሙ ተግዳሮቶች መካከል እነዚህ ጥቂቶቹ ናቸው የሚያበረታታቸው ነገር አምብዛም አይገኝም ዛሬ ግን ከምን ጊዜውም በተሻለ ሁኔታ ኔግሮው ከዕለት ተለት ኑሮው የወደፊት ዕድሉን ሊያስናከሉ የሚችሉ ሁኔታዎችን ለመለወጥ እርምጃ መውሰድ እንደሚችል ተረድቷል የዘር መድልኦን ለማስቀረት በመታገል ለራሱም ሆነ ለቀጣዩ ትውልድ ለውጥ በማምጣት ላይ ነው የኔግሮ ተማሪ ራሱንም ህብረተሰቡንም ሊጠቅም የሚችልበት መንገድ አለ ማህበራዊ ኃላፊነትንም አየተለማመደ ነው በራሱ ጥረት መተዳደርንም እየተማረ ነው ይኹ አሱ የሚፈልገው ውጤት ነው ወደ ፈለገበት የሚነዱት ደካማና ልፍስፍስ ሊያደርጉት የሚሞከሩም አሉ ነገር ግን ኔግሮ እንዲያልፍ የሚጠበቅባቸው መንገዶች ሁሉ አደገኛ እና ጥረትን የሚጠይቁ ናቸው ትግሉ ውስብሰብ ስለሆነ እንደ ዋዛ የሚታይ አይደለም ጥልቅ ዕውቀትና በጎ ፀባይ ልክ አንደ ጀግንነትና መስዋዕትነት ተፈላጊዎች ናቸው ስለዚህ ልንደርስበት ያቀድነውን ግብ የሚመጥን መልካም ስነ ምግባር አንዲኖራቸው እየተሠራ ነው በዚህ ማሰሮ ውስጥ ተቀቅሎ ነው በስሎ በህይወት ልምድ ዳብሮ ነቅቶ አዲስ ነገር ለመሞከር የማይፈራ ከሁሉ የበለጠ ደግሞ ህብረተሰቡን ለማገልገል ራሱን የሰጠ ሙሉ ሰው ሆኖ የሚወጣው ስለዚህ የዚህ ትግል ተሳታፊዎች ከሁለት አቅጣጫ ትምህርት ያገኛሉ የአካዳሚ ዕውቀትን በከፍል ውስጥ ከመጻህፍት የህይወት ትምህርትን ደግሞ በማህበራዊ ተሳትፎና ኃላፊነት ማንኛውም የተማረና የበሰለ አሜሪካዊ የትም ቦታ ከሚገኝ ወጣት የመወዳደር ጥያቄ መልስ የሚያገኘው ከዚህ አዲስ አንቅስቃሴ ውስጥ ነው በርግጥ በትግላችን ውስጥ የተሳተፈ ተማሪ ሁሉ ተጠቃሚ ሆኗል ለማለት አይቻልም በሰው የሚዘጋጅ ማንኛውም ዕቅድ ይህን ዕውን ማድረግ አይችልም አንዳንዶች ይህን ፅድል ቢያገኙም በባህሪያቸው ምከንያት የገጠሟቸውን ፈተናዎችና እንቅፋቶች ሊያልፉ አልቻሉም ጥቂት መቶኛ ተማሪዎች መቀመጫ በመያዝ አድማና በሌሎች ትግሎች በመሳተፍ ድከመታቸውን አካከሰው ከወቀሳ ለመዳን ችለዋል ነገር ግን አነዚህ ጥቂቶች ናቸው ምከንያቱም አንዲህ ዓይነቱ ከኃላፊነት የመሸሽ ሩጫ ለበለጠ ኃላፊነትና አደጋ ሊዳርግ ይችላል ስለ ኃይል አልባ ትግል ትከከለኛነትና ተግባራዊነት ከተማሪዎች ጋር በተወያየንበት ወቅት ብዙዎቻቸው ኃይል መጠቀምን ተቃውመዋል በአንድ ወቅት ሃሳቡን አንስተን ሁሉም ከተስማማበት በኋላ አንድ ተማሪ ዘንድ ስንደርስ አንዲህ አለ እኔ እንደማውቀው ጥንቸል ድንጋይ መወርወር ብትችል ኖሮ ወደ ዱር የሚገቡ አዳኞች ቁጥር ይቀንስ ነበር ይህ አባባል አንዲህ ያለ የሞቀና በውጥረት የተሞላ ውይይት ለማብረድ ከቀረበ አባባል በላይ ነበር ይህ አባባል ትልቅ ከፋት እየተሠራ ሳለ በጥቃቅን እርምጃዎች መታለፉ ያመጣው ቁጣ እና ታፍኖ የቆየ ትዕግስት ማጣት የወለደው ነው ስለዚህ ለአንዳንድ ተማሪዎች የሚታያቸው መልስ ኃይል መጠቀም ብቻ ነበር ሙኬድውሉዌ ለአብዛኛዎቻቸው ግን አሁንም ኃይል አልባ ትግል ትከክልና ውጤታማ ነው ይህን ለማድረግ ቅሬታቸውን መተው አይጠበቅባቸውም በአቅራቢያችን የምናየውን ኢፍትሀዊነትና የጭካኔ ተግባር በቅሬታ መግለጽ ተገቢና ትከከል ነው ኃይል አልበኝነት ከፋትን እንዴት እንደምንከላከል ብልሀት ይሰጠናል ጥይት ሳይተኩሱ አንዴት አድርጎ ባላጋራን ትጥቅ ማስፈታት አንደሚቻል ያስተምረናል የተቃዋሚያችንን ማንነት ያጋልጣል ሞራሉን ያዳከማል እንዲሁም ህሊናውን ይሸነቁጠዋል በትግል ላይ ያሉ የኔግሮ ተማሪዎች የሚጠቀሙበት ሌላው መሣሪያ አሽሙር ነው ይህ ዘዴም ጠላታቸውን ሳያስቆጡ እየቀለዱበትና ወጋ አያደረጉ ያሉበትን ሁኔታ ለመግሰጽ አስችሎአቸዋል የኃይል አልባ እርምጃ አንዱ ጥሩነት ቁጣን በማለዘብ ወደ ሌላ መቀየሩና በጣም ጥቂት ተማሪዎች ለምን የጥቁርን የበላይነት እንደሚያቀነቅኑ ማብራራት መቻሉ ነው እነዚህ ተማሪዎች ቁጣቸውን መቆጣጠር ችለዋል ስለዚህ በቁጣና በኃይል የሚገነፍሉት እንዲረጋጉ ይመክራሉ የኃይል አልባ ትግል ተሳታፊዎች በራሳቸው ተነሳሽነት ህጎችን እንዲጥሱ ብዙ ሥራ ተሰርቷል ታጋዮቹ የቶሮና የጋንዲን ስልቶች በአሜሪካ ታሪከ ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ የተጠቀሙ ቢሆንም ህግን ያከብራሉ ፍትሀዊ የሆነ ህግን ማክበር ኃላፊነታቸው አድርገው ይመለከታሉ ይሁን አንጂ ኢፍትሀዊ ህግ አንዳለም ያውታሉ ከሞራል አንጻር ስንመለከት ኢፍትሀዊ ህግ የዚህን ዩኒቨርስ ሞራላዊ ህግ የማይቀበል ህግ ነው በተጨባጭ ኢፍትሀዊ ህግ የሚባለው ብዙሀኑ ላይ የማይተገበርን ህግ ጥቂቶች እንዲቀበሉት የሚያስገድድ ከሆነ ነው በሌላ በኩል ኢፍትሀዊ ህግ የመራጭነት መብት የተነፈጋቸው ህዝቦች ራሳቸው ለማውጣት ባልተሳተፉበት ህግ አንዲገዙ የሚያስገድድ ሲሆን ነው እነዚህ ተማሪዎች ኃይል ሳይጠቀሙ በሰላምና በይፋ ህጎቹን ተግባራዊ ባለማድረግ ይቃወማሉ ከሁሉ የበለጠ ደግሞ እነዚህን ህጎች መጣስ የሚያመጣባቸውን ቅጣት ለመቀበል ዝግጁዎች ናቸው በዚህ መንገድ ህብረተሰቡ እነዚህን ህጎች አንደገና አጢኖ ሰብዓዊነትን ከፍ የሚያደርግ ነው ወይስ ዝቅ የሚያደርግ ነውን በማለት እንዲወስን ያደርጋል ህግን ስላለማክበር ያላቸው አቋም ነጭ ዘረኞች ህግን ስላለማከበር ካላቸው አቋም በጣም የተለየ ነው የዘረኝነት አራማጆች ኢፍትሀዊ ነው የሚሉትን ህግ መጣስና ማጣመም እንጂ በዚያ ምክንያት የሚደርስባቸውን ቅጣት ለመቀበል አይፈልጉም የተቃውሞአቸው ግብ ሥርዓተ አልበኝነትን መፍጠር ነው ለህግ ያላቸውን ጥላቻ መግለጽ ነው ተማሪዎቹ ግን አዕምሮአቸው ኢፍትሀዊ ነው ብሎ ያመነበትን ህግ በመጣስ ተከትሎት የሚመጣውን ቅጣት ተቀብሎ ለውጥ አስኪመጣ ድረስ እሥር ቤት ለመቆየት መወሰን ህግን የማክበር ምልክት ነው ብለው ያምናሉ የቆሙለት ዓላማ ፍትሀዊነትን በሰው ህሊና ማስረጽ ነው ከዚህም አልፎ እነዚህ ተማሪዎች ያለፈው ትውልድ ያልተረዳው ጉዳይ የገባቸው ይመስላሉ ህግ መብትን ያውጃል እንጂ መብትን አይሰጥም የተላለፈን አንድ ፍትሀዊ ውሳኔ ሁሉም ሰው ተቀብሎ የህይወቱ አካል እስኪያደርገው ድረስ የታወጀውን መብት ተጠቅመው ሥራ ላይ የሚያውሉ ቆራጥ ሰዎች ያስፈልጋሉ ተማሪዎቹ ይህን ህግ ሥራ ላይ ለማዋል ጉልበታቸውንና አካላቸውን ሰጥተዋል ራሳቸውንም አዲስ ሥርዓት እንደሚያዋልዱ ባለሙያዎች ይመለከታሉ በዚህ መንገድ ጊዜው የደረሰን አስተሳሰብ ይተገብራሉ ባለፉት ሁለት ዓመታት የተገኙ ድሎች በርካታ ናቸው መቀመጫ የመያዝ አድማ ባካሄዱ ተማሪዎች ምከንያት ደቡብ በሚገኙ ከተሞች ውስጥ ያሉ ምግብ ቤቶች ለጥቁሮችና ለነጮች ከፍት ሆነዋል ይህ ድል የተገኘው በአንድ በኩል ቀደም ሲል ህግን ተከትለው በተካሄዱ የሲቪልና የማህበራዊ ትግል እንቅስቃሴዎች አማካኝነት ጠንካራ መሠረት በመጣሉ ነው በሌላ በኩል ደግሞ የፌደራሉ መንግሥት ከውጪ አገሮች ጋር በሚያደርገው ግኑኝነት አገር ውስጥ በልዩ ልዩ ህዝቦች መካከል ያለው ግንነኙነት ወሳኝ መሆኑን ቀስ በቀስም ቢሆን አየተረዳ መምጣቱ ነው የውጪ ስማችን የውስጥ ባህሪያችንን ያንፀባርቃል በሰሜንና በደቡብ የሚገኙ ብዙዎቹ ሊብራሎች ባለፉት ዓመታት በዘረዘሯቸው ዋና ዋና ዕቅዶቻቸው ውስጥ የዕረፍት ጊዜ ወይም ፋታ ሊኖረን ይገባል። ቻ ኗሪፍምዮ ሐሟሮሪግ ዕኤ ዴዴ ዴጨጫ የተከበራቸሁ ያገሬ ካህናት አያካሄድን ያለነው ትግል ወቅቱን ያልጠበቀና ጥበብ የጎደለው መሆኑን በመግለጽ መግለጫ ማውጣታችሁን እዚህ በርሚንጋም በሚገኝ እሥር ቤት ውስጥ ሆፔ ሰምቻለሁ አስተሳሰቤንና ሥራዎቼን በተመለከተ ለሚነሱት ትችቶች መልስ ለመስጠት ጊዜ አባከፔ አላውቅም ለሚሰነዘሩብኝ ቅሬታዎች መልስ ለመስጠት ብሞከር ጸሐፊዎቹቼ ቀኑን በሙሉ ለሌላ ተግባር ጊዜ ማግኘት አይችሉም ነበር እኔም ለፍሬያማ ሥራ ጊዜ አይተርፈኝም ነበር ይሁን እንጂ ትችታቸችሁ ከቀና አስተሳሰብ የመነጨና በአግባቡ የቀረበ ሆኖ ስለ ታየኝ ለመግለጫችሁ ሚዛናዊና በትዕግስት የተሞላ ምላሽ ለመስጠት ተገድጃለሁ በመግለጫችሁ ውስጥ ስለ ውጪ ኃይሎች ስለጠቀሳቸሁ ለምን እዚህ በርሚንጋም እንደተገኘሁ መግለጽ ያለብኝ ይመስለኛል መቀመጫው አትላንታ ጆርጂያ ሆኖ መላውን የደቡብ ግዛቶች የሚያገለግል የደቡብ ከርስቲያን አመራር ምከር ቤት ለተባለ ድርጅት ፕሬዝዳንት ሆፔ እንድሠራ ዕድል አጋጥሞኛል ለሰው ልጆች መብት የአላባማ ከርስቲያናዊ ንቅናቄን ጨምሮ በመላው ደበብ ከኛ ጋር የሚሠሩ ሰማኒያ አምስት ድርጅቶች አሉ ከነዚህ ድርጅቶች ጋር አስፈላጊና አመቺ በሆነ ወቅት ሁሉ በሰው ኃይል በትምህርት መሳሪያዎችና በገንዘብ ስንረዳዳ ነበር ከጥቂት ወራት በፊት እዚህ በርሚንጋም ውስጥ ለሚገኝ አንድ ድርጅት አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ቀጥተኛ ኃይል አልባ እርምጃ ላይ መሳተፍ አንደምንቸል ቃል በገባንለት መሠረት በመርሀ ግብሩ ላይ እንድንሳተፍ ጋበዘን እኛም ጥሪውን ተቀብለን ወቅቱ ሲደርስ የገባነውን ቃል አከበርን በዚህ ምከንያት ነው ከባልደረቦቼ ጋር እዚህ በርሚንጋም የተገኘሁት የተገኘሁት ተጋብዝዢ ነው መሠረታዊ ድርጅታዊ ትስስር ስላለን እዚህ አለን ለእኔ እዚህ መኖር ሌላኛው ምከንያት የፍትህ እዚህ አለመኖር ነው የአሥራ ስምንተኛው ክፍለ ዘመን ነብያት ትናንሸ መንደሮቻቸውን ለቀው ጌታ አንዲህ ይላልን ተሸከመው ድንበር ተሻግረው ይሰብኩ አንደነበር ሁሉ ሐዋሪያው ጳውሎስ የትውልድ መንደሩ ቴርሴስን ትቶ የኢየሱስ ከርስቶስን ወንጌል ተሸከሞ ወደ ግሪክና ሮማ መንደሮች እንደተጓዘ ሁሉ አኔም የነጻነት ወንጌልን ተሸክሜ ከምኖርበት ከተማ ውጭ ለመጓዝ ተገድጃለሁ ጳውሎስ ለሜቄዶኒያ ጥሪ ምላሽ መስጠት እንደነበረበት ሁሉ እኔም መልስ መስጠት ነበረብኝ በዚህ ላይ ደግሞ የአገሪቱ ግዛቶችና በውስጣቸው የሚኖሩ ህዝቦች አንዱ ካንዱ ጋር የተሳሠሩ መሆናቸውን በዚህ አጋጣሚ ላስታውሳቸሁ አፈልጋለሁ አትላንታ ተቀምጩ በርሚንጋም ውስጥ የሚከናወነው ነገር አይመለከተኝም ማለት አልችልም አንድ ቦታ ያለ ኢፍትሀዊነት የትም ሥፍራ ለሚገኝ ፍትሀዊነት ጠንቅ ነው ልንለያይ እንዳንቸል ተደርገን የጋራ በሆነ ግብ በአንድነት ተሳስረናል በአንደኛው ላይ ቀጥተኛ ተጽፅኖ ያለው ነገር በሌላኛው ላይ የአጅ አዙር ተጽዕኖ ይኖረዋል ከዚህ በኋላ የውጭ ሰዎች የሚለውን ጠባብ አመለካከት ይዘን የትም ልንደርስ አንቸልም በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የሚኖር ማንኛውም ዜጋ በየትኛውም የአገሪቱ ክፍል አንደ ባዕድ ወይም እንደ መጤ ሲቆጠር አይገባም በበርሚንጋም እየተደረጉ ያሉ ሰልፎችን ታወግዛለችሁ ይሁን እንጂ መግለጫችሁ የነዚህን ሰልፎች መንስኤ ባለማብራራቱ አዝኛለሁ የአንድን ነገር መንስኤ በአግባቡ ሳይተነትኑ በውጤታቸው ላይ ብቻ ከሚያተኩሩ የማህበራዊ ሳይንስ ተመራማሪዎች ተሸላችሁ እንደምትገኙ ተስፋ አደርጋለሁ ባሁኑ ሰዓት በርሚንጋም ውስጥ በርካታ ሰልፎች እየተደረጉ መሆናቸው የሚያሳዝን ነው ነገር ግን የነጮቹ የሥልጣን መዋቅር ለጥቁሮች ከዚህ የተሻለ ምርጫ ባለመተዉ የበለጠ አሳዛኝ መሆኑን አበከሬ ላስገነዝባችሁ አወዳለሁ በማንኛውም የኃይል አልባ ትግል ውስጥ አራት መሠረታዊ ደረጃዎች አሉ ፍትህ አለመኖሩን ለማረጋገጥ መረጃ ማሰባሰብ ችግር መኖሩ ከተረጋገጠ ችግሩን ለመፍታት ከሚመለከተው አካል ጋር መነጋገር ራስን ማጽዳትና ለትግል መዘጋጀት ቀጥተኛ እርምጃ መውሰድ ናቸው በበርሚንጋም ባካሄድነው ትግል በነዚህ ደረጃዎች ሁሉ ውስጥ አልፈናል ህዝባችንን በዘረኝነት ላይ የተመሠረተ ኢ ፍትሀዊነት እየዋጠው መሆኑን መካድ አይቻልም በርሚንጋም ምናልባትም ከዩናይትድ ስቴትስ ከተሞች ሁሉ የዘር ልዩነት ሥር የሰደደባት ከተማ ሳትሆን አትቀርም የፖሊሶቿ አስቀያሚ ከፋት በየትኛውም የአገሪቱ ከፍሎች ይታወቃል በፍቤቶች ጥቁሮች ጥላቻ በተሞላበት ሁኔታ ይስተናገዳሉ ከሁሉም የአገሪቱ ከተሞች በይበልጥ በርሚንጋም ውስጥ መፍትሄ ያጣው የጥቁሮች መኖሪያ ቤቶችና አብያተ ከርስቲያናት በቦምብ መጋየት ትኩረትን ይሻል አነዚህ በጭካኔ የተሞሉ ተግባራት እውነትና ግን ለማመን የሚያስቸግሩ ናቸው በነዚህ ሁኔታዎች ላይ የጥቁር መሪዎች ከከተማይቱ ባለሥልጣኖች ጋር ለመወያየት ፈልገው ነበር ሆኖም ግን የፖለቲካ መሪዎቿ አሻፈረን ብለዋል ከዚያ በኋላ ባለፈው መስከረም ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር ውይይት ለማድረግ ዕድል ተገኝቶ ነበር በዚህ ውይይት ላይ ነጋዴዎቹ አንዳንድ የማስተካከያ አርምጃዎችን እንደሚወስዱ ለምሳሌ በየንግድ ድርጅቶቻቸው ላይ የተለጠፉ አዋራጅና ዘረኛ ማስታወቂያዎችና ምልክቶችን እንደሚያነሱ ቃል ገብተው ነበር በስምምነቱ መሠረት ቄስ ሻትልዎርዝና ለሰው ልጆች መብት የአላባማ ከርስቲያናዊ ንቅናቄ ብ ርቪር ርም ብን ጽር መሪዎች አቅደዋቸው የነበሩ ሰላማዊ ሰልፎችን ሁሉ ለሌላ ጊዜ ለማስተላለፍ ተስማሙ ሳምንታትና ወራት አለፉ የተገባው ቃል ግን አልተፈጸመም ምልከቶቹ እንዳሉ አሉ አንዳለፉት ጊዜያት ሁሉ ከባዶ ተስፋ ጋር ተፋጥጠን ቀረን ጥቁር ጥላና ትልቅ ሀዘን ላያችን ላይ ወደቀ ስለዚህ ይህን ጉዳይ ለግዛቲቱና ለአገሪቱ ህዝብ የህሊና ዳኝነት ለማቅረብ አካላችንን ለአደጋ በማጋለጥ ቀጥተኛ እርምጃ ለመውሰድ ዝግጅት ከማድረግ ውጪ ሌላ አማራጭ አልነበረንም የሚገጥሙንን ችግሮች ሳንረዳ ቀርተን አይደለም ከዚያ በኋላ ራስን በማጽዳት ሂደት ውስጥ ለማለፍ ወሰንን በኃይል አልባ ትግል ስልት ላይ ሳናቋርጥ ልዩ ልዩ ዋርከሾፖችን አካሄድን አያጠቃህ ባለ ሰው ላይ መልሰህ ሳትሰነዝር ትግል መቀጠል ትቸላለህ። አነዚህ ፍትሀዊ ህጎችንና ኢፍትሀዊ ህጎችን አስመልከቶ ጥቂት ምሳሌዎች ናቸው አንዳንድ ህጎች ደግሞ ላይ ላዩን ፍትሀዊ መስለው ኢፍትሀዊ በሆነ መንገድ ሥራ ላይ ይውላሉ ለምሳሌ እኔ ዓርብ ዕለት የታሰርኩት ያለፈቃድ ሰልፍ በመውጣቴ ነበር ለሰልፍ ፈቃድ አንደሚያስፈልግ ህግ መኖሩ ችግር የለውም ይሁን እንጂ ህጉ የዘር ልዩነትን የሚያራዝም ከሆነና ህገ መንግሥቱን በመጣስ ዜጎች በሰላማዊ መንገድ የመሰብሰብና የመቃወም መብታቸውን የሚገድብ ከሆነ ኢፍትሀዊ ይሆናል ለማሳየት እየሞከርኩ ያለውን ልዩነት ትገነዘባላቸሁ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ በምንም መልኩ ዘረኝነትን እንደሚያራምዱ አብድ ነጮች ህጎች እንዲጣሱ አንፈልግም ይሄ ወደ ሥርዓተ አልበኝነት ይወስደናል ህግን የሚጥስ ሰው ኦርሊንስ ውስጥ በጥላቻ ተሞልተው በቴሌቪዥን ላይ ባሪያ ባሪያ ብለው ሲጮሁ እንደሜታዩት ነጭ እናቶች ሳይሆን በይፋና በፍቅር ሊያደርገው ይገባል በዚህ ምከንያት የሚመጣበትን ቅጣት ለመቀበልም ዝግጁ መሆን አለበት አንድ ሰው ህሊናው ኢ ፍትሃዊ መሆኑን የሚነግረውን ህግ ጥሶ በዚያ ምከንያት አሥር ቤት በመግባትና እዚያ በመቆየት ህጉ ኢፍትሀዊ መሆኑን ህዝቡ እንዲገነዘበው ማድረግ ከቻለ ያ ሰው ለህግ የሚገባውን ከበሬታ ሰጥቷል የሚል እምነት አለኝ እንዲህ ዓይነቱ ህግን አለመታዘዝ አዲስ አይደለም ቀደምት ከርስቲያኖች ሲድራቅ ሜሳቅና አብድናጎ ለናቡከደነጾር ህግ ባለመታዘዝ የሮማ ነገሥታትን ህግ ጥሰው የተራቡ አንበሶች ወዳሉበት ጉድጓድ ተጥለዋል ብዙ መከራም ተቀብለዋል ዛሬ ያለው የአካዳሚ ነጻነት በከፊል የተገኘው በሶቅራጥስ የተመራ ህዝብ ባካሄደው የአምቢተኝነት ትግል ነው ሂትለር በጀርመን ውስጥ የፈጸማቸው ድርጊቶች ሁሉ ህጋዊ ሲሆኑ ሀንጋሪ ውስጥ የሀንጋሪ ነጻነት ተዋጊዎች የፈጸሙት ነገር ሁሉ ደግሞ ህገ ወጥ እንደነበሩ ልንዘነጋ አይገባም በሂትለሯ ጀርመን አንድን አይሁዳዊ መርዳትም ሆነ ማጽናናት ወንጀል ነበር ያን ጊዜ ጀርመን ውስጥ ነዋሪ ብሆን ኖሮ ህገወጥ ቢሆን አንኳን አይሁዳውያን ወንድሞቼን አግዛቸው ነበር ዛሬ በአንድ የኮሚኒስት አገር የምኖር ቢሆንና የከርስትና መሠረታዊ ሥርዓቶች የሚከለከሉ ቢሆን ህዝቡ እነዚህን ፀረ ሃይማኖታዊ ህጎች እንዲጥሳቸው እቀሰቅስ ነበር ለከርስቲያኖችና አይሁዳውያን ወንድሞቼ ሁለት አውነታዎችን ልመሰከርላቸው አፈልጋለሁ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ለዘብተኛ አቋም ባላቸው ነጭ ወድሞቼ ላይ በአጅጉ አዝኛለሁ ጥቁሮች ወደ ነጻነት በሚያደርጉት ግስጋሴ ዋነኛ እንቅፋቶች የሆኑት የነጭ ዜጎች ምከር ቤት ወይም ኩ ከላከስ ከላነሮች ሳይሆኑ ሃቅ ወይም ፍትህን ወደ ጎን በመተው ለህግ ተገዥ የሆኑት ለዘብተኛ ነጮች ናቸው ለዘብተኛ ነጮች የሚፈልጉት ሰላምና ፍትህ የሰፈነበት ዘላቂ ሰላም ሳይሆን ውጥረት የሌለበት ጊዜያዊ ሰላም ነው ለዚህ ነው ግባችሁ ላይ እንስማማለን ቀጥተኛ እርምጃ የምትሉት የትግል ስልታቾቸሁን ግን አንቀበልም የሚሉት በሌላ ሰው ነጻነት ላይ ባለቤት በመሆን ዕቅድ ሊነድፉለት የሚችሉ መስሎ ይታያቸዋል ስለዚህ ጥቁሮችን ተስማሚ ጊዜ አስኪመጣ ድረስ እንዲታገሱ አበከረው ይመከራሉ አንድን ሃሳብ ፊት ለፊት ከሚቃወሙት ይልቅ እነዚህ በቀዘቀዘ ስሜት የሚቀበሉት ይበልጥ ያስቸግራሉ ከዚህ በፊት እንዲህ ዓይነት ረጅም ደብዳቤ ጽፌ አላውቅም ሰፊ ጊዜ ሳልወስድባችቸሁ አልቀረሁም በምቹ ጠረጴዛ ላይ ብጽፈው ኖሮ ምናልባት ከዚህ ሊያጥር ይችል ነበር በሌላ በኩል ደግሞ በትንሽ ከፍል ውስጥ ለብቻው ታስሮ ያለ ሰው ረጃጅም ደብዳቤ ከመጻፍ በሃሳብ ከመንጎድ እና ለረዥም ሰዓት ከመጸለይ ውጪ ምን ሊያደርግ ይቸላል። ፊን ዉይሃሮ ዖሬሥ ሲቃፇ ፖናሇ ፇ ፊይ የጓግሂዳጩሴዕሮ መፇግሥሦ ይያቃሪያ ይመሰሰሷ ረዖ ግ ያፆያታ ሐጭር ፖ ኣጋር ብላለች በአገራችን ታሪከ ውስጥ ትልቁ የነጻነት ሰልፍ ሆኖ በታሪከ በሚመዘገብ በዚህ ሰልፍ ላይ ከመሃላችሁ ለመገኘት በመቻሌ ደስ ብሎኛል ከመቶ ዓመታት በፊት ዛሬ በምስሉ ጥላ ሥር የተሰበሰብነው ትልቁ የአሜሪካ ዜጋ የነጻነት አዋጅን በፊርማው አጸደቀ ይህ ታሪካዊ ሰነድ በአዋራጅ የኢፍትሀዊነት ወላፈን አየተለበለቡ ላሉ በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ የአሜሪካ ባሪያዎች እንደ ትልቅ ተስፋ ተቆጥሮ ነበር በምርኮ ሥር የነበሩበት የጨለማ ዘመንም አንዳበቃለት ተቆጥሮ ነበር ነገር ግን ከመቶ ዓመታት በኋላ ኔግሮው ዛሬም ነጻ አይደለም ከመቶ ዓመታት በኋላ ዛሬም በዘር ልዩነትና መድልኦ ሰንሰለት ጉልበቱ ተሽመድምዷል ከመቶ ዓመታት በኋላ ዛሬም ሞልቶ በተረፈ የሀብት ውቅያኖስ መሀል በድህነት ደሴት ላይ ብቻውን ተገልሎ ይኖራል ከመቶ ዓመታት በኋላ ኔግሮው ዛሬም በገዛ አገሩ አሜሪካ ወደ ጥግ ተገፍቶ ባዕድ ሆኖ ህይወቱን ይገፋል ስለዚህ ዛሬ ወደዚህ ሥፍራ የመጣነው ይህን አሳፋሪ ሁኔታ ለማጋለጥ ነው ወደ አገራችን ታላቋ ከተማ የመጣነው የተሰጠንን ቼክ ወደ ገንዘብ ለመለወጥ ነው የሪኙኾብሊካችን መሀንዲሶች ህገ መንግሥቱንና የነጸነት አዋጁን በትላልቅ ቃላት ሲጽፉ ለአያንዳንዱ አሜሪካዊ ዜጋ የወደፊቱን የቃልኪዳን ሰነድ መፈረማቸው ነበር ይህ ሰነድ አሜሪካውያን ሁሉ ነጭም ሆነ ጥቁር በህይወት የመኖር የነጻነት እና ማንም የማይወስድባቸው ደስታን የመሻት መብት እንዳላቸው የተገባላቸው ቃልኪዳን ነው አሜሪካ ዛሬ ልዩ ልዩ ቀለም ያላቸው ህዝቦቿን አስመልክቶ የገባቸላቸውን ቃል ማጠፏን ማንም ያውቀዋል አሜሪካ ይህን የተከበረ ቃልኪዳን ሕ ከመጠበቅ ይልቅ በቂ ገንዘብ የለውም ተብሎ የተመለሰላቸውን ሀሰተኛ ቼከ ለኔግሮ ዜጎቿ ሰጥታለች እኛ ግን የፍትህ ባንከ ባዶ ነው የተባለውን አባባል አልተቀበልነውም በዚህ አገር የዕድል ግምጃ ቤት ውስጥ ምንም የለም የሚባለውንም ልንቀበል አንቸልም ስለዚህ ይህን ቼከ ልንመነዝር መጥተናል በፈለግነው ጊዜ ነጻነትና ፍትሀዊ ደህንነትን የሚያስገኝልንን ቼከ ወደዚህ የተቀደሰ ሥፍራ የመጣነው አሁን የምንገኝበት ጊዜ የጥድፊያ መሆኑን ለማስታወስ ነው ወንበር ላይ በጀርባ ተለጥጦ ለመቀናጣት እና በቀስታ ለመራመድ ጊዜ የለንም አሁን ለዲሞከራሲ የተገባልንን ቃል ዕውን የምናደርግበት ጊዜ ነው አሁን ከጨለማ ሸለቆና ከዘረኝነት ባዶነት ወጥተን ወደ ዘር አኩልነት ብርሃን የምንሸጋገርበት ወቅት ነው አሁን አገራችንን ከዘር ልዩነት ማጥ ውስጥ አውጥተን በማይናወጥ የወንድማማችነት አለት ላይ የምናኖርበት ጊዜ ነው አሁን ለአግዚአብሔር ልጆች ሁሉ ፍትህ ዕውን የሚሆንበት ጊዜ ነው አገራችን አሁን ያለንበት ሁኔታ አጣዳፊ መሆኑን አያወቀች በችልተኝነት ከተመለከተቸው አደጋው የከፋ ነው አንደ ቀትር እሳት የሚንበለበለው የኔግሮው ህጋዊ ጥያቄ በነጻነትና በእኩልነት ምላሽ እስኪበርድ አይቆምም አሥራ ዘጠኝ ስድሳ ሶስት መጀመሪያ እንጂ መጨረሻ አይደለም ጥቁሮች ጮከው ቁጣቸውን ካስታገሱ በኋላ ተረጋግተው ወደ ቀድሞው ይመለሳሉ ብለው ተስፋ የሚያደርጉ ካሉ አገሪቱ ወደ ነበረችበት ተመልሳ ብትገኝ ፍርሀት ይውጣቸዋል ጥቁሮች የዜግነት መብት እስኪያገኙ ድረስ አሜሪካ ውስጥ ዕረፍትም ሆነ መረጋጋት አይኖርም የፍትህ ብርሃን ፈንጥቆ አስኪወጣ ድረስ የአብዮቱ ማዕበል የዚህን አገር መሠረት ማናወጡን ይቀጥላል በፍትህ ቤተመንግሥት ደጃፍ ላይ ቆሞ ለሚገኘው ህዝቤ የምናገረው አለኝ የሚገባንን ሥፍራ የማግኘት መብታችንን በመጠየቅ ሂደት ውስጥ ወደ ስህተት ድርጊት አንዳናመራ መጠንቀቅ ይኖርብናል የነጻነት ጥማታችንን ከጥላቻና ምሬት ዋንጫ ውስጥ በመጠጣት ልንረካ አይገባም ትግላችንን ምንዜም ከፍ ባለ የስነ ምግባርና የተከበረ ሜዳ ላይ ማከናወን አለብን በአዲስ መልከ የሚካሄደው ተቃውሞአችን በአካል ወደ መጋጨት አንዲዘቅጥ መፍቀድ አይኖርብንም መልሰን መላልሰን አካላዊ ኃይልን በመንፈሳዊ ኃይል ወደምንጋፈጥበት ከቡር ተራራ መውጣት አለብን በጥቁሮች መካከል የተቀጣጠለው መነሳሳት ሁሉንም ነጮች ወደ አለማመን ሊመራን አይገባም ዛሬ ከአኛ ጋር አዚህ በመገኘታቸው እንደተረጋገጠው በርካታ ነጭ ወንድሞቻችን መጻኢ ዕድላቸው ከኛ መጻኢ ዕድል ጋር የተያያዘ መሆኑን ተረድተዋል ነጻነታቸውም ከነጻነታችን ጋር አንደሚያያዝ አውቀዋል ስለዚህ በኢፍትሀዊነት ላይ በጋራ የምናደርገው ጦርነት ከሁለቱም ዘሮች በተውጣጡ ወታደሮች መካሄድ አለበት ለየብቻቸን መራመድ አንቸልም ጉዞአችንን ለማፋጠን ቃል መግባት ይኖርብናል ወደ ኋላ ልንመለስ አንቸልም አንዳንድ ሰዎች የሲቪል መብት ተሟጋቾችን ለመሆኑ የምትረኩት መቼ ነው። በሚለው መዝገብ ላይ አይገኝም ይሁን አንጂ ይህ ጊዜ አልፎ አሁን እየኖርንበት ባለንበት ዘመን ላይ አውነተኛ ብርሃን ሲበራ መልካም አገር ኑሮው የተሻሻለ ህዝብ እና አየኖርንበት ያለው ከፍ ያለ ሥልጣኔ የተገኘው ለሃቅ ሲሉ ራሳቸውን ለሰው መስዋዕት ባደረጉ የእግዚአብሔር ልጆች መሆኑን ትልቅ ትንሹ ይረዳዋል ህጻናቶቻችንም ይማሩታል ይህንን ሽልማት የምቀበለው አንድ ውድ የሆነን ፅቃ ባለቤቱ እስኪመጣ ድረስ ለመጠበቅ በአደራ አንደተረከበ ሰው ነው ስል ምን ማለቴ አንደሆነ አልፍሬድ ኖቤል ይረዱታል ብዬ አስባለሁ የዚህ ሽልማት ባለቤቶች ውበት ማለት እውነት ነው አውነት ማለትም ውበት ነው ያሉ እንዲሁም የእውነተኛ ወንድማማችነትና ሰላም ውበት ከአልማዝ ከብርና ከወርቅ ውበት የሚበልጥ መሆኑን አምነው የተቀበሉ ህዝቦች ናቸው ከአላባማ ሞንትጎመሪ ወደ ኦስሎ የሚወስደው ጠመዝማዛ መንገድ ለዚህ አውነት ማስረጃ ይሆናል ይህ መንገድ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኔግሮዎች ከብራቸውን ለማስመለስ የተጓዘበት ነው ይኸው መንገድ ለመላው አሜሪካውያን የዕድገትና የአዲስ ተስፋ ዘመን ከፍቷል አዲስ የሲቪል መብቶች ህግም አስገኝቷል ኔነግሮዎችና ነጮች የጋራ ችግራቸውን ለመፍታት እጅ ለእጅ በተያያዙ መጠን መንገዱ ወደ ትልቅ የፍትህ ጎዳና አየሰፋም እየረዘመም ይሄዳል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ ዛሬ ይህን ሽልማት የምቀበለው በአሜሪካና በሰው ልጅ መጻኢ ጊዜ ላይ ትልቅ ተስፋ በመጣል ነው የዛሬው የሰው ማንነት ነገ ሊደርስበት አሚፈልገው ታላቅ ማንነቱ ዘንድ እንዳይደርስ ያደርገዋል የሚለውን አስተሳሰብ እኔ አልቀበልም የሰው ልጅ በአካባቢው በሚገኘው የህይወት ባህር ላይ የሚንሳፈፍ ስብርባሪ ዕቃ ነው የሚለውን ሃሳብም አልጋራም እኔ በበኩሌ የሰው ልጅ በሚያሳዝን መልኩ የሰላምና የወንድማማችነት ብርሃን ፈጽሞ ዕውን ሊሆን የማይቸልበት የዘረኝነትና የጦርነት ድቅድቅ ጨለማ ነው በሚለው አስተሳሰብም አልስማማም አገሮች ሁሉ እየተከታተሉ አስከ ኒውክሌር እሳት አልቂት ድረስ ሄደው ከዚያ የጦረኝነትን ቁልቁለት መያያዝ አለባቸው ብዬም አላምንም መሳሪያን መከታ ያላደረገ አውነት እና ቅድመ ሁኔታ የሌለው ፍቅር አሁን ባለው ሁኔታ ውስጥ ወሳኝ መሆናቸውን አምናለሁ ለዚህ ነው ለጊዜው የተረታች ፍትህ ድል ካደረገ ክፋት ይልቅ ኃያል የምትሆነው ዛሬም ቢሆን በሞርታር ድምፅና በጥይት ጩኸት መካከል ተቀምጠን ብሩህ ተስፋ እንመለከታለን ቆስላ በደሟ በተበከሱ ጎዳናዎች ላይ በአፍጢሟ ተደፍታ ያለችው ፍትህ ከውርደት ትቢያ ላይ ቀና ተደርጋ በሰዎች መካከል በከብር ትነግሳለች ብዬ አምናለሁ የትም ቦታ ያለ ህዝብ ለአካሉ ሶስት ጊዜ ምግብ ለአዕምሮው ትምህርትና ባህል እንዲሁም ለመንፈሱ ደግሞ ክከብር አኩልነትና ነጻነት ማግኘት እንዳለበት በድፍረት እናገራለሁ ራስ ወዳድ ግለሰቦች ያፈረሱትን አሴት ከራሳቸው አልፈው ስለሌላ የሚያስቡ ዜጎች ደግሞ መልሰው መገንባት ይችላሉ ብዬ አምናለሁ የሰው ልጅ አንድ ቀን በጦርነትና ደም በማፍሰስ ላይ ድልን ተቀዳጅቶ በአምላኩ የመስዋዕት ሥፍራ ተንበርከኮ በራሱ ላይ አከሊል ደፍቶ ይሸለማል ብዬ አሁንም አምናለሁ ያን ቀን አንበሳና የበግ ጠቦት አብረው ይተኛሉ እያንዳንዱ ሰውም በራሱ የወይን ዛፍ ሥር ይቀመጣል የሚያስፈራውም የለም አንዲል መጽሐፉ አሁንም እናሸንፋለን ብዬ አምናለሁ ይህ እምነት ከፊታችን ያለውን የማይታወቅ መጻኢ ጊዜ በተስፋ ለመቀበል ጥንካሬ ይሰጠናል ጉዚችንን ወደ ነጻነት ከተማ ስንቀጥል ለደከመው ጉልበታችን ብርታት ይሆነናል ቀናችን አታካች ደመና ሲሆንብንና ሌታችን ከሺህ ዓመታት ጽልመት ሲበልጥብን እውነተኛ ሥልጣኔ ሊወለድ አየተፍጨረጨረ መሆኑን እንገነዘባለን ዛሬ ወደ ኦስሎ የመጣሁት አደራ እንደሚቀበል ሰው ለሰብዓዊነት ለመሥራት በታደሰ ተነሳሸነትና ቁርጠኝነት ነው ሽልማቱን የምቀበለው ሰላምና ወንድማማችነትን በሚወዱ ሰዎች ሁሉ ስም ነው ከፍል ሶስት የህልሙ መራዘም ለተሰዉ ህጻናት መታሰቢያ ዕኔፊ ያዎሸፖ ፅሐፍ ዕሴምሦ ደሥ ዕኃ ዝም ፈይቆዕ ሪ መጎ ዕሃሪኝኦ ለሐራሟደፇፖ ዕጋሼታ ፇሰፈም ዖያዓፈም ሦራሜቻሯ ቻ ያሪይወቻ ኖሮ ይነ ፇ ያረረውጋ ያዕያውቃ ጥረ ለሜሪካዊ ምሥረ ዶር ዊሏያም ቶያዮዎ። አሁን ወደ ፊት እየገሰገስን ነው አዎን በህብረት ተነስተናል ምንም ዓይነት ዘረኛ ማዕበል ሊገታን አይቸልም እየተጓዝን ነው ዛሬ ጉዞ ላይ ነን ቤተ ከርስቲያኖቻቸንን ማቃጠል ወደ ኋላ ሊመልሰን አይቸልም አሁን ተነስተናል መኖሪያ ቤቶቻችን ላይ ቦምብ መወርወር ተስፋ አያስቆርጠንም አዎ ዛሬ ጉዞ ላይ ነን የሃይማኖት መሪዎችንና ወጣቶቻችንን መደብደብ ከመንገዳችን ዝንፍ አያደርገንም ጉዞ ላይ ነን ዛሬ ገዳዮቻችንን ለጊዜው አስሮ መልቀቅ ወደ ኋላ አይመልሰንም ዛሬ ጉዞ ላይ ነን ጊዜው እንደደረሰ አስተሳሰብ ሁሉ ምንም ያህል ሠራዊት ሊያቆመን አይቸልም ወደ ነጻዩቱ አገር እየተጓዝን ነው ስለዚህ የአሜሪካን ህልም ዕውን ወደ ማድረግ ጉዞአችንን ተግተን አንቀጥል በተገለሉ መንደሮች ያለው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ድንዛዜ ተወግዶ ኔግሮዎችና ነጮች ጽዱና ምቹ በሆኑ ቤቶች ውስጥ ጎን ለጎን መኖር እስኪችሉ ድረስ በዘር በተከፋፈሉ ቤቶች ላይ ሰልፍ ማካሄዳችንን አንቀጥል ጥራት የሌለው ትምህርት ተወግዶ የዘር ከፍፍል ቁስል ሽሮ ኔግሮና ነጭ ያለፈውን ማህበራዊ ስብራት በሚጠግኑ መማሪያ ከፍሎች ውስጥ ጎን ለጎን ተቀምጠው መማር አስኪችሉ ድረስ በትምህርት ቤቶች ላይ መሰለፋችንን እንቀጥል ማንኛውም አሜሪካዊ ቤተሰብ ልጆቹን ለመመገብ ራሱ ጦም ማደሩን እስኪያቆም ድረስና የማይገኝ ሥራ ለመፈለግ መንገድ ላይ የሚንከላወስ የተራበ ሰው አስኪታጣ ድረስ በድህነት ላይ እንሰለፍ የዘረኝነት ወጥመድ ከፖለቲካ ሜዳ ላይ ተጠርጎ አስኪጠፋ ድረስ ለምርጫ ኮሮጆ እንሰለፍ የአገራችን ዋላሶች በዝምታ ከሥልጣን ገለል እስኪሉ ድረስ በኮሮጆ ላይ ሰልፋችንን እንቀጥል በከተማ ምክር ቤቶች ውስጥ በከልል ምቤቶች ውስጥ እንዲሁም በዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ውስጥ በሐቅ ለመሥራት የማይፈሩ ርህሩህና ፈሪሀ እግዚአብሔር ያላቸው ሰዎችን መርጠን መላክ እስክንቸል ድረስ ለምርጫ ኮሮጆ ሰልፋችንን አናቁም በመላው አላባማ የሚኖሩ የእግዚአብሔር ልጆች ሁሉ ሳይሸማቀቁ አንገታቸውን ቀና አድርገው በከብር መሄድ እስኪችሉ ድረስ ለምርጫ ኮሮጆ እንሰለፍ ጦርነት ውስጥ ነን ከፊታቸን ያለው መንገድ አልጋ ባልጋ አይደለም በቀላሉ በእርግጠኝነት ወደ መፍትሄው የሚወስደን ሰፊ መንገድ የለም ስለዚህ ጉዞአችንን ልንቀጥል ይገባል ህዝቤ ሆይ ስማኝ ህዝቤ ሆይ ስማኝ ህዝቤ ሆይ አድምጠኝ ጦርነቱ በኛ እጅ ነው ጦርነቱ በሚሲሲፒና አላባማ አንዲሁም በመላው ዩናይትድ ስቴትስ አጃችን ውስጥ ነው ዛሬ ምሸት ከዚህ ስንወጣ ከምን ጊዜውም የበለጠ ስለ ትግልና ስለ ሰላማዊ ትግል ስልት ቁርጠኛ ሆነን አንውጣ አሁንም ችግሮች ከፊታችን ተጋርጠው እንዳሉ ላስገነዝባችሁ እፈልጋለሁ በአብዛኛው የአላባማ ጥቁር ቀበቶ አካባቢዎች በብዙ የሚሲሲፒ ከፍሎች በበርካታ የሉዚያና ሥፍራዎች ትላልቅ ችግሮች ይጠብቁናል አሁንም ብዙ እሥር ቤቶች አፋቸውን ከፍተው አየጠበቁን ነው ከፉ የጨለማ ጊዜያት ከፊታችን እንዳሉ እገነዘባለሁ ይሁን እንጂ ኃይል አልባ የትግል ስልታችን የትናንቱን ጨለማ ወደ ነገው ብርሃን ይለውጠዋል በሚል እምነት ወደ ፊት እንጓዛለን አሁን ያለውን ሁኔታ በሙሉ መለወጥ እንትላለን ዓላማችን የነጩን ማህበረሰብ ማሸነፍና ማዋረድ አይደለም ይልቁንስ ማስገንዘብና ለመወዳጀት እንጂ መጨረሻ ላይ ማየት የምንፈልገው ከራሱ ጋር ሰላም ያለው ህዝብ ከህሊናው ጋር የሚኖር ማህበረሰብ ነው ይሄ ምን ያህል ጊዜ ይፈጃል ብላችሁ ዛሬ እንደምትጠይቁኝ አውቃለሁ እኔ ደግሞ እንዲህ አላችኋለሁፁ ዘመኑ ምን ያህል ከባድ ቢሆንም ጊዜው ምን ያህል አስፈሪ ቢሆንም ሩቅ አይደለም መሬት ላይ የተረገጠች ፍትህ መልሳ ቀና ማለቷ አይቀርም መቼ። ስለ ኃይል ትግል ብዙ ተሰምቷል ባለፉት አሥር ዓመታት በኃይል አልባ የትግል ስልት ላይም ብዙ ተብሏል ነገሩ የፈሪዎች ንግግር ነው እነዚህ ሰዎች ከተነካን ወይም ጥቃት ከደረሰብን መታገስ ስለማንችል ኃይል አልባ የትግል ስልትን ልንቀላቀል አንቸልም ይላሉ ዛሬ ሁኔታዎች ተቀይረው ስለ ኃይል ትግል ብዙ እየተወራ ያለ ቢሆንም በተግባር የታየ አንዳች ነገር ግን አልነበረም በቅርቡ ታትሞ በወጣው ኒው ዮርከር ጋዜጣ ላይ አንድ ሪፖርተር እንደገለጸው የእነቤክዊዝ ፕሪስ ሬኒ እና ኮሊ ሌሮይ ዊልከንስ በህይወት መኖር ኔግሮ አሁንም ኃይልን እንደ ትግል ስልት እየተጠቀመ አለመሆኑን ያረጋግጣል ይህ በቂ ማረጋገጫ ካልሆነ በቅርቡ በሁከት ውስጥ የተጎዱ ሰዎችን ቁጥር ብንመለከት ከሟቾቹ አብዛኞቹ ጥቁሮች መሆናቸውን እንገነዘባለን በሎስ አንጀለስ የፍጥነት መንገዶች ላይ እንኳን አንዳች ጉዳት አንዳልደረሰ መረጃዎች ያመለከታሉ ያ የቴከሳስ ዩኒቨርሲቲው ነጭ እብድ ወጣት አንድ የቆረጠ ሰው ምን ያህል ጉዳት ሊያደርስ አንደሚችል አሳይቶናል ይህ ወጣት ተማሪ በአንዲት ቀን ጀንበር የገደላቸው ሰዎች ቁጥር ሀርለም ውስጥ በ ብጥብጥ ከተነሳ ጊዜ ጀምሮ በሁሉም ከተሞች በሁሉም ሁከቶች ጥቁሮች ከገደሏቸው ሰዎች ቁጥር ይበልጣል ይኹ ጥቁሮች በኃይል ትግል ላይ ባላቸው አመለካከት ላይ ትልቅ ጥያቄ ያስነሳል በአጠቃላይ ምንም ያህል ቢማረር ኔግሮ ለነጻነቱ ሲል ነጭ መግደል አይፈልግም ይህ ማለት ኔግሮው የኃይል ተግባርን የሚጠየፍ መልአከ ነው ለማለት አይደለም እንዳለመታደል ሆኖ ቅዳሜ ምሸት የኔግሮ ማህበረሰብ ሆስፒታሎችን ተዘዋውሮ የተመለከተ ሰው በኔግሮው ማህበረሰብ ውስጥ ምን ያህል ሁከት እንዳለ ይገነዘባል በጥይት ተመትተው አሊያም በስለት ተወግተው በደም የተጨማለቁ በመቶ የሚቆጠሩ ጉዳተኞችን ማየት የተለመደ ሲሆን በጥቁሮች ጉዳት የደረሰባቸው ነጮች ግን አይገኙም በሰሜን በሚገኙ የድሀ መንደሮች ውስጥ የሚኖሩ ሰዎችን አግኝቼ ለማነጋገር ችያለሁ አነዚህ ሰዎች ኃይል መጠቀም እንዳለባቸው አበከረው ይናገራሉ ነገር ግን በችካጎ በተነሳ ብጥብጥ ውስጥ አንዳቸውንም አላየሁም በሀርለም ጎዳናዎችና ቺካጎ በሚገኘው ዋሸንግተን ፓርከ የምሬት ስብከቶችና የጥላቻ ንግግሮችን ሰምቻለሁ ነገር ግን አንዳቸውም ሁከት ወደ ማስነሳት አልተሸጋገሩም አስካሁን ድረስ ከፍርሀት ወይም ከጥላቻ የተነሳ ህዝቡን ወደ ብጥብጥ አየመራ ያለው ፖሊስ ነው አንዴ ሁከት ከተነሳ ሊቆም የሚችለው በፖሊስና በፌደራል የጸጥታ ኃይሎች ብቻ ነው ይህም ሁከቶቹ ያልታቀዱና ከቁጥጥር ውጭ መሆናቸውን መነሻቸው ደግሞ ለዘመናት የተጠራቀመ ምሬት ድህነት ውርደት ጭቆናና ብዝበዛ መሆኑን ያመለከታል ማህበራዊ ለውጥ ለማምጣት ኃይልን እንደ አማራጭ የትግል ስልት የሚጠቀም ቡድን አሜሪካ ውስጥ የለም ቁጣና ጩኸት ሁሉ እርባና አንደሌለው የፈሪዎች ድርጊት ይቆጠራል ከሞራላዊነትም ሆነ ከተግባራዊ ምከንያቶች አንጻር ህዝባችንን ወደ ነጻነት ሊወስድ የሚችለው ኃይል አልባ ትግል ብቻ ነው በኃይል ትግል ውስጥ ብዙ ጉዳት ሊያጋጥም እንደሚችል ተገንዝቦ መዘጋጀት ያስፈልጋል በቬትናም ጦርነት ውስጥ ዩናይትድ ስቴትስ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ለማረድ ሁለት መቶ ሺህ ያህል ዜጎቿንና በዓመት ሃያ ቢሊዮን ዶላር መስዋዕት ለማድረግ ቆርጣ ወደ ጦርነቱ ገባች ይህ ሁሉ አሥራ አራት ሚሊዮን ቬትናማውያንን ነጻነት ለማጎናጸፍ ነው በሚል ነበር ጦርነቱ የሚካሄደው በኤስያ ምድር አብዛኛው ኤስያዊ በሚኖርበት ቦታ ነበር። ስለዚህ ጦርነት ማካሄድ የሚፈልግ ሁሉ አንዲህ ዓይነት ጥናቶችን ማካሄድ አለበት አንድ በቁጥር አናሳ የሆነ ህዝብ ብዙሀኑንና እስከ አፍንጫው የታጠቀን ሀብታም ህዝብ የነጮች የበላይነትና የምፅራብ ቁሳዊነት አደጋ ላይ የወደቀ ከመሰለው የጥቁርን ህዝብ ድራሽ ለማጥፋት አይናቸውን የማያሹ አከራሪዎች ከሞሉበት ማህበረሰብ ጋር ሲዋጋ ሊደርስበት የሚቸለውን አደጋ ከወዲሁ መገመት ይገባዋል የአሜሪካ ኔግሮ የሚሆኑ ልዩ ልዩ ቀለም ያላቸው ህዝቦች የሚኖሩባት ዓለም አካል በመሆኑ እነዚህ ህዝቦች በጋራ ሆነው የነጮችን የጭቆና ቀንበር መስበር ይችላሉ የሚለው አስተሳሰብ ቢያንስ በመጪዎቹ ሀምሳ ዓመታት ዕውን የሚሆን አይደለም የተለየ ቀለም ካላቸው ህዝቦች መካከል ቻይናን ጨምሮ ለጊዜው ዓለም ሊሰማ የሚችለውን አብዮት ማካሄድ የሚቸል የለም ጋና ዛምቢያ ታንዛንያ እና ናይጄሪያ ከድህነት ከማይምነትና ኒዮኮሎኒያሊዝም ካመጣው ተጽዕኖ ጋር አየታገሉ ስለሆነ ለአሜሪካ ኔግሮ ይቅርና ለአንጎላ ለሮዴዥያ እና ደቡብ አፍሪካ አንኳን ተስፋ መሆን አልቻሉም የዛሬው እውነታ የሚያመለከተው ተስፋ የሌላቸው የዓለም ህዝቦች ተስፋቸውን የጣሉት በአሜሪካ ኔግሮና የኢምፔሪያሊዝምን ዘረኛ መዋቅር ለውጦ የምዕራቡን ሀብትና ቴከኖሎጂ ድህነትን ለማጥፋት በመጠቀም አቅሙ ላይ ነው ለነጻነት ያለንን ፍቅር በማውራትና ለፍልስፍና ክርክሮች የምናባከነው ጊዜ የለንም ይህ ወቅት የሥራ ጊዜ ነው አሁን የሚስፈልገው ለውጥ ሊያመጣ የሚችል ስትራቴጂና ኔግሮውን ወደ መደበኛው የአሜሪካ አኗኗር በአስቸኳይ የሚያመጣ ዕቅድ መንደፍ ነው አስካሁን ይህን አያደረገ ያለው የኃይል አልባ አንቅስቃሴ ነው በኃይል አልባ ትግል ስልት ያገኘነው ውጤት በጣም ከፍተኛ ነው በደቡብ ውስጥ የሜታየው አስገራሚ ማህበረሰባዊ ለውጥ በታሪክ ውስጥ ተወዳዳሪ የማይገኝለት ነው በሞንትጎመሪ አልባኒ በበርሚንጋም እና በሴልማ የተወሰዱት አርምጃዎች ለላቀ ለውጥ መንገድ ከፍተዋል አነዚህ ለውጦች በአነስተኛ የሀብትና የህይወት መስዋዕትነት መገኘታቸው ደግሞ የበለጠ አስገራሚ ነው ባካሄድናቸው ሰላማዊ ሰልፎች ውስጥ የአንድም ሰው ህይወት አላለፈም አሥራ ስድስተኛ መንገድ ላይ በምትገኘው የመጥምቃውያን ቤተከርስቲያን ላይ ቦምብ የተወረወረው ሰልፎች ከቆሙ ከብዙ ወራት በኋላ ነበር ቄስ ጀምስ ሪብ ወሮ ቫዮላ ሊውዞ እና ጂሚሊ ጀካስን የተገደሉት በሌሊት ሲሆን ሰልፎች ከተካሄዱ በኋላ ነበር በመላው ደቡብ በአሥር ዓመታት ውስጥ ከተገደሉት ሰዎች ቁጥር ይልቅ ዋትስ ውስጥ በሶስት ቀናት ሁከት ብቻ የተገደሉት ሰዎች ቁጥር ይበልጣል ጋንዲ ህንድን ነጻ ለማውጣት ባደረገው ትግል ውስጥ ወይም የትኛውም የአሜሪካ አገር ባደረገው የተጻነት ተጋድሎ ውስጥ ብዙ መስዋዕት ሳይከፈልበት እንደዚህ ዓይነት ለውጥ ተመዝግቦ አያውቅም ራስን የመከላከል ጥያቄ ራስን ስለ መከላከል አስፈላጊነት አጥብቀው ከልባቸው የሚያነሱ ሰዎች አንዳሉ አናውቃለን ይህ በበጎ ጎኑ መታየት አለበት ሰዎች ራሳቸውን ከጥቃት መከላከል አንዳለባቸው አያጠያይቅም ይህ መብት በህገ መንግሥታችን ከመረጋገጡም በላይ በአስቸጋሪው ደቡቡ ያገራችን ክፍል እንኳን የተከበረ መብት ነው ነገር ግን ራሳቸንንና ቤታችንን ከሌሊት ዘራፊዎች ለመከላከል ያለን መብት ሁከት እንዳይነሳ የማድረግ ስልት አይደለም ህግ የማውጣት ዕቅድ መኖር አለበት ጆርጅያ ውስጥ በሳቫና ማኮን እንደ ታዘብነው ኔግሮችን ለመራጭነት መመዝገብ ከዘረኛ ነጭ የፖሊስ መኮንኖች የበለጠ ህግን ማስከበር ከመቻል አልፎ ለኔግሮውም ከብር እንደመስጠት ነው በሰላማዊ ትግል ስልት ውስጥ ራስን የመከላከል ዘዴ በተለየ አቅጣጫ መታየት አለበት ሰልፍ የሚደረገው ባንድ ሥፍራ በደልና ጭቆና በመኖሩ ደፋርና ቅን አመለካከት ያላቸው ሰዎች ተባብረው ለመቃወም እንደ ሆነ ሁሉም ሊገነዘብ ይገባል ለምሳሌ ያህል ትምህርት ቤቶች በዘር ተለይተው መመደባቸውን ተቃውመን ሰልፍ የምንወጣው አኩል የትምህርት ዕድል ማጣት ዕለት ተለት የህጻናትን አዕምሮ እንደሚያደከም ስለምናውቅ ነው ስለዚህ ሰልፍ የሚወጡ ሰዎች ለአጭር ጊዜ የሚመጣባቸውን ችግር ተቋቁመው መጭው ትውልድ መሀይምነት ውስጥ ወድቆ ከሚቀር ለአጭር ጊዜ ራሳቸውን በአደባባይ ለመከራ ዳርገው መጋፈጥን ስለሚመርጡ ነው። የሞራል ልፅልና ስናጣ አገሪቱ የህዝብ ብዛት አንጻር ወዳለን አንድ አስረኛ ኃይል ዝቅ እንላለን ይህ ደግሞ በማህበረሰባችን ውስጥ እንኳን ትርጉም ያለው ለውጥ ለማመጣት አያስችለንም ኢኮኖሚውን የሚቆጣጠረው ሥልጣን ያለው መዋቅር ሰለሆነ የገንዘብ መተላለፊያ መንገድ ከተዘጋ ልማት ይደናቀፋል ባለፉት ሶስት ዓመታት ቁርጠኝነትና ሞራል ያለው አናሳ ህዝብ አገር ለመምራት ያለውን አቅም አይተናል በዘመነኛው ሊብራል አስተሳሰብ የበርሚንጋሙ ንቅናቄ አብያተ ከርስቲያናትን ሠራተኞችንና የአካዳሚውን ማህበረሰብ አንድ ላይ አገናኝቷቸዋል በኮንግረስ የተላለፉ ሊብራል ህጎች ሁሉ ሊጸድቁ የቻሉት በነሱ ምከንያት ነው በሁሉም ሥፍራ የተከናወኑት ሰላማዊ አንቅስቃሴዎችና የቬትናምን ጦርነት አስመልከቶ በሁሉም ግቢዎች ውሰጥ የተደረጉት ተቃውሞዎች መነሻቸው በኔግሮች የተመራው ኃይል አልባ አንቅስቃሴ ነው ከበርሚንጋም በፊት በማካርቲ ዘመን በተደረገው ድርጊት ምክንያት በፍርሃት ውስጥ ነበሩ ኮንግረሱ ደግሞ ዓመቱን በሙሉ በደቡቡ ዲሞከራቶችና በማዕከላዊ ምሥራቅ ሪፐብሊካኖች ሲታመስ ነበር ነገር ግን ኔግሮዎች አገሪቱ ወደ አወነተኛ ጠላቶቿ ማለትም ወደ ድህነት ወደ ጎስቋላ መንደሮችና ብቃት ወደሌለው ትምህርት ሥርዓት ፊቷን አንድትመልስ አድርገዋል የወደፊት አቅጣጫዎች ኔግሮዎች ሰልፍ የወጡ ዕለት ሁሉም አብሮአቸው አደባባይ ወጣ በኃይል አልባ ሰልፍ ውሰጥ ያለ እምቅ ጉልበት እንዴት አስገራሚ ነው ጥቂት መቶ ኔግሮዎች ሰልፍ ወጥተው በመላ አገሪቱ እንዲህ ያለ ምላሽ መገኘቱ ያስገርማል ተለይተው በታወቁ ጉዳዮች ላይ በጥንቃቄ የሚዘጋጅ ሰላማዊ ሰልፍ ቪከተር ሁጎ በዓለም ላይ ሃያል ብሎ የሰየመውን ሊያመለክት ይችላል በሱ አባባል ወቅቱ የደረሰን ጉዳይ ያህል ኃያል የለም እግር ሁሉ ለሰልፍ ሲወጣ አንድ ጉዳይ ጊዜው የደረሰ መሆኑን ያመለከታል ያ ጉዳይ ተቀባይነት ካገኘ መነሻው ፍትሀዊ ከሆነ ከኃይል የጸዳ ከሆነ ለውጥ ይመጣል ነገር ግን ከነዚህ አንዱ እንኳን ቢጓደል የለውጡ ኃይል የተሟላ አይሆንም ሄሮይን የመጠቀም መብት ለመጠየቅ ሺህ ስዎች ቢሰለፉ የሚያመጣው ተጽዕኖ ጥቂት ነው በተመሳሳይ አሥር ሺህ ሰዎች በቁጣ ገንፍለው አካባቢያቸው በሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ ላይ ሰልፍ በመውጣት አዛን ሲራገሙ ቢውሉ ተወዳጅ ከብር ያለውና ወገናዊ ያልሆነ ህግ አሰከባሪ ለማደራጀት ያለው አሰተዋጽኦ በጣም አነስተኛ ነው እንዲህ ዓይነት ሰልፍ ፍርሀትን በመፍጠር ተጨማሪ ኃይል ወደ ጣቢያው አንዲላከና የበለጠ እርምጃ አንዲወሰድ ከመገፋፋት የዘለለ ውጤት አያመጣም ወደፊትም ቢሆን መሰለፋችንን ልንቀጥል ይገባል ነገር ግን ስልፎቻችን ውጤታማ ሊሆኑ ይገባል ይሁን እንጂ ሰላማዊ ሰልፍ በአንድ ጊዜ ውጤት የሚያስገኝ አይደለም በማናቸውም መስከ በአንዴ የሚገኝ ሰኬት በጣም አናሳ ነው ወዳጄ ኬኔት ከላርከ ዳርከ ጌቶ በተባለው ጽሁፉ ውሰጥ እንደጠቀሰው እንዲህ ዓይነት ሰልፍ የታመቀን ቁጣ ለማብረድና ለለውጥ የሚያሰፈልገውን ኃይል ማባከን ነው ይሁን እንጂ ሰልፎችን ከፋትን ለማጋለጥ ቅኖችን ለማደፋፈርና ለማነሳሳት የለውጥ ኃይሎችን ለማንቀሳቀስ ከተጠቀምንባቸው ውጤታማ ይሆናሉ በተመከሮአችን መሠረት ከልምድ እንዳየነው ሰላማዊ ሰልፍ ውጤት እንዲያስገኝ ከተፈለገ ከሰላሳ አስከ አርባ አምስት ቀን መወጣትን ይጠይቃል ሥልጣን ላይ ያሉ ኃይሎችን ዕረፍት ለመንሳት የሰልፈኛው ቁጥር መበራከት አለበት ይህ ካልሆነ ትኩረት ሳያገኝ ያልፋል ይህ ማለት የመገናኛ ብዙሀንን ሽፋን ማግኘት አለበት ማለት ነው ለጉዳዩ ትርጉም የሚሰጡት ለህዝብ የሚገልጹት እንዲሁም የሚመለከተውን ከፍል ለለውጥ የሚገፋፉት እነሱ ናቸው ከሰላማዊ ሰልፍ በተጨማሪ ሌላኛው የኃይል አልባ የትግል መሣሪያ ዕቀባ ነው የኃይል አልባ ትግል ፍልስፍና መሠረቱ ከከፉ ድርጊት ጋር ያለመተባበር ነው በማህብረሰባችን ውሰጥ ክፉ ድርጊትን ከሚያራዝሙ ኃይሎችና ተቋማት ጋር በኢኮኖሚ ያለመተባበርን የመሰለ ውጤታማ ዘዴ የለም ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ የሺካጎ አገልጋዮች በደቡብ ከርስቲያናዊ አመራር ምቤት መሪነት የምግብ ቅርጫት በተሰኘ ዘመቻ አማካይነት በሁሉም የሥራ መስኮች ኔግሮዎችን በብቃት ከማይቀጥሩ ኩባንያዎች ላይ ምንም ባለመግዛት አድማ የኔግሮን ዓመታዊ ገቢ በሁለት ሚሊዮን ዶላር አንዲጨምር ለማድረግ ችለዋል። በማለት ይጠይቁኝ ነበር ይህን ስሰማ ስጋታቸውን ብረዳም እነዚህ ጠያቂዎች አኔንም ቁርጠኝነቴንም ጥሪዬንም መረዳት አለመቻላቸው ያሳዝነኛልራፊ በርግጥ የሚያነሷቸው ጥያቄዎች የሚኖሩበትን ዓለም ያለማወቃቸውን ያሳብቅባቸዋል አንዱ ሌላውን መረዳት በማይችልበት በዚህ ዓይነት ሁኔታ ውስጥ የመጋቢነት ሥራዬን የጀመርኩበት አላባማ የምትገኘው የሞንትጎመሪ መጥምቃውያን ቤተከርስቲያን የምትከተለው መንገድ ወደዚህ የሚያመራ መሆኑን ለምን እንደማምን መግለጽ አፈልጋለሁ ዛሬ እዚህ መድረከ ላይ የቆምኩት ለሃገሬ ከልብ የመነጨ ጥሪ ለማድረግ ነው የምናገረው ለሀኖይ ወይም ለብሔራዊ ነጻነት ግንባር አይደለም ለቻይና ወይም ለራሺያ አይደለም በወቅቱ ጉዳይና ቬትናም ውስጥ ያለውን ችግር አጢኖ መልስ ላለመስጠት አይቶ እንዳላዩ ለማለፍ የማድረግ ሙከራም አይደለም ሰሜን ቬትናምና ብሔራዊ የነጻነት ግንባርን ከደሙ ነጻ ለማድረግ ወይም ችግሩን ለመፍታት ያላቸውን ሚና ለማሳነስም አይደለም ሁለቱም በዩናይትድ ስቴትስ ዘንድ በጥራጥሬ ለመታየት በቂ ምከንያት ያላቸው ቢሆንም በመተማመን ላይ የተመሠረተ ሰጥቶ መቀበል በሁለቱም መካከል ከሌለ አለመግባባቱ መፈታት እንደማይችል ታሪክም ገሐዱ ዓለምም ያረጋግጡልናል ዛሬ ግን ከሀኖይና ከብሔራዊ የነጻነት ግንባር ጋር ሳይሆን በሁለቱ ዓለማት መካከል ከፍተኛ ዋጋ እያስከፈለ ያለውን ግጭት ለማስቆም ኃላፊነት ካለባቸው አሜሪካውያን ወገናች ጋር መነጋገር አፈልጋለሁ የቬትናም አስፈላጊነት ሰባኪ እንደመሆኔ መጠን የቬትናምን ጉዳይ ትኩረት ለመስጠቴ ሰባት ምከንያቶች አሉኝ በመጀመሪያ ደረጃ ቬትናም ውስጥ የሚደረገው ጦርነት እኔና ባልደረቦቼ አሜሪካ ውስጥ ከምናካሂደው ትግል ጋር ግንኙነት አለው ከጥቂት ዓመታት በፊት በዚያ ትግል ውስጥ መልካም ጊዜያት አሳልፈናል በድህነት ቅነሳ ዕቅድ አማካኝነት ለድሃ ነጮችና ጥቁሮች ተስፋ እንዳለ ቃል የተገባላቸው ይመስል ነበር ተስፋ ሰጭ ሙከራዎችና አዳዲስ ጅማሬዎች ነበሩ ከዚያ ቀጥሎ ቬትናም ላይ ተዘምቶ ዕቅዱ ከሽፎ በጦርነት ያበደች አገር የምትጫወተውን የፖለቲካ ጨዋታ ቁጭ ብለን ታዘብን ቬትናም ውስጥ የሚካሄደው የማንአለብኝነት ድርጊት ቀጥሎ የሰውን ልጅ ገንዘብ ዕውቀትና ጉልበት አንደከፉ ሰይጣን እየመጠጠ አሜሪካ ድሆቿን ለመንከባከብ የሚተርፍ ሃብትና ጉልበት እንደማይኖራት ተረዳሁ ለዚህም ነው ይህን ጦርነት የድሃ ጠላት ነው በማለት ለመቃወም የተገደድኩት ሌላው ምናልባትም የባሰ አሳዛኝ የሆነው ሁኔታ የታየኝ ይህ ጦርነት አገር ውስጥ ያሉ ድሆችን ተስፋ ብቻ ያጨሰመ አለመሆኑን በተረዳሁ ጊዜ ነበር ጦርነቱ በርካታ ሴቶች ልጆቻቸው ወንድሞቻቸው እና ባሎቻቸው ተሳታፊ ሆነው ውድ ህይወታቸውን እንዲያጡ አድርጎል በማህበራዊ ኑሮ የተሸመደመዱ ጥቁር ወጣቶችን ከቤታቸው ስምንት ሺህ ማይል አርቀን በደቡብ ምዕራብ ጆርጂያ አና ምሥራቅ ሀርለሞ ያላገኙትን ነጻነት በደቡብ ምሥራቅ ኤስያ እንዲያረጋግጡ ስንልካቸው ነበር በዚሁ መሠረት የኔግሮ ልጆችና የነጮች ልጆች ጎን ለጎን ተሰልፈው ሲገድሉና ሲሞቱ ቴሌቪዥን ላይ ስንመለከት ነበር ጎን ለጎን ቆመው በሚዋደቁላት አገር ውስጥ ግን በአንድ ትምህርት ቤት ጎን ለጎን ቁጭ ብለው መማር አይችሉም የድሆችን ቤቶችና መንደሮች በጭካኔ የማቃጠል ተግባር ላይ ሲደጋገፉ ተመልክተናል ነገር ግን ዲትሮይ ውስጥ አንድ ቅያስ ላይ መኖር እንደማይችሉ እናውቃለን እንዲህ አድርገው በድሃ ህይወት ሲጫወቱ ዝም ማለት አልቻልኩም ጭባ በሶስተኛነት የማቀርበው ሃሳብ ከበለጠ ጥልቅ መረዳት የመነጨና ባለፉት ሶስት ዓመታት በሰሜኑ የጥቁሮች መንደር ካገኘሁት ልምድ በመነሳት ነው የተዘነጉ ተስፋ የቆረጡና በምሬት የተሞሉ ወጣቶችን በማግኘት ችግራቸው በመሳሪያ ኃይል እንደማይፈታ ነግሬያቸው ነበር የሚገኙበት ሁኔታ አንጀት የሚበላ መሆኑን ብንረዳም ፍትሃዊ ማህበራዊ ለውጥ ሊመጣ የሚቸለው በኃይል አልባ እርምጃ አማካኝነት መሆኑን ነግሬያቸዋለው ነገር ግን አያይዘው ስለ ቬትናም ጉዳይ ጠየቁኝ አውነታቸውንም ነው ለመሆኑ አገራችን ችግሩን ለመፍታት ከልከ ያለፈ ኃይል አልተጠቀመቸም። ሲል ጦረኝነትን ያስጠነቅቃል የሰውን ልጅ በናፓል ማቃጠል ህጻናትን ያለ አባትና አናት ማስቀረት ሴቶችን መበለት ማድረግ በተፈጥሮ የዋህ የሆኑ ህዝቦችን የጥላቻ መርዝ መመገብ ሰዎችን በጦር ሜዳ አካላቸውን አጉድሎ ስነ ልቦናቸውን አሽመድምዶ ቤት መመለስ ከፍትህና ፍቅር ጋር የሚጣጣሙ ተግባራት አይደሉም አብዛኛውን ሃብቷን የሰውን ህይወት በሚያሻሸሉ ጉዳዮች ላይ ሳይሆን በጦርነት ላይ የምታባክን አገር ወደ መንፈሳዊ ሞት እየተጓዘች መሆኑን ያመለከታል የምድራችን ሃብታሟና ኃያሏ አገር አሜሪካ ይህን የለውጥ ጎዳና መምራት ትቸላለች ሞትን ሳንመኝ ለሰላም ያለን ፍላጎት ከጦርነት አንዲቀድም ፍላጎቶቻችንን በቅደም ተከተል ከማስቀመጥ የሚያግደን የለም በመካከላችን የነበረውን ኢፍትሃዊነት በሻካራ እጆቻችን አሽተን ወንድማማችነትን እስከንገነባ ድረስ ወደኋላ የሚመልሰን አይገኝም በመልካም እሴቶች ላይ የተገነባ እንዲህ ዓይነቱ ለውጥ ነው ከኮሚኒዝም ሊታደገን የሚችለው ጦርነት መፍትሄ አይሆንም ኮሚኒዝም በፍጹም በአቶም ቦምብና በኒውክሌር መሳሪያዎች ድል ሊሆን አይችልም ጦርነት የሚያውጁትንና ዩናይትድ ስቴትስ በተባበሩት መንግስታት ውስጥ የምትጫወተውን ሚና አንድታቋርጥ የሚወተውቱትን መደገፍ እናቁም ይህ ጊዜ ዕውቀት ላይ የተመሠረተ ትዕግስትና ምከንያታዊ መረጋጋትን የሚጠይቅበት ነው ቻይና በተባበሩት መንግስታት ውስጥ መቀመጫ ማግኘት አለባት የሚልን ሰው ሁሉ ወይም ጥላቻና ስሜታዊ አርምጃ በዚህ የትርምስ ወቅት መልስ ሊሆኑ እአንደማይቸሉ የሚያምን ሁሉ ኮሚኒስት ነው ብለን መጥራት የለብንም ጭፍን ፀረ ኮሚኒስታዊነትን ከመከተል መታቀብ አለብን ኮሚኒዝምን ልንከላከል የምንቸለው ፍትህን ለመንከባከብ ጠንካራ አርምጃ ስንወስድና በዲሞከራሲ ላይ ያለንን እምነት ስናጠናክር ነው በጥሩ ጥሩ እርምጃዎች ድህነትን ሁከትንና ኢፍትሃዊነትን ማስወገድ አለብን እነዚህ የኮሚኒዝም ፍሬ በቅሎ የሚያብብባቸው ለም መሬቶች ናቸውና ህዝብ ይበልጣል ይህ ጊዜ የአብዮት ጊዜ ነው በሁሉም ሥፍራ ህዝቦች በጨቋኝ ሥርዓቶች ላይ ተነሳስተው ከአሮጌው ዓለም ማህጸን ውስጥ አዲስ የፍትህና የአኩልነት ሥርዓት እየተወለደ ነው ራቁታቸውን በባዶ አግራቸው የሚሄዱ ህዝቦች ከምንጊዜውም የበለጠ አንገታቸውን ቀና አያደረጉ ነው በጨለማ የነበረ ህዝብ ታላቅ ብርሃን እያየ ነው አኛ ምዕራባውያን ይህን አብዮት መደገፍ አለብን ከምቾት ከምንቸገረኝነት ከጭፍን የኮሚኒዝም ፍርሃትና ከኢፍትሃዊነት ጋር በመላመድ ምዕራባውያን አገሮች ራሳቸው ያቀጣጠሉትን የአብዮት መንፈስ መልሰው ለማዳፈን ፀረ አብዮት ሆነው መገኘታቸው ያሳዝናል ይህ ደግሞ ሰውን ሁሉ ማርከሲዝም ብቻ ነው የአብዮት መንፈስ ያለው ወደሚለው አስተሳሰብ መራው ስለዚህ ኮሚኒዝም ሌላ ሳይሆን ዲሞክራሲን ዕውን ማድረግ ባለመቻላችንና ያስጀመርናቸውን አብዮቶች ማስቀጠል ባለመቻላችን የመጣብን ቅጣት ነው አሁን አንድ ያለን ዕድል ይህን የአብዮት መንፈስ ድጋሚ መቀበልና ወደ ዓለም ብቅ ብለን በድህነት በዘረኝነትና በጦረኝነት ላይ ጦርነት ማወጅ ነው በዚህ ቁርጠኝነት አሁን የምናየውን መበላለጥ ኢፍትሃዊ ስነ ምግባር ተቋቁመን ሸለቆው ከፍ የሚልበትና ተራሮቹ ዝቅ የሚሉበት እንዲሁም ጎባጣዎቹ የሚቀኑበትን ቀን ማፋጠን አለብን አውነተኛው የመልካም እሴት አብዮት ማለት መተማመናችንን አንድ ላይ ለማምጣት አንጂ ለመለያየት አይደለም ማንኛውም አገር በማህበረሰቡ ውስጥ ያለውን መልካም ነገር ተንከባከቦ ለማቆየት ከፈለገ አስቀድሞ ለመላው የሰው ልጅ ታማኝ መሆን አለበት ከራሳችን ጎሳ ዘር መደብና አገር ሌላ አልፈን አንድናስብ የሚያሳስበን ሁለንተናዊ የአንድነት ጥሪ ሁሉንም የሚያቅፍ ቅድመ ሁኔታ የሌለው የፍቅር ጥሪ ነው ይህ አመለካከት በሰዎች ዘንድ የተሳሳተ ትርጉም የተሰጠውና በኔዥ ፍልስፍና ተከታዮች የደካሞችና የፈሪዎች ሃሳብ ተደርጎ የተወሰደ ቢሆንም አሁን ግን ለሰው ልጆች ህልውና አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል ስለ ፍቅር ስናገር ስለ ስሜትና ስለ ደካማ ምላሽ አየተናገርኩ አይደለም የማወራው ሁሉም ታላላቅ ሃይማኖቶች የአንድነት መሠረት አድርገው የወሰዱትን ያንን ታላቅ ኃይል ነው ፍቅር ወደ እውነት የሚወስደውን በር የመከፈቻ ቁልፍ ነው በህንዱ በአስላም በከርስትና በአይሁድና በቡዲስት አምነቶች ውስጥ ስላለው የመጨረሻው እውነት በመጀመሪያው የዮሐንስ መልዕከት እንደሚከተለው ተጠቃሎ ተቀምጧል ንምርሮድያ ሪግሂ። ይሆ ድረሂም ለፍሪትሯ ርያዖ ሳተው ሜሪጳቋውያጋ ይ ዕዲሶዖምሜናኖ ያማሀሠጋራዊ ፈኗና ሪሄድ ፅታ ሰና ሮር ያማነትሄሯዮ ዕጎሜሪካ ያሃመፖሟሥ ሐማጋኛውም ፊጋ ዕዳሎ ሰታ ያለው መፆምን ሐመግ«ሄፍ ቦዖጄድሪፇግ ሙስሰራ ፅው አንድ ህዝብ ካለበት ጭቆና ለመላቀቅ የሚችለው ለውጥ ለማምጣት የሚያስቸለው ኃይል እንዳለው ሲገነዘብ ነው አምባገነኖች ምንጊዜም ዕድል አያጡም ፅድል በአጃቸው ነች በሌላ በኩል ደግሞ ኃይል የሌላቸው ዕድል የላቸውም ዕድል የሚያገኙት ዘግይቶ ነው ዛሬ የጥቁሮች ዋነኛ ሥራ መንግሥት ጥያቄያችንን ሰምቶ አንዳልሰማ ችላ ብሎ እንዳያልፍ መልስ እንዲሰጥ በሚያስገድድ መልኩ ጥንካሬያችንን እንዴት ወደ አቅም ልንቀይር እንችላለን የሚለው ነው ከጥንካሬያችን የተነሳ መንግሥት ከኛ ጋር ከመጋጨት ይልቅ ከኛ ጋር መግባባትን አንዲመርጥ የሚያስቸል ሁኔታ መፍጠር አለብን ምንም ነገር ሳንሠራ መንግሥት በፕሮግራሞቻችን ላይ ያስቀመጥናቸውን ፅቅዶች ሥራ ላይ አንድናውል መልካም ፈቃዱ ይሆናል ብለን እጃችንን አጣምረን ከተቀመጥን ከሁሉም የሚበልጥ ሞኝነት ይሆናል በርግጥ ባለፉት ዓመታት የፈጠራና አርቆ የማሰብ ችሎታችንን ተጠቅመን አንዴት አቅም መፍጠር እንዳለብን በመማር ላይ አንዳልተጠቀምንበት ማመን አለብን ከዚህ በፊት በሥራ ላይ ሊውል የሚቸል የኃይል አልባ ትግል ስልት አግኝተናል ህግጋቱንና የዕድገት አቅጣጫውን በጥልቀት ለመመርመር ጊዜ አልነበረንም እርምጃዎቻችን በድፍረትና በስኬት የታጀቡ ቢሆኑም ሳይታቀዱ በድንገት የተከናወኑ ነበሩ የታቀደላቸውን ግብ የመቱ ቢሆንም በቂ ተሞክሮ አንዳልነበረን የሚያሳብቁ ነበሩ ዛሬ የሲቪል መብት ትግል በዚህ ደረጃ ላይ ይገኛል በቀጣይ ወሳኝ እርምጃዎችን በመውሰድ ይህን ትግል የሚያካሂዱ አካላትን ፈትነን ማየት አለብን ሁኔታዎችን ፈር ለማስያዝ ይሄ ለጥቁሮች አስፈላጊያቸው ነው በህብረተሰባቸን ውስጥ አቅም ሁልጊዜ የሚመነጨው ፖለቲካ ኢኮኖሚና ርዕዮተ ዓለምን መሠረት በማድረግ ነው በርዕዮተ ዓለሙ ረገድ ከጥቂት የጥቁር ጸሐፊዎች ሥራና አስተዋጽኦ በስተቀር በታላቁ የአሜሪካ አስተሳሰብ ላይ ይህ ነው የሚባል ተጽዕኖ ሊያሳድሩ የሚችሉ ጥቁሮች ነበሩ ለማለት አያስደፍርም ይሁን እንጂ የአገሪቱ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ጉድለቶች ይፋ ወጥተው ጸሀይ እንዲመታቸው በማድረጉ ረገድ ይህ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት አንደገና እንዲጤንና በአግባቡ ሥራ ላይ እንዲውል ለማድረግ ጥረት አድርገዋል ጥቁሮች ባካሄዷቸው አንቅስቃሴዎች ምከንያት ባለፉት አሥር ዓመታት አገራችን ከኢኮኖሚና ከፖለቲካ አንጻር መሠረታዊ የዲሞከራሲ ባህሪያት እንዲፈተሹ ተደርገዋል ጥቁሮች ችግሮችን በግልጽ ይፋ በማውጣት ዲሞክራሲና ጉድለቱን በተመለከተ ተጨባጭ ትምህርት በመስጠት ወሳኝ በሆነ መልኩ በነጩ ማህበረሰብ አስተሳሰብ ላይ ተጽዕኖ ለማሳደር ችለዋል ጥቁሮች ቴሌቪዥን የመጠቀም የህትመት ውጤቶችን የማንበብና ትላልቅ መድረኮችን የመጠቀም ዕድል ስሰሴላቸው መልዕከቶቻቸውን ለማሰተላለፍ በየለቱ በዶለዶመው ብዕሮቻቸው በእጃቸው ለመጻፍ ተገደዋል ነጮቹ የፖለቲካ መሪዎች አንዲሁም አንዳንዶቹ ጓዶቻችን ሰልፍ አቁመን ወደ ቤታችን አንድንመለስ ሲመከሩን ዝም እንድንል መጠየቃቸው እንደሆነ አልተረዱትም ይሆናል በኃይል አልባ ትግል ወቅት የአሜሪካን ውርደት ተረድተው በመጨረሻም አንዳንድ አሳፋሪ ተግባራትን መጋፈጥ የጀመሩ የነጭ አሜሪካውያን ቁጥር ከዚያ በፊት በነበሩት አንድ ሺህ ዓመታት ውስጥ ከተፈጠሩት ይበልጣል ጥቁሮችን ወደ ሥልጣን ሊመራ የሚችል መንገድ መግቢያው ጠባብ ነው ጥቁሮች ከተሰማሩባቸው የንግድ መስኮች ውስንነት በላይ የዘረኝነትንና የመድልኦን አስከፊ ውጤት በገሀድ የሚያሳይ ነገር የለም የአሜሪካ ዓመታዊ የኢንዱስትሪ ምርት ከዓለም ኢንዱስትሪ ምርት ግማሹን ይይዛል። እነዚህ ሰዎች ከነጭ መራጮች የማይናቅ ድምፅ አግኝተዋል ይህ ድምፅ ለድል ባያበቃቸውም የወደፊቱን የደቡብ የፖለቲካ አቅጣጫ በማመልከት ረገድ ግን ከፍተኛ ሚና ነበረው በአርግጥ የጥቁሮች የምርጫ ድምፅ ሰሜኑን የአገሪቱ ከፍል አልቀየረውም ይሁን እንጂ ሰሜን ውስጥ ያለው የፖለቲካ እንቅስቃሴና ህብረት ደካማ መሆኑ በመላው ሰሜን ይስፋፋል ወይም በደቡብ ውስጥም ይደገማል ብለን መገመት አንቸልም የሰሜን ጥቁሮች ለውጥ ለማምጣት በስፋት ቀጥተኛ አርምጃ ወስደው አያውቁም ከአሥር ዓመታት በፊት የደቡብ ጥቁሮችም ተስፋ ቆርጠው ይተዋሉ ብሎ አስቦ ከሆነ ተሳስቶ እንደነበር አሁን ይረዳል ጥቁሮች የሚፈልጉት ነገር ሁሉ ከምርጫ ኮሮጆ የሚገኝ አይደለም ነገር ግን ምርጫን ወደ ሥልጣን አንደሚያደርስ መደላድል ቆጥረን ትኩረት ከሰጠነውና በተቃውሞ ወቅት ሥራ ላይ ያዋልናቸውን የፈጠራ ችሎታዎች አዳብረን መጠቀም ከቻልን በዕድሜያችን ዘመን ትላልቅ ለውጦችን ለማየት ይረዳናል በተለይም በሰሜኑ ክፍል ለሚገኙ ጥቁሮች የፖለቲካ ጥንካሬ ማጣት ዋነኛው ምንጭ በርካታ ጥቁሮች ያሰረጹት የቆየ ልማድ ነው ራሳቸውን ከፖለቲካ ማራቅ ይመርጣሉ ፖለቲከኞች አንደሚያታልሏቸው ይቆጥራሉ ማንም ሰው መልካም ያስብልናል ብለው ሰለማያምኑ ለማናቸውም ጉዳይ ፍላጎት የላቸውም በሁሉም አቅጣጫ ከሚፈጸምባቸው ዘረፋ ለመሸሸ ሲሉ ከፖለቲካ እንቅሰቃሴ ታቅበው አጃቸውን አጣምረው ይቀመጣሉ በጠለቀ የተስፋ መቁረጥ ውስጥ ናቸው ካሳለፉት ህይወት ልምድ አንጻር ስንመለከት አይፈረድባቸውም ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ የሥልጣን ምንጭ ነው ብለው አያስቡም ይህን አመለካከት ለመቅረፍ ትዕግስትና የማያቋርጥ ጥረት ይጠይቃል ይሁን እንጂ ባለፉት አሥር ዓመታት ባገኘነው ንቃት ተጠቅመን ጥቁሮች ገንቢ ሃሳባቸውን ወደ ፖለቲካ እንቅስቃሴ በማምጣት ጊዜው ያለፈበትን አስተሳሰብና ተሽመድምዶ አንድ ሥፍራ የቆመውን ትግል ወደ ፊት ማራመድ እንችላለን ወደ ፊት ብርቱ የፖለቲካ ታጋዮች መሆን አለብን ከየትኛውም የአሜሪካ ማህበረሰብ የበለጠ ፖለቲካዊ ጥንካሬ ስለሚያስፈልገን በዚሁ አቅጣጫ መመራት ይኖርብናል አብዛኞቻችን ድሀ በመሆናችን በቂ የኢኮኖሚ አቅም የለንም ብዙዎቻችን ካለው ባህል ተተፍተን ስላለን ሥልጣኑን የተቆጣጠረው ባህል አካል ልንሆን አንትልም ስለዚህ አዲስ ነገር የመፍጠር ችሎታችንን ተጠቅመን ፖለቲካ የሚያስገኘውን ሥልጣን እጃችን ውስጥ ማስገባት ግዴታችን ነው ጥቁሮች የአሜሪካ አይሁዳውያን ከፍ ያለ ማህበራዊ ሥፍራና ትልቅ ከብር ማግኘት የቻሉት ባለጸጎች በመሆናቸው ነው ብለው ያስባሉ እንዲህ ያለውን የተሳሳተ አመለካከት ዝም ብሎ ማሰፍ ተገቢ አይሆንም ባንድ በኩል ስናየው አስተሳሰቡ ፀረ ሴማዊነትን በማጠናከር የገንዘብንም ኃይል ከሚገባው በላይ አጉልቶ ያሳያል በሌላ በኩል ደግሞ እውነቱ ጠቅለል ተደርጎ ሲታይ ትምህርት ሊሆነን የሚችል ይመስለኛል የአይሁዳውያን ዕድገት መንስኤው ያላቸውን የትምህርት ባህል ከማህበራዊና ፖለቲካዊ አንቅስቃሴ ጋር ማዋሃዳቸው ነው አንድ አይሁዳዊ ቤተሰብ ለትምህርት ከፍተኛ ሥፍራ ይሰጣል ለማግኘትም ትልቅ መስዋዕትነትን ይከፍላል የዚህ ውጤት ደግሞ በገሃድ የሚታይ ነው አይሁዶች ማህበራዊ እንቅስቃሴአቸውን ከትምህርት ባገኙት ዕውቀት አዳብረው በፖለቲካው ውስጥ ስኬታማ ለመሆን ችለዋል ለምሳሌ ያህል የህግ ባለሙያ ነጋዴ ጸሐፊ የመዝናኛ ባለቤት የማህበር መሪ የጤና ባለሙያ የሆነ አይሁዳዊ በመደበኛ ሥራው ላይ ብቻ ተጠምዶ በዚያው ተውጦ አይቀርም በፖለቲካው ረገድም የፖለቲካን ጥበብና ስልት በመማር በንቃት ይሳተፋል በማህበራዊና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ውስጥ የሚሳተፉት ሀብታሞች ብቻም አልነበሩም ለግማሽ ምዕተ ዓመት ያህል በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አይሁዳውያን ድኾች ነበሩ ይሁን አንጂ በማህበራዊና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ባይተዋር አልነበሩም ፖለቲካ ከአፋቸው ውስጥ በማይጠፋ ቤተሰብ ውስጥ ያድጋሉ ይኖራሉ። ከናንተ ትልቅ መሆን የሚፈልግ ቢኖር የሁሉም አገልጋይ ይሁን ይኹ ነው ስለ ትልቅነት የተሰጣቸሁ አዲሱ ትርጉም ዛሬ ጠዋት ስለዚህ ትርጉም ደስ የሚለኝ አንድ ነገር አለ በዚህ ትርጉም መሠረት ሁሉም ሰው ትልቅ ሊሆን ይቸላል ምከንያቱም ሁሉም ሰው አገልጋይ መሆን ይችላል አገልጋይ ለመሆን ባለቤትና ግስን ማስማማት አይጠበቅንም ስለ አርስቶትልና ፕሌቶ ማወቅም አይጠበዋብንም አገልጋይ ለመሆን የአንስታይን የአንጻራዊነት ንድፈ ሃሳብ ማወቅ ግዴታ አይደለም አገልጋይ ለመሆን ሁለተኛውን የቴርሞዳይናሚክስ ንድፍ ሀሳብ ማወቅ አያስፈልግም የሚያስፈልጋችሁ በጸጋ የተሞላ ልብ ብቻ ነው በፍቅር የተሞላ ነፍስ ነው የሚያስፈልጋችሁ ያኔ ተፈላጊ አገልጋይም ልትሆኑ ትቸላላቸሁ አንድ ሰው አውቃለሁ ስለሱ ላጫውታችሁና ትልቅ ሰው ስለነበረ ከንግግሬ ማን መሆኑን ታውቁ ይሆናል የኖረው በአገልግሎ ብቻ ነበር የተወለደው በማትታወቅ መንደር ውስጥ የአንዲት ድሀ አርሶ አደር ልጅ ሆኖ ነበር ያደገውም እንደዚሁ በማትታወቅ መንደር ውስጥ ነበር ሰላሳ ዓመት አስኪሞላው ህይወቱን ያሳለፈው በአንጨት ሥራ ነበር ከዚያ ለሶስት ዓመታት እንቅስቃሴ ጀመረ ዞሮም ሰበከ በኋላ አንዳንድ ነገሮችን ማከናወን ጀመረ ምንም ግን አልነበረውም ፈጽሞ መጽሐፍም አልጻፈም ቢሮም ኖሮት አያውቅም ቤተሰብ አላፈራም ቤትም አልነበረውም ኮሌጅ አልገባም አንድም ትላልቅ ከተሞችን አልጎበኘም ከተወለደበት ቦታ ሁለት መቶ ማይል እንኳን ርቆ ሄዶ አያውቅም ዓለም ከዕድገት ጋር የምታያይዛቸውን ማናቸውንም ነገር አልፈጸመም አንድም የጽሁፍ ማስረጃ አልበረውም ማስረጃው ራሱ ነበር የህዝብ ማዕበል ተነስቶ ሲቃወመው ዕድሜው ሰላሳ ሶስት ነበር ሁከት ፈጣሪ ይሉት ነበር የችግር አባትም ይሉት ነበር ቀለቃሽም ይሉት ነበር የሰላማዊ ትግል ስልትን ሥራ ላይ አውሏሷል የፍርድ ቤት ትዕዛዝን አሽቀንጥሮ ጥሎሏል ከዚያም ለጠላቶቹ ተላልፎ ተሰጥቷል በችሎት ቀርቦ ተቀልዶበታል አስገራሚው ጉዳይ ወዳጆቹ ከጠላቶቹ ጋር ማበራቸው ነበር ከቅርብ ወዳጆቹም አንዱ ካደው ሴሎቹ ከተቃዋሚዎቹ ጋር ተባበሩ ሲሞትም ገዳዮቹ በልብሱ ላይ ዕጣ ተጣጣሉ ይኹ በዓለም ላይ ያለው ብቸኛ ሀብቱ ነበር ቀብሩም በተውሶ የመቃብር ሥፍራ ተከናወነ ከአንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ዓመታት በኋላ ይህ ሰው ዛሬ ካለፉት የዓለም ታሪኮች ሁሉ የላቀ ተጽዕኖ በመፍጠር ይታወሳል እስካሁን የዘመተ የምድር ጦር አስከዛሬ የተሰማራ የባህር ኃይል እስካሁን የተሰበሰበ ፓርላማ እና እስካዛሬ የነገሥ ነገሥታት ሁሉ ተደማምረው ይህ አንድ ግለሰብ የፈጠረውን ተጽዕኖ ሊፈጥሩ አልቻሉም ስሙ አዲስ ላይሆን ይችላል ይሁን አንጂ በዚህ ዘመንም ሰዎች ስሙን ሲያነሱ እአስማለሁ አሁንም አሁንም እሱ የነገሥታት ንጉሥ ነው ይላሉ ሌሎች ደግሞ የጌቶች ጌታ ሲሉ አሰማለሁ ደግሞ ሌላው ብድግ ብሎ በከርስቶስ ምሥራቅና ምፅራብ የለም ይላል በመቀጠል ብዙ ነገር ይናገራሉ በከርስቶስ ሰሜንና ደቡብ የለም ይሁን እንጂ በመላው ዓለም በፍቅር አንደ ወንድማማችነት ብቻ ይኖራል ይላሉ ምንም ነገር አልነበረውም ያደረገው ነገር በአካባቢው ያሉትን ማገልገልና መልካም ማድረግ ብቻ ነበር አስካገለገላችሁ ድረስ ዛሬ ጠዋት በቀኙ ወይም በግራው መቀመጥ ትችላላችሁ መንገዱ ይኹ ብቻ ነው አዎን ለሁላችን ስለማይቀረውና ስለምንፈራው ቀን ሞት ብለን ስለምንጠራው ነገር አልፎ አልፎ ማሰባችን አይቀርም ሁላችን ስለዚያ አናስባለን ደጋግሜ ስለ ራሴ ሞትም አስባለሁ ስለቀብሬም አስባለሁ ነገር ግን ስለ አሳዛኝነቱ አላስብም ደጋግሜ የሞቴ ዕለት ምን አንዲባልልኝ አፈልጋለሁ በማለት ራሴን አጠይቃለሁ ስለዚህ ያኔ ምን እንደምትሱ ለናንተ አተዋለሁ የመጨረሻውን የሞት ጽዋ ስጎነጭ ከናንተ ውስጥ አጠገቤ የሚኖር ሰው ድንገት ካለ ረጅም ስነ ሥርዓት እንደማልፈልግ ልነግራችሁ እፈልጋሁ እዚያ ላይ የሚያወድሰኝ ካለና አጠገቡ ብትኖሩ እንዳያስረዝመው ንገሩት ደጋግሜ ምን ቢባል ደስ እንደሚለኝ አስባለሁ አስፈላጊ ስላልሆነ የኖቤል የሰላም ሽልማት መቀበሌን እንዳይናገር አስታውሱት አስፈላጊ ባለመሆኑ ሶስት ወይም አራት መቶ ሌሎች ሽልማቶች እንዳሉኝ አንዳይናገር ንገሩት የትኛው ትምህርት ቤት እንደተማርኩ እንዳያነሳ ንገሩት ያን ዕለት አንድ ሰው ማርቲን ሉተር ኪንግ ትንሹ ሰዎችን ለማገልገል የራሱን ህይወት አሳልፎ ሰጠ እንዲል አፈልጋለሁ ያን ቀን አንድ ሰው ማርቲን ሊተር ኪንግ ሰዎችን ለመውድድ ሞከሯል እንዲል እሻለሁ ያን ዕለት በቬትናም ጦርነት ጉዳይ ላይ ትቸት በመሰንዘር ትከከለኛ ለመሆን መጣሬን እንድትናገሩ እአፈልጋለሁ የተራቡትን ለመመገብ መሞከሬን መናገር እንድትችሉ አፈልጋለሁ የታረዙትን ለማልበስ መሞከሬን ብትናገሩ መልካም ነው ያን ቀን በህይወት ዘመኔ አሥር ቤት ያሉ ወገኖችን ለመጎብኘት መሞከሬን ንገሩልኝ። ያ ጥያቄ በቀላሉ ወደ መንፈሳዊ ትምህርትና ፍልስፍና ከርከር ሊያስገባን ይችል ይሆናል ይሁን አንጂ ኢየሱስ ጥያቄውን ከአየር ላይ ቀልቦ ወዲያውኑ ኢያሪኮና ኢየሩሳሌም መካከል በሚገኘው ጠመዝማዛ መንገድ ላይ አኖረው ይህ ስለሆነ ኢየሱስ በሌቦች ቁጥጥር ሥር ስለ ዋለ አንድ ሰው አነሳ ከሌዋውያን ወገን የሆነ አንድ ሰውና አንድ ቄስ በሌላኛው የመንገድ ጫፍ ያልፉ እንደ ነበር ታስታውሳላችሁ ነገር ግን ቆመው አልረዱትም በመጨረሻ አንድ ከሌላ ወገን የሆነ ሰው በዚያ ያልፍ ነበር በርህራሄም ሊረዳው ፈለገ ይህን በቸግር ላይ ያለ ወንድም ሊረዳው አስቦ የመጀመሪያ ዕርዳታ አደረገለት ኢየሱስም ይህ ሰው መልካም ሰው ነው አለ ይህ ሰው ትልቅ ሰው ነው ምከንያቱም እኔ ከማለት አልፎ አንተ በማለት ለወንድሙ ቅድሚያ መስጠት ደረጃ ላይ ደርሷል አለ ኢየሱስ እስቲ ለአንድ አፍታ ሌዋዊው እና ቄሱ ለምን በሌቦች አጅ የወደቀውን ሰው መርዳት አልቻሉም ብሰለን እናስብ ምናልባት የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ስብሰባ ስላለ በጊዜ ኢየሩሳሌም ለመድረስ ቸኩለው ነው አንበል እንዲሁም በሌላ በኩል ሃይማኖታዊ አገልግሎት የሚሰጥ ሰው ያንን ሥርዓት ከመፈጸሙ ሃያ አራት ሰዓት በፊት ጀምሮ የሰውን ገላ መንካት አይችልም የሚል ሃይማኖታዊ ህግ አንዳለ እንውሰድ ምናልባትም ደግሞ ወደ ኢየሩሳሌም ወይም ወደ ኢያሪኮ ሄደው የኢያሪኮን መንገድ የሚያሻሸል ኮሚቴ ለመመሥረት ይሆናል ይህም ሊሆን ይቸላል ምናልባትም ደግሞ አንድን ሰው ከመርዳት ይልቅ ለዚህ ችግር መሠረታዊ መፍትሄ መፈለግ ይሻላል ብለው አስበው ይሆናል እኔ ግን የሚሰማኝን ልንገራቸሁ እነዚህ ሰዎች ፈርተው ይሆናል ብዬ አስባለሁ የኢያሪኮ መንገድ አደገኛ መንገድ ነው እኔና ባለቤቴ ወሮ ኪንግ ለመጀመሪያ ጊዜ በኢየሩሳሌም ያሳለፍንበትን ጊዜ አስታውሳለሁ መኪና ተኮናትረን ከኢየሩሳሌም ወደ ኢያሪኮ ጉዞ ጀመርን መንገዳችንን አንደ ጀመርን ባለቤቴን ኢየሱስ ይህን መንገድ ለምን በእንቆቅልሽ መልከ አንዳቀረበው አሁን ገና ገባኝ አልኳት መንገዱ ጠመዝማዛና ግራ የሚያጋባ ነው ለደፈጣ በጣም አመቺ ሥፍራ ነው ከኢየሩሳሌም ስትነሱ ማይል ወይም ከባህር ወለል ጫማ ከፍታ ይኖረዋል።

  • N.B. This Summary is Very Experimental!! based on the following scripts from:
    • https://github.com/millzon/textSummarizer-am
    • https://github.com/icoxfog417/awesome-text-summarization#motivation
Download Searchable PDF Download PDF

Comments:


memezon

Download options | Convert to Pdf | Book of the day

© dirzon | Terms of Service | Privacy | About | Services | Contact