Detecting...

Please whitelist dirzon to continue.

or subscribe for ad-free contenct.

dirzon
  • تحويل إلى قوات الدفاع الشعبي
  • قائمة القراءة
  • مختصر
  • كتاب مسموع
  • بحث
  • تحميل
  • myzon
  • تسجيل الدخول
  • تسجيل
English  አማርኛ  Français  العربية
كتاب اليوم

የልምዣት-ሀዲስ አለማየሁ.pdf


  • word cloud

የልምዣት-ሀዲስ አለማየሁ.pdf
  • Extraction Summary

ምእራፍ ሀያ አምስት በሻህ ደማሙ ደመቀች ወደ ወጥ ቤታቸው ውስጥ ተቀምጠው ያዛዥንና የበገናውን እንጉርጉሮ አዬሰሙ ምን ማድረግ እንደሚሻል ሲጨነቁ ሲቸገሩ እስከ ምኝታ ጊዜ ማምሸቱ የተለመደ ሆነና ያን የጭንቅ ጊዘ አጥብቀው ይጠሉት አጥብቀው ይፈሩት ነበር። ምን ወለ ወልዳው ነው። አዛዥ ተካልኝ ሊሞቱ አቅራቢያ ፈርተው እንደ ነበረው ባልተቤታቸው ወይዘሮ ጌጤና ወይዘሮ ውባዬሁ በናቶች ቦታ ሄደው አንደ ተቀመጡ ደመቀችና በሻህ ተከታትለው የናቶችንም ያባቶችንም ጉልበት ስመው ጉንጫቸውን ተስመው ቡራኬ ከተቀበሉ በሁዋላ አዲሱን ኑሮዋቸውን ወደሚጀምሩበት ቤታቸው ታጀበው ሲፄዱ የቀረው እድምተኛ ተነስቶ በደማቅ በጭብጨባ ሸኛቸው ልጠከበር በበዩኋበገከር።

  • Cosine Similarity

ሁልጊዜ ጸሀይ ዘቅዘቅ ስትል ማታ የሚገጥማት መከራ ከራሱ ከመከረው ብዙ ጊዜ ከፍቶ ይታያትና ጨካኝ አውሬ ሆኖ ይታያትና ማልቀስ ትጀምራለችፅ አትበላ አትጠጣ እንቅልፍ አይወስዳት ከስታ ከስታ ገላዋ አለቀና የገላዋ ጥላ ሆነች በሁዋላ አድሮ የማይሻላት ስለሆነና ታምራት በጁ አንዳትሞትበት ስለ ፈራ ሳይፈታ እንዲሁ እአወላጆችዋ ዘንድ እድንትቆይ ሰደዳት ጸንሳ ነበር አስራ ሶስት አመት እንኩዋ ሳይሆናት «ሞተች» ተብሎ ተስፋ ከተቆረጠላት በሁዋላ በብርቱ ጣር ወንድ ልጅ ተገላገለች ደመቀች ከባልዋ ቤት ወደ ወላጆችዋ ከተመለሰች በሁዋላ አስዋን ብቻ ሳይሆን ወላጆችዋን ጭምር በኑሮዋቸው ቀጥ አድርጎ የያዘ እሱ ነበር ወንድ ልጅ መገላገልዋን ሲሰማ አልሙ ሞለላትና እጅግ ደስ አለው የምሥራቹን የሰማ አለት አንድ የሰባ ፍሪዳ አስነድቶ ማርና ቅቤ አስጭኖ ልጁን ለማየት ወደ ንዶዳሞ ሄደ ከዚያ በሁዋላ በየግዜው አስጭኖ ልጁን ለማየት ቅቤውን ዱቄቱን በርበሬውን እያስያዘ ይፄሄዳል ደመቀች ግን «ታምራት መጣ» ሲሉዋት «ሞት መጣ» አንዳሉዋት ሁሉ የምትሸሽግበት ቦታ አልበቃት እያለ ትጨነቅ ነበር እሱም ምሽቱ እዚያ ያልተገኘበትን የውሸት ምክንያት ወላጆችዋ ፈጥረው በነገሩት ቀን ልጁን ብቻ አይቶ ይመለሳል ልጁ አውነትም ደስ የሚያሰኝ በጣም የሚያምር ነው ሰሙን አያቱ ባሻ ጸሀይ ከንስሀ አባታቸው ጋር ተመካክረው «ተከስተ» አሉት ታምራትም ምን ማለቱ መሆኑን ሲነግሩት ተስማማ ተከስተ በተወለደ ባመቱ ታምራት ሚስቱንና ልጁን እንዲሰጡት የደመቀችን ወላጆች ስለ ጠየቀ ወደ ባልዋ እንድትፄድ ቢያባብሉዋትም ቢያስፍራሩዋትም «እሺ» የማትል ሆነች አስገድዶ ለታምራት ለመስጠት መወሰናቸውን ያወቀች እለት እንደ ምትጠፋ ወይም ገደል ገብታ እንደምትሞት አባት እናትዋ በአንድ ላይ ባሉበት እየመላለሰች ስትነገራቸው እናትዋ ወይዘሮ ሙሉነሽ ይሰጉና ከስዋ ጋር ሆነው ሲሆን እንዲያፋቱዋት የለዚያም እንድትቆይ ባላቸው ይለምናሉ ባሻ ጸሀይ ግን ይቆጡና «ለልጆች ፊት መስጠትና እንዳላችሁ ማለት ያባልጋቸዋል እንጂ ምንም አይፈጥላቸው ይችም አንቺ አልሁሽ እያልሻት ነው እንዲህ ራስዋን አንቱ ብላ አልታዘዝም ያለች» ይላሉ ደመቀች እናትዋና የቤተሰቡ የንስሀ አባት ቄስ መንግሥቱ ከሌሎች ዘመዶች ጋር ሁኔታዋን አይተው ባይቃወሙ ኖሮ አባትዋ እስከዚያ ድረስም አስረው ለዚያ ጨካኝ አውሬ ለታምራት ይሰጡዋት እንደ ነበአና ወደፊትም አንድ ቀን ይህ እአንደማይቀርላት ስላመነች ከመጥፋት በቀር ሌላ ማምለጫ መገድ ጠፍታ ወዴት እንደ ምትሄድ አታውቅም። ነገር ግን ከደብረ ማርቆስ ወዲያ እንኩዋንስ መልኩንና አቅጣቻውን በሙሉ ጎጃም ስሙን ልጠከበር በበዩኋበገከር የማታውቀው ሩቅ አገር የለም ስለዚህ ከዚያ ተነስታ የምትፄድበት ጠፍቶዋት ዝም ብላ በግንዱ ላይ እንደ ተቀመጠች አሳብዋ በያቅጣቻው ሲባክን «እማ አንጣ» አለ ተከስተ አንጣ አብይኝ ማለት ነው «እሺ አብዬ» አለች ራስዋን የራሱ ላይ ወዳለበት ወደ ትከሻዋ አዙራ ተከስተ አንዳርሞ ወንዝ አንደ አንቀላፋ ታዝሎ ብዙ መንገድ ከተጉዋዘ በላ ሲነቃ አናቱ አንድ ጊዜ በመንገዱ ከዚያ በቁጥቋጦው አንደገና በመንገዱ ከዚያ በዱሩ ደግሞ እንደ ገና በመንገዱ በገባችና በወጣች ቁጥር የሚለዋወጠው አዳዲስ አካባቢ ከዚያ በፊት ከሚያውቀው ከባሻ ጸሀይ ግቢና በዙሪያው ካለው ጠባብ አለም የተለዬ ስለ ሆነበት አስገርሞት ይሁን አስፈርቶት ዝም ብሎ ከመመልከት በቀር አንድ ቃል ሳይተነፍስ ነው የዋለ አናቱ እዚያ ደረቅ ግንድ ላይ ተቀምጣ ካረፈችና አካባቢው ሁሉ በየደቂቃው መለዋወጡ ሲቀር የሱም ስሜት ከሚለዋወጠው አካባቢ ጋር መለዋወጡን ትቶ አረፈ ወዲያው ራብ ስለ ተሰማው «አንጣ» አለ «እንጣ አ» አለ ሁለተኛ የመጀመሪያው አንጣ ከተስፋ በቀር የሚበላ ነገር ስላላመጣለት እንደ ማልቀስ ቃጥቶት «እሺ አብዬ ትንሽ ቆይ» አለች ደመቀች ትንሽ መቆየት የሚባላ ነገር ይፈጥላት ይመስል። «አይዞሽ ልጄ አሁን ልጠከበር በበዩኋበገከር አናታችን አንዳሉት ተመካክረን የተሻለ መንገድ እስክናገኝ አባትም ሆኑ ሌላ ሰው አይመጣብሽም ማንም ሳያይሽ እዚህ ትቆያለሽ» አሉ እማሆይ ወለተየሱስ ደመቀችን ከናታችን አጅ ወስደው ግንባርዋንም ጉንጮችዋንም እዬሳሙ ደመቀች ሁለት እመበለቶች ሲያባብሉዋት በተለይ አማሆይ ወለተየሱስን አብረዋት ሲያለቅሱ ስታይ ያዘኑላት መሆናቸው ተስማትና ለመጀመሪያ ጊዜ ከናትዋ ሌላ ውስጣዊ ስቃይዋን የሚረዳላት ሰው ያገኘች መሰላትና በፍራትና በጭንቀት ጨልሞ የነበረው የልጅ ፊትዋ ከባድ ደመናው ጸሀይ እንዳሰገደችላት የክረምት ሰማይ በደስታ ወገግ አለ ደመቀች አዚያ መቃብር ቤት ከናታችንና ከማሆይ ወለተየሱስ ጋር ሶስት ሳምንት ያክል ስትሰነብት የምግብ ችግር አላዬችም አስዋና ልጅዋ የፈለጉትን ያክል እንጀራ በወጥ በፈለጉ ጊዜ እዬበሉ እስዋ ጠላ አሱ ውሀ አዬጠጡ እስዋ ለብዙ ጊዜ ትታው የቆዬችውን በጥዋት ተነስታ ዳዊት መልክ ኢዬሱስና መልከ ማርያም ከደገመች በሁዋላ በእማሆይ ወልተየሱስ እግር ተተክታ ቤት ስትጠርግና እቃ ስታጣጥብ በጣም ደስ ብሉዋት ሰነበተች ደመቀች ከመጣች በሁዋላ ጀምረው እማሆይ ወለተየሱስ ያለወትሮዋቸው ከተማ እዬሄዱ ቆይተው መምጣትን አዘውትረው ሰነበቱ አንድ ቀን እንደ መሰንበቻቸው ከተማ ቆይተው ተመልሰው ከናታችን ጋር ለብቻቸው ቀስ ብለው ሲነጋገሩ ቆይተው ደመቀችን ጠሩና «ሰማሽ ልጄ። ልጠከበር በበዩኋበገከር በማግሥቱ አንጋት ላይ የማሆይ ወለተየሱስ ዘመዶች ፈልገው ያገኙላቸው «አቶ መላኩ ረዳ» የሚባል ባለ ካሚዮን ነጋዴ የቤተ ክርስቲያኑ መንገድ መኪና ሊያስሄፄድ እስከሚችልበት ድረስ ካሚዮኑን ቀረብ አድርጎ አቁሞ አሱ ወደ አናታችን መቃብር ቤት መጣ ደመቀች ልጅዋን አንጀራ በወጥ አብልታ ውሀ አጠጥታ አስዋ ልብዋ አዬተሸበረና እዬተናነቃት መብላት ስላቃታት ትንሽ ከቀማመሰች በሁዋላ አቃውን አንስታ ተከስተን በኩታዋ አዝላ ትጠባበቅ ነበር አቶ መላኩ አናታችነን እጅ ነስቶ እንደ ተቀመጡ ጉልበታቸውን ለመሳም ጎንበስ ሲል «ተው ተው አግዚአብሔር ይባርክህ ልጄ ሀብት ያድልህ» ብለው በሁለት አጆቻቸው ቀና ካደረጉት በሁዋላ «በል እንግዲህ » አሉ አንድ ጊዜ አሱን አንድ ጊዜ ደመቀችን አያለዋወቱ እያዩ። «የሚሽክጥራት ሰው ፈልገ» ስላልከው ግን አንሻ ታማአቸው ሰዎች «ገረድ አኽጥራለሁ» ሲል የሰማሁት የለም» አውነትም ደምቀች እስከ ልጅዋ እወይዘሮ አልጣሽ ቤት አስራ አምስት ቀን ያክል ስትቀመጥ የተቸገራት ነገር የለም ተመችቶዋት ነው የሰነበተች ወይዘሮ አልጣሽ በሚኖሩበት ቤት አንድ ትንሽ ክፍል ውስጥ እንኩዋንስ ልትተኛበት ባይንዋ አይታው የማታውቀው አልጋ ተሙዋልቶ እንደ ተነጠፈ ተሰጥቶዋት በመብል በኩል ለስዋና ለልጅዋ ልጠከበር በበዩኋበገከር ቁርስ ምሳና ራት ጊዜው ተጠብቆ አዬቀረበላቸው በዚያ ላይ በምግብ ጊዜ ልጅዋን ወተት ተጠብቆ እአዬቀረበላቸው በዚያ ላይ በምግብ ጊዜ ልጅዋን ወተት አስዋን ጠጅ ሳይለያቸው በጥንቃቄ ተይዘው ሰነበቱ ብቻ ተከስተ አዲስ አበባ የገባ አለት ሌሊቱን ጀምሮ አንድ ሳምንት ያክል አያሳለው በዚያ ላይ ተቅማጥና አግባት ተጨምሮበት ስለ ታመመ አናቱ ተጨንቃ ከሱ ጋር እንደ ተቆራኘች ወጪውን ሳታይ ሰነበተች በመጀመሪያዎቹ ሁለት ቀኖች አመሙ በጣም ጽኑ ስለ ነአብረ ደመቀች የምትሆነው ቅጡ ጠፍቶዋት ነበር ሁዋላ ወይዘሮ አልጣሽ ከቤታቸው የማይለይ የሀኪም ረዳት የሆነ ዘመዳቸውን አንዲያየው ስለ ለመትት አሱ አይቶ መድሀኒት ከሚሰራትበት ሀኪም ቤት አምጥቶ አደራረጉን ለደመቀች አሳያትና ስታደርግለት እዬተሻለው ፄዶ በሳምንቱ መጨረሻ ድኖ ተነሳ አቶ መላኩ ጤፉን ከሸጠ በሁዋላ ፍርድ ቤት የተቀጠረ ጉዳይ ስለ ነበረው የቀጠሮው ቀን ባይደርስም ወዳገሩ ከመመለሱ በፊት ከጠበቃው ጋር እአዬተማከረ ጠበቃው «ያስፈልጉኛል» ያለውን ማስረጃዎች አዬፈለገ ሲሰጥና አገሩ የሚወስደውን ሸቀጣሸቀጥ ሲገዛ መሰንበቻውን ምንም አረፍት አልነበረውም ይሁን እንጂ ተከስተ ታሞ በነበረበት ጊዜ ምንም ቢሆን ጥዋት ወደሚሄድበት ከመሄዱ በፊት ደመቀችን አይቶ ልጅዋ እንዴት እንዳደረ ሳይጠይቃት ሄዶ አያውቅም ሰለ ራስዋ ጉዳይ ስለዋም ሆነ ለወይዘሮ አልጣሽ ለመንገር አልመቸው ብሉ ቀን ሲቀጥር ቆዬ እንጂ አዚያው አወይዘሮ አልጣሽ ጠጅ ቤት «አሻሻጭ» ሆና አንድትቀጠር ነው ያሰበ። » አለ መላኩ ከደስታው ብዛት የተነሳ ስልክ ባለበት ክፍል የነበሩት ሁሉ አንደ ነውረኛ ዘወር እያሉ እስኪያፈጡበት በጣም ጮሆ «አዎ የስዎን መቸገር አይቼ እኒያን ደንበኛዬ ናቸው ያልሁዎትን ታላቅ ሰው በጣም አጥብቄ ስለ ለመንሁዋቸው ምንም እንኩዋ ልጅ ያላት ገረድ ባልፈልግ ስራዋና አመልዋ ካማረ ላንተ ስል አቀጥራታለሁ ብለውኛል» «ትልቅ ውለታ ነው የዋሉልኝ በውነት በጣም ነው ደስ ያሰኙኝ አቶቱ በላይነህ አግዚሀር ደስ ያሰኝዎ ውለታዎን ለመክፈል ያብቃኝ» ብሎ አቶ መላኩ አቶ በላይነህም ራሱንም መርቆ የምሥራቹን ለመንገርና የስዋንም የልጅዋንም ልብስ አጥባ ሰውነትዋን አሰማምራ ለነገው እንድትሰናዳ ለማስጠንቀቅ ደመቀች ወዳለችበት ሄደ ደመቀች የምሥራቹን ስትሰማ ደብዝዞ የነበረ ፊትዋ እንደ ንጋት ሰማይ በደስታ ወገግ አለ ስራ ከማግኘትዋ ይልቅ ደስ ያሰኛት ልብዋን ተጭኖት ከሰነበተው ከባድ ሸክም ነጻ የሆነች መስሎ የተሰማት ከዚያ ባልዋ ካዬችበት ሰፈር ስትርቅ ካይኑም የምትርቅ ስለ መሰላት ነው በማግሥቱ ልጅዋን የታጠበ ልብሱን አልብሳ አሮጌውንና ቁንጮውን በሚዶ ነቃቅሳ አሳምራ እስዋም ተንጨብሮሮ የሰነበተ ጠጉርዋን ታጥባ አባብሳና ነቃቅሳ የታጠበ ልብስዋን ለብሳ እስከዚያ ቀን ድረስ ከነበረችው ከመክሳትዋ በቀር አምራ አቶ መላኩ ወዳቶ በላይነህ ልጠከበር በበዩኋበገከር ጽህፈት ቤት ይዞዋት ሄፄደ ከቢያ ሁለቱ ወደሚቀጥሩዋት ሰው ወደ ደጃዝማች አሰፋ ተጫኔ ቤት ወስደው ደጃዝማች «ገና ሰው ወደሚቀበሉበት ክፍል አልገቡም» ስለ ተባለና አቶ በላይነህ ወደ ስራው ስለ ቸኮለ ካዛዝ ጋር አገናኝተዋት ተመለሱ አቶ መላኩ ደመቀችን ሲሰናበታት አሰር ብር አጥፍ አድርጎ በጅዋ ውስጥ አስቀመጠና አስዋንም ልጅዋንም ስሞ «አይዞሽ እንግዲህ በርቺ ምናልባት ሳይመቸኝ ቀርቶ እንደገና ያልተገናኘን እንደሆነ እኒህን ስራ ያገኙልሽን ወዳጄን እንዲጠይቁሽ አደራ እላቸዋለሁና የሚቸግርሽ ነገር ሲኖር ለሳቸው ንገሪያቸው እኔም ስመጣ እጠይቅሻለሁ» ብሉዋት ሄደ ደጃዝማች ወደ እንግዳ ቤት አንደገቡ አዛዝ አቶ በላይነህ የምትቀጠር ልጅ ማምጣቱን ሲነግሩዋቸው «እ አመጣት። ከዚያ በሁዋላ እንዳሸናፊዎች ሁሉ ጠላቶችዋ ሁሉ አሸንፋ ሰላም አገኘች ልጠከበር በበዩኋበገከር ምዕራፍ አስር ደመቀችና ወይዘሮ ጽጌ ደመቀች ምንም እንኩዋ በግብረ ሥጋ ለሚከጀጅሉዋት ስትቆጣ እንደ አራስ ነብር የማታስቀርብ መሆንዋ ስለ ታወቀላት ሁሉም ተስፋ ቆርጦ ትቶዋት ሰላም ብታገኝ የመቤትዋ የወይዘሮ ጽጌ አመል እንኩዋንስ ሰው አህያ የማይችለው ከባድ ስለሆነ ሰላምዋ ሙሉ አልነበረም እዚያ ቤት ተቀጥራ አስክትገባ ድረስ አሽከር ሆና ባታውቅም ካሽከሮች ጋር ስላደረገችና «ጥሩ አሽከሮ» የሚባሉት የሚያደርጉት ታውቅ ስለ ነበረ አንደነሱ ጥሩ አድርጋ ሰርታ እንደነሱ «ጥሩ አሽከር» ለመባል አጥብቃ ትጥር ነበር እውነትም ከደጃዝማች ጀምሮ በቤት ውስጥም ሆነ በጎረቤት ከወይዘሮ ጽጌ በቀር በስራዋ የማያመሰግናት አልነበረምሲ ባጭር ጊዜው ውስጥ «አሽከር ብሎ ዝም» የሚባል ስም ወጥትሎላት ነበር ወይዘሮ ጽጌ ግን ምንም ማለፊያ ሰራተኛ መሆንዋን ልባቸው ቢያውቅ የልባቸውን ስሜት አፋቸው መስክሮ አያውቅም ይህ እንኩዋ በምነት ላይ የተመሰረተና ልማድ አድርገው የያዙት ጭምር ሆኖ ነው እንዲያው ከበላዩ ወይዘሮ ጽጌ የተቀጠረ አሽከር የተቀጠረለትን ስራ በትክክል ሰርቶ የተቀጠረበትን ደመወዝ በትክክል ካገኘ ከዚያ አልፎ ማመስገኑ ሆነ ማቆላመጡ የማያስፈልጉ ትርፍ እንገሮች መሆናቸውን የሚያምኑት ናቸው። ሁዋላ ግን ጊዜ እያለፈ በፄደ መጠን ስራዋን አእንደማይጠሉ ባንዳንድ ምልክቶች ስለ ተረዳች አሳብዋ ማረፍ ጀመረ ለምሳሌ ገላቸውን ለማጠብም ሆነ ጀርባቸውን ለማሸት ከስዋ በቀር የሌላ ሰው አጅ ሲነካቸው አይወዱም ሌሎች ያፈሉትን ቡና ቀጠነ ወይም ወፈረ ይሉና እንደ ገና አስዋ እንድታፈላ ከስድብ ጋር ያዝዙዋታል ይልቁንም ስጋትዋን ያካፈለቻቸው አንዳንድ እዚያ ኖረው ልጠከበር በበዩኋበገከር አመላቸውን የሚያውቁ ወዳጆችዋ በጠቅላላው አመላቸው አንዲያ አስቸጋሪ መሆኑንና እንዲያውም ከስዋ በፊት ለነበሩት የውስጥ አሽከሮቻቸው አንጻር እስዋ ልውጣ ካላለች እሳቸው ውጪ አእንደማይሉዋት ካረጋገጡላት በሁዋላ ልብዋ ጸጥ አለ ወይዘሮ ጽጌ ከክፉ አመላልቸው ሁሉ ቢቆጡ ቢሳደቡ ቢራገሙ «ጣሉልኝ ብለው ቢያስደበድቡም ይህን ሁሉ ያልቻሉ አሽከሮች ራሳቸው ይወጣሉ እንጂ «ውጡልኝ» በልው አያውቁም ደመቀች መቸም ከዚያ ቤት አንገትዋን አንቀው አውጥተው ካልጣሉዋት በቀር የወይዘሮ ጽጌ አመል ስለ ከፋባት ወይም ስራቸው ስድባቸውና ርግማናቸው ስለ በዛባት መውጣት የማትፈልግባቸው ምክንያቶች ነበሩ አንዱ የባልዋ ፍራች ነው ባልዋ ታምራት ተገኘ አዲስ አበባን ልክ እንዳገሩ አንደ ኤልያስ ስለሚያውቀው እስዋን ፍለጋ የመጣና ልትከላከል በማትችልበት ቦታ ያገኛት እንደሆነ አጅዋን አንጠልጥሉ ይወስዳታል የደጃዝማች አሰፋ ቤት ግን ልክ አንደ ታቦት መቅደስ የታፈረ ስለሆነ ዚያ አስካለች ድረስ የሚደፍራት የለም። » ልጠከበር በበዩኋበገከር «ስራ። ስለዚህ ወይዘሮ ጽጌ ያደረጉትን ካደረጉ በሁዋላ እንደገና አሳቸውን መለማመጥ ጅለንት ወራዳነት መስሎ ታያትና ምንጣፍዋንና አንዳንድ አቃዋን ጠቅልላ ወዳዛዥ ተካልኝ ቤት ሄደች ምዕራፍ አስራ ሶስት ደመቀች በትምህር ሚኒስቴሩ ፊት ደመቀች ልጅዋንና እቃዋን ይዛ አደጃዝማች አሰፋ ግቢ አምስት አመት ከኖረችበት ቤት ወጥታ አዛዥ ተካልኝ ቤት ያደረች አለት ባይንዋ አንቅልፍ አልዞረም ካገርዋ ከንዶዳም ኪዳነ ምህረት ወጥታ ማርቆስ ስትደርስ ከዚያ በሁዋላ ወዴት እንደምትሄድ ግራ እንደ ገባት ሁሉ ከደጃዝማች አሰፋ ቤት ልጅዋን ይዛ ወጥታ ወዴት እንደምትፄድ ጠፍቶዋት ዙሪያው ገደል ሆኖባት አንዲሁ አንደ ተጨነቀች አንደ ተወራጨች አድራ እንደ ሳታት ቁዋሚ ገና ሳይነጋ ተነስታ አዛዥን ቀሰቀሰችና «ትምህርት ምንስቴር ይውሰዱኝ» አለቻቸው «እንዴ። ልጠከበር በበዩኋበገከር ምዕራፍ አስራ አምስት ያራዳ ልጅ። አቶ ማንደፍሮ ባገራችን ትምህርት በጣም የላቁ የውጭ ቁዋንቁዎች የሚያውቁ በጣም የተማሩ ሰው ናቸው ከጠላት ወረራ በፊት በትምህርት ከዚያም እዬተላኩ ያልደረሱበት የፈረንጅ አገር የለም በጠላት ጊዜ ታስረው ከተፈቱ በሁዋላ ይቺን ሆቴል ከፍተው ለብዙ ሰው ቀን አወጡ ሆቴልዋን ሲከፍቱ መገናኛ ብለው ሰይመዋት ስለ ነበረ ጣሊያኖች ምን ብታስብ ነው እንዲህ ያለ ስም ያወታህለት ብለው ዘግተውባቸው ነበር ሁዋላ ባማላጅ ሀይል ስም እንዲለውጡ ተደርጎ ተከፈተችላቸው» «አንተ ታዲያ » አሉና አዛዥ ወሮበላ ወይም ጫማ ጠራጊ የነበረ መሆኑን መጠየቁ ያስቀመው ይሆናል ብለው ሰግተው መልሰው ዝም ሲሉ በሻህ አሳባቸውን ቶሎ ከግንባራቸው አነበቡና «አም ያን ጊዜ አጌ በዬተራ ጫማ ጠራጊም ወሮበላም ነበርሁ ከጠላት በፊት በሚሲዮን ትምህርት ቤት እማር ነበር አባቴ ማይጭው ሄዶ ሲቀርና አናቴም ባመቱ ጥላኝ አሱን ስትከተል ምንም እንኩዋ ትምህርቴን ባልጨርስ ያው የተማርሁት ያክል ረድቶኝ ላጭር ጊዜ ያንድ ጣሊያን ነጋዴ የሂሳብ ረዳትና መዝገብ ገልባጭ ሆኘ ሆዴን ደህና ተመችቶት ነበር በመጠኑ የወር ደሞዝም ነበረኝ ብቻ አሱ አሁን አንዳልሁት ላጭር ጊዜ ነው ትቸው ወጣሁ» «ታዲያ ከተመቸህ ለምን ትተኸው ወጣህ። በሻህ አንድ ክፍል ቤት ሰጥተው ምግቡንም አዚያው አሳቸው ቤት እዬተመገበ ነበር የሰነበተ «የማገኝ ከሆነ የመንግስት ስራ መስራት ነው የምፈልገው አባባ» አለ በሻህ «ስራ አይገድም ዛሬ አገራችን ስራ የሚሰራ እው ድሀ ናት እንጂ የስራ ድሀ አደለችም በመረጥኸው መስሪያ ቤት ስራ አታጣም» «የማገኝ ከሆነ በገንዘብ ሚኒስቴር ውስጥ መስራት ነው የምፈልግ ከጣሊያኖች ጋር አሰራ የነበረ የሂሳብ ስራ ስለሆነ በመጠኑም ቢሆን የሂሳብ ስራ ልምድ አለኝ» «ሌላዉ የምመክርህ ነገር» አሉ አቶ ማንደፍሮ እንዴት እንደሚቀበላቸው ስላላወቁ እያመነቱ «ሌላዉ የምመክርህ ነገር ስራ እንደ ያዝህ የምትስማማህና በመጠትም ቢሆን ትምርት ያላት ልጅ ፈልገህ አግብተውህ ትዳር እአድንትይዝ ነውፅ ትዳር መልካም ነው ልጄ ትዳር ይሰበስባል ይቀጣል የትዳርን ያክል አባት እናት አይቀጡም ይባላል። ከዚያ በሁዋላ የሽፍትነት ድርጅቱን ለማቁዋቁዋም ከመሄዱ በፊት ስራና ደመወዙን መልሰውለት እዚያው ከሳቸው ጋር ነዋሪ ሆነ እዚያ እንዳለ ነበር አዛዥ ተካልኝና ከደመቀች ጸሀይ እስከ ልጅዋ የተገናኙ ምእራፍ አስራ ሰባት የተከስተ ተፈሪ መኮንን ትምርት ቤት መግባት ደመቀች ልጅዋ ትምርት ቤት እንዲገባ የተፈቀደለት መሆኑን ረቡእ ወደ ማታ ከሰማች ጀምራ እስከ ቅዳሜ ጥዋት ድረስ ያላትን ትንሽ ገንዘብ እያወጣች ተከስተ እወደዋለሁ ያላትን ልብስና እቃ ስትገዛ ፍልውሀ ወስዳ አስታጥባ ጠጉሩን ስታስረከርክም ማታ ታጥቦ መተኮስ የሚያስፈልገውን ልብስ እያጠበች ስትተኩስ የድሀ ገንዘብዋ ሲወጣ ትንሽ አይከብዳትም ድካም አይሰማት ተከተ አንዳንድ እንገር ሲገዛለት ደስ ባለው ቁጥር አብራ ደስ እንዳላት እንዲሁ ልጠከበር በበዩኋበገከር ለልጅዋ የሚሆን ነገር ይገኛል ወይም ይደረጋል ወደ ተባለው ቦታ ሁሉ ደስታ እንደ መኪና ሲነዳት ሰነበተች በጣም ለሚወዱት የማድረግ መስዋእትነት ከማይደረግለት ይልቅ ያድራጊውን ልብስ ደስ ያሰኛል የሚሉት አሰት አሰት አይደለም ደመቀች ላንድ አሮጌ ልብስዋ መለወጫ ሳይኖራት ድንገት እመቤትዋ ቢያባርርዋት ላንድ ቀን ስንቅ የሚሆን እንኩዋ ሳታስቀር ያላትን ሁሉ ሙጥጥ አድርጋ አውጥታ በገዛችለት ልብስና ልዩ ልዩ እቃ ልጅዋን በጣም ደስ ሲለው ማየት የሰጣት ደስታ ይህን ያክል ነው የማይባል ቅጥ መጠን ያጣ ነበር ምንም እንኩዋ የምትርት ሚኒስትሩ የሰጥዋት ተስፋ የተረጋገጠና የማያወላውል ቢመስልም ተስፋዉ እጅግ ከፍተኛ በመሆኑ አንዲሁ ትልቅ ተስፋ እንዲሁ ሊደርስ የማይችል ጥሩ እልም ሆኖ እንዳይቀር ልብዋ በምስጢር እዬሰጋ በስተፋ ፈንታ ቁርጡን የምትሰማበት ቀን ደርሶ ካላዬች ማመን አቅትዋት ያን ቀን የሞት ወይም የህይወት ፍርዱን ለመቀበል እንድ ተቀጠረ ወንጀለኛ ፍራት በተቀላቀለበት ናፍቆት ትጠባበቅ ነበር አሁን ያ ቀን የምሥራቹን ይዞ ስለ ደረሰ ደስታዋ ቃል ሁሉ ተሰብስቦ ሊገልጸው የማይችሉ አንዲያው እንዲሁ ድህነትዋን ረስታ እንደ ሀብታም ተከስተን ደስ የሚያሰኝ የመሰላትን ሁሉ ልግዛ ስትል ድካም ሳይሰማት አረፍት ሳያምራት ጠቅላላ ሁኔታዋን በማየት ብቻ ሊገመት የሚችል እጅግ ትልቅ ነእብር ቅዳሜ ጥዋት አዛዥ ጌታቸው ግቢ ሄደው ሰራተኞችን በዬስራቸው አሰማርተው ከጌቶች ተሰናብተው አስኪመለሱ ደመቀች የመጨረሻውን መሰናዶ ታሰናዳ ጀመር ያነለት ወደ ትምርት ቤት ሲሄፄድ አንዲለብሰው ተመርጦ ከተቀመጠው በቀር የተከስተ ልብስ አዬታጠበ ተተኩሶ አምሮ ማታ በሻንጣ ተከቶዋል አሁን የቀረው አልብሳ አስጊጣ ወደ ትምርት ቤት ወስዳ አስረክባ መመለስ ብቻ ነው ስለዚህ እንደ ልማድዋ እያባበለች በታቦቱ ሁሉ እአያማጠነች ቁርሱን አብልታ አፉንም እአንጁንም አጥባ ስታበቃ ከጣፄር ሙደስር የገዛችለትን ዝጉርጉር ሸሚዝ ዝጉርጉር የግር ሹራብና ቀይ ጫማ በዚህ ላይ ከታዬ በፈቃዱ የገዛችለትን ጥሩ ሆኖ ተስፍኖ የተተኮሰ ካኪ ኮትና ቁምጣ ሱሪ አልብሳ ጠጉሩን ጥሩ አድርጋ አበጥራ አሳምራ እንደ መስታወት አፊትዋ አቁማ ስታየው ሌላ መሰላት። » አሉ አዛዥ ወደ ደመቀች ዘወር ብለው «ግሩም ነው አባባ። » አሉ አዛዥ ከዚያ ሁለቱም ትንሽ ዝም ብለው ቆዩና «እኮ ታዲያ መጨረሻው ምን ይሁን። » «ጥሩዋቸው ተባልን እንጂ ጠይቁ አልተባልንም ጌታየ» ልጠከበር በበዩኋበገከር «አስቲ አባካችሁ እባካችሁ እቤት እንግባና እንነጋገር» «የለም ሌላ የታዘዝነው ስራ ስላለ እንቸኩላለን» «ለሌላኮ አደለም እስዋ ልብስ አስክትለውጥ አደጅ ከምትቆሙ ብዬ ነው» ፖሊሶች እስበሳቸው ተያይተው እናዛዥ እንዳይሰሙ ድምጻቸውን ዝቅ አድርገው ትንሽ ሲነጋገሩ ቆይተው ጠመንጃቸውን እያወረዱ በጅ በጃቸው ይዘው ገብተው አንደ ተቀመጡ ወይዘሮ ጌጤ ስላልነበሩ ደመቀች ማንቆርቆርያ ሙሉ ጠላ አቅርባ ለነሱም ለአዛዥም እአዬቀዳች ከሰጠች በሁዋላ የተረፈውን አፊታቸው አስቀምጣ ልብስ በመለወጥ ፈንታ አብራቸው ተቀመጠች አዛዥ ገና አንዱን እንደ ያዙ ፖሊሶች ቶልቶሎ ሁለት ሁለት ጠጥተው ሶስተኛውን ሲይዙ «እባካችሁ ጌቶቼ መቸም ስራ ሆኖባችሁ ነው እንጂ እንደ ሁላችን ምሽት እህት እናት ሳይኖራችሁ አይቀርም። » ይላቸዋል ግሞ ሌላው «ኦሆ ሞት ያማራት አይጥ የድመት አፍንጫ ልትልስ ትሄዳለች የሚሉት ነው የፖሊስ ባለስልጣኖችን መክሰስ በዚች ልጅ የባሰ ችግር እንዲደርስባት ማድረግ ነውፊ ይልቅ ዘመድ የሆነ ሰው እንደ ምንም ተቸጋግሮ ከነሱ ጋር መስማማት ነው» ይላል አሁንም ሌላዉ አዛዥ ይህን ሁሉ ከያፉ ከሰሙ በሁዋላ አሳባቸው የባሰውን መሰብሰቢያ ያጣ ብትን ይሆንባቸውና ማነኛውን እንደሚይዙ ግራ ይገባቸዋል በደመቀች እስራት ወይዘሮ ጽጌ ያሉበት መሆናቸውን መጀመሪያ የወሰድዋት ፖሊሶች ከነገሩዋቸውም ሌላ ሻምበል ዳኘ ለብዙ ጊዜ ግቢያችውን ረግጦት የማይውቀውን በዬቀኑ አየመጣ በቆይታ መነጋገሩ አንድ ማስረጃ ሊሆን የሚችል ነው ብቻ ደመቀች በልጅዋ ትምህርት ቤት መግባት ምክንያት ሳትሰናበት ስራዋን ከማስታጎልዋ ሌላ በፖሊስ ያን ያክል ቀን የሚያሳስር ወንጀል ትሰራለች ተብላ የማትጠረጠር መሆንዋን ስለሚያውቁ ሳትሰናበት በመፄድዋ ብቻ በፖሊስ ያሳስሩዋታል ብለው ማመኑ አስቸገራቸው ስለዚህ ደመቀች የታሰረችበትን ምክንያትም ሆነ የምትፈታበትን መንገድ ለማግኘት የደከሙት ድክምና አናውቃለን ከሚሉት የተቀበሉት አሳብ ሁሉ እንደ ተቀላቀለ ብርቱ መጠጥ ራስ የሚያዞር እንጂ ምንም የማያሳይ ስለሆነ ሁሉም «ቀን ይፍታው» ብለው ትተው በቀን ሁለት ጊዜ ምግብ አዬወሰዱ ለፖሊሶች አደራ እያሉ እያስረከቡ ዝም ብለው ይጠባበቁ ጀመር አንድ ቀን ጥዋት ወይዘሮ ጽጌ ከግራና ቀኝ መከዳዎች መካከል በተነጠፈ ፍራሽ ላይ ተቀምጠው እፊታቸው ባትሮንስ ፈንታ አንድ መከዳ አስቀምጠው በዚያ ላይ ዳዊታቸውን ዘርግተው ሲደግሙ ወይዘሮ ማረክሻቸው ገብተው ዳኛቸው መጥተዋል አሉ። ልጠከበር በበዩኋበገከር ሻምበል ዳኙ ለተጠዬይቀው መልስ በመስጠት ፈንታ አንድ ጊዜ ወይዘሮ ማረክሻቸውን አንድ ጊዜ ወይዘሮ እያዬ ዝም አለ ከዚያ ወይዘሮ ማረክሻቸው ፊት መናገር አለመፈለጉን ተረድተው «እስቲ አንድ ጊዜ ዳኛቸውን ለብቻ ላነጋግረው እትዬ» አሉ ወይዘሮ ጽጌ ወይዘሮ ማረክሻቸው እንዳይቀዬሙ ለማባበል ያክል ትንሽ ፈገግ ብለው ወይዘሮ ማረክሻቸውም ምንም ቢደኸዩ መልካም አስተዳደግ የሚሰጠው ጸጋ ገና ያልተለያቸው ስለሆኑ «አረ አሱን ሳይ ጊዜ ልነግርለት ትመለስሁ እንጂ እኔም ማድቤት የማሰራው ብዙ ስራ ስላለኝ ወደዚያ መሄዴ ነው። በሻህን ደህና አድርገህ አታውቀውም መሰለኝ ውቤ» አሉ አዛዥ የሁለቱን በጣም ቅርብ ወዳጅነት ስላላወቁ «እንደ በሻህ ደህና አድርጌ የማውቀው ሰው የለም አባባ አዛዥ ብቻ እኔ የማውቀው በሻህ ዘለሌ ሰባዊ ስሜት የሌለው የማጀራት መችዎችና የሌቦች ሰራዊት ጠቅላይ አዛዥ ነው እንጂ የጨዋታ ሰው አደለም» «አ ይ ይህ እንኩዋ አይመስለኝም። » ልጠከበር በበዩኋበገከር «እንጃ። » አለች ደመቀች ትንሽ እንደ መሳቅ ብላ አንድ ጊዜ አዝማሪው ውቤን አንድ ጊዜ በሻህን እያለዋወጠች እያዬች «ያዝማሪው ግጥማ ግጥም ተቀንሶለት በሰባት ወር መወለዴ እውነት ነው። » አለች በሻህ ትንሽ እንደ መሳቅ ብሎ። ብቻ ዳኛቸውን ስለማላውቀው ባንቺና በኔ ላይ ይህን ስራ ይሰራል ብዬ አላምንም» አሉ ደጃዝማት «በዚህ እግዚአብፄር ይኮንነኝ እንጂ አኔ ሌላ ሰው ወሰደው አልልም ወርቄን የወሰደው አሱ ነው ደመቀችን ፈቶ ከለቀቀ በሁዋላ አዚህ መጥጦ ስድብ ቀረሽ የወረደብኝንና የዛተብኝን ዛቻ ባይሰሙ ነው» አሉ ወይዘሮ ጌ ልጠከበር በበዩኋበገከር ምአራፍ ሀያ አንድ ክፉ አጋጣሚ እየጠሉት ያስጠላል ደመቀች አስራ አምስት ቀን ያክል አዛዥ ቤት ካገገመች በሁዋላ ሙሉ ጤና አግኝታ ደምዋ ተመልሶ በርትታ ያዛዥን ባለ ቤት ወይዘሮ ጌጤን በቤት ስራ ትረዳ ጀመር ወደ ፊት እድልዋ ወዴት አንደ ሚመራት አሱ እንጂ አስዋ አታውቅም ካገርዋ ከመጣች ጀምራ ከደጃች አሰፋ ሰፊ ግቢና ካካባቢዋ በቀር ሌላ ቦታ አታውቅ ከደጃች አሰፋ በቅርብ ካሉ ጎረቢቶች በቀር ሌላ ሰው አታውቅም አዲስ አበባ አምስት አመት ተቀምጣ ላገሩ እንግዳ ለሰዉ ባዳ ነበረች። ለኔ ባል ሲባል ያው አፄ የማውቀው ሞትን የሚያስመርጠው መስሎ ነው የሚታዬኝ እንኩዋንስ ባል ስለ ወዳጅ ፍቅር ሴቶች የሚያስወሩት ሁሉ እውነት አይመስለኝም እስከ ዛሬ የገጠመኝ ሁሉ ሲያወሩ እንደምሰማው ሳይሆን ያው ዱሮ እንደማውቀው ጉሮሮ እያነቀ አጅ እዬይጠመዘዘ ጠጉር አእዬይጨመደደ የሚያሰቃይ ወንድ ነው አዚህ ግቢ አምስት አመት ስኖር ያሳለፍሁትን ጭንቅ ስለሚያውቁት ለርስዎም መንገር አያስፈልገኝም ስለዚህ ለባል ገና ልቤ አልሻረምና የማይቀየሙኝ ከሆነ ቢቀር ይሻላል አባባ » «አኔስ ልቀየምም ብቻ አንቺ ገና ምኑንም ሳታውቂ በልጅነትሽ ክፉ አጋጣሚ ስለ ደረሰብሽ ክፉ አጋጣሚ አይጠሉትን አስጠልቶ ይቀራል እንደሚሉት ሁልጊዜ ያው መስሉሽ የወንድ ጉዋደኝነት ጠልተሽ እንዳትቀሪ ነው የምመክርሽ የኛ ቤት ጎረምሶች ያስቸግሩሽ የነበረውንም ከቁም ነገር አለመጣፍ ነው አነሱ አእምሮ የሌላቸው ወጠጤዎች ናቸው» አሉ አዛዥ ቅር ያለው ፊታቸውን ቀና አድርገው ጣራውን እዬተመለከተኡ ልጠከበር በበዩኋበገከር «ይቅርታ ያድርጉልኝ አባባ» አለች ደመቀች አንገትዋን ደፍታ ስታስብ ቆይታ «ይቅርታ ያድርጉልኝ የሰው ነውር መግለጽ አይገባም ብዬ ለስም አንኩዋ ላባቴ ሳልገልጽልዎሥ የቆየሁት ነገር ነበር አሁን ግን ፈቃድዎን አፈጽማለሁ ብዬ ከማልሁልዎ በሁዋላ የተቸገርሁበትን ምክንያት ተረድተው ምህረት እንዲያደርጉልኝ ያን ሸሽጌው የነበረውን ነገር መናገር አለብኝ አቶ ካሳሁን አብጤን የማላውቃቸው ለመምሰል የሞከርሁ ሳብል ነው ድሀና አድርጌ አውቃቸዋለሁ። » አሉ አዛዥ «ያ በሻህ» «እ። » ልጠከበር በበዩኋበገከር «እንዴት። » አሉ አዛዥም ምእራፍ ሀያ ሁለት የማይበላ ካሳ ደመቀች ካገርዋ ከመጣች ጀምራ አምስት አመት የወይዘሮ ጽጌ ገርድ ሆና ስትኖር መጀመሪያ በወር አምስት ብር ከዚያ ሰባት ብር ታገኝ የነበረችው ፍል ውሀ ሀኪም ቤት የጽዳት ስራ ለምስራት በወር ሀያ አምስት በር በመቀጠርዋ ባንድ ጊዜ ከድህነት ወጥታ በሀብታሞች ተራ የገባች መስሎ ስለ ታያት በጣም ደስ አላት በሁዋላ ብቻ እያደር ለቤት ክራይ ለዱቄት ስጋ ቢቀር ለክክ ቅቤ ቢቀር ዘይት ኤሌክትሪክ ቢቀር ለኩራዝ ለቅመማ ቅመም ለማገዶ ለውሀና ይህን ለመሳሰለው ለዝቅተኛ ኑሮ አስፈላጊ ለሆነው ጥርቃሚ ነገር ሁሉ የሚያስፈልገውን ወጪ ስታስበው ጊዜ ከሀያ አምስቱ ብር የሚተርፈው ወይዘሮ ጽጌ ይህን ሁሉ ችለው ይሰጥዋት ከነበረው ሰባት ብር ቢያንስ እንጂ የማይበልጥ ሆኖ አገኘችውና በደስታ ሞቆ የነበረው ስሜትዋ በቅራታ ቀዝቀዝ ማለት ጀመረ ቤት ተከራይታ ለብቻዋ መቀመጥ ስታስብ ከወጪው መክበድም የባሰ የሚያስፈራ ነገር ታያት የልጅ አባትዋ ታምራት ተገኝ አዲስ አበባን በጋ በጋ ቢያንስ አንድ ጊዜ ሳይረግጠው እንደማይቀር የታወቀ ስለሆነ ምናልባት ጠይቆ ቤትዋን ያገኘው እንደሆነ አንቆ እንደሚወስዳት አይጠረጠርም አሱ እንኩዋ አምስት አመት ሙሉ ፈልጎ ስላጣት ተስፋ ቆርጦ ረስቷት እንደሆነ የከተማዉ ሴት አዳኝ ሁሉ ብቻዋን በባዶ ቤት ሲያገኛት እንዳይምራት የታወቀ ነው። ብቻ አዛዥ እንደ አውነተኞች አንደ ቅኖች ሁሉ በሳቸውም ይሁን በሌሎች ላይ ክፉ የተሰራ መረዳቱም ቁጣቸውን መግታት የማይችሉ እሳቸው ክፉ ሲሰሩ መረዳቱም ተጸጽቶ ንስሀ መግባቱም የማይከብዳቸው ስለ ነበሩ ቶሎ እንደ ተቆጡ ቶሎ ተጸጽተው ደመቀችን ይቅርታ ለመትና ሰላም ሆነ ወይዘሮ ጌጤና ደመቀች ተመካክረው በወር አስር ብር እንድትከፍል ተስማሙ አስር ብር ደመቀች ለብቻዋ ቤት ተከራይታ ብትቀመጥ ኖሮ ከምታውጣው በጣም ያነሰ ነው ለወይዘሮ ጌጤ ግን አንድ ቀዳዳ ይደፍንላቸዋል በዚያ ላይ ደመቀች ቅዳሜ ፍል ውሀ ሀኪም ቤት ስራ ስላልነበራት የቤተሰቡን ልብስ እያጠበች ባዘቦቱ ከስራዋ ስትመለስ ወይዘሮ ጌጤን በቤት ስራ አዬረዳች ጎዱኝ ጎዳችን የማለት ስሜት በመሀከላቸው ሳይኖር ሁሉንም ደስ ብልዋቸው ተቀመጡ አንድ ቅዳሜ ወይዘሮ ጌጤ ገበያ በፄዱበት አዛዥም ከደጃዝማች ግቢ ገና ሳይመለሱ ደመቀች የሳምንት ልብስ አጠባዋን ቀደም ብላ ጨርሳ አደጅ አንደ ተቀመጠች ቀጥላ የምትሰራውን ስታስብ በሻህ ዘለሌ መጣ ልጠከበር በበዩኋበገከር «እንኩዋን ደስ አለሸ ጥሩ ስራ ማግኘትሽን ሰማሁ። » አለ በሻህ እጅዋን ለቀዋት ትንሽ ዝም ብለው ከቆዩ በሁዋላ «በምሳ ጊዜ ነው» አለች ደመቀች አንገትዋን ደፍታ እንደ ተቀመጠች «ወይዘሮ ጌጤ ወዴት ሄደዋል። መጀመሪያ ወሬውን እንደ ሰማች ገና አጅዋ ሳይገባ ሀያ አምስቱ ብር ቢዝቁት የማያልቅ መስሉዋት አንዲሁ በገዛ አጁ አየወጣ የሚፈስበት ሀያ አምስት መንገድ ለመሰራት አቅዳ ነበር አሁን በጅዋ ገብቶ ብታየው ለችግርዋ እንኩዋ የማይበቃ ሆኖ ተገኘ ልግርዋ ጫማ እንኩዋ መግዛት አቅቶዋት አዩዋት ባዶ አግርዋን ናት» አሉ አፋቸውን እንደ ሁልጊዜው በሰፊው ከፍተው አንድ ጊዜ ደመቀችን አንድ ጊዜ ባለቤታቸውን እያለዋወጡ እያዩ አዛዥ ደመቀችን ሀያ አምስት ብር የምታወጣበት ሀያ አስምት መንገድ ለመስራት አቀደች ያሉት ወዲያው ስራ እንደ ያዘች ቤት ተከራይታ ለመውጣት ወይም አዚያው ለመኖሪያዋ ለመክፈል ስለ ለመነቻቸው ተነስቶ የነበረው ጥል መሆኑ ገባቸውና ወይዘር ጌጤና ደመቀች እስበሳቸው ተያይተው ይስቁ ጀመር አዝማሪውና በሻህ ሁለቱ ሴቶች የሳቁበት ስላልገባቸው ቀጥሉ የሚገልጽ መስሎዋቸው ቢጠባበቁ አዛዥም ሴቶቹም ሲስቁ ቆይተው ዝም ስላሉ ለውጭ ሰው የሚያካፍሉት የቤተሰብ ምስጢር መሆኑ ተስማምቶዋቸው እነሱም አስበሳቸው ተያይተው ዝም አሉ «ታዲያ» አሉ አዛዥ አሁንም ቀጠሉና «ታዲያ እዩትላችሁ ምንም ያልነበራት አሁን ትንሽ ስትቀምስ ጊዜ ብዙ አማራትና ደመወዝ ካልተጨመረልኝ መኖር አልችልም ታልለች» ትንሽስ ድሮም ነበረኝ አባባ አመይቴኮ ሰባት ብር ይሰጡኝ ነበር «አይ አሱን እንኩዋ ተይው። » አሉ ወይዘሮ ባፈና ከሜቴ ጋር ሲሉ ደመቀችን አመልክተው «አትተዋወቁም ፍል ውሀ ሀኪም ቤት የምትሰራ የኔ አት ናት ዛሬ ረፍታቸው ስለ ሆነ ትምህርት ቤትሽን ላሳያትና ካንቺ ጋር ላስተዋውቃት ነው ያመጣሁዋት» ልጠከበር በበዩኋበገከር «አግዚአብሄር ይስጥልኝ በሻህ አንግዲህ እአንተዋወውቅ አሜቴ ስሜ ባፈና ይባላል ባፈና ወልደየስ» «ደመቀች ጸሀይ ናትቆ ባለልለለመደቻቸው ሰዎች ፊት መናገር አትፈልግም ከለመደች በሁዋላ ደግሞ እኔን ስሙ እንጂ አትናገሩ ባይ ናት» አለ በሻህ ሲቀልድ ደመቀች መላስዋን እንደ ታሰረች አንገትዋን ደፍታ ዝም ስላለች ጥሩ ባህሪ ነው የጭዋ ባህሪፅ በሉ አንግዲህ ፍቀዱልኝና ቡና ልጋብዛችሁል ከዚያ በሁዋላ ላይነት ያክል አንድ ክፍል አሳይቻችሁ ወደ ስራየ አመለሳለሁ ብዙ ስራ አለብኝ» አሉ ወይዘሮ ባፈና ቡና መጥቶላቸው ሲጠጡ ይገርምሀል ሰዎች ይፈልጉሻል ሲሉኝ አሰቀቅ ጀመር። አለ በሻህ። » «አዎ ቦታስ የላትም ነገር ግን ከፈለግሽ መቀመጫው ቢጠብ እንኩዋ በአንዱ ማዕዘን ወንበር ሽጉጣም ቢሆን እንድትቀበልሽ እለምናታለሁ ብቻ ሁዋላ እንዳትጸጸቺ ቀድመሽ ንጋት የሚባለውን ትምርት ቤት አይው» ንጋት የማታ ትምርት ቤት ስለ ነበረ በሳልቱ ሰኞ ማታ ከስራዋ ስትመለስ ወስዶ አሳያትፁ ባለቤቱ በሻህ እንዳለው የድሮ ጉዋደኛው ስለ ነበረ በደስታ ተቀብሎ ትምርት ቤቱን እያዞረ አስጎበኛቸው ሴቶችና ወንዶች አንድ ላይ ባንድ ክፍል የሚማሩበት ትምርት ቤት ነበር ስለዚህ አስተማሪው ቆሞ ሲያስተምር ተጠንቅቀው ከሚያዳምጡት ከዬጎረቤታቸው ጋር ቀስ ብለው የሚያወሩት ይበዙ ነበር በጥያቄም ጊዜ ሶስት ተማሪዎች በተራ አማርኛ አእንግሊዝኛና ታሪክ ተጠይቀው አንግሊዝኛ የተጠዬቀችዋ ተማሪ ትክክለኛ መስል ስትሰጥ የሁለቱ መልሶች ስህተት ነበሩ በሻህና ደመቀች ከዚያ አንደ ወጡ የትምርት ቤቱን ባለቤት አመስግነው ወዲያውም ተሰናብተውት ወደ ደመቀች ቤት ሲሄዱ «ጋሼ ግልጥ አድርጌ አልነገርሁህም እንጂ እኔኮ በቀደም ያዬነውን ትምርት ቤት ፍኖተ ድህነትን በጣም ወድጀዋለሁጹ ሴትዬዋ የሚቀበሉኝ ከሆነ እዚያ ልግባ» አለች ደመቀች «ከወደድሽው ግዴለም አንደ ምንም ተቸጋግራ ቦታ እንድታገኝልሽ እለምናታለሁ አኛም ያን ትምርት ቤት ስታቋቁም አብረናት ሳንቸር አልቀረን። አስተማሪዎች ለጥዋት የተመደቡት ጥዋት ለቀትር በሁዋላ የተመደቡት ከቀትር በሁዋላ ለማታ የተመደቡት ማታ ወደ ፍኖተ ድህነት ፄደው ለማስተማር ፊታቸውን ሲያዞሩ ወደሚወዱት የጭዋታ ቦታ አንደሚፄዱ ልባቸው አስቀድሞ በደስታ ይጨፍር ነበር ያላንድ ቀይ ስናቲም በነጻ ያገልግሉ ለነበሩ ሁሉ ለመጀመሪያ ጊዜ ጊዜያቸውን ምቾታቸውን መስዋእት አድርገው ርዳታ የሚፈልጉ ወገኖቻቸውን ለመርዳት መቻላቸው አገልግሎት የሚፈልጉ ወገኖቻቸውን ለማገልገል መቻላቸው የልብ ደስታን ከመንፈስ ኩራት ጋር ይሰጣቸው ነበር ልጠከበር በበዩኋበገከር የወይዘሮ ባፈና ትምርት ቤት ፍኖተ ድህነት ያጭርና የረዥም ጊዜ ትምርት ለመስጠት የታቀደ ነበር የመጀመሪያ በድሜ ትንሽ ጸና ያሉትን ተማሪዎች እንደ አድሜያቸው ደረጃ ሁለትና ሶስት አመት ያማርኛ ንባብና ጽህፈት በመጠትኑ እንግሊዝኛ ንባብና ጽህፈት እንዲሁም በመጠኑ ሂሳብ የመዝገብ አያያዝ ጭምር የቤት አስተዳደርና ልዩ ልዩ የጅ ስራ አስተምሮ በዬይተማሩት ትምህርት ስራ እንዲይዙ ማድርግ ነበር ሁለተኛው የረዥም ጊዜ እቅዱ ወጣትነት ያላቸውን ተማሪዎች ጠለቅ ያለ ትምርት በተለይ ማህበራዊ ኑሮ ነክ የሆኑትን ትምርቶች አስተምሮ ለሴትኛ አዳሪነት በሽታ መነሻ ወይም ጠንቅ የሆኑትንና ሊሆኑ የሚችሉትን ነገሮች ሁሉ ከማህበሩ ውስጥ ለማጥፋት ሰራተኞች አስተማሪዎችና አማካሪዎች ሆነው እንዲሰሩ ማድረግ ነበር ፍኖተ ድህነት ከሌልቾ ትምህርት ቤቶች የሚለይበት አይነተኛው ነገር ወይዘሮ ባፈና «ሞግዚት» ብለው በሰዬሙት ክፍሉ ነበር ያ ክፍል ስራው ትምርታቸውን ጨርሰው የወጡ ተማሪዎች ስራ ሲያጡ ወደ ሴትኛ አዳሪነት አንዳይመለሱ ካንድ ወገን ከመንግሥትና ከግል መስሪያ ቤቶች ጋር የተቀራረበ ግንኙነት መስርቶ ስራ በሚገኝበት ማስቀጠር ሲሆን ከሌላ ወገን በመንግሥትና በግል ድርጅቶች ውስጥ ቦታ ላልተገኘላቸው ልጆች ብድር መሪና ተቆጣጣሪ አዬሰጠ በይተማሩት ትምርት ራሳቸውን ችለው የግል ስራቸውን አእንዲከፍቱና አዬተቆጣጠሩ ብድራቸውን በዬጊዜው እንዲመልሱ ማድረግ ነበር ትምርት ቤቱን ከሁሉም ያስደነቀው ይህ ትምርት ከስራ ጋር አያይዞ መስራቱ ያሳዬው አጅግ ደስ የሚያሰኝ ውጤት ነበር ፍኖተ ድህነት ትምርት መስጠር ከጀመረ በሁለተኛው አመት መጨረሻ ላይ የተመደበላቸውን ትምርት ጨርሰው የወጡት ሁለት መቶ ያክል ተማሪዎች ጥቂቱ ባል አግብተው ትዳር ሲይዙ የሚበዙትን የመንግሥትና የግል ድርጅቶች ቀጠሩዋቸው በመንግሥትና በግል መስሪያ ቤቶች ቦታ ያልተገኘላቸው በ «ሞግዚት» በኩል ትምርት ቤቱ ሰርተው የሚመልሱት ብድር ሰጥቶዋቸው የግላቸውን የጅ ስራ ድርጅት እዬከፈቱ በመስራትም በማስተማርም ራሳቸውን መቻል ብቻ ሳይሆን ለሌሎችም ስራ ለመስጠት በቁ ደመቀች ምንም እንኩዋ ትምርት የጀመረች ትንሽ ዘግየት ብላ ቢሆን አስቀድማ ዳዊት የደገመች ስለ ነበረችና ያማርኛ ጽህፈት እንጂ ንባብ መማር ስላልነበረባት አሳብዋንና ጊዜዋን በሌሎች ትምርቶች ላይ አተኩራ በርትታ በማጥናትዋ ከሁለት አመት ተማሪዎች ጋር የተመደበውን ትምርት ጨርሳ ወጣች ለሁለት አመት የተመደበው ትምርት ጨርሰው የወጡት የጥንት ሴትኛ አዳሪዎች ተቀጥረውም የዬራሳቸውን ስራ ከፍተኛውም የክብር ኩሮ በመመስረት ላይ መሆናቸውን የሶስተኛ አመት ተማሪዎች ሲያዩ ትምርታቸውን ሲጨርሱ የክብር ስራ ይዘው የክብር ኑሮ እንደሚኖሩ ሰዎች የነገሩዋቸውም ራሳቸው ተስፋ ያደረጉትም እአድኒሁ ወሬና ተስፋ ብቻ አለመሆኑን አውነት መሆኑን ባይናቸው አይተው ስለ ተረዱ አነሱም ቶሎ ጨርሰው የሚጠብቃቸውን የተሻለና የተረጋገጠ ስራ ለመያዝ ይናፍቁ ነበር መቸም የወይዘሮ ባፈና ደስታ ዳር ድንበር አልነበረውም። » ምአራፍ ሀያ አራት ወይዘሮ እሁድ ደመቀች ፍኖተ ድህነት ሁለት አመት የሚሰጡትን እንግሊዝኛ ሂሳብና ያማርኛ ጽህፈት ሌሎችንም ትምርቶች ከጨረሰች በሁዋላ የምትሰራበት ሀኪም ቤት እንደስዋ መጠነኛ እንግሊዝኛ ለሚያውቁ የሀኪም ቤቱ ሰራተኞች የሚያስተምረውን ትምርት እዬቀጠለች ደመወዝዋ ከሀያ አምስት ብር በዬጊዜው አዬተጨመረ ወደ ሰማንያ ብር ደረሰ ይሁን እንጂ በደመወዝዋ አድገት መጠን ኑሮዋ ምንም ያክል አልተሻሻለም ሀኪሙ በሽተኞችን ሲጎአብኝ ለምትከተለው አስታማሚ ረዳት ሆና አብራ መዞር ስትጀምር ጫማ ማድረግና ከድሮው የተሻለ ልብስ መልበስ ግዴታ ስለሆነ የሸራ ጫማና ጥቂት መለወጫ ልብሶች መግዛትዋ በቀር ከዚያ አልፋ በድሜም ሆነ በስራ ጉዋደኞችዋ ላይ የምታየው ልብስና ጌጣጌጥ አዛዥ ተካልኝ ቤት ለምትኖርበት አስር ብር እንድትከፍል ከወይዘሮ ጌጤ ጋር የተስማምሙ ደመወዝዋ ሀያ አምስት ብር በነበረበት ጊዜ ስለ ነበረ አሱን እንኩዋ ለመጨመር እዬፈለገች ስላቃታት አንዳንድ ጊዜ በጭዋታ መሀከል የኑሮ ውድነት ወይም የገንዘብ ማጠር ነገር ሲነሳ ታፍርና ትሰቀቅ ነበር አዛዥም ሆኑ ባልተቤታቸው ትከፍለው የነእአብረው በላይ አልከፈለችም ብለው ቅር አንደማይላቸው ታውቃለች ብቻ እነሱ አይሆንም ሲሉ ይቅር እንጂ አስዋ ደመወዝዋ ሲያድግ ላዛዥና ለወይዘሮ ጌጤ አንዳንድ ልብስ ወይም ሌላ ስጦታ ማለትዋ ቢቀር ለመኖሪያዋ እንኩዋ ትንሽ መጨመር አድርጋ ለመርዳት መጠዬቅ በተገባ ነበር ነገር ግን የማትችል መሆንዋን ስለምታውቅ እስከ ማንሳቱም ፈራች ከደመወዝዋ በጣም የሚበዛውን ክፍል የምታጠፋው በተከስተ ላይ ነበር በዬሳምንቱ አሁድ ተከስተ ትምርት ቤት ከገባ ጀምሮ አንድ ቀን እንኩዋ ታጉሎ የማያውቅ ምሳ ትወስዳለች ቅዳሜ እስከ ቀትር ድረስ የስዋንም ያዛዥንም የባልተቤታቸውንም ልብስ አጥባ ልጠከበር በበዩኋበገከር የሚተኮሰውን ተኩሳ ቤት አጽድታ ትጨርስና ከቀትር በሁዋላ ለተከስተ የሁድ ምሳ የሚያስፈልገውን ስትገዛ ታመሻለች ከዚያ ራት ተበልቶ አዛዥና ባልተቤታቸው ወደ ምኝታቸው ሲሄዱ እስዋ ድግስዋን መደገስ ትጀምራለች የተከስተ እንጀራ ልዩ ነው ጤፉ በውቅ ተገዝቶ በጥንቃቄ ተበጥሮ ተፈትጎ ከነጭም ነጭ ከጥሩም ጥሩ ከሆነ በሁዋላ ተፈጭቶና ተቦክቶ የሚጋገር ባፍ ገብቶ ሳይቆም ጉሮሮ የሚሰርቀው ነው። ተከስተ እኒያን እንባ ያዘሉ የናቱን አይኖች በነሱም በኩል አልፎ የናቱን የተጨነቀ ልብ ዘቅዝቆ ሲመለከት ትንሽ ቆዬና «ቬሪ ሶሪ ስላሳዘንሁሽ በጣም አዝናለሁ አመዬ» አለ ቁጣው ቀርቶ ጸጸት ባሰለሰለው ድምጽ «እኔንስ ምንም አላሳዘንኸኝ ይልቅ አንተን አሳዛንሁህ አልሞላልኝ ብሎ አሳዘንሁህ አለች ደመቀች አይኖችዋን ሞልቶ የነበረው እንባዋ ተርፎ መፍሰስ ሲጀምር እንዳያይባት አንገትዋን ወደ ላይ ካቀናችበት ወደ መሬት መልሳ ከዚያ ተከስተ አንገትዋን አቅፎ ራሱን በራስዋ ላይ ጥሎ ሁለቱንም ሳይናገሩ ዝም ብለው በዬልባቸው ራሳቸውን ሲወቅሱ ከቆዩ በሁዋላ «እባክህ አትዘን ብድር ያላገኘሁ እንደሆነ ብዬ ፈርቸ ነው እንጂ ገንዘብ መቆጠብ ፈልጌ አደለም» አለች በሹክሹክታ የሰይጣን ጆሮ ሰምቶ እርቁ እንዳይፈርስ «ሸሚዙና ጫማው ብቻ ለዛሬ ሳምንት እሁድ የሚደርሱልኝ ከሆነ ሌላው ቢቆይ ግዴለም ሲመችሽ ትገዥልኛለሽ ካልተመቸሽ ይቅር» አለ ልጅዋም እንደናቱ በሹክሹክታ ለጊዜው በናትና ልጅ መሀከል አርቅ ሰላም ወረደ ምእራፍ ሀያ አምስት በሻህ ደማሙ ደመቀች ወደ ቤትዋ ስትመልስ ምሳ ተበልቶ ሲያልቅ ደረሰች ወይዘሮ ላቀች ተገኔ የሚባሉት የወይዘሮ ጌጤ ዘመድና አቶ በላቸው ይፍሩም አዚያ ነበሩ ወይዘሮ ላቀች የደጃዝማች ሉልሰገድ ክንፌ ሚስት በድሮ ባህልና ልማድ አድገው የበለተቱ የዘመኑን ስልጣኔ አንደ አብደት የሚቆጥሩ እጆግ የተከበሩ ወይዘሮ ነበሩ ዘምዳቸው ወይዘሮ ጌጤ ታመው ሰንብተው በጎ ከሆነ በሁዋላ ስለሰሙ ሊጠይቅዋቸው መጥተው ነበር አቶ በላቸው ይፍሩ በትምርት ሚኒስቴር የትምርት አመራር ክፍል ሹም የወይዘሮ ላቀችን ዘመድ ያገባ ወጣት ነበር የወይዘሮ ላቀችን ኦቶሞቢል ባለቤታቸው ደጃዝማች ሉልሰገድ ይዘውባቸው ወደ ግቢ ስለ ፄዱ ሊያደርሳቸው መጥቶ ነበር ደመቀች ከመድረስዋ ትንሽ ቀደም ብሎ በሻህ ዘለሌም አዝማሪው ውቤን ፍለጋ መጥቶ ስላጣው ሊሄድ ከበሩ አጠገብ ቆሞ ነበር «ዛሬ እንኩዋን አገኘሁ ጋሼ ለልጄ አቃ ትገዛልኛለህ ተቀመጥና ምን ምን አንደምትገዛልኝ ልንገርህ» አለች ደመቀች ለወይዘሮ ላቀች ለጥ ብላ እጅ ነስታ ለሌሎች ሰላምታ ሰጥታ ስትቀመጥ «ምን እቃ ነው የምገዛልሽ። » አለ በሻህ «እንዴት። የዛሬን ልጆች ጥቅም እንጂ የወላጆችና የዘመድ ፍቅር አይስባቸውም» «የኔ ልጅ እንዲህ አደለም ባታውቀው ነው» አለች ደመቀች «ያንቺ ልጅ አንቺ አንደምትይው ይሆናል እኔ የማውቃቸው ግን እጌኔ አንደምለው ናቸው አንድ ማስረጃ የሚሆን ምሳሌ ልስጥሽ መንግስት አዬከፈላቸው ባዳሪነት የሚማሩት ልጆች ሁሉ ትምርት ቤት ሲዘጋ የረፍቱን ጊዜ ከዬዘመዶቻቸው ጋር ለማሳለፍ አዚህ ከተማ የሚኖሩት እዚህ ከዬጠቅላይ ግዛቱ የመጡት ወደያገራቸው ሲሄዱ በዬወሩ ለትምርት ቤት የሚከፍልላቸው ታስቦ ፄደው ለሚቆዩበት ጊዜ ገንዘቡን ይዘው ይሄዳሉ ያን ገንዘብ ይዘው አውነት ወደ ዘመዶቻቸው የሚሄዱ ይመስልሻል። በምሳ ጊዜም አዛዥና ባልተቤታቸው ከንግዳዋ ጋር ሲበሉ ወደ መሶቡ ለመቅረብ እንኩዋ አልፈለገም ባለቤቶቹ ለመና ሲያበዙ «አሱ ይህን የኛውን አይበላም ተዉት» አሉ ወይዘሮ ላቀች እሱም ልጠከበር በበዩኋበገከር «ጸረ አሁን በልቼ ስለ መጣሁ ነው» ብሎ ትንሽ አንደ መሳቅ አለና አንገቱን ደፍቶ ዝም አለ ከዚያ በሻህ ገብቶ እጅ ነሳ ተጠርጎም ተተኩሶም የማያውቅ ጠቆር ያለ ሱሪና ባለቀበቶ ካኪ ኮት ለብሶ ሁለቱም ባንድነት በቀበቶው ከርፈፍ አድርጎ ታጥቆ ከንጹህነቱ በቀር መተኮሻ ያልነካው ጨምዳዳ ሸሚዙን ለብሶ ቀለምና ቡርሽ ነክቶት የሚያውቅ የሚመስል ከባድ ጫማ አድርጎ እንደ ወጣቶች ፈጠን ፈጠን ሳይል ከባድ ጫማውን አእዬጎተተ ቀስ ብሎ ስለ ነበረ ገብቶ እጅ የነሳ በላቸው በድሜ ባይሆን በሌለው ሁሉ የናዛዥ ወይም የቀድሞው ትውልድ ውገን አድርጎ ቆጥሮት ትንሽ ቀና ብሎ ተመለከተውና አይኖቹን ወደ ነበሩበት መለስ እንዲያውም መጀመርያስ ካለባበሱና ከጠቅላላ ሁፄታው አዚያው ያዛዥ ዘበኛ ወይም አታክልተኛ ወይም ባልተቤታቸው ተነስተው የጅ ሰላምታ ሲሰጡና ከዚያም ደመቀች እንዲቆይ ስለ ለመነችው ቅር አያለው መቀመጡን ሲያይ አሽከርም ቀላዋጭም አለመሆኑን ገመተ ነገር ግን እንኩዋንስ እንደ ትምህርት አሰጣጥ ባለ ከፍተኛ ፍልስፍና ላይ አሳብ ለመስጠት የሚንጠራራ ንባብና ጽህፈት በቅጡ የሚያውቅ ይሆናል ብሎ አልጠረጠረም በሻህ መጀመሪያ ካዛዥ ጋር ተማሮችን እዬነቀፈ ሁዋላም ወይዘሮ ላቀች ተማሮች ከወገኖቻቸውና ከባህላቸው እዬራቁ ወደ ባእድና ወደ ባአድ ባህል አዬተጠጉ የሚሄዱ የሚማሩት የፈረንጅ ትምርት የሰይጣን ትምርት ስለሆነ ወይም ስምንተኛው ሺህ ስለ ደረሰ ነው ሲሉ አሳቸውን እዬደገፈ መናገሩ ያው የነሱ ቢጤ ያው እንደነሱ ከጥንቱ ዝባዝንኪ አንድ ነቁት ከሚወድቅ ሰማይና ምድር ቢያልፍ የሚመርጥ ያው እንደነሱ የዘመናዊን ትምርት ከፍተኛ ዋጋ የማያውቅ ስለሆነ መሆኑን አምኖ ይህ ሁሉ መጀመሪያ ስለሱ የገመተው ያልተሳሳተ መሆኑን አምኖ ይህ ሁሉ መጀመሪያ ስለሱ የገመተው ያልተሳሳተ ሆኖ ታዬው ስለዚህ መጀመሪያ ባላቸው እዚያ ያሉትን ሁሉ በሻህን ጭምር እንዳላዋቆች በድሜ ባይሆን በአእምሮ እንደ ህጻናት ስለ ዘመኑ ትምርትና ስለ ተማሮች እዬተከራከሩም እአያተቱም ሲለፈልፉና ሲንጫጩ ጫጫታው አያጫወተው እያተቱም ሲለፈልፉና አንገቱን ደፍቶ ራስን እአዬወዘወዘ አንዳንድ ጊዜም ከንፈሮቹን አያሞጠሞጠ ከመስማት በቀር አንድ ጊዜ እንኩዋ አፉን አልከፈተም። ስምህን አልያዝሁትም የኔ ስም በላቸው ይፍሩ ይባላል ስራየ በትምርት ሚኒስቴር ውስጥ ነው» ልጠከበር በበዩኋበገከር «በሻህ ዘለሌ እባላለሁ ስራየ ስራ የለኝም» አለ በሻህ ለስራው ስም ሲፈልግ ትንሽ ቆይቶ ካጣ በሁዋላ «ያ ውቤ እዚህ ቢኖር ስራህ ምን መሆኑን ይነግርልህ ነበር» አሉ አዛዥ አቁዋርጠው አዬሳቁ «አባባ። መቸም ስራ የሌለው ሰው ወሮበላ ነው የሚባል አለ በሻህ እንደ መሳቅ ብሉ «አየ እሱ እንኩዋ እንጂ። አቶ በሻህ አይደለም። » ልጠከበር በበዩኋበገከር «አይደለም» አለ በሻህ በለዘብታ «ታዲያ ምንድን ነው። » አለ በሻህ ለመሄድ ሲነሳ ትንሽ እንደ መሳቅ ብሉሎ «እንዲያው ተገኔ ይ ሙት ይህ ሰው በጣም ደማም ነው እባክህ እዬይመጣህ ጠይቀን» አሉ ወይዘሮ ላቀች ምእራፍ ሀያ ስድስት እስመ ነፍስ ተአምር ቀታሊሁ በሻህ የደመቀችን ልጅ ተከስተን አይወደውም ነበር ስለዚህ ደመቀች ለሹ ሸሚዝና ጫማ አንዲገዛለት ስትለምነው አልችልም ሊል ፈልጎ ነበርሱቆ ነገር ግን የሚያጠግብ ምክንያት ሳያሰናዳ ድንገት ስለ ነበረ የለመነችው ቅር አያለው እያመነታ የሸሚዙንን ቁጥሮች ከሚገዙበት ገንዘብ ጋር ተቀበለ ተከስተን መጀመሪያ ያየው ትምርት ቤት ከመግባቱ በፊት እናቱና አዛዥ ተካልኝ እቃ ሊገዙለት ገብያ ይዘውት ሄዶ ነው ከዚያ በፊት ሆነ ከዚያ በሁዋላ አይቶት አያውቅም። » አለ በሻህ ሁለቱም ዝም ብለው ከቆዩ በሁዋላ «አባባ አዛዥ ምን አሉ። » አለች ደመቀች። » «ይሆናል» አለች ደመቀች አዎታዋን ራስዋን ወደ ላይ በመግፋት ጭምር እዩገለጸች «አዎ ታዲያ ያንጊዜ መጀመሪያ ስንገናኝ ልጅሽ ሰባት አመቱ እንደ ነበረ ስትነጋገሩ መስማቴ ትዝ ሰለሚለኝ እንግዲህ ዛሬ ያስራ ሰባት ወይም ያስራ ስምንት አመት ገበዝ ነው ማለት ነው» ሲል በሻህ «እንዲያውም አሁን አስራ ዘጠኝ ሆኖታል» አለች ደመቀች «እሺ አስራ ዘጠኝ ታዲያ ያ የተገናኘንበት ቀን እሱን ትምርት ቤት ለማስገባት አባባ አዛዥና አንቺ አቃ ልትገዙለት ገበያ ወጥታለችሁ ነው። » ልጠከበር በበዩኋበገከር «ስማ በሻህ። ታዲያ ምንም እንኩዋ ከኒያ ሁሉ መሀከል ወዳንተ ክፍል የሚመጡት ጥቂት ቢሆኑ እነሱን በደህና ፊት ተቀብለህ ሳይጉላሉ ጉቦ አምጡ ሳይባሉ በዬለቱ ጉዳያቸውን አዬፈጸምህ ወደዬሰራቸው አንዲመለሱ ብታደርግ ባመቱ ብዙ ድሀ ስራ ከመፍታት ከመጉላላትና ከጉቦ ታድናለህ ማለት ነው አንዲህ ያለው ቅን አገልግሎት ከብዙዎች የመንግስት ሰራተኞች ስለማይገኝ ለባለጉዳዮች ትልቅ ርዳታ ትልቅ ጥቅም ነው «ኛ ደመቀች ልጅዋ አንድ በመሆኑ ከሱ የሚለይ ወይም በሱ ላይ አንድ ክፉ ነገር ቢደርስ የህወትዋ መጨረሻ የሚሆን አዬመሰላት ዘወትር እንደ ፈራችና ልብዋ እንደ ተንጠለጠለ ነው የምትኖር ታዲያ እድላችሁ አምሮ አንድም ይሁን ካንድ በላይ ብትወልዱ አሳብዋንና ፍቅርዋን ከሱ ሌላ የምታሳርፍበት ታገኝና እንዲያ ካለ የዘወትር ፍራት ምናልባትም ከክፉ አደጋ ትድናለች ያችን ውብና ደግ ልጅ ሊደርስባት ከሚችል ክፉ አደጋ መጠበቅ ከማይወጣ ጸጸት የሚያድንና አይከፈል ዋጋ የሚከፈልበት ነው» ሰምቶት ልቡ እንደ መታወቅ አለበትና ቀና ብሎ እንባ ባቀረሩ አይኖቹ ላንድ አፍታ አየት አድርጎ መልሶ ራሱን ሰፋ «ኛ የሚወዳትንና የምትወደውን ሴት አግብቶ የሚኖር ሰው ደስታው መልስ የሌለው የደስታ ሁሉ ቁንጮ ለመሆኑ አፄ አንድ ምስክር ነኝ ባሳለፍሁትና በምኖረው የችግር ኑሮ የምሽቴን የውባዬሁን ፍቅር ባያድለኝ ኖር ምን ይውጠኝ እንደ ነበር አላውቅም። ታዲያ ይህን የወገብ ሳብ ገፋና ያንገት ዘፈን የተዋሀዱበት ዳንስ አንዳንድ ሰዎች የፈረንጅ ያበሻ ክልስ ዳንስ ይሉት ነበር «አንቺ ልጅ አንቺማ «ሙዚቃ ሲጀምር ፈረንጅኛውን ተማሪዎቹ ሁሉ ግሩም አድርገው ስለሚያውቁት ወንድና ሴት እየሆኑ እንደ ተጣመሩ በዚያ ሰፊ ሜዳ «ዳንግላሳ» ግልቢያቸውን ይጋልቡ ጀመር ነገር ግን ካበሻ ያንገት ዘፈን ጋር የተዋሀዱትን ክልሱን «አንቺ ልጅ አንቺማ» ከሶስና በቀር አንድ እንኩዋ የሚያውቀው አልነበረም ስለዚህ ሶስና ጉዋደኛዋን አዬመራች «አንቺ ልጅ አንቺማ» ን እሱዋ በምትኖርበት በደጃች ውቤ ሰፈር በሚደነስበት ስልት ስትደንስ መጀመሪያ ባጠገብዋ የነበሩት ከዚያ በነሱ ሳቢያ የነሱን አይን እዬተከተሉ ራቅ ያሉት ሲያዩ ትንሽ በትንሽ ጨዋታቸውን ትትተው እዬቆሙ እስዋንና ጉዋደኛዋን ይመለከቱ ጀመር ጉዋደኛዋ ተከስተ ታምራት ነበር ተከስተ ያነለት ሶስና እይመራችው ከስዋ ቀድቶት ይሆን ወይም ቀደም ብሎ አሌላ ቦታ አይቶት «ክልሱን ዳንስ ሲደንስ በመጠኑ ደህና ነበር ልጠከበር በበዩኋበገከር መቼም እዚያ ለነበሩት ተማሪዎች ሁሉ አስተማሪ ሊሆን ይቻላል በመጨረሻም ተማሪዎች ሁሉ ደክሞዋቸው ስለ ነበረ ሜዳውን ለሶስናና ለተከስተ ትተው ወደ ጠረጴዛቸው እየተመለሱ ተቀመጡ እነሱን ይመለከቱ ጀመር ተከስተ ምን ጊዜም ቢሆን በግብዣ ልብስ መርጦ የመለበስ ልማዱ የታወቀለት ስለ ነበረ ያነለትም የለበሰው እዚያ ከጉዋደኞቹ መሀከል ተወዳዳሪ አልነበረውም ግራማፎኑ «አንቺ ልጅ አንቺማ» ን አንድ ዙር ተጫውቶ ሲጨርስ ብዙ ልጆች «ቢስ ቢስ ይደገም። ልጠከበር በበዩኋበገከር «እኔ እንጃ። ደመቀች ምንም እንኩዋ ከፊት በሩ ዘበኛ ስለ ልጅዋ የሰማችው ሁሉ በራስዋ ውስጥ ልዩ ልዩ ተቃራኒ አሳቦች አለ ፈጠረ ሙሉ ሰላም ማግኘት ባትችል ያን ያክል ጊዜ ወሬው የጠፋ ያለ ጥርጥር ክፉ አደጋ ቢደርስበት ነው ብላ ተጨንቃ ስለ ነበረ ከዚያ ተጭኖዋት ከነበረው ከባድ ጭንቀት ቀለል ብሎዋት ተመለሰች ልጠከበር በበዩኋበገከር ብቻ የምእራብ በር ዘበኞች እንዳሉትና ደመቀችም ወደ ቤትዋ ስትመለስ ተስፋ እንዳደረገችው ተከስተ እንኩዋንስ በማግስቱና በሳልስቱ በሳምንትም ሆነ ባስራ ምስት ቀን ውስጥ ለናቱ ስልክ አልደወለም አውቆ የተሸሸገ ቢጠሩት አይሰማም እንደሚሉት የምአራብ በር ዘበኞች ገና በሩቅ ሲያያቸው እዬተሰወረ እስከ ብዙ ቀን ድረስ ፈልገው ሊያገኙት አልቻሉም አንደ ምንም ፈልገው አግኝተውት የናቱን መጨነቅና በስልክ እንዲያነጋግራት አደራ ማለትዋን ከነገሩት በሁዋላ እንኩዋ አንዳንድ ጊዜ «ስልክ ደውዬ የሚያነሳ አጣሁ እያለ አንዳንድ ጊዜም እስዋን ላገኛት ስላልቻልሁ ደህንነቴን እንዲነግርልኝ ለደጃዝማች አሰፋ ስልከኛ ነግሬ ነበር አያለ ውሸት ሲነገራቸው ሰነበተ እስዋም እሁድ አሁድ ስትሄድ አታገኘውም ይሸሸጋል አንድ ቅዳሜ አናዛዥ ተካልኝ ቤት ምሳ ከተበላ በሁዋላ እሳቸው ወደ ስራቸው ሊሄዱ ሲነሱ በሻህ ዘለሌ ደረሰ «የምንጠላህ ይመስል ምሳችነን በልተን ስንነሳ የመጣህ ስም ነው። » አያለች አንደገና ምሾዋን መጥራት ጀእአምረች መቸም የሚወዱት ሲበደል እንኩዋንስ ምክንያት ተገኝቶ ባይገኝ ፈጥኖ ለተወዳጁ በደለኛ ይቅርታ ማድረግ ቀላል ስለሆነ ዘበኛው የነገራት የማይበቃ ምክንያት ልጅዋን ከበደሉ አጥቦ አጥርቶ አሳያትና ልጅ ልጄ ማለትዋን ቀጠለች ከዚያ በሻህ ከተቀመጠበት ተነስቶ ትከሻዋን ይዞ «አባክሽ ይብቃሽ የኔ እመቤት አሁን አሱ ወንድሜ እንደ ነገረን ተከስተ እዚያ እንደ ደረሰ ስለሚኖርበት መልካም ሁኔታም ከዚህ ሳይሰናበትሽ ስለ ሄደበት ምክንያት ትክክለኛውን በዝርዝር ሲስፍልሽ ነገሩ ሁሉ እንዲህ አሁን ከፍቶ እንደሚታይሽ አለመሆኑን ትረጃለሽ አሁን ተነሺ እንዚድ» ብሎ አሰንሳትና ዘበኛውን አሱም እስዋም አመስግነው ተመለሱ አዛዥ ቤት እንደ ደረሱ «ሂድ እንግዲህ ጋሸ እአእግዚአብፄር ይስጥልኝ» አለች ደመቀች በግድ ፈገግ ለማለት አዬሞክከረች ነገር ግን ፈገግ እንዲል የተገደደው ፊትዋ የሚያሳዬው ቢኖር ጭንቀትዋን ብቻ ነበር ያነለት አዛዥና ወይዘሮ ጌጤ ቢያባብሉዋትም ቢቆጡዋትም ሰውነትዋ ከመታወኩ የተነሳ ትኩሳት ስለ ነበረባት ውሀ ደጋግማ ከመጠጣት በቀር ራት አልበላችም ልጠከበር በበዩኋበገከር ምእራፍ ሰላሳ አንድ በፍቅር ፊት የሚቆም ቆራጥ ጀግና አለ። ደመቀች የምስራች መርሶዋን ከተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት አረጋግጣ ወደ ቤትዋ አንደ ተመለሰች በሻህ አድርሶዋት አስዋ ወደ መኝታ ቤትዋ ስትገባ አሱም በቀጥታ ወደ ቤቱ ሂዶ ራሱን ከበላ በሁዋላ ሌሊቱን ሙሉ እንቅልፍ ባይኑ ሳይዞር አደረ ካንድ ወገን የደመቀች ጭንቅ ምጥዋ አንዲያው ሁኔታው ሁሉ ባይነ ህሲናው መጥቶ እዬታየው አንድ የሚያጽናናት ነገር ቶሎ ካላገኘች ክፉ አደጋ ሊደርስባት ይችላል ብሎ ስለ ሰጋ ከሌላ ወገን ስለሱና ስለስዋ ጋብቻ ያሰበው አሳብ የሚፈጸም ቢሆን እንኩዋ ገና ጊዜ ስለሚወስድ ስለ መሰለው እነኝህን ሁለት ተቃራኒ ነገሮች ለማስታረቅ ነበር እንቅልፍ አጥቶ ሲታገል ያደረ በሻህ በኢትዮጵያ «ነጻነት» የሚባለው ቃል የውነተኛ ትርጉሙን እንዲያገኝና የኢትዮጵያ ህዝብ ለዜግነት ግዴታው ተገዥ ብቻ ሳይሆን ለመብቱ ባለቤት ጭምር እንዲሆን የሚያደርግ ስራተ መንግሥት ተቋቁሞ እስኪያይ ድረስ ምሽት አግብቶ ንብረት መስርቶ ላይኖር ሁልጊዜ ለትግል ታጥቆና ተጠንቅቆ ሊኖር ቃል ኪዳን የገባ ሰው ነበር ነገር ግን አንድ ቀን አዝማሪው ውቤን ጋብዞ አንድ መጠጥ ቤት ተቀምጠው አእዬጠጡ በረዥሙ ከተነጋገሩ በሁዋላ የጊዜው ትውልድ ያስተሳሰብም ሆነ ያሰራር መንፈስና ባገሩ የነበረው ጠቅላላ ሁኔታ ሁሉ እንዳለ እስከ ቆዬ ድረስ ብቻውን ምንም ያክል ራሱን በድሉ ቢኖር ያ ቃል ኪዳን የተገባለት የተቀደሰ ተግባር ፍጻሜ ሊያገኝ የማይችል መሆኑን ተረድቶ ኑሮውን አዝማሪው ውቤ በመከረው መንገድ ለመምራት ስለ ወሰነ ራሱን አስችሎ የሚያኖረው ስራ ይዞ ደመቀችን አግብቶ ለመኖር የሚችልበትን መንገድ በማሰብና በማጥናት ላይ ነበር ስራ የማግኘቱ ነገር እንኩዋ አምብዛም አላሰበውው ስራ በፈለገው የመንግስት መስሪያ ቤት ቢጠይቅ እንደማያጣ እርግጠኛ ነበር እርግጥ በመጀመሪያ ሰውነቱ እንደ ተጎሳቆሉ ጎስቁዋላ ልብሱን ለብሶ ስራ ፍለጋ ከፄደ ምንም ያክል አዋቂ ቢሆን ከተላላኪነት በላይ ላለ ስራ የሚከጅለው መስሪያ ቤት አንደሌለ ስለሚያውቅ ለሰውነቱና ለልብሱ ግሩም አድርጎ መጠንቀቅ ጀምሮዋል ሌላ በስራ በኩል የሚያሳስበው ነገር ቢኖር የሚሰራው ስራ በመጠኑም ቢሆን ለሱ ደስታን ለሚያገልግላቸው ለመስሪያ ቤቱም ወደሱ ክፍል ለሚመሩት ባለ ጉዳዮችም ጥቅምን የሚሰጥ እንዲሆንና ወዲያው ምሽት ማግባት አስከትሎ ለሚመታው ጉዋዝና መዘዝ የሚበቃ ደመወዝ የሚያስገኝ እንዲሆን ነው ለብዙ ሴቶች ባሎቻቸውን ለሚወዱት እንኩዋ በጥሩ አቃ ያጌጠ ጥሩ ቤት ኖሮዋቸው ያን ለማሳየት ሲጋብዙ በጉዋደኞቻቸው ፊት መቶ ብር እንደ ትንሽዋ መሀረባቸው ከቦርሳቸው ሲመዘዙ መታየቱ የሚሰጣቸው ደስታ የባሎቻቸው ፍቅር ከሚሰጣቸው ደስታ ባይበልጥ አያንስምፁ ስለዚህ በጋብቻ ኑሮ አቤት ውስጥ ሰላም አግኝቶ ለመኖር ያን ያክል ባይሆን አንኩዋ ምሽት በጉዋደኞችዋ ዘንድ የማታፍርበት ቤት እንዲኖራትና በገንዘብ ተቸግራ ከጉዋደኞችዋ ያነሰች መስሎ አንዳይሰማት ራስን የሚያስችል ደመወዝ የሚያስገኝ ስራ መያዝ አስፈላጊ ነው ብቻ ይህ አስቸጋሪ ሆኖ አልታዬውም። ትናንት ጦምሽን እንዳደርሽ ዛሬም ቁርስ አለመቅመስሽን ጌጤ ነገረችኝ» ልጠከበር በበዩኋበገከር «ጥዋት እንዳመመኝ ነበርሁ ከረፈደ በሁዋላ ነው የተሻለኝ አሁን ከተሻለኝ በሁዋላ ግን ቁርስ የበላሁ እንደሆነ ምሳየን ይከለክለኛል ብዬ ከናንተ ጋር እንድበላ ነው ቁርስ ያልበላሁ» አለች አውነትም አምሳ ላይ ሆድዋ ተቀብሎዋት አዬሳቀች አዬተጫወተች ደህና አድርጋ ስለ በላች አዛዥንና ወይዘሮ ጌጤን በጣም ደስ አላቸው ማታ ጉዋደኛዋ የሽመቤት መጥታ ካልተሻላት በነጋው ሰኞ ወደ ሀኪም ቤት ፄዳ አንድትመረመረና መድሀኒት እንዲታዘዝላት ከተሻላት ግን ሳታርፍ ዘለግ ያለ ጊዜ በስራ ላይ ስለ ቆየች አስር ቀን ያክል አርፋ እንድትመለስ» የሀኪሙን መልእክት ነግራ ስታጫውታት አምሽታ ሄደች ምእራፍ ሰላሳ ሁለት የተባረከ ሴራ በሻህ ቀጨኔ አዝማሪው ውቤ ቤት ሲደርስ የምሳ ጊዜ ተቃርቦ ስለ ነበረ ያዝማሪው ምሽት ውባዬሁ ማድቤት ከሰራተኛዋ ጋር ምሳ ለማሰናዳት ደፋ ቀና ትል ነበር አዝማሪው ብቻውን ሲሆን የክራሩንና የገዛ ድምጹ አያጫወቱት አደጅ ተቀምጦ ነበር መቸም ትልልቅ ሰዎችና ድርጅቶ ግብዣ አድርገው አንግዶቻቸውን እአእንዲያጫውትላቸው ተዋውለው ካልወሰዱት ወይም አእወዳጆች ቤት ተለምኖም ይሁን ራሱ ፈልጎ ሲጫወት ካልሄደ አዝማሬው ውቤ እንደ ተራ አዝማሪዎች ትንንሽ ገንዘብ ለመለቃቀም በዬቤቱና በዬመሸታ ቤቱ ይዞራል አይባል። » ይባላል ትል ነበር ልጠከበር በበዩኋበገከር ባገር ካለህ ምንም ቢሆን በምሳ ጊዜ አላጣህ ብዬ ነው አሁን የመጣሁ ወዲያውም ምሳየን አዚህ አንድበላ ጭምር ነው» አለ በሻህ ገና አጥሩን ሲገባ ስላምታ አንኩዋ ከመስጠቱ በፊት ከዚያ አዝማሪው ውቤ ተነስቶ ሰላምታ ሰጥቶት ተያይዘው ወደ ቤት ገቡ ያዝማሪው ውቤ ቤት ከማድቤቱ ሌላ አንድ የንግድና የመብል ቤት ባንድ ላይ አንድ ምኝታ ቤት አንድ መታጠቢያ ቤት ብቻ ያላት ካባቱ ከባላምባራስ አጎናፍር የወረሳት ትንሽ ቤት ነበረች መታጠቢያ ቤቱን እንዲያውም ሁዋላ እሱ ያስቀጠለው ነበር ያች ትንሽ ቤት እሱና ከሱ በሁዋላ ተከታትለው የተወለዱት ሁለት እህቶች የስበሳቸውንና የወላጆቻቸውን ፍቅር አንዲሁም ሌላውን ስጋዊና መንፈሳዊ ሀብት ሁሉ አንድ ላይ በማህበር እዬተካፈሉ የልጅነትና የወጣትነት አድሜያቸውን ያሳለፉባት በውስጥና በዙሪያዋ ያለው እያንዳንዱ ጥቃቅን ነገር ሁሉ የዚያ ቤተሰብ የህይወት ታሪክ በዝርዝር እንደማይጠፋ ሆኖ ተቀርጾ የሚያይባት ያን ሁሉ የምታስታውሰው የዚህ ሁሉ የትዝታ ማህደር ስለ ነበረች ለምንም ትልቅ እንገር ሊለውጣት አይፈልግም ነበር «አሜቴ የት ትሄዳለች። » «ጥሩ አሳብ ነው አሁን እንዳልኸው ለሁድ ጭምር ፈቃድ ካገኘችና ካዲስ አበባ ውጭ ለመሄድ እሺ ካለች ወዳንድ የመዝናኛ ቦታ ይዘናት እንሄዳለን ነገር ግን እስከ ቅዳሜና እስከ አሁድ ቀን ቀን እንኩዋ መቸም እስራዋ ትውላለች ማታ ማታ ቤት ዘግታ ልጅዋን እያሰበች ስታለቅስ እንዳትሰነብት ወደ ሲኒማ ቤቶች እዬያዝናት ስንወጣ ብንሰነብት ደህና ይመስለኛል» «እስማማለሁ እንሂድ እንግዲህ የምትመለስበት ጊዜ እንኩዋ ገና ትንሽ ይቀረዋል ግን አስዋና አባባ አዛዥ እስኪመለሱ ከማማ ጌጤ ጋር ስንጫወት እንቆያለን» አለ አዝማሪው ሁለቱ አዛዥና ቤት ሲደርሱ ወይዘሮ ጌጤ አውጭ ተሰጥቶ የዋለ ልብስና አንዳንድ እቃ አሽከራቸው እዬሰበሰበች ስታነሳ እአበረንዳቸው ቆመው ይመሰከቱ ነበር «አባባ አዛዥ ገና አልተመለሱም። » አሉ አዛዥ በሩን ከፍተው ገቡና «እንኩዋን መጣችሁ እስቲ እባካችሁ ይችን ልጅ አበረታቱዋት ሆደ ባሻ ሆና አስቸግራናለች» አሉ ቀጥለው ሰላምታው ከተሰጣጡ በሁዋላ ከዚያ ሁሉንም ወደ እንግዳ ቤት ይዘዋቸው ሄደው ጠጅ ቀርቦ አእዬጠጡ በሻህና አዝማሪው እንደ ልማዳቸው እይስበሳቸውን ነውር እዩተዘካዘኩ ዱላ ቀረሽ የውሸት ጥል ሲጣሉ ሌሎች ደመቀች ጭምር እነሱን እያዩና አእዬለሙ በሳቅ ሲያወኩ አመሹ ልጠከበር በበዩኋበገከር ምእራፍ ሰላሳ አራት እድሜ ላምቦ ጠበል ደመቀችን ወደ ሲኒማ ቤቶችና ወደ ሌሎች የመዝናኛ ቦታዎች ለመውሰድ በተስማሙ ማግስት ካስራ ሁለት ሰአት ቀደም ብለው በሻህና አዝማሪው ውቤ ከባልተቤቱ ጋር አናዛዥ ተካልኝ ቤት ደረሱ አዛዥ ከስራቸው ገና ስላልተመለሱ አቤት ያገኙዋቸው ወይዘሮ ጌጠንና ደመቀችን ብቻ ነበር «የምትጠጡት ምን እናምጣላችሁ። እም አንጓ አለች ለጥያቄዋ ሁሉ መስል ለመስጠት የሚችል በፍቅር የተነካ ሰው ባጠገብዋ ስላልነበረ የደመቀችና የበሻህ ፍቅር በቃል ወይ በግብር ተገላጸውት ባያውቁም ረዥም ጊዜ አብሮዋቸው የኖረ ነው አዝማሪው ውቤ አዛዥ ተካልኝ ቤት የበሻህን የሚወደዱና የሚደነቁ ባህሪዎችም ስራዎምች በተለይ የጀግናነቱን ታሪክ በረጅም ሲተርክ ከሰማችበት ቀን ጀምራ ደመቀች ከሌሎች ወንዶች ስትሸሽ የኖረችውን ያክል አሱን ስትከትል የኖረች ነበረች ነገር ግን በዚያ ረዥም ጊዜ ውስጥ በተገናኙ ቁጥር የሰላምታ አጁን ከመስጠቱና ሁለት ጊዜ ያክል እጅዋን ከመሳሙ በቀር አንደ ያነለት አንገትዋን አቅፎ ወደሱ አስጠግቶ ከገላው ሙቀት ኣካፍሎዋት አያውቅም ስለዚህ ያ ሙቀት በገላዋ ሲሰራጭ እንደ ወባ በሽታ ያንቀጠቀጣት እጁን በንገትዋ ላይ ሲያደርግ አስማት እንዳስነካት ሁሉ የስዋ ፈቃድ ትቶዋት ሸሽቶ እንዲሁ ግብዝንዋን የሱ ፈቃድ ብቻ የምትከትል ያደረጋት ምን እንደሆነ ስም ልታገኝለት ስላልቻለች እም እኔ እንዲያው እንጻ አለች ልጠከበር በበዩኋበገከር ከዚያ ውባዬሁ ባልዋ ሲስማት ትሆነው የነበረው ታሰባት ውባዬው ባልዋ ሲስማት አፍዋን መሳሙ አላጠግበው ብሎት እንዲያውም የተኛ የፍቅር ራብዋን ቀስቅሶባት አስዋን ደመቀችን እንደ ተደገፈች ጉንጮቹን ራሱን ጆሮዎቹን አንገቱን ትከሻዎቹን ወገቡን እንዲያው በቅርቡ ልታገኝ የቻለችውን የሰውነት ክፍሉን ሁሉ በሁለት እጆችዋ ጥ ብቅ እያደረገች እዬያዘች ስትወራጭ አንድ የፍቅር ጠብታ በሰውነቱ ውስጥ እንዳይቀር ሁሉንም አየጨመቀች ለመዋጥ የምትፈልግ ትመስል የነበረው ያ ሁኔትዋ ያንጊዜ እዚያ አፊትዋ እንደ ሆነው ሁሉ አንድ ደስ የሚያሰኝ ሙቀት በሰውነትዋ ውስጥ ስለ ተሰማት «ወዬው ጉ ድ። አለ አይኖቹን እጨለማው ውስጥ አፍጥጦ አልጋው ላይ እንደ ተንጋለለ ደግ ጉዋደኛውን እፊቱ አቁሞ ከቅርታ ፈገግታ ጋር ባይነ ህሊናው እአዬተመሰለከተ በሻህ ከስኒማ እንደ ተመለሰ ዘግይቶ ራቱን ሲበላ ለማግስቱ ባስራ ሁለት ሰአት ዳቦና ሻይ ቁርስ አእንዲያሰናዳለት የሆቴሉን ወጥ ቤት ለምኖት አድሮ ስለ ነበረ ያን ቁርስ አድርጎ በጥዋት ደመቀችን ሊቀሰቅስ ሄፄደ እስዋም አዛዥንና ወይዘሮ ጌጤን ማታውን ተሰናብታቸው ስላደረች ቀደም ብላ ተነስታ እንደ ቤቱ ልማድ እንጀራ ባዋዜና ጥቁር ቡና ቁርስዋን አድርጋ ያንድ ጊዜ መለውወጫ የሚሆን ልብስና የሴት እቃዋን መስትዋት ሚዶና እነሱን የመሳሰሉ በትንሽ ሻንጣ ከትታ ትጠብቀው ነበርና እንደ ደረሰ ወዳዲስ ከተማ ኦቶብስ መቆሚያ ለመሄድ ቸኮሉ እዚያ ሲደርሱ አንድ ሰአት ሆኖ ነበር ስለዚህ ባምቦ አልፎ ወደ ወለጋ የሚሄደውን ኦቶብስ ሰው በሰው ላይ እየተደራረበ ሞልቶ በሩ ተዘግቶ አገኙትሹኹ ነገር ግን መቸም ልጠከበር በበዩኋበገከር በበለኦቶብሶች ዘንድ የተሳፋሪ ገንዘቡ አንጂ ምቾቱም ሆነ ጤንነቱ ከቁጥር ስለማይገቡ በሻህና ደመቀች እንዲያ አስኪጨንቀው በሞላው ኦቶብስ ውስጥ ለመግባት ሲጠይቁ በር ተከፍቶላቸው ገቡ ያንጊዜ ደንበኛ ኦቶብሶች የሚያገልግሉ ባዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ነበር ባዲስ አበባና በጠቅላይ ግዛት ከተሞች መሀከል በኦቱብሱስ ስም አዬተመላለሱ የሚያገለግሉ ሸራ የተከደኑ ካሚዮኖች ነበሩ እኒያ የኦቱቡስ ስም የተሰጣቸው ካሚዮኖች ከሁዋላ እስከ ፊት በቀኝና በግራ ሁለት አግዳሚ መቀመጫዎች ብቻ ነበሩዋቸው አነሱም እንዲያ ሰው ሲበዛ የሚቀመጡባችው ቢኖሩ በጣም ጥቂት ይሆናሉ የቆሙት በዝተው ሲጨናነቁ የተቀመጡትን ስለሚጫኑዋችውና ብዙ ጊዜም ስለሚወድቁባችው የሚበዙት ሰዎች ቆመው መጉዋዙን ይመርጣሉ ስለዚህ መቀመጫዎች ተሳፋሪ በሚበዛበት ጊዜ ቦታ ከማጣበብ በቀር አምብዛም አገልግሎት አልነበራቸውም ደመቀችና በሻህ አዝማሪው ውቤና ምሽቱን አውጭ ሲያጡዋቸው ከኦቶብሱ ውስጥ ቀድመዋችው የገቡ መስሉዋቸው ነአብር ነገር ግን መቸም አዚያ ሰው በሰው ላይ ተደራርቦ በሰፈረበት ሩቅ ማየት አይቻል ገብተው እዳር እንደ ቆሙ ባቅራቢያቸው ተጨናንቆ ከቆመው ተሳፋሪ መሀከል ቢፈልጉ ሊያዩዋቸው አልቻሉም ጭራሹን ኦቶብሱ ውስጥ አለመኖራቸው ያረጋገጡ ካምቦ በፊት ባሉት ከተሞች የሚቀሩት መንገደኞች የሰዉ ብዛት እአዬተቀነሰ በመፄዱ እሁዋላ ከቆሙበት አስከ ፊት ማየት ሲችሉ ብቻ ነበር «ሀ ያ አልቃሻምና ምሽቱ አልመጡም ማለት ነው። » አለ በሻህ አጠረጴዛው ላይ ያስቀመጠውን አምስት ብር አያመለከተ «እግዚአብሄር ይስጥልኝ ግብዣው አዲስ አበባ ለሌላ ጊዜ ይሁንልኝ ለዚህ የሚበቃ ገንዘብ ይፔ ስለ መጣሁ አንተን የሚያሳስብህ ነገር የለም» አለችና ያስራ አምስት ሳንቲም መልስዋንም ሳትጠብቅ ተነስታ ወደ ምኝታ ክፍልዋ ሄደች እሱም ሂሳቡን ከጉርሻ ጋር ላሳላፊው ከሰጠ በሁዋላ ርሱን ደፍቶ በተቀመጠእአብት ከትናንት ማታ ጀምሮ በመሀከላቸው የተፈጠረውን አለመግባባት ሲያሰላስልና ያ አለመግባባት ጭራሹን ወደ መለያየት ሊያደርሳቸው የሚችል ስለ መሰለው ሰግቶ ምን ማድረግ እንደሚሻለው ሲያስብ ቆይቶ በመጨረሻ ተንስቶ ወደ ክፍሉ ሄደ ወደዬክፍላችወ ከገቡ በሁዋላ ሁለቱም እንኩዋንስ አንቅልፍ ያሳብ አረፍት አላገኙም ባልጋቸው ላይ እንደ ሆኑ እስዋ ያ ገደ ቢስ ያምቦ መንገዳቸው ከበሻህ ጋር የሚለያዩበት መሆኑን አረጋግጣ ለጉዋደኛነቱም ከዚያ በላይ በተስፋ ትጠብቀው ለነበረ ደስታም መጨረሻ መሆኑ ቁርጥ አውቃ አንዳንድ ጊዜ ስታለቅስ አንዳንድ ጊዜ አዝማሪው ውቤ ወዳምቦ የመሄድ አሳብ በማምጣቱና አስዋም በመስማማትዋ አሱንም ራስዋንም ስትረግም በሻህ በበኩሉ ጭራሹን ተለያይተው እንዳይቀሩ ቁጣዋን የሚያበርድበት ዘዴ ሲፈልግ ሁለቱም እንኩዋንስ አንቅልፍ ያሳብ ሆነ የልብ እረፍት አላገኙም መጨረሻ ለበሻህ የተሻለ መላ መስሎ የታዬው ያነለት አመሻሽ ላይ ወደ ፍል ውሀው ጠበል አብራው እንድትሄድ ለማድረግ ቢችል እዚያም ሆነ ሲመለሱ ያልተቀዬመ መስሎ ፊቱን ልጠከበር በበዩኋበገከር ሳይከብደው አንደ ድሮው በፈገግታ ሲያነጋግራት ማምሸት ያ ቁጣዋን በረድ አድርጎት ያደረ እንደሆነ በነጋው ወደ መዋኛው ቦታ መውሰድና ከዚያ ቀስ እያለ አባብሎ ወዳዲስ አበባ ለመመለስ ያሰበችውን ማስተው ነው መላውን እንዲያ አድርጎ ከስራ በሁዋላ አስራ አንድ ሰአት እስኪደርስና ወደ ክፍልዋ ሂዶ ፍልውሀ ጠበል ለመጠጣትና ለመጠመቅ አብራው እንድትሄድ አስኪነግራት ቸኩሎ በያጫጭር ጊዜ ሰአቱን እአያዬ ተነስቶ አክፍሉ ውስጥ ይንቆራጠር ጀመር አስራ አንድ ሰአት ግድም ወደ ክፍልዋ ፄዶ መዝጊያዋን ሲመታ «ማነው። በሻህ ተከታዩን ቀን እዚያው ለማሳለፍ ያሳሰበ ምናልባት አዝማሪው ውቤ የመጣ እንደሆነ ለዚያ በመሀከላቸው ለተፈጠረው ችግር በሻህ ራሱ ለፈጠረው ችግር መድሀኒት አእንደሚያገኝለት በማመን ብቻ ነበር አሳላፊው ሂሳባቸውን ይዞ መጥቶ አእጠረጴዛው ላይ ከማስቀመጡ በፊት በሻህ ቶሎ ከጁ ተቀብሎ ተመለከተና የሂሳብ ወረቀት በጁ እንደ ያዘ አስር ብር አውጥቶ ሲሰጠው «አስቲ አባክህ ሂሳቡን አጌም ልየው» አለች ደመቀች ከጠረጴዛው ማዶ በአንጻሩ አንደ ተቀመጠች አጆዋን ዘርግታ «ሂሳብ ለማስወረድ ማስታወቂያ ያስፈልገኛል ጌታዬ» አለ አሳላፊው ከበሻህ ጋር ተመሳጥረው ስለ ነበረ አሱም እጁን ዘርግቶ ልጠከበር በበዩኋበገከር «ያው እንደ ቀኑ ነው» አለና በሻህ የሂሳቡን ማስታወቂያ ለስዋ በመስጠት ፈንታ ላሳላፊው ሰጠው አሳላፊው አስሩን ብርና የሂሳቡን ማስታወቂያ ይዞ መልሱን ሊያመጣ ሲሄድ «ይቅርታሽን በስራቱ ወንድና ሴት አብረው ሆቴል ሲበሉ ወይም ስኒማና ትያትር ሲገቡ ወንዱ ገንዘብ ባይኖረው እንኩዋ ከሴትዋ ተበድሮም ቢሆን መክፈል የሚገባው አሱ ነው ቅድም ስራት ተላልፈሽ ስትከፍይ ዝም ያልሁ ከከፈልሽ በሁዋላ መልሺ ማለቱን ፈርቼ ነው ስለዚህ እባክሽ ገንዘብ ካነሰኝ እንድታበድሪኝ ስለምጠይቅሸ አዚህ ሆቴልም ወደ ጠበል የሄድን እንደሆነም ሰው እንዳይነቅፈን ገንዘብ ልክፈል አትበይ። አትተኛም ብሎ ለጥያቄው መልሱን ራሱ ሰጥቶ ክፍሉን ቆፎ መንገዱን ቀጠለ እስዋም እንዲሁ ገላዋን በንጹህ ውሀ ተለቃልቃ ልብስዋን ለውጣ መከዳዋን ካልጋዋ ራስጌ አስጠግታ እሱን ተደግፋ ያነለት ጥዋት ሁለት ሰአት ባልሞላ አጭር ጊዜ ውስጥ የሆኑትን ብዙ ነገሮች አምጥታ ባይነ ህሊናዋ ፊት በተራ አሰልፋ ስሜትዋ እዬተለዋወጠ እንዲያ ከሚለዋወጠው ስሜትዋ ጋር አንዳንድ ጊዜ ፊትዋን ፈገግ አንዳንድ ጊዜም ፊትዋን ክርር ግንባርዋን ኩስትር እያደረገች ትመለከት ጀመር በሻህ ልብሱን ውልቅልቅ አድርጎ ባጠገብዋ ጥሎ በዋና ልብሱ አፊትዋ ተንጠራርቶ ቆሞ ያካላቱን ቅርጽ ያን አውነተኛ የወንድነት ውበት ሲያሳያት በሻህ ፊቱን ወደስዋ አዙሮ ስገድላት እንደ ተባለ ሁሉ በጁ መሬት እስኪነካ እያጎነበሰና ተመልሶ ወደ ሁዋላው አዬታጠፈ ብዙ ጊዜ በፊትዋ ደፋ ቀና ሲል በሻህ አንደ ኮርማ አንበሳ አዬተጎማለለ ከፊትዋ ወደ መዋኛው ሲሄድ በሻህ ከመዝለያው ሳንቃ ላይ አጆቹን አስቀድሞ እንደ ተወረወረ ጣምራ ጦር ውሀውን ከላይ ቀዶ ገብቶ ከታች ቀድዶ ሲወጣ ባሻህ ያን የሚያባብል ውብ አጅ አጣጣሉን መዋኛውን በሙሉ ርዝመቱ አዬተመላለሰ ሲዋኝ በሻህ ዋና ሊያስተምራት ከንብርት ዋና ከደረትዋ ስር በሁለት እጆቹ እቅፍ ድግፍ አድርጎ እንደ ያዛት አሱ የሚያናገረውን እንዳትሰማ አስዋ የምታደርገውን እንድትረሳ አድርጎ ከተንበለበለችበት ግልብጥ ብላ አንገቱን እቅፍ አድርጋ እንድትስመው የሚገፋፋ ጽኑ አምሮት በውስጥዋ ተቀጣጥሎ ሲያሞቃት ሲያግላት ያ ሁሉ በተራ ታያትና ያ ሁሉ ያን ጊዜ እዚያ አልጋዋ ላይ እንዳለች በትዝታ ሳይሆን በገሀድ አንደሚሆን ሁሉ አንድ ደስ የሚያሰኝ ሙቀት በሰራ አካላትዋ ስለ ተሰራጨ ደስ ብሉዋት መከዳዋን አድነ ተደገፈች አይኖችዋን ለበስ ፊትዋን ፈገግ አድርጋ ዝም ብላ ትንሽ ቆዬች። አዝማሪው ውቤ አንዳንድ ጊዜ ከመሰንቆ ጋር አንዳንድ ጊዜም በቃሉ ብቻ ሲዘፍን ወይም እሱና በሻህ ዱላ ቀረሽ ሲሰዳደቡ ቤቱ የሳቅና የጭዋታ ቤት ሆኖ ስለሚያመሽ የነሱን መምጣት ወይዘሮ ጌጤና ደመቀች አጥብቀው ይናፍቁ ነበር አንድ ማታ አዝማሪው ውቤና በሻህ መጥተው ራት ከተበላ በሁዋላ ጭዋታው ከቀልድና ከተራ ጭዋታ አዝማሪው መሰንቆውን አንስቶ ወደ ዘፈን ተላለፈ መሰንበቻውን አእናዛዥ ቤት ጠላ ብቻ እንጂ ጠጅ አለመኖሩን ተመልክተው አዝማሪው ውቤ አንድ ማንቆርቆሪያ ጠጅ በሻህ አንድ ጠርሙስ ኮኛክ ይዘው መጥተው ነበርል ስለዚህ ራት እስኪበላ ጠላ ሲጠጣ ቆዬና ወንዶች ሁሉም ጠጅ ወይዘሮ ጌጤና ደመቀች ኮኛክ ይዘው ጭዋታቸው አንደ ቀጠለ «አባባ አዛዥና አማማ ጌጤ ሳይቆጡኝ ቃላችሁን ስጡና ምስጢር ላውጣ መቸም አንዳንድ ምስጢር የማይጎዳ ከሆነ አውጭ አይወጣም እንጂ በቤተሰብ ውስጥ እንዲነገር ይፈቀዳል» አለ አዝማሪው ውቤ የመሰንቆ ግርፉን አቁዋርጦ «ምን ምስጢር ነው ገጤንና እኔን አስፈቅደህ የምታወጣው። ልጠከበር በበዩኋበገከር ምእራፍ ሰላሳ ሰባት የደመቀችና የታምራት ተገኘ መፋታት በሻህና ደመቀች አምቦ እንዳሉ ወዳዲስ አበባ ሲመለሱ ጋብቻቸውን ማዘጋጃ ቤት አስመዝግበው ወዲያው ሊጋቡ ተስማምተው ወስነው ነበር ግን መቸም በማህበር ውስጥ የሚኖሩ ሁሉ ለኑሮዋቸው ያቀዱትን ልክ እንዳቀዱት ወደ ፍጻሜ ለማድረስ ሁልጊዜ ስለማይሙዋላላቸው አነሱም ሲመለሱ አዛዥ ተካልኝን ለሞት ያደረሳቸው ችግር ተፈጥሮ የቆያቸው በመሆንና ከዚያም ሞታቸው ስለ ተከተለ የሚጋቡበት ቀን ላንድ አመት እንዲዘገይ ሆነ አዛዥ ከሞቱ በሁዋላ በሻህ አዝማሪው ውቤና ያዛዥ ባልተቤት ወይዘሮ ጌጤ ጭምር ጋብቻቸው አርባቸው አንደ ወጣ ያለዚያም መንፈቃቸው ከወጣ በሁዋላ አንዲሆን ፈልገው ነበር። » «ተሰነባብተን ሲወጡ ይህ ሙታን ሳላስቆርብ አላገባም የምትለው «ምናልባት አኔን ማግባት ስላልፈልገች የምትፈጥረው ምክንያት ልሆን ይችላል ብሎ አዬተበሳጨ ለውቤ ሲነግረው ሰምቸ ነበር» «መጀመሪያ ለምክንያት የፈጠርሁት መስሎት ተቀይሞ ለኔም እንዲያ ብሉኝ ነበር ነገር ግን መሰለው አለመሆኑን ሳስረዳው አመነ» «አኔ እንኩዋ የሚያስፈልግ አልመሰለኝም ነበር ግን ሁለታችሁ ከተስማማችሁ ይሁን» አሉ ወይዘሮ ጌጤ ምንም እንኩዋ ለጋብቻ እንዲጠይቃት ላመታት ደጅ ስትጠናው የኖረች መሆንዋን አምቦ ኑዛዜያቸውን ሲለዋወጡ ብትነግረው ጋብቻቸው ተፈጽሞ እጁ እስኪያደርጋ ድረስ አንዳንድ የምታደርገው ወይም የምትናገረው ነገር ልታገባው በሰጠችው ቃል ተጸጽታ ወደ ሁዋላ ለመመለስ የምታደርገውና የምታናገረው መስሎት እዬጠረጠረ በሻህ ያለወትሮው ጠባዩ ይከፋ ነበር ልጠከበር በበዩኋበገከር መጀመሪያ ቃልውና ለማጠፍ ያሰበች መስሎት በሻህ እንደገና ጥርጣሬ ያደረበት ካምቦ አንደ ተመለሱ የጋብቻ ውላቸውን ማዘጋጃ ቤት ለማስመዝገብ በተቃጠሩበት ቀን አሱ ምስክሮች አንዲሆኑ የተሰማሙባቸውን አቶ ማንደፍሮን አቶ ታችበሌንና አዝማሪው ውቤን ይዞ ሂዶ ሲጠብቃት ሳትገኝ በመቅረትዋ ነበር አንዳጋጣሚ ሻሸመኔ አካባቢ ባንድ ያሜሪካን ሚሲዮን ውስጥ የሚሰራ አስተማሪ ይሁኑ ሰራተኛ አሜሪካዊ በጽኑ ስለታመመ ቶሎ አዲስ አበባ መጥቶ እንዲታከም ተወስኖ የሚያመጣው ሀኪም ሲላክ ደመቀች ረዳቱ ሆና አንድትፄድ ታዘዘች በማግስቱ የጋብቻዋን ውል ማዘጋጃ ቤት ለማስመዝገብ ከጮኛዋ ጋር ቀጠሮ ሌላ በሽተኛው ቶሎ ሀኪም ቤት ደርሶ አርዳታ ከስዋም ቀጠሮ ሌላ በሽተኛው ቶሎ ሀኪም ቤት ደርሶ አርዳታ እንዲያገኝ ሲባል ጭምር አለቱን የሚመለሱ የሚመለሱ እንጂ አዚያው የማያድሩ መሆናቸውን ስላረጋገጠላት ቅር ቢላትም ትእዛዙን ተቀብላ ፄደች ታዲያ «ምናልባት በጊዜ ያልደረስሁ እንደሆነ ብላ ለጥንቃቄ ያክል በትእዛዝ ሻሸመኔ መሄድዋን በዛዥ ተካልኝ ቤት በኩል በሻህ አንዲያውቀው ላንድ ጉዋደኛዋ መልእክት ትታ ፄዳ ነበር ነገር ግን በሻህ ተቀጥቶ በለቱም ሆነ በማግስቱ ወዳዛዥ ቤት ስላፄደ መልእክቱ በለቱም ሆነ በማግስቱ ወዳዛዥ ቤት ስላልፄደ መልእክቱ አልደረሰውም ነበር አውነትም የፈሩት ይደርሳል የጠሉት ይወርሳል። » አለች ካሽሙር ፈገግታ ጋር ላንድ አፍታ ፊቱን ባይኖችዋ ዳሰስ አድርጋው ስትመለስ እሱም «ሳንጋባ እስከ ዛሬ ለመቆዬታችን አላፊው አንተ ነህ ማለትዋ መሆኑ ገባውና ፊቱ በፍረት ቀለም ትንሽ አንደ መቅላት ብሎ አይኖቹን ከስዋ ዘወር አደረገ ከዚያ አንገቱን እንደ ደፋ ዝም ብሎ ቆይቶ «እኔ እንኩዋ ተስማምተን ከወሰን በሁዋላ በተለይ አሁን ሙታመት ለማስቆረብ አንድ አመት እንቆይ ስላልሽ በጣም ረዝሞ ስለ ታዬኝ ምንም ጥቅም ለሌለው ነገር ለምን ያን ያክል ጊዜ እናባክናለን ማለቴ ነበር» ልጠከበር በበዩኋበገከር «አዬህ ጋሼ እፄ ፊት ከደጃች አሰፋ ቤት አሁን ከዚህ ሀኪም ቤት ወጥቼ ከዚህ አገር ሰው ጋር ደህና አድርጌ ስላልተዋወቅሁ ያገሩን ልማድ አላወቀውም እንጂ ተወልጄ ባደግሁትበት አገር በጎጃም እናት አባት ልጅ ወይም ባል የሞተባት ሴት ሙታመት ሳታስቆርብ ክርዋን ካንገትዋ አትፈታም ሙታመት ሳታስቆርብ ክርዋን ፈትታ ማተብ ድሪና መስቀል ወይም ሌላ ጌጥ ባንገትዋ አድርጋ ብትታይ ወይም ባል ብታገባ ከውሾች እንጂ ከሰዎች ተራ አግብቶ የሚቆጥራት የለም ሁሉም ውሻ ውሻ አያለ መድረሻ ነው የሚያሳጣት። የጋብቻውን ቀን በብርቱ ናፍቆት ይጠባበቁ ለነበሩት ለበሻህና ለደመቀች ያዛዥ ተካልኝ ሙታመት አስኪወጣ አንድ አመት ሙሉ መጠበቁ ምንም አንኩዋ ወደው ያደረጉት ቢሆን የምእአይት አመት ያክል ረዝሞ ታይቶዋቸው ነበር ነገር ግን ለጋብቻ ኑሮዋቸው ከሚያስፈልገው መሰናዶ ገና አንዱም ያልተያዘ ስለ ነበረ ባንድ ላይ ተቀምጠ እዬተመካከሩ የሚያስፈልጋቸውን ነገሮች በቅደም ተከተል ጽፈው በሚነጋገሩበት ጊዜ በቅድሚያ ከሚያስፈልጉት አይነተኛ ነገሮች አንዳንዶቹ ባመቱ ውስጥ ተሰናድተው ሊደርሱ የማይችሉ መስሎ ተስማቸውና ያ ረዝሞ ታይቶዋቸው የነበረው አንድ አመት ያጥራቸው ጀመር ከሁሉም አስቀድሞ ተጋብተው የሚሜገቡበት ቤት አልነበራቸውም የኪራይ ቤት በከተማው ስለ ጠፉ አልነበረም አሱም ሞልቶ ነበር ነገር ግን ያዛዥ ተካልኝን ባለተቤት ወይዘሮ ጌጤን ለመርዳትና ለማጽናናት ባጠገባቸው የሚከራይ ቤት አለመኖሩ ስላወቁ እዚያው አዛዥ ግቢ ውስጥ አንድ ቤት ሰርተው አብረዋቸው ከመኖር በቀር ብቸኛነት አንዳይስማማቸው ለማድረግ የሚችሉበት ሌላ መንገድ አልነበራቸውፊ በቤት እቃ በኩልም ችግሩ ከቤቱ ችግር አምብዛ የቀለለ አልነበረ በሻህ በትዳር ላይ በነበረበት ጊዜ ገዝትቶ የነበረውን የቤት እቃ ሁሉ ምሽቱን ፈትቶ አቶ ማንደፍሮ ሆቴል ሲገባ ስለ ሸጠው ገና ሁሉም አንድ ተብሎ የሚገዛ ነበር ስለዚህ ቤት አፋጥነው ለመስራትና ሊቆይ የሚችለው ቆይቶ እቤት ሲገቡ ግድ አስፈላጊ የሚሆነውን የቤት እቃ ለመግዛት ተስማምተው ወሰኑ። » ባል ወገብዋን በሁለት አጆችዋ ይዛ ቆማ አውነት በሚመስል የውሸት መመረርና መጸየፍ የሚያሳይ ፊት የታች ከንፈርዋን ረዘም ቅንድቦችዋን አንዱን ወደ ላይ አንዱን ወደ ታች ጠምም አድርጋ ደመቀችን ዘቅዝቃ ስታይ ቆዬችና አንዲያ ተጨፍግጎ እንዲያ ከፍቶ የነበረ ፊትዋ ከመቅጽበት የስዋ ብቻ በሆነ ለዛ ያስጌጠው ፈገግታ በርቶ አእዬሳቀች ሮጣ በደመቀች አቅፍ ላይ ወድቃ ትስማት ጀመር ያን የውባዬሁን በያጭሩ ጊዜ መለዋወጥና በተለዋወጠች ቁጥር የምታደርገውን እያዩ ሁሉም መቀለጃ የሆነችቱ ደመቀች ሳትቀር ስቀው አልወጣላቸው አለ ያ ከሰርጉ ቀን በፊት አስራ አስምት ቀናት ያክል ማታ ማታ አዝማሪው ውቤና ውባዬሁ ከወይዘሮ ጌጤ ከደመቀችና ከበሻህ ጋር የነደመቀች ቤት መሰናዶ እስኪጠናቀቅ ድረስ አወይዘሮ ጌጤ ቤት መሰናዶው ከተጠናቀቀ በሁዋላ አዚያ ራታቸውን በልተው ሲጫወቱ ሲደሰቱ ሲስቁ ያመሹ የነበሩት ጊዜ ለበሻህና ለደመቀች በዬለቱ ይሰጣቸው ከነበረው ደስታ አልፎ በጋብቻ ህይወታቸው ሁሉ ሊረሱት ያልቻሉ ባነሱት ቁጥር የህይወት ጉዋደኛቸው ሆኖ ሲያስቃቸው ሲያስደስታቸው የኖረ ነበር ውባዬው «አግዜር ሲንቆጠቆትር ሁሉን አሞዋልቶ አይሰጥ» ትል ነበር እናቴ እንዳለችው ፈጣሪ ሁሉን አሞዋልቶ ያደላቸው ቢኖሩ እጅግ ጥቂት ይሆናሉ ደመቀች የወደደችውን አንድትጠላ የጠላችውን አንድትወድ ወይም ያመነችበትን እንድትክድ የካደችው የማትመለስ ደፋር ነበረች ነገር ግን በተወለደችበት ቤተሰብና ባካባቢው ሀጢያተኛ ነው ነውር ነው ሴት ልጅ ይህን ወይም ያን ማድረግ አይገባትም ወዘተ ሲባል እአዬሰማች ተምራ አምናበት ያደገችውን ሁሉ እንኩዋንስ አስዋ ልታደርገው ሌሎች ሲያደርጉት ማየቱ ከተረዳች በሁዋላ ፈሪ ነበረች አምናበት የኖረች ስህተት መሆኑን ከተረዳች በሁዋላ እንኩዋ አስተሳሰብዋንና አሰራርዋን ቶሎ ለውጣ ባካባቢው የሚኖሩትን ለመምሰል ጊዜ የሚወስድባት ዳተኛ ነአብረች በሻህ በበኩሉ የሰው ክብር የማይነካ የራሱን ክብር የማያስነካ ኩሩ ጀግና ደግ ቸር ነበር በኢህ መስመሮች እንኩዋንስ የሚበልጡት የሚያክሉት ብዙ አይኖሩ ይሆናል ነገር ግን ቁች ብለው ተረት አዬተረቱ ቀልድ አዬቀለዱ አዳዲስ ወሬ አዬፈጠሩ ወይም የተፈጠረውን አያሰማመሩ እንዲሁ ወዘበሬታ ወይም አሉባልታ ጭዋታዎች ናቸው ከሚባሉት ሰዎች ጋር የሚቆጠር አልነበረም ሌሎች እንዲያ ያለ ጭዋታ ሲጫወቱ መስማት ወይም መመልከት በጣም ቢወድም አሱ አያውቅበትም ነበር አዝማሪው ውቤ አሱን የሚነካ ቀልድ ያመጣ እንደሆነ በስድብ ነበር አጠፋውን የሚመልስለትኹ ተማርረው አይለያዩም እንጂ በጭዋታ ላይ ዱላ ቀረሽ የሚጣሉ ለዚህ ነበር ልጠከበር በበዩኋበገከር ለዚህም ከሰርጋቸው በፊት አስራምስት ቀናት ያክል ማታ ማታ አዝማሪው ውቤና ምሽቱ ውባዬሁ አብርዋቸው እያመሹ ውባዬሁ በቃልዋም ባንገትዋም እዬዘፈነች ከዚያ ብሶትዋን ለራስዋ እንደታዋይ አሮጊት ጸሎት ከትአዛዝና ከስድብ ጋር እያሰባጠረች አንደምትደግም ግብዝ አመቤት ተቀጥታ ወጥታ ብቻዋን አመቤዋን አንድምትሰድብ አገልጋይ አዬሆነች አዝማሪው ውቤ ከመሰንቆው ጋርም በቃሉም ብቻም እዩዬዘፈነ አንዳንድ ጊዜ እንደ ኮከብ ቆታሪ አንዳንድ ጊዜም እንደ ጠንቁዋይ እአዬሆነ ባልና ምሽቱን ሲያጭውቱዋቸው ያን አይነት ጭዋታ በሻህና ደመቀች ቢወዱትም አነሱ ያልነበራቸው ከፈጣሪ ያልታደሉት ሆነና ለጊዜው ይሰጣቸው ከነበረው ደስታ አልፎ በጋብቻ ህይወታቸው ሁሉ ባነሱት ቁጥር አያጫወተ ሲያስቃቸው ሲያስደስታቸው የድሜ ልክ ጉዋደኛቸው ሆኖ ቀረ ለደመቀችም ለበሻህም ሁለተኛ ጋብቻቸው ስለ ነበረ ለሰርጉ ብዙ ድግስ መደገስም ብዙ ሰው መጥራትና ለመጀመሪያ ጋብቻ የተለመደውን ስነ ስራት ሁሉ ማድረግም እንደሚያስፈልግ ተስማምተው ነበር ወይዘሮ ጌጤ ብቻ ወልጄ ለመዳር ባልታደል በዚች በምወዳት በመንፈስ ቅዱስ ልጄ የናትነት ወግ ይድረሰኝ ብለው ለመጀመሪያ ጋብቻ የሚደረገው ሙሉ ሰርግ እንዲደረግ ወጥረው ይዘው ነበር የደመቀች ምኞት እንደ ወይዘሮ ንጤ ነበር ነገር ግን በሻህ ብቻ ሳይሆን አዝማሪው ውቤ ጭምር እንዲህ ያለ በነሱ ደረጃ ያሉ ተራ ሰዎች አድርገውት የማያውቁ ነገር ማድረግ ከውጪና ከድካሙ በላይ እንደ ቅብጠት ተቆትሮ ላሜተኞችና ላሽሙዋጣጮች የሚያጋልጣቸው ከመሆኑ በቀር ጥቅምም ደስታም የማይሰጥ መሆኑን እዬገለጹ ባንድነት ስለ ተቃወሙዋቸው ወይዘሮ ጌጤ ተሸነፉ ደመቀችም የነሱን ውሳኔ ተቀበለች «እሺ እስቲ ይሁን የኛን አሳብስ አይሆንም አላችሁ ታዲያ የሰርጉ አለት ከቤተ ክርስቲያን ስትመለሱ አብረዋችሁ የሚመጡና አዚህ ምሳ የሚበሉት እንግዶች ስንት እንደሚሆኑ አስባችሁዋል። » አለ አዝማሪው ወይዘሮ ጌጤ ነገሩ እውነት አጥተው የማይመስ ስራ ሆነባቸው የሚናገጉትን አጥተው አንድ ጊዜ አስማሪው ውቤን አንድ ጊዜ በሻህን በመገረም አይን አዩና ልጠከበር በበዩኋበገከር «ታዲያ እንዲህ ያለ ጉድ እንዲህ ያለ አይሰሩት ስራ ስትሰሩ ባይሆን ቀደም አድርጋችሁ አትነግሩንም ኖሮዋል። » አለ በሻህ እንደ መሳቅ ብሎ «ታዲያ ምኑ ነው ትንሽ። ስለዚህ ለሰላሳ ሰው የተሰናዳው ድግስ ለመቶ በቅቶ ለሌላ መቶ እንዲተርፍ ለማድረግ እንደ ልማዱ ታምር እንዲሰራ እንድለምነዋለንና አነሜቴን አታስቸግሩዋቸው» አሉ አቶ ማንደፍሮ በቀልድ መልክ በሻህ አሳባቸው ስለ ገባው ልቡ ተነክቶ ስሜቱ ከፊቱ እንዳይታይበት ቶሉ ዘወር አለ ከዚያ በማግስቱ ስለሚከተሉት ስለ ጋብችው የስነ ስራት ተራ እድንኩዋነኑ ውስጥ ቁጭ ብለው ተነጋግረው ከተሰማው በሁዋላ አቶ ማንደፍሮ ቶሎ ወደ ቤታቸው ፄዱ ያነለት ማታ ራት ቀደም ብሎ በገዜ ተበልቶ በሻህና አዝማሪው ውቤት ወደ ምኝታቸው ሲሄዱ ወይዘሮ ጌጤ ደመቀችና ውባዬሁ ከሌሎች ሴቶች ጋር ወደዬስራቸው ተሰማሩ እራት ላይ ወይዘሮ ጌጤ ከሰርጉ እለት በሁዋላ መሰንበቻውን ለሚመጣ እንግዳ መጋበዣ ይሆናል ብለው በጎን ያስቀመጡት ተጨምሮ የተሰናዳው መሰናዶ ለለቱ የሚበቃ መሆኑን አይተው ስላረጋገጡ በሻህና አዝማሪው ውቤ ለሰላሳ ሰው የሚሰናዳው ድግስ ያቶ ማንደፍሮ ሆቴል አዛዥ ታሪኩ አሻግሬ በታምር ለመቶ ሰው አንዲበቃ የሚያደርገው መሆኑን አቶ ማንደፍሮ በዘይቤ ስለ ነገሩዋቸው ሁለቱም ወገኖች ምክንያቱን አይገላለጹት እንጂ በማግስቱ የሚደርስባቸው መስሉዋቸው የነበረው ውርደት የማይደርስ መሆኑን አውቀው እንደ መሰንበቻው አዬተጨዋወቱ እዬተሳሳቁ በልተው ተነሱ አዝማሪው ውቤና በሻህ አቶ ማንደፍሮ ሸኝጠ እንድኩዋኑ ውስጥ እንደ ተቀመጡ አንድ ልጅ አየሮጠች መጥታ «ለራት ትጠበቃላችሁ ተብላችሁዋል» ብላቸው ስለ ሄደች እነ ወይዘሮ ጌጤ ቀርበው የሚጠብቁዋቸው መስሉዋቸው ተእንስተው እአዬተቻኮሉ ራት ሲበሉ ወደ ሰነበቱበት ወዳዲሱ ቤት ቢፄዱ እንኩዋንስ ራት ሊቀርብ እነወይዘሮ ጌጤም በቦታው አልነበሩ ወይዘሮ ጌጤ ደመቀችና ውባዬውሁ ራቱን ይዘው አነሱ ከገቡ በሁዋላ መጡ ወይዘሮ ጌጤ ፊት ለፊት ውባዬሁና ደመቀች ቀላል ራት ይዘው ተከታትለው ከነሱ በሁዋላ የጣት ውሀ የያዘች ልጅ ተከትላ ሲገቡ አዝማሪው በዘፈን ስለ ተቀበላቸው ዘፈኑ ቀደም ብለው ከነበሩበት ከባድ ቅርታ በቀጥታ ወደ ጭዋታና ወደ ሳቅ ለመተላለፍ በር ከፋች ሆናቸው «አማማ ጌጤነሽ ዝንክትዋ ወይዘር እንኩዋን ደህና መጡ ተጨንቀን ነበረ ቅድም ተቆጥተው ትተውን ሲወጡ ልጠከበር በበዩኋበገከር እሲ እንደ ድሮዎ በደስታ ፍንክንክ ብለው ይቀመቱ ፈገግ ይበሉና ሽሙንሙን እያሉ ጥርስዎን ይግለጡ ይቅርታዎንና ፊትዎ መጥፎ ነው አያምሩም ሲቆጡ» ሲል አዝማሪው እንደ አንዲር በሚዝገመገም ውብ ድምጽ «ውይ። ሙሽሮች ከተቀመጡ በሁዋላ ትናንቱን አዝማሪው ውቤ ከበሻህ ጋር እንደ ተስማሙት የክብር እንግዶችን ከሙሽሮች አቅራቢያ ሌሎችን እንደ አድሚሜያቸውና የፈልጉትን በዬጉዋዳቸው አንደዬዩምርጫቸው አስቀመጠ ነገር ግን ያነለት የመጡት የተጠሩት እንግዶች ብቻ አልነበሩም ለምሳሌ ሙሽሮችን ካቆረቡት አምስት ቀዳስያን ሌላ አስር ካህናት አብረው መጥተው ከተጠሩት ጋር ተዳብለው የመጡት ብዙ ነበሩ ስለዚህ ድንኩዋኑ እስከ ቻለ ድረስ እድንኩዋኑ ውስጥ አሳላፊዎች አእዬረዱት ካቶ ማንደፍርሮ ሆቴል ለመጠባበቂያ የመጡትን ጠረጴዛዎችና ወንበሮች ከድንኩዋኑ ጥግ ለግጥ ሰርተው አዚያ አስቀመጡዋቸው አንግዳው ሁሉ ቦታ ቦታውን ይዞ አንደ ተቀመጠ ያቶ ማንደፍሮ ሆቴል ስልጡን አሳላፊዎች ነጫጭ ሽርጣቸውን ወደ ሁዋላ ሸብ አያደረጉ ከሆቴሉ በገፍ የመጣውን ልዩ ልዩ የፈረንጅና የኢትዮጵያ አረቄ ከምግብ በፊት ማባያ አንዲሆን ተሸክመው ማሳለፍ ጀመሩ ታምር ሰሪው ታሪኩ አሻግሬ ጥር ይዞ ቆሞ አንደ የሙዚቃ መሪ የሚያደርጉትን ባፉ ሳይሆን በጁ እዬነገራቸው ላልደረሳቸው ለማዳረስ መድገም ለሚፈልጉት ለመድገም የጠርሙስና የመለኪያ ኩዋኩዋታ ወይ የቃል ጫጫታ ሳያሰሙ ጸጥ ብለው አዬተዘዋወሩ ሲጋብዙ እንኩዋንስ ተጋባዞችን ተመልካቾችን ደስ ያሰኙ ነበር ከማባያው አንዳንድ የበቃእው ባንዳንድ ቆመው መደጋገም የፈለጉት ደጋግመው ሲያበቁ ሁሉም መብላት የፈለጉ መሆናቸውን አዝማሪው ውቤ ከያይናቸው ገምቶ ወዲያውም የጊዜውን መገባደድ ተመልክቶ ይህን ወደ ሙሽሮቹ ቀረብ ብሎ ስለ ነገራቸው ተነስተው ወደ ልጠከበር በበዩኋበገከር መቃረቢያው ድንኩዋን ሄደው ማእአዱን ባርከው ተመለሱ ከዚያ የክብር እንግዶች አዝማሪው ውቤ አስነሳቸው ከነሱ በሁዋላ ሌሎች አዬተከታተሉ ከዚያ በሁዋላ ሌሉች ባንድነት አዬተግተለተሉ ምግቡ በያይነቱ ወደ ተደረረበት ጠረጴዛ ሄደው መምረጥ የፈለጉት የመረጡትን መጥገብ የፈለጉት የቻሉትን እየያዙ ተመልሰው መብላቱ ተጀመረ ያ ሁሉ ድንኩዋኑን የሞላው ሰው የሚበላውን ይዞ ጠረጴዛው እየከበበ ተቀምጠው መብላት እንደ ጀመረ ጸጥ ከማለቱ የተነሳ ያን ያክል ብዙ ህዝብ ባንድ ላይ ተሰብስቦ እዚያ የተቀመጠ አይመስልም ነበር የዚያ ሁሉ ህዝብ አፍ ከሚናገረው ይልቅ የሚያላምጠው ጎላ ብሎ ለጆሮ ይሰማ ነበር ቀስ እያለ ብቻ ሁሉም የመብል አምሮቱን በመጠኑ ካስታገሰና ወደ መጠጡ ከተመለሰ በሁዋላ በድንኩዋኑ ውስጥ ንግግሩ ጎላ ብሎ ይሰማ ጀመር ከዚያ አሳላፊዎች ምግብ በያይነቱ ይዘው በዬጠረጴዛው አዬዞሩ አዚያው ተቀምጠው መመገብ ለፈለጉት አዚያው አየሰጡ ራሳቸው ከመቃረቢያው አምጥተው መብላት የፈለጉት አያመጡ ሲበሉ ቆይተው ሲበቃቸው ጠላና ጠጅ በገፍ ስለ ነበረ አዬተጠጣ መደሰቱ መዝናናቱ ቀጠለና ሞቅታ ሲመጣ መዝናናቱና መደሰቱ ወደ መሳቁና ወደ መፈንደቁ ከዚያ ወደ ውካታውና ወደ ጫጫታው እየተሸጋገረ ፄዶ ሁሉም ለየራሱ በተናገረው የሚስቅ አንጂ ሌላው የተናገረውን ሰምቶ የሚስቅ ከማይመስልበት ደረጃ ደረሰ ሙሽሮች ያን ሁሉ ጭዋታና ደስታ ያን ሁሉ ውካታ ከከፍታኛ ቦታዎች ዘቅዝቀው አያዩ የዚያ ሁሉ ደስታ ምክንያት እነሱ መሆናቸው ሲታሰባቸው እዚያ እንደ ነበሩት ሁሉ በሳቅና በውካታ ሊገልጹት የሚይችሉ እንዲሁ በዝምታ ለውስጣዊ ልባቸው ሙቀትን ላፋዊ አካላታቸው ውበትን የሚሰጥ ልዩ ደስታ ተሰምቶዋቸው ስለ ነበረ የሁለቱም ፈቶች እንደ በጋ የንጋት ሰማይ ወገግ ብለው ሁለቱም በጣም አምሮባቸው ነበር ከዚያ የደመቀች በደስታ ወገግ ብሎ የነበረ ፊት ትንሽ በትንሽ የቅርታ ጥላ ሲያጠልለው አንደ ሰማያዊ ፈርጦች ይፍለቀለቁ የነበሩ ውብ አይኖችዋን እንባ ሲመላቸው በሻህ አዬና «ምነ ምን ሆንሽ።

  • N.B. This Summary is Very Experimental!! based on the following scripts from:
    • https://github.com/millzon/textSummarizer-am
    • https://github.com/icoxfog417/awesome-text-summarization#motivation
Download Searchable PDF Download PDF

تعليقات:


memezon

خيارات التنزيل | تحويل إلى قوات الدفاع الشعبي | كتاب اليوم

© dirzon | شروط الخدمة | خصوصية | حول | خدمات | اتصال