Detecting...

Please whitelist dirzon to continue.

or subscribe for ad-free contenct.

dirzon
  • تحويل إلى قوات الدفاع الشعبي
  • قائمة القراءة
  • مختصر
  • كتاب مسموع
  • بحث
  • تحميل
  • myzon
  • تسجيل الدخول
  • تسجيل
English  አማርኛ  Français  العربية
كتاب اليوم

አንድ ልጅ ነበረ.pdf


  • word cloud

አንድ ልጅ ነበረ.pdf
  • Extraction Summary

ይመልሳል ስምህን ወረቀቱ ላይ አልፃፍክም። ብሎት ስለነበር የወጣው ስሙን ሊፅፍ ሲል አንድ ጭርር። ከሁለቱ በቀር ሌላ ሰው እንዳልነበረ ለመገንዘብ ጊዜ አልፈጀበትም ያንን ቤት ይበልጥ ፈራው የሰውዬው ብቻውን መነጋገርም የሰይጣን ነገር። ሲቧል የሰማውን አስታወሰውና እናቱን በሆዱ ይጣራ ጀመር ወዲያው ሰውዬው ጥቁሩን ነገር አስቀምጦ ወደ ልጁ አየት አድርጎ ወጣ ልጁም ይህንን ትንግርተኛ ቤት መቃኘቱን ቀጠለ የሚያየው ነገር ሁሉ እንግዳ ነው ስም ሊሰጠው የማይችል የማያውቀው የማይገባው ነገር ይበዛበታል ወደመሬት ሲያይ በቀለም ባሸበረቀውና በለስላሳው ብርድልብስ ይደመማልሱ በልዩ ልዩ ቀለማት ያጌጡ እሠፈራችን ባሉ ጠጅ ቤቶች ውስጥ አይቶ የሚያውቀውን አግዳሚ የሚመስል ነገርም አለ ከብዙ ዓመታት በኋላ ነው የነዚህ ለስላሳ መቀመጫዎች ስም ሶፋ መሆኑን ያወቀው ትናንሽ ክብና አራት ማእዘን ጠረጴዛዎችም በየቦታው አሉ ልጁ መቃኘቱን ቀጥሏል በሩ ድንገት ሲከፈት ባነን እንደማለት ብሎ ወደበሩ ሲመለከት ፈረንጁንና አጎቱን አየ ወዳጠገቡ ቀርበው የፈተናውን ወረቀት ተመልክተው ተያዩ ምንም አልተፃፈበትም ነበር ምነው። እንኳን በምናባችን የምናሰላስላቸው ረቂቅ ሀሳቦችና ስሜቶች በእጅ የሚዳሰሱ በዓይን የሚታዩ በምላስ የሚጣጣሙ ቁሳዊዎች ነገሮች እንኳ ከግለሰብ ግለሰብ በሚለያይ መንገድ ነው ትዝ የሚሉ ስለ ሰዎችና ስለ አካባቢዎች ከብዙ ዘመን በኋላ የሚታሰቡ ነገሮች ያሳቢውን አሻራ እጅግ ግላዊ በሆነ መንገድ ቀርሰው ነው የሚገኙ። ብዙ ተማሪዎች እርሳቸውን ከማማታቸውም በፊት ሆነ ሌላ ጥፋት የመሰላቸውን ነገር ከመፈፀማቸው በፊት ግራና ቀኝ ይቃኙ እንደነበር በትዝታ ያወጋሉ ይሁን እንጂ ከሚያመልጡበት የሚያዙበት ጊዜ እንደሚበልጥም ያምናሉ እኔ በግሌ የነዚህን ሰዎች እጅ የቀመስኩበት ጊዜ ትዝ አይለኝም ብዙ ግርፊያዎች ግን ተመልክቻለሁ እኔም ምናልባት የጋሼ ብሩን እጅ አንዴ ቀምሼ ይሆናል ይህ ማለት ግን የልጅ መልአክ ነበርኩ ማለት አይደለም እንዲያው ነገሩ እዚያ ባይደርስ ይመስለኛል እንጂ ትናንሽ ረብሻስ ያው እንደ ብዙ ልጆች አላጣም ነበር እንደ ኃይሉ ዶሰኛው ወይም እንደ ዋሴ ዓለሙ ግን አልሆንምበፍፁም። ሌላው የሚስተር ጋኞ የቅጣት ዓይነት በትምህርት ቤቱ ዙሪያ ለሜሄደው የግንብ አጥር ግንባታ ድንጋይ ማጓጓዝ እና አንዳንዴ ለግንበኞቹ ድንጋይ የማቀበል ሥራ ነው በጊዜው እነዚህ ድርጊቶች ያበሳጨ ነበር። ምሥጢሩ ይሄ ነበር። ትለዋለች ፊቷ ፍም እየመሰለና እየተመናጩቀች ወደ ላይ መገስገሱን ሊቀጥል ከመቀመጫው ሲነሳ እጂን መንጭቃ አስለቅቃ ወደ ጋኞ ቢሮ በጥድፊያ ርምጃ ትሄዳለች ከዚያማ ኃይሉን አያድርገኝ ነው። መሆን የምችለው እንዴት ነው። በምሳ ሰዓት ሁለተኛ ሜዳ የነበረው የጋለ የእግር ኳስ ጩዋታ በተለይ የጥበበ መንክር ፊንታዎች የተዝናና ጥበባዊ ችሎታ የፋሲል ዳዊት ኳስ ይዞ ሩጫ የእሸቱ በኋላ አንበሳ ቡድን የገባው ተአምራዊ አጩዋወት ዛሬ ወዳጆቼ አዲስ አበባ ስታድዮም እየሄዱ ከሚቃጠሉባቸው ጋር የሚሜነፃፀሩ አይደሉም ለአጭር ጊዜ ትምህርት ቤቱ ውስጥ ኳስ ሲጫወት ያየሁት ሌላው ታዋቂ ተጫዋች ሸዋንግዛው ነበር አንድ ቀን የተማሪዎችና የመምህራን ምርጥ ቡድኖች ይመስሉኛል አንደኛ ሜዳ ይጫወታሉ ተማሪዎቹ የማእዘን ምት ያገኙና ሸዋንግዛው ይመታል ኳሷ በቀጥታ ልትገባ ስትል ተከላካይ ሊያወጣት እየተዘጋጀ ሳለ መምህር በጋሻው ይመስሉኛል የራሳቸው ወገን የሆነውን ተከላካይ እንዳይነካት ይገፉታል ከዚያ ምን እንደሆነ ዛሬ በትክክል ማስታወስ ተሳነኝ በዚህም እልህ ይዞኛልእየተናደድሁም ነው። ሳስበው ግን ነገሩ እውስጤ የተቀረፀው ብትግባ ይሆናል ብዬ እንድመሰክር እየተገፋፋሁ ነው ይህ ደግሞ በቂ ምስክርነት አይሆንም የማይታበለው ሀቅ ግን ድንቅ ምት ቆረጣ መነበሯ ነው የአምኀ አስፋው ኦፔራዊ ድምፅ የስነፅሁፍ የፊዚክስና የማትስ ፍቅሩ እና ውፍረቱ የነጋ ብሩ ጭንቅላት ውስጡም ቅርፁም የጥላሁን ጮሌ ልዩ ዩኒክ ፈገግታ የሙሉሸዋ ሙላትና የመኮንን በላይ የስራ ዲሲፕሊን ትጋትና በዝምታ የሚኪያሄድ የሚመስለኝ ጤናማ የትምህርት ፉክክር የናይነሸ ራቲላልና የኪሾር ቅባት እና የኪሾር አኪያሄድ አነጋገርና ከዓይኑ ውስጥ ብልጭ የምትል የምትመስል ፈገግታ የጌታቸው ድረሴ ቁመት ውፍረት አኪያሄድና ፈገግታ እና የኩርያን ሀሜትዛሬ ብልጭ ያሉብኝ ናቸውቁጭ ብሎ ማሰላሰያ ጊዜ በነበር ስንት ይፃፍ ነበር። እንዲህ ነው በህዝብ አነጋገር በጊዜው የታኅሳስ ግርግር እየተባለ የሚጠራው እንቅስቃሴ የተካሄደው እኔ የአምስተኛ ክፍል ተማሪ ሆፔ ነበር ባልለመድነው የተኩስ ብዛት ሁላችንም ተደናግጠን ነበር ። ሲል እሰማለሁ ለሁለት የተለያዩ ቡድኖች ማጩብጩባቸው ለጊዜው ደነቀኝ እንጂ የሰማኋቸው አረፍተ ነገሮች በደንብ አልገቡኝም ነበር።

  • Cosine Similarity

አንድ ልጅ ነበረ ቤቱ ከራስ ደስታ ሠፈር ዝቅ ብሎ ተሚገኘው ተወይዘሮ አስካለ ጆቴ ቤት አጠገብ ነበር በየቀኑ ከዚያ ተነስቶ ቁስቋም ድረስ እየተመላለሱ መማር ገና በአንድ ተርም ልጁን ይሰለቸዋል ተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት እሚያስተምር አጎቱ አንድ ቀን ወደዚሁ ትምህርት ቤት ይወስደዋል የወሰደው ወደ ትምህርት ቤቱ ለመግባት ላመለከቱ ልጆች በዚያን ዕለት የሚሰጠውን ፈተና እንዲፈተን ነበር የስምንት ዓመቱ ልጅ ግን ገና ወደ ግቢው ሲገባ መደመም ይጀምራል። የግቢው ስፋት የኳስ ሜዳው ብዛት የአትክልቱና የግቢው ፅዳት የቤቶቹ ብዛት የፎቁ ማማርና መርዘም አሌላ ዓለም ውስጥ የገባ ያስመስሉታል ከዚያ በፊት ከቄስ እና ከቁስቋም ትምህርት ቤቶች ሌላ የሚያውቀው ነገር ስላልነበረ ይሆናል እንዲያ መደነቁ ብዙ ሰዎች ከተሰበሰቡበት ሲደርሱ እሱና አጎቱ ይቀላቀላሉ ልጁ ዙሪያውን በአድናቆት መቃኘቱን እንደቀጠለ ስሙ ሲጠራ ይሰማል ስማቸው የተጠራ ሌሎች ልጆች የሚሄዱበትን አቅጣጫ በጭፍኑ ተከትሎ ይሄዳል ለካስ ፎቁ ውስጥ ወዳለው የፈተና አዳራሽ ነበር የሚያመራው ከፊቱ ያሉት ልጆች ከፊታቸው ያለውን አንድ ትልቅ ሰው እየተመለከቱ ካንዱ ደረጃ ወደሌላው ደረጃ ሲራመዱ አሱም እነርሱን ተከትሎ ይራመድ ጀመር በመራመዱ መሄዱን ያውቃል ወዴት እንደሚሄድ ግን በወጉ አያውቅም ነበር ይሄ ራሱ እያስደመመው ነበር ከፊቱ ያሉትን እግሮች እየተመለከተ የእነርሱ እግሮች ሲነሱ በተነሱት እግሮች ላይ ወዲያው የእርሱን አስተካክሎ ያሳርፍ የነበር ቀስበቀስ ግራና ቀኝ ለመቃኘት መድፈር ይጀምራል ወደግራው ሲመለከት እውጭ እሠፈሩት ሰዎች ላይ ዓይኑ ያርፋል ቆም ብሎ ልብ ሲል ወደታች ነው የሚሜያያቸው ለካስ ወደላይ ነበር የሚሄደው ከዚያን ዕለት በፊትየዛን ዕለት ባደረገው ዓይነት እቤት ውስጥ ሽቅብ ሄዶ አያውቅም ነበርና ይህንን መገንዘቡ ብቻ ለብዙ ዓመታት ተመራምሮ ተመራምሮ አንድ የመልካም ውጤት ፍንጭ እንዳየ ምሁር ፈገግ አስደረገው ጉዞውን ቀጠለ ከፊት ከፊቱ የነበሩት ጥለውት ሄደዋል ከኋላው ይከተሉት ከነበሩቱ ጋር ጉዞውን ቀጠለ አሁን ርምጃው ፈጠን ፈጠን ይል ገባ ልበሙሉነት ተሰማው ገና ትምህርት ቤቱ ገብቶ መማር ሳይጀምርም የተማራት ነገር ያለች ይመስለው ጀመር ከአዳራሹ በር ላይ ቁሞ ወደ ውስጥ ሲመለከት ጃንሜዳ በአራት ግድግዳ ታጥሮ እፊቱ የተደቀነ መሰለው ሌላ ጥያቄ ሌላ መደመምአንድ ቤት ይሄንን ያህል ይሰፋል። ብሎት አጎቱ ይወጣል ሲመለስ ልጁ ፈተናውን ሠርቶ ጩርሶ ነበር ወደ ተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት የዛሬ አርባ አንድ ዓመት ገደማ የገባበትን ሁኔታ ስለተፈሪ መኮንን አውርቶ የማይጠግበው ይህ ልጅ እድል ባጋጠመው ቁጥር ይህንንም ገጠመኝ ለወዳጅ ዘመድና ለልጆቹ ባጭሩ ይተርካል እንደዛሬ ቁጭ ብሎ ግን ዘርዘር አድርጎ በፅሁፍ ገልፆት አያውቅም እንኳን ትምህርት ቤቱ ኛውን ዓመት አከበረ የሚለው አንድም ለእርሱ ይህቺን ነገር በሩጫ መጫር ምክንያት ስለሆነው ነው ይህ ልጅ እኔ ነኝ ስሜ ፈቃደ አዘዘ ይባላል ተፈሪ መኮንን ትምህርቴን ጀምሬ ከኛ ክፍል በኋላ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ገብቼ አሁንም እዚያው ግቢ ዛሬ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ይባላል የምገኝ ነገር ነኝ ከዚህ በኋላ ፍቀዱልኝና ከሌሎች ትዝታዎቼ ጥቂቱን ልንገራችሁ ትዝታ መቼም በጣም ግላዊ ጉዳይ ነው በዚህ ሳይ በክንድ ተለክቶ በቁና ተሰፍሮ ልኩ አይታወቅም። ስለዚህም በዚህች ፅሁፍ ውስጥ ስለተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት በዚያ በኩል ስላለፉት ተማሪዎችና መምህራን የሚነገረው ብዙው ነገር ከተናጋሪው የግል አመለካከት የመነጩ ነው እውስጡ የሚጠቀሱት ሃሳቦችና ስሜቶች ትምህርት ቤቱንም ሆነ መምህራኑን በአዎንታዊም ሆነ በአሉታዊ መንገድ እንዳሉ ይቀርፃሉ ማለት አይደለም ያንድን ሰው ግላዊ ስሜትና ሃሳብ አንዴ በልጅ አንዴ በጎረምሳ እና አንዴ ደግሞ በጎልማሳ ዕድሜ ውስጥ እየተመላለሱ በቁርጥራጭ ትዝታዎች ይስላሉ ማለት ግን ይቻላል ትምህርት ቤቱ ከተቋቋመ ጀምሮ በውስጡ እየተማሩም ሆነ እያስተማሩና እየሰሩ ያለፉ ብዙ ሰዎች ትዝታቸውን በዚህ መልክ ቢያቀርቡ ትምህርት ቤቱ በየዘመኑ የነበረውን ገዕታ ለመገመት ይረዳል ተማሪዎች መምህራን ዳይረክተሮችና አስተዳዳሪዎች አትክልተኞች የፅዳት ሠራተኞች ዘበኞች የጤናና የቢሮ ሠራተኞች በየዘመኑ የነበሯቸውን ትዝታዎች መቅረፅ ቢቻል ይህ የትምህርት ቤቱን ታሪክ ሕይወታዊ በሆነ መንገድ እንደ መቅረፅ ይቆጠራል። ይሁን እንጂ አሁንም በዘመኑ በገባቸውና በሚያውቁት መንገድ ተማሪዎችን በዲሲፕሊን ለማነፅ የፈፀሙት እንጂ እኩያዊ መጩፎጩር ስሜታቸውን ሊወጡብን የፈፀሙት ነበር ብዬ ዛሬ አላስብም እንዲያውም ማንኛውንም ስራ አክብሮ የመሥራትን ሃሳብ እውስጣችን ያሰረፁ ይመስለኛል ለባለአለንጋው መምህርና ለአሴ ሳይንቲስቱ ማስመሪያ ግን የሚፍለቀለቅ ትዝታ የለኝም አራተኛ ኢ ክፍል ሆፔ ያስተምሩን ከነበሩ ሰዎች መሀል አንድ ፀጉረ ሉጫ ቀጠንና ረዘም ያለ የቀይ ዳማ ዘናጭ መምህር ነበር ይገርማል ስሙም ሆነ ያስተምር የነበረው ትምህርት ትዝ አይለኝም እስከዛሬ በማላውቀው ምክንያት ጭኔን ሰምበር በሰምበር ያደረገኝን ሳስብ ግን ድርጊቱ የጤና አይመስለኝም አሴ ሳይንቲስቱም ተማሪ እክፍል ውስጥ ሲያወራ የክፍል ስራ ሰርቶ ሲያሳርምና ሲሳሳት ወሬና ስህተቱን የሚቀጡበት መንገድም የጤንነት መስሎ ያኔም ዛሬም አይታየኝም የውስጥ እጁን ጠረጴዛው ላይ እንዲያስቀምጥ ያዛሉ ከዚያ በማስመሪያ በጠፍጣፋው በኩል ሳይሆን በሾለው ማእአዘንማው በኩል አምስቱን ጣቶቹን ርኅራጌ በሌለው አሰነዛዘር ያደቋቸዋል ሊደግሙት ሊደጋግሙትም ይችላሉ በቀልዳቸው በጩዋታቸውና አየር ሞልቼ አህያ ወደ ጩረቃ ላክሁ በሚለው ወጋቸው የሚወደዱትና የሚታወቁት ዝነኛው አቶ አሰፋ ይህንን ዓይነቱን ቅጣት ለምን እንደመረጡ እሰከዛሬ ሙሉ በሙሉ አልገባኝም ዋናዎቹ የተፈሪ መኮንን መራር የሚባሉ ትዝታዎቼ እነዚህ ናቸው ኛው የትምህርት ቤቱ በዓል በሚከበርበት ወቅት ያነሳኋቸውም ለወደፊቱ ትምህርት ቢሰጡ በሚሜል እንጂ እበዓሉ ስሜት ላይ ቀዝቃዛ ውሃ ለመርጩት አይደለም እንግዲህ ሬቷ ይህቺው ናት ለእኔ ሌላ ምን ትዝ ይለኛል እስቲ በአእምሮዬ ብራና ስክሪን ላይ እየተሽቀዳደሙ ተግ ተግ የሚሉትን እንዳመጣጣቸው ልደርድራቸው። የጋኞ ግንብ ሲሰራ በተለያዩ ጊዜያት ያስተዋልኳቸው ነገሮች ትዝ ይሉኛል ሰዎች ተማሪዎችና ለግንቡ ሥራ የተቀጠሩ ሠራተኞች ድንጋይ ተሸክመው ሲሄዱ ድንጋይ ሲፈለጥ ሲከረከም አሸዋ ሲቦካ ያለው እንቅስቃሴና መዋከብ ከሚስተር ጋኞ የጠደፍ ጠደፍ እርምጃና ስራውን በየቦታው እየሄደ የመቆጣጠር ተግባር ጋር ዓይኔ ላይ ዛሬም አሉ የቲቸር ዘለቀ ስላንት ከ የቲቸር ግርማ ፖርች የሚስተር ቱሬን እንቁላል። ይሉት እንደነበርና እጎኑ ያለው የሰልካካው የከተማ ጥርስና ፊትም በመገረም ብልጭ ይሉ እንደነበር ትዝ ይለኛል በኋላ በኋላ በትምህርት ቤቱ እንደታወቁት እንደ ኃይሉ ዶሰኛውና እንደ ዋሴ ዓለሙ ግን አይሆንም ክረ ጩርሶ አይደርስባቸውም አንድ ቀን ሳይገረፉ ለጋኞ ግንብ አንድ ቀን በቅጣት መልክ ድንጋይ ሳያቀብሉ አንድ ቀን ወላጅ አምጡ ሳይባሉ ከትምህርት ቤቱ በጠባይ አንደኛ ሆነው የዘለቁና ሚስተር ጋኞ እሰከዛሬ በስም እያስታወሰ የሚያደንቃቸው ጠባየ መልካም ጠባየ ላ ተማሪዎች ነበሩ አይደል። በተለይ የአፍሪካ ታሪክ ነው ሌላ ትምህርት ቤት የሚማሩ ጓደኞቼ ብዙ ጊዜ ያወሩ የነበረው ስለአውሮፓና አሜሪካ በተለይም ስለሁለቱ ጦርነቶችና መሪዎች ነበር እንጂ ስለራሳቸው አኅጉር አልነበረም መምህር ብርሀኑ ኅሩይ ራሜላስ የተባለውን መፅሀፍ እንደመኪና ሞተር አውርደው ፈታትተው በታትነው ተንትነው ሲገጥሙት እሰከዛሬ ትዝ ይለኛል ከአምሐ አስፋው ጋር ስለነበራቸውም የቃላት ግብግብ አስታውሳለሁ የመፅሀፉ ይዘት በወቅቱ ምን ያህል እንደገባኝ አላውቅም በደስታ በተመስጦ የምከታተለው ትምህርት ግን ነበር ዛሬ ስንት የቋንቋ መምህራን እርሳቸው እንደቀልድ ተዝናንተው ያንዬ እክፍል ያደርጉት የነበረውን ሲያስተምሩ ማድረግ እንደሚችሉ ለመገመትና ለመናገር አልደፍርም ሚስተር ቱሬን የአፍሪካን ጂኦግራፊ እንድንማር ለማድረግ ይጠቀምበት የነበረው ዘዴ በአራዳ ቋንቋ አሪፍ ነበር ትምህርቱን በወቅቱ ብዙም ባልወደውም በተቻለ መጠን እከታተለው ነበር ከፍ ብዬ በጠቀስሁት ምክንያት አፍሪካ በሚል በእንግሊዝኛ በተዘጋጀ መፅሀፍ ነበር የምንማረው የእያንዳንዱ የአፍሪካ ሀገር ካርታ መልክዓምድራዊ ሁኔታ ተራራሸለቆወንዝ የአየር ሁኔታ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ጉዳይ ሁሉ አጠር አጠር ብሎ መፅሀፉ ውስጥ አለ ጠዋት ክፍል ስንገባ ሜስተር ቱሬን ከጉድ ሞርኒንግ። ይህንን ሁሉ የሚያደርገው በቃሉ ነው ሚስተር ቱሬን የማንን ስም እንደሚጠራ ስለማይታወቅ ሁልጊዜ ሁላችንም ተዘጋጅተን መገኘት አለብን አውቆ በተከታታይ አንዳንድ ተማሪዎች ወጥተው እንዲያስተምሩ ስለሚጠይቅ ሁልጊዜ በተጠንቀቅ ላይ ነበርን በጊዜው በዚህ ሁኔታ የተማረርን ጥቁት ነን ብዬ አላስብም እያደር ግን በተለይ ዩኒቨርሲቲ እንደገባን ሁሉን ነገር በራስ ማዘጋጀትና መሥራት የግድ በሆነበት ሁኔታ ውስጥ በተለይ የቱሬን ዘዴና በጥቅሉ ደግሞ የትምህርት ቤቱ የማስተማር ዘዴ በሌክቸር አስተማሪው ብዙውን ነገር እየተናገረ ዋናዋና ነጥቦችን ብቻ ሰሌዳው ላይ የሚፅፍበትን የማስተማር መንገድ ለመጠቆም ነው ላይ ማተኮሩ በጣም ጠቃሚ መሆኑን የተገነዘብን ይመስለኛል አንድ ህንዳዊ መምህር ዘጠነኛ ክፍል ሳለን ሰሌዳው ላይ ከዳር እዳር ፅፎ ያንን መገልበጤ ሁልጊዜ በብስጭትና ምሬት ትዝ ይለኛል ከዚያ በስተቀር ብዙውን ትምህርት የተማርኩት ከፍ ብዬ በጠቀስኩት በሌክቸር መንገድ መሆኑ ነው እሰከዛሬ ትዝ የሚለኝ እንደ አንዳንድ በወቅቱ ዝነኛ እንደነበሩ ትምህርት ቤቶች በአፍ በአፋችን በእንክብካቤ እየጎረስን ሳይሆን ያደግነው በራሳችን ጥረን ግረን ራሳችንን እንድናጎርስ መንገድ እየተመራን ነው ተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት ያደግነው ብዬ አምናለሁ በዚህ ላይ የየዕለቱን ትምህርት በየዕለቱ የማደራጀትና የማከናወንን ባህል የተማርን ይመስለኛል ይህንን ያዳበሩ ሌሎች ተግባራትም ነበሩ። በዚህ ላይ ማተሚያ ቦታ ለዚህም መኖሩ ያጠራጥራል ስለዚህ ተጣድፌ የጀመርኩትን የሚከተሉትን ነጥቦች ጫጭሬ በጥድፊያ ላብቃ ተፈሪ መኮንን በራስ መስራትን ማንበብን ምግባርን እና ዲሲፕሊንን አስተምሮኛል ስለ ሌሎቹ አንዳንድ ነገር ጣል ያደረግሁ ስለሆነ ስለምግባርና ዲሲፕሊን ብቻ ጥቂት ልናገር የየጠዋቱ የባንዲራ ማውጣት የየጠዋቱ ፀሎት የግብረገብ በኋላ ኤቲክስ ተብሎ በእንግሊዝኛ ይሰጥ ነበር ትምህርት መምህር በገባ ቁጥር ከመቀመጫ መነሳት ዩኒፎርም መልበስና ባጅ ማድረግ ባንድ ላይ ሆነው በውስጤ ያሰረፁት አንድ ሥነሥርዓት አለ ለባንዲራ ተሰልፎ ዘምሮ ባንዲራ ከወጣ በኋላ ተሰልፎ በፀጥታና በቅደም ተከተል ያለረብሻ ሁልጊዜ ወደየክፍል መግባት በልማድ በኩል ሥነሥርዓትን ያስተምራልበተጨማሪም ስለሀገር ምንነት ፍቅርና አንድነት የሆነ ሀሳብ ያስጩብጣል አንዳንድ ሰዎች ይህንን የንጉሠ ነገሥቱን ስምና ዝና ከማስፋፋት ጋር ያያይዙትና ሥነሥርዓቱንና መዝሙሩን አሉታዊ በሆነ መንገድ ይተቻሉ በአፍላ ወጣትነቴ ዘመን እኔም ከተቺዎቹ አንዱ ነበርኩ ከአፍሪካና ከዓለም የፖለቲካ አኪያሄድ ጋር የሀገራችንን ሁኔታ ያቅሜን ያህል ማገናዘብ ከጀመርኩበት ጊዜ ጀምሮ ግን የባንዲራውና የመዝሙር ሥርዓቱ በልጅነት እድሜዬ ያስጩበጠኝ ዐቢይ ነጥብ እንደነበር ቀስበቀስ ትንሸ ትንሽ እየገባኝ የሄደ ይመስለኛል ዝርዝሩን በልጅነቴ ባልረዳውም የሀገር ፍቅርንና የአንድነትን ጠቀሜታ በጭፍኑም ቢሆን እውስጤ አስርዖልኛል በዚያ ላይ ተመርኩዢም ዛሬ የኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን የአፍሪካንና የሰውልጆችን አንድነት እምመኝበት ደረጃ ደርሻለሁ ስለዚህ የባንዲራ መስቀልና የመዝሙር ስነስርዓት የታረቀ ዲሲፕሊንና ምግባር ከማስጩበጥ የላቀ አስተዋፅኦ ነበረው ብዬ አምናለሁ በቀጥታ ለፈተና ውጤት ለሜሚጠናው ከተማርኩት ይበልጥ በተዘዋዋሪ የተማርኩት እሰከዛሬ አብሮኝ አለ ለምሳሌ የእርሻና የእንጨት ሥራ ትምህርቶች ከሚያስገኙት ማርክ የላቀው ቁምነገር ማንኛውንም ሥራ የማክበርን ባህል በየውስጣችን ማስረጉ ይመስለኛል ሌላው ዘላቂ ነገር ከትምህርት ቤቱ ቤተመፃህፍት ያገኘሁት ነው በእረፍት ሰዓት ብዙ ጊዜ ቤተመፃህፍት እየሄድኩ ኢንሳይክሎፒድያ አነብ ነበር ይህንን ማድረግ የጀመርሁት ከዘጠነኛ ክፍል ጀምሮ ይመስለኛል የፊደል ተራውን ተከትዬ በተለይ የሰዎችን እና የሀገራትን ታሪክና ሁኔታ ነበር የማነበው አስራ አንደኛ ክፍል ስደርስ ቶማስ ፔይንን አገኛለሁ ለአጭር ጊዜ ዲያቆን ከነበርኩበት ጊዜ ጀምሮ ይጎተጉተኝ ለነበር የሀይማኖት ጉዳይ ፍንጭ ሰጠኝና ሌሎች ፅሁፎቹን እንዳነብ ገፋፋኝ ሀገሬ ዓለም ነው ሀይማኖቴም በጎ መስራት ነው ሰ ርዐሀበከሃ ከ ነዛቪቧ እሃ ከ በ የሚለው አባባሉም ስለ ሀይማኖትና ስለህይወት በጭንቀት የማስበውን አቅጣጫ አስያዘልኝ ከዚያ በኋላም በሌላ ታላቅ ፈላስፋ አስተያየት ከቶማስ ፔይን ያገኘሁትን አበለፀግሁ በዚህም ምክንያት ተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤትን ሳስታውሰው እኖራለሁ ስለመንግስትና ህዝብ ነፍስ ካገባሁ በኋላ ጀምሮ እሰከዛሬ ለማሰሳስላቸው ነገሮች ዋና መነሻ እየሆነ የሚያገለግለኝን ሀሳብ በአስተውሎት የመዘገብሁትም እዚሁ ትምህርት ቤት መሆኑን አስታውሳለሁ።

  • N.B. This Summary is Very Experimental!! based on the following scripts from:
    • https://github.com/millzon/textSummarizer-am
    • https://github.com/icoxfog417/awesome-text-summarization#motivation
Download Searchable PDF Download PDF

تعليقات:


memezon

خيارات التنزيل | تحويل إلى قوات الدفاع الشعبي | كتاب اليوم

© dirzon | شروط الخدمة | خصوصية | حول | خدمات | اتصال