Detecting...
Please whitelist dirzon to continue.
የዚች ተአምራዊ የሆነች ልጅና የአስተማሪዋ የአኔ ሱሊቫን ታሪክ በአለም ዙሪያ አድናቆትን ያተረፈ ታላቅ ገድል ሆነ። ትኩሳቱ በድንገት እንደ ተነሳባት ሁሉ በድንገት ለቀቃት። ይህም ክስተት ቤተሰቦቿንና ሀኪምዋን ትልቅ ሀዘን ላይ ጣላቸው። ሄለን የሚያያት ሰው ሁሉ እንዲያዝንላት በማሰብ ፊቷን አጥቁራ በሚያሳዝን ሁኔታ ሰውን ከመቅረብ ይልቅ እንደዚህ አምራና ሸንቅጣ ራሷንም ከሌሎች አስበልጣ ሰውፊት ለመቅረብ ባደረገችው ጥረት እንግዳው በጣም ተደነቀ። ከዚህም ባሻገር ጠንካራ በሆነ ስራ ወዳድነትዋ ቤታቸውን ቀጥ አድርጋ ይዛለች።በሌላ በኩል ደግሞ የጤንነትዋ ሁኔታ በቀላል ሊታለፍ የሚችል ነገር አልሆነም። ከአንድ ጓደኛዋ በተገኘ ገንዘብ ከተማረችበት የቦስተን ከተማ ትንሽ ወጣ ብሎ ዋረንትሃም በተባለ ቦታ አንድ መጠነኛ የእርሻ ቦታ ያለው የአንድ ገበሬ ቤት ገዛች። ፊዝ የተባለው የሄለን አዲሱ ውሻም እንደ ልቡ ተሯሩጦ ሊጫወት የሚችልበት ከሩብ ጋሻ በላይ የሚሆን የተመቻቸ ቦታ አገኘ። በሁለቱ ክፍሎች መካከል የሚገኘውን ግድግዳ አፍርሰው በማገናኘት አንድ ሰፊ የሆነ የጥናት ክፍል ለመስራት መቻላቸው ነበር ከፍተኛ የሆነ ደስታ ለሄለን የሰጣት። ይህ በር የጥድ ዛፎች ወደሚገኙበት የመናፈሻ ቦታ ያስወጣል። እያደርም በቁንጅናዋ በተመሰከረላት የሄለን አስተማሪና ውድ ጓደኛ በአኔ ሱሊቫን ፍቅር ተነደፈ። የአኔና የጆን ሜክ እንግዳም ደብዳቤውን አንብባ ለሄለን አስረዳቻት። ሄለን ደግሞ ቁርስ የተበላበትን ጠረጴዛ አፅድታ የሚታጠቡትን ሳህኖች አጥባ ቤታቸውን ከአፀዳች በኋላ ከአኔ ጋር ደብዳቤ የመፃፍ ስራቸው ላይ ያተኩራሉ። በጊዜው የነበረው የአሜሪካን መንግስት የዚህን ማህበር አላማ ጠቃሚነትና አስፈላጊነት በመገንዘብ እውቅናና ድጋፍ እንዲሰጠው ማድረግ አስፈላጊ ሆነ። በእጃቸው ያያሉ» የሚል እምነት ነበራት። የእርሷ ምሳሌነትም በጃፓን ለሚገኙ አካል ጉዳተኞች ህያው አብነት እንደሚሆን ሙሉ እምነት አደረባቸው። የማወቅና የመማር ፍላጎቷ ከመጨመሩ የተነሳ የአእምሮዋም የመቀበል ችሎታ የዚያኑ ያህል የዳበረና የቀለጠፈ ሆነ። በ ሄለን በአንድ ረጅም ጉዞ ላይ እንዳለች ከጓደኛዋ ከፖሊ ቶምሰን ጋር በኬኔክቲኬት የገነቡት ቤታቸው በድንገት አመድ ሆኖ ተቃጠለ። አዲሱ ቤቷም በተቃጠለው ቤት ቦታ ላይ ከበፊቱ በበለጠ ሁኔታ ተገነባላት።
ሄለን ኬለር በዚያው አመት በራድፊልድ ኮሌጅ ትከታተለው የነበረውን ትምህርት የመጀመሪያዋ አይነ ስውርና መስማት የተሳናት ምሩቅ በመሆን ለማጠናቀቅ ቻለች። ሄለን በዚህ አይነት መንገድ ፍላጎቷን ለሌሎች ሰዎች ግልፅ የምታደርግበትን የመግባቢያ መንገድ ቀስ በቀስ እያዳበረች መሄድ ቻለች። ሄለን በራሷ የፈጠራ ችሎታ የቀየሰችውን የመግባቢያ ዘዴ ወላጅ እናቷና የወጥ ቤት ሰራተኛቸው ልጅ ማርታ ዋሽንግተን ከሌሎች ሰዎች በፈጠነና በበለጠ ሁኔታ ሊረዱላት ቻሉ። ሄለን ከሌሎች ሰዎች ጋር ሃሳቧንም ሆነ ስሜቷን ልትገልፅ የምትችለው በጣቶቿ አማካይነት ነበር። ሄለን አስተማሪዋ በሰጠቻት አሻንጉሊት ትንሽ ከተጫወተች በኋላ አኔ ሱሊቫን በሄለን መዳፍ ላይ አሻንጉሊት የሚለውን ቃል ፊደላት ተራ በተራ አንድ በአንድ አሻንጉሊት ብላ ፃፈችላት። አንዳንድ ጊዜ ሄለን ለትምህርቱ በጣም ፍላጎት ስታሳይ በሌላ ጊዜ ደግሞ መስማት ማየትና መናገር ባለመቻሏ አስተማሪዋ ልታስረዳት የምትሞክረው ነገር ሊገባት አይችልም። ይህ የሄለን ሁኔታ ማየት መስማትና መናገር ስለ ተሳናት ነው እየተባለ ወላጆቿን ጨምሮ ሌሎች ሰዎች የተቀበሉትን ስሜት አኔ ልትጋራቸው አልቻለችም። ሄለን ማየት መናገርና መስማት ቢሳናትም በሌላ በኩል ደግሞ ጤነኛ አእምሮ ያላት ልጅ ነበረች። ሄለን ከዚህ በፊት ትረዳው ከነበረው ሁኔታ ይበልጥ ማንኛውም ነገር የራሱና የማያሻማ ብቸኛ የሆነ የመጠሪያ ስም እንዳለው መገንዘብ ቻለች። አስተማሪዋ አኔ ሱሊቫን በሚያሰለችና በሚያስቆጣ ሁኔታ ዘወትር ስር ስሯ በመከተል ፊደሎችን አንድ በአንድ በመዘርዘር እጄ መዳፍ ላይ በመፃፍ ቃላትን እንድትለይ የምታደክማት ይህንኑ የመግባቢያ ዘዴ ልታስተምራት መሆኑ ግልፅ ሆነላት። አኔ ሱሊቫን በመጀመሪያ ራሷን ለማስተዋወቅና በራስዋና በሄለን መካከል ግልጽ የሆነ መግባባትን ለመፍጠር በማሰብ አስተማሪ የሚለውን ቃል የሚወክሉትን ፊደላት በሄለን መዳፍ ላይ አንድ በአንድ በመዘርዘር ፃፈች። ከዚህ በኋላ አኔ አስተማሪ እንደ ሆነችና ሄለን ደግሞ ተማሪ እንደ ሆነች አስረዳቻት። አንድ ጠዋት አስተሣሪዋና እናቷ ወይዘሮ ኬለር በአንድ በሆነ ነገር ከልብ ያሳቃቸውን ሁኔታ ሄለን እንድትረዳው በመጓጓት ከነበረችበት ስፍራ እንደ ተቃረበች አኔ በችኮላ የሄለንን እጆች በመያዝ በምትስቅበት ጊዜ ከሳቅዋ የተነሳ የተሸበሸበውን የፊቷን ገፅታ እንድትዳስስ አደረገቻት። ሄለን በሳቅ ምክንያት የተሸበሸበውን የአኔን ገፅታ እንደ ነካች አኔ ሳቅ የሚለውን ቃል የሚወክሉትን ፊደሎች በጣቶቿ በሄለን መዳፍ ላይ ፃፈችላት። ሄለን ማየት እንደሚችሉ ሰዎች በአንድ ጊዜ ብዙ ነገሮችን መለየት አትችልም። ይህም እለት ሄለን አስደናቂ ሆኖ ያገኘችውን ሁኔታ ሳይሳሳትና ሳይዛባ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሌላ ሰው በሚገባ ማስተላለፍ የቻለችበት ቀን ነበር። ወጣቷ ሄለን የተለየ ዝንባሌ እየታየባትና ገፅታዋም በእለቱ የሚሰማትን ደስታና እርካታ የሚያንፀባርቅ ሆነ በማስተማር ችሎታዋ እየተደነቀች በመሄድ ላይ ያለችው አኔ ሱሊቫንም ሄለን ትምህርቱን እንዴት አድርጋ በተሻለ ሁኔታ ልትቀበል እንደምትችል በየእለቱ ታሰላስል ነበር። ሄለን አንድ ቀን አስተማሪዋን አኔን «ፍቅር ምንድነው። ሄለን በዚህ አይነት መንገድ አካል ጉዳተኝነቷን በመታገል ላይ ሳለች አንድ ቀን ጓደኛዋ ጥሩ ዜና ይዛላት መጣች። በአንድ አጋጣሚ አስተማሪዋና ጓደኛዋ የሆነችው አኔ ሱሊቫን «ሄለን ማየት መስማትና መናገር የሚሳናት ብትሆንም በሌላ በኩል ደግሞ የታወረ አይኗ የማይሰማ ጆሮዋና የማይናገር አንደበቷ ተፅእኖ ሊያሳድርባት አልቻለም። ይህ በመሆኑም ሁለቱ አብረው በሚያሳልፉት ጊዜ ሁሉ አስተማሪዋ ሄለንን የምትመለከታት ማየት መናገርና መስማት እንደ ተሳናት አካል ጉዳተኛ አልነበረም። ሄለን የክረምቱ ወራት በገባ ቁጥር ቦስተን ወደሚገኘው የአይነ ስውራን ትምህርት ቤት ትሄድ ነበር። ሄለን በተገኘው ውጤት ከፍተኛ የሆነ ደስታ ተሰማት። አኔ ሄለንን የምትመለከታት ማየት መስማትና መናገር እንደ ተሳናት አካል ጉዳተኛ ሳይሆን እንደ ማንኛውም ጤናማ ሰው ነበር። በዚሁ ምክንያት ሄለን ለመላው የአሜሪካ ግዛት አይነ ስውራን የሚያገለግል አንድ አይነት የሆነ የፅህፈት ስርአት በስራ ላይ እንዲውል ጥረትዋን ቀጠለች። ዛሬ በአሜሪካ አገር የአይነ ስውራን የፅህፈት ስርአት አንድ አይነት መልክ በመያዙ ማንኛውም አይነ ስውር በየትኛውም የአሜሪካ ግዛት ውስጥ የሚታተሙትን የብሬል መፃህፍት ማንበብ ይችላል። ሄለን ለአይነ ስውራን ጥቅም የቆምኩ እስከ ሆንኩ ድረስ የግል ችሎታዬን ማሻሻል አለብኝ ህዝብ ፊት ቆሜ ንግግር በማደርግበት ጊዜ በተሻለ ሁኔታ መናገር መቻል አለብኝ ሰዎች አይነ ስውራንን መርዳት እንደሚያስደስታቸው አውቃለሁ። በዚህ በማይታክት ጥረቷና ትግሏ ምክንያት ሄለን ብዙ መስማት ከማይችሉ ሰዎች በጣም በተሻለ ሁኔታ ትናገር ጀመር። ሄለን ድምፅዋ አንዳንድ ጊዜ ከፍ እያለ ሲሄድ በሌላ ጊዜ ደግሞ በጣም ዝቅተኛ ይሆናል። በአንድ ወቅት ሄለን «አይነ ስውራን እንደ ማንኛውም ሰው ደስተኛ የመሆን መብት አላቸው» በማለት የጀመረችውን ንግግር በመቀጠል «ነገር ግን ይህ ሊሆን የሚችለው እነርሱም እንደ ማንኛውም ሰው በህብረተሰቡ ውስጥ ውጤት ያለው ተግባር መፈፀም ሲችሉ ነው። አንድ ጊዜ ንግግር ለማድረግ ከአኔ ጋር ወደ አንድ ትልቅ ክተማ ሄዱ። ሄለን ኬለርና አስተማሪዋ አኔ ሱሊቫን «በጣት ንግግር» ሐሳብ ሲለዋወጡ። ሄለን በበኩሏ አኔ ምን እንዳለቻት መረዳት ትችላለች። ሄለን እነዚህን የመሳሰሉ ሰዎች ሲያጋጥሟት ተስፋ ከመቁረጥ ይልቅ አይነ ስውራን እንደ ማንኛውም ሰው እኩል እድል ከተሰጣቸው ብዙ ነገሮች ሊሰሩና ውጤታማነትን ሊያስመዘግቡ እንደሚችሉ ለማስረዳት ጥረት ታደርግ ነበር። ሄለን በአንድ መፅሀፍዋ ውስጥ እነዚህን ለመሰሉ ሰዎች «አይነ ስውራን ልክ በጭለማ ውስጥ እንደ ተቀመጡ ጤናማ ሰዎች የሚታዩ ናቸው። አንድ ጊዜ አንድ የአካል ጉዳት የደረሰበት ህፃን ሄለን ከተቀመጠችበት ቦታ ድረስ በመምጣት በርከት ያለ የገንዘብ ስጦታ ከእቅፍ አበባ ጋር አበረከተላት። ለዚህም ዋና ምክንያቱ ሄለን ከአንዱ የአሜሪካ ግዛት ወደ ሌላው በምትጓዝበት ወቅት የሚያጋጥሟት አንዳንድ ሰዎች ስለ አይነ ስውራን ያላቸው ግንዛቤ በጣም ደካማ መሆኑ ነበር። ሄለን እነዚህን በየእለቱ የሚያጋጥሟትን ነገሮች በማስታወሻዋ ላይ አንድ በአንድ ትመዘግባቸው ነበር። ሄለን ኬለር በደረሰችበት ሁሉ ሰዎች በደስታ ተቀበሏት። ሄለን ኬለር በጉዞዎችዋ ከጎበኘቻቸው አይነ ስውራን ተማሪዎች ጋር ከዚህ በኋላ ሄለን ከጓደኛዋ ከፖሊ ቶምሰን ጋር ረጅም ጉዞዎችን ማድረግ ጀመሩ።