Detecting...

Please whitelist dirzon to continue.

or subscribe for ad-free contenct.

dirzon
  • Convert to Pdf
  • Reading List
  • Summary
  • Audiobook
  • Search
  • Upload
  • myzon
  • Log in
  • Register
English  አማርኛ  Français  العربية  Portuguese
Book of the day

ነገረ ቅዱሳን 2(5).pdf


Advertisement
  • word cloud

ነገረ ቅዱሳን 2(5).pdf
  • Extraction Summary

እነርሱም አማላጅ ተማላጅና የሚማለድለት ናቸው ሀ አማላጅ ማማለድ ለፍጡራን ባሕርይ የሚስማማ የትህትና ሥራ ነው በመሆኑም ሁል ጊዜ ስለ ኃጥአን በሚለምኑት ልመና ምሕረትና ይቅርታ የሚያገኙት እያሉ የሚያስተምሩ መናፍቃን ጌታችን የመቶ አለቃው ልጅ የፈወሰው በማን አምነትና ልመና ነው።ጸ ጌታ ሆይ ቡችሎችም እኮ ከጌቶቻቸው ማዕድ የወደቀውን ፍርፋሪ ይበላሉ አለች በዚያን ጊዜ ኢየሱስ መልሶ አንቺ ሴት እምነትሽ ታላቅ ነው እንደወደድሽ ይሁንልሽ አላት ልጅዋም ከዚያች ሰዓት ጀምሮ ዳነች ከነናዊት ሴት ልጂ የዳነችው በማን ልመናና አምነት ነው። እግዚአብሔርም አንኳን ፃዛምሳ ጻድቃን ዐሥር ጻድቃን ቢገኙ ከተማይቱ ስለእነዚህ ዐሥሩ ብሎ እንደማያጠፋት መለሰለት ይህ የእግዚአብሔር የመሓሪነቱና የይቅርታ ብዛት የሚያሳይ ድንቅ ምስክር ነው እንኳን ሕዝቡ ንስሐ ገብቶ ይቅርና ንስሐ ሳይገቡ በመካከላቸው ቅዱሳን የሆኑ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ቢኖሩ ስለ እነዚህ ቅዱሳን ብሎ አግዚአብሔር ምሕረት ያደርጋል ዘፍ የአባታችን የአብረሃምና የንጉሥ የአቤሜሌክ ታሪክ ደግሞ አቤሜሌክ በሠራው ኃጢአት ምክንያት እግዚአብሔር መቅሰፍት ልኮበታል ይህንንም መጽሐፍ ሲገልጸው አግዚአብሔርም ሌሊት በሕልም ወደ አቤሜሌክ መጣ እንዲህም አለው አንሆ አንተ ስለ ወሰድሃት ሴት ምውት ነህ አርሷ ባለ ባል ናትና በዚህም ምክንያት አግዚአብሔር በአቤሜሌክና በቤተሰቦቹ ላይ መቅሰፍትን አመጣ እንዳይወልዱም ማኅፀናችን ሁሉ በፍጹም ዘግቶ ነበርና በመጨረሻም ከመቅሰፍቱ የተፈወሰው በአቤሜሌክ ከኃጢአቱ በመመለሱ ብቻ አይደለም በአብረሃም ጸሎት ጭምር እንጂ ለዚህም ነው መጽሐፍ አብረፃምም ወደ እግዚአብሔር ጸለየ አግዚአብሔርም አቤሜሌክን ሚሜስቱንም ባሪያዎቹንም ፈወሳቸው ያለው ያዕ ኑ ከእናንተ የታመመ ማንም ቢኖር የቤተክርስቲያን ቀሳውስት ወደ እርሱ ይጥራ በጌታም ስም እርሱን ዘይት ቀብተው ይጸልዩለት የአምነትም ጸሎት ድውዩን ያድናል ጌታም ያስነሣዋል ኃጢአትም ሠርቶ እንደሆነ ይሠረይለታል ትፈወሱም ዘንድ አያንዳንዱ ስለ ሌላው ይጸልይ የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች ግልጽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ነው። እያንዳንዱ ክርስቲያን ሌሎች እንዲጸልዩለት መጠየቅ ይልቁንም ቅዱሳንን ጸልዩልን ከፈጣሪ ዘንድ አማልዱን ማለት ትክክለኛ ክርስቲያናዊ ሕይወት ነው። ትኢሳ ከሱራፌልም አንዱ እየበረረ ወደ እፄ መጣ በአእጁም ከመሠዊያው በገሩጠት የወሰደው ፍም ነበረ አፌንም ዳሰሰበትና እነሆ ይህ ከንፈሮችህን ነክቶአል በደልህም ከአንተ ተወገደ ኃጢአትህም ተሰረየልህ አለኝ የአንገት መስቀል ምእመናን በማተባቸው አስረው በአንገታቸው በማድረግ ለጌታችን ያላቸውን ፍቅር የሚገልጡበት ነው አርዌ ብርት መስቀል ሊቃነ ጳጳሳት ሲሾሙ የሚይዙት የበግ ቀንድ የመሰለ ቅርጽ ያለው ቆለፍ ያለ መስቀል ነው ለ ታቦተ ሕግ ጽላት ታቦት ማለት ማደሪያ መሰወሪያ የእግዚአብሔር መገለጫ ማለት ነው። ዘጸ እንዲሁም በከበሮና በዘፈን አመስግኑት በአውታርና በእምቢልታ አመስግኑት መዝ ከበሮ ከከብት ቆዳ ተጠፍሮ ከእንጨት ወይም ከብር የሚሰራ የዜማ መሳሪያ ነው ይህም የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ነው ሽፋኑ ግምጃ ለመዘባበቻ አይሁድ ሸፍነው በጥፊ የመታህ ማን ነው። ሰማያዊ ሰማያዊውን ፃብት ገንዘብ ለማድረግ በፈቃደ ነፍስ ድል ማድረጋቸውን አንድም ትህትናን ያሳያል ቅዱሳን በትሕትና ለመኖራቸው ማሳያ ነው ። ቀይ ሰማዕትነትን ያሳያል ይህም ቅዱሳን ነፍሳቸውን ለመከራና ለሞት አሳልፈው ስለክርስቶስና ስለቤተክርስቲያን ብለው መስጠታቸውን ለማመልከት ይህን ቀለም እንጠቀመዋለን የመስዋዕትነት የነዛ አውጭነት ምልክት ነው። ብሎ ጠየቀው እርሱም አይደለሁም እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ሆሼ አሁን መጥቻለው አለው ኢያሱም ወደ ምድር በግምባሩ ተደፍቶ ሰገደናኑ ጌታዬ ለባሪያው የሚነግረው ምንድር ነው። ኢያ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብርፃሃነ መለኩቱን የገለጠበትንና ከአብ ዘንድ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው የሚል ያ ድምፅ በመጣበት ጊዜ ከእግዚአብሔር አብ ክብርንና ምስጋናን ተቀብሏልና እኛም በቅዱሱ ተራራ ከእርሱ ጋር ሳለን ይህን ድምፅ ከሰማይ ሲወርድ ሰማን ጴጥ ኢየሩሳሌም በተደጋጋሚ ቅድስት ከተማ ገቡና ለብዙዎች ታዩ ይላላ ማቴ በራእየ ዮሐንስ ላይም በመቅደሱም ውጭ ያለው አድሞ ለአሕዛብ ተሰጥቷልና ተወው አትለካውም በእነርሱም አርባ ሁለት ወር የተቀደሰችውን ከተማ ይረግጧታል ይላል ራእ ስለዚህ በመጽሐፍ ቅዱስ የተገለጠ ነው የን።

  • Cosine Similarity

ምዕራፍ አንድ የቅዱሳን አማላጅነት መግቢያ ቅዱስ የሚለው ቃል የተገኘው ቀደሰ ከሚል የግእዝ ግስ ሲሆን ቀደሰ ማለት አመሰገነ ለየ አከበረ ማለት ነው በዚህም ቅዱስ ማለት ክቡር ምስጉን ልዩ ምርጥ ንፁህ ጽሩይ ማለት ነው በተለያዩ ጥንታሚ ቋንቋዎች ቅዱስ የሚለው ቃል በዕብራይስጥ ቅዳሺሲ በሱርስት ቃዲህ በዐረብኛና በግዕዝ ቅዱስ ይባላል ቃሉ በቀዳሚነት የሚያገለግለው ለፈጣሪ ሲሆን ለፍጡራን ማለትም ለመላእክት ለሰው ለቦታ ለዕለታትና ለቤተ ክርስቲያን ንዋያተ ቅድሳት መጠሪያ ሆኖ ያገለግላል ነገር ግን ለፈጣሪ ሲገለጽና ለፍጡራን ሲገለጽ ትልቅ መሠረታዊ ልዩነት አለው ቅድስና ለእግዚአብሔር የባሕሪ ገንዘቡ ነው የእግዚአብሔር ቅድስና ለእግዚአብሔር ቅድስና የባሕርይ ገንዘቡ ነው ሲባል አንደ ቅዱሳን ገድል ትሩፋት በመሥራት ያገኘው ወይም በጊዜ ሂደት የተሰጠው አይደለም አርሱ አግዚአብሔር ሁልጊዜ ቅዱስ ነው በመሆኑም መቸም መች ቅዱስ ነው የሚመስለው የሚተካከለው የለም ስለ እግዚአብሔር የባሕርይ ቅድስና በመጽሐፍ ቅዱስ በተለያየ ቦታ ተጽፎ እናገኛለን ለምሳሌ ሩ አግዚአብሔር ለሙሴ እንዲህ አለው ለእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ እንዲህ ባላቸው አኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ቅዱስ ነኝና እናንተ ቅዱሳን ሁኑ ዘሌ ሩ አንግዲህ እተካከለው ዘንድ በማን መሰላችሁኝ ይላል ቅድሱ በማለት ስለ እግዚአብሔር የባሕርይ ቅድስና ተናግሯል ኢሳ ጉ ሩ ቅዱሱም አምላክ በጽድቅ ተቀድሷል ኢሳ ሩ ለዘለዓለም የሚኖር ስሙም ቅዱስ የሆነ ከፍ ያለው ልዑል ኢሳ ሩ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ኢሳ ሩ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ የነበረውና የሚመጣው ሁሉንም የሚገዛ ጌታ ራእ ሩ ቅዱስና እውነተኛ ጌታ ሆይ ራአ ሩ ስሙም ቅዱስ ነው ሉቃ ሩ በሁሉ ላይ ቅዱስ ስምህን ከፍ ከፍ አድርገፃልና መዝ የቅዱሳን ቅድስና በባሕርዩ ቅዱስ የሆነ እግዚአብሔር በረድኤት ያደረባቸው በጸጋ የተዋሐዳቸው የፃይማኖት ሰዎች እና መላእክት ቅዱሳን ይባላሉ አርሱ ራሱ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ቅዱስ ነኝና እናንተም ቅዱሳን ሁኑ ዘሌ ብሎ እንደተናገረ ቅድስናን ገንዘብ እንድናደርግ አዞናል የክርስትና ዓላማውና ግቡ ሰዎችን ወደ ቅድስና መምራትና ቅዱሳን እንዲሆኑ ማድረግ ነው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው ሆኖ የተገለጠው ለሰዎች ቅድስናን ለመስጠት ነው በወንጌል እንዲህ ተብሎ እንደተጻፈ እነርሱም ደግሞ በእውነት የተቀደሱ እንዲሆኑ እኔ ራሴን ስለ አነርሱ አቀድሳለው ዮሐ ስለዚህ የፍጡራን ቅድስና ምንጩና በጸጋ የሰጣቸው አግዚአብሔር ነው ጸጋ ማለት ቸርነት ምሕረት በጎነት ያለ ብድራትና ያለ ዋጋ የሚደረግ ስጦታ ማለት ነው እግዚአብሔር በቸርነቱ ምሕረቱ በበጎነቱ ያለ ብድራትና ያለ ዋጋ በነጻ ፍጡራን ቅዱሳን አንዲሆኑ በስጦታ ሰጥቷቸዋል በመሆኑም ቅዱሳንን ቅዱስ ስንል ደግሞ ቅድስናቸው የጸጋ መሆኑን ይታወቃል የጸጋ ቅድስና እግዚአብሔር ለፍጥረቱ በነጻ ያለዋጋ የሰጠው ሥጦታ ነው የፍጥረታት ፈጣሪ የሁሉ ነገር አስገዢ የሆነው አግዚአብሔር በሥራ ለመሰሉት ቅዱሳን የሚሰጠው ስለሆነ የጸጋ ቅድስና ተብሏል ለቅዱሳን የጸጋ ቅድስና እግዚአብሔር ራሱ እንደሰጣቸው ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስ በመልእክቱ ዳሩ ግን እኔ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁኑ ተብሎ ስለተጻፈ የጠራችሁ ቅዱስ አእንደሆነ እናንተም ደግሞ በኑሮአችሁ ቅዱሳን ሁኑ በማለት የጸጋ ቅድስና ለቅዱሳን የተሰጠ መሆኑን ያረጋግጥልናል ኛ ጴጥ በተጨማሪም ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ መልእክቱን ጽፎ ለሚልክላቸው ክርስቲያኖች በመልእክታቱ መጀመሪያ ላይ በእግዚአብሔር ለተወደዳችሁና ቅዱሳን ልትሆኑ ለተጠራችሁ በሮሜ ላላችሁ ሁሉ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ስም በየስፍራው ከሚጠሩት ሁሉ ጋር ቅዱሳን ለመሆን ለተጠሩት እያለ ቅዱሳን አንዲሆኑ ያስታውሳቸውና ያሳስባቸው ነበር ስለዚህ እግዚአብሔር የልጁን መልክ እንዲመስሉ ወስኖ የጠራቸው የመረጣቸው ያጸደቃቸውና ያከበራቸው ነቢያት ሐዋርያት ጻድቃንሰማዕታትነገሥታትካህናት አበውአርድእትጳጳሳትሊቃውንትደናግልምአመናን ቅዱሳን ይባላሉ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያናችን ቅዱስ የሚለውን መጠሪያ አምላካቸው እግዚአብሔርን ዘወትር ያለማቋረጥ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እያሉ ለሚያመሰግኑ ቅዱሳት መላእክት በዓላውያን ነገሥታት ፊት አምላካቸው እግዚአብሔርን በመመስከር አንገታቸውን ለስለት ሰውነታቸውን ለእሳት በመስጠት ሥጋን የሚገድሉትን ነፍስን ግን መግደል የማይቻላቸውን አትፍሩ ይልቅስ ነፍስንም ሥጋንም በገፃነም ሊያጠፋ የሜቻለውን ፍሩ በወንጌል የተጻፈውን ቃል በተግባር የፈጸመ ሰማዕታት ይህን ዓለም በመናቅ ዓለሙም ምኞቱም ያልፋሉ ብለው የላመ የጣመ ሳይበሉ ጸብአ አጋንንትን ግርማ ሌሊት ድምፀ አራዊትን ታግሰው በጾምና በጸሎት በመወሰን የጠራቸው አግዚአብሔርን አስከ ሕይወታቸው ፍጻሜ ያገለገሉ ጻድቃን በተለያዩ ዘመናት የኑፋቄ ትምህርታቸውን ወደ ቤተ ክርስቲያንን ለማስገባት የመጡ የውስጥና የውጪ መናፍቃንን ባፍም በመጽሐፍም የረቱ ሊቃውንት አባቶቻችንን ቅዱስ አያለች ትጠራቸዋለች የቅዱሳን አማላጅነት የምልጃ ትርጉም በምልጃ ውስጥ የሚሳተፉ አካላት በአማላጅነት ተግባር ውስጥ ሦስት አካላት አሉ። ይላል እግዚአብሔር ብሎታል የምልጃ አስፈላጊት ምልጃ አንዱ ስለ ሌላው የሚያቀርበው ጸሎት ስለሆነ በክርስትና ሕይወት ውስጥ አስፈላጊና አንዳችን ለሌላችን ያለንን ፍቅር የሚያሳይ በመሆኑ በአግዚአብሔር ዘንድ የተወደደ ነው ሐዋርያው ቅዱስ ያዕቆብ በመልእክቱ የምልጃ አስፈላጊነት በተመለከተ እንዲህ ብሏል ከእናንተ የታመመ ማንም ቢኖር የቤተክርስቲያን ቀሳውስት ወደ አርሱ ይጥራ በጌታም ስም አርሱን ዘይት ቀብተው ይጸልዩለት የእምነትም ጸሎት ድውዩን ያድናል ጌታም ያስነሳዋል ኃጢአትም ሠርቶ እንደሆነ ይሰረይለታል ትፈወሱም ዘንድ እያንዳንዱ ስለ ሌላው ይጸልይ የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች ያዕ ይህ መልእክት ስለ ምልጃ አስፈላጊነት ከያዛቸው መሠረታዊ ትምህርቶች ውስጥ የተወሰኑትን ለማየት ያህል ሀ የእምነትም ጸሎት ድውዩን ያድናል ጌታም ያስነሳዋል በእምነት አንዱ ስለ ሌላው የሚያቀርበው ጸሉሎት ከድውይ ደዌ እንደሚፈውስ ለ ኃጢአትም ሠርቶ እንደሆነ ይሰረይለታል በ ያዕ ውስጥ ከምናገኛቸው መሠረታዊ ትምህርቶች ሌላኛው ኃጢአት የሠራ ሰው ሌላው በሚጸልይለት ጸሎት የኃጢአት ስርየት ይቅርታ ያገኛል ሊቀ ነቢያት ሙሴ ከደብረ ሲና ዐሠርቱ ቃላት የተጻፈበት ጽላት ይዞ ሲመለስ ሕዝበ አስራኤል ጣዖት ማምለክ ስለጀመሩ አግዚአብሔር ተቆጥቶ እንዲ አለ ቁጣዬ እንዲቃጠልባቸው እንዳጠፋቸውም ተወኝ አንተም ለታላቅ ሕዝብ አደርግፃለው ሙሴም በእግዚአብሔር በአምላኩ ፊት ጸለየ አለምከመዓትህ ተመለስ ለሕዝብህም በክፋታቸው ላይ ራራ ብሎ በመጸለዩ አግዚአብሔር የሙሴን ልመና ተቀብሎ አግዚአብሔር በሕዝቡ ላይ ሊያደርግ ስላሰበው ክፋት ራራ ይላል ዘጸ ሐ ትፈወሱም ዘንድ እያንዳንዱ ስለ ሌላው ይጸልይ አንዱ ስለ ሌላው የሚያቀርበው ጸሎት ሐዋርያት በመልእክቶቻቸው ከገለጹዋቸው ተግባራት አንዱ ነው ሐዋርያው ያዕቆብ ትፈወሱም ዘንድ እያንዳንዱ ስለ ሌላው ይጸልይ ያለው ክርስቲያኖች ሊያደርጉዋቸው ከሚገቡ የፍቅር መገለጫዎች ለሌሎች መጸለይ አንዱ ስለሆነ ነው ቅዱስ ጳውሎስ በቀረውስ ወንድሞች ሆይ የጌታ ቃል እንዲሮጥ በአናንተም ዘንድ ደግሞ እንደሚሆን እንዲከበር እምነትም ለሁሉ ስለማይሆን ከዓመፀኞችና ከክፉዎች ሰዎች እንድንድን ስለ እኛ ጸልዩ ያለው ለዚህ ነው ተሰ እንዲሁም በ ሮሜ በአግዚአብሔር ፈቃድ በደስታ ወደ አናንተ መጥቼ ከአናንተ ጋር እንዳርፍ በይሁዳ ካሉት ከማይታዘዙ እድን ዘንድ በኢየሩሳሌምም ያለኝ አገልግሎቴ ቅዱሳንን ደስ የሚያሰኝ ይሆን ዘንድ ጸልዩ ብሉ ቅጳውሎስ በመልእክቱ እየደጋገመ እንዲጸልዩለት አሳስቧቸዋል ዳግመኛም ሐዋርያው ለጢሞቴዎስ በላከለት የመጀመሪያው መልእክቱ ላይ ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት አመክራለው ሰዎች ሁሉ ሊድኑና እውነቱን ወደ ማወቅ ሊደርሱ በሚወድ በእግዚአብሔር በመድኃኒታችን ፊት መልካምና ደስ የሚያሰኝ ይህ ነው እያለ ምልጃ ምን ያህል አስፈላጊና መሠረታዊ የፍቅር መገለጫ እንደሆነ በሚገባ አስተምሯል ጢሞ መ የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች መዝሙረኛው ዳዊት በመዝሙሩ መዝ የእግዚአብሔር ዐይኖች ወደ ጻድቃን ጆሮዎቹም ወደ ጩኸታቸው ናቸው እያለ የዘመረው እግዚአብሔር የጻድቃንን ጸሎት ስለሚሰማና ጸሎታቸውም ኃይል ስላለው ነው አንዱ ክርስቲያን ለሌላው የሚጸልየው ጸሉት ምልጃ ዋጋ ያለው ከሆነ በጸጋ ያደጉ በተጋድሎ የጸኑ ጻድቃን ቅዱሳን የሚያደርጉት ጸሎት ደግሞ የበለጠ ኃይልና ጠቀሜታ አለው ከኃጥአን ይልቅ የጻድቃን ጸሎት ዋጋ እንዳለው ሲያመለክት የኃጥአን መሥዋዕት በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊ ነው የቅኖች ጸሎት ግን በአርሱ ዘንድ የተወደደ ነው ይላል ምሳ የቅዱሳን አማላጅነት በሕይወተ ሥጋ ቅዱሳን በዚህ ዓለም በሕይወት በሚኖሩበት ዘመን የሚያቀርቡትን ምልጃ ጸሎት እግዚአብሔር እንደሚቀበልና ስለ አነርሱም ሲል ምሕረትንና ይቅርታን እንደሚያደርግ በብሉይ ኪዳንና በሐዲስ ኪዳን ከተገለጹ ትምህርቶች ውስጥ ለአብነት የተወሰኑትን ማንሳት ይቻላል ሀ ዘፍ እግዚአብሔር ለአብረሃም ስለ ሰዶምና ገሞራ ጥፋት በነገረው ጊዜ ይምራቸው ዘንድ ደጋግሞ ለመነ ፃምሳ ጻድቃን በከተማይቱ ውስጥ ቢገኙ በውኑ ሁሉን ታጠፋለህን። ብሎ በለመነው ጊዜ እግዚአብሔርም በሰዶም በከተማይቱ ውስጥ ፃምሳ ጻድቃን ባገኝ ስፍራውን ሁሉ ስለ እነርሱ አምራለሁ ብሎታል ነገር ግን በከተማይቱ ሃምሳ ጻድቃን ስላልተገኙ አብረፃም እግዚአብሔርን ዐርባ አምስት ጻድቃን ዐርባ ጻድቃን ሠላሳ ጻድቃን ፃያ ጻድቃን በመጨረሻም ዐሥር ጻድቃን ቢገኙ ከተማይቱንና በውስጧ ያሉት ስለ እነዚህ ጻድቃን ብሎ ይምራቸው እንደሆነ ጠይቆታል ነገር ግን በከተማይቱ ዐሥር ጻድቃን እንኳን ባለመገኘታቸው ሀገሪቱ በእሳት ተቃጥላ ጠፍታለች ከዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የምንማረው በሰዶም ዐሥር ጻድቃን ቢገኙ ኖሮ ከተማይቱ በአሳት ተቃጥላ አትጠፋም ነበር የሰዶም ኃጢአት ምንም እንኳን በእግዚአብሔር ዘንድ አጸያፊ ቢሆን መሐሪው እግዚአብሔር ግን ስለ ዐሥሩ ጻድቃን ስል አላጠፋትም ብሎ ለአብረፃም መልሶለታል ለ ዘፍ አብረሃምና ሚስቱ ሣራ ወደ አቤሜሌክ ንጉሠ ጌራራ በተሰደዱ ጊዜ ሣራ መልከ መልካም ስለነበረች የዚህ ሀገር ሰዎች አንቺን ፈልገው እንዳይገድሉኝ ወንድሜ ነው በይ እኔም አኅቴ ናት አላለው አላት ከዚያ ሲደርሱም እሱም እኅቴ ናት ሲል ሣራም ወንድሜ ነው አለች ከዚያም የጌራራ ንጉሥ አቤሜሌክም ላከና ሣራን ወሰዳት እግዚአብሔርም ሌሊት በሕልም ወደ አቤሜሌክ መጣ እንዲህም አለው እንሆ አንተ ስለ ወሰድዛት ሴት ምውት ነህ አርሷ ባለ ባል ናትና በዚህም ምክንያት አግዚአብሔር በአቤሜሌክና በቤተሰቦቹ ላይ መቅሰፍትን አመጣ እንዳይወልዱም ማኅፀኖችን ሁሉ በፍጹም ዘግቶ ነበርና ከዚህ መቅሰፍት የተፈወሱት በአብረፃም ጸሎት ምልጃ መሆኑን መጽሐፍ ሲናገር የሰውየውን ሚስት መልስ ነቢይ ነውና ስለ አንት ይጸልያል ትድናለህም አለው እግዚአብሔር ለአቤሜሌክ በሕልም የገለጠለት ከመቅሰፈቱ ለመዳን ሣራን መመለስ ብቻ ሳይሆን አብረፃም እንዲጸልይለት ጭምር ነው አቤሜሌክ ከመጣበት መቅሰፍት የዳነበትን ሁኔታ ሲያመለክት አብረፃምም ወደ እግዚአብሔር ጸለየ እግዚአብሔርም አቤሜሌክን ሚስቱንም ባሪያዎቹንም ፈወሳቸው ይላል ምልጃ ይህ በነቢያት በሐዋርያትበጻድቃንና በሰማዕታት ጸሎት እንደ አቤሜሌክ ያሉ ምግባረ ደካሞች ነገር ግን እግዚአብሔር ሲቆጣቸው በኃጢአታቸው ደንግጠው የእግዚአብሔርን ገጸ ምሕረት የሚናፍቁ ሰዎች በቅዱሳን ጸሎት የሚረዱበትና የሚጠቀሙበት ነው ስለዚህ ቅዱሳን በሕይወተ ሥጋ እያሉ እንደሚያማልዱና እግዚአብሔርም ጸሎታቸውን ሰምቶ ለኃጢአተኞች ይቅርታና ድኅነት እንደሚያደርግ በማያሻማ ሁኔታ ግልጽ አድርጎ በመጽሐፍ ቅዱስ ተጠቅሷል ሒ ዘጸ ሙሴ ከደብረ ሲና ዐሠርቱ ቃላት የተጻፉበትን ጽላት ይዞ እስኪመለስ ስለዘገየ ሕዝበ አስራኤል አሮንን ሙሴ ምን እንደሆነ አናውቅምና ተነሥተህ በፊታችን የሚሔዱ አማልክት ሥራልን ብለው ጣዖት አሠርተው በሰገዱ ጊዜ አግዚአብሔር ተቆጥቶ እኔ ይህ ሕዝብ አየሁት እነሆም አንገተ ደንዳና ሕዝብ ነው አሁንም ቁጣዬ እንዲቃጠልባቸው አንዳጠፋቸውም ተወኝ አንተም ለታላቅ ሕዝብ አደርግፃለው አለው ከግብፅ ባርነት በብዙ ተአምራት ከፈርኦን አጅ እንዲሁም የኤርትራን ባሕር ከፍሎ ያሻገራቸው አግዚአብሔርን ትተው ጣዖት ማምለክ በመጀመራቸው ሊያጠፋቸው ተቆጥቶ የነበረው አግዚአብሔር በሙሴ ምልጃ አንዴት እንደዳኑ ሲናገር ሙሴም በአምላኩ በአግዚአብሔር ፊት ጸለየ አለም አቤቱ ቁጣህ በታላቅ ኃይልና በጽኑ አጅ ከግብፅ ምድር ባወጣኸው በሕዝብህ ላይ ስለ ምን ተቃጠለ። ይህ የሆነው እግዚአብሔር የቅዱሳኑን ጸሎት ሰምቶ ምሕረት እንደሚያደርግና አንደሚራራ ሕዝቡ ስለሚያውቁ ነው ብዙ ጊዜ በቅዱሳን አማላጅነት የማያምኑ ሰዎች ከሚናገሩት ውስጥ በቀጥታ ወደ እግዚአብሔር ብቻ መጸለይ በቂ ነው ሌላ አማላጅ አያስፈልገንም ሲሉ ይደመጣሉ እንደዚህ ለሚሉ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ በተደጋጋሚ የኤርምያስንና የሕዝበ እስራኤል ታሪክ በቂ መልስ ነበር ነገር ግን እያነበቡ ስለማያስተውሉና ስለማያምኑ ከአግዚአብሔር ቃል በተቃራኒ ይጓዛሉ እነዚህ ከላይ ለማሳያነት የተጠቀሱት የመጽሐፍ ክፍሎች የሚገኙት በብሉይ ኪዳን ነው በሐዲስ ኪዳን ስለ ምልጃ በብዙ ቦታ ተጽፎ ይገኛል ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ምድር በሥጋ ይመላለስ በነበረበት ጊዜ ብዙ ሰዎች በሌሎች ልመና የተፈወሱና የተጠቀሙ አሉ። አንዳንድ መናፍቃን ደግሞ አንደዚህ ያሉ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ሲመለከቱ የቅዱሳንን ምልጅ መቃወም እንደማያዋጣ ሲገባቸው ሌላ ማምለጫ ቀዳዳ ሲፈልጉ ቅዱሳን በሕይወተ ሥጋ እያሉ ያማልዳሉ ቢባል እንኳን ከሞቱ በኋላ አያማልዱም እያሉ ለመናገር ይጥራሉ ከዚህ በመቀጠል ቅዱሳን ከዚህ ዓለም ከተለዩ ካረፉ በኋላ ስለ አማላጅነታቸው የተነገሩ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችን ቀርበዋል የቅዱሳን ምልጃ በዓጸደ ነፍስ የቅዱሳን አማላጅነት በተመለከተ ቀደም ብሎ የተጠቀሰውን የሚመስል ብዙ ማስረጃዎች ከመጽሐፍ ቅዱስ ሲገኝባቸው አንዳንድ መናፍቃን ክህደታቸው ቀየር አድርገው ቅዱሳን በምድር ላይ በሕይወተ ሥጋ እያሉ ያማልዱ ነበር ከሞቱ በኋላ ግን አያማልዱም ይላሉ ነገር ግን ቅዱሳን ከዚህ ዓለም ወደዛኛው ዓለም ከተሸጋገሩ በኋላ እንደሚያማልዱ በቅዱስ መጽሐፍ የተረጋገጠ ነው የዚህ የስህተት አመለካከት መነሻው ቅዱሳን ካረፉ በላ አንዳች አያውቁም በምድር ስለሚደረገውም አውቀት የላቸውም የሚሉ የሰውን የነፍስ አፈጣጠርና ከዕረፍት በኋላ ስላለው ሁኔታ ካለማወቅ የሚመነጭ ነው ሀ ነገሥት ኤልሳ ከሞተ በኋላ ነፍስ የተለየው አጥንቱ የአንድ የሞተ ሰው ሬሳ እንዳስነሣ በዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ይናገራል ቅዱሳን በዚህ ዓለም በሕይወተ ሥጋ እያሉ ብቻ ሳይሆን ካረፉ በኋላም ተአምራትን ይሠራሉ ሙት ያስነሣሉ ስለዚህ ቅዱሳንን ካረፉ በኋላ ሙት ካስነሠ ስለ እኛ ይጸልያሉ ቢባል ምኑ ይደንቃል ለ ማቴ ኢየሱስም እንዲህ አላቸው አውነት አላችኋለሁ እናንተስ የተከተላችሁኝ በዳግመኛ ልደት የሰው ልጅ በክብሩ ዙፋን በሚቀመጥበት ጊዜ እናንተ ደግሞ በአሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገድ ስትፈርዱ በአሥራ ሁለት ዙፋን ትቀመጣላችሁ ቅዱሳን ካረፉ በኋላ እንኳን ማማለድ የመፍረድ ሥልጣን እንደተሰጣቸው ጌታችን በወንጌል እንዲ ግልጽ በሆነ ሁኔታ ለሐዋርያቱ አስተምራቸዋል ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም በ ኛ ቆሮ ላይ ለቆሮንቶስ ክርስቲያኖች ቅዱሳን በዓለም ላይ እንዲፈርዱ አታውቁምን። ከዚህ በመቀጠል እነዚህ መናፍቃን ተጠራጣሪዎች የቅዱሳንን ምልጃ በተመለከተ የሚያነሷቸው የጥርጥር ጥያቄዎችን ቀርበዋል እግዚአብሔር በቀጥታ ስለሚሰማን አማላጅ አያስፈልገንም የዚህ አስተሳሰብ መሠረታዊ ስህተት ቅዱሳን ያማልዳሉ ሲባል ወደ እግዚአብሔር በቀጥታ መጸለይ አንደማይቻል ወይም አንደማይሰማ አንደ ተባለ አድርጎ የማሰብ ችግር ነው አግዚአብሔር በባሕርዩ መሓሪና ይቅር ባይ ስለሆነ ወደ አርሱ የሚጸለየውን ጸሎት ይሰማል ኃጢአትን እንጂ ኃጢአተኛን አይጠላም በመጽሐፍ ቅዱስ ወደ እግዚአብሔር ጸሎት ጸልየው የተሰማላቸው ሰዎች እንዳሉ ሁሉ በቅዱሳን ጸሎት አማላጅነት ምሕረትና ይቅርታ የተደረገላቸው ሰዎች በዙዎች ናቸው ለምሳሌ ል ው ን ር ነ ር ዘፍ እግዚአብሔር ስለ ሰዶምና ገሞራ ጥፋት ለአብረፃም በተናገረው ጊዜ አብረፃም ያለው እንዲህ ነበር ፃምሳ ጻድቃን በከተማይቱ ውስጥ ቢገኙ በውኑ ሁሉን ታጠፋለህን። እግዚአብሔርም አንኳን ፃዛምሳ ጻድቃን ዐሥር ጻድቃን ቢገኙ ከተማይቱ ስለእነዚህ ዐሥሩ ብሎ እንደማያጠፋት መለሰለት ይህ የእግዚአብሔር የመሓሪነቱና የይቅርታ ብዛት የሚያሳይ ድንቅ ምስክር ነው እንኳን ሕዝቡ ንስሐ ገብቶ ይቅርና ንስሐ ሳይገቡ በመካከላቸው ቅዱሳን የሆኑ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ቢኖሩ ስለ እነዚህ ቅዱሳን ብሎ አግዚአብሔር ምሕረት ያደርጋል ዘፍ የአባታችን የአብረሃምና የንጉሥ የአቤሜሌክ ታሪክ ደግሞ አቤሜሌክ በሠራው ኃጢአት ምክንያት እግዚአብሔር መቅሰፍት ልኮበታል ይህንንም መጽሐፍ ሲገልጸው አግዚአብሔርም ሌሊት በሕልም ወደ አቤሜሌክ መጣ እንዲህም አለው አንሆ አንተ ስለ ወሰድሃት ሴት ምውት ነህ አርሷ ባለ ባል ናትና በዚህም ምክንያት አግዚአብሔር በአቤሜሌክና በቤተሰቦቹ ላይ መቅሰፍትን አመጣ እንዳይወልዱም ማኅፀናችን ሁሉ በፍጹም ዘግቶ ነበርና በመጨረሻም ከመቅሰፍቱ የተፈወሰው በአቤሜሌክ ከኃጢአቱ በመመለሱ ብቻ አይደለም በአብረሃም ጸሎት ጭምር እንጂ ለዚህም ነው መጽሐፍ አብረፃምም ወደ እግዚአብሔር ጸለየ አግዚአብሔርም አቤሜሌክን ሚሜስቱንም ባሪያዎቹንም ፈወሳቸው ያለው ያዕ ኑ ከእናንተ የታመመ ማንም ቢኖር የቤተክርስቲያን ቀሳውስት ወደ እርሱ ይጥራ በጌታም ስም እርሱን ዘይት ቀብተው ይጸልዩለት የአምነትም ጸሎት ድውዩን ያድናል ጌታም ያስነሣዋል ኃጢአትም ሠርቶ እንደሆነ ይሠረይለታል ትፈወሱም ዘንድ አያንዳንዱ ስለ ሌላው ይጸልይ የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች ግልጽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ነው። ቅዱሳት የተባሉትም በባሕርዩ ቅዱስ የሆነ እግዚአብሔር የሚመሰገንበትና የሚቀደስበት ስለሆና አግዚአብሔር በፀጋ ያደረባቸው ቅዱሳን ስማቸው የሚጠራበት ገድላቸው የሚተረክበት ሥራቸውና እምነታቸው የሚነገር ስለሆነ ከቦታዎች ሁሉ ተለይተው ቅዱሳት ይባላሉ አግዚአብሔር አምላካችን በሁሉ ያለ ቦታና ስፍራ የማይወሰንለት ይልቁንም ዓለማትን የፈጠራቸውና የሚወስናቸው አርሱ የሆነ አምላክ ነው እግዚአብሔር ማሉእ በኩለፄ በሁሉም ቦታ ያለ እንደመሆኑ በዚህ ቦታ ይገኛል በዚህ ቦታ አይገኝም አይባልም እግዚአብሔር አርሱ ባወቀ ከቦታዎች ሁሉ ለይቶ ምሥጢር የገለጠባቸውና ተአምራት ያደረገባቸው ቅዱሳት ቦታዎች መካናት አሉ እነዚህ ቦታዎች ቅዱሳት ያሰኛቸው በተፈጥራቸው በባሕርያቸው ከሌላ ቦታ የተለየ ነገር ኖራቸው ሳይሆን እግዚአብሔር እርሱ ባወቀ የተለየ ተአምራቱን ስለገለጠባቸውና ለእርሱው አገልግሎት የተለዩ በመሆናቸው ነው በመሆኑም ቅዱሳት መካናት የቅድስናቸው ምክንያት ራሱ ቅዱስ እግዚአብሔር ነው እርሱ በባሕርዩ ቅዱስ ሲሆን መካናቱ ቦታዎቹ ደግሞ በፀጋ ቅዱሳት ይባላሉ ቅዱሳት መካናት በመጽሐፍ ቅዱስ ለሊቀ ነቢያት ሙሴ የምድያምን ካህን የአማቱን የዮቶርን በጎች በኮሬብ ይጠብቅ በነበረበት ጊዜ ዮጥቋጦው በአሳት ሲነድድ ሆኖም ግን ከአሳቱ የተነሳ ሩጥቋጦው ሳይቃጠል ባየ ጊዜ ልሂድና ዮጐጥቋጦው ስለ ምን አልተቃጠለም። አንዳንዴ አገልግሎቱ በዝቶ ፃያ አራት ሰዓት ላይበቃ ይችላል አጅግ የሚመስጠው ያሬዳዊ ዜማ አየደረሰ ቀን ማታና ሌሊት ሊፈራረቅ ይችላል በዚህም ቅዱሳት መካናት የተቀደሱ የተለዩ ናቸው እነዚህን ቦታዎች መሳለም ስለሚያስገኘው በረከት ደግሞ ቀጥሎ ይቀርባል ቅዱሳን መካናት መሳለም ወደ ቅዱሳት መካናት መፄድና እግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝን ሥራ መሥራት በመጽሐፍ ቅዱስ በተደጋጋሚ የተጻፈ እውነት ነው አምላካችን እግዚአብሔር በብሉይ ኪዳን አባቶቻችንን እነ አብርፃምን ይስሐቅንና ያዕቆብን እንዲሁም ሌሎች አባቶችን ወደ አንዳንድ የተለዩ ቦታዎች እንዲሄዱ ይነግራቸውና ያመለክታቸው ነበር ለምሳሌ ከአብረፃም ጀምሮ የነበሩ አበው ቤቴልን ልዩ ስፍራ ይሰጧትና ድንኳናቸውን ይተክሉባት ነበር ዘፍ ዘፍ ዘፍ እንዲሁም ዘፍ አግዚአብሔር ለሙሴ በሐመልማልና በነበልባል ተዋሕዶ የተገለጠበትን የኮሬብ ተራራ በተመለከተ ሲናገር ወደ እግዚአብሔር ተራራ ወደ ኮሬብ መጣ ይላል። ታም መልአክ ፊልጳስን ተነሥተህ በደቡብ በኩል ከኢየሩሳሌም ወደ ጋዛ ወደሚያወርደው ምድረ በዳ ወደ ሆነ መንገድ ሂድ አለው ተነሥቶም ፄደ እነሆም ህንደኬ የተባለች የኢትዮጵያ ንግሥት አዛዥና ጃንደረባ የነበረ በገንዘብዋም ሁሉ የሠለጠነ አንድ የኢትዮጵያ ሰው ሊሰግድ ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ ነበር ሲመለስም በሰረገላ ተቀምጦ የነቢዩን የኢሳይያስን መጽሐፍ ያነብ ነበር ይላል የሐዋ የዚህ ጃንደረባ ጉዞ የተቀደሰና በአግዚአብሔር የተወደደ መሆኑ የምንረዳው በሐዋርያው በፊሊጾስ አጅ ሥርዓተ ጥምቀት ተፈጽሞለት ክርስቲያን በመሆኑ ነው የዚህ ጃንደረባ ኢየሩሳሌምን ለመሳለም መሄዱ ያገኘው በረከት እንዲሁ ቀላል ሳይሆን የእግዚአብሔር ልጅነትን ነው ወደ ቅዱሳት መካናት መሄድ ጉብኝት አይደለም መንፈሳዊ ዓላማ ያለው መንፈሳዊ ሥራ ነው እንጂ የምናገኘው በረከትም እጅግ ትልቅ ነው ታላቁ ሐዋርያ ቅዱስ ጳውሎስ የኤፌሶን ክርስቲያኖችን ሲሰናበታቸው የሚመጣውን በዓል በኢየሩሳሌም አደርግ ዘንድ ይገባኛል ያላቸው መንፈሳዊ በዓላትን እንደ ኢየሩሳሌም ባሉ ቅዱሳት መካናት አግዚአብሔር ሥራውን በሠራባቸው የተቀደሱ ቦታዎች ማሳለፍ ተገቢ ስለሆነ ነው የሐ እንዲሁም ጳውሉስ ቢቻለውም በዓለ ኀምሳን በኢየሩሳሌም ይውል ዘንድ ይቸኩል ነበርና በማለት መንፈሳዊ በዓላትን በተቀደሱ ቦታዎች መዋልና ማሳለፍ ሐዋርያዊና መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሆኑን ቅዱስ መጽሐፍ ይነግረናል የሐዋ ቅዱሳን መካናት መሳለም ጥቅም ቅዱሳት መካናትን መሳለም ብዙ ጥቅም አለው ቦታው እግዚአብሔር ድንቅ ሥራውን የገለጠበት ከሆነ ከዚያ ቦታ በአካል ስንገኝ ለኅሊናችን የእግዚአብሔርን ሥራ በሚገባ ያስታውሰናል በዓይነ አንደ ማየት በእጅ እንደ መዳሰስ ያህል ድርጊቱ ቀርቦና ጎልቶ ይታየናልያ የእግዚአብሔር ሥራ ሲፈጸም በጊዜው የነበርን ያህል ሆኖ ይሰማናል ራሳችንን ወደ ኋላ መልሰን የተደረገውን ድርጊትና ድርጊቱ ሲፈጸም የነበረውን ነገር እንድናዘክር ያደርገናል ኅሊናችን ይመሰጣል ቅዱሳን ጻድቃንና ሰማዕታት የኖሩባቸውን የተጋደሉባቸውን ፈጣሪያቸውን ያገለገሉባቸውንና ትሩፋታቸውን የፈጸሙባቸውን ቦታዎች ስናይ የዘመን ርቀት ሳይገድበን በኅሊና መነጽር የራቀውን አቅርበን ሥራቸውንና ሕይወታቸውን ሁሉ በፊታችን እንድናይ ቦታው ያነሳሣናል ያ ቦታ ቅዱሳኑ በኪደተ አግራቸው የባረኩት የትሩፋት ወዛቸው የነጠበበት ብዙ ሥራ የሠሩበት በጸሎታቸውና በጾማቸው የቀደሱት በኋላም ዐፅማቸው ያረፈበት ቦታ ነውና ከዚህም በላይ አግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አገልጋዮቹን ለማጽናትና ለማጽናናት የሚገኝበት ክርስቶስ ከትንሣኤ በኋላ ለሐዋርያት እንደ ተገለጠ እንዲሁ የሚገለጥበት ቅዱሳን መላእክት ለአዕርጎተ ጸሎት ለጥበቃና ለተራድኦ የሚወጡበትና የሚወርዱበት ነውሱ እንዲሁም እግዚአብሔር በዚህ ዓለም የሕይወት ውጣ ውረድና ፈተና ድል ለሚያደርጉት ኋላ ለሚያገኙት የክብር አክሊል ዐረቦን የሆነውን ጸጋውንና ክብሩን የሚያድልበት ስለሆነ አንዲህ ያለው ቦታ እግዚአብሔር ሥራውን የሚሠራበትና በጸጋ የማይለየው ቦታ ነው ይህ ሁሉ የሆነበትን ቦታ መሳለም በረከት ነውር ቅዱሳኑ በኖሩበት ቦታ መቀመጥና ማደር አነርሱ በእጃቸው የሠሩትን ቤተ መቅደስ መንካትና መዳሰስ በአግራቸው በተመላለሱበት ቦታ መራመድ ለአንድ ክርስቲያን ታላቅ መታደል ነው በአካል ባያገኛቸውም በእምነት በመንፈስ ያገኛቸዋልና እንዲሁም በዚህ ቦታ አሁንም በሕይወተ ሥጋ ከሚገኙ በዓይን ከሚታዩትና ከተሰወሩትም ቅዱሳን በረከት ያስገኛል በአጠቃላይ ዘርዝሮና ቆጥሮ ማተትና መግለጽ ከሚቻለው በላይ በረከትንና መጽናናትን እንዲሁም መንፈሳዊ ብርታትንና መነሳትን ያስገኛል የራስን ማንነት እንዲመረምሩና እንዲጠይቁ ያደርጋል ከዚያም ወደ ንስሐ ይመራል።

  • N.B. This Summary is Very Experimental!! based on the following scripts from:
    • https://github.com/millzon/textSummarizer-am
    • https://github.com/icoxfog417/awesome-text-summarization#motivation
Download Searchable PDF Download PDF

Advertisement
Bottom banner

Download options | Convert to Pdf | Advertise on dirzon

© dirzon | Terms of Service | Privacy | About | Services | Contact