Detecting...
Please whitelist dirzon to continue.
መላእክት ከእግዚአብሔር እየተላኩ ሰውን ይራዱ ነበር ከዚህም ውጪ አንገታቸውን ለሰይፍ ጀርባቸውን ለጅራፍ ሰጥተው ሰማዕት ሆነዋል ከአቤል ጀምሮ እስከ በራክዩ ልጅ እስከ ዘካርያስ ድረስ የነቢያት ደም እንደ ጎርፍ ፈሷል ሆኖም ግን ነቢያትም ቢሆኑ የአዳምን አዳ ለመክፈል አልቻሉም ነበር ዝዛላገሆፀርኪ በአዳም የፈረደበት እግዚአብሔር ነው ከዚህም ውጪ አዳም የነበረበትን እዳ የመክፈል አቅም ሥልጣን ያለው ብቸኛ አካል እግዚአብሔር ብቻ ነው። ሥጋ ነው። እንዳንል መለኮት ይበላና ይጠጣ ዘንድ በሰርግ ቤት አይገኝም በግዝፈት ይገለጥ ዘንድ ባህርይው አይደለምና ነገር ግን ይህንን ድንቅ ምሥጠ ር ሊገልፅ የሚችል ፍፁም ምሳሌ የለም ኛው የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ቄርሎስ የተዋሕዶን ምስጢር በብረትና በእሳት መስሉታል ብረት እሣት ውስጥ ከገባ በኋላ ግን ይለዝባል የጋለ ብረትን በመዶሻ ዝዛላገሆፀርኪ ብንመታው የመታነው ማንን ነው።
እኔ ዛሬ ወለድሁህ» ብሎአል መዝ ቅዱስ ጳዉሎስም ስለ ደኅራዊ ልደቱ ሲናገር «የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግ በታች የተወለደውን ልጁን ላከ» ገላ ብሎአል ይህንንም መሠረት በማድረግ ቤተክርስተያን ጌታችን ሁለት ልደታት እንዳሉት ትመሰክራለች ቅዱስ ሳዊሮስም ቀዳማዊ ልደቱ በድኃራዊ ልደቱ እንደታወቀ በሃማኖት አበው አስተምሯል ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በኋላኛው ዘመን ሥጋን ተዋሕዶ ሰው ቢሆንም ከአምላክነቱ ክብር አልጎደለበትምነጹ ይህም ማለት ጌታችን ሰው ሲሆን አምሳላክ አምላክ ሲሆን ደግሞ ሰው ነው ሐዋርያው ቅዱስ ጳዉሎስም ይህን ሲገልጽ «እርሱ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር አልቆጠረውም» ብሏል ፊሊ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም በቅዳሴው «ከአንድነቱ ሳይለይ መጣ ከሦስትነቱ ሳይለይ ወረደ ከሙላቱ ሳይጐል በማሕጸን ተወሰነ» በማለት የጌታችንን አምላክ ሲሆን ሰው መሆን አስተምሯል ወንጌልም ጌታ በምድር ሲመላለስ ከአባቱ እንዳልተለየ ትገልጻለች «በአባቱ አቅፍ ያለ አንድ ልጁ እርሱ ተረከው» ዮሐ ቤተክርስቲያናችን ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ በቂሣርያ የመሰከረውን ሐዋርያት የሰበኩትንና ሊቃውንቶቿ ያስተማሩትን መሠረት በማድረግ ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ፈጣሪሃ እግዚአብሔር መድኃኒት ወዘተ አንደሆነ ታምናለች ታስተምርማለች ቤተክርስቲያናችን ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ማንነት አምልታና አስፍታ የምታስተምር ሲሆን እኛ ግን በጥቂቱ እንደሚከተለው እንመለከታለን ሀ ጌታችን ኢየሱስ ክርሰቶስ መድኃኒት አዳኝ ነው ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያናችን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የአዳምን ልጆች ሁሉ ከኃጢአያት ደዌ ያዳናቸው መድኃኒት እንደሆነ ታስተምራለች ለዮሴፍ በህልሙ ዝዛላገሆፀርኪ የታየው የእግዚአብሔር መልአክ «ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ኢየሱስ ትለዋለህ» ሲል ተናግሯልፎ ማቴ ሶርያዊው ቅዱስ ኤፍሬምም ይህን ቃል በመያዝ « ዘያድህኖሙ ለሕዝቡ እምኃጢአቶሙ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው የሚያድናቸው ነው» በማለት ተናግሯል ውዳሴ ማርያም ዘሐሙስ ለኖሎት ለእረኞች የጌታችንን መወለድ ያበሰራቸው መልአክ «ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋል» በማለት የክርስቶስን መድኃኒትነት ነግሯቸዋል ሉቃ ሐዋርያትም የጌታቸውን መድኃኒትነት ሲመሰክሩ «መዳን በሌላ በማንም የለም እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና» በማለት የክርስቶስን ብቸኛ መድኃኒትነት ይገልጻሉ ሐዋ ሳምራዊቷ ሴት ስለ ክርስቶስ የነገረቻቸው የሰፈሯ ሰዎች «እርሱ በእውነት ክርስቶስ የዓለም መድኃኒት እንደሆነ እናውቃለን» ብለዋል ዮሐ ከዚህም በተጨማሪ የሚከተሉትን ጥቅሶችም ይህንኑ ያስረዳሉ ሐዋ ሐዋ ሮሜ ፊሊ ጴጥ ለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ነው ስለ ኢየሱስ ክርሰቶስ አምላክነት ነቢያት ሐዋርያትና ጌታችን ራሱም በስፋት የመሰከሩ ሲሆን ለአብነት ያህል የሚከተሉትን እንመልከት ኢሳ «ሕፃን ተወልዶልናልና ስሙም ድንቅ መካር ኃያል አምላክ የዘላለም አባት የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል» ዮሐ «እኔና አብ አንድ ነን» ሮሜ «ክርስቶስ በሥጋ መጣ እርሱም ከሁሉ በላይ ሆኖ ለዘላለም የተባረከ አምላክ ነው አሜን» ቲቶ እርሱም የታላቁ አምላካችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ እየጠበቅን» ጴጥ «በአምላካችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ» ዮሐ «እርሱም ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው» ሪዕይ « ፊተኛውና መጨረሻው ህያውም እኔ ነኝ» እነዚህንና ሌሎችን መሠረት በማድረግ ቤተክርስቲያን ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ እንደሆነ ታምናለች ትመሰክራለች ዝዛላገሆፀርኪ ሐ ጌታችን ኢየሱስ ከርስቶስ እግዚአብሔር ነው ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔርነት የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት የመሰከሩ ሲሆን አባቶቻችንም አምልተውና አስፍተው አስተምረዋል ቅዱስ ዮሐንስ ምስጢረ ሥጋዌን በተናገረበት አንቀጽ «ቃልም እግዚአብሔር ነበር ቃልም ሥጋ ሆነ» ብሎአል ዮሐ ዳግመኛም ንጉሥ ዳዊት ስለ ክርሰቶስ ዕርገት በዘመረበት መዝሙሩ «ዐርገ እግዚአብሔር በይባቤ ወእግዚእነ በቃለ ቀርን እግዚአብሔር በመለከት ድምጽ ዐረገ» ብሎአል መዝ ቅዱስ ሉቃስም ግብረ ሐዋርያትን ሲጽፍ በዝ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተክርስቲያን ትጠብቋት ዘንድ በማለት ደሙን በቀራንዮ ያፈሰሰው ኢየሱስ ክርስቶሰ እግዚአብሔር እንደሆነ መስክሯልፎ ቅዱስ ቄርሎስም «እስመ እግዚአብሔር ውእቱ ወአኮ ገብር ወተለዐለ ኅበ ስብሐተ እግዚአብሔር ወዳዕሙ ነሥአ አርአየ ገብር እንዘ ሀሎ በጳዱ ዕሪና ምስለ አብ ወኢኮነ ሰብአ ወእምዝ ረከበ ብዕለ መለኮት» «እርሱ እግዚአብሔር ነውና ተገዥ ሆኖ ኖሮ ወደ እግዚአብሔርነት ክብር የደረሰ አይደለም ከአብ ጋር በአንድ ትክክልነት ሳለ የተገዥ ባሕርይን ነሣ እንጂ መለኮት ሰው ሆኖ ኋላ ክብርን ያገኘ አይደለም» ብሎአል ስለዚሀ ሐዋርያት እንዳስተማሩት ሊቃውንትም እንደመሰከሩት ቤተክርስቲያናችንም እንደምታምነው ኢየሱሰ ክርስቶስ እግዚአብሔር ነው መ ጌታችን ኢየሱሰ ክርስቶስ ፈጣሪ ነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሁሉ ነገር አስገኝና ፈጣሪ ነው ቅዱስ ዮሐንስም በወንጌሉ «ሁሉ በእርሱ ሆነ ከሆነውም አንዳችስ እንኳ ያለ አርሱ አልሆነም» በማለት ፈጣሪነቱን መስክሯል ዮሐ ዳግመኛም ቅዱስ ጳውሎስ «ሁሉ ለእርሱና በእርሱ ተፈጥሯል» ብሎአል ቆላ ቅዱስ ኤፍሬምም በውዳሴ ማርያም ድርሰቱ «እስመ ውእቱ ፈጠረነ እርሱ ፈጥሮናልና» በማለት የጌታን ፈጣሪነት መስክሯል። ነገር ግን የአዳምን እዳ መክፈል ያለበት አዳም ነው ቢሆንም ግን አዳም እዳውን ለመክፈል ከአቅሙ በላይ ነበር ስለዚህ አዳም እንዲድን የግድ እግዚአብሔር ሰው መሆን ነበረበት በዚህም መሠረት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የአዳምን ሥጋ ተዋሕዶ ሰው ሆነ በቤተ ክርስቲያናችን ትምህርት ተዋሕዶ ስንል ሥጋዊ አካል ከመለኮታዊ አካል መለኮታዊ አካል ከሥጋዊ አካል ሥጋዌ ባሕርይ ከመለኮታዊ ባሕርይ መለኮታዊ ባሕርይ ከሥጋዊ ባሕርይ አንድ ሆነ ማለታችን ነው ይህም ማለት ጌታችን ከሁለት አካል ከሥጋዊ አካልና ከመለኮታዊ አካል አንድ አካል ከሁለት ባህርይ ከሥጋዊ ባህርይና ከመለኮታዊ ባህርይ አንድ ባህርይ ሆኗል ማለት ነው ይህ ተዋሕዶ በተአቅቦ በመጠባበቅ ማለትም ሁለቱ ባህርያ ሳይጠፉ ነው ቤተ ክርስቲያናችንም የአካልንም የባህርይንም ተዋሕዶ እንደሚከተለው ታስተምርማለች ዖላሳል ታፖዎእዶ የቤተ ክርስያናችን መሠረተ እምነት ከሆኑት ትምህርቶች መካከል አንደኛው የሥጋዊ አካልና የመለኮታዊ አካል ተዋሕዶ ነው በምስጢረ ሥላሴ ትምህርት ሥላሴ በአካል ሦስት እንደሆኑ እንማራለን ለእያንዳንዳቸውም ፍፁም መልክዕ ፍጹም ገፅ ፍጹም አካል እንዳላቸው እናውቃለን መለኮታዊ አካል ግን የማይታይ የማይዳሰስ የማይጨበጥ ረቂቅ ነው በሌላ በኩል ሥጋዊ አካል ግዙፍ የሚታይ የሚዳሰስ እንደሆነ እናውቃለን በቤተ ክርስቲያን ትምህርት የእነዚህ የሁለት አካላት የሥጋዊ አካልና መለኮታዊ አካል ተዋሕዶ የአካል ተዋሕዶ ይባላል ይህንንም መጻሕፍት በምልዐትና በስፋት ይመሰክራሉ ጌታችን ከአይሁድ ጋር በተከራከረበት ምዕራፍ «እውነት እውነት እላችኋለሁ አብርሃም ሳይወለድ እኔ አለሁ አላቸው» ዮሐ በዚህ ዐረፍተ ነገር አብርሃም ሳይወለድ ጌታ እንደነበር ቢናገርም ጌታችን በሥጋዊ አካል ከተገለጠ ገና ሃምሳ ዓመት እንዳልሞላው አይሁድ ተናግረዋል። ሆኖም ግን እነዚህ ምሣሌዎች ተዋሕዶን ፈፅሞ የሚገልፁ አይደሉም ሕፀፅ አለባቸው የተዋሕዶ ምስጢ ር ሊፃፍም ሊነገርም ከሚችለው በሳይ ረቂቅ ነውና ምስጢርን የሚገልጽ አምላካችን ልዑል እግዚአብሔር የረቀቀውንና የራቀውን ምስጢር ይግለፅልን አሜን ቃሩ ዖታዎሪዶ ለፅፈጎም አንዳንድ ሰዎች እግዚአብሔር ሰው ሳይሆን አዳምን ማዳን ሲችል ለምን ሰው እንደሆነ ይጠይቃሉ እግዚአብሔር አምላክ ከሀሌ ኩሉ እንደመሆኑ መጠን ሰው ሳይሆን አዳምን ማዳን ቢችልም የመለኮት ከሥጋ ጋር መዋሐድ ግን አስፈላጊ ነበር ከላይ እንደተመለከትነው አዳም የበደለውን በደል የመካስ አቅም አልነበረውም ነገር ግን እንዲድን ከተፈለገ የግድ መለኮት የአዳምን ሥጋ ተዋሕዶ መገለጥ ነበረበት ከዚህም በተጨማሪ አዳም ሞት ነግሶበት ለ ዘመን ኖሯልና ጌታችን ሥጋን ተዋሕዶ አድኖታልፎ በሌላም በኩል ዲያብሎስ በእባብ ሥጋ ተሰውሮ አዳምን ከእግዚአብሔር ቢለየው ጌታችን ሥጋን ተዋሕዶ አድኖታል በተረቱበት መርታት ልማድ ነውና ዝዛላገሆፀርኪ ያፇዎጓዶ ፈፀ ዖሟእአራ ዖፖሥጎንሪ ለመያፆቻ ጌታችን ሰው የሆነው በተዋሕዶ እንደሆነ ከላይ ተመልክተናል ከእዚህ ውጪ ግን በጌታችን ተዋሕዶ ላይ የሚነሱ የተሳሳቱ አመለካከቶች አሉ እንደሚከለተው እንመለከታቸዋለን እንበለ ውላጤ ያለመለወጥ አንዳንዶች የጌታችን ሰው መሆን በመለወጥ መሆኑን ያስተምራሉ ይህም የቃና ውሃ ወደ ወይን እንደተለወጠ የሎጥ ሚስትም ወደ ጨው ሐውልትነት እንደለወጠች መለኮትም ከመለኮትነት ወደ ሥጋነት ተለውጧል የሚሉ አሉ ነገር ግን ይህ ትምህርት ከነገረ ድህነት አንፃር ስንመለከተው እጅግ ከንቱ ሆኖ እናገኘዋለን በመጀመሪያ ደረጃ ሰው ሰውን ሊያድነው አይችልም መለኮት ሰው ወደ መሆን ተለውጣል ካልን ፍፁም ሰው ብቻ ነው ማለት ነው ይህ ደግሞ በቀጥታ ከነገረ ድህነት ትምህርት ጋር ይጋጫል። «እኔ እግዚአብሔር ነኝ ከእኔ በቀር ሌላ የሚያድን የለም» ኢሣ ከዚህም በተጨማሪ የውላጤን ትምህርት ማመን ክርስቶስ በከንቱ እንደሞተ ማመን ነው ምክንያቱም አዳምን ሰው ማዳን ቢችል ኖሮ ከአቤል ጀምሮ እስከ ዘካርያሰ ድረስ የፈሰሰው የነቢያት ደም ባዳነው ነበር ራሱም እግዚአብሔር በቃሉ «እኔ እግዚአብሔር አልለወጥም» ሲል ተናግሯልር ሚል ቅዱስ ጳውሎስም በመልዕክቱ «ኢየሱስ ክርስቶስ ትላንትና ዛሬ እስከዘላለም ያው ነው» ሲል ገልጂል ዕብ በተለይ በዚህ ዐረፍተ ነገር ትላንትና ብሎ ቅድመ ሥጋዌውን ዛሬ ብሎ መዋዕለ ሥጋዌውን እስከ ዘላለም ብሎ ድህረ ሥጋዌውን ገልፆ በሦስቱም ጊዜያት እንዳልተለወጠ እደማይለወጥም አመልክቷል ቅዱስ ኤፍሬምም በድርሰቱ «ዘኮነ ሰብአ ዘእንበለ ፍለጠት ወኢውላጤ መለኮት ንጹህ ዘአልቦ ሙስና» ያለመለየትና ያመለወጥ ሰው የሆነ ይኸውም መለወጥ የሌለበት ንፁህ መለኮት ነው» ብሎአል ወማዘሰንበት እንበለ ሚጠት ያለመመለስ የሥጋና የመለኮት ተዋሕዶ ወደ አለመዋሐድ የሚመለስ አይደለም ሚጠት ማለት መመለሰ ማለት ሲሆን ማየ ግብዕ የግብጽ ውኃ አስቀድሞ ውሃ በመቀጠልም ደግሞ ደም ከዚያም ተመልሶ ውሃ አንደሆነ እንዲሁ ደግሞ በትረ ሙሴ አስቀድሞ በትር በኋላም እባብ በመቀጠልም ተመልሳ በትር እንደሆነች መለኮትም አስቀድሞ መለኮት ከዚያም ሥጋ በኋላም ተመልሶ መለኮት እንደሆነ የሚናገሩ አሉ የሚጠት ዝዛላገሆፀርኪ ትምህርት ብዙም ከውላጤ ያልተለየ በመሆኑ ከላይ የተናገርናቸው ነገሮች በሙሉ ለእነዚህም ይሠራሉ ከዚህም በተጨማሪ መለኮት ከሀሊ ኩሉ አንደመሆኑ መጠን ሥጋ መሆን ቢችልም ሥጋ ግን ወደ መለኮትነት የመመለስ ስልጣን የለውም ይህም የሚጠት ትምህርት እርስ በራሱ የሚጣላ መሆኑን ያመለክታል እኛ ግን ጌታችን በተዋሕዶ ሰው እንደሆነ እናምናለን እንበለ ህድረት የህድረት ትምህርትን ለመጀመሪያ ጊዜ ያስተማረው የቁስጥንጥንያው ሊቀ ጳጳስ መናፍቁ ንስጥሮስ ነው ንስጥሮስ «እመቤታችን የወለደችው አምላነክነት የሌለው ሰው ብቻ ነው» ይላል «ኋላ ግን ሲጠመቅ የአብ ልጅ መጥቶ አደረበት በዚህም የጸጋ አምላክነትን አገኘ» በማለት የህድረትን ምንፍቅና አስተማረ ህድረት ማለት ሰይፍ በሰገባው ዳዊትም በማህደሩ እንደሚያድር እንዲሁ መለኮት በሥጋ እንዳደረበት የሚናገር ኑፋቄ ነው ነገር ግን ጌታችን ከመጠመቁ በፊት አምሳክ እንደሆነ የሚናገሩ የመጽሐፍ ቅዱሰ ክፍሎች አሉ «ሕፃን ተወልዶልናልና ወንድ ልጅም ተሰጥቶናል ስሙም ድንቅ መካር ኃያል አምላክ » ኢሳ ቅዱስ ገብርኤልም «እርሱም ታላቅ የልዑል ልጅ ይባላል ለመንግሥቱም መጨረሻ የለውም» በማለት ከጥምቀት በፊት አምላክ መሆኑን አብስሯል ሉቃ መጥመቁ ዮሐንስም በማኅጸን ሆኖ ለጌታ የአምልኮት ስግደት ለእመቤታችን የፀጋ ስግደት በመስገድ ጌታችን እንኳን ከመጠመቁ ከመወለዱ በፊት አምላክ መሆኑን በተግባር አሳይቷል እናቱ ቅድስት ኤልሣቤጥም «የጌታዬ እናት» ሉቃ በማለት እመቤታችን ወላዲተ ሰብእ ሳትሆን ወላዲተ እግዚእ ወላዲተ አምላክ እደሆነች ተናግራለች ሰብአ ሰገልም ከምስራቅ በመምጣት ለተወለደው ሕፃን ሰግደዋል እንበለ ቱሳሔ ያለመቀላቀል ቱሳሔ ማለት መቀላቀል ማለት ነው እንደ ማርና እንደ ውሃ እንደ ቡናና እንደ ወተት ማለት ነው ማርና ውሃ ሲቀላቀሉ ውሃው ማሩን አሟምቶ ማሩም ውሃውን ያጣፍጠዋል እንዲሁ ደግሞ ቡናና ወተት ሲቀላቀሉ ቡና ወተቱን አጥቁሮ ወተቱም ቡናውን ያነጣዋል ጣዕም ማዕከላዊ መልክዕ ማዕከላዊ ይሆናልር በቱሳሔ ትምህርት መለኮት ከሥጋ ጋር ተቀላቅሏል። ማርና ውሃ ሲቀላቀሉ ሁለቱም ባህርያቸውን ለቀው መካከኛ ብርዝ እንደሚገኝ እንዲሁ ደግሞ ቡናና ወተት ሲቀላቀሉ ሁለቱም ባህርያቸውን ለቀው መካከለኛ ማኪያቶ እንደሚሆኑ በቱሳሔ ትምህርት መለኮትና ሥጋ ባህሪያቸውን ለቀው መካከለኛ ነገር ተፈጥሯል የሚሉ ናቸው ዝዛላገሆፀርኪ ይህ ግን ከብዙ ነገሮች አንጻር ስህተት ነው የመጀመሪያው ከመዳን ትምህርት አንፃር ሲሆን ሰውን ሊያድነው የሚችለው እግዚአብሔር ብቻ እንጂ መካከለኛ ነገር አይደለም በእግዚአብሔርና በአዳም መካከል ያለ ፍጡር አዳምን ማዳን ቢችል ኖሮ ነቢያት ይልቁንም ደግሞ መላእክት በሰውና በእግዚአብሔር መካከል ሆነው አዳምን ባዳኑት ነበር ከዚህም ውጪ መለኮት ለቅፅበት ያህል እንኳ ባህርይውን አለቀቀም ሥጋም እንዲሁ ቱሳሔ ካልን ግን እግዚአብሔርን ከእግዚአብሔርነቱ እንደማዋረድ ነው በቤተ ክርስቲያን ትምህርት ግን ጌታችን ሰው የሆነው እንበለ ተሳሔ ያለመቀላቀል በተዋሕዶ ነው እንበለ ቡዐዴ ያለመወዳጀት ቡዐዴ ማለት መወዳጀት የወዳጅነት ማለት ነው እንደ ዛቢያና እንደ ምሣር ዛቢያና ምሣር ሲያስፈልግ እንደሚገናኙ አለበለዚያም እንደሚለያዩ በቡዐዴ ትምህርት መሠረት «ለመለኮትና ለሥጋም እንደዚሁ ነው የሚሉ አሉ ሌላው «በቡዐዴ ትምህርት መከራን የተቀበለው ሥጋ ብቻውን ነው ምክንያቱም ለመለኮት መታመም አይስማማውምና ይላሉ ይህም በቀጥታ ከድህነት ጋር ስለሚያጋጭ ጌታችን ሰው የሆነው እንበለ ቡዐዴ ያለመወዳጀት ለዘለዓለም እንደሆነ እናምናለን እንበለ ትድምርት ያለመደረብ ትድምርት ማለት መደመር መደረብ ማለት ነው ለትድምርት ትምህርት መሠረት ሰው ልብስ እደሚሜደርብ እንዲሁ በሥጋ ላይ መለኮት ተደርቧል የሜል ነው በመሰረቱ ለመለኮት በሥጋ ላይ መደረብ አይችልም ምክንያቱም ሥጋ እጅግ ደካማ ሲሆን መለኮት ግን ኃያል ነው ከዚህም ውጪ መለኮት በሥጋ ላይ የመደረብ ባህርይ የለውም ይህም ጌታችን ሰው የሆነው እንበለ ትድምርት መሆኑን ያሣያል በቤተ ክርስቲያናችን ትምህርት እግዚአብሔር ሰው የሆነው እንበለ ውላጤ እንበለ ሚጠት እንበለ ህድረት እንበለ ቱሣሔ እንበለ ቡዐዴ እንበለ ትድምርት በተዋሕዶ በተአቅቦ በመጠባበቅ ያመጠፋፋት ነው ዝዛላገሆፀርኪ አንድ ባህርይ በርበ እከኪ የምስራቅ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት ከ ከህርከ የሚባሉት የኢትዮጵያ የግብፅ የህንድ የአርመን የሶርያ አብያተ ክርስቲያናት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተዋህዶ ከሁለት አካል አንድ አካል ከሁለት ባሕርይ አንድ ባሕርይ መሆኑን ያምናሉ ለመጀመሪያ ጊዜ ዓለም አቀፋዊቷ ቤተ ክርስቲያን ለሁለት የተከፈለችበት ዋናው ምክንያት የአንድ ባህርይ እና የሁለት ባህርይ ትምህርት ነው ባሕርይ ሳንል የመለኮትና የሥጋ ባሕርይን ማለታችን ነው የመለኮት ባሕርይ ምሉዕ ረቂቅ ኃያል ባዕድ ሕያው ወዘተ ሲሆን የሥጋ ባሕርይ ደግሞ ውሱን ግዙፍ ድኩም ነዳይ መዋቲ ወዘተ ነው በ ዓም በተደረገው የኬልቄዶን ጉባኤ በሮማው ፖኘ ሊዮን ሁለት ባሕርይ በሚል ደብዳቤ የተመሩት የቁስጥንጥንያና የሮም አብያተ ክርስቲያናት የሁለት ባህርይ የሚል አዲስ አሳብ በማምጣት ኑፋቄ ሲያቀርቡ የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳስ ዲዮስቆሮስና ተከታዮቹ በተዋህዶ አንድ ባህርይ ብለው ጉባኤውን ጥለው ወጥተዋል የቤተ ክርስቲያን አባቶችም ይህንን ጉባኤ ጉባኤ ከለባት የውሾች ጉባኤ በማለት ይጠሩታል ኦርቶዶክሳዊያን ክርስቲያኖች በአንድ ባህርይ የሚያምኑት ከሁለቱ ባሕርያት የአንዱን የክርስቶስ ባህርይ ክደው አይደለም በሁለቱ ባህርያት የባሕርየ የመለኮትና የባሕርየ ሥጋን ተዋህዶ በማመን እንጂሖ ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስን የሰውነት ባህርይም ሆነ የአምላክነት ባህርይ አትክድም ነገር ግን ጌታችን በተዋህዶ ፍፁም ሰው ፍፁም አምሳክ እንደሆነ ታምናለች የጌታችንን የባህርይ ተዋህዶ መላእክት መጥምቁ ዮሐንስ እግዚአብሔር አብ ሐዋርያት እንዲሁም ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን መስክረዋል ይህንንም አንድ በአንድ እንመለከተዋለን የመላእክት ምስክርነት መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ እመቤታችን ለብስራት በተላከበት ወቅት ስለምትፀንሰውና ስለምትወልደው ልጅ «በያቆብ ዝዛላገሆፀርኪ ቤትም ላይ ለዘላለም ይነግሳል ለመንግስቱም መጨረሻ ያለውም» ብሎአታል ሉቃ መፀነስና መወለድ የሰው ባህርይ ሲሆን ፍፃሜ የሌለው የመንግስት ባለቤትነት ደግሞ የአምላክነት ባህርይ ነው የቅዱስ ገብርኤል ብስራት ሁለቱ ባህርያት እንደተዋሀዱ ያመለከታል ዳግመኛም የጌታን ልደት ለእረኞቹ ያበሰረው መልእክ «አትፍሩ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋል» ብሏቸዋል ሉቃ ይህም በዳዊት ከተማ በሥጋ የተወለደው የማርያም ልጅ የመለኩትን ባህርይ እንደተዋሀደ ያመለክታል ቅዱስ ያሬድም ስለመላእክት በተናገረበት ድርሰቱ «ወሶበ ርእዩ እግዚኦሙ ዘአስተጋብአ ከሩሎ ፍጥረታተ እንዘ ይነብር ውስተ ኅፅንኪ ወዘይሴሲ ለኩሉ ፍጥረት ይጠቡ ሐሊበኪ ከመ ሕፃን ኀሠሥዎ ውስተ አርያም ወበህየ ረከብዎ ምስለ አቡሁ ወመንፈስ ቅዱስ ከመ ትካት» «ፍጥረትን ሁሉ የሚመግብ ጌታ በብብትሽ ተቀምጦ ጡትሽን እንደ ሕፃን ሲጠባ ባዩ ጊዜ በአርያም ፈለጉና በዚያም እንደ ቀድሞው ከአባቱና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አገኙት» አንቀጸ ብርሃን በማለት በቤተልሄም የተወለደው ኢየሱስ ክርስቶስ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አንድ ባህርይ እንደሆነ መላእክት መስክረዋል የቅዱስ ዮሐንስ መጥምቁ ምስክርነት ስለ ብርሃን ይመሰክር ዘንድ መጣ የተባለለት ቅዱስ ዮሐንስ በስብከቶቹ ሁሉ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን አንድ ባህርይነት መስክሯል ይህንንም ለአይሁድ ሲናገር «እኔም አይቼአለሁ እርሱም የእግዘብሔር ልጅ እንደሆነ መስክሬአለሁ» ብሏል ዮሐ ይሄም በዮርዳኖስ የተጠመቀው የእግዚአብሔር አብ የባህርይ ልጅ የሥጋን ባህርይ የተዋሀደው መሆኑን ልብ ይሏል ዳግመኛም ቅዱስ ዮሐንስ ጌታችንን ከማጥመቁ አስቀድሞ «እኔ በአንተ ልጠመቅ ያስፈልገኛል አንተ ወደ እኔ ትመጣለህን።