Detecting...

Please whitelist dirzon to continue.

or subscribe for ad-free contenct.

dirzon
  • Convert to Pdf
  • Reading List
  • Summary
  • Audiobook
  • Search
  • Upload
  • myzon
  • Log in
  • Register
English  አማርኛ  Français  العربية  Portuguese
Book of the day

aynuma አይኑማ (1).pdf


Advertisement
  • word cloud

aynuma አይኑማ (1).pdf
  • Extraction Summary

ብላ መታወቂያዋን በያዘ እጂ ወደ ሰባት ቁጥር ክፍል ውስጥ አልጋ ላይ እንዳያት በጀርባዋ ተኝታለች በራሱ እንደማፈር ብሎ በብብቱ የያዘውን ጋዜጣ አወጣና ትናንት ጠዋትና ማታ ያነበበውን አንድ ሪፖርት ለሶስተኛ ጊዜ ለማንበብ በቀስታ ገላለጠ ገና ትኩስ ወሬ ነው የዜናውን ሃያልነት ለመረዳት ደበሌ አይከብደውም ግን ዘውዲ ከሞተች ጀምሮ ስለ ዘውዲ ሞትና አሟሟት የተፃፈላት ወሬዜና እንዳለ ቢፈልግ ነገ ከነገወዲያ እያለ ቢጠብቅ አንድ መስመር እንኳን አልተፃፈላትም አሁን የሚያነበው ዜና በስህተት እንደሞተ ተቆጥሮ መቃብር በመውረድ ላይ እያለ ከሞት ስለተነሳው ሚኒሊክ ስለሚባለው የሰፈሩ ሰው ነው በዚህ ዘመን ያለ ገንዘብ ሕይወት የለም ለሚቀርቧት እንደምትለው ሀብት ቢኖራት ከደበሌ አትለይም ገንዘብ ከሚሰጧት ጋር ስትተኛ በልቧ ሁልጊዜ ደበሌ ነው አጠገቧ ደሞ ከሌለ ልክ እሱ መዋደድን እንዳበላሸ ሁሉ ጎርበጥባጣ ውስጥዋ ላይ ቅናት ይዘንባል እጁን እየጎተተችው እሱም እየተጎተተ ወደ መኝታ ቤቱ ገቡ በሩን መለሰችና ሹፍ የያኩትን ለማንም እንዳትናገል ምን።

  • Cosine Similarity

ና ልነእዚሀከጎሰለ ዐይኑማ የማነሽ ዐይናማ ደበሌ እጀታውና ክሳዱ መቆሸሽ የጀመረ የካኪ ካፖርት ለብሷል በቀኝ ጆሮው ሕፅን ቀለሙ ሊያልቅ ትንሽ የቀረው የላስቲክ ቱቦው ነጭ የሆነ ቀይ ቢክ ስክሪፕቶ ሰክቷል አራት ማዕዘን ቅርፅ ብጣቂ ጨርቅ ከካፖርቱ ግራ የደረት ኪስ እፊያ ጠርዝ ላይ ተጣብቃለችፁ ስራ እያጣደፈው ወዲያ ወዲህ ሲል ወይም እቆመበት ሲነቃነቅ ይህቺ ብጣሽ ጨርቅ ላይና ታች ግራና ቀኝ እያለች በና ለመሄድ የምትከጅል ትመስላለችፁ ወደ ላይ ስትገለብ ሮ ዎሬል የሚል መደብዘዝ በጀመረ ቀይ ማርከር የተፃፈ ፅሑፍ ይታያል በግራ ክንዱ ብብት በስልት የተጠቀለለ የጋዜጣ ቱቦ ወሽሸቋል እጆቹን ካፖርት ኪሶቹ ከቶ ከሁለት ሳምንታት በፊት ያጋጠመውን ነገር ያስባልይሄን ሲያስብ አይኖቹ እንባ አቅርረው እንደ እርጥብ ብዮች መፍለቅ ጀመሩ ችት ሻገር ሆቴል ሁለት መግቢያዎች አሉት አንደኛውና ዋናው ትልቁ መንገድ ጎን ያለው ሲሆን ሁለተኛውና ትንሹ ደሞ በጀርባ ነው እዚህ ሆቴል ደበሌ አራት አመታት ሲሰራ ምናልባት እሱ ተረኛ ባልሆነበት ዕለት ካልሆነ በተቀር ለብቻዋ ያደረች ሴት ለብቻው ያደረ ወንድ አጋጥሞት አያውቅም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ዝዋይ ከተማ አጠናቆ በውጤቱ ዝቅተኛነት ዩንቨርሲቲ ወይም ኮሌጅ ሊገባ አልቻለም ገንዘብም ስላልነበረው በግሉ ከፍሎ መማር አልሆነለትም በዚህ ጭንቀት ውስጥ እያለ ረብሻ ይነሳና የሆነ የፖለቲካ ድርጅት ሊያሳስርህ እየፈለገህ ነው ሲባል ጥቁት ቀናት እዛና እዚህ ሲንከራተትና ሲደበቅ ቆይቶ አንደኛውኑ ወደ አዲስአባ ይመጣና በነሲብ በመረጠው ድያልሐ ያሐ በተባለ የውሸት ስም የቀበሌ መታወቁያ አወጣ ለሆዱና ለልብሱ የሚሆን ትንሽ ገንዘብ ለማግኘት ሸገር ሆቴል ተቀጠረ እስከዛሬ ይፈልግሃል የተባለው ድርጅት አላገኘውም ዛሬም እንደ ዝዋዩ ጊዜ በፍርሃት ባይሆንም አሳሪው ያለበትን ቦታ ደርሶበት እስኪወስደው ይጠብቃል እዚህ ሆቴል ተቀጥሮ ሲሰራ የተለያዩ ከባድና ቀላል አይነት ችግሮች አጋጥመውታል ቀልዶችና አሳዛኝ ሁኔታዎች ታዝቧል በሚያስቀው ስቋል በሚያሳዝነውም አዝኗል ከሶስት ሳምንታት በፊት ሚያዚያ መጨረሻ አካባቢ እንደሆነው አይነት ከስር መሰረቱ ያነጋው ሁኔታ በዚህች ምጥን ዕድሜው አጋጥሞት አያውቅም የሆነው በአጨሩ እንዲህ ነው ከምሽቱ አንድ ሰአት ላይ ዕድሜዋ በግምት ወይም የሚሆን ጥለቱ ቀይ ቀለም ያለው ነጠላ የተከናነበች ልጅ በጀርባ በር ገባችና ማከራያ ቢሮው ድረስ ቀጥ ብላ መጥታ ማረፊያ ክፍል እንደምትፈልግ ተናገረች ደበሌ መልኳን እንኳን በደንብ ሳያጤነው አለቃው ትጊትዕግስት የሰው መልክ በተቻለህ መጠን ልብ ብለህ እይ እንዳላለችው ሁሉ ውብ ገፅዋ ላይ ማፍጠጡ በሌላ ነገር እንዳይተረጉምበት በማሰብ ብቻ ካልተያዙት መኝታ ቤቶች እንዳመጣለት አምስት ቁጥርን መደበላትፁ እሷ ግን ሆቴሉን እንደምታውቀው ሁሉ ያንን ትሰጠኛለህ። ብሎ ሊጠይቃት አስቦ በአካባቢው የነበረው ጫጫታ የልጅትዋ ችኩል የመሰለ አረማመድና ተከትሏት የሚጎተት የመሰለ እንግዳ ድባብ አገቱትና ሳያደርገው ቀረ ይሄ የምትጎትተው ወይም ከቦ የሚከተላት ድባብ ከተሰራባቸው ነገሮች አንደኛው ውብ አይኖቿ እንደጉም የለበሱት ኮስታራነት ነበር በጨለማ ሰበብ አልታየውም እንጂ ይሄ ሰው የሚያሸሽ ድባብዋን ግትር ብሎ ከተዘረጋው ካልተዝናናው ፌስታሉን ካልያዘው ግራ እጂ ማረጋገጥም ይችል ነበር ግራ እጂ ግን በወዲያ በኩል ነው እንደተለመደው እኩለ ሌሊት ላይ ከእሱ የሚጠበቅበትን ስራ ሁሉ አጠናቆ የሆቴሉ በሮች በሙሉ መዘጋታቸውን ማረጋገጥ ራት መብላት ለመጨረሻ የሚያጤሰውን አንድ ሲጋራ መግዛት ሊተኛ ሰራተኛ ክፍል ገባ ልብሱን አወላልቆ እንቅልፍ እስኪወስደው ድረስ አልጋ ውስጥ ጋደም ብሎ ሲያጤስ ጩኸት ሰማ መጀመሪያ ድምፁ ከጓሮ በኩል የትጊ ወዳጅ ከነበረው አቶ ጅግሳ ከሚኖርበት የሆቴሉ ተጎራባቾች ከሚኖሩበት ድርድር ቤቶች ከአንዱ የመጣ መስሎት ነበር በዛ በኩል ግን የዚያ አይነት ጩኸት ይቅርና ሰው ሲጠራራ ሰምቶ አያውቅም ምናልባት ደሞ ከሴተኛ አዳሪዎቹ አንዷ ከደንበኛዋ ወይም ከወዳጅዋ ጋር በልፊያ መሃል የምታሰማው ድምፅ መሰለው ግን እንዲህ አንዴ ብቻ ከፍ ብሎ የሚሰማበትና ጩኸት የሚመስልበት ምክንያት ግልፅ አልሆነለትም አልጋው ላይ ቁጭ ብሎ እንደገና የሆነውን በልቦናው ሲከልስ የድምፁ ልዩ የመሆን ነገር ከነከነው ከእንግዳ ውበቱ ላይ ወፍራም መከራ የተለሰነበት ድምፅ ነው የሲጋራው ቁሩ እንዳይበላሽበት ሲጋራውን በጥንቃቄ ተርኩሶ አልጋው ዳር እንደተቀመጠ ያንን ጩኸት ዳግመኛ ለማዳመጥ ጠበቀ ምክንያቱም የሰማው ድምፅ ውብና መከረኛ ብቻ ሳይሆን መረጃ የሆነ የመቀጠል ተስፋ ያለው ይመስል ነበርፁ ለምን እንደሆነ አሁን ድረስ አይገባውም ለሁለተኛ ጊዜ ድምፁ ቁልጭ ብሎ መጣ ለሁለተኛ ጊዜ ድምፁን ሲሰማ አእምሮው ውስጥ የመጣችው ማታ ላይ ክፍል የተከራየችው ዘውዲት ነበረች ድምፁን ለሁለተኛ ጊዜ ሲሰማ ከማንም ከምንም ቀድማ በሃሳቡ የመጣችው ዘውዲት መሆንዋን ግን ለፖሊስ አልነገረም ለምን አእሷ። ሱሪውን ሲያጠልቅ አንድ የስራ ጓደኛው በር በርግዶ ገባና ቁጥር ሰባት ያለችው ልጅ አንድ ነገር ሆናለች አቦ ሌላ ሰው ደሞ ክፍልዋ አብሯት የለም አለው ደበሌ ምንም ሳይናገር የጫማዎቹን ሲር ሳያብት ጓደኛውን ተከትሎት ወጣ ዋናው ቤት መውጫና መግቢያ ላይ አለቃው ትጊ ከእሁድ ዙረቷ መጥታ ገና ቦርሳዋን በትከሻዋ እንዳንጠለጠለች ቆማለች ምን ሆናችሁ። እያለ የሰባት ቁጥርን በር በቀስታ ገፋ አደረገና ወደ ውስጥ አየ ትጊ ከጀርባው እየተንጠራራች ትገፋዋለች የሽቶዋና የላብዋ ጠረን ተመሳጥሮ ይሰማዋል በስተግራው ሁለት ሴቶችና ስለ ጩኸቱ የነገረው የስራ ጓደኛው ቆመዋል አንድ እርምጃ ተራምዶ ወደ ውስጥ ገብቶ ፊቱን ወደ ግራ እንዳዞረ በድንጋጤ የተከፈተ አፉን በእጁ ከደነ ይሄን ሁኔታውን ሲያዩ ምን እንደሆነ ባይረዱም የስራ ባልደረቦቹና ትጊ የማይታይ እጅ እንደገፋቸው ሁሉ ወደ ኋላ ወደ በረንዳው ጠርዝ አፈገፈጉ ዘውዲት አልጋው መሀል ደም የተነከረ አንሶላ ብርድልብስ ላይ ራቁቷን ተኝታለች እጆቿ ግራና ቀኝ መስቀልኛ ተዘርግተዋል ከአልጋው ስር እስከ በሩ ድረስ ጥቁር የደም ኩሬ ተኝቷል በስተግራ ግድግዳው ላይ ደም ጠበልኛ ተረጭቷል በዛሬ ድረስ ይሄ እንዴት ሊሆን እንደቻለ ይጠይቃል መልሱን አላገኘም ደበሌ ይሄ ሲያጋጥመው የተነገረለት ድፍረቱ አብሮት አልነበረም ተሳድቦ የሚያስከፍል አስፈራርቶ የሚያሳምን ተቆጥቶ የፈለገውን የሚያገኝ ደበሌ አልነበረም ፊቱን መለስ አድርጎ አናቱን በሁለት እጆቹ ያዘ እግሮቹ ክፍሉን እንደለቀቁ በረንዳው ላይ ቆሞ ከአንድ ሰአት በፊት የበላውን መፅሐፈ ዶሮ ወደ ታች ወደ አትክልቱ መደብ አስታወከ ማስመለሱ ታገስ ሲልለት እጁን ወደ ደረቱ ሰዶ የልቡን የጥንቸል ሩጫ ሲያዳመጥ ቆየ ትጊ ደበሌ ያየውንና የተረበሸበትን ነገር ላለማየት እንደገባትና ሁሉን ነገር እንደምታውቅ ሁሉ እጆቿን እያራገበች በሉ ዞር በሉ ፖሊስ ልጥራበት በሉ ዞር በሉ በሉ እንጂ እያለች ሰዎችን እየገፋች እየነዳች ወደ ዋናው ቤት ሄደች የደበሌ የስራ ጓደኛ ወንድ ነውና ከደበሌ የማላንስ ደፋር ነኝ ለማለት ከሴቶቹ ኋላ ቀርቶ ኮሰስ እያለ ወደ ክፍሉ በር ሲጠጋ ደበሌ ዞር ብሎ ልትችትታመም ፈለክ። ተው ይቅርብህ አለው ልጁ አልሰማም ገና ፊቱን ወደ ውስጥ ብቅ ከማድረጉ በሁለት እጆቹም አናቱን ይዞ ተመለሰ ደበሌ ፊቱን ከበሩ አዙሮ የሚያቃጥል መራራ ምራቅ እየተፋ ቆሟልነ በድጋሚ የሚያስታውከው መስሎት ጎበጥ ብሎ ይጠብቃል ትንሽ ሻል ሲለውና የሆዱ ነገር ሲያስተማምነው ጓደኛውን በረንዳ ላይ ትቶ ወደ ዘውዲት ክፍል ተመልሶ ገባ አሁን ትዕይንቱ እንደ መጀመሪያው አልሰቀቀውም የግራ እጅዋ አምባር ማሰሪያ ላይ ቆዳዋ ሶስት ወይም አራት ሳንቲ ሜትር ያህል ተሸንትሮ መድረቅ በጀመረ ደም ተመርጓል ገላዋ ከጡቶችዋ ጀምሮ እስከ ጉልበትዋ ደረስ የገረጣ ጠይም ነው በስስ ፀጉር የተጋረደ የአፍረቷ ፍዝ ሽንትር ይታያል አቁ በትንሹ ተከፍቶ የምትተነፍስ ትመስላለች የሚያምሩ ዐይኖቿ ምንም ነገር ያልተሰቀለበትን ግድግዳ የሚያዩ ይመስላሉ የሆነ ነገር ይመጣል ብላ የምትጠብቅም ትመስላለችፈ ከማሰሪያው የወጣ ፀገሯ ከፊሉ በደም ላቁጧል ደበሌ ባየው አልባሌ አለባበስዋ ስር የዚህ አይነት ማራኪ ገላ የያዘች አልመሰለውም እየቆየ የደነገጠው ደም በማየቱ ይሁን ወይ እንዳዛ የሚያምር ገላ በደም ተነክሮ ማየቱ ተምታቶበታል ነጠላዋ በደም ተነካክቶ በከፊል ወንበር ላይ በከፊል ወለል ላይ ነውአልጋው ራስጌ ካለው ጠረጴዛ ላይ ጥቁር የፕላስቲክ ማሰሪያ ያለው የኤሌክትሮኒክስ ሰአት ጀርባውን ወደ እሱ አድርጎ ተቀምጧል ለሁለት የተሰበረ ባለ ሶስት ቀዳዳ ምላጭ ከሰአቱ ጎን ደም ለብሶ ተጋድሟል ከእሱ ጎን የተጣጠፈ ሰፊ ብብት ያለው ወረቀት ተቀምጧል ከእሱ ጎን ክዳኑ በቆቡ የገባ ቢክ ስክሪፕቶ አለ አላህ ነፍሷን ማራት አላህ አድናት እያለ ፀሎት አጉተመተመ ትጊ ባለተረከዝ ጫማዋን አውልቃ ባዶ እግርዋን ወደ ሰባት ቁጥር እየመጣች ብቻዋን ነበረች። አለችው በደከመ ድምፅ ተጠጋትል ጣቶቹ ካፖርት ኪሱ ውስጥ በቁልፉ ይጫወታሉ ከአልጋዋ ይዛው የመጣችው ሙቀት በቁመቱ ሙሉ ይሰማዋል አይዞህ አለችው ያሳዝናል በጣም አለ እጁን ትከሻው ላይ ጣል አድርጋ ወደ ደረቷ ሳበችው ደበሌ አንጎል ውስጥ የዘውዲት የሚያማምሩ አይኖች ቦግ ብለው የሚያፈሱት ፈገግታ ትዝ አለው በሞት የሚወሰዱ አይኖች አልነበሩም ውበት ዝም ብሎ እንዲህ የሚደረገም አይመስለውም ነበር የትጊን ትከሻና መአዛ ተደግፎ ድምፁን ዝቅ አድርጎ መንሰቅሰቅ ጀመረ ትጊ ልጅ የላትም ልጅ ቢኖራት ደበሌ ቢሆን ትወዳለች ምክንያቱም ደበሌ ለዘውዲት እያለቀሰ ነው ለምን ዘግይቶ እንዳለቀሰ አልገባትምነቶ ጀርባውን እየዳበሰች ጥት ቆሙ መላከሞትን ያኮረፉ ከንፈሮቹን መርጠብ የጀመሩ ጉንጮቹን ብትስማቸው ትወዳለች ግን የእናት አልመሰላትም እሱን እንዳቀፈች ከርቀት የተዘጋውን ሰባት ቁጥር እያየች በለሆሳስ ድምፅ ደብዬ ተኛ እንቅልፍ ጥሩ ነው አለችው ከትከሻዋ ላይ ቀና ብሎ ራሱን ደፍቶ በዝምታ ወደ መኝታ ቤቱ ሄደ እሱ ክፍሉ ገብቶ በር ሲዘጋ በትጊ ጉንጮች ላይ መንታ የእንባ ዘለላዎች ወረዱ ከወር ተኩል በኋላ ጉዳዩን እንዲያጣራ የተመደበው ኮንስተብል ሻገር መጥቶ ትጊና በዛን ቀን ተረኛ የነበሩ ሰራተኞች ተጠራርተው ክብ ሰርተው ይሄን አዳመጡት በመጀመሪያ ምርመራውን ያቀለለልን ልጅቷ የሞተችበት አካባቢ ስላልተረበሸ ነው ማጅራቷ ላይ በፕላስተር የተጣበቀ ደብዳቤ አገኘን ለምን እዛ ላይ እንዳጣበቀችው አይገባንም እኛም እናንተም ባንጠነቀቅና ወረቀቱ ቢጠፋ ኖሮ ተጠርጣሪ ትሆኑ ነበር በደብዳቤው ላይ ራሷን እንዳጠፋች ገልፃለች ሟቿ አርግዛ ወዳጂ እግርዝናዋን ስለካደ ራስዋን ለመግደል ወስናለች ወንድሞቼና እህቶቼ ያን ዕለት ሁለት ነፍስ ነው የጠፋው እንደዚህ አይነት አሰቃቂ ድርጊት በራሷ ላይ የፈፀመችው እዚሁ ወዳጅዋ ጋር የምታድርበት ሆቴል መጥታ ነው ሆቴሉ ብቻ ሳይሆን ያን ቀን የተከራየችውና ህይወቷን ያሳለፈችበት ሰባት ቁጥር ክፍል ከሰውዬው ጋር ደጋግመው ያርፉበት የነበረ ነው አላማዋ የእሷን ነፍስ ብቻ ሳይሆን ከፍቅረኛዋ ጋር ያሳለፈችውንም የደስታ ጊዜ የደስታ ታሪክ ለማጥፋት ያቀደች ይመስላል መፈላሰፍ ለፖሊስ ቤቱ ባይሆንም ሰውዬው ተገኝቷል እሱን በሚመለከት ጥልቅ ምርመራ እየተካሄደ ነው ስራችን የተጠናቀቀ የሚመስለው ይኖራል በነገራችን ላይ አስከሬን መርማሪዎቹ የገረማቸው የሟቿ አይኖች ቅጠልያና እጅግ ውብ መሆን ነው ታዝባችኋል። የካኪ ካፖርቱን ነፋስ እየገለበው ከሆቴሉ ውጭ ቆሞ አየር ሲቀበል የለቀስተኛ ሰልፍ በወዲያ በኩል ወደ ዮሴፍ በዘገምታ ሲያልፍ ያያልር ሞተ በተባለው ሰው ምትክ እዛ ሬሳ ሳጥን ውስጥ ዘውዲት ያለች መሰለችው በሃሳቡ ሰባት ቁጥር ክፍል ውስጥ አልጋ ላይ እንዳያት በጀርባዋ ተኝታለች በራሱ እንደማፈር ብሎ በብብቱ የያዘውን ጋዜጣ አወጣና ትናንት ጠዋትና ማታ ያነበበውን አንድ ሪፖርት ለሶስተኛ ጊዜ ለማንበብ በቀስታ ገላለጠ ገና ትኩስ ወሬ ነው የዜናውን ሃያልነት ለመረዳት ደበሌ አይከብደውም ግን ዘውዲ ከሞተች ጀምሮ ስለ ዘውዲ ሞትና አሟሟት የተፃፈላት ወሬዜና እንዳለ ቢፈልግ ነገ ከነገወዲያ እያለ ቢጠብቅ አንድ መስመር እንኳን አልተፃፈላትም አሁን የሚያነበው ዜና በስህተት እንደሞተ ተቆጥሮ መቃብር በመውረድ ላይ እያለ ከሞት ስለተነሳው ሚኒሊክ ስለሚባለው የሰፈሩ ሰው ነው በዚህ ሰሞን ስለዚህ ተአምር የማያወራ ሰው በከተማዋ አለ ማለት ይከብዳል አንዳንዶቹ እንደውም ቢቢሲና ቪኦኤ ሁሉ መዝግበውታል ይላሉ ብዙ ሰዎች በዚህ ዞግ ስለ ፍካሬ ኢየሱስ መድረስ ያነበንባሉ ሚኒሊክ አንዳንዴ ብቻውን እየመጣ የሚስተናገድ የሻገር ደምበኛ እንደ ነበር ትጊ ስታወራ ሰምቷታል የጋዜጣው ሪፖርት በድጋሚ የሳበው የሆነ የቀረ ማንም ሊረዳው ያልቻለ ወይም በመጀመሪያ ንባቡ ያልደረሰበትን ትርጉም የሚያገኝ ስለመሰለው ነው የመጀመሪያ ገፅ ላይ በስተግራ ጥግ ወዳለው አምድ አይኖቹን ወረወረ የጋዜጣው ስም በትልቁ በማያምር ደብዛዛ ቀይ ቀለም ከወረቀቱ አናት ላይ አለ ። በወፍ እንደሚጠራ ነው የቹቹ ፀባይ ሙሉ በሙሉ ተመችቶት አያውቅም የደበሌ ችግር በሁሉ ነገር ውስጥ ፍቅር የመፈለግ ነው ስለፍቅር የመፈረም ነው የሚበላውን ሲያካፍል ካንጀቱ ነው የሚጠጣውን ሲያካፍል ከኩላሊቱ ነው የሰጡትን ሲቀበል በልቡ የፍቅር እንዲሆን ተመኝቶ ነው በዚህ በዚህ ብልቶቹ ነርኮቹና ልቡ ስራ አንደበዛባቸው ትዝ አይለውም ሆቴሉ በሰው ከሞላ ቹቹ ሁልጊዜ ሻገር የምትገባው በጀርባ ነው ቹቹ ለግላጋ ገላ ስር የሚረማመደው ደመነፍስ ሳይሆን ብልጠትና ፍቅር ነው ከነዚህ ከመንታዎቹ አንዱን አንጥራ ማውጣት ከብዲታል ከሁለት ሳምንታት ወዲህ ደበሌ ቹቹ ገላ ላይ ተነቃንቆ የሚደርስበት ደርሶ በጀርባው ሲገለበጥ እሷ ከአልጋ ተነስታ ውስጥ ሱሪዋን እየለበሰች ያላወለቀችውን አጭር ቀሚሷን ወደ ታች ስትጎትት ከተንጋለለበት አይኖቹን ጨፍኖ ወይም በውስጥ ሱሪ አልጋ ደርዝ ላይ ተቀምጦ መሬት ላይ እዛና እዛ የወደቀ የሶፍት ፔፐር ቁርጥራጮች ዘሩን የሰበሰበ ጎማ እያየ ለምን ባዶነት እንደተሰማው ለራሱ ማሰብ ጀምሯል እና አሁን ቹቹ ስትጠራው ሰምቷታል ደሞ አልሰማትም እጅግ በፍጥነት የዘነጋት ይመስላል ዞር ሲል ልብ ያለው ነገር በአይኖቹ ሙሉ ዕንባ መከተሩ ነው ከላይ አስከታች በቁመቱ ሙሉ በሚፋጅ ዕንባ የተሞላ መሰለው ፊቱን ከእሷ ዞር አድርጎ ዕንባው በነፋስ እስኪደርቅ ጥሪዋን ሳይመልስላት ቆሞ ጠበቃት ደህና አይደለህም። አለችው ከጀርባው አቅፋው እንደተደበረ ከአቋቋመሙና ከገፁ ስርአት ገብቷት ደህና ነኝ ግራና ቀኝ አይታደሞ ወደ ጀርባዋ አይታማጅራቱ ላይ ስርቆሽ ሳመችው ዞር ብሎ የሚንቀራፈፍ እጁን ወገቧ ላይ አስቀመጠ ቀይ ቢላቢሎ ቀሚሷ እንደ ጉም ዙሪዋን እየተርገበገበች የሰሊጥ ብጥብጥ የመሰሉ ጭኖቿ ጠቅላላ ነፋስ ስልክ ላይ አስማታቸውን እየቀለሙ ትጊን ጠየኩሁዋት እሁድ እረፍት ትሰትነሃለች በሚያፈዝ ኮልታፋ አንደበት ይሄን ብላው ፈገግ እያለች እሱ ብቻ እንዲሰማ ድምፅዋን ዝቅ አድርጋ ክፍሉ እንዲሄዱ ጠየቀችው ብዙ ስራ አለብኝ ለምን የማይሆን ጊዜ ብሎ አይኖቿን አተኩሮ አያቸው ካፖርቱ ደረት ኪስ ላይ ባለችው ጨርቅ እየተጫወተች ተገብክ አሁንስ አንድ ሚስትር አሳይሃለሁ አለችው እየሳቀች ቹቹ ለአልጋ ብቻ አይደለም የተፈጠረችው ቁሌታሞች እንደሚሉት እንደቀረፋ እንጨት ተሰባብራ ሻይ ቡናና ወጥ የምትሆን ናት የቹቹን ገላ ማንም እምቢ አይልም የነካው ካልሆነ ቹቹ ከደበሌ ከፍ አድርጋ የምትወደው ገንዘብ ብቻ ነው በዚህ ዘመን ያለ ገንዘብ ሕይወት የለም ለሚቀርቧት እንደምትለው ሀብት ቢኖራት ከደበሌ አትለይም ገንዘብ ከሚሰጧት ጋር ስትተኛ በልቧ ሁልጊዜ ደበሌ ነው አጠገቧ ደሞ ከሌለ ልክ እሱ መዋደድን እንዳበላሸ ሁሉ ጎርበጥባጣ ውስጥዋ ላይ ቅናት ይዘንባል እጁን እየጎተተችው እሱም እየተጎተተ ወደ መኝታ ቤቱ ገቡ በሩን መለሰችና ሹፍ የያኩትን ለማንም እንዳትናገል ምን።

  • N.B. This Summary is Very Experimental!! based on the following scripts from:
    • https://github.com/millzon/textSummarizer-am
    • https://github.com/icoxfog417/awesome-text-summarization#motivation
Download Searchable PDF Download PDF

Advertisement
Bottom banner

Download options | Convert to Pdf | Advertise on dirzon

© dirzon | Terms of Service | Privacy | About | Services | Contact