Detecting...

Please whitelist dirzon to continue.

or subscribe for ad-free contenct.

dirzon
  • Convert to Pdf
  • Reading List
  • Summary
  • Audiobook
  • Search
  • Upload
  • myzon
  • Log in
  • Register
English  አማርኛ  Français  العربية  Portuguese
Book of the day

የውል ህግ ሞጁል(Revised).pdf


Advertisement
  • word cloud

የውል ህግ ሞጁል(Revised).pdf
  • Extraction Summary

ወይስ ህጉ በወጣ ጊዜ እንዲህ ያሉትን ምዝገባ የማያከናውኑ ተቋማት ባልነበሩበት ጊዜ ስለሆነ በጊዜው የነበሩትን ውሎች ሁሉ ፍርስ የማድረግ ውጤት የለውም ውጤቱም ቢሆን በ ላይ አለመገለፁ ለዚህ ጠቋሚ ነው ማለት ምን ማለት ነው። ኤልያስ መጋቢት ቀን ዓም መመለስ አለበት በዚህ ጊዜ አልተከፈለም ከሳሽ ሌንጮ ዘገየ ዋናውን ገንዘብ እና መቀጫውን አቶ አብዱራህማን ይክፈለኝ በማለት ይጠይቃል ይችላል። ውል ያፈረሰ ውሉ ለፈረሰበት ወገን ብር ለመንግስት ብር የሚሉ ስምምነቶች ይደረጋሉ ተዋዋዩ ውሉን ያፈረሰ ቢሆን ለመንግስት ይከፍላል የተባለውን ብር እንዲከፍል ሊወሰንበት ይችላል። አቶ ማሞ ገብና ለአቶ ወርቅነህ በላቸው አንድ ላንድሮቨር መኪና በብር ሸጠዋል ተከፍሏል ቀሪው ብር ስላለተከፈለ ከነመቀጫው ብር እንዲከፍሉ ሲስማሙ አቶ በቃሉ ለቀርባባቸው ክስ መልስ ሲሰጡ ተራ ዋስ መከሰስ ያለበት መቼ ነው። ለምሳሌ ለአንድ የፍርድ ቦለዕዳ ዋስ የሆነ ሰው በፍርድ ቤት ቀርቦ ለመዋስ እንደሚፈልግ በዝርዝር ተነግሮት ይኸው በዝርዝር ከተመዘገበ በኃላ ባለዕዳው ዕዳውን ሳይከፍል ቢቀር ዋሱ በጽሁፍ አለመደገፉን መከራከሪያ ሊያደርገው ይችላል። በጽሁፍ ሆኖም ቢሆን እንኳ የገንዘቡ መጠን አልተገለፀም ወይም ሁለት ምስክሮች አልፈረሙለትም ብሎ ሊከራከር ይችላል።

  • Cosine Similarity

የዬደዬቤበ የጹትህ ከካሳት ባስበሙዎች ከሰጠካና ማስከበ ስቅደድመ ስራ ሰስጣሻኝች የተዘጋጀ የስፀጠናዛ ማኑዋስ በፌደራስ የፍትህ ስካሳት ባስሙያጠች ስስጠና ማከከስ የተዘጋደ መግቢያ ሰዎች በማህበራዊ ህይወት ውስጥ ሲኖሩ ያላቸውን ይሰጣሉ ያሌላቸውን ይቀበላሉ የሚበሉት የሚጠጡት የሚጓጓዙበት የሚያስደስታቸውን ነገር የሚያገኙበት ሁኔታ ሁሉ ምንጩ ከሰዎች ጋር የሚኖራቸው የሸቀጥ ልውውጥ ነው ታዲያ ሂደቱ አስተማማኝ እንዲሆን በንብረቶቻቸው ላይ ያሏቸው መብቶች ዋስትና እንዲያገኙ የልውውጡን ሥርዓት የሚገዛ ህግ ያስፈልጋልን ይህ ሲሆን ልወውጡ እርካታን ያስገኛል በፍርሃት ወይም በሥጋት የተነሳ የልውውጡ አድማስ ያልጠበበት ግንኙነት ይፈጠራል ማንም ሰው በቀላሉ ወደ ገበያ ይገባል ይወጣል ቀልጣፋና ውጤታማ የሆነ የንግድ ልውውጥ ይመሰረታል ማለት ነው በዚህ የተነሳም ልማት ይፋጠናል ህብረተሰቡም ያተርፋል የዚህ ሁሉ መሠረት በአግባቡ የተደራጀ በልውውጥ ሂደት የሚኖሩ ግንኙነቶች የሚመራ የውል ህግ መናሩ ነው ስለሆነም ህጉ ይህን ውጤት እንዲያስገኝ ታልሞ የተሠራ መሆኑን ማጤን ያስፈልጋል ትርጉም ባለው መንገድ ለማስፈፀምም መሠረቱ የቆመበትን የኢኮኖሚ አመክንዮት መረዳት ግድ ይላል አርግጥ የውል ህግ የኢኮኖሚ አመክንዮ ውጤት ብቻ ነው ማለት አይደለም ማህበራዊ ታሪካዊ ሞራላዊ አሴቶች ማራመጃ መሳሪያም ጭምር በመሆኑ የፅንሰ ሃሳቦቹን መነሻ ምን እንደሆን ማወቅ ተደራርበው በተገኙ ጊዜም በየጉዳዩ ልዩ ሁኔታ የትኛው የተሻለ ውጤት እንደሚያስገኝ መለየትን ይጠይቃል በዚህ እሳቤ መነሻነት መጠነኛ ሃሳብ ለማግኘት እንዲረዳ የዚህ ማኑዋል ሁለተኛ ምእራፍ የውል ህግ በህብረተሰቡ ውስጥ ያለውን ሚና ለማሳየት ይሞክራል አልፎ አልፎም በየቦታው ይኸው ፃሳብ ይንፀባረቃል በቂ አይደለም ጊዜ ወስዶ መስራት ይጠይቃል የሆነ ሆኖ ግን የዚህ ምአራፍ ዋና አላማ ህጉ በህግ ንድፈ ሃሳብ እና አመክንዮት ብቻ የታጠረ አለመሆኑን ለማሳየት ነው ከዚህ በኋላ ያሉት ምዕራፎች በውል ህግ ሊነሱ የሚገባቸውን ዝርዝር ነገሮች በተሟላ መንገድ የያዙ ሳይሆን ብዙ ጊዜ በፍርድ ቤት የሚያጋጥሙትን ውይይት ያስፈልጋቸዋል የተባሉትን ርዕሶች ብቻ የያዘ ነው በመልመጃዎች የተደገፈ ስለሆነ ሠልጣኞችን በሚገባው ደረጃ በማወያየት ወደ ስራ ሲሰማሩ በክህሎት ዝግጁ ያደርጋቸዋል የሚል እምነት አለን በምዕራፍ ሦስት ስለውል ማፍረስ አና መሠረዝ ውል እንዲፈርስ ለመጠየቅ መብት ስላለው ወገኖች እናያለን በምዕራፍ አራት ደግሞ ስለውል አለመፈፀም ደንብ እና ስለውጤቱ እንነጋገራለን በመጨረሻው ምዕራፍ ስለዋስትናዎች በአጠቃላይ እናያለን የንብረት ዋስትናን በተመለከተ ከዚህ ቀደም በተዘጋጀው የሥልጠና ማኑዋል ብዙ ጊዜ የማናስተውላቸው ድንጋጌዎች በየመልኩ ተዘጋጅተው የቀረቡበት ስለሆነ በዚህ የሥልጠና ማኑዋልም ባሉበት ሁኔታ እንዲካተቱ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን ምዕራፍ አንድ የውል ህግ መሠረታዊ ሃሳቦች አጠቃላይ ዓላማዎች ሠልጣኞች በዚህ ምዕራፍ ማብቂያ ላይ የውል ህግ በሰዎች ግንኙነት ውስጥ የሚጫወተውን ሚና ይለያሉ የውል ህግ መሠረታዊ ዕሳቤዎችን ይረዳሉ ዝርዝር ዓላማዎች ሠልጣኞች ሥልጠናውን ሲጨርሱ የውል ህግ በሰዎች ግንኙነት መፃል ሊኖር ኃላፊነትን የሚደለድል መሆኑን ይረዳሉ አስተተማማኘኝ የወደፊት ግንኙነት መመሥረቻ መሳሪያነቱን ይገነዘባሉ ከኢኮኖሚ ሥልጠት ጋር ያለውን ግንኙነት ይረዳሉ ኪሳራን የማሸጋገር ዓላማ ያለው መሆኑን ይረዳሉ የውል ህግ ተግባራት የተዋዋዮችን ግንኙነት ማደራጀት ከ ዐቪቨበቪዐበ ር ውል ማለት ንብረታቸውን የሚመለከቱ ተነፃዛሪ ግዴታዎችን ለማቋቋም ለመለወጥ ወይም ለማስቀረት ሁለት ወይም ከዚያ በላይ በሆኑ ሰዎች መካከል የሚደረግ ስምምነት ነው የፍብህቁ ስምምነቱ የሚቆመው በነፃ ፈቃድ ላይ ነው ይህ በሁሉም የህግ ስርዓቶች ያለ መሰረታዊ ሀሳብ ነው በነፃ ፈቃድ የመሠረቱት ውል ሊከበርን ይገባል ብለው ባሰቡት መንገድ የሚፈልጉትን ቁምነገር እንዲያካትት አድርገው ይቀርጹታል ይህም በተዋዋዮች መካከል ዕርካታን ያመጣል ተብሎ ይታሰባል ይሁንና የሰው ልጅ ውሱንነት ዘገዘ ልከበከ ያለበት በመሆኑ የህይወት አጋጣሚዎች በስምምነታቸው ላይ ሊያስከትሉ የሚችሉትን ተፅፅኖ አስቀድሞ ለማየት ከመቸገር ክፍተቶቸ ሊፈጠሩ ይችላሉ ውሉ ምሉዕነት ይጎድለዋል በዚህ ጊዜ ማን ምን ማድረግ አለበት የሚለው ጉዳይ በተዋዋዮች መካከል ውዝግብ ሊፈጥር ይችላል በመተማመን ላይ የሚመሠረቱ ግንኙነቶችን ይጎዳል ዳፋውም ተከታታይ የሆኑ የንግድ ትስስሮችን ያበላሻል የልውውጥ ሄደትን ይጎዳል ማለት ነው የውል ህግ መኖር አስፈላጊነት የሚመጣው እዚህ ላይ ነው ተዋዋዮች ሳይገልዷቸው ያለፏቸው ነገር ግን ግንኙነታቸውን የሚጎዱ ነገሮች ሲኖሩ ህጉ በነርሱ ዝምታ ውስጥ የታለፈውን ጉዳይ ለመሸፈን ይመጣል ሀዚ ቪ ይባላሉ ከተዋዋዮቹ ውስጥ ማን ምን እንደሚጠበቅበት በመግለጽ አያንዳንዳቸው በውሉ ውስጥ የሚኖራቸውን ሚና ያጠራል ነገሩ እንዴት መፈጸም አንዳለበት በዝርዝር በማስፈር አንዱ ወገን በውሉ ዝምታ ምክንያት ተገቢ ያልሆነ ጥቅም እንዳያገኝ ይገታል በተዋዋዮች መካከል የሚኖረውን ትርምስ ያስቀራል ወንድማማችነት ይፈጠራል ግንኙነታቸውንም መልክ በማስያዝ ልውውጦችን ቀና ያደርጋል በሌላ አገላላጽ ለጋራ ጥቅም ኃላፊነትን በመደልደል በተዋዋዮች መካከል ሊኖር የሚገባውን ግንኙነት ያደራጃል ያቀናጃል ማለት ነው ደግምም ሀህዚ ቪዉን በመተማመን በያንዳንዱ የግንኙነቶቻቸው ሄደት ውስጥ ምን ማድረግ እንዳለባቸው እየተጨነቁ ሳያስቡ ግንኙነቶቻቸውን እንዲመሩ ይረዳል አፈፃፃማቸው ጊዜ የሚጠይቅ ስምምነቶችን አስተማማኝ ማድረግ ውሎች በአብዛኛው የሚፈፀሙት እጅ በእጅ በ ከ በሚደረግ ልውውጥ ሲሆን የትኛውም ወገን ከስምምነቱ አገኛለሁ የሚለውን ጥቅም ስምምነቱ እንደተፈፀመ ያገኛል ውሉ የሚመሰረተውም የሚፈፀመውም አዚያው ላይ በመሆኑ በለውጡ የሚያገኘው የሚፈልገውን አንደሆነ ይታሰባል በየዕለቱ የሚታዩትን ልውውጦች ያህል ውዝግብ አለመኖሩ የሚያሳየውም ይህንኑ ነው ይሁንና በገዘዛዱ ዓለም ስምምነቶች ሁሉ እጅ በእጅ የሚከናወኑ ናቸው ማለት አይቻልም አፈፃፃማቸው በጊዜ ሂደት የሚከናወን ስምምነቶችም አሉ በውሉ አመሰራረትና በአፈጻጸሙ መዛል የጊዜ ክፍተት ሲኖር ተዋዋዮች እንደስምምነቱ ቃላቸውን የሚያከብሩ ስለመሆኑ እርግጠኛ መሆን ያስቸግራል መተማመን ይጎድለናል አናም እንዲህ ያሉ ስምምነቶች ውስጥ ለመግባት አእናመነታለን ብንገባም እንኳ ሊደርስ የሚችለውን ኪሳራ በማሰብ ስምምነቶቻችንን ከምናውቃቸው እና ከምንተማመንባቸው ሰዎች ጋር ብቻ እንዲሆን እንፈልጋለን የልውውጡ አድማስ ይጠባል ማለት ነው ይህ የሸቀጦችን ዋጋ ያንራል በመደበኛ ሂደት የሚኖረውን የልውውጥ ወጪ ከፍ ያደርጋል የውል ህግ መኖር ይህ እንዳይሆን ይጠብቃል ሰው በቃሉ ይታሰራል ሠቋሪ ሀህ «ጋዐ የፍብህቁ የሚለው ጽንሰ ሃሳብ መሠረትም በፈቃድ የገቡትን ግዴታ ተዋዋዮች እንዲያከብሩ በማድረግ የሞራል ግዴታ ይጥልባቸዋል አንዱ ተዋዋይ በሌላው ላይ ያደረሰውን ጉዳት እንዲክስ የፍብህቁ እና በመደንገግም ጉዳት ሊደርስበት የሚችል ተዋዋይ ቢኖር እንዳይሰጋ ያደርጋል ጥበቃው በውሎች ላይ ሊኖር የሚችለውን መተማመን ይጨምራል ይህ ባይሆን ኖሮ ማንም ሰው ያለውን ለሌላው አሳልፎ ይሰጣል ብሎ ማሰብ ይከብዳል አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ጥቅሞቻችን በሁኔታዎች ላይ የተመሰረቱ ይሆኑና ልናገኝ የምንፈልገው ነገር ከአንድ ክስተት በፊት ወይ በኃላ የመምጣቱ ነገር ውል ለማድረግ በሚኖረን ውሳኔ ላይ የራሱ የሆነ ተጽዕኖ ይኖረዋል በምሳሌ ለመግለጽ ያህል አንድ አደጋ ከተከሰተ በኃላ ንብረቱ የወደመበት ሰው አረቦን ሀጠ ህጠ ልክፈልህ እና በንብረቴ ላይ የደረውን ጉዳት ጠግንልኝ በማለት አንድን የኢንሹራንስ ኩባንያ ቢጠይቅ ኩባንያው ፈቃደኛ አይሆንም በተመሳሳይ ሁኔታም ጉዳት ከመድረሱ በፊት የንብረቱ ባለቤት የሆነ ሰው አረቦን ዌጠክህጠ የመክፈል ዝንባሌ አይኖረውም ወይም አነስተኛ ነው እንዲህ ያለውን ልውውጥ በእጅ ለእጅ ገበያ ውስጥ ማግኘት አይቻልም አስቀድሞ የሚደረጉ የቃል መግባቶችን የሚጠይቁ ናቸው ታዲያ ህጉ ይህን እና መሰል ስምምነቶች እንዴት መመስረትና መመራት እንዳለባቸው ሥርዓት በማበጀት ልውውጡን ቀና ያደርጋል ስለሆነም በአንድ ውል መመስረት እና በአፈፃፀሙ መፃል ያለው የጊዜ መስፋት ስለ አፈፃፀሙ ያለንን ዕምነት ሳይሸረሽር ወደፊት ሊኖረን የሚገባውን ግንኙነትም ከወዲሁ ለማዘጋጀት የሚያስችል ማዕቀፍ በማዘጋጀት ልውውጦችን ቀና እና አስተማማኝ ያደርጋል ማለት ይቻላል ስምምነቶች የሚኖራቸውን ጉድለት መሙላት በህግ ክልከላ የተደረገበት ካልሆነ በቀር ውል ያቋቋሟቸው ወገኖች ስምምነታቸውን በፈቀዱት መንገድ ለመፈጸም ቃል የሚገቡበት ሰነድ ነው በዚህ ስምምነት ተዋዋዮች ምን ሰጥተው ምን መቀበል እንደለባቸው ያውቃሉ መቼ እና እንዴት ማከናወን እንዳለባቸውም በዝርዝር በመግለጽ ይስማማሉ ሆኖም ስምምነታቸው በሚከሉት ምክንያቶች ምሉዕ ላይሆን ይችላል ሯ ያፉሥዎዎዎቻ ውታኑታፉ ተዋዋዮች በአንድ ጉዳይ ሊደራደሩ ይችላሉ ሲስማሙ ውዝግብ ቢነሳ እንኳ ማንም ሰው ሊረዳቸው በሚችል መንገድ የተስማሙባቸውን ነጥቦች በግልጽ እና በዝርዝር ለመቅረጽ ይጥራሉ ነገር ግን ሰዎች ውሱን አፅምሮ ያለቸው በመሆኑ በጊዜ ሂደት የህይወት ውጣ ውረድ በልሸሀ በግንኙነታቸው ውስጥ ሊፈጥር የሚችለውን ተፅዕኖ አስተማማኝ በሆነ መንገድ ሊያውቁ አይችሉም ወይም ለማወቅ ይቸገራሉ ስለሆነም በግንኙነታቸው ሚዛን ላይ ጊዜ የሚፈጥረውን ተፅዕኖ አለማወቃቸው ውሉ ምሉዕነት እንዲጎድለው ምክንያት ይሆናል ሐ ቋፈሂገጀ መያፖያ ቦዖጃዉጨፀፇው ዎ ሰዎች ሊኖራቸው የሚችለውን የውል ግንኙነት ምን መምሰል እንዳለበት እስከ ፍፃሜው ድረስ አስቀድሞ በማየት የተሳካላቸው ሊሆኑ ይችላሉ ነገር ግን ዋና ከሚባሉ ጉዳዮች አልፈው የታዩዋቸውን ጥቃቅን ዝርዝሮች ሁሉ መፃፍና መስማማት ላይፈልጉ ይችላሉ በመጀመሪያ ደረጃ ጥቃቅን ዝርዝር ላይ የሚደረገው አለመስማማት ዋና እና መሰረታዊ ነው የተባለውን ጉዳይ ሊያደፈርስ ይችላል በሁለተኛ ደረጃም በእያንዳንዱ ጥቃቅን ዝርዝር ላይ ለመነጋገር መጨነቅ የራሱን ጊዜ የሚወስድና ወጪንም የሚጠይቅ ዛደት በመሆኑ ነው ስለሆነም ተዋዋዮች በ ሀዚ ቢ በመተማመን ዋና ነገሮች ላይ ብቻ በማተኮር ዝርዝሩን ሊተውት ይችላሉ ጨሑ ውሳ ታሳ ፈጸም ያሟቻሳ መሆት ማረጋም ለሪመፖጳ በብዙ አጋጣሚዎች ስምምነቶች እንደተዋዋዮች ፈቃድ መፈጸማቸውን ማረጋገጥ ይቻል ይሆናል አንዳንድ ጊዜ ግን እርግጠኛ ለመሆን አይቻልም እጅ በአጅ በሚደረግ ልውውጥ ውስጥ እንኳ ይህን መተማመን ለማግኘት ያስቸግራል አንድን ምርት በግዢ የተቀበለ ሰው የተረከበው ምርት ጥራት አሰራር በውሉ ላይ በሰፈረው ዓይነት ስለመሆኑ በርክክቡ ጊዜ ለመረዳት ይከብደው ይሆናል ተፈላጊው ማሽን ለተፈለገበት ዓለማ የተገባ መሆኑን ለማወቅ በዕጃችን ከገባ በኋላ ሥራ ላይ ስናውለው ችግር መፍጠሩን እስክናይ የተረከብነው በስምምነቱ መሰረት እንደሆነ ልናስብ እንችላለን በተመሳሳይ ሁኔታም የተረከብነው የስንዴ ዱቄት ጊዜው ያለፈበት የተበላሽ መሆኑን የምንረዳው በርክክቡ ጊዜ ሳይሆን ከርክክቡ በኃላ ስናቦከውም ሆነ ስንጋግረው ከደንበኛው ዱቄት የምንጠብቀውን ውጤት ያልሰጠን መሆኑን ስናይ ነው እንደውሉ ያልተፈፀመልን መሆኑን የምንረዳው ታዲያ ውሉ በሚመሰረትበት ጊዜ እንዲህ ያሉትን ሁኔታዎች ቀድመን ለማወቅ አእንቸገራለን ምክንያቱም በዚያን ጊዜ በነገሩ ላይ ያለን ዕውቀት ዝቅተኛ መሆን ወይም በጊዜው ዝርዝር ነገሮችን ማረጋገጥ ውስብስብነት ያለው ጊዜና ወጪን የሚጠይቅ መሆኑ በዝርዝሩ ላይ በርግጠኝነት ለመደራደር እንዳንችል ያደርገናል ስለዚህም መሠረታዊ በሆኑት ላይ ብቻ በማተኮር ቀሪዎችን ዝርዝሮች እናልፋለን አንዱ ተዋዋይ አውቆት ቢሆን እንኳ ፍርድ ቤቶች በጉዳዩ ላይ ያላቸውን የፅውቀት ውሱንነት በመገመት በዕኩይ መንፈስ ነገሩ ሳይነሳ እንዲያልፍ መፈለግም ሌላው ለዝርዝር ነገሮች መታለፍ አንድ ምክንያት ሊሆን የሚችል ነው በአጠቃላይ ሲታይ አንድ ውል በየትኛውም ምክንያት ቢሆን ምሉዕነት ላይኖረው ይችላል በዚህ ጊዜ ህጉ ተዋዋዮች በውሉ ጊዜ የነበራቸውን ሀሳብ ምን እንደነበር ለማወቅ ዳኛው ጥረት ማድረግ አንዳለበት ያዛል ይህን ለማድረግ የተዋዋዮች ግንኙነት ምን እንደነበር በውሉ አፈፃፀም ሂደት የነበራቸው ሚና መለየት ፍትህ እና የኢኮኖሚ ሥልጠት እንዲሁም ሌሎችንም ምክንያታዊ የሆኑት ነገሮችን የሚጠይቁትን ሁሉ ከግምት ውስጥ በማስገባት መመርመር የሚጠይቅ ይሆናል ማለት ነው የሆኖ ሆኖ ህጉ የአተረጓጎም ሥርዓቶችን በማበጀት ክፍተቱን የውሉን ጉድለት ይሞላል የውል ህግ አወቃቀር ከከ ዐበከ ዕየ ዕዐበከጧር። ዉህ የኢኮኖሚ ስልጠትን መፍጠር ቀደም ሲል እንደተገለጸው ውል ንብረቶቻቸውን የተመለከቱ ግዴታዎችን ለማቋቋም ለመለወጥ ወይም ለማስቀረት ባላቸው ተወዳዳሪ ግንኙነት የተነሳ ሰዎች በመካከላቸው የሚመሰረቱት ስምምነት ነው ብለናል የግንኙነታቸው መሰረት ንብረት ነው ወጪን ያንራል በገበያ ላይ ያለን መተማመን ያጎድላልና ሰዎች ንብረቶቻቸው ከአንዱ ወደ ሌላው ሲያሳልፉ የልውውጡ ፍሰት እንዲታጎል አይፈልጉም ይህ የተዋዋዮች ብቻ ሳይሆን የጠቅላላው ሕዝብ ፍላጎትም ጭምር ነው ይህ እንዲሆን ታዲያ የውል ህግ የገበያው ተሳታፊዎች ሊኖራቸው የሚገባው ጠባይ ምን መሆን እንዴት መመራት እንዳለበት ደንብና ሥርዓት በማበጀት የልውውጡ ሂደት መተማመን ያለበት ጊዜና ወጪን የሚቆጥብ የሰዎችን ዕርከታ የሚያስገኝ እንዲሆን ተደርጎ ይዋቀራል ስለሆነም የውል ህግ በሰዎች መካከል ያለውን ቀና የሆነ የኢኮኖሚ ግንኙነት የሚገዛ መሳሪያ ነው ቢባል ስህተት አይሆንም ነገሩን ለማብራራት ያህል ስልጠት ከሰዎች ርካታ አንጻር ሊገለጽ ይችላል አንድ መጽሀፍ የገዛ ሰው ለገዛው መጽሀፍ የከፈለው ዋጋ መጽሀፉ ለርሱ ከሚሰጠው ጠቀሜታ አንጻር ሲታይ ጥሩ ነው ማለት ይቻላል አነስተኛ ዋጋ ሊሰጠው የሚችል ሌላ ሰው አለ ተብሎ አይታሰብም ቢታሰብም ራሱን የቻለ የጊዜና የገንዘብ ወጪ ሳይጠይቅ የሚፈፀም አይሆንም በሌላ በኩል ደግሞ መጽሀፉን የሸጠው ሰው በበኩሉ ስለመጽሀፍ ሽያጭ የተቀበለው ዋጋ ዕርካታን ይሰጠዋል በተመሳሳይ ዋጋ መጽሀፍን የሚገዛው ሰው ባለመኖሩ ከሽያጩ ደስታን አትርፏል እንዲህ ሲሆን ሸቀጦች ሀህር ከፍ ያለ ተጠቃሚነት ወደሚያገኙት ሰዎች ተሸጋግሯል ማለት ይቻላል ስልጠት ማለትም ሀብቶችን ለሰዎች ከፍተኛ ዕርካታን በሚያስገኝ በዚህ ዓይነት መንገድ መጠቀም ማለት ነው ህጉ ይህንን እንዲያበረታታ ተደርጎ የተቀረጸ ነው ሰው በቃሉ ይታሰራል የሚለውን መርህም አንዱ የዚህ ማስፈጸሚያ መሳሪያ አድርጎ መውሰድ ይቻላል በአንዛሩ አንድን ሸቀጥ በማታለል ወይ በኃይል ያገኘ ሰው ቢኖር በዚህ መንገድ የተደረገው ልውውጥ የኢኮኖሚ ስልጠትን የሚያስገኝ አይሆንም ምክንያቱም አንዱ ወገን መረጃን በሞኖፖል መያዝ ብቻ ሳይሆን መረጃን በማሳሳት ወይም ደግሞ ከተዋዋዮቹ ውስጥ የአንዱ የመደራደር አቅም በማይገባ ሁኔታ በከፍተኛ ደረጃ ላይ መገኘቱ መተማመንን በማጉደል የገበያ ውድቀትን የሚያስከትል በመሆኑ ነው በግለሰብም ሆነ በህብረተሰብ ደረጃ ሁኔታውን ለመቆጣጠር ከፍ ያለ ወጪን ይጠይቃል እናም የኢኮኖሚ ስልጠትን አይፈጥሩም ህጉ ይህን አያበረታታም መገደድ አና ማታለልን የማይደግፉ ህጎች የተቀረጹትም እንዲህ ያሉ የኢኮኖሚ ስልጠት የማይፈጥሩ ጠባያትና ሁኔታዎችን በመቆጠጠር ተፈላጊውን ስልጠት ለማስገኘት ሲባል ነው ስለሆነም ህጉ ብቸኛው ባይሆንም አንድ የኢኮኖሚ ስልጠትን የሚያስገኝ መሳሪያ ተደርጎ ሊወሰድ ይቻላል ማለት ነው ኪሣራን ማሸጋገር ሸቀጦች በጊዜ ሂደት የዋጋ ልዩነት ሊኖራቸው ይችላል ይህ ፍርሀትን ይፈጥራል በዚህ የተነሳ ሰዎች በመጪው ጊዜ በሚኖረው የዋጋ ልዩነት ተጎጂ እንዳይሆኑ ከወዲሁ ስምምነት በማድረግ የወደፊቱን ዋጋ ዛሬ ላይ ለማሰር ይገፋፋሉ ሱራፌል በመጪው ሰኔ በብር አንድ ኩንታል ስንዴ ሊያስረክበኝ ቃል ባይገባ ኖሮ ሰኔ ሲደርስ በብር ለመግዛት እሱም ቢሆን ዋጋው ሲወርድ በወረደው በብር ዋጋ ስንዴውን አንደቅደም ተከተላችን ለመግዛትና ለመሸጥ እንገደድ ነበር ስምምነት ከተደረገበት ዋጋ አንፃር የወጣውን ወይም የወረደውን ዋጋ ልዩነት ስናይ የልዩነቱ መጠን በአንዳንችን ላይ ሊደርስ ይችል የነበረው በስምምነት አንዳችን በሌላችን ላይ ያስተላለፍነው ኪሳራ ነው በመሰረቱ ማንኛውም ሰው በሚፈፅመው ውል ላይ ይህን አገላለጽ ቃል በቃል ላያገኘው ይችላል ይሁንና የስምምነቱ ይዘት በጥልቀት ሲመረመር የሚያሳየው ይህንኑ ነው ታዲያ የተደረገውን ስምምነት የሚያስፈጽም የውል ህግ ባይኖር መጪውን ጊዜ ባየነው መጠን የሚደርሰውን ኪሳራ ለማስተላለፍ ባልተቻለን ነበር አሁን ግን ተዋዋዩ በስምምነታችን መሰረት ስንዴውን ሊያቀርብልኝ ይገደዳል በርክክቡ ጊዜ ባለው ዋጋ መሸጡ የበለጠ ሊያተርፈው ቢችል እንኳ የውሉን ግዴታ ከመፈጸም ሊሸሽ አይችልም መሸሽ ቢችልም በርክክቡ ጊዜ ስንዴ ለመግዛት የምገደድበትን የኪሳራ ገንዘብ እንዲተካ ይገደዳል ህጉ ይህን ዓይነት ግንኙነት እንዲያበረታታ ሆኖ የተቀረጸ ነው ይህ ብቻም አይደለም ተዋዋዮች በስምምነታቸው ላይ ሳያሰፍሩት በቀሩ ጊዜ እንኳ ህጉ ለውሉ አለመፈፀም ምክንያት የሆነውን ችግር በተሻለ ሁኔታ ለመቆጣጠር ማን ይችል እንደነበር ከግምት ውስጥ በማስገባት ኪሳራን ያሸጋግራል ማህባራዊ ፍትህ እና ርትዕን ማስፈን አስከሁን ያነሳናቸው በአብዛኛው ከኢኮኖሚ ጋር የተያያዙ ናቸው ይህ ማለት ግን ውል በኢኮኖሚክ አመክንዮ ብቻ የተተበተበ ነው ማለት አይደለም በውል ስምምነት ውስጥ እንዲኖር የሚፈላገውን ነፃነት ከተጠያቂነት ጋር አጣጥሞ በማየትም ማህበራዊ ፍትህን የሚያሰፍን መሳሪያ ጭምር ተደርጎ ሊታይ ይችላል ለምሳሌ የተዋዋዮች ስምምነት በነፃ ፈቃዳቸው ላይ የተመሰረተ መሆን ይገባዋል አንዱ ወገን የሌላውን ፈቃድ ያገኘው በማስገደድ እንደሆነ እንዲህ ያለውን አጉል ጠባይ በመቆጣጠር አቅም የሌላቸውን ሰዎች ጥቅም ይጠብቃል እናም ማኅበራዊ ፍትህን ያሰፍናል ርትዓዊ ከመሆን አንጻርም አንዳንድ ግንኙነቶች የሚፈጥራቸውን ውጤቶች ከማኅበራዊው አኗኗር መለኪያ አንፃር እየታየ እንዲመዘን የሚፈቅድም ነው ውጤቶቹ ፍትሀዊ መስለው በማይታዩ ጊዜ በተለያዩ ቦታዎች ዳኞች በርትዕ እንዲወሰኑ ህጉ መብት የሚሰጣቸውም በዚህ መነሻ ነው ህጉ ስለ መጎዳት ሀበርበርበቨክ እና ስለ ቅን ልቡና የሚያነሳውም ከዚሁ የርትዕ ጉዳይ ጋር የተያያዘ መሆኑን ማጤን ይገባል ምዕራፍ ሁለት ውል ማፍረስመሠረዝ የሥልጠናው ዓላማ ሠልጣኞች ከሥልጠናው መጠናቀቅ በላ የውል ማፍረስ ወይም መሠረዝ የኢኮኖሚክ አመክንዮቱን ይገነዘባሉ በሞራል ዕሴቶች ማራመጃ መሆኑን ይረዳሉ ከማህበራዊ ፍትህ ጋር ያለውን ግንኙነት ይረዳሉ ውል እንዲፈርስ ለመጠየቅ መብት ያለውን ወገን ይለያሉ የውል መፍረስ ውጠየትን ይገነዘባሉ ውል የሚፈርስባቸው ሁኔታዎች ህግ የሚጠይቀውን ሥርዓት ተከትሎ የተሰራ ውል በህግ ፊት ሊፈጸም የሚችል ነው የተዋዋዮችን ጥቅም የሚያስጠብቅ ዕርካታን የሚያስገኝላቸው በመሆኑ እንደስምምነታቸው እንዲፈጸም የህጉ ፍላጎት ነው ይሁንና ህጉ እንዲኖር የሚፈልገውን ወይም የሚጠይቀውን ሁኔታ የሚያሟላ ሳይሆን የገበያ ውድቀትን ዘበልዘ ቧህጩ ሊያመጣ የሚችል በመሆኑ ፍርስ ይሆናል ወይም እንዲፈርስ ይደረጋል ይህ አይነቱን ችግር ያስከትላሉ የሚባሉት የሚከተሉት ሁኔታዎች ናቸው የፈቃድ ጉድለት ውል ተነፃፃሪ ግዴታዎቻቸውን ተረድተው ጥቅሞቻቸውን ለማስከበር በሚችሉ ሰዎች መካከል የተፈጸመ መሆን አለበት አንዳንድ ሰዎች በዕድሜ ማነስ በመጃጀት ወይም በአዕምሮ ጤንነት ጉድለት ምክንያት ጥቅሞቻቸውን ተገቢ በሆነ መንገድ ከከሄ ለማስጠበቅ ይችላሉ ተብሎ አይታሰብም ይህ ህጉ የሚፈልገውን የጋራ ጥቅም የሚያስገኝ አይሆንም እነሂህ ጥበቃ የሚያስፈልጋቸው ለአደጋ የተጋለጡ ክፍሎች ስለሆኑ ህጉ ከለላ ይሰጣቸዋል ስለሆነም የፈፀሙት ውል እንዲፈርስ ይደረጋል ይህን ማድረግ የሚችለውም በውሉ ተጎድቻለሁ የሚለው ወገን ብቻ ነው ችሎታ ማጣቱን መከላከያ ሊያደርገው የፈለገ እንደሁ ውሉ በተደረገ ጊዜ ችሉታ እንደልነበረው ማስረዳት ይጠበቅበታል ምክንያቱም ህጉ ማንኛውም ሰው ችሎታ አለው የሚል ግምት የሚወስድ በመሆኑ ፍርስ ከመሆን ይልቅ ፈራሽ እንዲሆን የተደረገው ጠቃሚ የሆኑ የኢኮኖሚ ልውውጦች በየሰበቡ እንዳይታጎሉ ለማድረግ ነው በተመሳሳይ ሁኔታም ህጉ መሰረታዊ ነው ብሎ የሚጠይቀው የነፃ ፈቃድ መኖር ለአንድ ውል ህልውና ወሳኝ ጉዳይ ነው በነፃ ፈቃድ ላይ ያልተመሰረተ ስምምነት የጋራ የሆነ የኢኮኖሚ ጥቅምን ፀዕዐበበዝር ህፀሸ ዋጋ የሚቀንስ ነው ስለሆነም ህጉ በነዓ ፈቃድ ላይ ያልተመሰረተ ስምምነትን አያበረታታም ቀደም ሲል በነበረው ክፍል እንደተገለጸውም አስተማማኝነትን የሚያጎድል በግለሰብም ሆነ በህብረተሰብ ደረጃ የሚኖረውን ትርምስ ለመቆጣጠር ከፍ ያለ ወጪን የሚጠይቅ በመሆኑ ተፈላጊውን ስልጠት አያስገኝም ስለሆነም በፈቃዱ ጉድለት የተደረገውን ስምምነት እንዲፈርስለት ተጎጂው እንዲጠይቅ ህጉ እድል ይሰጠዋል ለአንድ ተወዳዳሪ ገበያ ርክዐፀከቨፀ ዘበጺቨ መኖር አስፈላጊ ነው የሚባለው በቂ መረጃ ነው በቂ መረጃ በሌለበት ሁኔታ የገበያው ተሳታፊዎች በሂደቱ ደስታን በሚያስገኝላቸው መንገድ የጋራ ጥቅማቸውን ያስከብራሉ ተብሎ አይታሰብም ስለሆነም ህጉ ቀና የሆነ የገበያ ውድድርን ለመጠበቅ ሲል በቂ መረጃ እንዳይኖር ዕንቅፋት የሚፈጥረውን አጋጣሚ አያበረታታም ስለዚህም በስህተት በተንኮል እና በመጎዳት ሀበርዐበርበከ የሚደረጉ ስምምነቶች ሲኖሩ ተዋዋዩ ውሉን እንዲያፈርስ ዕድል ይሰጣል ከህግ ውጪ ለሞራል ተቃራኒ መሆን እና ለውሉ አፃዛፍ የተደነገገውን ስርዓት ያልተከተለ መሆን ፉራ ህሀ ወጩ ና ምራጳሳ ፖቃራኒ መያፖፇ ማንኛውም ውል የህብረተሰቡን ጠቅላላ ጥቅም ለመጠበቅ በተዘጋጀው የህግ ማዕቀፍ ውስጥ እንዲከናወን ይፈለጋል ማኅበራዊ ህጉን ሀ ጪለ ፖሊሲዎችን በሚቃረን መንገድ የተፈጸመ እንደሆነ ዕውቅና አያገኝም ይህን መጣስ ተፈላጊውን ማህበራዊ ፍትህ አያስገኝም ስለሆነም አይበረታታም ይህ ብቻም አይደለም ህብረተሰቡን ከሚያስተሳስሩት ማህበራዊ ዕሴቶች ውስጥ አንዱ የኔ ናቸው ሊጠበቁልኝ ይገባል የሚላቸውን የሞራል ዋጋዎች ጠዐ ሄህሀ መጠበቅ አንዱ የህጉ ዓለማም ነው ስለሆነም እነሺህን ሁኔታዎች ከግምት ውስጥ ያላስገባ ስምምነት ፅውቅና አይሰጠውም ፍርስ እንደሆንም ይታሰባል ሐ ሀታ ዖያሟጨመይፇው ያይላፃሃጀ ሥሂንዖ ሥታሥ ዖያሥፅራ ለሪመያቻ ውሎች በተዋዋዮች ፈቃድ ላይ የተመሰረቱ መሆን አለባቸው እንዴት እና በምን ዓይነት ሁኔታ መዋዋል እንደሚፈልጉ የሚወስነት አነሱው ናቸው ህግ ጣልቃ አይገባም ይሁንና የህብረተሰቡን ጠቅላላ ጥቅም ከማስጠበቅ አንጻር የተወሰኑ ገደቦች ይጣሉባቸዋል አንዱ ህጉ ወሳኝና አስፈላጊ ናቸው በሚላቸው የውል ዓይነቶች ላይ ተዋዋዮች ሊከተሉ የሚገባውን የአፃፃፍ ሥርዓት የሚመለከት ነው የተለየ የአፃፃፍ ሥርዓት እነዲከተሉ በህግ የታዘዘ በሆነ ጊዜ የህጉ ቃል መከበር አለበት ሐ ይህ ማለት ህጉ በመርህ ደረጃ በፈቃድ ላይ የተመሰረተ ከመሆን አልፎ ፎርምን በመርህ ደረጃ አይጠይቅም ማለት ነው ስምምነቶች አንድ ዓይነት የአፃፃፍ ሥርዓትን እንዲከተሉ የሚፈለግበት ምክንያት ህጉ ዋና ናቸው በሚላቸው ጉዳዮች ላይ የተዋዋዮቹን ጥቅም አስተማማኝ በሆነ መንገድ ለመጠበቅ ታስቦ ነው ለምሳሌ አንድ ውል በጽሁፍ እንዲሆን መታዘዙ የውሉን ይዘት ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት ያቀላል በዚህ ረገድ ሊኖር የሚችለውን ውዝግብም ይቀንሳል በዚህ የተነሳም የሰዎችን የውል ግንኙነት ውጤታማ በሆነ መንገድ መምራት ይቻላል ማለት ነው ኢኮኖሚያዊ በሆነ አስተሳሰብም ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጊዜ ወጪ አና ድካምን በመቀነስ ስልጠትን የሚፈጥር ነው ተዋዋዮች በችኮላ ቃል ከመግባታቸውና ይህም በነርሱ ላይ አስገዳጅ ከመሆኑ በፊት በጉዳዩ ላይ እንዲያስቡበት የአፍታ ጊዜ እንዲያገኙ ፀጩርሀከበቫ ማድረግ ነው ደካማውን ተዋዋይ ወገን ለመጠበቅም ይረዳል ሌለው ወገን ማስረጃው እንዲደርሰው በመጠየቅ የመደራደር አቅም የሌለውን ተዋዋይ ጥቅም ያስጠብቃል ሀፀርክከህ በዕቨዐበ በአሠሪና ሠራተኛ ህግ ላይ አሠሪው ለሠራተኛው መቀጠሩን በጽሁፍ እንዲያሳውቀው እንደሚያዘው ማለት ነው ታዲያ በነፒህ መሰረቶች ላይ የቆመውን ዓለማ ለማሳካት ውሉ ውጤት እንዲኖረው ከመደረጉ በፊት የተጠየቀውን ሥርዓት ማሟለቱን ማረጋገጥ ይጠይቃል ከተዋዋዮች እንዲነሳ ሳይጠበቅ ፍርድ ቤቱ ሊያነሳው የሚችለው ጉዳይ ነው የህጉን ዓላማ ለማስፈፀም ከፍርድ ቤቶች የተሸለ ዕድል ያለው የለም ስለሆነም ፍርድ ቤቶች በዚህ ረገድ ንቁ መሆን ይገባቸዋል ውል እንዲፈርስ ለመጠየቅ መብት ስላለው ሰው ስለሚጠየቅበት ጊዜ እና ስለውል መፍረስ ውጤት ውል እንዲፈርስ ለመጠየቅ መብት ስላለው ሰው እና ስለሚጠየቅበት ጊዜ ለአንድ ውል ውጤት ማግኘት የሚያስፈልጉት ሁኔታዎች የተሟሉ እንደሆነ ይፈፀማሉ የተጓደሉ አንደሆነ ግን ውሉ እንዲፈርስ ይደረጋል ጥያቄውን ለማቅረብ የሚችለውም በፈቃዱ ጉድለት ወይም በችሎታው ማጣት ሰበብ በውሉ የተጎዳው ወገን ብቻ ነው ሌላ ሰው ጥቅም ኖሮት ቢሆን እንኳ ለመጠየቅ አይፈቀድም ውሉ ከህግ ውጪ ነው ለህሊና ይቃረናል ወይም የተደነገገውን የአፃፃፍ ሥርዓት አልተከተለም በሚል ውሉ እንዲፈርስ ለመጠየቅ ሥልጣን የተሰጠው ግን ለተዋዋዮችና በጉዳዩ ላይ ጥቅም አለኝ ለሚል ማንኛውም ሰው ነው ይህ ልዩነት የኋለኞቹ ምክንያቶች ጉዳቱ ከተዋዋዮች ማሕበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ደህንነትም በላይ ጠቅላላውን ህዝብ የበለጠ የሚጎዱ ቀውስን የሚፈጥሩ ናቸው በሚል ትኩረት የተደረገባቸው መሆኑን የሚጠቁም ነው ከዚህ በተረፈ ጥያቄዎቹ የሚቀርቡበት ሁኔታ በጊዜ የተገደበ ስለመሆኑ ከፍብህቁ መረዳት ይቻላል ውል የማይረጋበት ምክንያት ከቀረበት ጊዜ ጀምሮ በሁለት አመት ውስጥ ውል እንዲፈርስ መጠየቅ አለበት ውል የማይረጋበት ምክንያት ከቀረበት ማለቱ ውሉ የማይረጋበት ምክንያት የሚቀርባቸውን አንደችሎታ ማጣት አቅመአዳም አለመድረስ ወይም መገደድ ያሉትን አጋጣሚዎች ለመግለጽ የታለመ ነው ሌላው የጊዜ ገደብ የተቀመጠው በጉዳት ምክንያት ሀበርበርከ ርበክር የተደረጉ እና አካለ መጠን ያደረሰ ሰው ያደረጓቸውን ውሎች የሚመለከቱ ናቸው ውሉ ከተደረገበት ጊዜ ጀምሮ በሚቆጠር በሁለት ዓመት ውስጥ እንዲፈርሱ ካልተጠየቁ ይፀናሉ የውል መፍረስ ውጤት አንድ ውል የማይረጋ በመሆኑ ምክንያት እንዲፈርስ የተደረገ እንደሆነ በተቻለ መጠን ተዋዋዮች ወደነበሩበት ቦታ እንደመለሱ ማድረግ ይገባል ውሉ የፀና ነው በሚል ዕምነት ውሉን በመፈፀም ረገድ የተደረጉ ስራዎች ካሉ ቀሪ ይሆናሉ ውጤት ያሌላቸው ወይም የማያስገኙ ይሆናሉ ይህ ማለት ስለውሉ አፈፃጸም የተደረጉትን አንዱ ለሌላው መመለስ ይኖርበታል ማለት ነው ይህ የውል ማፍረስ ውጤት አንዱ ገጽታ ሲሆን ሌላው ደግሞ ተዋዋዮችን በተለያየ ምክንያት አእነበሩበት ቦታ መመለስ የማይቻል አስቸጋሪ ወይም ከፍ ያለ መሰናከል የሚያመጣ ሲሆን ህጉ የሚያስቀምጠው አማራጭ ነው ስለውሉ አፈጻጸም የተሰሩ ሥራዎች ሁሉ እንደረጉ እንዲቀሩ ያዛል ሁልጊዜም ማለት በሚቻል ደረጃ ውል ከፈረሰ በኋላ የመጀመሪያውን አማራጭ በመጠቀም ተዋዋዮች ወደነበሩበት እንዲመለሱ በማድረግ ውሳኔ የሚሰጥ ስለመሆኑ በርካታ የፍርድ ቤት ውሳኔዎችን በማየት መረዳት ይቻላል ፍርድ ቤቶች ሁለተኛውን አማራጭ ሲጠቀሙ አይታይም መመላለስ የሚቻልበት ሁኔታ ሁልጊዜም ስላለ ነው ብሎ መደምደም ያስቸግራል በቅርብ ጊዜያት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በነ ወሮ ጎርፌ ላይ የሰጠውን ውሳኔ ተከትሉ በየፍርድ ቤቱ የሚቀርቡ ጉዳዮች መብዛት ይህንን ክፍተት ለመጠቀም ከመሻት የሚነሱ ናቸው ብሎ በድፍረት ለመናገር ብዙ የሚያሳቅቅ አይደለም የውል መፍረስመሠረዝ ላይ ለማወያያነት የቀረቡ መልመጃዎች የማይንቀሳቀስ ሀብት ሽያጭን በተመለከተ ውሉ ውል ለማዋዋል ሥልጣን በተሰጠው አካል ፊት ወይም በሚገባ አኳኋን በፍርድ ቤት መዝገብ ፊት መሆን አለበት በማለት በፍትሐብሔር ህግ ቁጥር ላይ ተገልሏዷል ይህን አለማሟላት ውሉን ፍርስ ያደርገዋል። አስተያየትዎን ይስጡበት ምዕራፍ ሶስት የውል አለመፈፀም ደንብ የሥልጠናው ጠቅላላ ዓላማ ሠልጣኞች ከሥልጠናው በላ በውል አለመፈፀም ምክንያት የሚደርሱ ጉዳቶችን ይለያሉ በውሉ አለመፈፀም ምክንያት የተጎዳ ሰው ያለውን አማራጭ ይለያሉ ውል ያልተፈፀለት ሰው ሊኖረው የሚገባውን ጥንቃቄ ይገነዘባሉ የሥልጠናው ዝርዝር አላማዎች ሠልጣኞች ከውይይቱ በኋላ ውልን በግዴታ ማስፈፀም የሚቻልበትን ሁኔታ ይለያሉ በኪሳራ አከፋፈል ረገድ የውል እና ከውል ውጪ ህጎች ያላቸውን ግንኙነት ይገነዘባሉ የጉዳቶች ዓይነቶችን ይለያሉ የኪሳራ ዓይነቶችን ይለያሉ በኪሳራ አከፋፈል ረገድ ዳኛ ሊኖረው የሚገባውን ሚና ይለያሉ የውል አለመፈፀም ደንብ ሰዎች የውል ግዴታ ውስጥ የሚገቡት በአንድ ምክንያት ነው ይህ ምክንያታቸው እንዲሳካ ይፈልጋሉ የሚያስገኝላቸውን ጥቅም ያስባሉ የሀብት ልውውጥ በራሱ አንድ ዓይነት የኢኮኖሚ ጥቅምን ያስገኛል የበለጠ ገንዘብ ለማትረፍም ይረዳል ጥሬ ሀብቶች ወደሚፈለጉበት ውጤት የሚቀየሩት በዚሁ መንገድ ነው ምርታማነት ይበረታታል ነገር ግን ይህ እንዲሆን የሰዎችን መተማመን ለማትረፍ በሚችል ደረጃ የውል ግንኙነት ጥበቃ ያስፈልገዋል ልውውጥ ቀና የሚሆነው በዚህ ሁኔታ ነው በዚህ የተነሳ ለውል ጥበቃ መደረጉ የተገባ ነው ሰው በቃሉ ይታሰራል የሚለው ብሂልም የዚህ መሠረታዊ ሀሳብ ነፀብራቅ ነው ይህ ቢሆንም ታዲያ በተለያዩ ምክንያቶችውል አፈፃፀም ችግር ሊገጥመው ይችላል አንዱ ወይም ሌላው ተዋዋይ ውሉን ለመፈፀም የማይችልበት ወይም የማይፈልግበት ምክንያት ሊፈጠር ይችላል አንዲህ ሲሆን የህጉ ጥበቃ ትርጉም የሚያገኘው ውሉን ያላከበረው ወገን የገባበትን ስምምነት በግዴት እንዲፈፅም ወይም ውሉ ላልተፈፀመለት ሰው ካሳ እንዲከፈለው በማድረግ ነው ውሉ የፈረሰበት ወገን ከነዚህ ምርጫዎች ውስጥ አንዱን በመውሰድ መብቱን ለማስከበር ይችላል የሁሉንም አሠራር እንደየቅደም ተከተሉ የምናየው ይሆናል ውል በግዴታ እንዲፈፀም ስለመጠየቅ አንዲህ ያለው መፍትፄ ውሉ የፈረሰበት ወገን መብት በተሻለ መንገድ የሚያስጠብቅ ነው የባለዕዳውን ፈቃድ ማግኘት ሳያስፈልግ በፍርድ ሀይል በስምምነቱ መሠረት ቃል የተገባውን አንድ ነገር ለማስገኘት ይረዳል ውሉ በፈቃድ ተፈጽሞ ቢሆን ኖሮ ውሉ የፈረሰበት ወገን ይገኝ የነበረበት ቦታ ላይ የሚያስቀምጠው ይሆናል ርግጥ መብቱን ሁልጊዜም በቀላሉ የምናገኘው አማራጭ አይደለም ለምሳሌ አንድን ምርት በአንድ የተወሰነ ጊዜ ለማቅረብ ግዴታ የገባ ሰው ቃሉን ለማክበር ሳይችል ወይ ሳይፈልግ ቀርቷል እንበል ውሉ የፈረሰበት ሰው ውሉ በግዴታ እንዲፈፀምለት ይፈልጋልበክርክሩ ሂደት ግን ምርቱ ከዓለም ገበያ ይጠፋል እንዲህ ሲሆን ውሉን በግዴታ ለማስፈጠም አይቻልም ሌላ አማራጭ በመጠቀም ውሉ የፈረሰበት ወገን ካሳ እንዲያገኝ ከማድረግ በቀር በጥያቄው መሠረት ለማስተናገድ ያስቸግራል ይህ ማለት አንድ ውል ለመፈፀም የማይቻል መሆን ይህንን መፍትፄ ለመጠቀመም ያለንን ዕድል ያጠባል ማለት ነው ሌላው ውሉን በግዴታ ለማስፈፀም የባለዕዳውን ፈቃደኝነት የሚያስፈለግበት አጋጣሚ መኖር ነው አርሱ ያልፈቀደ እንደሆን መፍትሄውን በአማራጭነት ለመጠቀም የባለዕዳው ነፃነት የሚነካበት ሁኔ ይፈጠራል ለምሳሌ ሥዕል ለመሳል የተስማማ ሰው ፃሳቡን ቢሠርዝ በፍርድ ኃይል ሥዕል ሠርቶ እንዲያስረክብ ማድረግ አይቻልም በግዴታ ውስጥ ያለ ሰው በነፃ አዕምሮው የፈጠራ ክህሉቱን ተጠቅሞ ውጤት ያለው ሥራ ይሠራል ተብሉ አይታሰብም ስለሆነም ማስገደዱ በአንድ በኩል ሰዎች ነፃ ሆነው የማሰብን የመሥራት መብታቸውን የሚነካ በሌላ በኩል ተፈላጊውን ውጤትም የሚያስገኝ አይሆንም እንዲህ ባለ ሁኔታ ይህን መፍትፄ መተቀም አስቸጋሪ ይሆናል የፍህቁ እና ከዚህ በቀር ውልን በግዴታ ለማስፈፀም ሁለት ነገሮች መሟላታቸውን ማረጋጥ ይጠይቃል አንዱ የውሉ መፈፀም ለባለገንዘቡ የተለየ ጥቅም የሚሰጠው መሆኑን ነው በህግ ግምት ካልተወሰደበት በቀርይህን ማስረዳት የሚተበቅበት ባለገንዘቡ ነው ሁለቱ የማይነጣጠሉ በአንድነት መታየት ያለባው ነጥቦች ናቸው። የነሂህ ሁኔታዎች መሟላት ነው ባለገንዘቡን የመፍትሄው ተጠቃሚ የሚያደርገው ውል እንዲሠረዝ ስለመጠየቅ ከፍ ሲል የተጠቀሰውን መፍትፄ መጠቀም የማይችል ሰው ውሉ እንዲሰረዝና በምትኩም ካሳ እንዲከፈለው ለመጠየቅ ይችላል ይህ ሁለተኛው አማራጭ መሆኑ ነው የካሳው ክፍያ ጥያቄ እንደሚከተለው በሁለት መንገድ ሊቀርብ ይችላል በፍርድ የሚወሰን ኪሳራ ውል ሲፈርስ በተዋዋዮች ላይ ጉዳትን ሊያስከትል ይችላል የተጎዳ ሰው ሲኖር ደግሞ ጉዳቱ ሊጠገንለት ይገባል ይህ በሁሉም የህግ ሥርዓቶች ያለ በፍትህ መሠረት ላይ የቆመ አሠራር ነው የካሳውን መጠን በተመለከተ በመርህ ደረጃ ከደረሰው ጉዳት ጋር የተመዛዘነ መሆን አለበት ፐከፀ ፀዘበርዐፅ ዐቪ ፀባሀከጪፀበርፀ ይባሳል እንደሌሎች ሁሉ የኢትዮጵያ ህግም ለደረሰ ጉዳት ሊከፈል የሚገባው ካሳ ከጉዳቱ ጋር የተመዛዘነ መሆን እንዳለበት ይቀበላል የፍህቁ የሚነግረንም ይህንኑ ነው ከውል መፍረስ ጋር በተያያዘ ሊከፈል የሚገባው ካሳም ከውል ውጪ ለሚደርስ ኃላፊነት በሚከፈለው ዓይነት እንደሚመራ በፍህቁ መገለፁ የዚህ መርህ ተፈፃሚነት በውል ግንኙነቶችም ላይ አንደሚሆን የሚያጠይቅ ነው ርግጥ የህጉን ዝርዝር ይዘት ስንመለከት ሁፄታዎች በመጠኑ የተለዩ ሆነው እናገኛለን ለምሳሌ የፍብህቁ ከፍ ሲል ከተተቀሰው መርህ በመለየት የካሳ ክፍያውን መጠን አስተዋይ አዕምሮ ያለው ሰው የውሉ አለመፈፀም ያደርሳል ብሎ በሚገምተው አስተያየት ልክ እንደሚሆን ይገልፃል ፍርድ ቤቶች የመንሸራሸር ነፃነታቸውን ትርጉም ባለው መንገድ እንዲጠቀሙበት ይረዳ ዘንድ ህጉ ከግምት መግባት ያለባቸውን ዝርዝሮች በአመልካችነት ጠቁሟልየውሉ ዓይነት የተዋዋዮች የሞያ ሥራ ቀደም ሲል የነበራቸው ግንኙነት ባለዕዳው የሚያውቃቸው ሁኔታዎችና ማንኛዎቹም አጋጣሚዎች ሚዛናዊ ውሳኔ ላይ ለመድረስ ያስችላሉ የተባሉ ነጥቦች ናቸው የፍህቁ የህጉ መለኪያ አስተዋይ አዕምሮ ያለው ሰው አስተያየት መሆኑን ቢገልፅም ዕዳውን የሚያከብዱ ልዩ ሁኔታዎች ስለመኖራቸው ባለገንዘቡ አስታውቆት እንደሆነ ጉዳቱ የደረሰው ባለዕዳው ሆነ ብሎ ባለገንዘቡን ለመበደል ባደረገው ተግባር ምክንያት ወይም ባሳየው ጉልህ ቸልተኝነት እንደሆነ ወይም የደረሰው ጉዳት አስተዋይ አዕምሮ ያለው ሰው ከገመተው መጠን በታች መሆኑን ያስረዳ እንደሆነ የካሳው ክፍያ በደረሰው ዕርግጠኛ ጉዳት ልክ ይሆናል የፍብህቁ እና በማለት ወደቀደመው የጉዳት ካሣ ተመዛዛኝነት መርህ መልሶ ይወስደናል በዚህ መሠረት ዕርግጠኛ የጉዳት ካሳ ክፍያውን ያገኛል ማለት ነው ፅርግጠኛውን የጉዳት ካሳ ግን በማንኛውም ሁኔታ የሚያገኝ አይደለም ተበዳዩ የሚደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ በሚያደርገው ጥረት ይወሰናል ሊደርስ የሚችለውን ጉዳት ለማሳነስ በርሱ በኩል ሊፈፅመው ወይም ሊቆጣጠረው ይችል የነበረ ተግባር ካለ ተባዳዩ ይህን ለመቆጣጠር መትጋት አለበት በልታው ምክንያት ጉዳቱ ቢበዛ ሊያርቀው ይችል በነበረው ጉዳት መጠን የሚደርሰውን ኪሳራ ራሱ እንዲሸከም ይገዳደል ለምሳሌ አበበ በምርት ሂደት የሚያስፈልገውን አንድ ጥሬ ዕቃ ሱራፌል ሊያቀርብለት ስምምነት አድርጓል ሱራፌል ግዴታውን እንደማይወጣ አበበ ተረድቷል ይህን አንዳወቀ ምንቸገረኝ ኪሳራዬ አንደሁ አገኛለሁ ብሎ ቸል ቢል ጌላ ጥሬ ዕቃው ባለመቅረቡ ምክንያት የደረሰበትን ኪሳራ ሁሉ መጠየቅ አይችልም ጉዳቱን ለመቀነስ ማድረግ የሚገባው ያንኑ ጥሬ ፅቃ ከገበያ ላይ ፈልጎ ማግኘት የሚችል ሲሆን መተካትና ሥራውን ማከናወን ነው በዚህ ሁፄታ ኪሳራውን መቀነስ ይችላል ከዚያ በተረፈ ይህን ዓይነት የጥንቃቄ ዕርምጃ ያልወሰደው ጥረቱ አስቸጋሪና ብዙ ወጪን ስለሚያስከትልበት መሆኑ ማስረዳት ይጠበቅበታል አሊያ ግን ሊያርቀው ይችል በነበረው መጠን ካሳውን እንዳያገኝ ህጉ ያግደዋል ጉዳት እንዳይበዛ ቸልታም እንዳይኖር የሚረዳ ማትጊያ ነው በ ዕበዕበዝር ከዝ ቪ ልበ ዘበርበክህ አጠቃላይ ስለሆነው የካሳ ክፍያ ይህን ካልን አሁን ደግሞ ውል ባለመፈፀሙ ምክንያት ስለሚደርሱት የጉዳት ዓይነቶች እናያለን እንደሚከተለው በሦስት ሊከፈሉ ይችላሉ ሯ ውታ ማፇሃታ ደታፅዕያው ፖዕፉ ማጣታ ዖሟደረነጎ ፖታ ዐ ወሯፀሪረሠ ቀደም ሲል እንደተገለፀው በውል ግንኙነት ውስጥ ያሉ ተዋዋዮች በየራሳቸው ከውሉ አናገኛለን ብለው የሚያስቡት ጥቅም አለ አንዱ ተዋዋይ ውሉን ለመፈፀም በማይችልበት ወይም በማይፈልግበት ጊዜ ሌላው ተዋዋይ ከውሉ ማትረፍ ይፈልግ የነበረውን ተስፋ ያጣል እንዲህ ያሉ ሰዎች የፀና ውልን በመተማመን ለሚደርስባቸው ጉዳት ህጉ ዋስትና ይሰጣል ይህም ካሣ አንዲያገኙ በማድረግ ይተረጉማል ተዋዋዮቹ በየበኩላቸው የሚፈለግባቸውን ግዴታ ተወጥተው ውሉ ተፈፅሞ ቢሆን ኖሮ አንድ አስተዋይ አዕምሮ ያለው ሰው ተበዳዩ ሊደርስበትሊያገኝ ይችል ነበር ብሎ በሚሰጠው አስተያየት መነሻነት ተበዳዩ ቀርቶበታል የተባለውን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም በማስላት ነው በምሳሌ ለመግለጽ ያህል ዓለማየሁ በብር ሊሸጣት ያሰባት አንዲት ቶዮታ ኮሮላ መኪና አለችው በቀለ በተመሣሣይ ዋጋ እንዲህ ያለች መኪና ማግኘት እንደማይችል በማሰብ የተሰጠውን ዋጋ ይቀበላል ውሉ ከተፈፀመ በጊላ ዓለማየሁ መኪናዋን በተሻለ ዋጋ ለመሸጥ እንደሚችል በማሰብ ገዢ አፈላልጐ በብር ይሸጣል በቀለ ውሉ ስለፈረሰበት ዓለማየሁን ካሣ ሊከፍለኝ ይገባል በማለት ይከሳል ለበቀለ መክፈል ያለበት የጉዳት ካሣ የሚሰላው አስተዋይ አዕምሮ ያለው ሰው ውሉ በተመሠረተ ጊዜ የመኪናው ዋጋ ርክክብ በሚደረግበት ጊዜ ምን ያህል እንደሚሆን በሚሰጠው አስተያየታዊ ግምት መነሻነት የሚሰላ ነው በዚህ ሰው አስተያየት የመኪናዋ ዋጋ ብር ይገመት የነበረ ከሆነ በቀለ የደረሰበት ጉዳት ሲቀነስ እሱ መኪናዋን ለመግዛት የተስማማበት ዋጋ ብር ይሆናል ማለት ነው በሌላ ምሳሌ ለማብራራት አንድ የታክሲ ባለቤት ለሌላ የታክሲ ባለቤት አንድ በታክሲ አገልግሎት ልትሠማራ የምትችል ሚኒ ባስ በብር ሸጠለት ዓለማየሁ መኪናውን በተሻለ ዋጋ የሚገዛው ሰው በማግኘቱ ከበቀለ ጋር ያደረገውን ውል ያፈርሳል በቀለ ለጉዳቱ ካሣ እንዲከፈለው ይጠይቃል የዚህ ሰው የጉዳት ካሣ ውሉ ተፈፅሞ ቢሆን ኖሮ ሊያገኝ ይችል የነበረው ጥቅም ነው አሱም የመኪናውን ዋጋ በተመለከተ ከፍ ሲል እንደተገለፀው የደረሰበት ጉዳት መኪናዋን በታቀደው ጊዜ አግኝቷት ቢሆን ኖሮ በታክሲ አገልግሎት ላይ አሠማርቶ ያገኝ የነበረው ጥቅም አስተዋይ አዕምሮ ያለው ሰው በሚሰጠው አስተያየት ልክ ይሆናል ማለት ነው ሐ ውሳዎ ዐመታማመ ምፖዖታ ዖሟደረነ ሦሪ። ሰዎች የውሉን ቃል ወይም ተፈፃሚነቱን በመተማመን ለተጨማሪ ወጪዎች የሚዳረጉበት ሁፄታ አለ ከፍ ሲል በተጠቀሰው ምሳሌ በቀለ የተደረገውን ውል በመተማመን ለመኪናዋ ይሆናል ብሎ ያሰበውን አራት ብሪጂስቶን ጐማ እያንዳንዱን በብር በድምሩ በብር ገዝቶ ሊሆን ይችላል ወጪው የተደረገው የውሉን መከበር በመተማመን ነው ውሉ በሌላው ተዋዋይ ሲፈርስ ለመኪናዋ ሲል ያወጣው ብር ኪሣራ ይሆንበታል ማንኛውም ሰው የመሠረተውን ውል በመተማመን በሚያከናውናቸው ተግባራት ምክንያት ጉዳት የደረሰበት እንደሆነ ውሉን ያፈረሰው ወገን ይህንን ጉዳት መካስ ይገባዋል ውሉን በመተማመን በአንድ ተዋዋይ ላይ የሚደርስ ጉዳት ማለት ይህ ነው ጨ ው ምሃጋዖ ዕጎፍ መደ ፊጎው ያታሳሰፈ ምፖ ምሟዖቦታ ዖሚሟደረነ ፖዳሥ ውል በመደረጉ የተነሣ አንዱ ለሌላው ያስተላለፈው ሀብት ወይም የፈፀመው ከፊል ክፍያ ሊኖር ይችላል ውሉን ሌላው ተዋዋይ ሳያከብር ሲቀር ሀብቱ ባፈረሰው ሰው እጅ ይቀራል በዚሁ መጠን ጉዳት ይደርሳል ስለሆነም የተወሰደው ንብረት የተከፈለው ገንዘብ እንዲመለስ በማድረግ ጉዳቱ ይጠገናል ስለሆነም በተራ ቁጥር ለ እና ሐ የሚደርሱ ጉዳቶች ተዋዋዩን ውሉ ከመፈፀሙ በፊት እነበረበት ቦታ ላይ የሚያስቀምጡት ይሆናሉ ማለት ነው በተዋዋዮች በቁርጥ የሚወሰን ኪሳራ ሀህ አንዳንድ ሰዎች ውል ሲመሰርቱ ውሉ ላይፈፀም የሚችልበትን ሁኔታም አስቀድመው ያያሉ ይህ በሚሆንበት ጊዜ ሊደርስባቸው የሚችለውን ጉዳት በማሰብ በውሉ አለመፈፀም ምክንያት በሚደርስባቸው ጉዳት ላይ ስምምነት ያደርጋሉ ወይም ተዋዋዩ ስምምነቱን እንዳይፈርስ ይረዳል ብለው የሚያስቡትን መቀጫ ሐረግ ባሉ ላይ ያስገባሉ የመቀጫ ስምምነቱ ሁለት መልክ ሊኖረው ይችላል አንዱ ተዋዋዮቹ ይደርሳል ብለው ያሰቡትን ገንዘብ ኪሳራ ልክ የሚወስኑበት ነው ቪ ርዐጠዐፀከዉርባ ርግጥውሉ በተሠረዘ ጊዜ የደረሰው ጉዳ ተዋዋዮች አስቀድመው ከወሰኑት መጠን ያነሰ ወይ የበዛ ሊሆን ይችላል ይሁንና የሚያገኙት በስምምነታቸው መሰረት አንዱ ለሌላው ሊከፍል ያሰበውን ካሳ ነው በበዛው ወይ ባነሰው መጠን የሚታየው ልዩነት ተዋዋዮች ኪሳራውን ለመካፈል እንደወሰኑ ያሰገምታል ስለሆነም መብዛት ወየ ማነሱ ከግምት ሳይገባ የተስማሙበትን መጠን ውሉ ለፈረሰበት ወገን ይከፍላሉ አስቀድመው መስማማታቸው በክርክር ሂደት መጠኑን በመወሰን ረገድ ያለውን ውስብስብ የማስረጃ ሂደት ያቀላል ሊፈፀም ከሚችል ግድፈትም የሚጠብቅ ነው ውሉ ቢሠረዝ የሚደርስባቸውን የካሳ ክፍያ መጠን እንዲያውቁ ዕድል በመስጠት በግንኙነታቸው ዕጣ ፈንታ ላይ ተገቢ ነው የሚሉትን ውሳኔ ለማሳለፍ ያስችላቸዋል ለምሳሌ ይታይአንድ መጽሐፍ በብር ሊገዛኝ ተስማምቷልበአምስት ቀናተወ ውስጥ ባላመጣለት ኪሳራ ብር ልከፍለው ተስማምተናል ቀለም ይህንኑ መጽሐፍ በብር አገዛሃለሁ ብሎ ቀረበ ለዚህ ሰው ብሸጥለት ከይታይ ጋር ያለኝን ውል በማፍረሴ ልከፍል ከምችለው ኪሳራ ብር አንፃር ሲታይ ውጠየቱ ልዩነትን አይመጣም ስለሆነም ውሉን ለማፍረስ ያለኝን ፍላጎት እሠርዛለሁ ለኔ የሚያዋጣኝ ከብር በላይ ሊገዛኝ የሚመጣ ሰው ያለ እንደሆን ነው ለይታይ ካሳ ከፍዬም ቢሆን የተሸለ ጥቅም ማግኘት የምችለው በዚህ ጊዜ ብቻ ነው ይህን መወሰን የቻልኩት የመጀመሪያውን ውል ባፈርስ የሚጠበቅብኝን የኪሳራ መጠን በማወቄ ነው ማንም ሰው ሳይጎዳ ሀብትን ወደተሻለ ተጠቃሚ ለማስተላለፍ ይረዳል ማለት ነው የዚህ ዓይነቱ በውሉ ፋንታ የሚከፈለው የካሳ መጠን ውሉ ባለመፈፀሙ ምክንያት የሚደርሰውን ጉዳት የሚክስ በሚገባ የሚክስ ነው ስለሆነም ተዋዋዩ በጉዳቱ የሚደርስበትንካሳ ተቀብሎ ይሄዳል ውሉ ይፈፀምልኝ ካሳውም ይከፈለኝ ብሎ መጠየቅ አይችልም ሁለተኛው የመቀጫ ስምምነት ዓይነት ደግሞ በውሉ ላይ በተመለከተው ጊዜ ውስጥ ተዋዋዩ ግዴታውን እንዲወጣ ለማስገደድ ወይም ለተጨማሪ ግዴታዎች መፈፀም ዋስትና እንዲሆን ተብሎ የሚወሰን ነው ከፍ ሲል ከተተቀሰው መቀጫ የሚለየው ከዋናው ግዴ ጋር የሚፈፀም መሆኑ እና ዓላማው ተዋዋዩ ውሉን እንዲያከብር ለማስገደድ ርወ ሪጋፀዐቁወስርሪፀ መሆኑ ነው በመጀመሪያውም ሆነ በሁለተኛው መንገድ በተዋዋዮች የሚወሰነው ኪሳራ እርግጠኛ ከሆነው የካሳ መጠን የበዛ ወይ ያነሰ ሊሆን ይችላል ይህን ምክንያት በማድረግ ግን ዳኞች መጠኑን ሊያሻሽሉት አይችሉም ይሁንና ውል የተሠረዘበት ወገን ሳይጎዳ ፖጋፈውፇ ጎ ዖሟያሃኝ ዕመሆያፉ ነገር ግን ሀብቱ ወደተሻለ ተጠቃሚዎች ሊያልፍ የሚችልበት አጋጣሚ ቢኖር ይህን ዓይነት የሸቀጥ ልውውጥ የሚገታ የካሳ መጠን ተደርጎ ቢሆን ፍርድ ቤቶች ምን ዓይነት ውሳኔ ማሳለፍ አለባቸው። ምዕራፍ አራት ዋስትናዎች በፅለት ተዕለት ግንኙነቶቻችን ውስጥ ሰዎች በውል የገቡልንን ግዴታ የሚወጡ ስለመሆኑ ጥርጣሬ ሊገባን ይችላል ንቁ ሆነንም ሊደርስብን የሚችለውን ኪሳራ ሊተካልን የሚችል ማረጋገጫ ለማግኘት እንተጋለን ካላገኘን ውል ለመፈጸም የነበረንን ውሳኔ እንሰርዛለን በድፍረት ከገባንም ፅዳውን ለማስመለስ ያለንን ዕድል ልናጣ እንችላለን እንዲህ ያለው ጥርጣሬ ቀና ለሆነ የንግድ ልውውጥ ሂደት እንቅፋት ነው ስለሆነም ህጉ ቀና የሆነ የሸቀጥ ልውውጥን በማበረታታት የሚፈለገው የኢኮኖሚ ዕድገት እንዲኖር የፈጠረው አንድ መሳሪያ ዋስትና ነው ዋስትና በውል ግዴታ የገቡልን ሰዎች ቃላቸውን አክብረው አንደሚፈጽሙ ሦስተኛ ወገኖች ባለገንዘብ ለሆንነው ለኛ መተማመኛ የሚሰጡበት ስለእነርሱ ሆነውም ግዴታውን ለመወጣት የሚስማሙበት መንገድ ነው ይህ ባለገንዘብ ለሆነለሚሆን ሰው ፅዳ ከፋይ ከሆነ አንድ ሰው ይልቅ በርካታ ሰው ዕዳ ከፋይ በማድረግ ገንዘብ የማስመለስ ዕድላችንን ያሰፋዋል በለልውውጡ ላይ ያለንን ዕምነትም ያሳድጋል ይህ ዓይነቱ ግዴ የመግባት ሥርዓት በአብዛኛው ከውል የሚመነጭ ቢሆንም ከህግ ወይም ከፍርድ ሊመነጭም ይችላል ዋስትና የሚደረግበት ሁኔታ የዋስትና ግዴታ አሁን ያለን አንድ የተረጋገጠ ዕዳ ወይም ወደፊት በዋናው ባለዕ ላይ ሊመጣ የሚችልን ኃላፊነት ለመቀበል ሊደረግ ይችላል በኋእለኛው ምክንያት የሚያደረገው የዋስትና ግዴታ በዋናው ባለዕዳ ላይ ዕዳ ከሌለ በቀር ዋሱ ዋስትናውን ሊያስቀር ይችላል ብዙ ጊዜ አንድ ግዴታ ከመጠየቁ በፊት የሚመሰረት ቢሆንም ዕዳው በሚጠይቅበት ጊዜ ዘዐ ፅ ዐፀዕሪ ዐወሀሀ ወይም ዕዳው መጠየቅ ከጀመረ በጊላም ቢሆን ሊደረግ ይችላል በየትኛውም መንገድ ቢሆን ግን ካለ ወይም ከሚመጣ ዕዳ ጋር የተቆራኘ ነው ሃ ቋርርፀዐ ቋወፅዚቹ ዕዳ ሳይኖር የዋስትና ግዴታ አይኖርም ዋናው ግዴታ የማይፀና ሲሆን የዋስትና ውሉም እንዲሁ አይፀናም የባለዕዳውን ችሎታ አለመኖር ወይም የፈቃድ ጉድለት እያወቀ ዋስ ከሆነ ግን ዋናው ግዴታ የሚፀና ባይሆንም እንኳ ዋሱ ለባለገንዘቡ ግዴታ የገባበትን ገንዘብ መክፈል ይጠበቅበታል የዋስትናውን ልክ በተመለከተ ዋስትና ከዋናው ግዴታ በላይ ሊሆን አይችልም ዋናው ባለዕዳ የማይጠየቅበትን ዋሱ አይጠየቅበትም እንዲህ ያለ ስምምነት ተደርጎ ከሆነም በዋናው ዕዳ ልክ ይቀነሳል የዋስትና ግዴታ ሊከተለው የሚገባ የአፃፃፍ ሥርዓት የዋስትና ግዴታ ከፍ ያለ ኃላፊነትን የሚያስከትል በመሆኑ ዋስ የሚሆን ሰው የሚገባበት ግዴታ የሚያስከትልበትን ኃላፊነት እንዲረዳው ያስፈልጋል ስለዚህም ዋሱ በጥድፊያ ግዴታ ውስጥ ሳይገባ የአፍታ ጊዜ አግኝቶ እንዲያስብበት ዕድል ለመስጠት ውሉ በጽሁፍ እንዲሆን ህግ ያዛል ርህ ግዴታ የሚገባበት የገንዘብ መጠንም መታወቅ አለበት ይህ ያልተሟለ አንደሆን ውሉ ፈራሽ ይሆናል የዋስትና ግዴታዎች ዓይነት ከኃላፊነቱ ቆይታ አንፃር ለተወሰነ ጊዜ ወይም ላልተወሰነ ጊዜ በክበህህ ሀበ። ፀ ይባላል በትራንስፖርትና መገናኛ ሚኒስቴር በዘበኝነት የተቀጠረ ሰው በሥራው ላይ ባለበት ጊዜ ሊጠፋበትሊጠይቅበት ለሚችል ዕዳ እስከ ብር አምስት መቶ ሺህ ብር ድረስ ዋስ እንደመሆን ማለት ነው ዕዳው አልመጣም የሚመጣበት ሁኔታ ግን ሊኖር ይችላል የዋስትናው ኃላፊነት ቆይታም በጊዜ የተገደበ አይደለም እንዲህ ያለውን የዋስትና ግዴታ በተመለከተ የዋናው ባለዕዳ ተጠያቂነት ካልደረሰ በቀር ዋሱ ዋስትናውን እንዲወርድለት ለመጠየቅ ይችላል ጭነጨጩጭቃድ ጳቋደረያ ማለት ዋሱ ዋስትናው እንዲቀርለት በሚጠይቅበት ጊዜ ዋናውን ባለዕዳ ተጠያቂ የሚያደርግ ነገር ያልተገኘ አንዲሁ ማለት ነው መስሪያ ቤቱ ይህንነ አጠርቶ ነባ ማድረግ ይገባዋል ሠራተኛው ምትክ ዋስ ማቅረብ ካለበት ያንኑ መጠየቅ የመስሪያ ቤቱ ድርሻ ነው ይህ ግን የዋሱን የዋስትና ግዴታ ከማውረድ መብቱ ጋር የተያያዘ አይደለም ምትክ ዋስ ቢገኝም ባይገኝም ዋሱ ግዴታው እንዲወርድለት ከጠየቀበት ጊዜ ጀምሮ ቀሪ ሊደረግለት ይገባል ተራ እና የአንድነት ዋስትና ሯ ፇራ ያዎዕታና ፇዴታ ይህ ዓይነቱ የዋስትና ግዴታ ዋናው ባለዕዳ ግዴታውን ሳይፈፅም ሲቀር ብቻ የሚመጣ ነው ባለገንዘቡ የዋናውን ባለዕዳ ግዴታ ዋሱ እንዲፈፅምለት የሚጠይቀው ይኸው ባለዕዳ ግዴታውን ለመፈጸም የማይቻል መሆኑ ሲረጋገጥ ብቻ ነው ባለዕዳ መክሰሩ በፍርድ ካልተረጋገጠ በቀር ዋሱ እንደተከሰሰ ባለገንዘቡን ከዋናው ባለዕዳ ጋር ተከራከር የማለት መብት ይኖረዋል ካለነሳው ግን ባለገንዘቡ ከባለዕዳው ጋር ለመከራከር ሳይገደድ በዋሱ ሀብት ላይ ዕዳውን ሊያስፈጽም ይችላል መከራከሪያውን አንስቶ ቢሆን እንኳ የባለዕዳውን ንብረቶች መምራትና ለዚሁም ክርክር የሚያስፈልገውን በቂ ወጪ ለባለገንዘቡ መስጠት ይጠበቅበታል ይህን አለማድረግ ከባለዕዳው ጋር ተከራከር የማለት መብቱን የሚያሳጣው ይሆናል ሐ ይነጋድቀኑታ ዎዕጎታና የአንድነት ዋስትና የሚመሰረተው ዋሱ ከባለዕዳው ጋር በጋራ ተጠያቂ መሆኑን ወይም ይህን በመሰለ በማናቸውም ሌላ መንገድ ሀሳቡን በመግለጽ ግዴታ የገባ እንደሆነ ነው ከዋናው ባለዕዳ ጋር ተከራከር የማለት መብት አይኖረውም ባለገንዘቡም ከዋናው ባለዕዳ ጋር በአንድነት ምናልባትም ከዋናው ባለዕዳ በፊት ሁሉ ክስ ሊቀርብበት የሚችል ሰው ነው የዋስ መብቶች ያመረፇ መሀት ዋሱ ስለዋናው ባለዕዳ ሆኖ የከፈለውን ተገቢ የሆነ ክፍያዎች ሁሉ በባለገንዘቡ መብት ተዳረጊ ሆኖ ባለዕዳውን ሊጠይቀው ይችላል ሐ ዎናው ሪና ጋሮ ፇራዕረ ያማ መጋታ ቀደም ሲል እንደተገለፀው ይህ የተራ ዋስትና ግዴታ ያለበት ሰው የሚኖረው መብት ነው እንደተከሰሰ ወዲውኑ ከዋናው ባለዕዳ ጋር ተከራከር በማለት ባለገንዘቡን የመከራከር መብት ይኖረዋል ጨጹ ዕው ሒሲጋሃፖው ዖሟቻው መቃወጄሟያረዎቻ ማቀ ከግዴታው ዓይነት የተነሳ እንዲቀሩ ካልሆነ በቀር ለምሳሌ ውሉ የተፈፀመው በስህተት መሆኑን ወይም ባለፅዳው ለአቅም አዳም ያልደረሰ መሆኑን እያወቀ የገባበት ግዴታ ባለዕዳው ሊነሳቸው የሚችላቸውን መቃወሚያዎች እያነሳ ሊከራከርባቸው ይቻላል የዋስትና ዓይነቶች የግል የንብረት ዋስትና የሚንቀሳቀስ የማይንቀሳቀስ ፕሌጅ ሞርንጅ ወለድ አገድ የሞርጌጅ የሚመሰረትበት መንገድ በህግ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ በውል ሀ በህግ እና ህጉ ራሱ የሚሰጠው ዋስትና ነው የዋስትና ሰጪ ስምምነት አስፈላጊ አይደለም ለሁለት አይነት ሰዎች ዋስትና ይሰጣል የማይንቀሳሰስ ንብረት ለሸጠ ለሽያጩ ዋጋ አከፋፈል እና በሽያጩ ውስጥ ለተመለከቱት ሌሎች ግዴታዎች የማይንቀሳቀስ ንብረት የጋራ ተካፋይ ለሆነ ከክፍያው ውስጥ ለሚጎድልበት እና በክፍያው ያገኘው ሃብት እንዲለቅ ለተወሰነበት ለ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ዳኞች ወይም ሽማግሌዎች ለሰጡት ብይን ወይም ትዕዛዝ ተፈጻሚነት ዋስትና እንዲሆን የሚሰጥ በዳኞች ወይም በሽማግሌዎች ትዕዛዝ ብቻ የሚመሰረት የዋስትና የሚሰጠው ጉዳዩ በክርክር ላይ እያለ ውሳኔ ከማግኘቱ በፊት ሊሆን ይችላል አላማው እረታለሁ ብሎ የሚያስብ ተከራካሪ ንብረቱን ቀድሞ በማሸሽ አፈጻጸሙን እንዲያስናክል ነው ዋስትናው የሚመሰረተው ንብረቱ ዋስትና የሆለነትን የገዘብ መጠን እና የንብረቱን አይነት ለይቶ በመግለፅ እና ትዕዛዙን በማስመዝገብ ነው ትዕዛዙ በንብረቱ ሌላ ገደብ መጣል የለበትም በፍርድ ቤቶች ለውሳኔ ማስፈጸሚያ እንዲሆን ንብረቶች በፍሥሥህቁ መሰረት የሚያግዱ ሲሆን ይህ ሥነ ሥርዓት ህግ አላማ የተለየ ነው ውሳኔ ለማስፈጸም በማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ የሚሰጥ ዋስትና ሲመሰረት ንብረቱ እንዳይሸጥ እንዳይለወጥ ወይም በሌላ እዳ እንዳይሰጥ አስፈላጊ አይደለም ሐ በውል የሚቋቋም መያዣ ተበዳሪው ራሱ ንብረቱን በማስያዝ ሌላ ሰው ለተደደሪው ንብረቱን በማስያዝ ይመሰረታል ለሚጸና ሞርጌጅ አስፈላጊ ሁኔታዎች ያሟቋቋምታ ፅኔድ በውል የሚቋቋም መያዣ በፁሀፍ መሆን አለበት አዋዋይ ወይም ዳኛ ፊት መደረግ አለበት ይህ ፎርማሊቲ ማስፈለጉ በፍህቁ ተመልክቷል በውል የሚቋቋም ሞርጌጅ ውል እንደመሆኑ የጠቅላላ የውል ህግ ድንጋጌዎች የሞርጌጅን ህግ አስካልተቃረኑ ድረስ ተፈፃሚ ሊሆኑ ይችላሉ አዋዋይ ወይም በዳኛ ፊት መደረጉ የራሱ አላማ አለው « መያዣ የተሰጠበት የገንዘብ ልክ እና የንብረቱ አይነት በግልፅ መግለፅ ያስፈልጋል ምዝገባ የመያዣ መብቱ በማይንቀሳቀስ ርስት መዝገብ ውስጥ ካልተፃፈ በቀር ማንኛውም አይነት ውጤት አያስገኝም በየትኛውም ዓይነት መንገድ የተመሰረተ ሞርጌጅ ሊመዘገብ ይገባል ምዝገባው በንብረቱ ላይ ያለውን ግዴታ ለሶሰተኛ ወገን ከማሳወቅ ባለፈ በተዋዋዩቹ መሃከል ውጤት አለው ከዚህ በተጨማሪ የቀዳሚነት መብትን ለመወሰን አስፈላጊ ነው ምዝገባው ውጤት የሚኖረው ንብረቱ የተላለፈለት ሰው መብቱን ከማስመዝገቡ በፊት ወይም ንብረቱ ከመያዙና ከመመዝገቡ በፊት ከተከናወነ ነው እና መያዣ ለመስጠት የሚያስፈልግ ችሉታ ለራሱ እዳ ንብረቱን በመያዣ ለመስጠት ንብረቱን በገንዘብ ለሌላ ኛ ሰው ማስተላለፍ መብት ያለው ነው ለሌላ ሰው አዳ ንብረቱን በመያዣ መስጠት የሚችለው ደግሞ ንብረቱን ያለወጋ ማስተላለፍ መብት ያለው ነው ሓ ችሉታ የሌለው ሰው የሰጠው መያዣ ዋጋ የሌለው ሲሆን መብቱን ወይም ችሎታውን ንኋላ አግኝቷ እንኳን ሆን ቀድሞ የሰጠው መያዣ ዋጋ የለውም በሚመለከተው አስተዳደር ክፍል የባለቤትነት ምስክር ወረቀት ከተሰጠው ሰው ጋር የተመሰረተ መያዣ ውል ምስክር ወረቀት የተሰጠበት ማስረጃ ፍርስ ሆኖ ቢሰረዝ እንኳን ህጋዊ ውጤት አለው ምረሄጅሯ ቦዖሟመቋታፖው ረፉፇቻ የማይንቀሳቀስ ንብረት ሞርጌጅ የሚመሰረተው በማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ ብቻ ነው ህጉ የሚንቀሳቀሱ ንብረቶች እንደማይንቀሳቀስ ንብረት በመያዣ ሊሰጡ እንደሚችሉ ሊደነገግ ይችላል ለምሳሌ የንግድ መደብር የማንቀሳቀስ ንብረት የሚባሉት መሬትና ህንፃ ቢሆኑም አሁን ባለው ሁኔታ በመያዣ መስጠት የሚቻለው ህንፃን ብቻ ነው የከተማን ቦታ የማከራየት መብት በመያዣ ሊሰጥ ይችላል አዋጅ ቁጥር አንቀፅ ወደፊት የሚሰሩ ህንፃዎች በመያዣ መስጠት አይቻልም ዖጋመሪራ ሙታ ፍሷ ዕር ይፀያኗ ዳና ፖሬጩጨማሪቋርርፀዐወ ዐሪፅ ኣሓ ው ሓ ከንብረቱ ላይ ንብረቱ ሳይጠፋ እና አጉል ሳይሆን ለመለየት የማይቻል የንብረቱ ሙሉ ክፍል የመያዣው አካል ነው አንድን ነገር በሚጠቀምበት ሰው ሀሳብ ይህ ነገር ለሚገለገልበት ጉዳይ በነዋሪ ዓይነት ከዚሁ ጋር ተያያዞ የሚኝ ነገር ተጨማሪ ነገር ወይም ደባል ነገር ይባላል ይህም የመያዣው አካል ነው እነዚህ ንብረቶች ከዋናው ንብረት ላይ ከተለዩ ግን የሚንቀሳቀስ ንብረት ሆነው ስለሚቆጠሩ የመያዣው አካል መሆናቸው ይቀራል ከመያዣው ላይ በመነሳታቸው የንብረቱ ዋጋ ከቀነሰ ባለገንዘቡ አግባብነት ባላቸው ሞርጌጅ ህግ ድንጋጌዎች ሊሰራባቸው ይችላል ያፇያረጭ ይ ያዖሟደረምፆ ለዲዕ ዉፀም ሦሠጨማሪ ፅሰራዎቻ ዐ« ሩ በህንፃው ላይ ተስፋፍተው የተሰሩ ወይም በንብረቱ ላይ የተደረጉ የማሻሻያ ስራዎች የመያዣው አካል ናቸው « ሲራይረ ዖታለዕፈሰፅ ዲራዕረራ ፈሐፇቀ ዖሟዕፈፅው ሳጎዓ ይዶያታ ዖመያዖዣው ፅሳጳ ናውሪቹ ምረ መድ ዖፖነጎፖው ዳዳሥቻ ዋናው እዳ ወለድ » ተዋዋይ ወገኖቹ በውላቸው ላይ የተስማሙበት የወለድ መጠን ሩ መያዣው መድን የሚሆንለት ወለድ ግን የ ዓመት ብቻ ነው ፍሩ ከ ዓመት በላይ ለሆነው ወለድ መያዣው የቀዳሚነት መብት አይሰጠውም ቀዳሚነት መብት እንዲሰጠውም መስማማት አይችሉም ተዋዋዮች የተስማሙበት ወለድ ባይኖር እንኳን ንብረቱ ተይዞ እስከሚሸጥ ድረስ ህጉ ው የሚያስበው ወለድ ባለገንዘቡ የከፈለው የኢንሹራንስ ክፍያ ባለአዳው ዋናውን ግዴታ ባለመወጣቱ ባለገንዘቡ ንብረቱን ተከታትሎ ለማስያዝ እና ንብረቱን ለማሸጥ የወጣ ወጪ ያምርረሄሯ ውጨፇ። የንብረቱ መጥፋት ወይም መበላሸት ንብረቱን የገዛው ኛ ወገን ኃላፊ የሚሆነው ሆነ ብሎ ወይም በቸልተኛነት ድርጊትን የፈፀመው ከሆነና ይኸውም የተከናወነው ንብረቱ በፍርድ የማስያዝ ስነስርዓት ከተጀመረና ማስታወቂያ ከተላከ በኋላ ከሆነ ነው የተራ ባለገንዘብ መብት ሩ ንብረቱ ተሸጦ ሽያጩ ገንዘብ እዳውን ያልሸፈነ ከሆነ ባለገንዘቡ የተራ ባለገንዘብ መብት አለው ንብረቱን ባስያዘው ሰው ላይ ያለው ውጤት ንብረቱን የማስተላለፍ በድጋሚ በመያዣ መስጠት ገቢና ጥቅሙን መሰባሰብ ዐዕ ግዴታው ከንብረቱ ዋጋ አይበልጥም ሞርገጅ የሚፀናው ለ አመት ብቻ ነው « ለንብርቱ ዋጋ መጓደል ዛላፊ ነው በንብረቱ ላይ የተሰራ አዲስ ስራ እና ማሻሻያ የመያዣው አካል ነው አእዳው ካልተከፈለ ንብረቱ ተይዞ ይሸጣል የንብረቱን ዋጋ ከፍሎ መያዣውን የማስለቀቅ ክቨጠፀክበ መብት የለውም በኛ ወገኖች ላይ ያለው ውጤት ዋስትና በሌላቸው ባለገንዘቦች ላይ ያለው ውጤት ፍሩ እዳ መክፈያቸው ከደረሰ ንብረቱ ተያይዞ እንዲሸጥ ሊጠይቁ ይችላሉ ዋስትና ባላቸው ባለገንዘቦች ያለው ውጤት ሩ ብዙ መያዛ ያላቸው ባለገንዘቦች ሊኖሩ ይችላሉ ሩ የቀዳሚነት ቅደም ተከተላቸው መያዣቸውን ባስመዘገቡበት ቀን ይወስናል ሩ በአንድ ቀን ያስመዘገቡ ባለገንዘቦች መብት በአኩል ደረጃ ይታያል ሩ የቀደሚነት መብት ተራ በክፍያ ሊወስድ ይችላል ሀከከርበ ንብረቱ በተላለፈለት ሰው ላይ ያለው ውጤት ሀ የስራቸው የማሻሻያ ስራዎች ሩ ለስራቸው አዲስ ስራዎች ወይም ማሻሻያዎች ዋጋ እንዲከፈለው ሊጠይቅ ይችላል ሩ ዋጋውን ሊጠይቅ የሚችለው የሽያጩን ፁሁፍ ካስመዘገበ በኋላ ለሰራው ስራ ብቻ ነው ለ የንብረቱ መጥፋት ወይም መበላሸት ፍሩ ለንብረቱ መጥፋት እና መበላሸት መያዣ ገንዘብ ጠያቂዎች ኃላፊ አይሆንም ፍሩ ኃላፊነት የሚኖርበት ንብረቱ የጠፋው ወይም የተበላሸው የንብረቱ መያዝ ሥነሥርዓት ከተጀመረ በኋላ በርሱ አድራጎት እና ቸልተኛነት ከሆነ ነው ሐ መድን ህዉበባከቨ ሩፍ በመያዣ የተሰጠውን ንብረት የገዛ ሰው ንብረቱን እንዲለቅ ቢደረግ ሻጩን መድን እንዲሆነው ሊያስገድደው ክስ ሊያቀርብበት ይችላል ሩ ይህ ክስ ሊወገድ የሚችለው በሽያጩ ውል ላይ ሻጩ መድን የማይሆን መሆኑን በግልፅ ተመልክቶ ከሆነ ብቻ ነው ሩ ንብረቱ ያለዋጋ የተላለፈለት ሰውም የመድንነት ክሰ ሊያቀርብ ይችላል መ መተካት ሀከከ ፍሩ በማይንቀሳቀሰው ንብረት ላይ የመያዣ መብት በነበረው ሰው በመተካት በመብቱ ሊሰራበት ይችላል ሩ ንብረቱ በገንዘብ ጠያቂው ምክንያት የተሸጠበት ሰው ዋናውን ባለእዳ ለባለገንዘቡ ሊከፍለው የሚገባውን ያህል እንዲከፍለው የመጠየቅ መብት አለው ሠ ፈቅዶ ገንዘብ በመክፈል ንበረቱን ማስቀረት ህዐህበክዛቫሃ ርከ ረ ሩ ንብረቱ የተያዘበትን ሙሉ እዳ በመክፈል ንብረቱን ከመያዣው ነፃ ማድረግ ይችላል ሩ ክፍያው ያልደረሰውን እዳ ከፍሎ ንብረቱን ነፃ ማድረግ የሚቻለው የባለገንዘቡ ስምምነት ሲኖር ነው ፍሩ ንብረቱ በመያዣ ከተያዘ በኋላ ግን ስምምነቱ አስፈላጊ አይደለም ማስለቀቅ ዌጩጨዐከበፀከክ ፍሩየንብረቱን ትክክለኛ ዋጋ በመክፈል ንብረቱን ማስለቀቅ ይቻላል ሩንብረቱ መያዣ የሆነለትን እዳ በሙሉ መክፈል ሳያስፈልግ የንብረቱን ትክክለኛ ዋጋ ብቻ በመክፈል ንብረቱን ማስቀረት ቀሩይህን ለማድረግ የሁሉም የመያዣ መብት ያላቸው ባለገንዘቦች ስምምነት ያስፈልጋል ሩየማስለቀቅ መብት ተጠቃሚ የሆነው እዳው በግል የማይመለከተው ሰው ብቻ ነው ጥያቄው መቅረብ ያለበት የንብረቱ የመያዝ ትዕዛዝ ከመመዝገቡ በፊት ነው የማስለቀቁ ጥያቄ ከቀረበ በኋላ ጠያቂው ለሁለት ወር በጥያቄው ይገደዳል እስከ ሁለት ወር ባለገንዘቦቹ ተቃውሟቸውን ካላሳወቁ እንደተስማሙ ይቆጠራል ሩካለተስማሙ ንበረቱ በሐራጅ ይሸጣል ሸ እንደዋስ ስለመቆጠር በዘርከ ሀየከከሯ ሩ ገዢው ከባለገንዘቡ ጋር በሚኖረው ግንኙነት በጠቅላላ ውል ህግ ላይ ዋሱ ሊያነሳቸው የሚችላቸው መብቶች እንዲጠቀምባቸው መብት ተሰጥቶታል ፍሩ ባለገንዘቡ አዳውን ዋሱ እንዲከፍል ከማስገደዱ በፊት በዋናው ባለአዳ ዛሣብቶች ላይ እንዲከራከር ይፈቅድለታል ሩ ይህንኑ መብት መያዣ የተሰጠበትን ንብረት የገዛው ሰው እንዲገለገልበት ህጉ ፈቅዶለታል ሩ ንብረቱን አስይዞ ለሌላ ሰው ዋስ የሆነ ሰው መያዣ የተሰጠበትን የማይንቀሳቀስ ንብረት እንደገዛ ኛ ወገን ይቆጠራል የንግድ መደብር ሞርጌጅ የሚንቀሳቀስ ንብረት ላይ የሚመሰረት ሞርጌጅ ነው በንግድ ሕጉ በተለየ ሁኔታ ካልተመለከተ በቀር የሚተዳደረው በፍሕጉ ውስጥ በሚገኙ ድንጋጌዎች ነው ሕቁ የመያዣው አመሠራረት ከውል ወይም ከሕግ ይመሠረታል ፍሩ በፍርድ የሚቋቋም ለመሆኑ የንግድ ሕጉ አያመለክትም ከሕግ የሚመነጭ ሩ የንግደ መደብሩን ለሸጡ በነጋዴው መክሰር በወል ገንዘብ ጠያቂዎች ለሻጮች የተሰጠው የሕግ መያዣ መብት » በሸጡት የንግድ መደብር ላይ የመያዣ መብት አላቸው » የሸያጭ ውሉ እንዲፈርስ ለመጠየቅ ይችላሉ የመያዣ አመዘጋገብ » ሕጋዊ ውጤት እንዲኖረው ምዝገባ አስፈላጊ ነው ንሕቁ » ምዝገባው በተወሰነ ቀን ውስጥ መደረግ አለበት ቀ መያዣው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ሩ መያዣው ፀንቶ የሚቆየው ለ ዓመት ብቻ ነው ለባንክ በመያዣ የተሰጡ ንብረቶች በተወሰኑ የፍትሐ ብሔር እና የንግድ ሕጉ ድንጋጌዎች ላይ ማሻሻያ ተደርጓል የመጀመሪያውን ማሻሻያ ያደረገው አቁ ነው ይህ አዋጅ በፍሕቁ እና ዐዐ ላይ ማሻሻያ አድርጎባቸዋል ማሻሻያው የሚመለከተው ባንክ በመያዣ የተያዙ ንብረቶች አሻሻጥ ሥርዓትን ነው ባንክ በመያዣ የያዘውን ንብረት ወደ ፍቤት መምጣት ሳያስፈልገው ራሱ እንዲሸጥ የሚያደርገ ስምምነት ሕጋዊ ውጤት እንዲኖረው ተደርጓል አቁ ዐ ከፍ ሲል የተጠቀሰውን አዋጅ ሽሮታል በሌላ በኩል ደግሞ ለባንክ በመያዣ የተሰጠ የንግድ መደብርን በተመለከተ አቁ በንግድ ሕጉ ላይ ማሻሻያ አድርጓል እነዚህ አዋጆች ባንክ በመያዣ የያዛቸውን ንብረቶች ራሱ እንዲሸጥ የሚያደርገውን ስምምነት ህጋዊነት ይቀበላሉ አዋጆቹ ከመውጣታቸው በፊት እና በኋላ በመያዣ በተሰጡ ንብረቶች ላይ ልዩነት አድርገዋል አዋጆቹ ከመውጣታቸው በፊት ለባንክ በመያዣ የተሰጡ ንብረቶችን በተመለከተ ባንኩ የተዋዋዮቹ ስምምነት ሳያስፈልገው ንብረቶቹን ራሱ ለመሸጥ ህጉ መብት ሰጥቶታል አዋጆቹ ከወጡ በኋላ በመያዣ የተሰጡ ንብረቶችን በተመለከተ ራሱ ለመሸጥ ግን ስምምነት ያስፈልገዋል ባንኩ ንብረቶቹን ራሱ ለመሸጥ ስምምነት ካላደረገ የፍትሐብሔር ህጉ ድንጋጌዎች ተፈፃሚ ይሆናሉ በአሻሻጥ ሥርዓቱ ላይ ከተደረገው ለውጥ በቀር የፍትሐብሔር ህጉ ሆነ የንግድ ህጉ ድንጋጌዎች ተፈፃሚነት አላቸው ሞርጌጅ ቀሪ የሚሆንባቸው ምክንያቶች መያዣው የሚመለከተው የገንዘብ መጠየቂያ መብት ቀሪ ሲሆን የመያዣ መብት ያለው ገንዘብ ጠያቂ የመያዣው ይቅርብኝ ብሎ ሲተው ሠ ንብረቱ በሐራጅ ተሸጦ ገንዘቡ ለባለገንዘቦቹ ሲከፈል መያዣው እንዲለቀቅ ጥያቄ በቀረበበት ጊዜ የቀረበውን ገንዘብ ገንዘብ ጠያቂዎች ተቀብለው በባለመብቶቹ መካከል ገንዘቡን የተከፋፈሉ ከሆነ ሞርጌጁ ከተመዘገበ ዓመት ሲያልፈው መያዣ የተሰጠበት ንብረት ሲወድም በዋስትና ጉዳዮች ለመወያየት የቀረቡ መልመጃዎች ኃይሉ ኤጀርሳ ለአቶ ታደሰ ኃሚካኤል ብር አድጓል በውሉ ላይ በተገለፀው ቀን ገንዘቡን ባይመልሱ ብር መቀጫ ጨምረው ለመክፍል ተስማምቷዋል ስለዕዳው አፈፃፀምም አቶ ፀጋው ወሌ ዋስ በመሆን ግዴታ ገብተዋል ብር ከተከፈለ በኃላ ቀሪ ገንዘብ በጊዜው ባለመክፈሉ አቶ ኃይሉ ቀሪው ብር ከመቀጮ ገንዘብ ጋር ተደምሮ ይከፈለኝ በማለት ጠየቁ ዋሱ እኔ የተዋልኩት ለዋናው ዕዳ አፈፃፀም እንጂ ለመቀጫው አይደለም ስለሆነም በገደብ ገንዘቡ ላይ ልጠይቅ አይገባም ይላሉ ዋስ የሆነ ሰው እነዲህ ያለ መከራከሪያ ሊያነሳ ይችላል።

  • N.B. This Summary is Very Experimental!! based on the following scripts from:
    • https://github.com/millzon/textSummarizer-am
    • https://github.com/icoxfog417/awesome-text-summarization#motivation
Download Searchable PDF Download PDF

Advertisement
Bottom banner

Download options | Convert to Pdf | Reading List | Advertise on dirzon

© dirzon | Terms of Service | Privacy | About | Services | Contact