Detecting...

Please whitelist dirzon to continue.

or subscribe for ad-free contenct.

dirzon
  • تحويل إلى قوات الدفاع الشعبي
  • قائمة القراءة
  • مختصر
  • كتاب مسموع
  • بحث
  • تحميل
  • myzon
  • تسجيل الدخول
  • تسجيل
English  አማርኛ  Français  العربية
كتاب اليوم

የኢትዮጵያ_ኦርቶዶክስ_ቤተክርስትያን_ሥርአተ_ትምህርት.pdf


  • word cloud

የኢትዮጵያ_ኦርቶዶክስ_ቤተክርስትያን_ሥርአተ_ትምህርት.pdf
  • Extraction Summary

  • Cosine Similarity

ክፍል ሦስት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓተ ትምህርት ኢትዮጵያ ጥንታዊት ሀገር እንደ መሆኑዋ ጥንታዊ የሆነ ራሱን የቻለ ኢትዮጵያዊም የሆነውን ሁሉ የሚያኮራ ልዩ ጥናትንም የሚጠይቅ የራሱ የሆነ ጥንታዊና ብሔራዊ ሥርዓተ ትምህርት አላት ሀገራችን ኢትዮጵያ ቅድመ ልደተ ክርስቶስ በሕገ ኦሪት ድኀረ ልደተ ክርስቶስ በሕገ ወንጌል ያመነች ጥንታዊት ሀገር ከመሆንዋም በላይ በዚያው የዘመን ርዝመት መጠንም በሥነ ጽሕፈት የታወቀችና የሕዝቡዋ ሥልጣኔ ጀግንነቱ እምነቱና ባሕሉ ሌላውም ሁሉ እንዴት አንደ ሆነ ሊታወቅ የቻለው መጀመሪያ በሐውልቶች በጠፍጣፋ ድንጋዮችና በሸክላ ዕቃዎች ላይ በኋላም በብራና ተጽፈውና ተሥለው ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተላለፉ በመጡት የቅርጻ ቅርጽ የጽሑፍና የሥዕል ቅርሶች ነው ይህም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለረጅም ዘመናት የትምህርት ማዕከል ሆና ኀብረተ ሰቡን ስታገለግል ከመኖሩዋ የተነሣ ለሀገሪቱ ያተረፈችው የሥልጣኔ ውጤት መሆኑን የሚያሰገነዝብ ነው በሀገራችን ትምህርትና ሥነ ጽሕፈት የተጀመረው ከጥንት ዘመን ጀምሮ ለመሆኑ ብዙ ማስረጃዎች ይገኛሉ ለምሳሌ ያህል በአክሱም ሐውልቶች ላይ በሳባውያን በግሪክና በግዕዝ ቋንቋ የተጻፉት ጽሑፎች የዓይን ምስክሮች ናቸው የገናናው የኢትዮጳያ ንጉሠ ነገሥት የኢዛና ታሪክም በአክሱም ሐውልቶች ላይ በግዕዝ ቋንቋ ተጽፎ ይገኛል በሐውልቱ ላይ የሰፈሩት ቁም ነገሮችም ንጉሥ ስለ ፈጸማቸው ተጋድሎዎችና ስለ ተቀዳጀቸው ድሎች የሀገሪቱን ግዛት ለማስፋፋት የተደረገውን እንቅስቃሴና ሕዝቡ ለአምላኩ ያቀርብ የነበረውን ምሥጋ ያንጸባርቃል በአክሱም መንግሥተ ከላይ በተጠቀሰው ዓለም ዐቀፍና ብሔር ሀቀፍ ቋንቋዎች ትምህርትና ሥነ ጽሕፈት የዳበረ ስለ ነበር ሀገሪቱ የአንድ ቋንቋ ባለቤት ብቻ እንደ አልነበረች መገመት ይቻላል በግብረ ሐዋርያት ምቿ ላይ እንደ ተመዘገበው የንግሥት ሕንደኬ መልእክተኛ የነበረው ጃንደረባ ለጸሎት ወደ ኢየሩሳሌም ሔዶ በነበረበት ወቅት በሠረገላ እየተጓዘ ሳለ መጽሐፈ ኢሳይያስን በግዕዝ ቋንቋ ሲያነብ መገኘቱ ተጽፎዋል ይህመ ሁኔታ በሀገራችን ከጥንት ጀምሮ የማንበብና የመጻፍ ትምህርት ተስፋፍቶ አንደ ነበረ የሚያስረዳ ነው ሆኖም የትምህት መሠረት የሆነው ፊደልና የሥነ ጽሕፈት ስልት በመላ ኢትዮጳያ መስፋፋት ከጀመረበት ዘመን አንሥቶ መሆኑ ግልጽ ነው የኢትዮጵያ ኣርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአራተኛው መቶ ዓመት ብሔራዊት ቤተ ክርስቲያን ሆና ከተቋቋመችበት ጊዜ ጀምሮ ትምህርትን በኃላፊነት ስትመራ ኑራለች በተለይም የመጀመሪያው ጻጳስ ሆኖ የተሾመው ፍሬምናጦስ በላ ከሣቴ ብርሃን ሰላማ የተሰኘው ቀደም ብሎ ሲሠራበት የቆየውን ፊደል እንዲሻሻል ከማድረጉም በላይ አያሌ መጻሕፍትን ከጽርዕና ከዕብራይስጥ ቋንቋዎች ወደ ግዕዝ ቋንቋ እንዲተረጉሙ አድርጎአል ለግዕዝ ፊደላት መልክና ቅርጽን በመስጠት የሥነ ጽሕፈት አውቀት እንዲስፋፋ ያደረጉት በአክሱም ዘመነ መንግሥት የነበሩት የቤተ ክህነት ሊቃውንት መሆናቸው የታወቀ ነው በመሆኑም የኢተዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ኢትዮጵያ ሀገራችን የራስዋ የሆነ ፊደልና ትምህርት ባለቤት አንድትሆን በማድረግዋ ለሀሪቱና ለሕዝቡ ለሥልጣኔ አድገት ያበረከተችው አስተዋጽኦ ከፈተኛ ግምት ተሰጥቶታል በአፍሪቃ አህጉር ከሚገኙት ሀገሮች ሁሉ ከቀድሞ ጀምሮ የራስዋ ፊደል የነበራትና የአላት ኢትዮጵያ ብቻ በመሆንዋ በቤተ ክርስቲያኒቱ በተገኘው በረከትና ጸጋ መላው የሀገሪቱ ሕዝብ ሲመካበት ይኖራል ለማንኛውም ትምህርት ሥነ ጽሕፈትና ቋንቋ መሠረቱ ፊደል ስለሆነና መሠረታዊ ቋንቋ ታሪካዊ ተብሎ ሊሠየም የሚችለውም ፊደል ተቀርጾለት የሥን ጽሕፈት መሠረት በመሆን ማንኛውም ነገር ለትውልደ ትውልድ በጽሑፍ ተላልፎ ሲገኝ ነው የኢተዮጳያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የታሪክ ምንጭ እንደ መሆንዋ መጠን ለሀገሪቱ ቋንቋዎች መሠረት የሆነውን ጥንትም ሆነ አሁን የምንገለገልባቸውን ፊደላት ቀርጻና መልክ ሰጥታ ሕዝቡ እንዲጠቀምበት ሥነ ጽሕፈት እንዲስፋፋበት ታሪክ አንዲመዘገብበት ቤተ ክህነትና ቤተ መንግሥት እንዲገለገሉበት ማድረግዋ ለሀገሪቱና ለሕዝቡ ያላትን በአለውለታነት የበለጠ ገናና ያደርገዋል ብዙው የዓለም ክፍል ገና በጨለማ ውስጥ በነበረበትና የእውቀት ብልጭታ በአልፈነጠበቀት አንደ አሁኑ ሁሉ የሕትመት መኪና ከመፈልሰፉ በፊት የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ከበግና ከፍየል ቆዳ ብራና አውጥተው ሪምመው ዳምጠው አፍፈውና ከፍፈው እንደ ዛሬው ወረቀት በመስመርና በኅዳግ በግሌትና በዓምድ አስምረው አዘጋጅተው ቀለሙንም በልዩ ልዩ የቤት ዕቃዎች ጥላሸቶችን በመሰብሰብ ከተለያዩ ፅጸዋት ቅጠሎችም እያሳረሩ ደቁሰው ከእህል ሐሩርና ከሙጫ ጋር ቀላቅለው በማሸትና በማዋሐድ ደንበኛ የሆነና ዛሬ ለሕትመት አገልግሎት ብቁ ናቸው ተብለው ከሚታመንባቸው የቀለም ዓይነቶች የማያንሱ የተለያዩ ቀለማትን በመቀመም በሸምበቆ መቃ ብርዕ ቀርጸው በጉልህ ወይም በረቂቅ ለመጻፍ በሚያስችል ሁኔታ በሚፈልጉት ዓይነት አያዘጋጁ ከፊደል ጀምሮ ያሉትን ልዩ ልዩ የቤተ ክርስቲያንና የሀገር ታሪክ ሌሎችንም መጻሕፍት በየደረጃው በቁም ጽሕፈት ጽፈው በሚፈልጉት ቅርጽ ያዘጋጃሉ ቀጥሎም ከዘመናዊው የአጠራረዝ ስልት በማያንስ ሁኔታ እየጠረዙና እየደጎሱ ለተጠቃሚው ሕዝብ ያቀርባሉ በዚህ ሁኔታ አሁን እስከ አለንበት ዘመን ድረስ ያበረከቱት የትምህርትና የሥነ ጽሕፈት ጥበብ ከፍተኛ በመሆኑ ለኢትዮጵያ ሕዝብ የሥልጣኔ ዕድገት አኩሪ ታሪክ ነው የጥንቱ የብራና መጻሕፍት ገበታቸው ከዕንጨት ውስጣቸው ከብራና የተዘጋጁ ስለሚሆኑ ከጠንካራነታቸው የተነሣ በሺ ዓመታት የሚቆጠሩ ዘመናት ያሳለፉ በጥንካሬአቸው ወደር የሌላቸው በመጠን ትላልቅ የሆኑ ቅዱሳት መጻሕፍትና የታሪክ መጻሕፍት በአድባራትና ገዳማት ስለሚገኙ የጥንቱን የሥነ ጽሕፈት ዕድገት በዚህ መለካት ይቻላል አሁንም ሀገሪቱ ተወዳዳሪ የሌላቸው የብዙ ታሪካዊ ቅርሶች ባለቤት ሆና ልትገኝ የቻለችው በጽሑፍና በሥዕል አርት ከታወቁት በሥልጣኔ ከገፉት ቀደምት ሀገሮች አንደኛ ለመሆን የበቃችው በኢተዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ከፍተኛ ጥረትና ድካም ነው ሕዝቡም የዚህ ሥነ ጥበብ ተካፋይ በመሆን በሀገሩ በሃይማኖቱ በባህሉና በታሪኩ ሲኮራ ይኖር ዘንድ ታላቅ ዕድል አጋጥሞታል የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ብራና አውጥተው ቀለም አሽተው ብርፅ ቀርጸው ዓይናቸው እአስከሚፈዝ ጉልበታቸው እስከሚደነዝዝ የጻፉዋቸው የእምነት የቀኖና የሥነ ምግባር የታሪክ መጻሕፍት ጉልቄ መሳፍርት የላቸውም አነዚህ መጻሕፍት በየአብያተ ክርስቲያናቱ የሚገኙ ሲሆን ብዙዎቹ በሕገ ወጥ መንገድ ከሀገር ውጭ ወጥተው በተለያዩ አህጉር ዩኒቨርሲቲዎችና ቤተ መዘክሮች ይገኛሉ መጻሕፍቱ ከቀድሞ ጀምሮ የነበረውን የኢትዮጵያ ታሪክ የሥልጣኔ እድገት በጉልህ እያስረዱ ቢሆንም በሕገ ወጥ መንገድ ወጥተው በባዕድ ሀገር መቅረታቸው እጅግ ያሳዝናል ቤተ ክርስቲያኒቱ በየዘመኑ ማይምነትን ስትዋጋ ከኖረችባቸው ዘዴዎች አንዱ የሥነ ጽሕፈት ጥበብ ነው ምክንያቱም ገዳማቱንና አድባራቱን የትምህርት ማዕከል በማድረግ ከመንፈሳዊው ትምህርት ጋር መሠረታዊ የሆነውን የንባብና የሥነ ጽሕፈት ትምህርትን አጣምራ ስትሰጥ የኖረች በመሆንዋ ነው ይህም በአለፉት ዘመናት ይፈጸም የነበረ በቻ ሳይሆን አሁንም ያለማቋረጥ ሲሠራበትና ሲካፄድ የሚታይ ተግባር ነው በሀገራችን የዘመናዊውን ትምህርት አሁን በመምራት ላይ የሚገኘው የትምህርት ሚኒስቴር ከመቋቋሙ በፊት ለሦስት ሺህ ዘመናት ያህል ትምህርቱ ይካሄድ የነበረው በቤተ ክህነት አንደ ነበር ታሪክ ይመሰክራል ሊቃውንቱና ካህናቱ በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ብቻ ሳይወሰኑ ከሀገር መሪነት አስከ ተራ ሠራተኛነት ያለውን የመንግሥት ሥራ ያካሔዱ የነበሩት የቤተ ክርስቲያን ምሁራን እንደ ነበሩ የታወቀ ነው ከዚህም ጋር ፍትሐ ነገሥት የተማሩት በዳኝነትና በአስተዳደር አስፈላጊ በሆኑ ሥራዎች ሁሉ በመመደብ የመንግሥቱን ሥራ አመራር እያቃኑ ፍትሕ ርትዕ እንዲሰፍን እያደረጉ ሕዝቡን ሲያገለግሉ ከመኖራቸውም በላይ የሀገሪቱን ነጻነትና ደኀንነት በመጠበቅና በማስጠበቅ ረገድም የሚጠበቅባቸውን ግዳጅ አየተወጡ ለሕዝቡ መልካም አርአያና ምሳሌ ሆነው ኖረዋል በኛው መቶ ክፍለ ዘመን ትምህርት ሚኒስቴር በሀገሪቱ ተቋቁሞ ዘመናዊ ትምህርት ወደ ኢትዮጵያ ከገባ በኋላም ቢሆን የሚኒስቴሩን መቤት በማጠናከርና የትምህርቱን ሂደት በማካሔድ ከፍተኛ ሚና ይጫወቱ የነበሩት የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ናቸው ሊቃውንቱ በየትምህርት ቤቱ ተመድበው ለተማሪዎቹ ከመጀመሪያው መሠረታዊ ትምህርት እስከ ከፈተኛው ደረጃ ከማስተማር ጋር የሃይማኖትና የሥነ ምግባር ትምሀርትን ፍቅረ ሀገርን ለዘመኑ ትውለድ በማሳወቅ በአኃዝ የማይቆጠር አገልግሉት አበርክተዋል ዛሬም ቢሆን ዘመናት የማይቆጠርላቸው የሙዓለ ሕጻናት ትምህርት ቤቶች እንደ አሁኑ ከመቋቋማቸው አስቀድሞ ለዘመናዊ ትምህርት ቤቶች መጋቢዎች ሆነው አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩትና ያሉት እነዚሁ ጥንታውያን የቤተ ክርስቲያኒቱ የንባብ ትምህርት ቤቶች ናቸው በመላ ኢትዮጵያ ከቋሺ በላይ የአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ሲኖሩ አብዛኛዎቹ መንፈሳዊ ትምህርት ቤት ያላቸው ናቸው በዚህም መሠረት አሁንም የነበረው የቤተ ክርስቲያን ትምህርት በጥልቀትና በስፋት እየተሰጠ ይገኛል መምህራኑም ቀደም ሲል ከነበረው በበለጠ በንቃትና በትጋት እያስተማሩ ነው ከነበሩት የቤተ ክርስቲያን ትምህርት ጋር ዘመናዊው ትምህርትም እንዲሰጥ ጥረት እየተደረገ ነው በዚህ ዓይነት የተማሪው ቁጥር አጅግ ብዙ ስለሚሆን በቤተ ክርስቲያኒቱ የሚካሔደው መሠረታዊ የሆነው ጥንታዊ ትምህርት እየተስፋፋና እድገት እያሳየ መምጣቱን ስናይ በዚያው አንጻር ማይምነት እየቀነሰ የማያነቡ እንዲያነቡ የማይጽፉት እንዲጽፉ እየተደረገ ነው በዚህ መነሻነት ኀብረተሰቡ በተለይም የዘመኑ ትውልድ ስለግኝቱ ማለትም ስለ ፊደል አመጣጥ ብቻ ሳይሆን ስለ አስገኝዋ ስለ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውለታ ብዙ ያውቃል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርሰቲያን የምታስተምራቸው የትምህርት ዓየነቶች የሚከተሉት ናቸው ኛ ፊደልና አቡጊዳ ኛ ቁጥር አገዝ ኛ ንባብና ጽሕፈት ኛ ሥነ ፍጥረትና ሕገ አግዚአብሔር ኛ አምስቱ አዕማደ ምሥጢር ኛ ጸዋትወ ዜማ ኛ የግዕዝ ቋንቋና ቅኔ ቿኛ የመጻሕፍት ትርጓሜ ኛ አቡሻህር የቁጥር ትምህርት ኛ ሥዕል ሐረግና ቅርጻ ቅርጽ አርት ኛ ሀ ፊደል አንደ ቤተ ክርስቲያናችን ትምህርትና እምነት የፊደል ስልት ተጀመረ የሚባለው በሄኖስ ዘመን ነው ፄኖስ እግዚአብሔርን በማገልግል የታወቀ ደግ ስለ ነበር ለደግነቱ መታወቂያ ይሆነው ዘንድ በእግዚአብሔር ፈቃድ የሕግ መሣሪያ የሚሆነው ፊደል በጻፍጸፈ ሰማይ ተገልጦ ታይቶታል ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ፊደልን ለሥነ ጽሕፈት በር መክፈቻ በማድረግ ተጠቅሞበታል ስሙንም ጽሑፍ ለማለት ፊደል ብሉታል የግእዝ ፊደላት ቁጥራቸው ነው የግአዝ ፊደላችን ጥንታውያን መጽሐፍቶቻችን ሁሉ የተጻፉበት ብዙ ድርሰቶች የተደረሱበት ነው የግእዝ ፊደል እስከ ሳብዕ አልነበረውም በግእዙ ብቻ ይነገርና ይጻፍ ነበር ለምሳሌ ብርሃኑ ለማለት በረሀነ ጥበቡ ለማለት ጠበበ ይል ነበር ማለት ነው ይህ አነጋገርና አጻጻፍ እምነተ ክርስትና ወደ ኢትዮጵያ እስከ ገባ ድረስ ያገለግል እንደነበር ከታሪክ ማኀደር መረዳት ይቻላል ከዚህ የተነሣ በአባ ሰላማ ከሣቴ ብርፃነን አመራር ሰጭነት የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት የግአዝን ፊደል በሁለት ወገን በመከፈል ሕዝቡ እንዲገለገልበት በማድረጋቸው ለዘለዓለም የሚያኮራቸውና የሚያስመሰግናቸው ነው አንደኛው ክፍል ቀደም ሲል የሕዝቡ መገልገያ የነበረው በ «አ» ጀምሮ እስከ «ፐ» አበገደ በመባል ይታወቅ የነበረው የጥንቱ የኢተዮጵያ ፊደል ሲሆን ሁለተኛው ፊደል ደገሞ ለአጠቃቀም በሚያመች ሁኔታ በሊቃውንቱ ተሻሽሎ እስከ ዛሬ እየተሠራበት ያለውና መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚጠቀምበት ከሀፐ ያለው ፊደል ነው እነዚህ ፊደላት እንደ ዕብራይስጡ ፊደል በእግራቸው በወገባቸውና በራሳቸው ልዩ ልዩ ቅጥያዎችና ምልክቶች በማድረግ ካዕብ ሣልስ ራብዕ ሐምስ ሳድስ ሳብዕ በሚል የድምጽ መስጫና ነቁጦች አናጋሪ ዋየል አንዲነበቡ ሆነው የተዘጋጁ ናቸው የግዕዝ ፊደል ግዕዝ የተባለበት ምክነያት ቀደም ሲል እንደ ተናገርነው በአንደኛው ፊደል ብቻ ይነገር ሰለነበር ነው አስከ ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በእነዚህ የግዕዝ ፊደላት ብቻ ሲሠራ ኖሮአል አየዋለ እያደረ የአማርኛ ቋንቋ ሲስፋፋ የአማርኛ ፊደላት ሊፈጠሩና ከግዕዙ ፊደላት ጋር አብረው የአማርኛው ጽሑፍ ሊጻፍባቸው ቻለ የአማርኛ ፊደላት የተባሉበትም ምክንያት በግፅዝ መጻሕፍት የማይገኙና በጥንታዊ አነጋገርም የማይገቡ ስለ ነበርና በኋላ ዘመን የገቡ ስለሆነ ነው ቁጥራቸው ነው በተጨማሪ የግዕዝና የአማርኛ ፊደላት ዲቃሎች የሚባሉ ሌሎች ፊደላት አሉ አነዚህም የግፅዝ ፈደላት ዲቃሎች የሚባሉ ቁጥራቸው ሲሆን የአማርኛ ፊደላት ዲቃሎች የሚባሉት ደግሞ ቁጥራቸው ነው ለ አቡጊዳ አቡጊዳ እንደ አሁኑ ፊደል የቁጥር ትምህርት አለው ማለትም የፊደሎች ቅርጽ በተለያየ ቦታ ሲገኝ ተማሪው እንዴት ሊለያቸው እንደሚችል ሆኖ የተዘጋጀ ስለሆነ ፊደሎቹን አንድ በአንድ እየቆጠረ ከላይ ወደ ታች ከታች ወደ ላይ ከቀኝ ወደ ግራ ከግራ ወደ ቀኝ እያለ እየመላለሰ ይማራል ኛ ቁጥር አኃዝ በኢትዮጵያ የቁጥር ስልት አጠቃቀም በቅርብ ጊዜ የተጀመረ ሳይሆን ኢትዮጵያ ፊደልንና ጽሑፍን ማስተማር ከጀመረችበት ጊዜ ጀምሮ ሲሠራበት የኖረ ነው የሌሎች ዓለማት ሕዝቦች አብዛኛዎቹ የዓረብኛ የቁጥር ስልት ሲጠቀሙ የኢትዮጵያ ሕዝብ ግን የራሱ በሆነ ፊደል ብቻ ሳይሆን የራሱ በሆነ አኀዝም ቁጥር ሲጠቀም የኖረና አሁንም የሚሠራበት ነው ሕጻናትም ይሀንን የአኀዝ ቁጥር ትምህርት ከፊደሉ ጋር አብረው ይማሩታል ኛ ንባብና ጽሕፈት ሀ የንባብ ትምህርት የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የንባብን ትምህርት ለማስተማር የምትጠቀምባቸው መጻሕፍት ኛ ፊደል ሐዋርያ ኛ መልእክተ ዮሐንስ ኛ ገበታ ሐዋርያ መልእክታተ ሐዋርያት አርጋኖን ውዳሴ አምላክ ኛ ወንጌለ ዮሐንስ ፀኛ መጻሕፍተ ሰሎሞን ኛ መጽሐፈ ሲራክ ሄኛ መዝሙረ ዳዊት ናቸው ፊደለ ሐዋርያና ገበታ ሐዋርያ የተባሉት የትምህርት ዓይነቶች ከአቡጊዳ ቀጥለው የሚሰጡ የትምህርት ዓይነቶች ናቸው ተማሪው እነርሱን የዘር መለያ የንባብ መማሪያ አርጎ ከፊደል ቆጠራ አንደ ወጣ የሚጠቀምባቸው የመማሪያ ዘዴዎች ናቸው ፊደለ ሐዋርያና ገበታ ሐዋርያ የተባሉት ራሳቸውን የቻሉ መጻሕፍት ስለ ሆኑ መልካቸውን ቅርጻቸውን በመለየት ተማሪው ጠንቅቆ ይቆጥራል ያግዛል ውርድ ንባበም ያነብባል ተማሪው በደንብ የፊደላትን ዘር መለየቱ ሲረጋገጥ ደግሞ ቁም ንባብ ያነብባል «ቅድመ መሐርዎሙ ለውሉ ድከሙ መጽሐፈ ሰሎሞን ወሲራክ ወመዘሙረ ዳዊት ለልጆቻችሁ አስቀድማችሁ የሰሎሞንና ሲራክን አንዲሁም የዳዊት መዝሙርን አስተምሩአቸው» ሲል ዮሐንስ አፈወርቅ የተናገረውን መሠረት በማድረግም በተከታታይ እነዚህን መጻሕፍት አንዲያነቡ ይደረጋል ለ የጽሕፈት ትምህርት ጽሕፈት ለኢተዮጵያውያን ከፍ ያለ ሙያ ትልቅ ቁም ነገር ነው ተማሪውም የፊደል ቆጠራ ትምህርት እንደ ጀመረ ከፊደሉ ቁጥር ጋር ጽሕፈቱንም አብሮ ያጠናል የዘመኑን ትውልድ ወደ አድናቆት የመለሱትን ታላላቅ የብራና መጻሕፍት በቁም ጽሕፈት እየጻፉ ያቆዩን በዚህ መልክ የተማሩ ሁሉ ናቸው ብዙዎች መምህራን ከትምህርቱ አንዱ የቁም ጽሕፈት ስለ ሆነ ደረጃ ሰጥተው የፊደሎችን ቅርጽ በጠበቀ የቁም ጽሕፈት ትምህርትን ለተማሪዎቻቸው ያስተምራሉ የአጻጻፉ ሥርዓትም ቀጥሎ እንደ ተገለጠው ነው አርእስት አርእስት የሚባለው የመጽሐፉ ራስ ያልተጻፈበት ቦታ ነው ኀዳግ የሚባለውም በግርጌ ያለው ማለትም የልተጳፈበት ባዶ ቦታ ሲሆን ትርጉሙም ያልተጻፈበት ወይም የተተወ ማለት ነው ግሌት ግሌት የሚባለው ወደ መጨረሻው ያለው ያልተጻፈበት ቦታ ነው ኀላፍ ሁለተኛ ቅጠል የሌለው አኩሌታ ቅጽ ነው ሐውልት ሐውልት የሚባለው በሁለቱ ዐምዶች መካከል የማይጻፍበት ቦታ ነው ሄ ዓምድ ዓምድ የሚባለው በሐውልት ተከፍሎ ጽሑፉ ያረፈበት ነው ሲራክ ሲራክ ወስፌው ያለፈበት ሰምበሩ ወይም መስመሩ ነው ምስማክ ምስማክ ዕጥፋቱን አንደ ወንዝ አማክሎ ወደ ጥራዝ ያለው ማዶና ማዶው ነው ማንጸን ማኀጸን በፊደል መካከል የሚገኘው ቦታ ነው ሕጽን ሕጽን በፊደሉ ውስጥ የሚገኘው ክፍት ቦታ ነው መስመር መስመር ቀለም የሚወድቅበት ተላላው ነው ቀለም ጎኀርወት ቅርጽ ማለት ነው ልክ ንባብ ልክ ንባብ ቃል ማለት ነው ይህንንም የመሰሉ ሌሎች ይገኛሉ መ። ቿ። አእነደሁም ጽሕፈቱ ሲጻፍ ሥርዓተ ፊደልን በመጠበቅ ነው ለምሳሌ ሀሌታው ሀ ሐመሩ ሐ ብዙኃኑ ኀ ንጉሥ ሠ አሳቱ ሰ አልፋው አ ዓየኑ ዐ ጸሎቱ ጸ ፀሐዩ ፀ እንዲሁም ሌሎቹ ሆቴያት ሳይደባለቁ ተጠብቀው በየአገባባቸው ይጻፋሉ በተለይም ከፊደሎቹ ውስጥ ግፅዙና ራብዑ ቅርጻቸው ልዩ ይሁን እንጂ በድምጽ ስለሚመሳሰሉ ለማያውቃቸው ለይቶ ለመጻፍ ያስቸግራሉ ለምሳሌ ሀ ግዕዝና ፃ ራብዕ ሐ ግዕዝና ሓ ራብዕ ኀ ግዕዝና ኃ ራብዕ እንዲሁም አ ግዕዝና ኣ ራብዕ ዐ ግዕዝና ዓ ራብዕ እነዚህ በጥንቃቄ ካልተጻፉ ትርጉሙንና ምሥጢሩን ስለሚያፋልሱ መምህራኑ በከፈተኛ ጥንቃቄ ባሕርያቸውን ጠብቀው ያስተምሩዋቸዋል ዜማ የቃሉ ትርጓሜ ዜማ ማለት ስልት ያለው ጩኸት ወይም ድምጽ ማለት ሲሆን በሌላ መልኩ ደግሞ ዜማ ማለት ለጆሮ የማያስደስት ለስሜትም ትርጉም የሚሰጥ ድምጽ ነው ዜማ ማለት በልዩ ሕብር የተደራጀ ወይም የተቀነባበረ ድምጽ ማለት ነው ማንኛውም ድምጽ በከፍተኛና በዝቅተኛ የድምፅ መያያዝ መካከል ቃና አለው ቃናው ግልጽና ለመለየት ቀላል ከሆነ ድምፁ አንደ ዜማው በዜማ ምልክት ወይም በኖታ ሊገለጽ ይችላል ሰለዚህ ዜማ ሲባል በአጠቃላይ የምስጋና መዝሙር የደስታ ድምጽ ማለትም ነው ዜማ ከመላእክት ጋር አብሮ የተገኘ ቀዳማዊ ነው ይህንነም በማስመለከት ራሱ ቅዱስ ያሬድ «ቀዳሚ ዜማ ዘሰማዕኩ በሰማይ ዘ መላእክት ግናይ» በማለት ቀዳማዊነቱን አርያም በተባለው ድርሰቱ ገልጦ አስረድቶአል ዜማ ቀደማዊ ብቻ ሳይሆን ታላቅም ነው ይህንንም ቅዱስ ያሬድ ሲያስረዳ ዓቢይ ዜማ ተሰምህ በሰማይ ዘመላእክት ግናይ አንዘ የዓርግ ወልድ ዲበ መንበሩ ከጭሉሙ መላእክት ትንሣኤሁ ዘመሩ» ሲል ገልጾታል ዜማ በኢትዮጵያችን በተለይም በመንፈሳዊ ክፍል ማለትም በቤተ ክርስቲያን ጽኑ መሠረት ይዞ ትውልድ የሚከተለው መደበኛ ትምህርት ለመሆን የበቃው ዘመነ መንግሥት ሲሆን ደራሲውም ሊቁ ቅዱስ ያሬድ ነው ዜማ ሰውም ሆነ እንስሳ ያለ አስተማሪ በሕገ ተፈጥሮ የሚያገኘው የስሜት መግለጫ ሲሆን በተለይ ሰው ግን ዜማን ከዕለት ወደ ዕለት እያሻሻለ ከልዩ ልዩ መሣሪያዎች ጋር እያስማማ ለኀዘንም ሆነ ለደስታ ስሜቱን ይገልጽበታል ዜማ ከተፈጥሮ ጋር የተያያዘና የተሰናሰለ በመሆኑ ዜማ የሌለው ሕዘብ በዓለም ላይ አይኖርም ዜማ ቤተ ክርስቲያንን ከማገልገሉም በላይ ለመዝሙር ለደስታና ለኀዘን ለቀረርቶ ለዘፈን ለአእንጉርጉሮ በአጠቃላይ እነዚህን ለመሳሰሉትና ዓለም ለሚፈልጋቸው የስሜት መግለጫዎች ሁሉ ጠቃሚ ነው በቤተ ክርስቲያናችን ዜማን መንፈሳዊና ዓለማዊ ብሎ ከሁለት መክፈል ይቻላል ከነዚህ ሁለት ክፍሎች የስም ልዩነት ያላቸውን ያህል በአገልግሎትና በአፈጻጸም በኩልም ልዩነት አላቸው ይኸውም አደሚታወቀው መንፈሳዊ ዜማ የሚባለው ካህናት በቤተ ክርስቲያን አንዳንድ ጊዜም ከቤተ ክርስቲያን ውጭ በተለያዩ ዕለታትና በዓላት በመዓልትም ሆነ በሌሊት በሠርክም ሆነ በነግሕ ሥርዓትና መልክ በአለው ሁኔታ እየተሰበሰቡ አግዚአብሔርን በማመስገን የሚያዜሙት ወይም የሚዘምሩት ዜማ ነው በመሆኑም በምስጋና ቃለ አግዚአብሔርን አንደሚያመሰግኑት መላአክት እንሁን በየማዕርጋቸውና በየማኀበራቸው በየነገዳቸውና በየሠራዊታቸው በየስማቸው በየቁጥራቸውም የሚጋርዱ አሉ የሚከቡም አሉ በዜማ የሚያመሰግኑም አሉ የሚዘምሩም አሉ» በማለት ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋረያዊ የተናገረውን መጥቀሱ ይበቃል መጽሐፈ ቅዳሴ አተቁጥርኛቹ ይህ አገላለጽ የሚያመለክተው ዜማ በምድራውያን ፍጡራን ብቻ ሳይሆን በሰማውያን መላእክትም ዘንድ አንኳ ሳይቀር ምን ያህል ክብርና ተወዳጅነት ያለው መሆኑን ነው ዓለማዊ ወይም ሕዘባዊ ዜማ የሚባለው ደግሞ ሕዝቡ እንደእየቋንቋውና እንደ አየባህሉ በኀብረትም ሆነ በተናጠል ቡድን እየአቋቋመ በተለያዩ ፅለታትና በዓላት ለምሳሌ በሠርግ ቤት በአጨዳ በውቂያና በመሳሰሉት ሁሉ የሚያዜመው ዜማ ወይም ዘፈን ነው በመንፈሳዊውም ሆነ በዓለማዊ ለዜማ አገልግሎት የሚውሉት መሣሪያዎች ከዚህ የሚከተሉት ናቸው ፅኛ ከበሮ ኛ ከራር ኛ ጸናጽል ቿኛ በና ኛ መቋሚያ ኛ ዋሽንት ፀኛ መሰንቆ ኛ እንዚራ ኛ እምቢልታ ፅኛ አረጋኖን በመባል የታወቃሉ ኛ መለከት በአጭሩ ከዚህ በላይ የተጠቀሱት ዐበይት መሣሪያዎች ሁሉ የኢተዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንትና ኀብረተ ሰብእ የፈጠራ ውጤቶች ስለ ሆኑ ቤተ ክርስቲያንንም ሆነ ኀብረተ ሰቡን የሚያኩሩ ናቸው ሀ የዜማ ምልከቶች ኢትዮጵያ ሀገራችን የቤተ ክርስቲያን ዜማዎችን በምልክት ኖታ እነዲዜሙ ያደረገች ጥንታዊትና ታሪካዊት ሀገር መሆንዋን የዓለም ሊቃውንት ይመሰክራሉ ሥራውም ራሱ ምስክር ነው በመሠረቱ ምልክት ሲባል የአንድ ነገር ማረጋገጫ ማስረጃ ማወቂያና ማሳወቂያ መገንዘብያ ማለት ነው በዚህ መሠረት ምልክት የሚለው ቃል በቤተ ክርስቲያን ትምህርት ቤት ብቻ ሳለይሆን በሌላም በተለያዩ ነገሮች ሊያገለግል ይችላል ማለትም በዜማ በትርጓሜ በንባብና በመሳሰሉት ሁሉ ማለት ነው በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የሥነ ጽሕፈት ስልት መሠረት የዜማ ምልክት የትርጓሜ ምልክት የንባብ ምልከት አሁን በዘመናችንም የአቋቋምና የወረብ ምልክት እየተባለ ይጠራል በመሆኑም ዜማውን በምልክት ምልክቱን በዜማው በመወሰን የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የምትገለገልበት ለእግዜአብሔር ምስጋና የሚቀርብበት ለደስታም ለኀዘንም መግለጫ የሆነ ራሱን የቻለ ምልክት ያለው ትክክለኛ መንገድን የተከተለ መሆኑን የምንረዳበትና የምናስረዳበት የጥበብ ጥበብ ነው የዜማ ዓይነቶች በቤተ ክርስቲያናችን የዜማ ዓይነቶች ሦስት ናቸው አነሱም ግዕዝ ዕዝል አራራይ ይባላሉ ምሳሌያቸውም ግዕዝ በአብ ዕዝል በወልድ አራራይ በመንፈስ ቅዱስ ይመሰላሉ ግዕዝ ፅኑፅ ማለት ነው በአብ የተመሰለበት ጸኑዐ ባሕርይ ለማለት ፅዝል ማለት ብርቱ ማለት ነው በወልድ የተመሰለበት መከራ ለመቀበል የበረታ ለማለት ነው አራራት ማለት አራጎኀራጊ ወይም የሚያራራ ማለት ነው በንመፈስ ቅዱስ የተመሰለበት መንፈስ ቅዱስን የሰውን ልቡና የሚያራራ ለማለት ነው ጸዋትወ ዜማ ጸዋትወ ዜማ የዜማ ወገኖች አምስት ናቸው እነርሱም ኛ ድጓ ጾመ ድጓ ኛ ምዕራፍ ኛ ዝማሬ ኛ መዋሥዕት ኛ ቅዳሴ ናቸው ኛ ድጓ ድጓ የሚለው ቃል የዜማ መጽሐፍ ስም ነው አሱም ቅዱስ ያሬድ በሻዛ ዓም የደረሰውና ያዜመው የዘመረው ነው ድጓ ዮሐንስ አስተምህሮ ፋሲካ ተብሎ በሦስት ይከፈላል ጾመ ድጓ ጾመ ድጓ ከድጓው አንድ ክፍል የሆነ ለጾም ወራት አገልግሎት የተቀመረ ነው መጀመሪያ በድጓው ክፍል በአስተምህሮ ይገኝ ነበር ነገር ንግ በሀኛው መቶ ክፍለ ዘመን በደብረ ነጎድጓድና በደብረ አግዚአብሔር የነበሩ ሊቃውንት አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫን መሪ በማድረግ ከአስተምህሮው ድጓ አውጥተው ራሱን የቻለ ክፍል እንደ አደረጉት ይነገራል ጾመ ድጓ በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን በዓቢይ ጾም ወራት ሀ በሰዓት ለ በዕለት ጠ በሳምንት የሚጸለይና የሚዘመር ሁኖ የተዘጋጀ ነው ኛ ምዕራፍ የምዕራፈ ዜማ ትምህርት የዘወትርና የጾም ምዕራፍ ተብሉ በሁለት ክፍል ይከፈላል ሀ የዘወትር ምዕራፍ የዘወትር ምዕራፍ የሚባለው ዓመቱን ሳይጠብቅ በዓመቱ ውስጥ ባሉት ሳምንታትና በዓላት ወቅቱን እየጠበቀ በአገልግሎት ላይ የሚውል ነው ለ የጾም ምዕራፍ የጾም ምዕራፍ የሚባለው ደግሞ በጾመ አርብዐና በአንዳንድ የምሕላ ቀኖች የሚዘመር ነው የሁለቱም ክፍሎች ዋና መሠረታቸው የዳዊት መዝሙርና ድጓ ወይም ጾመ ድጓ ነው የትምህርት አሰጣጣቸው እንደ ድጓው ወይም እንደ ዝማሬውና እንደ መዋሥዕቱ በመጽሐፍ ሳይሆን በቃል የሚጠኑ ናቸው ኛ ዝማሬ ዝማሬ ማለት መዝሙር አዘማመር ዝመራ በዜማ የሚቀርብ ማኀበራዊ ምሥጋናና ጸሎት ነው ይህም ከአምስቱ ጸዋትወ ዜማ አንዱ የሆነ በቅዳሴ ጊዜ የሚቃኝ የሚዜም የሚዘመር የጸሎት ቅዳሴውን ምሥጢርና ዓላማ ተከትሎ የሚሔድ ነው ይኸው ጸሎት ቅዳሴው ግአዝ ሲሆን በግእዝ ዕዝል ሲሆን በዕዝል የሚዘመር ነው ኛ መዋሥዕት መዋሥዕት ለዕለት ሙት ፍትሐትና ለሙት ዓመታት ለመሳሰሉትም ሁሉ የሚጸለይ ጸሎት ነው ከዚህ በስተቀር መዋሥዕት በበዓለ ሰንበት በጌታችን በአመቤታችን በጻድቃንና በሰማዕታት በመሳሰሉት በዓላት ሁሉ በዜማ ይጸለያል መዋሥዕት ከዝማሬ ጋር የተደረሰ የታላቁ ኢትዮጵያዊ ሊቅ የቅዱስ ያሬድ ድርሰት ነው በትምህርትም ጊዜ ከዝማሬው በአለመለየት መምህራኑ ለተማሪዎች አብረው ያስተምሩታል የማስመስከሪያው ቦታም በደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት በጋይንት አውራጃ ልዩ ስሙ ዙር አባ በተባለው ገዳም ነው ኛ ቅዳሴ የቅዳሴ መጻሕፍት በየጊዜው የተደረሱና ደራሲያኑ ልዩ ልዩ ሊቃውንት ሲሆኑ ዜማውን ያቀናበረው አንድም የደረሰው ቅዱስ ያሬድ ነው ስለ ቅዳሴ ትምህርት ከቅዱስ ያሬድ ጀምሮ በጥንት ዘመን ከዝማሬ መዋስዕት ጋር በዙር አባ ያስተምሩት ያስመሰክሩትም እንደ ነበር ይተረካል እየቆየ ግን የቅዳሴ ምስከር ቦታ ተብሎ ይነገርለት የነበረው በታሪክም ጎልቶ እስከ አሁን ድረስ የሚታወቀው ስለልኩላ የሚባለው ገዳም ነው በቅርቡ በአ ምኒልክ ዘመነ መንግሥት ግን በተጨማሪ ደብረ ዓባይ የቅዳሴ ምስከር ቦታ ሆኖአል በመጀመሪያ ደብረ ዓባይን የቅዳሴ ምስከር ቦታ ያስደረጉት መምህር ገብረ ኢየሱስ የተባሉ መምህር ናቸው እሳቸው ግን ለመጀመሪያ ጊዜ ስለልኩላ ተምረው ያስመረቁም በዚያው ነበር ነገር ግን በጣም ድምጻዊ ስለ ነበሩ እራሳቸው ወዝ አየሰጡት ዜማውን እያስረዘሙ በማዜማቸው ዜማቸው ተወዳጅ ሆነ ወደ ደብረ ዓባይም ገብተው ወምበር ዘረጉ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ መምህር ንብረ ኢየሱስ የቅዳሴ ምስከር ደብረ ዓባይም የምስከር ቦታ ለመሆን በቁ የቅዳሴ ዜማ ወዙ ለዛው እንደ ዝማሬና መዋስዕት ለየት ያለና ረዘም ያለ ቢሆንም ምልክቱ እንደ ድጓው ነው ቅዱስ ያሬድ በዜማ የደረሳቸው የኢትዮጵያ ቅዳሴዎች ናቸው እነዚህም ጳኛ ና ኛ ፀኛ ኛ ኛ ኛ ኛ ኛ ኛ ኛ ኛ ኛ ፀኛ ቅዳሴ ሐዋርያት ቅዳሴ አግዚእ ቅዳሴ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ቅዳሴ ሕርያቆስ ቅዳሴ ማርያም ቅዳሴ ሠለስቱ ምዕት ቅዳሴ አትናቴዎስ ቅዳሴ ባስልዮስ ቅዳሴ ጎርጎርዮስ አኀወ ባስልዮስ ቅዳሴ ኤሏፋንዮስ ቅዳሴ ዮሐንስ አፈወርቅ ቅዳሴ ቄርሎስ ቅዳሴ ዲዮስቆሮስ ቅዳሴ ያዕቆብ ዘሥሩግ ቀዳሴ ጎርጎርዮስ ዘአርማንያ ናቸው ከነዚህ ፍሬ ቅዳሴያት ሌላ ከፍሬ ቅዳሴ በፊት የሚጸለዩ ኛ ሥርዓተ ቅዳሴ ኛ ኪዳን ኛ ሊጦን ኛ መስተብዮዕ ኛ ዘይነግሥ የተባሉ በዜማ የሚጸለዩ ድርሰቶች ሁሉ ዜማቸው የተደረሰው በቅዱስ ያሬድ ነው እነዚሁም ቅዱስ ያሬድ በትምህርት የወለዳቸው አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ የተባሉት ታላቅ ሊቅ በንባብና በዜማ የደረሱት በሌሊትና በመዓልት የሚጸለይ ሰዓታት የተባለ ድርሰት አለ የዚህም ድርሰት የዜማ ላህይ ለየት ያለ ቢሆንም ምልክቱ እንደ ድጓና እንደ ቅዳሴ ነው የቅዱስ ያሬድ የዜማ ዘር ድርሰት ምነጮች ሀ ብሉይ ኪዳን ለ ሐዲስ ኪዳን ሐ መጻሕፍተ ሊቃውንት መ መጻሕፍተ መነኩሳት ሰ ድርሳናትና ሌሎችም ናቸው ቅዱስ ያሬድ ዜማውን ሊደርስ የቻለው ከዚህ በላይ የተጠቀሱትን መጻሕፍት መሠረት በማድረግ ንባቡን ለዜማው እንደሚስማማ በማቃናትና መሠረት አሳቡን ሳይለቅ ንባቡ ከነምሥጢሩ በመንፈስ ቅዱስ ተገልጾለት እንጂ በዘፈቀደ ከልቡ አንቅቶ ከአፉ አውጥቶ አልተናገረውም አቋቋም ከቁም ዜማ የተለየ ሆኖ በመቋሚያ በጸናጽልና በከበሮ እግዚአብሔር የሚመሰገንበት የማሕሌት ዜማ ነው የቤተ ክርስቲያናችን የማኅሌት ሥነ ሥርዓት ጥንታዊ ሲሆን የተጀመረው በቅዱስ ያሬድ ነው ጀማሪውም አሱ ራሱ ነው አሱ በጸናጽል እና በከበሮ ምሥጋና ለእግዚአብሔር ያቀርብና ማኀሌትም ይቆም እንደ ነበር በታሪክም በሥዕልም ሁል ጊዜ ይገለጻል የግዕዝ ቋንቋና ቅኔ ሀ የግዕዝ ቋንቋ ከባቢሎን ግንብ መፍረስ በጊላ አንድ የነበረ ፊደልና ቋንቋ ሲለያይ የሰዎች ቋንቋ በየነገዳቸውና በየስማቸው ተሰይሞዋል በሀገራችንም ከግዕዝ ቋንቋ በፊት የሳባንና ሳባን የመሳሰሉ ቋንቋዎች እንደ ነበሩ ይታወቃል ይኸውም በየዋሻውና በየድንጋዩ በየሐውልቱም ላይ ተጽፎ ይገኛል የግፅዝ ቋንቋ ግን በአብርፃም የልጅ ልጅ በያዕቆብ ዘመን በባብዕል መንደብ ወደ ኢትዮጵያ የገቡት የሴማውያን ነገደ ዮቅጥን ቋንቋ ነው ግዕዝ ማለት አንድ ጥንት መጀመሪያ ማለት ነው መጀመሪያነቱም ከካዕብ እስከ ሳብፅ ላሉት ዋየሎች ሲሆን በቋንቋ መጀመሪያነቱ ደግሞ በባቢሎን መበታተን ምክንያት ከተፈጠሩት በብዙ ከፍለ ዓለማት የሚገኘው የሰው ልጅ ከሚጠቀምባቸው ልዩ ልዩ ሴማዊ ቋንቋዎች የተለየ የመጀመሪያ ሰው አዳም ይናገርበት የነበረ ጥንታዊ ቋንቋ በመሆኑ ነው ሴማውያን ከነገደ ካም ከኩሽ ልጆች አየተጋቡና አየተዋለዱ የኹሽን መንግሥት ወርሰው አነሱ አግአዝያን ተብለው ሀገሪቱንም ብሔረ አግዓዚት አሰኝተው ሲኖሩ ግዕዝ ቋንቋቸው እያበበ አስከ ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ድረስ ሕዝባዊ ወይም ብሔራዊ ቋንቋ ሆኖ ቆይቷል በዚህ ዘመን የአማርኛ ቋንቋ ብቅ ብሎአል ቢሆንም አማርኛ እስከ አሁን ድረስ የሚነጋገሩበት ወይም የዘር መነጋገሪያ ቋንቋ እንጂ በቤተ መንግሥትና በቤተ ክርስቲያን የሥራ ቋንቋ አልነበረም ለምሳሌ በቤተ ክርስቲያን የሚጸለይበት እግዚአብሔር የሚመሰገንበት በአጠቃላይ ሥርዓተ አምልኮት የሚፈጸመበት ሁለተኛም በቤተ መንግሥት የሰው ጉዳይ የሚታይበት የሚተችበት የሚፈረድበት የነገሥታቱ ታሪክ የሚመዘገብበት አልነበረም ስለዚህ ነው በቤተ ክርስቲያናችን ተጠብቀው ያሉት በውጭ ሀገርም ሳይቀር የሚገኙት የፃይማኖት የሥርዓተ አምልኮት የትምህርትና የታሪክ መጻሕፍታችን በግዕዝ ቋንቋ ተጽፈው የሚገኙት አሁን ግፅዝ የቤተ ክርስቲያን የግል ሀብት መስሎ በቤተ ክርስቲያን ብቻ «ይቤ መተርጎም» አየተባለ መጻሕፍተ ብሉያትና መጻሕፍተ ሐዲሳት አንዲሁም መጻሐፍተ ሊቃውንት እየተተረጎሙበት እገዚአብሔር አምላክ እአየተመሰገነበት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ይገኛል የግዕዝ ቋንቋ በሀገራችን በኢትዮጵያ ጥንታዊ መሆኑ ይታወቃል በየአደባባዩና በቤተ መንግሥት ሰዎችንና አሳባቸውን በመመዝገብ የሰጠውን የረዥም ዘመን አገልግሎት ቤተ ክርስቲያን ትመሰክርለታለች ታስታውሰው ማለች የአገር ውስጥ የውጭ አገር ሊቃውንትም ያረጋግጡለታል በመሠረቱ ግዕዝ የተለያዩ ባሕርያት ያሉት በአንድ ቃል ብቻ ብዙ መልእክታት ማስተላለፍ የሚቻልበት ኀብር የሆነ ሰፊ ቋንቋ መሆኑ ግልጽ ነው የኢተዮጵያን ታሪክ አጠናለሁ አመረምራለሁ የሚል ማንም ተመራማሪ የአባቶቹን ታሪክ ማጥናትና መመራመር የሚችለው በቅድሚያ የግዕዝ ቋንቋና አገባቡን አጣርቶና አጥንቶ ሲገኝ ነው በተጨማሪም በግዕዝ ቋንቋችን ውስጥ ለባህላችንና ለታሪካችን እድገት ለአሁኑ የግምባታ ሒደታችንና ለእውቀታችን መለኪያ የሚሆኑ ብዙ ቃላት አሉ ቃላቱን እየመረመሩ በየሚጠቀሙበት ሐረግ እያስገቡ መጠቀም የቃላትን ብድር ፍለጋ ወደ ውጭ ከመሰደድ ያድናል ራስን በራስ ያሰተምራል ያኮራል የኢትዮጵያ ኣርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዜማን ካስተማረች በላ ይህን የግእዝ ቋንቋ ትምህርት ከነቅኔው ታስተምራለች የግዕዝ ትምህርት መጀመሪያው ግሥ ይባላል ተማሪው ቅኔን ከመቁጠሩ በፊት ግሥ መግሠሥንና ማውረድን ያጠናል ለ ቅኔ ቅኔ ማለት መገዛት አገልግሎት ነው ለምሳሌ ቅኔ ደብተራ ቅኔ ማኀሌት አንዲሉ ከዚህም ጋር በቅኔ ሙሾ ግጥም ቅንቀና የፍትሐት የልቅሶ ዜማ እንዲሁም የምስጋና ግጥም መግጠም ይቻላል የጥንት ሰዎች በተለይ ዕብራውያን በቅኔ ግጥም እየገጠሙ ማለት ቅኔ አየተቀኙ አምላካቸውን ያመሰግኑ ነበር በተለይም ነቢዩ ዳዊት ራሱ ግጥም እየገጠመ ፈጣሪውን ከማመስገኑ በላይ ሌላውም ሰው በቅኔ እገዚአበሔርን እንዲያመሰግን ሲያዝዝ «ተቀነዩ ለእግዚአብሔር በፍርሐት» በማለት ዘምሯል ሌላውንም አዝዛል በኋላም ኢትዮጵያዊው ሊቅ የዜማና የቅኔ ደራሲ ቅዱስ ያሬድ ተቀነዩ ለእግዚአበሔር በፍርሐት ሲል ዘምሯል የቅኔው ደራሲ ቅዱስ ያሬድ እንደ ሆነ ቢታወቅም ከአሥራ አራተኛው ምእት ዓመት ጀምሮ በየጊዜው የተነሥት እነ ሐዊራ መንከሪ እስክንድራ እስካንድራ አቢዳራ ደቀ እስጢፋተዋነይ ዮሐንስ ገብላዊ የመሳሰሉት ሊቃውንት ሰምና ወረቅን ኀብርን ውስጠ ወይራን አንጻርን ምጸትን ልዩ ልዩ ዓይነት ጎዳናን የመሳሰሉ ምሥጢራውያን ምሳሌዎችና የምሥጢር ጥልቀትንና ምጥቀትን በመፈልሰፍ አስፋፍተውታል ቅኔ በግጥሙ በምሥጢሩ በቃለ አሰካኩ ተወዳጅነት ስላለው ብዙ ኢትዮጵያውያን ይማሩታል ኢትዩጵያውያን ነገሥታት ሳይቀሩ እስከ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ድረስ ይማሩት እንደ ነበር ይታወቃል ኪነ ጥበባት በኢትዮጵያ ኪነ ጥበባት በኢትዮጵያ በምንልበት ጊዜ የቅርጻ ቅርጽን የሥዕላ ሥዕልንና የመሳሰሉትን የፈጠራ ውጤቶች ያጠቃልላል የኢተዮጵያ ሊቃውንት የቅርጻ ቀርጽም ሆነ የአሳሳል ስልት እጅግ የተወደደና ከዘመን ወደ ዘመን እየተሻሻለ የመጣ ጥበብ ስለ ሆነ የኢተዮጵያን ሕዝብ ዕድገትና የሀገሪቱን ጥንታዊነት ከሚገልጡት ጥበባት ጥቂቶችን ከዚህ በታች በአጭሩ ለመግለጥ እንሞከራለን ሀ የውቅር አብያተ ክርስቲያናት ቀደም ባሉት ዓመታት ሊቃውንቱ በዙሪያቸው ከሚገኙት የዓለት ተራራዎችና ኮረብታዎች ፈልፍለው ሕንጻዎችን በማውጣት በኪነ ጥበብ የተራቀቁና የተሳካላቸው የድንጋይ ጠራቢዎችና ጠቢባን ነበሩ የፈጠራቸው ውጤቶች የሆኑት ቅርሶችና ከአንድ ወጥ ድንጋይ ያነጹዋቸው ሐውልቶች የገነቡዋቸው ቤተ መቅደሶችና አብያተ ክርስቲያናት የሚመለከታቸውን የሰው አእመሮ በአድናቆት ይመስጣሉ ከሥራዎቻቸው አብዛኛዎቹ ከሺ ዓመታት በፊት የተሠሩ መሆናቸው ሲታሰብ ከአድናቆትም በላይ አልፈው ተርፈው የሰውን አእምሮ በአንክሮ ውቅያኖስ ውስጥ ይከታሉ በኢትዮጵያችን ውስጥ በመቶዎች የሚቆጠሩ ከድንጋይ ፍልፍል የተሠሩ ቤተ መቅደሶችና አብያተ ክርስቲያናት ይገኛሉ ለምሳሌ ያህል በትግራይና በወሎ እንዲሁም በሸዋና በጎንደር በጎጃም የሚገኙትን ፍልፍል አብያተ ክርስቲያናት እንደ ምሳሌ መጥቀስ ይቻላል ለ ቅርጻ ቅርጽ ከላይ የተጠቀሱት የውቅር አብያተ ክርስቲያናት የሥርዓተ አምልኮት መፈጸሚያ በሆኑት ልዩ ልዩ መስቀሎችና ለዓይን በሚማርኩ ልዩ ልዩ ጌጣጌጦች የተጌጡና በቅርጽ የተዋቡ ናቸው ይህንንም ለመረዳት የኢትዮጵያ መስቀሎች ኢትዮጵያን ክሮስስ የሚባለውን መጸሐፍ አንብቦ መረዳትና ማየት ይበጃል ከዚህም ሌላ በቤተ ክርስቲያን ሕይወት ውስጥ ዕለት ተዕለት አያሌ ቅርጻ ቅርሶች ይገኛሉ ሒ ሥዕል ብዙዎቹ አብያተ ክርስቲያናት በግርግዳቸው በጣራቸው በአምደቻቸው በየመስኮቶቻቸውና በየበሮቻቸው በጌታ በእመቤታች በቅዱሳን መላአክት በነቢያት በሐዋርያት በጻድቃንና በሰማዕታት ሥዕሎች የተዋቡና ያሸበረቁ ናቸው ይህም የሚሆንበት ምክንያት የጌታም ሆነ የአመቤታችን እንዲሁም የቅዱሳን መላእክትም ሆነ የጻድቃንና የሰማዕታትም ሥዕላቸው በየቤተ ከርስቲያኑ መሣሉ ለሰው ልጅ የተደረገውን ደኅንነትና ትድግና እንዲሁም ሥራቸውንና ቅድስናቸውን አጉልቶ ለማሳየት በሥዕላቸው ለመማጠንና ምዕመናንን በሥዕል ለማስተማር ነው ከዚህ ጋር ሊቃውንቱ ቅዱሳት መጻሐፍትን በሚጽፉበት ጊዜ በየመጻሕፍታቸው አርአስትና ማፅከል ወደር የማይገኝላቸውን የተለያዩ ሐረጎችንና ሥዕሎችን ይሥላሉ ይህ የሥዕልና የሐረግ ጥበብ ከሥነ ጽሕፈት ጥበብ ጋር ተዳምሮ የኢተዮጵያን ቤተ ክርስቲያን ጥንታዊነት የሊቃውንቱን የፈጠራ ችሎታና የኀብረተ ሰቡን በሊቃውንቱ መገልገል አጉለቶ የሚያሳይ የጥበብ ጥበብ መሆኑን መገመት አያዳግትም ጥንታውያን የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሠዓሊዎች የጌታችንና የእመቤታችንን የጻድቃንና የሰማዕታትን ወዘተ ሥዕል ሥርዓተ አምልኮውን ደስታውንና ኀዘኑን ጀግንነቱንና ድል አድራጊነቱን ሥልጣኔውንና አገር ወዳድነቱን ጉስቁልናውንና እድገቱን አጉለተው ይሥሉና ለታሪክም ያቆዩት እንደ ነበር ሥራቸው በዓይን የሚታይ በእጅ የሚዳሰስ ሕያው ማስረጃ ነው ይህም ጥበብ ዘመናትን ያስቆጠረ ከመሆኑም በላይ በዘመናችንም ከአለፈው በተሻለ መልኩ እየተስፋፋና በመሠራትም ላይ የሚገኝ ነው «አባት ያቆየው ለልጅ ይበጀው» አንዲሉ የጥንት አባቶቻችን ያቆዩት የዜማና የቅኔ የሥነ ጽሕፈት የቅርጻ ቅርጽና የሥዕል ጥበብ በዘመናችንም በስፋትና በጥልቀት በቤተ ክርስቲያኒቱ ትምህርቱ እየተሰጠ ስለሆነ የፅውቀት ባለቤትና የጥበብ መገኛ የሆነውን አግዚአብሔርን እናመሰግናለን ወስብሐት ለእግዚአበሔር ምንጮች ሰማንያ አሐዱ ቅዱሳት መጻሕፍት ጽ መዝገበ ቃላት የአለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ የኢትዮጵያ ጥንያዊ ትምህርት የሊቀ ሥልጣናት አባ ሀማርያም ያሬድና ዜማው የሉቀ ካህናት ጥዑመ ልሳን ካሣ ፁ የኢትዮጵያ ታሪክ ነብያ አክሱም የተክለ ጻድቅ መኩሪያ ጽ የኢትዮጵያ ሥልጣኔ የአቶ በላይ ግደይ የኢኦርተቤክርስቲያን ሥነ ጽሑፍ ለኢሕዝብ ዕድገት ያስገኘው አስተዋጽኦ የሊካብርሃኑ ገአማኑኤል የአጅ ጽሑፍ ጵ ዮዬ ደ።

  • N.B. This Summary is Very Experimental!! based on the following scripts from:
    • https://github.com/millzon/textSummarizer-am
    • https://github.com/icoxfog417/awesome-text-summarization#motivation
Download Searchable PDF Download PDF

تعليقات:


memezon

خيارات التنزيل | تحويل إلى قوات الدفاع الشعبي | كتاب اليوم

© dirzon | شروط الخدمة | خصوصية | حول | خدمات | اتصال