Detecting...

Please whitelist dirzon to continue.

or subscribe for ad-free contenct.

dirzon
  • ወደ ፒዲኤፍ ቀይር
  • የንባብ ዝርዝር
  • አጠሬራ
  • ኦዲዮ መጽሐፍ
  • ፍለጋ
  • ይስቀሉ
  • የኔዞን
  • ይግቡ
  • ይመዝገቡ
English  አማርኛ  Français  العربية
የዕለቱ መጽሐፍ

የኢትዮጵያ_ቤተ_ክርስቲያን_ተግዳሮቶች.pdf


  • የቃላት ደመና

የኢትዮጵያ_ቤተ_ክርስቲያን_ተግዳሮቶች.pdf
  • የማውጣት አጠሬራ

ይህንን ጥያቄ ለመመለስ የቤተ ከህነቱን ሠራተኞች ዘር ብንቆጥር በሊቀ ጳጳሱ ዙርያ የሚሽከረከር ሆኖ እናገኘዋለን ያውም ከአንዲት መንደር ሳይወጣ የዋናው ቤተ ከህነትም አሠራር ተመሳሳይ ነው በቤተ ክህነት ሀገርህ የት ነው። ማለት ከልልን ዞንን ወይንም ዘርን አያመለከትም ትርጉሙ የተወለድከው የት መንደር ነው። የሚያውቀው የለም በየቀኑ አዳዲስ ሰው ከመጨመር በቀር በአንድ ደብር ልከ የሌላቸው ሰባከያነ ወንጌል እየታዩ ነው አራቱም ግን ተመሳሳይ ሥራ ነው አንድ የገጠር ጉባኤ ለመሄድ በትንሹ አምስት ሺ ብር በሚሸጥበት ዘመን ላይ ነን ጉባኤ እናዘጋጅና በፐርሰንት እንካፈል መባል ነውር መሆኑ ቀርቷል ገበያው በመድራቱ የተነሣ በአሁኑ ጊዜ ከሦስት መቶ በላይ የመዝሙር ካሴቶች በዓመት ይወጣሉ ስብከት እና ዝማሬ እንጀራቸው ነው መናገር እና ድምጽ እንጂ ዕውቀት እና እምነት ለአገልግሎት አይጠየቁም ተሐድሶዎች ይህንን የተበላሸ መሥመር ነው ቤተ ክርስቲያኒቱ ያልጨረሰቻቸው ጉዳዮች መኖር የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ናት።

  • Cosine ማጠቃለያ

የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የወቅቱ ችግሮችተግዳሮቶች እና ፈተናዎች ለሰሜን አሜሪካ የሰንበት ትቤቶች አንድነት ጉባኤ የቀረበ ዴንቨር ነሐሴ ቀን ዓም ጠቅላላ መግቢያ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ዘመናዊ ታሪክ ገጽታዎች የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ዘመናዊ ታሪክ የሚባለው የራስዋ ሲኖዶስ ኖሯት ራስዋን መምራት ከጀመረችበት በኋላ ያለው ታሪክ ነው ይህንን የታሪክ ምእራፍ ከቀደምቱ ልዩ የሚያደርጉት ገጽታች አሉ የቤተ ክርስቲያኒቱ ሁለት ገጽታዎች በሚገባ ተለይተው የታወቁበት ዘመን መሆኑ እነዚህ የቤተ ክርስቲያኒቱ ሁለት ገጽታዎች የምንላቸው ቤተ ክርስቲያናዊ ገጽታዋን እና ቤተ ክህነታዊ ገጽታዋን ነው ቤተ ክርስቲያናዊ ገጽታ ቤተ ክርስቲያናዊ ገጽታ የምንለው ትምህርተ ሃይማቷን ሥርዓትዋን ትውፊቷን ቅዳሴዋን መጻሕፍቷን ወዘተ ነው ይህ ገጽታዋ ሃይማኖታዊውን ጉዞዋን ብቻ ያሳያል ቤተ ክህነታዊ ገጽታዋ የቤተ ክርስቲያኒቱን የሰው ኃይል የንብረት የገንዘብ የቦታ የሕግየአሠራር ወዘተ ገጽታዋ ነው በዚህ ዓለም ላይ እንደ መኖርዋ መጠን እንደ ማንኛውም መሥሪያ ቤት የሚኖሯት መዋቅሮች አሠራሮች ደንቦች የሰው ኃይል እና የፋይናንስ እና ኢኮኖሚ አውታሮች አሉ የመጀመርያው ለሁለተኛው መሠረት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ለመጀመርያው ድጋፍ ሰጭ ነው የመጀመርያው መሥመሩን ከሳተ ቤተ ክርስቲያኒቱ በጠቅላላው መሥመ ሯን ትስታለችር ሁለተኛው መሥመሩን ከሳተ ደግሞ ቤተ ክርስቲያኒቱ በሚገባ ተልዕኮዋን እንዳትወጣ ትገደባለች መንግሥት እና ሃይማኖት በሕግ የተለያዩበት ዘመን መሆኑ ቤተ ክርስቲያን የሀገሪቱ የትምህርት የሥልጣኔ የሞራል የሕግ የሥልጣን ምንጭ ሆና ለዘመናት ኖራለች ነገሥታን ቀብታ ታነግሥ የነበረች አስፈላጊ ሲሆንም ሥልጣናቸውን ነጥቃ ታሰናብት የነበረች ተቋምም ነበረች ከ ዓም በኋላ የተከሰተው እና መንግሥት እና ሃይማኖትን የለያየው ፍልስፍና በቤተ ክርስቲያኒቱ ታሪክ እንግዳ ክስተት ነው ምክንያቱም በሕግ መንግሥት እና ቤተ ክርስቲያን ቢለያዩም የቤተ ክርስቲያኒቱ ሥልጣን እና ዐቅም ተዳከመ እንጂ በአሠራር ግን መንግሥት እና ቤተ ክርስቲያን የተለያዩበትን ሁኔታ ለማየት አስቸጋሪ የሚሆንባቸው ነገሮች አሉና የቤተ ክርስቲያኒቱ የኢኮኖሚ ሥሪት መቀየር ለ ዘመናት ያህል የቤተ ክርስቲያኒቱ የኢኮኖሚ ሥሪት መሬትን መሠረት ያደረገ ነበር በመሆኑም ቤተ ክርስቲያኒቱ የኢኮኖሚ ድህነት ጥያቄ አልነበረባትም የ ዓም አብዮት ያለ ዝግጅት በድንገት የቤተ ክርስቲያኒቱን የኢኮኖሚ መሠረት ከመሬት ወደ ምእመናን መዋጮ ቀየረው ይህ ሁኔታ ደግሞ ቤተ ክርስቲያኒቱን ወደ ኢኮኖሚ ድህነት ካህናቱንም ወደ ጥገኛነት ቀየራቸው ሁለት ዓይነት የተማሩ ትውልዶች መከሰት ቀድሞ በሀገሪቱ ይፈጠሩ የነበሩ ምሁራን በቤተ ክርስቲያኒቱ የትምህርት ሥርዓት የሚያልፉ ነበሩ የሀገሪቱን መንግሥታዊም ይሁን መንግሥታዊ ያልሆነውን ሥልጣን የሚይዙት እነዚሁ ከቤተ ክርስቲያኒቱ የትምህርት ተቋማት የሚወጡት ምሁራን በመሆናቸው ቤተ ክርስቲያኒቱ በሀገሪቱ የሥልጣንየአስተሳሰብ የእምነት የሞራል እና የሥርዓት ሁኔታዎች ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ የማሳረፍ ዐቅም ነበራት በዘመናዊው የሀገሪቱ ታሪክ የተፈጠሩት ዘመናውያን ትምህርት ቤቶች ግን የተማረውን የሀገሪቱን ትውልድ ወደ ሁለት ከፈሉት በአንድ በኩል ከነባር የቤተ ክርስቲያኒቱ ትምህርት ቤቶች የሚወጣ በሌላ በኩል ደግሞ ከዘመናዊ ትምህርት ቤቶች የሚወጣ ከነባር ትቤቶች የሚወጣው ዘመናዊውን ሳያይ መምጣቱ በዘመናዊው የትምህርት ተቋማት የሚያልፈውም ነባሩን የቤተ ክርስቲያን ትምህርት ሳያይ ማደጉ ሁለቱም መንታ ሆነው እንዲወጡ አደረጋቸው ይህ ሁኔታ ደግሞ ተጣጥመው መጓዝ የነበረባቸውን የሀገሪቱን ትውልዶች እርስ በርስ የሚተጋገሉ እንዲሆኑ አድርጓል በተላይም በሀገሪቱ የሥልጣን የሕግ የቢሮክራሲ የሳይንስ የቴክኖሎጂ የባህል የትምህርት እና የሚዲያ ተቋማት ውስጥ በብዛት የሚገባው ትውልድ ከዘመናዊው የትምህርት ተቋማት የሚወጣው ትውልድ መሆኑ የቤተ ክርስቲያኒቱን የተጽዕኖ ክልል አጥብቦታል የቤተ ክርስቲያኒቱ አገልግሎት በዓለም ዐቀፍ ደረጃ መስፋፋት ቤተ ክርስቲያን በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም እና በግብጽ ከነበሯት አብያተ ክርስቲያናት በተጨማሪ በሌሎች የዓለማችን ከፍሎች አዳዲስ አጥቢያዎች የተተከሉት በዘመናዊው የቤተ ክርስቲያኒቱ የታሪክ ዘመን ውስጥ ነው በአውሮፓ በመካከለኛው ምሥራቅ በአሜሪካ እና በአውስትራልያ ብሉም በመካከ ለኛው የአሜሪካ ሀገሮች አያሌ አጥቢያዎችን ተክላለች ነገር ግን ለእነዚህ የሚመጣጠን የሰው ኃይል የአሠራር ሥርዓት ሕግ የመገናኛ እና የመረጃ አውታር አለዘረጋችም እነዚህ ቤተ ክርስቲያኒቱ የገጠሟት አዳዲስ ክስተቶች ወደ ኋላ ላይ ላጋጠሟት ችግሮች ፈተናዎች እና ተግዳሮቶች ከፍተኛውን አስተዋጽዖ አድርገዋል የቤተ ክርስቲያን ችግሮች ፈተናዎች እና ተግዳሮቶች ቤተ ክርስቲያን በዚህ ዓለም ላይ የምትቀዝፍ ሰማያዊት መርከብ በመሆንዋ ዓለም አትስ ማማትም ይህንን ሰማያዊ ጉዞዋን ስታከናውን በመንገዷ ላይ ሦስት ነገሮች ይገጥ ሟታል ችግሮች ፈተናዎች እና ተግዳሮቶች። የምትችላው ፈተናዎችን መቋቋም እና ማሸነፍ ብቻ ነው እነዚህን ፈተናዎች ለመቋቋም እና ለማሸነፍ ደግሞ ከምንም በላይ ውስጣዊ መንፈሳዊ እና መዋቅራዊ ጥንካሬ ወሳኞች ናቸው የቤተ ክርስቲያን ችግሮች እየተባባሱ ሲመጡ ግን መንፈሳዊም ሆነ መዋቅራዊ ዐቅሟ ይዳከምና አጠር እንደሌለው የወይን እርሻ የየትኛውም ፈተና መራኮቻ ትሆናለች አሁን የምናየውም ይህንኑ ነው ተግዳሮቶች ተግዳሮቶች የምንላቸው ቤተ ክርስቲያን ከሚኖረው የዓለም ሥርዓት የሚመጣባትን ግፊት ነው የዓለም ሥርዓት በየጊዜው ይቀያየራል ይህ የዓለም ሥርዓት መቀያየር ደግሞ የተለያዩ አመለካከቶችን የአሠራር መንገዶችን ጥያቄዎችን ማኅበራዊ ክዋኔ ዎችን የፖለቲካ ሂደቶችን እና የግንኙነት መንገዶችን ይፈጥራል ቤተ ክርስቲያን በዓለም ላይ እንደ መኖርዋ የምታገለግላቸው ልጆቿም በዚህ ዓለም ላይ እነደ መኖራቸው መጠን ከዚህ የዓለም ጉዞ ተግዳሮቶች ይገጥሟታል የዴሞክራሲ እና የሰብአዊ መብት መሠረተ ሃሳቦች በጋብቻ ላይ የተፈጠሩ አዳዲስ አመለካከቶች የሉላዊነት ወይንም ግሎባላይዜሽን ሂደት የኢንተርኔት የሚዲያ እና ፊልም መስ ፋፋት ስለ እምነት የሚነሥ አዳዲስ ሃሳቦች አና ጥያቄዎች የአንድ ሀገር የፖለ ቲካ እና የዕውቀት ኃይሎች የሚያደርጉባት ግፊት አዳዲስ የሳይንስ ግኝቶች ወዘተ የቤረ ክርስቲያኒቱ ተግዳሮቶች ናቸው ቤተ ክርስቲያን እነዚሀን ተግዳሮቶች ማስቀረትም ሆነ መቀነስ አትችልም ምክንያቱም የሚሙት ከእርስዋ ውጭ ካሉ አካላት ነውና መቋቋም እና ማሸነፍ ግን ትችላለች የእነዚህ ተግዳሮቶች መኖር ቤተ ክርስቲያንን ሊጠቅማትም ሆነ ሊጎዳት ይችላል ቤተ ክርስቲያን አሠራርዋን እንድትፈትሽ እንድትዘጋጅ እና እንድትተጋ በማድረግ ረገድ ተግዳሮቶች ጥቅም አላቸው ይህ የሚሆነው ግን ከላይ ያነሳናቸው የቤተ ክርስቲያን ችግሮች ቤተ ክርስቲያኒቱን እጅ ከወርች አሥረው ካልያዚት ነው የእነዚህ ተግዳ ሮቶች መኖር ቤተ ክርሰቲያኒቱ ትምህርቷን እና ሥርዓትዋን በሚገባ እንድታብራራ እንድታስረዳ እና እንድትጽፍ ያደርጓታል አዳዲስ የመገናኛ አውታችን እንድትጠቀም ያስገድዷታል የሰው ኃይል ሥልጠናዋን እንድታሳድግ ያደርጓታል የስብከት ዘዴዋን እና መንገዷን እንድታበለጽግ ያስችሏታል የትምህርት ተቋማቷን በትምህርት ጥንታ ውያን በአሠራር ዘመናውያን እንዲሆኑ ያደርጓታል መዋቅሯን እና የአሠራር ሥርዓ ትዋን በየጊዜው ለማሳደግ ያስችሏታል በሌላ በኩል ደግሞ ቤተ ክርስቲያኒቱ በውስጣዊ ችግሮች ከተያዘች እነዚህ ከዓለም የሚመጡ ተግዳሮቶች ያለ ምንም ተቋቋሚ ሰተት ብለው ወደ ቤተ ክርስቲያኒቱ እንዲ ዘልቁ ያስችላቸዋል። የእነዚህ ዘመ ቻዎች ዓላማ ቤተ ክርስቲያኒቱን ቀይሮ ሌላ ተልዕኮ መስጠት ነው እነዚህ ኃይሎች ቤተ ክርስቲያኒቱ አጥፍተው ሌላ ተቋም እስካልተኩ ድረስ የማይረኩ ናቸው በቤተ ክርስቲያን ጉዞ ውስጥ አስቸጋሪው እና ከባዱ ነገርም ይኹው ነው አሁን ቤተ ክርስቲያን ያጋጠሟት ችግሮች ፈተናዎች እና ተግዳሮቶች ምንድን ናቸው። ይህንን ጥያቄ ለመመለስ የቤተ ከህነቱን መሠረታዊ ችግሮች መመልከት ይገባል ብዙ ሰዎች እንደ ሜመስላቸው የወቅቱ የቤተ ከርስቲያን አደጋዎች ቤተ ከርስቲያንን እናድሳለን የሚሉ አካላት መነሣት የገዳማት እና አድባራት መቸገር በስብከተ ወንጌል መድረኮች ዙርያ እየታዩ የመጡ ከስተቶች ያሬዳዊ ያልሆኑ መዝሙራት መብዛት «የባሕታውያን» ማደናገር ወዘተ አይደሉም እነዚህ ነገሮች መኖራቸው ርግጥ ነው ነገር ግን ለቤተ ከርስቲያኒቱ አደጋ እስከመሆን የደረሱት ሥር የሰደዱ የውስጥ ችግሮች በመኖራቸውና የመቋቋም ዐቅማችን በመዳከሙ ነው ዋናዎቹ የቤተ ከህነቱ ችግሮች ሲፈቱ ከላይ የጠቀስናቸውና ሌሎቹም ችግሮች አብረው ይፈታሉ አስካሁን ልዩ ልዩ አገልጋዮች ማኅበራት አና ኮሚቴዎች ተነሥተው ከላይ የጠቀስናቸውን ችግሮች ለመፈታት ታግለዋል ነገር ግን የሚራቡ ገዳማት ደመወዝ የሚያጡ ካህናት በቤተ ከርስቲያኒቱ ላይ የሚነሥ ተቃዋሚዎች ሳይቀደስባቸው የሚውሉ አጥቢያዎች ከቤተ ከርስቲያኒቱ ሥርዓት ውጭ የሚሰበኩ ስብከቶች አና የሚዘመሩ መዝሙሮች ቁጥራቸው አየጨመረ እንጂ እየቀነሰ ሊመጣ አልቻለም ይህ ሁኔታ አንድ ነገር ይጠቁመናል የችግሮቹን የስበት ማዕከል አለማግኘታችንን የችግሮች የስበት ማዕከል ማለት ለሌሎች ቅርንጫፍ ችግሮች መራባት ምከንያት የሆነ እና አርሱ ሲፈታ ቅርንጫፍ ችግሮቹም አብረው ሊፈቱ የሚችሉ ችግር ማለት ነው የስበት ማዕከሉን ትቶ ቅርንጫፍ ችግሮችን ብቻ እየፈቱ መጓዝ ሁለት አይነት መከራ ያመጣል የመጀመርያው ኃላፊነት የተሰጠው አካል አርሱ ምንም አስተዋጽዖ ሳያደርግ ሥራው ስለ ሚሜሠራለት ትኩረቱን ወደ ግል ጥቅሙ እና ዝናው እንዲያደርግ ያስችሱታል ችግር ለመፍታት የተነሣው አካል ሁለተኛው ደግሞ ችግሮቹን ከመሠረታቸው ከመፍታት ይልቅ አንጥፍጣፊዎች ላይ ስለሚያተኩር ችግሮቹ ዘላቂ ችግሮች አንዲሆኑ ያደርጋቸዋል በመሆኑም ቤተ ከርስቲያንን በአንድም በሌላም መልኩ እናገለግላለን አስተዋጽዖ እናደርጋለን ገንዘባችንን ጊዜያችንን እና ፅውቀታችንን እንሠዋለን ብለው የተሰባሰቡ አካላት እና ግለሰቦች የማርሽ ለውጥ ማድረግ ያለባቸው ጊዜ አሁን ይመስለኛል ከቅርንጫፍ ችግሮች ወደ ችግሮቹ የስበት ማዕከል መዞር ለመሆኑ በአሁኑ ጊዜ የቤተ ከህነቱ የችግር የስበት ማዕከል ምንድን ነው። የቤተ ከርስቲያኒቱ የመጨረሻ ወሳኝ አካል ሲኖዶሱ ነው ሕግ ማውጣት ቀኖና መደንገግ አሠራር መዘርጋት ችግሮችን ለመጨረሻ ጊዜ መፍታት ስሕተቶችን ማረም እና እንቅፋቶችን ማስወገድ የሚችለው አርሱ ነው መንፈሳዊም ምድራዊም ሥልጣን አለውና መንፈሳዊው ሥልጣን በመንፈስ ቅዱስ እና በቅዱሳት መጻሕፍት የተሰጠ ምድራዊ ሥልጣን በሀገሪቱ ሕግ የተደነገገ ነው ነገር ግን ሲኖዶሱ ራሱ በችግሮች ተተብትቦ ተይዚል ዐቅም አግኝቶ ውሳኔ መወሰን አልቻለም ቢወስንም አያስፈጽምም በቤተ ከርስቲያኒቱ ገንዘብ እና ንብረት ላይ በሙሉ ሥልጣኑ አያዝም በቤተ ከርስቲያኒቱ የሥልጣን እርከኖች ላይ በሙሉ ሥልጣን አያዝም የመቆጣጠርያ የመከታተያ እና የማስፈ ጸሚያ ስልትና አሠራር የለውም የቤተ ከህነቱን አሠራር ሕግጋት ሥርዓት እና አስተሳሰብ አሁን ቤተ ከርስቲያን እና ሀገሪቱ በምት ፈልገው መጠን ማስተካከል እና ደረጃውን ከፍ ማድረግ አልቻለም ይህንን እንዳያደርግ ደግሞ እርሱ ራሱ በመሠረታዊ ችግሮች ተይዘል ይህን የቸግር የስበት ማዕከል ቀፍድደው የያዙት አራት መሠረታውያን ችግሮች ናቸው እነዚህን ስንፈታ የስበት ማዕከሉ ቸግር ይፈታል የስበት ማዕከሉ ችግር ሲፈታ ደግሞ የቤተ ከርስቲያኒቱ ችግር ይፈታል አራቱ መሠረታውያን ችግሮች የምንላቸው የመንፈሳዊነት መጓደል ሙስና መንደርተኛነት አና ኋላ ቀርነት ናቸው የመንፈሳዊነት መጓደል መንፈሳነት የመጀመርያው እና የመጨረሻው ወሳኙ ነገር ነው መንፈሳውያን በሌሉበት ቦታ መንፈሳዊ ነገር መፍትሔ አያገኝም መንፈሳዊነት ማለት የሃይማኖትን ትምህርት ማወቅ ቤተ ከርስቲያን መሄድ የቃል ጸሎትን መሸምደድ የቤተ ከርስቲያንን መዓርጋት መያዝ በቤተ ከርስቲያን መዋቅር ውስጥ ማገልገል ማለት ብቻ አይደለም እነዚህ መንፈሳዊነትን የሚያጎለብቱ ነገሮች አንጂ በራሳቸው መንፈሳዊነት አይደሉም መንፈሳዊነት ኑሮ ነው አመለካከት ነው ሕይወት ነው ቅኝት ነው መንፈሳዊነት በፈሪሃ እግዚአብሔር ተቃኝቶ በቃለ አግዚአብሔር ተመርቶ መንፈሳዊን ጥበብ ገንዘብ አድርጎ ውስጥን መለወጥ ነው አንድ ከርስቲያን አግዚአብሔርን በምንም መንገድ ካልፈራ ቃለ አግዚአብሔርን ከተለማመደው የማያ ምንባቸውን ነገሮች ለሥነ ሥርዓት ሲል ብቻ የሚያደርግ ከሆነ ምንም ዓይነት መንፈሳዊ ነገር ከስሕተቱ ካላቆመው «እግዚአብሔርን የማይፈራ ሰውንም የማያፍር» ከሚባልበት ደረጃ ደርሷል ማለት ነው አንዲህ ያለው ሰው የተአምራት ቅጣት እንጂ ምከር እና ተግሣጽ አይመልሰውም በመሆኑም የሳአልን ኃጢአት የሚመከት የዳዊት መንፈሳዊነት የኤልዛቤልን ኃጢአት የሚመከት የኤልያስ መንፈሳዊነት የድርጣድስን ኃጢአት የሚመከት የጎርጎርዮስ መንፈሳዊነት የብርከልያን ኃጢአት የሚመከት የዮሐንስ አፈወርቅ መንፈሳዊነት የግራዚያኒን ኃጢአት የሚመከት የአቡነ ጴጥሮስ መንፈሳዊነት በቤተ ከህነታችን ጎድሏል ዛሬ ዛሬ መንፈሳዊ አገልግሎት አገልግሎት መሆኑ ቀርቶ የቢሮ ሥራ ሆኗል መቀደስ ሰዓታት መቆም ፍትሐት መፍታት ኪዳን ማድረስ ማኅሌት መቆም ሥራ ብቻ ነው የጽደቅ አገልግሎት መሆኑ አየተረሳ ነው በዚሀም ምከነያት በዓለማዊ መሥሪያ ቤቶች አንኳን የማናየውን የጉቦየዘመድ አሠራር የፍትሕ መዛባት አምባገ ነንነት ሥርቆት እና ሌሎች ነገሮችን በእኛ ዘንድ መስማት ነውርነቱ አልፎበታል መዋቅር እና አሠራርን የሚያጠኑ ሰዎች አንደ ካቶሲከ ቤተ ከርስቲያን የሚያመሰግኑት የለም ብዙዎቻችን ልምድ ልንቀስምባቸው የሚያስችሉ አሠራች እና አወቃቀሮች አሏቸው ነገር ግን ዋናው ነገር መንፈሳዊነቱ ጎደለና ዛሬ ዛሬ የካቶሊከ ካህናት የሚወቀሱት ሕፃናትን በመዳፈር ሆነ «ምላጭ ቢያብጥ በምን ይበጡታል ውኃ ቢያንቅ በምን ይውጡታል» የተባለው ደረሰ ማለት ነው አንድ የጥንት አባት «በቤተ ከርስቲያን ውስጥ ትልቁ ችግር የሚፈጠረው መንፈሳውያን ያልሆኑ ሰዎች መንፈሳዊ ሥራ ሲሠሩ ነው» ብሎ ነበር ያልመነኑ ሰዎች ከመነኮሱ ከርስቲያን ያልሆኑ ሰዎች ከቀሰሱ አግዚአብሔርን የማያውቁት ሰዎች ካስተማሩ ደመወዝቤት አና መኪና የሚያጓጓቸው ሰዎች ከአጳሱ ፍትፍት ያልሰለቻቸው ሰዎች ባሕታውያን ከሆኑ የዘር ዛር ያልለቀቃቸው ሰዎች የሁሉ አባት ከተባሉ ከራሳቸው ጋር ያልታረቁ ሰዎች ለታራቂነት አና አስታራቂነት ከተቀመጡ መንፈሳዊነት ሽታውም ጠፍቷል ማለት ነው ለዚህም ሳይሆን አይቀርም ለመንፈሳዊ ችግሮች የታከቲከ እና የቴከኒከ እንጂ የመንፈስ መፍትሔ ስንፈልግ የማንገኘው አንዳንድ ጊዜኮ አኛ በቤተ ከርስቲያን ውስጥ አለን ቤተ ከርስቲያን ግን ከአኛ ውስጥ ወጥታለች እኛ በከርስትና ውስጥ ነን ከርስትና ግን ከአኛ ውስጥ ወጥቷልእኛ በከህነቱ ልብስ ውስጥ ነን ከህነቱ ግን ከእኛ ውስጥ ወጥቷል እኛ በስብከቱ ቀሚስ ውስጥ ነን ስብከቱ ግን ከውስጣችን ወጥቷል እኛ በገዳም አንኖራለን ገዳማዊ ሕይወት ግን በኛ ውስጥ የለም ለአንዳንዶቻችን ጵጵስና ፕሮፌሽን ነው ቅስና ፕሮፌሽን ነው ሰባኪነት ፕሮፌሽን ነው ምንኩስና ፕሮፌሽን ነው ዝማሬ ፕሮፌሽን ነው እንደ ጥብቅና እንደ ንግድ አንደ ሕከምና አንደ ጋዜጠኛነት እንደ ምሕንድስና የእንጀራ ማግኛ ሞያ ታድያ እንዴት መንፈሳውያን መሆን ይቻላል። አሁን ያለው የቤተ ከህነት መዋቅር የተዘጋጀው ከሃምሳ ዓመታት በፊት ነው ከዚያ በኋላ የተጠና ማሻሻያ አልተደረገለትም በዚህም ምከንያት አንዳንድ መምሪያዎች ከኃላ ፊው በቀር ሌላ የሰው ኃይል የላቸውም አንዳንድ መምሪያዎችም የሚሠሩት የፅለት ተዕለት ሥራ የላቸውም የየመምሪያው ኃላፊዎች በዚያ መምሪያ የተሰየሙበት የሞያ እና የብቃት አግባብነትም የላቸውም ከመመደባቸው በቀር ይህ ኋላ ቀር የሆነው አሠራር ለሙስና እና ለመንደርተኛነት አሠራር በሩን ወለል አድርጎ ከፍቶላቸዋል ቤተ ከህነቱም ብቃት ያለው አሠራር እና ሠራተኛ አንዳያገኝም በድሎታል ዛሬ ሰባኪ የሆነው እና ያልሆነው እንዳይለይ ያደረጉት ኋላ ቀር አሠራር ሙስና እና መንደርተኛነት ናቸው ቤተ ከርስቲያኒቱን አናድሳለን ብለው ለተነ አካላት ምቹ የሆነላቸው ቤተ ከህነቱ በኋላ ቀር አሠራር የተተበተበ በሙስና የሚሠራ እና በመንደርተኛነት የታጠረ መሆኑ ነው ገዳማት አድባራቱን ለመርዳትኮ ቤተ ከርስቲያን የገንዘብ ችግር የለባትም ልዩ ጽሐቤቱ በዓመት ሜሊዮን ብር ማውጣት ከቻለ የገንዘብ ችግር የለም ማለት ነው የጻድቃኔ ማርያም የቁልቢ ገብርኤልን እና የቤቶች ኪራይን ገንዘብ በሚገባ መጠቀም ከተቻለ ችግር ደኅና ሰንብት ማለት ይቻል ነበር ቤተ ከርስ ቲያኒቱ የአሠራር እንጂ የሀብት ችግር የለባትም እነዚሀን መሠረታዊ ቸግሮች ቀድመን ከፈታን ሌሎቹን ችግሮች ሁሉ ሳንፈታቸው ራሳቸው በራሳቸው ይፈቱ ነበር ይህንን ሁሉ ችግር ተመልከቶ ቆራጥ መፍትሔ መስጠት የነበረበት ሲኖዶሱ ነበር ሕግ ማውጣት አሠራር መዘርጋት ብቁ ባለሞያዎችን መመደብ ችግሮችንም በጊዜ መፍታት የነበረበት ሲኖዶሱ ነበር ነገር ግን እርሱ ራሱ ከላይ በተጠቀሱት ሦስት ችግሮች ተተብትቦ ነው ያለው እናም ለቤተ ከርስቲያኒቱ ቅንዓት ያላቸው አባቶች ምእመናን መንግሥት እና የቤተ ከርስቲያኒቱ ወዳጆች ሁሉ አሁን ፊታቸውን የሲኖዶሱን ችግር ወደ መፍታት ማዞር አለባቸው ባይ ነኝ የሲኖዶሱ ችግር ሲፈታ የቤተ ከህነቱም ችግር ይፈታል የችግሮቹ የስበት ማዕከል እርሱ ነውና ቅዱስ ፓትርያርኩም ሆኑ ሌሎቹ የሲኖዶሱ አባላት አሁን ለሚታየው የቤተ ከህነቱ ችግር ዋነኞቹ ተጠያቂዎች እና የችግሮቹም ምንጮች ናቸው ማለት ይቻላል እንደ እኔ አምነት አሁን ያሉት የሲኖዶስ አባላት አና የሲኖዶሱም አደረጃጀት እነዚሀን ሦስት መሠረታዊ የቤተ ከህነቱን ችግሮች ለመፍታት በሚያስቸል ዝግጁነት አደረጃጀት እና ብቃት ላይ አይደሉም ተግዳሮቶቿ ቤተ ክርስቲያን በአሁኑ ዘመን አራት ዓይነት ዋነኛ ተግዳሮቶች ገጥመዋታል የቋንቋ በሀገር ውስጥ ክልሎች በተለያየ የሥራ ቋንቋ መጠቀማቸውና ትውልዱም በየአካባው ቋንቋዎች ተምሮ ማደጉ ለቤተ ክርስቲያኒቱ ተግዳሮት ሆኗል በልዩ ልዩ ቋንቋ የሚያስተምሩ የሚቀድሱ እና የሚያገለግሉ አገልጋዮችን የማፍራት መጻሕፍይን የመ ተርጎም አሠራርዋን ከእነዚህ አንፃር የመቃኘት ሥራ አሉባት በሌላ በኩል ደግሞ ከሀገር ውጭ እየመጣ ያለው ትውልድ የየሀገሩን ቋንቋ ብቻ የሚናገር እየሆነ ነው ይህንን ትውልድ የቤተ ክርስቲያን ትውልድ አድርጎ መቀጠል ከተፈለገ ለርሱ የሚሆኑ አገልጋዮችን ማፍራት የመማርያ ሥርዓቶችን መቅረጽ አገልግሉቱን ከቋንቋ አንፃር መቃኘት ያስፈልጋል የፖለቲካ የሀገሪቱም ሆነ የዓለም የፖለቲካ ምሕዳር ተቀይሯል የተለያዩ የፖለቲካ ኃይሎች በአንድ ሀገር የሚፈጠሩበት ሁኔታ ተከስቷል የአንዲቷ ቤተ ክርስቲያን ልጆች የተለ ያዩ የፖለቲካ አመለካከቶች አሏቸው። ቤተ ክርስቲያን እነዚህን ተግዳሮቶች መመርመር መለየት እና ወቅታዊ ምላሽ መስጠ ት ይጠበቅባታል ይህንን ለማድረግ ደግሞ የቤተ ክህነቱ መስተካከልመጠናከር እና ነጥሮ መውጣት ወሳኝ ነው ፈተናዎች በአሁኑ ዘመን የሚታት የኢትዮያ ቤተ ክርስቲያን ፈተናዎች ሦስት ናቸው። መጻሕፍቷን ሠፍራ እና ቆጥራ አልጨረሰችም መልስ ቢኖራቸውም መል ሷን ያልገለጠችባቸው ጉዳዮች አሉ በቤተ ክርስቲያን ስም የሚወጡ ነገሮች የቤተ ክርስቲያኒቱን ቡራኬ እና ፈቃድ የሚያገኙበት ሥርዓት የለም አገልጋዮቿ በቁርጥ አይታወቁም ስሟን ለሚያጠፏት ሰዎች ይህ እኔን አይመ ለከትም የምትልበት መንገድ አልፈጠረችም አንዳንድ ጊዜ በሀብትነት በያዘቻቸው ነገር ግን የርሷን እምነት እና ሥርዓት በማያንጸባርቁ ነገሮች ሁሉ ተጠያቂ ትሆናለች የግራኝን ካባ የሕንዶችን የብርሃማኒስት መጽሐፍ የአሪስቶትልን እና የፕላቶን ፍልስፍና ቿብቃ ያቆየች መሆንዋ ተረስቶ ሁሉም የርሷ ጥፋት እየሆነ ይነገርባታል ቤተ ክርስቲያን የርስዋ የሆኑትን ሠፍራ እና ቆጥራ በመግለጥ የማይመለከቷትን አይመለከቱኝም ማለት ባለመቻሏ ስሟ በከንቱ እየጠፋ ነው በዚህ የተነሣ ዛሬ ተሐድሶ በየገዳማቱ ተሠግስነጎ ቅዱሳት መካናትን ለመቀሰጥ እየጣረ ነው በቤተ ክርስቲያኒቱ የትምህርት ተቋማት ሠርጎ ትምህርቷን ለማስለወጥ እየሠራ ነው ቤተ ክህነቱን ተገን አድርጎ ተሐድሶን ያነሣ ውሾ እያስባለ ነው በዓመት ከ በላይ ቤተ ክርስቲያንን የሚፃረሩ መጻሕፍት ያሳትማል ሰባት ጋዜጦችን እና አምስት መጽሔቶችን ያዘጋጃልፎ አራት ዌብሳይቶች ከፍቷል ማጠቃለያ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ላይ በየዘመናቱ የሚነሠሥ አጽራረ ቤተ ክርስቲያን በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ የሚያደርሱት ጉዳት በእነርሱ ዐቅም መጠን ሳይሆን በእኛ ዝግጅት እና ጥንካሬ መጠን የሚለካ ነው አርዮስ ቢነሣ አትናቴዎስ ነበረ ንስጥሮስ ቢነሣ ቄርሎስ ነበረ ልዮን ቢነሣ ዲዮስቆሮስ ነበረ ካቶሊኮች በኛው ክዘን ቢነሥ እነ እምነ ወለተ ጴጥሮስ እነ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ጴጥሮስ ነበሩ ጣልያን አምስት ዓመት መከራ ቢያመጣ እነ አቡነ ጴጥሮስ ተነሥተውላት ነበር አጽራረ ቤተ ክርስቲያን እንዳይነ ማድረግ አይቻልም እንክርዳዱን የሚዘራው ሌላ ነውና መፍትሔው እንክርዳዱ በስንዴው መካከል እንዳይዘራ ነቅቶ መጠበቅ ከተ ዘራም እርሻውን ፈጽሞ ከመዋጡ በፊት በጊዜ ማረም ነው ጌታችን በማቴ ባስተማረን የስንዴው እና የእንክርዳዱ ምሳሌ ጠላት እንክርዳዱን የዘራው የስንዴው ቿ ባቂዎች በተኙ ጊዜ ነው ምንጊዜም እንክርዳዱን በስንዴው ውስጥ እንዲበቅል በቅሎም ስንዴውን እስከመዋጥ ድረስ እንዲደርስ የሚያደርገው ሲብስም ማረም እስከማይቻልበት ደረጃ የሚያደርሰው የገበሬዎቹ መተኛት ነው በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ችግሮች ተግዳሮቶች እና ፈተናዎች ይኖራሉ ፈተናዎቹ እና ተግዳሮቶቹ ከውጭ ወደ ውስጥ የሚመጡ ናቸው ችግሮች ግን ከውስጥ ወደ ውጭ የሚመጡ ናቸው እኛ ውስጣችንን ካጠነከርን የትኛውም ዓይነት ፈተና ቢመጣ አያስ ጨንቀንም።

  • N.B. This Summary is Very Experimental!! based on the following scripts from:
    • https://github.com/millzon/textSummarizer-am
    • https://github.com/icoxfog417/awesome-text-summarization#motivation
Download Searchable PDF Download PDF

አስተያየቶች:


memezon

የማውረድ አማራጮች | ወደ ፒዲኤፍ ቀይር | የዕለቱ መጽሐፍ

© dirzon | የአገልግሎት ደንቦች | የግላዊነት መምሪያ | ስለ | አገልግሎቶች | መልእክት