Detecting...

Please whitelist dirzon to continue.

or subscribe for ad-free contenct.

dirzon
  • Convert to Pdf
  • Reading List
  • Summary
  • Audiobook
  • Search
  • Upload
  • myzon
  • Log in
  • Register
English  አማርኛ  Français  العربية
Book of the day

የትንፋሽ_ማዕበል፣_ቅጣው_ተክለማርያም_.pdf


  • word cloud

የትንፋሽ_ማዕበል፣_ቅጣው_ተክለማርያም_.pdf
  • Extraction Summary

አርፏል ሞቷል አልኩ ጥርሶቼን ጨፍልቄ እንደማንገጭገጭ እያልኩ የ ወር የቲቢ ህክምና ስትወስድ የመጀመሪያህ ነው። እስሬ አንገቴ ስር ተወሽሸሽቃ በከረመችበት ጊዜ ሳስልባት ሳስነጥስባት ስተነፍስባት በዚህ አስከፊ የቲቢ በሽታን ካወቀው በኋላ በተለይ ለልጁ ትልቅ ስጋት ውስጥ ገብቷል አይኗን ብቻ አይቶ ሳይዳብሳት መመለስ ቁጭት ውስጥ ከቶታል ወደ ዋርዱ ሲመለስ ደግሞ የሁለት አመት ህፃን በሞ ላትመለስ ሄዳ እናት በሰቀቀን እየጮኸች ስታለቅስ ደርሷል ሁላችንም ወደ ልጆቻችን በሀሳብ ቆዝመን እንደሄድን ሳንነጋገር በዝምታ ተኛን ከውድቀት ለሊት በኋላ የሆዴ ነገር ምቾት ነሳኝ በከፍተኛ ደረጃ ፈጥሮ የማይረሳ ትዝታዎችን ይሰጣል ቀን ላይ አልፎ አልፎ እየሠካሁት ነው ለሊትም ቢሆን የመቆጣጠሪያ ቁትሩን ሁለት ላይ አድርጌ በስሱ እየተጠቀምኩ ነው የማድረው በቅርቡ ከአጠገብህ እንደሚነሳ ተስፋ አደርጋለሁ የቆመውን የኦክስጅን በርሜል እያሳየችኝ በምትፈልገው ጊዜ ልትውልልኝ ትችላለህ አሁን ከነገ ወዲያ እዚህ ግቢ የማዘጋጃት ዝግጅት እየሠራሁ ስለሆነ ልሂድ ሲስተር አይናለም የምን ዝግጅት ነው። መርፌ መርፌ ወንዶቹ ባይወጉኝ ይሻላል ሴቶቹ ጠንቃቃ ነቸው የነሱ አያምም የሚገርም ነው ወንዶቹን ሴቶቹ ወንዶቹን ይመርጣሉ የተሻሉ ናቸው ብለው ያምናሉ ምክንያቱ ለእኔ አይገባኝም አብዛኛዎቹ ግን ምርጫቸው ተቃራኒ ፆታቸው ነው ከገባችሁ ምክንያቱን እናንተው ንገሩኝ አሁን ትንሽ ደከም ስላኝ መኝታዬ ላ ጋደም ብዬ ኦክስጅን በመጠኑ ተጠቀምኩ በማስከተል ወደ እዮብ ወማርያም የሜተኛበት አንድ አልጋ ብቻ ያላት ክፍል አመራሁ አንድ እግሩን ወጥሮ ዘርግቶ ማፍ አይችልም ተለጥጦ ተቀምጦአል ድምፃዊ እዮባ ሰላም ነው ልጨብጠው እጄን ብዘረጋለት ለካ ቀኝ እጁ ታጥፎ ቀርቶ ስለማይታዘዝለት በግራው መዳፌን ያዝ አርጎኝ ጎኑ ቁጭ አልኩ እዩካ መድኃኒት እየወሰድክ ወደ ውጭ ወጣ እያልክ ጠጅ ትጠጣለህ ይላሉ እውነት ነው።

  • Cosine Similarity

የቅጣው ተማርያም የትንፋሽ ማዕበል ቅጣው ተክለማርያም አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ከደራሲው ፍቃድ በማግኘት የማሳተምና የማከፋፈል መብታችሁ የተጠበቀ ነው የቀደምት ስራዎች የትውልድ ስጋት ቁጥር የትውልድ ስጋት ቁጥር ዘጋቢ ፊልሞች ድርሰትና ዝግጅት ዲዛይን ፅ ቅጣው ተክለማርያም ትየባ ሐዊ ገብሬ ሽፋን ሚኪያስ ወርቁ መታሰቢያነቱ በቲቢ እና መድሃኒቱን በተለማመደ ቲቢ በህመም ስቃይ ላሳለፉ ብሎም ህይወታቸውን ላጡ ለዓለም ወገኖቻችን ክብርና ምስጋና በጤናው ዘርፍ ለሚሰሩ ኢትዮጵያውያን ወገኖች በተለይ ለቅዱስ ሌሴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሰራተኞች በሙሉ የካቲት ሆስፒታል የድንገተኛ መውጫው በር ላይ ቁጥር ታርጋ የለጠፈች የግቢው አንቡላንስ አፍንጫዋን ወደ አደባባዩ አዘሩ የኋላ ሁለት በሮቿን ከፍታ ባዶዋን ሞተሯ ሥራ ላይ ሆኖ ለቀጣይ ተግባሯ በዝግጁ ቆማለች ሹፌሯ ሥራ ላይ ሆኖ ለቀጣይ ተግባሯ በዝግጁ ቆማለች ሹፌሯ መረጋጋት የፈጠረበት አይመስልም ልክ እንደ አንቡላንስ ችኩል ችኩል ይላል ቀስ ብሎ አይራመድም ገባ ወጣ ይላል ከመኪናዋ አይን ግን ፈፅሞ መራቅ የሚወድ አይመስልም በዝግጁነት እንደሚጠብቅ ያስታውቃል ሶስት የህክምና ባለሙያዎች የድንገተኛ ክፍሉ ውስጥ ከተኙ የእሳት ቃጠሎ ከደረሰባቸውና አሲድ ከለበለባቸው ታካሚዎች መሀል በተለያየ ምክንያት ከተኙት ውስጥ አንደኛው ስትሬቸር ላይ ተደርድረው ቆመዋል አቶ ቅጣው ተማርያም አለኝ አንዱ ባለሙያ አቤት አልኩት ብዙም በማይሰማ ድምፅ አይኖቼን ፊቱ ላይ ተክዬ አተነፋፈስህ እንዴት ነው የሚያፍንህ ነገር አለ አለኝ ቁልቁል እየተመለከተኝ ድካሙ ነው እንጂ ጥሩ እንደሆንኩ ነው የሚሠማኝ አልኩት የገረጣ ፊቴን ፈገግ ለማድረግ እየሞከርኩ ከተገጠመለት ኦክስጂን ጋር ሲለካ ነው እያነበበ ያለው አለች መሀላ ላይ የቆመችው የጤና ባለሞያ ሌባ ጣቴ ላይ የሠካቻትን መመርመሪያ እየነቀለች ፐልሱም ለአደጋ የሚሰጥ አይደለም ኦክስጂኑን ከአፍንጫው ነቅላች ነበር ብሎ በማመላለስ እኔንም እሷንም ተመለከተን መተንፈሻ ማሽኑ ተነቅሎ ከ ደቂቃ በኋላ ለክቼው ነበር ነው ያገኘሁት አለችው በሜራራ አይን አዘቅዝቃ እያየችኝ እንግዲያውስ ከዚህ እስከ ቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል እስከምናደርሰው ጊዜ ይኖረናል ማለት ነው አለ ሶስተኛው ሰው የህክምና መዝገቤን እያገላበጠ አይኖቹን ከወረቀቶቹ ሳይነቅል በሉ መፍጠን አለብን ጊዜያችንን በአግባቡ እንጠቀም ጣደፍ ጣደፍ እያለ ግራና ቀኝ ባሉ ታካሚዎችና አስታካሚዎች መሀል ሰንጥቆ በስተግራ ወደሚገኘው የምርመራ ክፍል ገባ ከዚህ በኋላ ህክምናህን የምትከታተለው ሌላ ሆስፒታል ነው አንቡላንስ ቆሟል መዝገቡን እየዘጋ አወራኝ አጠገቤ የቀረው ሰው የት ሆስፒታል ነው የምሄደው ለማረጋገጥ ጠየኩት ቅዱስ ጴጥሮስ እንሄዳለን ብዙም አይርቅም በትንሽ ደቂቃዎች እንደርሳለን መፍጠን ግን ይጠበቅብናል እንስቷ ባለሙያ መለሠችልኝ ሆስፒታሉን አውቀዋለሁ ታላቅ ወንድሜን አስታምሜበታለሁ መጣደፉ ግን ለምንድን ነው ጥርጣሬ ተሰምቶኝ ጠየኩት አንቡላንሱ ላይ ኦክስጂን የለም አንተ ደግሞ በቂ ጊዜ ያለ ሰው ሰራሽ መተንፈሻ መቆየት ስለምትችል እንዲሁ ልናደርስህ አስበን ነው አለኝ በእግሬ በኩል እጁን አጣምራ አይኖቿን አንድ ቦታ ተክላ ለፈዘዘችው የልጄ እናት ትዕዛዝ በሚመስል መልኩ እቃዎችሽን ሰብሰብ ሰብሰብ አርጊ አለቻት ቀኑን ሙሉ በነፃነት መተንፈስ እችላለሁ መሀል መሀል ላይ ልታፈን ለጨናነቅ ይሆናል እንጂ ለክፉ እኮ አያደርሰኝም ተረጋጉ አልኩ በማይሰማ ቀርፋፋ ድምፅ የእናቴ ሆድ ወደፊት ተወጥሮ ለዘጠኝ ወራት በማህፀኗ ከኖርኩ በኋላ በ አብዮቱ በአገራችን በፈነዳ ሠሞን መስከረም ቀን ተወለድኩ ፈነዳሁ አልወጣኝም አሁን ተልብማ ፀጉር ነው ያለኝ ነጫጮቹ በርከት ብለዋል ዓመቴ ነው ቁመቴ ሠውነቴ ከመገርጣት አልፎ አጥንቶቼ ብቻ በመላ አካላቴ ገጠው ቆዳ ለብሠዋል ስጋ ለአመል በብሩሽ እንኳን የተቀቡ አይመስሉም አይኖቼ ከመንጣታቸው ሌላ ወደ ውስጥ ጎድጉደዋል ፀጉሬ በከፊል የተነቃቀለ ይመስላል ሙልጭልጭ ብሎ ሳስቷል የእጄን ጣቶች ሳያቸው የእኔ አይመስሉኝም ስልል ብለው ረዘሙብኝ የምግብ ጉልኮስ ተገጥሞልኛል የሽንት መውረጃ ቱቦ ርከጪ በብልቴ ውስጥ ዘልቆ ተጠምዶአል ሽንቴን መቆጣጠር አልችልም ምግብ ከተመገብኩ ቀናት ስላለፉኝ በሠገራ በኩል ማስቸገር ካቆምኩ ሠንብቻለው መላ አካላቴ መንቀሳቀስ አይችልም አንገቴ ብቻ ከግራ ወደ ቀኝ በእርጋታ ይዘዋወራል አይኖቼ አጣርተው ያያሉ መላ አካባቢው ላይ ይቅለበለባሉ ጆሮዎች ኮሽታ ሳይቀር አጥርተው ይሠማሉ ሌላ ነገሬ ግን በድን የሆነ ይመስለኛል ለቀናት ስተነፍስበት የነበረው ሠው ሰራሽ ኦክስጂን ተነቅሎልኝ በስትሬቸር እየገፉኝ አዲስ ለህክምና የገቡ ቀድመው ለቀናት ግራና ቀኝ የተኙ ታካሚዎችና አስታማሚዎች ብሎም ጥቂት ጠያቂዎችና የሚዋከብ የህክምና ባለሙያዎች መሀል ለመሀል እየሰነጠቅን በታላቅ አክብሮት መንገዱን እየለቀቁልን በከፊል እግዚአብሔር ይማርህ ይማርልሽ አይዞህ አይዞሽ እያሉ እኔንም የልጄን እናትም ሸኙን አብዛኛዎቹ ሴቶች በተለይ እናቶች አንቡላንሱ ድረስ ከንፈር በመምጠት ምፅ ምጭጭ የሚሉ ድምፆች በተለያየ ፍጥነት ቅጥነትና ውፍረት ሲያሰሙ የሆነ የመቆርቆር ስሜት የማዘን ቅላፄያቸውን ስሰማ በአንድነት የሆነ የሚኮረኩር ዜማ ይሠራ ነበር አንቡላንሱ ከኋላ ያለው ቦታ ላይ አስገብተው በጀርባዬ አስተኙኝ የሽንት ማጠራቀሚያውን ወለሉ ላይ ተደረገ ጉሉኮሴ ተንጠልጥሎ በእርጋታ ተከፍቶ ግማሽ ድረስ ተገባዷል ግን አይወርድም ተከፍቶ እንኳን ምንም የሚንጠባጠብ ነገር የለም የልጄ እናት የሸከፈቻቸውን እቃዎች ካስገባች በኋላ በግርጌ በኩል የገባንበት በር ጋር በስተቀኝ ቁጭ አለች አቅፎ ደግፎ ወደ ውስጥ ያስገባኝ ነርስ ከመውረዱ በፊት እባክህ ከወገቤ ከፍ ታደርገኝ አልኩት ብፈገግ እንኳን የማያምርብኝን የገረጣ ፊቴን ፈታ ለማድረግ እየሞከርኩ እዴታ በሚገባ ይቻላል እንጂ አለኝ የተኛሁበትን ስትሬቸር ከወደ እግርጌው ነካ ነካ ሲያደርገው ከወገቤ በላ ከፍ ከፍ እያለ በከፊል እንደመቀመጥ አልኩ ኩለ በምቾትና በፍጥነት እናደርሳችኋለን ምንም ስጋት እንዳይሠማችሁ ብሎ ዘሎ ወረደና የኋላውን በር ገጭ አድርጎ ዘጋው ወደ ጋቢናየፊት ወንበር አመራ ሾፌሩ ለመንዳት እንደቸኮለ ያስታውቃል እግሮቹ ሲራመዱ ፈጠን ፈጠን ይሉ ነበር አይኖቹም ከቦታ ወደ ቦታ ቶሎ ቶሎ ይቅለበለባሉ ብቻ ሁሉ ነገሩ ችኩል ነው የኋላውን መስታወት ከፈት አደረገና መንቀሳቀስ ልንጀምር ነው ሀሳብ አይግባችሁ ጥርሴን የነቀልኩበት ነው አብርሐም እባላለሁ አሁን ነው የማደርስህ ተረጋጋ አትጨናነቅ ብሎ ተናግሮ ሳይጨርስ መስታወቱን አንሸራቶ ዘጋው ሲያወራም ይፈጥናል ርጋታ የሚባል ነገር አልፈጠረበትም ደግሞ ሲናገር በጣም ይጮሀል ልክ እንደመኪናዋ መጣደፉም ከስራው ጋር የተያያዘ መሠለኝና የዳምጠው ሾፌር ቢሆን ኤሊ ሊሆን ነበር አልኩኝ ለባለቤቴ እሷ ግን የሰማችኝ አይመስልም አንቡላንሷ ጭንቅላቷ ላይ ያለውን ቀይ መብራት አያውለበለበች እንደሆነ ይሠማኛል ገና ከሆስፒታሉ ፊት ለፊት ያለው የስድስት ኪሎ አደባባይ መዞር ስትጀምር ዋይ ዋይ እያለች መጮህ ጀመረች ቀና አድርገው በጀርባዬ ስላጋደሙኝ አልፈን የምንሄደውን ጎዳና እናቴን ለሾፌሩ ስለሰጠው ወደኋላ ውጭውን ማየት እችላለሁ ግርግሩ የመኪናዎቹ ሁካታ የሠው ትርምስ ለተከታታይ ቀናት ተለይቼው ስለነበር አሁን ስመለከተው እንደናፈቀኝ ታወቀኝ አደባባዩን ዞረን ቀጥታ በአሜሪካን ኢንባሲ መስመር ዳገቱን ወደ ሽሮሜዳ መስመር መጓዝ ጀመርን አንቡላንሷ ድምፅ ቀይራለች የልጄን እናት ቀና ብዬ አየኋት ተስፋ የመቁረጥ ይነበብባታል ላለፉት ቀናት ወገቧ መኝታ ሳያገኝ ማንም ሳይተካት ቀን ከለሊት ወንበር ላይ ቁጭ ብላ አሳልፋለች ማንቀላፋት እንኳን ቢያስፈልጋት እንደተቀመጠች የተኛሁበትን ደገፍ ትላለች እንጂ ተጋድማ አታውቅም ድክምክም ብላለች አኮራሁሽ አይደል አልኳት ድምፅ ለመጨመር እየሞከርኩ አይዞህ እኔ ግን እንደምትድን አምናለሁ አለችኝ እንደፈዘዘች እንዴት ትጠራጠሪያለሽ ልክ እኮ ነሽ አሁን ደግሞ ልብ አላልሽም መሰለኝ መኪናው የሚያሰማው ድምፅ ባለሥልጣን ያጀበ ሞተር ሳይክል የሚያሰማው አይነት ነው መንገዶች በክብር እየተለቀቁልን ነው የብዙ መንገደኞች አይን እየሸኘን ነው በእርግጠኝነት ደግሞ ሁሉም መልካም እየተመኙልን በሁለት የጤና ባለሙያዎች ታጅበን ምንም አይነት ገንዘብ ሳንከፍል አክብረው እየወሰዱን ነው ስለዚህ ዘና በይና ተቀመጭ ባለስልጣኗ አንቺ እኔ ደግሞ የክብርት ባል ነኝ አብዬ ደግሞ ድንቅ ልጃችን ነች አልኳት ላበረታታት እያሰብኩ አንተ መቼም በዚህ ሰዓትም ትቀልዳለህ በል ብዙ አታውራ ተብለኃል ዝም በል እረፍት አድርግ ኦክስጂን ያጥርሃል ዝምታ በመካከላችን ነገሠ በምናባችን በአካባቢው እንዳልነበርን ያስታውቃል አብሳላት የአብራካችን ክፋይ አንድ ልጃችን ነች ገና ሁለት ዓመት ከስምንት ወር እድሜ የያዘች ሴት ደስተኛ በአስተሳሰቧ ፈጣን በጣም በጣም በምድር ላይ መኖር ከጀመርኩ ጀምሮ እንደሷ የወደድኩት ሠው የለም በፍቅር ነው የምወዳት እንደውም እሷን ከማግኘቴ በፊት የወደድኳቸውን ሠዎች መውደዴን እስክጠራጠር ድረስ መናፈቅ ብሎም ለሌላ ሠው መጨነቅ የጀመርኩባት የመጀመሪያዋ ነች የመውደድ ጥጉ ላይ መድረሴን ግን እጠራጠራለሁ ለምን አትሉኝም ከአብሳላት ልጄ በፊት ለኖርኩባቸው ዓመታት ከቤተሰብ አባላት ጀምሮ አሳዳጊዎቼን እንዲሁም በተለያየ ጊዜ ያገኘኋቸውን በርካታ ሠዎች ከልቤ በመጨረሻው መውደድ ፍቅር የወደድኳቸው መስሉኝ ነበር አብቲ ስትመጣና ከጨቅላነት ግዜዋ ጀምሮ እለት በእለት ገላዋን በጥንቃቄ በእጆቼ ሳጥባት በእቅፌ አንገቴ ስር ስከታት ጠረኔን በአፍንጫዋ ስትስብ መአዛዋ ያልተነካካ ያልተበረዘ ሰው ሰው ልጅ ልጅ ሲሸተኝ ጥርስ ባላበቀለ ድዷ ፈገግታ ስትመግበኝ ያልተበረዘ ለማሳመር ያልተሞከረ እንደወረደ የተፈጥሮ የህፃንነት ሳቋን እና ለቅሶዋን እየመገበችኝ ተንገዳግዳ መራመድ ጀምራ በተኮላተፈ ማር አንደበቷ አባ አባዬ ብላ ጠርታኝ ተኝታ ተማምናብኝ ክንዴ ላይ እንቅልፏን እየለጠጠች ታድር በነበረበት ጊዜ ነው ብን ብን የሚል ሳል የጀመረኝ በመጀመሪያዎቹ ጊዜያት እንደ ኢትዮጵያዊነቴ ትኩስ ትኩስ ነገር ቤት ውስጥ ተሰጠኝ ለውጥ አልነበረም ለሊት ስተኛ ያልበኝ ጀመር ስራ ላይ የማሳልፈው ጊዜ እየቀነሰ ድካም እየበረታብኝ መጣ ሄድ የሚል ትኩሳት ጀመረ የምግብ ፍላጎቴ ቀነሰ በዚህ ግዜ አቅራቢያችን የሚገኝ የግል ከፍተኛ ክሊኒክ ሄድኩ ከካርድ ጀምሮ የላብራቶሪ ምርመራን ጨምሮ ሞቅ ያለ ክፍያ ተከፈለ ውጤት ተነገረኝ የተበከለ ውሃ አልያም ምግብ ሳትመገብ አልቀረህም ታይፉድና ታይፈስ ይታያል ተባልኩ የመድኃኒት መአት ታዘዘልኝ ገዛሁና አወሳሰዱ ተፅፎልኝ ወደ ቤት ተመለስኩ ክሊኒክ እያለሁ አንድ ወሳኝ ፍቱን መርፌ በመቀመጫዬ ተወግቼ ነበር መርፌ መወጋት ስማልወድ ይቅርብኝ ብዬ ነበር ይሁንና ግን አሁን ጥሩ ስሜት ስለሰጠኝ ብሉም የህመም ስሜቶቼ በሙሉ ጠፍተው ደህንነት እንዲሰማኝ ስላደረገች ያቺን የመጀመሪያዋን መርፌ አደነኳት ልጄን እያጫወትኩ ሠላማዊና የተረጋጋ ደስ የሚል ለሊትን አሳለፍኩ በንጋታው ግን በዛው አልቀጠለም በበረታ መልኩ ድካሙ ጨመረ እርምጃዬ የማዝገም ያህል ሆነ የጀመርኩትን መድኃኒቶች ሰዓት እየጠበኩ መዋጥ ተያያዝኩ ቀን ቀንን እየተካ የኪሂኒኖቹ ቁጥር እየቀነሰ መጣ አገባደድኳቸው በጤናዬ ላይ ግን ለውጥ የለም ትኩሳቴ መረን ለቀቀ ለሊት የሚያልበኝ ላብ አካባቢውን ማርጠብ ጀምሮአል የምግብ ፍላጎቴ ከመቀነሱ ባሻገር የምግብ መአዛ በአፍንጫዬ ሲገባ ያቅለሸልሸኝ ጀምሮአል ከቤት የምወጣበት ጊዜ ቀርቶ አብዛኛውን ጊዜ መኝታዬ ላይ ማሳለፍ ጀመርኩ ብን ብን ይል የነበረው ሳሌ ደረቅ ነው ግን ያጣድፈኝ ጀመር አንዴ ከጀመርኩት ማቋረጥ የለም ነፍስ ውጭ ነፍስ ግቢ ነው ደረቴን ደግፌ ለጉድ አስለዋለሁ በዚህ ጊዜ አጠገቤ ያለችውን ህፃን በጉንፋን ኢንፍሊዌንዛ ይመስለኝ ስለነበር እንዳትያዝብኝ በስጋት ፊቴን አዞር ነበር አይዞህ አባ አይዞህ አባዬ ስትለኝ ከፊት ለፊቴ ድቅን አለችብኝ ካየኋት ቀናት አልፎኛል ድምጺ ናፈቀኝ እንባ አይኔ ላይ ግጥም አለ ማልስ አልፈለኩም ወደ ውስጥ ዋጥ አደረኩትና አጠገቤ ያለችውን እናቷን ተመለከትኳት በሐሳብ ነጉዳለች ተከታትለን ወደ ልጃችን እንደሄድን ገባኝና አይኖቼን ጠረግረግ አድርጌ አንቡላንሷ ወደ ቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል መግባት መጀመሯን ከመግቢያው በር ፊት ለፊት ወደሚታየው የጣራው ክዳን ቀይ ከለበሰው የራስ አበበ አረጋይ መኖሪያ ቤት ነበር ተብሎ የሚነገረው ጥንታዊ ባለ አንድ ፎቅ በአሁኑ ጊዜ የቲቢ ህክምና ከሚሰጥበት አቅጣጫ መጓዝ ጀምረናል ከመግቢያው በር ወደ ውስጥ እንደዘለቅን በስተግራ ገዘፍ ያለ ህንፃ በመገንባት ላይ ይገኛል ከሰዓት በኋላ ሰዓት አካባቢ ነው ወቅቱ ሐምሌ በመሆኑ የክረምቱ ቅዝቃዜ ይሰማናል እንደምንም ድምፄን አሰባሰብኩና ለሚ ደርሰናል አልኳት በተቆራረጠ ድምፅ የልጄ እናት ካቀረቀረችበት ቀና ሳትል ሳታስበው አንባዊቿ በሁለቱም አይኖቿ ወረዱ ምነው እናቴ አብሳላት ጋር ሄድሽ አይደል አልኳት እንባዋን ለመቆጣጠር ስትሞክር አዎ ናፈቀችኝ በጣም ናፈቀችኝ ስትል ግን መቆጣጠር አልቻለችም ነበር እኔስ ብትዬ መቼ ይሆን የማገኛት አልኩኝ ሲቃ በተናነቀው ስሜት እንባዬ ወረደ በዝምታ ተላቀስን አንቡላንሷ ባለ አንድ ፎቁ ጋር እንደደረሰች ወደ ግራ ታጠፈችና ትንሽ ተጠግታ ቆመች ሁለቱ የህክምና ባለሙያዎች በፍጥነት ወርደው እኛ ያለንበትን የኋላ በር ከፍተው ፍቅር በተሞላበት ስሜት መድረሳችንን አብስሮን የሪፈራል ወረቀቱንና ሲደረግልኝ የነበረውን ክትትል ሙሉ ለሙሉ የሚገልፀውን የህክምና መዝገብ ቤት ይዘው ወደ ሆስፒታሉ ድንገተኛ ክፍል ዘልቀው ገቡ ብዙም ሳይቆይ ይዘውን የመጡት ሁለት የህክምና ባለሙያዎች የሆስፒታሉ ሰው ሳይሆን አይቀርም አንድ ሌላ ነጭ ጋዋን የለበሠ ወጣት ጨምረው ባዶ ስትሬቸር እየገፉ አምጥተው አንቡላንሱ የኋላ በር ላይ ደቀኑት ተረዳድተው እቅፍ ድግፍ አድርገው አውርደው በጀርባዬ አጋደሙኝና የቆምንበት ፊት ለፊት ያለውን በር አዝልቀው አስገቡኝ በወቅቱ የድንገተኛ ህክምና አገልግሎት የሚሰጥበት ቦታ ከሚገኙ አምስት ክፍሎች ውስጥ እንደገባን በስተቀኝ ታጥፈው የመጨረሻው ክፍል ውስጥ አስገቡኝ ግራና ቀኝ ሁለት ታካሚዎች የተኙበት ቦታ ላይ መሀል ክፍት የሆነ አልጋ አጠገብ አስጠጉኝ ሁለቱ የጤና ባለሙያዎች ለተከታታይ ቀናት በኦክስጂን ነበር የሚተነፍሰው ግጠሙለት ብለው እዚህ ይንከባከቡሃል ጥሩ ቦታ ነው የመጣኸው አይዞህ በርታ በማት በንፅህና የተነጠፈው አልጋ ላይ ተጋግዘው ካስተኙኝ በኋላ ወደገባንበት በር በፍጥነት ገሰገሱ ችኩልኩል የሚለው የአንቡላንስ ሹፌር ጋር እንደሆን የሚሄዱት ሲታወሰኝ መቸኮላቸው ብዙም አላስገረመኝም ጊዜ ያለአግባብ መባከን የለበትም የሚል ነው የሚመስለው ይሄኔ አይጠብቃቸው ይሆናል ብዬ አሰብ አደረኩና እንደባለስልጣን አፍነሽንሾ ሳያንገላታ ስላመጣኝ ከልቤ አመሰገንኩት እያክለፈለፈ ወደ ህክምና ካመጣቸው በሽተኞች አንዱ ስለሆንኩ መዳንን ተመኘሁ የተኛሁበት አልጋ ተመችቶኛል ላለፉት ቀናት በደረቅ ሰውነቴ ስትሬቸር ላይ ተኝቼ እንደነበር ከመቅስፈት ረሳሁት ተደላድዬ በጀርባዬ ተጋድሜያለሁ ለምለም የምግብ አቃዎቹን ከመጠጫዎቹ መደርደር ይዛለች በስተግራ ዙሪያውን አልጋው የተጋረደ ታካሟ ተኝቷል አይታየኝም ወደ መኝታው እየገቡ የሚወጡት የቤተሰቡ አባላት የሚመስሉት ግን ተደናግጠዋል ሁሌም በሀዘን ተውጠዋል የባሰበትና ኮማ ውስጥ ገብቶ ለሞት የሚጠበቅ ይመስላል በስተቀኝ በእድሜያቸው ገፋ ያሉ አዛውንት ሁለት ልጆቻቸው በሚመስሉ ወጣቶች ግራና ቀኝ ተከበው ተኝተዋል አዲስ ገቢ ነኝና በፀጥታ ያዩኛል በክፍሉ ውስጥ የሚሆኑ ባለሙያዎች ወጣ ገባ ይላሉ አንዲት ዶር ፊቷ ላይ ብስጭት እና ንዴት ብጤ በገሃድ ይታያልያለፈውን የህክምና ካርዴን ገለጥ ገለጥ አድርጋ ካየች በኋላ እንደተበሳጨች ተጠጋችኝ ምን አይነቶቹ ናቸው የአከታ ምርመራ ማድረግ እንዴት ይሳናቸዋል ቲቢ ነው ካሉ መመርመር ነበረባቸው አጠገቤ ቆማለች ብስጭቷ አለቀቃትም ቅጣው መጀመሪያ ቲቢ እንደተገኘብህ መቼ ነው ያወከው መናገር አልቻልኩም ቁና ቁና እተነፍሳለሁ መጨናነቅ ጀምሬያለሁ እንደመታፈን እያደረገኝ ነው ኦክስጂኑን ላኩልኝ አለች በተበሳጨ አንደበቷ ከመቅፅበት አጠገቧ ያለችው መልከ መልካም ነርስ የሌባ ጣቴ ላይ መለኪያ መሳሪያውን ሰካችልኝ ቀኝ እጄን ሰብሰብ አድርጋ ቀጭን ጡንቻዬ ላይ የደም ግፊቴን መለኪያ ተግባር መተግበር ጀመረች ጆሮዎቿ ላይ ማዳመጫውን ከሠካች በኋላ በእርጋታ ማዳመጥ ጀመረች የግራ ጣቴ ላይ የተሰካውን መሳሪያ እያወለቀች ምን አይነቶቹ ናቸው እነሂህ የማይረቡ እንዴት ካለ ኦክስጂን ያመጡታል ብሽቆች ናቸው አፍጥኑት ኦክስጂን አምጡ በቁጣ ተናገረች ጣቴ ላይ እንዳለ ቀና አድርጌ አይቼው ነበር የኦክስጂን ልኬቴን ይላል ፐልስ ዘጠና ሁለት ጥሩ ነው አተነፋፈሴ ተዛብቷአል አፍና አፍንጫዬን የሆነ ሰው ይዞ እያፈነ ያዝ ለቀቅ እያደረገኝ ይመስል እየተጨናነኩ ነው አካባቢዬን በትክክል ማስተዋል እየተሳነኝ መጣ አፍና አፍንጫዬ በአረንጓዴ የትንፋሽ መከላከያ ማስክ ተደርጎልኝ ስለነበር እሱ ያፈነኝ ይመስል ከፊቴ ላይ ለማንሳት እወራጫለሁ ችግሩ እሱ አይደለም ቅጣው ቆይ ይኹው መቶልሀል ኦክስጂን ይኸው ማስኩን አታውልቅ እወራጫለሁ ብዙ ነገሮች የቅዣት ያህል ነው የሚሰማኝ ህልም የሚመስል ነገር ማየት ጀመርኩ ውዷ ልጄ አባ አባቴ የሚለው ድምጺ ይሰማኝ ጀመር ዛቄቋ ቄ ታይፎድና ታይፈስ ተብሎ የታዘዘልኝን መድኃኒቶች ወደ መጨረሱ ደርሻለሁ ጤናዬ ግን ከእለት ወደ እለት እየባሰብኝ ነው ከመጀመሪያው ህክምና በኋላ ለሁለት ጊዜ ያከመኝ ሐኪም ጋር ተመላልሻለሁ ቢሆንም ግን መድኃኒቱን እስከመጨረሻው መውሰድ እንዳለብኝ ያኔም እንደሚሻለኝ ከመንገር በተጨማሪ ያቺን መጀመሪያ የተወጋኋትን ፍቱን የህመም ማስታገሻ ትመስለኛለች እወጋና ተረጋግቼ ጥሩ ስሜት ተሰምቶኝ አድራለሁ አሁን ድጋሚ መሄድ አልፈለኩም ሌላ የህክምና ቦታ እንደሚያስፈልገኝ ጎረቤቶች ጓደኞቼ የወዳጆቼ ቤተሰቦች በሙሉ መከሩ እሁድ ቀን ነው ብዙ ነገሮቼ ጥሩ አይደሉም በሁለት ሰዎች ግራና ቀኝ ድጋፍ የተወሰነ እንቀሳቀሳለሁ ደረቴን በቀኝ በኩል ውጋት የቀላቀለ ከፍተኛ ህመም ይሰማኛል በጀርባዬ ካልሆነ በጎኔ መተኛት ቀርቷል አልፎ አልፎ ፋታ የማይሰጥ ሳል አለ ምግብ ፍላጎቴ ጠፍቷል ክብደቴ ከመጠን ያለፈ አሽቆለቆለ የተስተካከለ እንቅልፍ የለም ሸለብ እያደረገ ያነቃኛል የቅርብ ጓደኛዬ መኪና ይዞ መጣ ከምኖርበት ገርጂ ወደ መገናኛ አካባቢ ወደሜገኝ ስመጥር ከፍተኛ የግል ክሊኒክ ሄድኩ ምርመራ ክፍል ውስጥ ከትልቁ ወንድሜ ጋር ገባሁ አስፈላጊው ጥያቄዎች ተጠየኩ መለስኩ የደምና የሠገራ ናሙና ሠጠሁ ውጤቱ እስኪመጣ ድረስ አንድ አልጋ ተሰጠኝና በተከታታይ ሁለት ጉሉኮስ በፍጥነት እየወረደ ወሰድኩ አንዱን ጠጣሁ ሌላ በምግብ ጉሉኮስ ውስጥ ተደርጎ ተሰጠኝ አሁንም ፈጣን የሆነ የህመም ማስታገሻ ተወጋሁ ማበረታቻ ቫይታሚኖችን ተሰጠኝ ጥሩ አይነት ስሜት ተሰማኝ ተነቃቃሁ ቆሜ ለብቻዬ በእግሬ ተንቀሳቀስኩ በንጋታው መጥቼ የደረት ራጅ መነሳት እንዳለብኝና ሌሎች ምርመራዎች እንደሚያስፈልጉኝ ተነግሮኝ በተሻለ ጉልበት ወደ ቤቴ አመራሁ ሁሉም ስሜቴ በዚህ ሊቀጥል አልቻለም በንጋታው የቀደሙት የህመም አይነት ተባብሰው ሄዱ ብዙ መንቀሳቀስ አልችልም ሁኔታዎች ሁሉ ከረሩ የቅርብ ወዳጄ እናት ተማከሩና ለአንዴ ለመጨረሻ ጊዜ ባቅራቢያዬ የሚገኘው የገርጂ ጤና ጣቢያ ሄድኩ የተለመደው መጠይቆች ከተደረጉልኝ በኋላ የደረት ራጅ ተነስቼ ውጤት እንዳመጣ ተነገረኝ ሐያ ሁለት ማዞሪያ የሚገኘው የአርሾ ላብራቶሪ ከምሳ በፊት የተነሳሁትን ውጤት ባለሙያ አስነብቦ ውጤቱን በፖስታ አሽጎ ሰጠኝ ትዕዛዙን ወደ ሰጠችኝ ባለሙያ በፍጥነት አመራሁ እሽጉን ከፈተችው ዘና ባለና ባልተጨናነቀ ስሜት አሁን በሽታው ተገኝቷል ውጤትህ እንደሚያሳየው የቲቢ ባክቴሪያ ተገኝቶብሃል ስለዚህ ችግሩ ከተገኘ መፍትሄው ቀላል ነው ለማንኛውም ተነስ ተከተለኝ ብላ አብሮኝ ካለ ጓደኛዬ ጋር ተያይዘን አብረን ወረድን የውጭው ዋናው ግቢ መውጫ ላይ አንድ ክፍል ይዛን ገባች ውስጥ ካለው ባለሙያ ጋር አስተዋወቀችኝ የቲቢ ህክምና ክፍል ነው ከአሁን በኋላ ግንኙነትህ ከእርሱ ጋር ይሆናል ታካሚዎቹ በሙሉ ይወዱታል በቅርቡ ደህና ሆነህ አግኝሃለሁ ብቻ የሚልህን በሙሉ ስማ ከመተግበርም አትቦዝን መልካሙን ሁሉ እመኝልሃለሁ በፈለከኝ ጊዜ ልታገኘኝ ትችላለህ ሙሉ ፍካት ባለው ፊቷ ተሰናብታኝ ወጣች ወጣቱ የጤና ባለሙያ ስሙን ከነገረኝ በኋላ ከዚህ በፊት የቲቢ ህክምና አድርጌ እንደነበር ከቤተሰብ መሀል በቲቢ የተያዘ ሰው ከዚህ በፊት እንዳውቅ አሁን ከማን ጋር እንደምኖር ምልክቶቹ የሚታዩበት ሰው በአቅራቢያዬ እንዳለ የምንኖርበት ቤት ይዘትና የክፍሎቹን ብዛት አከታትሎ ከጠየቀኝ በኋላ የኤች አይ ቪ ምርመራ አሁኑኑ እንደሚመረምረኝ ነግሮኝ ስለቫይረሱ የምክር አገልግሎት ሰጠኝ በቀጣይ ሚዛን ላይ ወጣሁ አስደንጋጭ ነበረ በፍጥነት ነው የወረድኩት ኪግ በቀጣይ ወራት የማይቋረጡ በአፍ የሚዋጡ ኪኒኖችን መውሰድ እንዳለብኝና በመጀመሪያዎቹ ሁለት ወራት በቀን ሶስት ተመሳሳይ ኪኒኖችን ጠዋት ጠዋት እንደምወስድ ቀሪዎቹን ወራት የመድኃኒቱ አይነት እንደሚቀየርልኝና በመሀል ለአንድ ቀን እንኳን ማቋረጥ እንደማይቻልና በትክክል ከጨረስኩ ወደ ቀድሞ ጤናዬ እንደምመለስ ይህ ካልሆነ ግን ባክቴሪያው መድኃኒቱን ተለማምዶ ከተገኘ በቀጣይ ለ ዓመት በቀን በላይ ኪኒኖችን እና ለ ወራት የማይቋረጥ መርፌ መወጋትህ አይቀርም ይኹ ሁሉ ተደርጎም ላትድን ትችላለህ ስለዚህ ያለህ አማራጭ ምንም ስህተት ሳትሠራ በትክክል ወራት መከታተል አለብህ መድኃኒቱን እየወሰድክ የተለየ ስሜት ካጋጠመህ ከመናገር አትቦዝን ሁሉንም ነገር በቅርብ እንከታተልነሃለን ሁሉም ህክምና መድኃኒቶቹን ጨምሮ ያለምንም ክፍያ በነፃ ነው የምታገኘው ከነገ ጠዋት ጀምሮ መከታተል ትጀምራለህ መዘንጋት የሌለብህ ነገር ዕለት በዕለት በጠዋት ከ ድረስ ውሃ በመያዝ እዚህ ትገኛለህ እዚሁ እኛ ፊት ለፊት ነው የምትውጠው ነገ አስቀድመው መድኃኒት የጀመሩ ወገኖችን እዚህ ታገኛቸዋለህ ሁሉም በመልካም ጤንነት ላይ ይገኛለ ለማንኛውም በመድኃኒት አወሳሰድ ላይ ፈፅሞ ስህተት መስራት የለብህም የአንድ ቀን ስህተት ህይወትህ ሳይ አደጋ ይጥላል በትክክል ከተገበርክ ግን ያልተጎዳውን የሳንባህን ክፍል ትጠብቃለህ የተጠቃውም ሙሉ ለሙሉ ይድናል ቤት ውስጥ ላሉት ደግሞ በጣም ተጠንቀቅ በተለይ ከ ዓመት በታች ያሉ ህፃናት በባክቴሪያው የመጠቃት እድላቸው ሰፊ ነው ሲለኝ ከዚህ በፊት ከአንዷ ልጄ ጋር ያለ ጥንቃቄ ሳላውቀው ያሳለፍኩት ጊዜ ሲታወሰኝ ታምሜ ተኝቼ እንኳን እስሬ ስትሸጎጥ ስስማት እቅፌ ውስጥ ስከታት የነበረው በአይነ ህሊናዬ ሲታወሰኝ እናቷንም አሰብኩና የሁለቱን ጉዳት መቋቋም አልቻልኩም አናቴን በመዶሻ የተመታሁ መሰለኝ ደርቄ ቀረሁ ዛቄቋ ቄ አጠገቤ የተኙትን አዛውንት የሚንከባከቡት ወጣት ልጆች አይን አይኔን ያያሉ ነርሶችና አንድ ሴት ዶር መኝታዬ አጠገብ ቆመው ቁልቁል ያዩኛል ሌላኛዋ ነርስ የኦክስጂን ማሽኑን ልኬት ታስተካክላለች አጠገቤ በኤሌክትሪክ ኃይል የሚሠራ መተንፈሻ ማሽን በየ ሰከንዱ ጊዜ ቡፍ ቡፍ የሚል ድምፅ ያሰማል ቀኝ እጄ መሀል ጣት ላይ የተገጠመልኝን መለኪያ ወደ አይኔ አዙሬ ገርመም አደረኩት ከላይ ኦክስጂን ከታች ፐልስ ይላል በረዥሙ ተነፈስኩና ዶክተሬን አየኋት ምንም ያልተጓደለ ሙሉ ርህራሄ አዘል ፈገግታ ተላብሳለች አይዞህ ቅጣው ምንም አትሆንም በቅርቡ ደህንነትህ ይመለሳል እነኝህ ብሽቆች አለችና ለመሆኑ ከዚህ በፊት የአክታ ምርመራ ተደርጎልሃል በፍፁም ሰጥቼም አስመርምሬም አላውቅም። አልኩ ራሴን እየነቀነኩ በራጅ ውጤትህ ብቻ ነው መድኃኒቱን የተለማመደ ቲቢ ነው የተባልከው አጠገቧ ያለውን ራጅ ወደ ላይ አንስታ እየተመለከተች አዎ እሱ የመጀመሪያውን የቲቢ መድኃኒት መውሰድ ጀምሬ ሁለተኛው ወር ላይ ነው የተነሳሁትን አልኩ መረጃው ያስፈልጋል ብዬ አውቄያለሁ ያለፈ የህክምና ታሪክህ በሙሉ ተዘርዝሮልኛል አሁን የአክታ ምርመራ ይደረግልሃል ሁለት የናሙና መውሰጃ እቃ ተቀምጦልነል ረዥሙ የካልቸር ምርመራ የሜደረግበት ነው የባክቴሪያውን ደረጃ መድኃኒቱን ይልመድ አይልመድ በአጠቃላይ ያለበትን ደረጃ የምናውቅበት ነው እላዩ ላይ ቁጥር ይታይሃል በማርከር ምልክት እስከተደረገበት ወይም ቁጥር ድረስ ከውስጥ የወጣ አክታ ታደርግበታለህ በትንሺ እቃ የተወሰነ ታደርግበታለህ አለች በተረጋጋ ስሜት ዶር እኔ እኮ ብዙ መኩሪያለሁ ሳሌ ደግሞ ደረቅ ነው አክታ የሚባል የለኝም አልኩ የካቲት ሆስፒታል ብዙ ጊዜ ሞክሬ እንዳልተሳካልኝ እያሰብኩ እንግዲህ ይኹ ግዴታ ነው አለበለዚያ ህክምናውን መቀጠል አትችልም የምትወስደውን መድኃኒት ለማዘዝም ግዴታ ያስፈልጋል አክታ ከሌለህ አስቸጋሪ ነው ታግለህ አምጣ አለችኝ ቁጣ የተቀላቀለበት ስሜት በዝምታ አየኋቸው በርትተህ ብትሞክር ይሻልሃል ጭንቅላቴን ደበስበስ አድርጋኝ በትዕዛዝ መልክ ከአጠገቤ ሄደች የምርመራ ናሙናው ጠዋት በባዶ ሆድ ቢሰጥ የተመረጠ ነው ጊዜው እየመሸ ቢሆንም ምግብ በአፌ ቀኑን ሙሉ ስላልገባ የተሰጠኝን እቃ በመዳፌ ጨብጩ መታገል ጀመርኩ በልጄ እናት ማበረታታት እና እልህ አስጨራሽ ትግል በኋላ የተወሰነ ተፋሁበትና ድክምክም ብሎኝ ጋለል እንዳልኩ መውጫው በር አካባቢ በመጠኑ አንድ እግሯ አንከስ የሚለው ነርስ ከሌላ የስራ ባልደረባዋ ጋር ሲያወሩ ጆሮዬ ጥልቅ አለ ባለቀ ሰዓት እንዴት ደስ እንዳለኝ ልነግርህ አልችልም ትለዋለች ቀና ብላ እያየችው ምን ተገኘ ገዋኑ ኪስ እጁን ከቶ ቀውላላው የጤና ባለሙያ አከታ የለኝም ብሎ ያዝን የነበረ ሰውዬ ሲታገል አሳዝኖኝ ነበር ልክ ሲተፋ እንዴት እንደተደሰትኩ አለች እየተፍነከነከች ስለ እኔ እንደዚህ ተጨንቃ ነው ለእኔ ነው እንደዚህ የተደሰተችው ትግሌና መከራዬ ገብቷታል ማለት ነው ውስጤ የተደበላለቀ ስሜት ተሰማኝ ተገረምኩባት ባለቤቴን አምጭ ሁለተኛውን እቃ ብዬ ተቀብልኳት ሁለት ጊዜ ከደረቴ አካባቢ ወደ ላይ ሳብኩና ሞከርኩ አታምኑኝ ይሆናል ወፍራም የጓጎለ የሚመስል አከታ ዱብ አደረኩት የወለድኩ መሠለኝ እረካሁ የተፋሁት እንቁ እስኪመስለኝ ድረስ ተመለከትኩት ከረዥም ያልተቋረጡ ቀናት በኋላ ለምለም ይዘናት የነበረውን ትንጂን ተጣጣፊ ፍራሽ አልጋዬ አጠገብ መሬት ላይ ዘርግታ ተንጋላ ሳትገላበጥ ነው ያደረችው የድካም የመጨረሻው ጥግ ላይ እንደነበረች ያስታውቃል አሁን ሁለተኛ ቀኔ ምሽት ነው ውጤቴ እንደታየና መድኃኒቱን የተለማመደ ቲቢ ህክምና የሚሰጥበት ክልል ውስጥ ተኝቼ ህክምናውን መከታተል እንዳለብኝ ተነግሮኝ ቀደም ብላ አልጋዬን አይታ መታለች መኝታዬ አጠገብ ከመድረሴ በፊት የምጠቀምበትን ኦክስጂን ባለሙያዎቹ እያሰናዱልኝ ነው ከነበርኩበት አልጋ እንክብካቤ ባልተለየው መልኩ አንስተው ዊልቸር ላይ አስቀመጡኝ ከምሽቱ ሰዓት አካባቢ በለምለም ገፊነት ሽቅብ ዳገት ወጣን ግቢው ውስጥ ከጥንታዊው ባለ አንድ ፎቅ ጀርባ ፈንጠር ብሎ ለብቻው በአሁኑ ጊዜ ረዘም ባለ የሽቦ አጥር ዙሪያውን ተከቦ የብረት መዝጊያ የተገጠመለት ቦታ ከአንድ ረዳት ጋር እየገፉኝ ገቡ መግቢያው ላይ በኤል ሼፕ የተሰሩ በሁለቱም መደዳ አምስት አምስት ክፍሎች አሉሌ የኤሉ ቅርፅ መሀል ላይ ሁለት በጎጆ ቤት ቅርፅ የተሰሩ ክብ ከወገባቸው በላይ ከምሶሶአቸው ውጭ ክፍት ሲሆኑ መዝጊያ በር የሌላቸው በግንብ የተሠሩ የታችኛው ግማሽ ክፍላቸው ቢጫ ቀለም የተቀቡ መግቢያቸው ላይ ባለ ሁለት መወጣጫ ደረጃ ሲኖራቸው ውብና ማራኪ ይመስላሉ አንገቴን እንዳቀረቀርኩ ገረመምኳቸው በሁለቱ መደዳ ረጅም ክፍሎች መጋጠሚሜያቸው ላይ በሚገኝ ክፍት በር አለፍን መተላለፊያ መንገዱን እንደወጣን መጀመሪያ ተደርድረው ያየናቸው ቤቶች የአንዱ ረድፍ ጀርባ ጓሮ ሌሎች አምስት ክፍሎች ጀርባቸውን ሠጥተው አንድ ግድግዳ ለሁለት እየተጋሩ ተደርድረዋል በረንዳዎቹ ላይ ያሉት ረዣዥም የሸንበቆ መብራቶች ወገግ ብለው በርትተዋል ስድስት ቁጥር የህክምና ክፍል አልጋዎች አሉት በኋላ ላይ እንደተረዳሁት ሲገባ በስተቀኝ በኩል ተኝቶ የነበረው በዎቹ መጀመሪያ ላይ የሜገኝ ከሰንዳፋ የመጣው ታከለ ተሾመ ሲሆን በስተግራ በኩል ከዚሁ ከአዲስ አበባ ወጣት የፕሪፓራቶሪ ተማሪ ካሳሁን አቢ ከአስተማሚ አዛውንት አያቱ ጋር ለተመሳሳይ ህክምና ተኝተዋል መሀል ያለው ለእኔ ተሰናድቶ በንፁህ አንሶላና ለአይን በማይከብድ የአልጋ ልብስ አሸብርቆአል ዊልቸሬ ላይ እያለሁ በተጠንቀቅ ይጠብቀኝ የነበረው ኦክስጂን ተሰጠኝና አፍንጫዬ ላይ ሰካሁት በዚያው ፍጥነት የእለቱ ተረኛ ሐኪም እግር በእግር ተከትሉኝ ገባ ሐሪፍ ሰላምታ ከሰጠኝ በኋላ አንድ አንድ ጥያቄዎችን ጠይቆኝ መዝገቤ ላይ ከታተበ ሣገ ጠዋት ሙሉ ማብራሪያ ይሰጥሃል እዚህ ቦታ ላይ ያሉት በሙሉ አንድ አይነት ህክምና ነው የምትወስዱት ጥሩ ጓደኞች ይኖሩሃል በአገልግሎሉታችንም ትደሰታለህ መልካም አዳር ብሎን ወጣ ወቅቱ የሐምሌ ክረምት መሆኑ ብቻ ሳይሆን ያለንበት የቦታ አቀማመጥ እንጦጦ ተራራ መውጫ ከፍታ ላይ በመሆኑ ቀዝቃዛ አየር ነው ያለው ጓሮ ተብሎ የሚጠራው አሁን የተኛሁበት ክፍል መደዳ ያሉ እያንዳንዳቸው ባለ እና ባለ አንድ ነጠላ አልጋዎችን የያዙት ቤቶች ደረታቸውን የሠጡት ለእኔ ወደሚሜያስደምም ስፍራ ነው ቤቶቹ ባለሁለት ተካፋች ረዣዥም በሮች ሲኖራቸው ግራና ቀኝ በመስታወት የተሰራ መስኮቶች አላቸው ከጣራውና ከግድግዳው መሀል በሽቦ መረብ የተዘጋ ሲሆን ቀዝቀዝ ያለው አየር እንደልብ ወደ ውስጥ ይገባል የመጀመሪያው ቀን አዳሬ ነው በጀርባዬ ተጋድሜ በእግሬ በኩል ፊት ለፊት በሮቹና መስኮቶቹ ጠዋት ከንጋቱ ሰዓት አዳር በነበሩት ተረኛ ነርሶች ተከፋፈቱ እስከ መጨረሻው ተለጥጠው ከትንሽ ደቂቃዎች በኋላ ሁለት ነርሶች አነስተኛ አራት እግር ያላት ጋሪ እየገፉ ወደ ውስጥ ዘለቁ ትኩስ ቁርስ ደርሷል ተነሱ መነቃቂያ ነው አፍና አፍንጫዋን በነጭ ማስክ ተሸፍኖአል ቢሆንም በግልፅ ያስታውቅበታል እየተፍነከነከች ነው በጣም ነው የምትስበው እስከዘላለም አልረሳትም አዲስ ገቢው ለአንተ ዛሬ አልተዘጋጀልህም እመነኝ ነገ ጠዋት እኔው ነኝ የምሰጥህ የሺ እባላለሁ እየተግባባን እንሄዳለን በማለት እግሮቼን ነካ ነካ አድርጋ ግራና ቀኝ ላሉት ከሰጠቻቸው በኋላ ምንድን ነው እንደዚህ የሚያስደስታት ብዬ ልመራመር እስከምከጅል ድረስ መልካም ተመኝታልን ወደ ቀጣይ ክፍል አመራች ሁለተኛዋ ነርስ ከያዘቻቸው በርካታ መድኃኒት የተከፋፈለባቸው እቃዎች ታከለ ተሾመና ካሳሁን የሚሉትን መርጣ ለክፍል አጋሮቼ ሰአት ማሳለፍ ክልክል ነው በማለት አስቀምጣላቸው ሐኪሞች መጥተው ያዩሀል አለችኝ ቁልጭ ቁልጭ ስልባት ለእኔስ የሚል ሳይመስላት አልቀረም ቁመት ክብደት ኪግ የደም ግፊት ኦክስጂን መሳሪያ ተገጥሞልኝ ፐልስ ሌሎች የላብራቶሪ ውጤቶቼ መተዋል የካቲት ሆስፒታል ከረጢት ህበቬ ደም ወስጄ የነበረውን ሒሞግሎቢን ደርሷል ከአንገቴ በላይ ብቅ ያለው ጭንቅላቴ ካልሆነ በስተቀር መኝታ ውስጥ ያለው ሌላ አካሌ ሰው ያለ አይመስልም አልጋው እንደተነጠፈ ነው አፅሜ ቆዳ ለብሶ ተጋድሞአል ዶር በቀለ ፍቃዱ ናቸው መኝታዬን ገጠጥ አድርገው ከነርሶቻቸውና ከባለቤቴ ጋር ደገፍ አድርገው አስቀመጡኝ የመጡትን ውቴቶች አገላብጠው ካዩ በኋላ ከዚህ በፊት የቲቢ ህክምና አድርገሃል ጠየቁኝ የመጀመሪያ ነው እንደተደፋሁ መለስኩ ከዚህ በፊት በቲቢ ከተያዘ ሰው ጋር አብረህ ኖረሀል ወይም በቅርብ የምታውቀው አለህ ጫር ጫር እያደረጉ ያወሩኛል የእኔ ሁለተኛ ታላቅ ወንድሜ በቲቢ ተይዞ ነበር ለረዥም ጊዜ እኔ ነበርኩ የማስታምመው ግን ዓመታት አልፈውታል እስካሁን ደህና ነበርኩ ወንድምህ አሁን የት ነው ያለው። ስኳር ደም ብዛት የመሳሰሉት በፍፁም ጤነኛ ነኝ የሚጥል በሽታ ማንቀጥቀጥ የመሳሰሉት አጋጥሞህ ያውቃልገ በፍፁም አያውቅም እግርህ መደንዘዝ ሰውነትህ አልታዘዝ ብሎ ድርቅ ግትርትር ብሉሎብህ ያውቃል ያው ከአልጋ ላይ ወርጄ በእግሬ መንቀሳቀስ ካቆምኩ ወር ላስቆጥር ነው መደንዘዝ ግን የለም ሰውነቴን ግን ማዘዝ አልችልም መገላበጥ እንኳን ተስኖኛል ጥሩ ካለው ታሪክህና አሁን ካለህበት ደረጃ መድኃኒቶችህን አስተካክለን እንሰጥሃለን ቢሆንም ግን መጠኑ የሚገልፅልህ ቢሆንም ከነገ ጠዋት ጀምሮ ለሚቀጥሉት ወራት እሁድን ብቻ በማረፍ ሌሎቹን ቀናት መርፌ ትወጋለህ በአፍ የሚወሰዱ የተለያዩ ኪኒኖችን በየቀኑ ትወስዳለህ ሁልጊዜ አብረንህ ነን የተለየ ችግር ካለ እንከታተልሃለን ጥያቄ ካለህ ጠይቅ አሉኝ ዶር በቀለ ወደታች ቁልቁል እያዩኝ ለኝም አልኩ ደረቅ ሰውነቴና ወራት መርፌ መወጋት በየእለቱ እየታየኝ ለነገሩ ለመወጋትም በህይወት መቆየት ይጠይቃል አጉተመተምኩ ለማንኛውም በአቅራቢያህ የነበሩ በሙሉ የቲቢ ምርመራ ማድረግ እንዳለባቸው እንመክርሃለን ሲሉኝ የ ዓመት ልጄ ትውስ አለችኝ እሷም ተይዛ ከሆነ ለ ወራት ልትወጋ ሰቀጠጠኝ የልጄ እናት ከአያሌ ቀናት የየካቲት ሆስፒታል ብቸኝነት ተገላግላለች የውስጧን የምታወራቸው ሰዎች አግኝታለች እኔማ ተለጉሜባታለሁ ክፍሌ ውስጥ በስተቀፔሄፔ ወደ ዩኒቨርስቲ ለመግባት በዝግጅት ላይ የነበረ ወጣት በሌላኛው ጎኔ ደግሞ በዎቹ የሚገመት እድሜ ላይ የሚገኝ ለቀሪው ህይወቱ ትዳር ልጅ የተደላደለ ኑሮ እኖራለሁ በማለት አጠራቅሞ የነበረውን ገንዘብ በህክምና ካገባደደ በኋላ መድኃኒቱን የተለማመደ ቲቢ መሆኑ ታውቆለት ከተኛ ኛ ቀኑ ነው ሁለቱም ታካሚዎች የተጎዱ አይደሉም ከቦታ ቦታ ይንቀሳቀሳሉ ራሳቸውንም መርዳት የሚችሉበት ደረጃ ላይ ናቸው ይሁንና ግን የወጣቱ ሴት አያት አላስችል ብሎአቸው በዚያ አስከፊ ቦታ ለራሳቸው ግድ ሳይሰጡ ያስታምሙታል ለምለም ከእሳቸው ጋር ነው መስኮቱ ስር መሬት ጥግ ላይ አነጥፈው የተኙት እራታቸውን አንድ ላይ ተመግበዋል መሀል መሀል ላይ ቀና እያሉ ልጃቸውን ከማየት ሌላ ለጥ ብለዋል ንጋት ሰዓት ላይ እንደትላንትናው በርና መስኮቶቹ በሀይል ተከፈቱ ትኩስ ቁርስ ጎበዝ ትኩስ ደርሷል የሚፍነከነክ የሚመስል ድምጽ ወደ ውስጥ ገባ እንቅልፍ የለም እንዳፈጠጥኩ ነኝ አፍንጫዬ ላይ ኦክስጂን ተሰክቷል አንገቴን ግራ ቀኝ አወዛውዛለሁ ለምለም ከመቅፅበት ተነስታ አጠገቤ ቆማለች ምግብ ከበላሁ ሰነባብቻለሁ ጉሉኮስ ተሰክቶልኛል ፍላጎቱም የለኝም ትኩስ ቁርስ ምንድን ነው በጠዋት በአይነ ህሊናዬ እንፋሎቱን ሳልኩትና የሆነ የምግብ መአዛ በአፍንጫዬ መፈለግ ጀመርኩ ፍቱን ቁርስ ብላ አየት አረገችኝ በሚያበራ አይኗ ቆይ ላስተካክልልሽ አለች ለምለም ገልበጥ አድርጋ በጎኔ አስተኝታኝ ያዘችላት አይዞህ ተረጋጋ ሰውነትህን አፍታታ መቀመጫዬ አካባቢ አልኮል በነካው ጥጥ ጠረግ ጠረግ አደረገችና ስጋ የማል ነገር ስላልነበረኝ በግራ እጆ ቆዳዬን ሰብሰብ አድርጋ ሳበችውና አንድ መርፌ ወጋችኝ መድኃሂቱ በመላ አካሌ ሲሰራጭ በተወጋውበት አካባቢ ሲበተን ተሰማኝ የመጀመሪያዋ የማለዳ ትኩስ ቁርስ ለ ወራት ይቀጥላል ተከታይዋ ነርስ የተለያዩ ውህድ ኪኒኖችን የሚሆኑ ናቸው ራስጌ አስቀምጣልኝ ሁሉም በአንድ ጊዜ እንደሚወሰዱ ከተጨማሪ ማብራሪያ ጋር አስቀምጣልኝ ወጣች ከጠዋቱ ሰዓት ነው ታካሚዎች ወደየክፍላቸው መግባት ጀምረዋል አንድ ክፍል የሚጋሩኝ ሁለቱም ገቡ ሰዓት ደርሷል ጎበዝ የመድኃኒት ሰዓት የሚሉ ድምፆች ከየአካባቢ ማስተጋባት ጀመሩ የኔዋ ለምለምና በስተቀኝ የተኛው ወጣት አስታማሚ አዛውንት አያቱ ከቤተ ክርስቲያን እንደሆነ በሚያሳብቅ የነጠላ ክንብንብ አለባበሳቸው ወደ ውስጥ ዘለቁ በእጃቸው አንድ ሊትር ውሃ ይዘዋል በኋላ እንደተረዳሁት ከበላያችን የምትገኘው የጉስቋም ማርያም ጠበል ነበር እኔ ብዙም ተስፋ መቁረጥ የለብኝም እውነት ለመናገር መንቀሳቀስ በማልችልበት የሰለሉ እጆቼ ብቻ በቀስታ እየተንቀራፈፉ አንድ አንድ አካላቶቼን ፊቴን ጨምሮ መዳበስ መነካካትና አጥንቶቼን የመቁጠር ያህል ማሻሸት ከመቻላቸው በስተቀር አንገቴ ብቻ ከግራ ወደ ቀኝ በማንቀሳቀስ አይኖቼ አካባቢያቸውን የመቀላወጥ ያህል ከመንቀዋለላቸው ሌላ አእምሮዬም ያስባል ጆሮዎቼ በንቃት ያዳምጣሉ አብሶ ተስፋ የቆረጡብኝ ሰዎች ከንፈራቸውን ሲመጡና አይ ይሄማ አይተርፍም አበቃለት የሚሌ ቃላትንማ በጣም እንዲያው ከደጃፍ ሁሉ ሳይቀር ከሩቅ ይሰማሉ እሞታለሁ ብዬ አስቤ አላውቅም አሁንም አላስብም መኖር ስለምሻ መሞት አልፈልግም መምጣቱ ስለማይቀር ደግሞ አልፈራውም የማምነው እውነት ይሄ ነው አሁን ያለሁበት ደረጃ የመኖር የህይወት አንዱ ክፍል ነው ብዩ አምን ነበር ሰዎች በዚህ ግዜ የተለያየ ኑሮ ይኖራሉ በሀብት በድሎት የተንደላቀቀ ምንም ያልተጓዘለበት ከሚመስል ጀምሮ እስከ ታች የሚለብሰው እንኳን የሌለው በጎዳና የሚኖሩት ድረስ በየደረጃው አልያም በምክንያቶች በየእስር ቤቱ በየገዳማቱና በየእምነት ቦታዎች ብሎም በየበረሀው በስደት ይኖራሉ እኔ ደግሞ በሆስፒታል ከሚኖሩት ጋር የተመደብኩ ነዋሪ ነኝ ሞትን አልፈራውም ግን አልፈልገውም ከመጣ ደግሞ የትም ቦታ እየኖሩ ያሉ ጋር እንደሚመጣ አውቅ ነበር በሐይማኖት በኩል አድሎና መድሎ አላውቅም ሁሉም የዕምነት አይነቶች የመኖር ህጋቸው በሙሉ መልካምና ትክክል ነው ብዬ አምናለሁ አብዛኛዎቹን በጥልቀት ለማወቅ ሞክሬያለሁ ያደኩበት ካቶሊክ ጀምሮ ኦርቶዶክስ ፕሮቴስታንት የይህዋ ምስክሮች ሠባተኛው ቀን አድቬንቲስት ስስልምና በቃ ሁሉም ይመቹኛል ይመስጡኛልም በአፍ የሚዋጡትን ኪኒኖች ሁለቱን በአንድ እንኳን የምውጥበት አቅም ስላልነበረኝ ቀና አድርጋ አንጋላኝ አንድ በአንድ አፌ ውስጥ እየከተተች ውሃ በመጠኑ እየጋተችኝ በተወሰኑ ደቂቃዎች ውስጥ አጠገቤ ተቀምጣ አስጨረሰችኝ እሺ የምላት ስላልመሠላትና ይቃወመኛል ብላ ስላሰበች ከአዛውንቷ እናት ጋር ተማክራ ስታጣኝ የነበረው የልጄ ልጃቸው ከተካፈሉት ይዘው ከመጡት የማርያም ጠበል ነበር እኔ ግን አውቄያለሁ ነቄ ነኝ ቢሆንም በታላቅ ደስታና እምነት ነበር የምወስደው ማንስ ቢሆን ሊያድነው የመጣ ነገርን የማይቀበል የሚያዋርድና የሚንቅ አለ ብዬ አላምንም ምንም ይሁን ምን ማዳን የመልካም እንጂ የክፉ ይሆናል ብዬ አላምንም የክፍል አጋሮቼ ግን ደቂቃም አላቆያትም ክኒኖቹን ሁለት ቦታ አካፍለው በርከት ያለ ውኃ ለቀቁበትና ትንሽ እንደመቀመጥ ብለው ተጠቅልለው ተኙ ግቢው ሙሉ ለሙሉ ፀጥ አለ ተንቀሳቃሽ ጠፋ ህይወት ያለው ያለ አይመስልም መድኃኒቶቹ በተለይ ገና አዲስ ለጀመርነው ታካሚዎች በጣም እጅግ በጣም ከምገልፀው በላይ ኃይለኛ ናቸው ሠውነት ድክምም ይላል ደረት አካባቢ ልብ የዛለች ይመስላል የሚያቅለሸልሻቸው የሚያስመልሳቸውም አሉ ያነጫንጫል ሁሉም ነገር ያስጠላል ድበታው ወደር የለውም እኔም የዚህ አካል ሆንኩ ገና ለ ወራት ይቀጥላል የመጀመሪያ ቀኔ ነው ቅዥት የተቀላቀለበት ሰመን ውስጥ ገባሁ ከሁለት ሰዓታት በኋላ አምስት ሰዓት ላይ አንድ ሰው መኝታችን አጠገብ ያለ ኮመዲኖ ላይ ሁለት ሁለት እያንዳንዱ ባለ ሚሊ የታሸገ ፓስቸራይዝድ ወተት ሲያስቀምጥ በደብዛዛው ውስጤ እንደተጨናነቀ በድብርት አይቼዋለሁ በስተግራዬ የተኛው ታከለ ተሾመ ፊቱን እንደጣለው አይኖቹን ቡዝዝ አድርጎ አልጋው ጠርዝ ላይ ተቀምጦ አንደን የላስቲክ ወተት ግጥም አድርጎ አጣጣማት እንደመረጋጋት ብሎ በጀርባው ጋለል አለ እኔም አንድ ብርጭቆ ተቀድቶልኝ ፉት ፉት እያልኩ እሩብ ያህሏን በአስገዳጂ ለምለም አማካኝነት የግዴን ጠጥቼ እቁለጨለጫለሁ አዛውንቷ የልጅ ልጃቸው የመጨቃጨቅ ያህል እየተነታረኩ ግድ ነው ጠጣ ይሉታል ፊት ለፊቱ ተገትረው ቀስ ብዬ እጠጣለሁ እማ አረጋጊው እንጂ መድኃኒቱ ከባድ ነው ተነስ አንዱን ውሰድ ትንሽ ልተኛ አትረብሸኝ ሐኪሞቹ ስሚሜያውቁ እኮ ነው አሁን ያመጡልህ እማ ደግሞ ድርቅ ካልሽ አትመለሽም እየተነጫነጨ ትንሽ ቀና ብሎ ግጥም አደረገ አጠጣጡ አስቀናኝ ምን ያደርጋል ለመጠጣት ቀርቶ ለማውራት የሚሆን አቅም የለኝም ትዝብቴን ግን ቀጥያለሁ አፍና አፍንጫቸውን በአረንጓዴ ማስክ ሠርጀሪ ማስክ የሸፈኑ ታካሚዎች ወደ ቀኝ ሲሄዱ ባዶ ሠሀን ሲመለሱ ከበድ ያለ ሠሀን ብሎም እንጀራ ይዘው ይመለሳሉ ምሳ ሰዓት መሆኑ ነው አሁን አካባቢው ህይወት ያለባቸው ያሉ መሠለ ሁሉም ወተቱን ጠጥቶ እንደተነቃቃ ጠረጠርኩ አይ ምርምና ጥናት ብዬ በሀኪሞቼ ተደመምኩ ታከለ ተሾመና በስተቀ ያለው ወጣት በአያቱ ጉትጎታ የተወሰነ ተመግበዋል እኔ በትንጂቪ ያጎረሠችኝን መዋጥ አቅቶኝ ለረዥም ደቂቃዎች አፌ ውስጥ ሳንገዋልላት ቆየሁ ስማ ቅጣው ካልበላህ ትሞታለህ ለምለም ቆጣ አለች አንጂም ትሞቻለሽ አጉተመተምኩ እኔማ ብላና እበላለሁ ትንሽዬ ጉርሻ ይዛለች አልቻልኩም ለሜ ተይኝ ፊቴን አዞርኩባት ሣሬ ሁለት ነገ ሶስት ጉርሻ አለች ለመለመን ያህል ባይሆን ወተቱን አጠጭኝ ለመገላገል ነበር ያልኳት እሱም ጥሩ የያዘችውን ጉርሻ ሰሀኑ ላይ አስቀምጣ ወተቱን አፌ ላይ ደቀነችው ትንሽ እጅግ በመጠኑ ቀመስ አደረኩና ይበቃኛል አልኩ እኔ እኮ ለምን እንደምደክም አላውቅም ካልበላህ ትንሽም ቢሆን ካልጠጣህ መድኃኒቱም እጅግ ከባድ ነው ተቆጥታ ከአጠገቤ ተነሳች ምሳቸውን ሊመገቡ ሰሀናቸውን ይዘው ከአዛውንቷ አያት ጋር ወደ ውጭ ወጡ በጀርባዬ ከተኛሁ ወራት እያስቆጠርኩ ነው ተንጋልዬ አየዋቸው እየተነጫነጩ ከአይኔ ጠፋ አስታማሚዎች እራሳቸውን በቲቢ ባክቴሪያ እንዳይያዙ አ የተባለ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ማስክ ያደርጋሉ ምግብ ለመመገብ ማውለቅ ግድ ስለሚላቸው መመገቢያ ቦታ ግቢው ውስጥ እንዳላቸው ሰምቻለሁ ወቅቱ ክረምት ስለሆነ የቀትር ፀሐይ የለችም አየሩ ውሽንፍር የበዛበትና ቀዝቃዛ ነው እኔ እንኳን ሰው ሰራሽ ኦክስጂን ቢገጠምልኝም የአካባቢው ሰዎች ግን ወበቅ የሌለው ነፋሻማ ለስለስ ያለ አየር እየተነፈሱ ነው በየክፍሉ ያሉ ታካሚዎች በርና መስኮታቸውን እስመጨረሻ ለጥጠው ከፍተውታል ሁሉም በቲቢ ባክቴሪያ የተጎዱ ሰውነታችንም የደከመ ነው ታዲያ በዚያ ቅዝቃዜ የክፍሉቹ መከፋፈት ምንም ጉዳት ሳያደርስብን ጥቅሙ አይሎ ሳይ በየቤታቸው ጤነኛ ሆነው በርና መስኮታቸውን ጥርቅምም አድርገው ዘግተው የታፈነ አየር እየተመገቡ ብርድ ይመታኛል በሚል በበብ የነፃነት ንፁህ አየር የሚያጡ ብሎም ኢንፍሎዊዛን ቲቢን ጨምሮ ሌሎች ባክቴሪያዎችን ሲመጋገቡ የሚኖሩትን ወገኖቼን ሳስብ ብስጭት የተቀላቀለበት ሐዘን ተሰማኝ ከምሳ በኋላ ታካሚዎች በየክፍላቸው መኝታቸው ላይ ሆነው ከአጋሮቻቸው ጋር የልብ የልባቸውን ይጫወታሉሌ ስላለፈ ታሪካቸው በቲቢ ከተያዙ በኋላ ስላደረጉት ህክምና መድኃኒቱን የተለማመደ ቲቢ ነው የተባሉት መቼና የት እንደሆነ ስለሚወስዷቸው ተመሳሳይ ስለሆኑ በርካታ የየእለት የሚዋጡ ኪኒኖች ስለሚያስከትሉት የጎንዮሽ ጉዳት በየቀኑ ስለሚያደርጋቸው ሁኔታ ስንት ጊዜ እንደሆናቸው እንደቀራቸውም የወደፊት አላማቸውን ሁሉ ሳይቀር ይጫወታሉ የክፍሌ አጋር ታከለ ተሾመ ከምነግራችሁ በላይ ዝምተኛ ነው ጠዋት አነጋገሩ ላይ ከሀይለኛ ሳል በስተቀር ምንም ድምፅ አይሰማም ብቻ በጣም እየተጨነቀ ደረቱን ይዞ ይታገላልና የረጋ የጓጎለ ብሎም በርካታ ደም ይተፋል ግማሽ የሚሆን ማስታጠቢያ ሰሀን ከውስጡ ይወጣል ሐኪሞች እንደሚናገሩት ሳንባ በባክቴሪያው ከመጠቃቱ የተነሳ በቁስለት ሊመታ ይችላል በዚህ ጊዜ የቆሰለው ክፍል ስለሚሟደማ ደም መትፋት ቁስሉ እስከሚያገግም ድረስ የሚኖርና ህክምናውን በአግባቡ ከተከታተለ ቁስለቱ ጠፍቶ መድማቱ ቆሞ በጊዜ ሂደት ወደ ጤናው እንደሜለስ ይናገራሉ ታኬም እንደዚሁ ነው አበዛዙ የሚያስደነግጥ ደም በከፊል የጓጎለ ከተፋ በኋላ የተጨመላለቀ ቁስሉ በማጠቢያ ታጥቦ እንደፀዳለት ሰው ከመጠን ባለፈ ሁኔታ ይረጋጋል ሰላሙም ይመለሳል ትንሽ አረፍ ካለ በኋላ ደሙ ውስጥ ውኃ ይሞላበትና ወደ ሽንት ቤት ሄዶ ይደፋል የተወሰነ ተንቀሳቅሶ የፈረደበትን በርካታ ኪኒኖች ውጦ ቀርዝዞ ተደብቶና ተደብሮ ይተኛል በተለመደው ሰዓት ወተቱን ጨልጦ ተረጋግቶ ምሳውን ከቀማመሰ በኋላ ለተወሰኑ ደቂቃዎች በደረቱ ተረጋግቶ ይተኛና ተነስቶ የቀረችውን አንድ ባለ ግማሽ ሊትር ፓስቸራይዝድ ወተት ለግቶ ድምፅ ሳያሰማ ሰአቱን ገፋ አድርጎ አመሻሽ ላይ ፊልም አልያም አንዱን የቴሌቪዥን ጣቢያ ሊኮመኩም በእግርጌዬዩ በኩል ተበርግዶ በሚውለው በር በኩል ጋቢውን ተከናንቦ አረንጓዴ ማስኩን አፍና አፍንጫውን ሸፍኖ በፀጥታ ሹልክ ይላል ከሠአታት በኋላ እንደ አወጣጡ ድምፅ ሳያሰማ በአይን ብቻ እየተያየን ወደ ውስጥ ይዘልቃል አልጋው ጠርዝ ላይ ሆኖ እራቱን ይቀማምስና የማታውን ሁለት ኪኒኖች ው በተለመደው ትንፋሽ በማያሰማ ፀጥታው ለጥ ይላል ለሊት ለሽንት ካልተነሳ በስተቀር እስከ ንጋቱ የመርፌ ሰዓት ይተኛል በዝምታ ይሄ የእለት ከእለት ተግባሩ ነው ለረዥም ሰዓታት ከአጠገቤ የጠፋችው ለምለም አይኗን ቁልጭ ቁልጭ እያደረገች ሳትገባ ታኬ ጋቢውን ተከናንቦ ሲወጣ በር ላይ ተላለፉ በአንገት ሰላምታ ተሰጣጡ በማይሰማ አነስተኛ የማጉተምተም ድምፅ ጋር በጣም ዝምተኛ ነው ከመጠን ባለፈ መልኩ ያስባል ይጨነቃል ሲያሳዝን ብላኝ መኝታዬ እግርጌ ጠርዝ ላይ ተቀመጠች የሚያሳዝን ነገር አይቼ መጣሁ የሠለሉ እግሮቼን ከብድር ልብሱና አልጋ ልብሱ በላይ እየደባበሰች እኔ ካለሁበት ደረጃ የከፋ ምን አይታ መጣች በማለት ለመስማት ጆሮዎቼን ከፈትኩ አንዲት በሀያዎቹ አጋማሽ እድሜ የምትገኝ ሴት የስድስት ወር ህፃን እያጠባች እዚህ ግቢ ውስጥ አየኋትና ገርሞኝ ተጠጋኋት ሠላም አልኳት አዲሷ ጎረቤት እንዴት ነሽ በተከሰከሰ ፊቷ መለሰችልኝ እዚህ ምን ታደርጊያለሽ። ተስፈ በሌለው ቅስሙ በተሰበረ ድምፅ ተነፈስኩ ኛ የት ሄደን ነው የምትቸገረው አታስብ ሁላችንም እንደግፍሃለን ሊያፅናናኝ መሠለኝ ብየቀኑ ብዙ እርዳታ ያስፈልገኛል ሁላችሁም ደግሞ አንድ አይነት ልትሆኑ አትችሉም በአንዳንዶች ተራ ልቸገር እችላለሁ ደግሞ መሰልቸት አለ አልኩኝ የለምለም ንግግሮች እየታወሱኝ ሐረር ነው አይደል የተወለድከው ቆየህ እንዴ አዲስ አበባ ከገባህ ጨዋታ ለመቀየር ይመስላል ጠየቀኝ እስከወጣትነት ጊዜዬ እዚያው ነበርኩ በ ዓመቴ ነው እዚህ የመጣሁት ሐረር የት አካባቢ ነበርክ በእጆቹ እየደባበሰ በተቀራረበ ስሜት አወራኝ የተወለድኩት ቀላዳንባ ነው እናትና አባቴን በተወለድኩ በአንድና ሁለት አመቴ በተከታታይ በሞት ስላጣሁ ማልቴዝ ቤተልሄም ተብሎ በሚጠራው የካቶሊክ ሚሽነሪዎች ጋር ከበርካታ የተለያዩ ልጆች ጋር ነው ያደኩት ከዚያ አዲስ አበባ አመጡኝ በአንክሮ ስለሚያዳምጠኝ ተረጋጋሁ ሐረርን አውቃታለሁ ኖሬባታለሁ አነጋገሩ ርጋታ የተሞላበት ነው ያምራል ተው ባክህ እዛ ዘመድ አለህ ከፍተኛ መረጋጋት ውስጥ እየገባሁ እንደሆነ ታውቆኛል የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ነበርኩ ሁለት ቦታ ቆይቼያለሁ በተለይ ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ረዘም ላለ ጊዜ ነው ያገለገልኩት ብታይ ተመችቶኝ ነበር ሲለኝ በትክክል መንፈሳዊ ሰው መሆኑ ቁልጭ ብሎ ይነበብበት ነበር አሁንም እየሰራህ ያለኸው ፈጣሪን ከማገልገል በፍፁም አይለይም አመሰግንሃለሁ ኩራት ተሰማኝ ምን ግዜም አብሬህ ነኝ ምንም እንዳይሰማህ አሁን ምን ላርግልህ ፍቃደኝነት እየተነበበት ጠየቀኝ ራሴን በጣም እያመመኝ ነው ጥሩ እንቅልፍ አስፈልጎኛል አልኩ መተኛት ስላማረኝ የሙቀት መለኪያ አምጥቶ ብብቴ ውስጥ በአክብሮት አስገብቶ ጊዜውን ጠብቆ አወጣው በጣም ትኩሳት ነበረኝ የማታውን ኪኒን በሰአቱ አስለውጦኝ ከትንሽ ጊዜ በኋላ ወተት አቀማመሰኝ አንድ መርፌ ማስታገሻ መሠለኝ ወጋኝና መልካም ለሊት ተመኝቶልኝ ጉሉኮሴን አስተካክሎ መተንፈሻዬን አመቻችቶ በርና መስኮቶቹን ዘግቶኝ ወጣ ታላቅ እረፍት ተሰማኝ ከትንሽ ደቂቃዎች በኋላ በላብ ተዘፈኩ የራስ ምታቴ ቀስ እያለ በኖ ጠፋ ጭልጥ ያለ ሰላማዊ እንቅልፍ ወሰደኝ በቀን ውስጥ ከምመገባት ምግብ ላይ እጆቼን ብሎም አንገቴን እና እግሬን ብቻ ስለሆነ የማንቀሳቅስበት እንብዛም የማቃጥለው ንጥረ ነገር የለኝም የምወስዳቸውን መድኃኒቶች ከመደገፍ ባሻገር የውስጥ አካላቶቼ ተግባራቸው በአግባቡ እንዲያከናውኑ ለማገዝ ጉሉኮስ ከቫይታሚን ጋር ተቀላቅሎበት ከበላዬ ተንጠልጥሎ በደም ስሬ እየተሰጠኝ ያለው አጋዥ ቦቲዬ ነበር ሽንቱ ግን አይጣል በርካታ ነው ዛሬ ደግሞ ጉዴ ፈልቷል ጭልጥ ካለው እንቅልፌ ስባንን የክፍሉና የበረንዳው በርካታ ባለሸንበቆ ነጭ መብራቶች ወከክ ብለው በርተዋል ከፊት ለፊት ያለው በዛፎች የተሞላው ጫካ መሠል ቦታ በጭለማ ተውጦአል ፀጥታው ወደር የለውም የጅቦች ድምፅ በቅርበት ይሠማል እኩለ ለሊት እንዳለፈ ተጠራጠርኩ ግራ ቀኝ አየሁ ማንም የለም ባለ ሶስት አልጋ ክፍል ውስጥ እኔ ብቻ ፊኛ ከመጠን ባለፈ በሽንት ሞልቷል ወጥሮኛል መሽኛ እቃ ለማንሳት ቀኝ እጄን ሰነዘርኩ በአየር ላይ ተንጠልጥ ቀረ ቀዘፍኩ ልደርስ አልቻልኩም በጣም ተጨናነኩ በሽንት ከመወጠሬ የተነሳ እንደ ድሮ ልቁነጠነጥ ፈለኩ ወገቤ መንቀሳቀስ አይችልም እግሬን ወደ ላይ ታች አንቀሳቀስኩ አልተቻለም ጠበቅ አድርጌ ግራና ቀኝ ገጥሜ ጭኖቼን ያዝኩ ጨመኩት ተወጠርኩ ፊኛዬ በንፋስ የተሞላ ኳስ መሠለኝ ቆጠቆጠኝ ሽንቴ ዘንጉ ላይ የደረሰ እንደሆነ ታወቀኝ ከእግር እስከ ፀጉሬ ተሳስሮ ተኮማትሮ የነበረው አንዴ ተፍታታ ለቀኩት በር በሩን እያየሁ ሙቀት የዛበት ሽንት ከጉልበቴ እስከ ጀርባዬ ድረስ አረጠበኝ እፎይ የወለድኩ ነው የመሠለኝ የበሰበሰ ዝናብ አይፈራም ይባል የለ ሊነጋጋ ሲል ድጋሚ ሽንቴ መጣ የሚረዳኝ አልፈለኩም እቃውም ትውስ አላለኝም እንደተንጋለልኩ ለቀኩት እንደተጨመላለኩ የጠዋት መርፌዬን ገለጥ ገልበጥ አድርጎ ወጋኝ በፀጥታ ገባ በፀጥታ ወጣ አይቼው የማውቅ አልመሰለኝም ወጣት ነርስ ዶር በቀለ የማለዳ የታካሚዎቻቸውን ጉብኝት በሁለት ነርሶቻቸው ታጅበው መጎብኘት ጀምረዋል በዋርዱ በእድሜያቸው የአባልነት አቋም ላይ ያሉት እሳቸው ብቻ ናቸው ሌላ አንቱ ብለን የምንጠራው የለም ሽማግሌም አይደሉም ብቻ ከነተግባራቸው የክብር ደረጃ ላይ የደረሱ ሐኪም ናቸው በአገራችን ማለትም በዚህ ሆስፒታል የኤም ዲ አር ህክምና መሰጠት ከጀመሩት ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን በዘርፉ እያገለገሉ ይገኛሉ ባለፉት ዓመታት በሙሉ ከአንድ ሺህ ስድስት መቶ በላይ ታካሚዎች ተኝተው በነበሩበት ጊዜ በእርግጠኝነት ሁሉንም ዳብሰዋል ህክምናውን ተከታትለውታል አባታዊ ምክራቸውን ለግሠዋል ታካሚያቸው ጋር ሲደርሱ ስሙን እስከ አባቱ በመጥራት ነው የሚጀምሩት በእጃቸውም በመመርመሪያቸውም ይዳብሱናል አይኖቻቸውን ሳይነቅሉ በርህራሄ ያዩናል ማውራት ከጀመርን ትንፋሽ ሳይሉ በፀጥታ ያዳምጣሉ የማጠገብ ምክራዊ አንደበታቸውን ይለግሱናል አይሰለቹም አሁን ታጅበው አጠገቢ ቆመዋል ቅጣው ተማርያም አሉ የህክምና መዝገቤን ገለጥ ገለጥ እያደረጉ በእግርጌ ጋር ቆመዋል አቤት ዶር ነርሶቹን እየተመለከትኩ ምን የተለየ ነገር አለ ከመዝገቡ ላይ አይናቸውን ነቅለው ፊት ፊቴን እያዩ ሸንቴን መቆጣጠር አልቻልኩም የተዘጋጀሁበት ውሸት ነበር ማለት በጣም ይወጥርሃል እ እ መጣሁ መጣሁ ይልህና ከዚያ አቋረጥኳቸው አይደለም ዶር ፊኛዬ ውስጥ እራሱ የሚጠራቀምም አይመስለኝም ዝም ብሎ ይፈሳል ነርሶቹ ያወቁብኝ ስለመሰለኝ አፍጥጩባቸዋለሁ ከዚህ በፊ ካቲተር የሽንት መውረጃ ቱቦ ትጠቀም ነበር ወደምፈልገው አቅጣጫ ገቡ በቃ እንደዚህ ሲያደርገኝ ነው የተገጠመልኝ እዚህ ሆስፒል በገባው በትንሽ ቀናት መቆጣጠር ችዬ ነበር አሁን ግን እንደበፊቱ ይፈሳል መበስበስ ብቻ ነው ብርድ ልብሱን ገለጥ አድርጌ በሽንት መጨመላለቄን አሳየኋቸው ለትንሽ ጊዜ ካቲተር መጠቀም አለብህ ስጋት አይግባህ መድኃሂትህን በአግባቡ ውሰድ ጠንከርከር ስትል መቆጣጠር ትጀምራለህ እንደተሳካልኝ ገባኝ አመሰግናለሁ ዶር ለምለምም ጥላኝ ሄደች አሁን ብቻዬን ነኝ ብዙ ስጋት አይግባህ ሁላችንም ከጎንህ ነን መሄዷን አውቄያለሁ እንደ ግል ችግራቸው ስለእያንዳንዳችን እንደሚወያዩ ሳስብ በውስጤ ጀግና ነኝ አልኩ የተወሰኑ ቀናት አብራኝ ብትሆን ደስ ይለኝ ነበር እሷ ግን ጨከነች አይኔን ወደ ግድግዳው አዞርኩ መሄዷ አይከፋም ለእሷ እዚህ ቦታ መሆን ብዙ አይመከርም እንድትሄድ የመከራት መሰለኝና ሸምቀቅ አልኩ መልካም ተመኝተውልኝ ክፍሌን ለቀው ወጡ ቢረጋ ወፃዲቅ ያለፉትን ሁለት ቀን ከፅዳቶቹ ጋር አላየሁትም በመተላለፊያው ላይ ግን ቢያንስ በቀን አንዴ ነጭ ጋዋኑን ለብሶ ሽር ጉድ ሲል ውልብ ይልብኛል ሐኪሞቹ በወጡ ከተወሰነ ደቂቃዎች በኋላ መቶ በስተቀ ያለውን ታከለ ተሾመ ተኝቶበት የነበረውን አልጋ በንፁህ አንሶላዎች ጀምሮ እስከ ባለ ደቃቅ አበባዎች አልጋ ልብስ ድረስ ሸጋ አድርጎ አነጠፈው ደግፎ አነሳኝና ሲስተር ቤት ተብሎ ከሚጠራው ቦታ መቶ ሌላ ታካሚ ከሚያስታምም ጎረምሳ ጋር ተጋግዞ ንፁህ የበሽተኞች የደንብ ልብስ ቢጃማ አለበሱኝ በሽንት የራሰውን ጠቅልሎ ነጫጭ ጓንት ግራብ ባደረጉ እጆቹ ጥግ ላይ አደረገና ወደተነጠፈው አዲሱ መኝታዬ ላይ አስተኛኝ ሲያነጥፍ ሳየው ክፍል የሚጋራኝ አዲስ ጎረቤት የሚያጣልኝ መስሎኝ ከብቸኝነት ተገላገልኩ ብዬ ተደስቼ ነበር ይሁንና ግን በወንድማዊ አስተቃቀፍ የማዘል ያህል ደግፎ ተሸክሞኝ ማለት ይችላል እንክብካቤ በተሞላበት ስሜት ሲያስተኛኝ የተደበላለቀ ስሜት ፈጠረብኝ ምን አይነት ስሜቶች እንደሆኑ እናንተው ገምቱ ለነገሩ በእኔ ቦታ ካልሆናችሁ ሙሉ ለሙሉ ውስጤ ምን ያህል እንደተፍለቀለቀ አይገባችሁም የቢረጋ ወፃዲቅ እግር ክፍሌን ለቆ በወጣ አስር ደቂቃ ውስጥ አይኖቿ የውበት ዜማን የሚያዜሙ ሲያይዋት ቢውሉ የምታምር ነርስ ከወጣት የስራ ባልደረባዋ ጋር መጡ ብቸኝነቱ እንዴት ይዞሃል ወንድዬው ነበር የጠየቀኝ መቼም አይለመድም በህይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ ማንንም አጣሁ አንድ እንኳን በቅርቡ አጠገብህ ሌሎች ይመጣሉ እኛም ሁልጊዜ ከአንተ ጋር ነን አይኗ እያበራ ታወራለች መልካም አመሰግናለሁ በእጃቸው የያዙትን በደስታ እያየሁ ነው ሽንት መቀበያ ፕላስቲክ ነው ለጊዜው ሸንት መቆጣጠር አትችልም ስለዚህ ያስፈልግሃል ዶር ቀደም ብለው ነግረውኛል በድጋሚ አመሰግናለሁ ከላይ ከአልጋ ልብሱ ጀምሮ እስከ ውስጥ ድረስ ገለጡልኝ ቱታዬን ገለጥ አድርገው ወጣቷ የጤና ባለሙያ በእንስቷ እየታገዘ በማለስለሻ ቅባት ጄል በመቀባት መካከለኛ የሆነ የፕላስቲክ ቱቦ አይዞህ ተረጋጋ ምንም ስሜት አይሰማህም እንዳትፈራ አለኝ ልምዱ አለኝ መልካም ነው ቀጥል አልኩ አዘቅዝቄ እያየሁ ከዚህ በፊት ተጠቅመነላ ነርሷ ነበረች አንድ ጊዜ በቅርቡ አዎ ማስገባት ሲጀምር እስቲ ስጠኝ እኔ ልሞክር አለችው ብዙ የሚከብድ አይደለም አብረን እንስራው አቀበላት ቀና ብሎ እያያት በግራ እጀ ብልቴን በቀኝ እጄ የፕላስቲክ ቱቦውን ካቲተር ይዛ ለማስገባት ተመቻቸች ከሠውነቴ መገርጣትና መደካከም በተጨማሪ የመራቢያ የወንድ ብልቴም ጥንት ከነበረበት አቋም ወርዶ ሳስታ ተልፈስፍሳ ጨርቅ ሆናለች ክልትውትው ስራ ያቆመች ይመስላል በምታምረዋ ባለክብልል አይኗ ነርስ እጅ ተይዛ እንኳን ብልቴ ከቦታዋ አልተንቀሳቀሰችም አዘንኩላት አብዛኛው አካላቶቼ ከአገልግሎት መስጫ ውጭ እየሆኑ እንደሆኑ ታወቀኝ ጨርሰው ወጡ አሁን ትልቅ እረፍት ተሰማኝ ሽንት አይወጥረኝም ለሊትም ሆነ ቀን መሽኛ እቃ የሚያቀብለኝ አልፈልግም ወደ ውስጤ ዘልቆ ፊኛዬ ድረስ በገባው ቱቦ እየወረደ የሚጠራቀምበት ባለ ሁለት ሊትር የፕላስቲክ ከረጢት አለ እሱ እስኪሞላ ያለመጨነቅ በሽንት ያለመወጠር መብት እና እድል ተሰጥቶኛል በማንኛውም ሰዓት ወይም ግዜ አንድ ሰው ገልብጦ ይደግፈኛል አሁን የቀረኝ ኦክስጅን ስጨርስ ባለሙያ መጥራት የሚችልልኝ ረዳት ማግኘት ይኸም ቀላል ነበር የሞሼንና የሰለሞንን የእጃቸውን ስልክ መቀበል እችላለሁ ባለሙያዎቹ እነሱና ጓደኞቻቸው ናቸው ለሊት ላይ የምሸናበትን እቃ የሚያቀብለኝ አጥቼ ነው ብዬ ከመናገር ይልቅ መቆጣጠር ሳልችል አምልጦኝ ነው ዝም ብሎ ይፈሳል ብዬ ያዥጎደጎድኩት ውሸት ምንም አልቆጨኝም እርግጥ ለጠበቃና ለሀኪም መዋሸት መዘዙ ብዙ እንደሆነ ባውቅም ለዛሬው ግን የተሳካልኝ ይመስላል መልካም እረፍት ሳልንቆራጠጥ ባልረጠበ መኝታ ላይ አድሬ የማለዳዋን መርፌ ተወግቼ ረፋድ አካባቢ ይመስለኛል አንድ ሐኪም በመስኮት በኩል ቆሞአል ማነህ አንተ ስምህ ማን ነበር አክብሮት በጎደለው ድምፅ ጠየቀኝ ቅጣው ነኝ እንዲያናግረኝ ፈለኩ ስማ ዝም ብለህ በጀርባህ ብቻ አትተኛ ገልበጥ ለማለት ሞክር ቁጣ ያለበት ትዕዛዝ ብችል ደስ ይለኝ ነበር ግን ዝም አልኩ በኋላ ጀርባህ ይቆስልና ሌላ ጣጣ እንዳታመጣብን ስንቱ አስቸግሮናል ተንቀሳቀስ አሊያም ገልብጡኝ በል ያልተገላበጠ ብቻ በርታ ሄደ መጀመሪያ ተናደድኩ ብቆስል እኔ ጣጣው ለእኔ ስቃዩ ለእኔ ብሞት እኔ እሱ ምን ይሆናል ከዚህ በፊት አይቼው አላውቅም እንደ መስቀል ወፍ አንዴ የሚከሰት ሐኪም ብቆስል ቢያየኝ ለደቂቃዎች ነው ብሽቅ አልኩኝና መልሼ ፈገግ ስንት አይነት ሰው አለ እባካችሁ ምን እንደማስብ ምን እንደምል ጠፋኝ ምን ነበር ያለው በተደበላለቀ ስሜት አጨበጨብኩና በረዥሙ ተንፍሼ ሁለቱንም የእጆቼን መዳፎች ግራና ቀኝ አልጋዬ ላይ አድርጌ ወደ ታች ገፋሁ ከወገቤ በላይ ከፍ አልኩ ተስፈንጥሬ እግሮቼን በመጠኑ እንዳጠፍኩ መኝታዬ ላይ ቁጭ አልኩ ደነገጥኩ መልሼ በጀርባዬ ብተኛ መነሳት የማልችል መሰለኝ መቀመጥ ናፍቆኝ ስለነበረም ይሆናል እንደዛው ቀረሁ ውስጤ ተፍለቀለቀ መኝታዬ ላይ እንደተቀመጥኩ አሮጊቷ ወደ ውስጥ ዘልቀው ሲገቡ በደመ ነፍስ እያየዋችሁ ነው በሐሳቤ ግን ተበታትኛለሁ ምን ልርዳህ ልጄ የአዛውንቷ ድምጽ ያምራል ደህና ነኝ እማማ ያሉትን በደንብ አልሰማሁም ነበር ሁልጊዜ ነው የማይህ አንተ አታውቀኝም እንጂ በእናትነት ስሜት ማውጋት ቀጠለሉ በመስኮቱና በበሩ በኩል ሲመላለሱ አዮታለሁ ሰው እያስታመሙ ነው አልኳቸው አፍና አፍንጫቸውን የከለሉበት ማስክ የሀኪሞቹን እና የአስታማሚዎቹን አይነት መሆኑን ልብ ካልኩ ቀናት አስቆጥሬያለሁ የ ወር ህፃን ልጄን ነው የማስታምመው ልቤ ትርክክ አለች ደነገጥኩ ስድስት ወር ምን ማለትዎ ነው ገና ጡት የምትጠባ ጨቅላ የእሳቸውን እድሜ እየገመትኩ ልክ ብለሃል ለጡት አልታደለችም እናቷም አባቷም በሞት አታለች እኔ የሟች አባቷ እናት ነኝ የማይሰማ ጉድ የለ ትኩር ብዬ አየኋቸው ቀይ በወጣትነታቸው መልከ መልካም እንደነበሩ አሁንም ያስታውቃል ከቁመታቸው ዘለቅ ብለው ፊታቸው ብሎም አንገታቸው አካባቢ የእድሜ መንጎድ የሚያመጣው ጨምደድ ማለት ተጀምሮአል እጥፋቶች በርከት ብለው በቅርብ ጊዜ ውስጥ መጎሳቆል እንደጀመሩ አይኖቻቸው ያስታውቃል እንደው ዞር ብዬ ሳይህ ቁርጥ ልጄን ነው የምትመስለው እና ታሳሳኛለህ ከሞተው ጋር እንዳይሆን የሚያመሳስሉኝ በልቤ ነው ያልኩት ሁልጊዜ መቼ ነው ሠላም የምልህ እያልኩ እጨነቃለሁ የህፃኗ ነገር እረፍት ነሳኝ እንጂ ውስጤ ትመላለሳለህ የምታስብልኝ እናት አገኘሁ መሰለኝ ብዙ ጊዜ ሆናት ከታመመች አሁን መቀመጫ እየደከመኝ መቷል ሁለት ሳምንት ጨርሳለች ለውጥ ግን የላትም መድኃኒቶች እየወሰደች ነው በአፍንጫዋ ቱቦ ተደርጎላት እለት እለት ኪኒኖቹን እያሟሟን በስትሪንጅ በቱቦው በኩል እናስገባላታለን ምግብም በፈሳሸ መልክ እንደዛው ነው እንዳንተው መተንፈሻ ኦክስጂን ተገጥሞላታል መስማቱ እራሱ አመመኝ እማማ አይዞት እግዚአብሔር የሚሆነውን ሁሉ ያውቃል በድፍረት ይኹን ማወቁን እየተጠራጠርኩ ሁላችንስ ነፍስ በእሱ እጅ አይደለች ጌታ ያውቃል ተስፋችን ማን ሆነና ሲሉኝ አምላኬን በመጠራጠሬ ከመቅፅበት ተፀፀትኩ ዛሬ ገና ተቀምጠህ አየሁህ እንዴት ነህ በስስት ያዩኛል እኔማ ምን እሆናለሁ ደግሞ መተኛት ደከመኝ ነገ ከነገ ወዲያ ወደ ውጭ እወጣለሁ ከእኔ የባሰችውን ጨቅላ እያሰብኩ ነበር ታ ይፈውስሃል ከለምለም ጋር ብዙ ተጫውተናል ስለእኔ ጥናት አድርገዋል ለካ የሚል ስሜት ተሰማኝ ለሚ እኮ ጥላኝ ሄደች እግዚአብሔር ያክብራት አክብራኝ ነበር መጨረሻ ዘረጠጠችኝ እንጂ ፈገግ ለማለት እየሞከርኩ አውቃለሁ ልጄ ወዳ አይደለም ልጃችሁም እናትም አባትም አጠገቧ ከምታጣ የሷ መሄድ ደግ ነው የኔዋን አታይም ከሁለት አንድ የላት ብቻዬን መሆኔ ከፋኝ እንጂ ቂም የምይዝበት ምን ምክንያት አለኝ ማዘር ታም የሚወደው እሱን ነው ጥላቻ አስወግዱ ፍቅራችሁ ይብዛ ደግሞ ትድናለህ እርግጠኛ የሆኑ ይመስላል አመሰግናለሁ እማማ ትንሽ አረፍ ልበል በጀርባዬ ዘፍ ብዬ ወረድኩ በጣሙን እጅግ ደክሞኝ ስለነበር ተንጋልዬ ስተኛ ታላቅ እረፍት ተሰማኝ ቆይ ቆይ ይኹ ሸንት እንዴት ነው የሚያደርገው ሲሉኝ ከሀኪሞቹ ቢሮ የእጅ ጓንት ግላብ እንዲያመጡ ጠየኳቸው ከአንድ ነርስ ጋር በመሆን በርካታ ግላቦችን በአስተኛ ካርቶን አምጥተው ላንተ ነው ማንም ሰው በዚህ እየተጠቀመ ሊረዳህ ይችላል በማለት አዛውንቷ ሌላ ጊዜ እኔን ለመርዳት እንዲመቻቸው ነርሷ ምኑ ጋር ከፍታ ሽንቱን ወደ መድፊያው እንደምትገለብጥ ካዩ በኋላ ከአሁን በኋላ አይከብደኝም እኔ ነኝ የምደፋልህ ብለው መልካም ተመኝተውልኝ ተያይዘው ወጡ የስድስት ወር ጨቅላ ህፃን አንደበቷ ከለቅሶ በስተቀር ተኮላትፎ ለመናገር ብሎም ለመሳቅ ሳይታደል አልፎ አልፎ ከምታሰማቸው እሪታ በስተቀር በዝምታ ተለጉሞ ወላጅ እናትና አባቷን በተመሳሳይ ሁኔታ በሞት አጥታ ትሁት በሆኑ አዛውንት አያቷ እጅ ላይ ወድቃ ማደግና መጦር ያለባቸውን ሁለት ወገኖቼን ማሰብ ብቻውን ይሰቀጥጣል እውነት ባይሆን ተመኘሁ ግን በውኔ ነው እያየሁ እየሰማሁም ያለሁት የሁለት አመት ዕድሜ ያላትን ልጀን እያስታመመች እንደሆነ ለምለም የነገረችኝ የደቡብ አካባቢ ቅላፄ ባለው አማርኛ የምታወራው ወጣት የታካሚዋን ተከታይ ልጄን በጀርባዋ አዝላ አጠገቤ ያለውን የምግብና የመጠጥ መደርደሪያ አስተካክላልኝ ጨርሳለች ውኃ ሲያስፈልግ እዚ ጋር ተቀምጧል እንድደርስበት ወደ መኝታዬ ጠጋ እያደረገች አመሰግናለሁ አሁን እኮ ትንሽ መንቀሳቀስ ችያለሁ እጆቼን ወደ መደርደሪያ እየዘረጋሁ ቲድናለህ የአንተ ሚስት ክፉ ነው ጢሎ ሄደ ሚንድኖ ችግር ነው አንተ እሱ ወደ ቤት በለምለም እንደተናደደችባት ያስታውቃል አን ልጅሽ እንዴት ነች ጨዋታ መቀየር ፈልጌያለሁ መልሷም ያስፈልገኛል ዔታ ይባረክ ዛሬ ጢሩ አደረች የጌታ ስም ይባረክ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ ጴንጤ መሆን አለባት ተጠራጠርኩ ቢረጋ ወፃዲቅ በቀን ሁለት ጊዜ ወይ ይቀይራል አልያም ያጥበዋል መሰለኝ ከላይ የሚርበው ነጭ የሀኪሞች ገዋን ንፁህ ነው ጠቆር ካለው የቆዳ ቀለሙ ጋር አብሶ ፈክቶ ነው የሚታየው ብዙም በማይነበበው በማይስቀውም በማይቆጣውም ፊቱ ዘው ብሉ ገባ ባለበት ቆሞ እንደቀረ አንቺ አላት ስሟን ከነአባቷ እየጠራ አጠገቤ ልጅ አዝላ የቆመችውን ወጣት የታካሚዎች ክፍል አትግቢ ብዬሽ አልነበር ይቆጣ አይቆጣ አልገባኝም ሰው ሲለሌሎ ነው ውኃ ይሠጣል ብዬ እኮ አቋረጣት ይኸውልሽ በሽታው የሚተላለፈው በትንፋሽ ነው የተለያዩ ታካሚዎች ጋር በገባሽ ቁጥር ለአደጋ መጋለጥሽ ሰፊ ነው ለራስሽ እንኳን ባታስቢ ላዘልሻት ህፃን አስቢ ባንቺ ተማምና ጀርባሽ ላይ ተኝታለች አንቺ ግን ወደ አደጋ ትወስጃታለሽ በይ አሁን ውጭ ከዛሬ በኋላ ተጠንቀቂ በጣም ተጠንቀቂ እንድታልፍ መንገዱን እየለቀቀላት ነበር ቅጣው መድኃኒትህን በአግባቡ እየወሰድክ ነው አስተያየቱ ደስ ይላል ለመግለፅ ግን የሚቻል አይደለም መርፌውን እየለመድኩት ይመስላል የሚዋጡት ግን በጣም ይከብዳሉ ፊቴን እያጨማደድኩ ለመግለፅ ሞከርኩ አሁን ወደ ፊት ለፊት ልንወስድህ ነው በማለት ተከትሎት ከመጣው የጤና ባሙያ ጋር ከተኛሁበት አንስተው ዊልቸር ላይ አስቀመጡኝ ለኦክስጅኑ ይመስላል በተረጋጋ ስሜት አፈጣጥነው ይዘውኝ ወጡ የማዘል ያህል አቅፎና ደግፎ ዊልቸር ላይ ያስቀመጠኝ ቢረጋ የኦክስጅኑን በርሜል እያንከባለለ ሌላኛው ነርስ ደግሞ እንደተቀመጥኩ በተሽከርካሪው ወንበር እየገፋ ወደ ፊት ለፊት በኤልሼፕ የተሠሩት ሁለት ረድፍ የሀኪሞቹን ቢሮ ጨምሮ ከአስራ አንድ ክፍሎች ውስጥ ማዕዘኑ ላይ ያለው በውስጡ ስድስት አልጋዎች ያሉት አስገብተው በመስኮቱ በኩል ተነጥፎ የተዘጋጀ መኝታ ላይ አስተኝተውኝ ወጡ እኔ የገባሁበት ክፍል መደዳ አራት ተመሳሳይ መኝታ ያላቸው በይዘታቸው ሰፋፊ ብሎም እኩል የሆኑ ሁለት የሴቶች ሁለት የወንዶች ክፍል ሲኖሩ በአጠቃላይ ሃያ አራት አልጋዎች አሉ በኤል ቅርፅ የተሰራው ሌላኛው መደዳ ደግሞ ሁለት ባለ ሶስት አልጋና ሶስት ባለ አንድ አንድ መኝታ የያዙ ክፍሎች በጠቅላላው ዘጠኝ ታካሚዎች ሲኖሩ በሁለቱ ተርታ ቤቶች መገናኛ ላይ የሐኪሞች ቢሮ አለ በመካከል ቀጭን አዲስ ታካሚዎች የሚገቡበት ወደ ጓሮ የምታሳልፍ መጠነኛ መንገድ አለኝ በጠቅላላው በዚህ ቦታ ላይ ከጀርባ ያሉትን ሳይጨምር ሰላሳ ሶስት የታካሚዎች አልጋ አለ ሁሉም በተለያየ የህክምና ደረጃና ጊዜ ላይ ባሉ ወገኖች ከእናታቸው ማህፀን በወጡ በወራት እድሜ ላይ ከሚገኙ ህፃናት ጀምሮ እድሜ ጠገብ አዛውንቶች ድረስ በሁለቱም ፆታ ተሰባስበውበታል ብቻ ለማንኛውም ዘር ፆታ እድሜ ሐይማኖት ሀብታም ደሀ የተማረ ያልተማረ የእምነት መሪ የተፈረደበት ወንጀለኛ መላ ቅጡ በማይታወቅ መልኩ ከአራቱም የአገራችን አቅጣጫ የተሠባጠሩ ሰዎች በብዙ መልኩ የሚለያዩ ቢሆንም አንድ ቦታ ተገናኝተናል ለአንድ ሰዓት ስብሰባ አልያም ለቀናት አይደለም ቀን ከለሊት ሳንለያይ ወራት ልናሳልፍ በአንድ ጉዳይ ግን አንድ አይነት ነን በጠቅላላው መድኃኒቱን የተለማመደ ቲቢ ባክቴሪያ ተጠቂ በመሆናችን ይሁንና ግን እድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች አልያም አዛውንቶች በተጨማሪም በተጓዳኝ የኤች አይ ቪ ቫይረስ በደም ውስጥ ሲኖር ስኳር ደም ግፊት ኮንስሮይል የኩላሊት የልብ ችግሮች ሲኖሩ ህክምናው ውስብስብ ሆኖ የተለየ የሐኪም ክትትል መድኃኒቶችን ማመጣጠን ከመጠየቁ ባሻገር ሁላችንም ተከታታይ መርፌዎችን ለስምንት ወራት እንወጋለን ከአስር ያላነሱ ኪኒኖችን እንውጣለን ለአስራ ስምንት ወራት ይኹ ያመሳስለናል አራት ነጥብ ሶስት ሶስት አልጋዎች ትይዩ ተደርድረዋል በሁለቱ ረድፎች መሀል ሁለት ሜትር የሚያክል በየመኝታዎቹ መሀል ደግሞ አንድ ሜትር ተኩል ልዩነት ሲኖር ባለሁለት ተካፋች ሠፊ በር ግራና ቀኝ እያንዳንዳቸው አንድ ሜትር ከ ሴሜ የሚሆን ስፋት ያላቸው በመስታወት ያጌጡ መስኮቶች ሲኖሩ ከነሱ ትይዩ ያለው ግድግዳ ተመሳሳይ ሌላ ሁለት መስኮቶች ስር አንዱ መኝታ የእኔ ነው ክፍሎቹ ጣራቸው ከፍ ያለ በመሆኑ ብሎም ሁሉ ነገሩ ሲከፋፈት ሁልጊዜ ቀዝቃዛና ነፋሻማ ነው ሆስፒታል ሆስፒታል የሚሸት የአልኮል አልያም የመድኃኒቶች ጠረን እንኳን አይሰማም ሁልጊዜ ጠዋት ጠዋት ግን የፅዳት ሠራተኛችን እስከሚወጣ ድረስ ዲቶል ብሎም የዱቄት ሳሙና ቤቱን በሚያጥቡበት ጊዜ ይሸታል በግራ ጎኔ ስተኛ በመስኮቱ በሻገር ሌላኛው የግቢው ጓሮ ይታየኛል ማንም ሰው አይንቀሳቀስበትም እጅብ ብሎ ከፍታ የጨመረ የጫካ ሳር በቅሎበታል ከስር የዝናብ ከአሸንዳ መቀበያ ቦታ አለ ከአራት ሜትር በኋላ የሆስፒታሉ የመጨረሻ የግንብ አጥር ይታያል ወደ ቀኝ ጎኔ ስዞር ክፍሌ ውስጥ ከተኙት የክፍል አጋሮቼ በሻገር ፊት ለፊት በተበረገዱት በርና መስኮቶች ውጭ በክልሉ ያሉ ታካሚዎች አረንጓዴ የትንፋሽ መከላከያ አድርገው ውር ውር ሲሉ በተጓዳኝ የጤና በለሞያዎች አልያም የክልሉ የስራ ባልደረቦች ሲመላለሱ ማየት እችላለሁ ከብቸኝነት ተገላግዬ ሌላ ኑሮ ጀመርኩ በአንሶላዎቹ ንፅህና እንዲሁም በአነጣጠፍ በኩል ነርሶቹ አስደማሚ ስልጡን ናቸው አሁን የተኛሁበት መኝታ ዘና ባለ እረፍት መስጦኛል በእርጋታ እየተገላበጥኩ ሰው ሰራሽ ኦክስጂኔን እንዲሁም አካባቢዬን በአይኔ በብረቱ እየኮመኮምኩ ነው አመሻሽ ላይ ነው በረንዳዎቹ ላይ ብሎም በየክፍሉ ከበሩት ረጃጅም ሸንበቆ መብራቶች በስተቀር አካባቢው ፀጥ ረጭ ብሎአል በቅርብ ርቀት የቴሌቪዥን ድምፅ ይሰማል እኔ ክፍል ያሉት ስድስቱም አልጋዎች ሰው እንዳለባቸው አጠገባቸው ከተቀመጡት ጭማቄ ውኃ ፍራፍሬ ሠሀን ኩባያ ፖፖ ጋቢ የመሳሰሉትን በማየት መገመት አያዳግትም ለጊጊው ግን አምስታችን መኝታችን ላይ አለን አንደኛው ቲቪ እያየ እንደሆነ ገምቻለሁ መቼም በመሠለኝ በግምት ብዙ ዘመን ኖሬያለሁ አይኖቼን ከድሄ በሰመመን ውስጥ የሆነ ድምፅ ሰማሁ በደንብ እስከማረጋግጥ ድረስ በእውኔ ይሁን በህልሜ አልገባኝም ነበር ቁራሌው ቆራሌ ው ዜማው አንድ ቱታ ለብሶ ማዳበሪያ የያዘ ሰው ይመስላል ቆርቆሮ ያለሸ ብልቃጥ ጠርሙስ አሮጌ ጫማ ያለሽ ጓሮ እያለሁ በመተላለፊያው ሳይ ያለማቋረጥ እየዘፈነ ሲያልፍ አንድ ሶስት ጊዜ አይቼዋለሁ አሁን አዲሱ መኝታዬ እግርጌ ጋር ቆሞአል ብረታ ብረት አሮጌ ጫማ የለህም ቁራሌው ቁሬ ቁሬ ቁሬ ሌው እጆቹን ለመጩበጥ ዘረጋልኝ ደህና ነኝ እንደምን ነህ ፈገግ ለማለት እየሞከርኩ በመዳፌ መዳፉን ያዝኩት እድለኛ ነህ ሁለት ወር እዚህ አልጋ ላይ ተኝቻለሁ የኔን አልጋ በማግኘትህ እግዚአብሔርን አመሰግን እሺ አመሰግናለሁ እግዚአብሔር ይመስገን ከረዥም ጊዜ በኋላ ድምፅ ያለት ሳቅ ሳቅኩኝ ፈታ ዘና በል እንግዲህ ላዲሱ ገቢ አንድ ነጠላ ዜማ ልልቀቅለት እጁን ማይክራፎን የያዘ አስመስሎ አፉ ላይ ደቀነና አስቀድሜ የማውቀውን የፀሐዬ ዮሐንስን ዜማ ግጥሙን ቀይሮ ያንቆረቁረው ጀመር ተባለ ተባለ እንዴ ተባለ ተባለ እንዴ ሲያስለኝ ሲያልበኝ ሳስቼ በመድቀቄ ሊሞት ነው ለየለት ተባለ እንዴ ይህም ተባለ እንዴ ተባለ ተባለ እንዴ መንቀሳቀስ አቅቶኝ አልጋ በመውደዴ መተንፈስ አይችልም ሐኪም አጣለት ዘዴ ይህም ተባለ እንዴ ተባለ ተባለ እንዴ ድምፅ እንዴት እንደሚያምር በመሀላ የማምን ሰው ብሆን ኖሮ አሁን ነበር የምምልላችሁ ሐሪፍ አቀንቃኝ ነው ሁሌም ከነአባት ስሙ ነው የሚጠሩት እዮብ ወማርያም እዮብ ወማርያም ስማኝማ ሳልጠይቅህ መቼ ነው መድኃሂትህን የምትጨርሰው እግርጌዬ ፊት ለፊት አልጋው ጠርዝ ላይ የተቀመጠው ክልስ መሳይ ደሙ ኢትዮጵያዊ የሆነ ታካሚ ጠየቀው ጋሽ አበራ እስካሁን እጨርስ ነበር ትንሸ ሳይመረቅልኝ አልቀረም ክልሱ አበራ እንደሚባል አወኩ ምን ማለትህ ነው በህክምና ደግሞ የምን ምርቃት አመጣህ ትሁት እንዴት ነው ያለው አበራ ከሁለት ዓመት በላይ ይሆነኛል መድኃኒት ከጀመርኩ በጣም የተረጋጋ ነው አነጋገሩ ታዲያ ለምን አልጨረስክም ለራሴ ስል መልሱን ለመስማት ጓጓሁ መጀመሪያ ህክምና ስጀምር በጣም ደክሜ ነበር ከአልጋ መነሳት ቀርቶ መገላለጥ አልችልም ነበር ልክ እንደእኔ አልኩ በልቤ ጆሮዬን አቁሜ አሁን ግን ደህና ነህ ለብዙዎች ትላላካለህ ቀን ላይ ስተኛ አይቼህ አላውቅም ክልሱ ጠየቀ መድኃኒቱን ስጀምር በትክክል ነበር የምወስደው ስምንት ወር መርፌዬን ጨርሼ አስራ ሁለት ኪኒኖችን በየቀኑ የመቃም ያህል እየዋጥኩ ነበር ጤንነቴ ተመልሶ ደህና የሆንኩ ሲመስለኝነ ወደ ቀድሞ ስራዬ ስመለስ በአስራ አራተኛው ወሬ ለመጨረስ አራት ወር ሲቀር አቋረጥኩኝ ከሚከታተሉኝ ሐኪሞች ደብዛዬን አጠፋሁ አልሰማ ብዬ አለ እያጉተመተመ እና ታዲያ ለምን ተመለስክ የእኔም ጥያቄ ነበር ለተከታታይ ትንሽ ጊዜያት ደህና ነበርኩ ከጊዜ በኋላ ግን እንደቀድሞ አይነት ስሜቶች ይሠሙኝ ጀመር አነስተኛ ሳል መጣ ለሊት ያልበኝ ጀመር ክብደቴ መቀነስ የምግብ ፍላጎቴ መጥፋት ጀሠመረ ትንሽ ሰርቼ ቁና ቁና መተንፈስ ሆነ ተጠራጠርኩና ጤና ጣቢያ ሄጄ ተመረመርኩ የፈራሁት አልቀረም ቲቢ አገርሽቶብሃል ተባልኩ ቀጥጣ ወደዚህ ሆስፒታል መጣሁ ስሸሻቸው የነበረው በእጃቸው ወደኩ በጣም እንደተቆጪ ጠይም ክብ ፊቱ ያሳብቅበት ነበር አንተ በቃ ይሞታል ሐኪም መስማት የለም መድኃኒት አቋረጠ ነው አለቀ ይሞታል አንተ በስተቀኙ የተኛው ኮልታፋ የሚሉ ጣፋጭ አማርኛ የሚያወራው ትውልደ ኢትዮጵያዊ የሆነው ሶማሌ አብዱሜሊክ ነበር የተናገረው አብዱመሊክ በቃ አንተ ጥሩ ነገር ከአፍህ አይወጣም እዮባ እየተንጎራደደ ነው የሚያወራው አብዱመሊክ ከተጋደመበት ትንሽ ቀና እንደማለት ብሎ የእጁን መዳፍ ወደ እዮብ አቅጣጫ ዘረጋና ና አሁን ሻይ ፍላ ብር እኔ ይሠጣል አለው እኔ ለገንዘቡ አይደለም ወንድሜ አይደለህ አፈላልሃለሁ አምጣ የታለ ማንቆርቆሪያህ ተባለ ተባለ እንዴ ተባለ ተባለ እንዴ እያዜመ ማንቆርቆሪያ ሻይ ቅጠል ስኳር ይዞ ወጣ ሲማ የሶማሌ ሻሂ ነው የሚፈላ ይጣፍጣል የለም አስር ብር የለም አነጋገሩ ያምራል የክፍሌ ስድስተኛው አልጋ ላይ ማን እንዳለ አረጋገጥኩ ቴሌቪዥን ተመልክቶ እየገባ እንደሆነ ከልምዴ አረጋግጫለሁ ጓሮ በስተቀኝ የነበረው ታከለ ተሾመ ጋቢውን ተከናንቦ ገባና አልጋው ጠርዝ ላይ ቁጭ አለ ሁላችንም በተመሳሳይ ሰዓት ስለነበር የምንወስደው ደርሷል ደርሷል ተባባሉና የማታውን ሁለት ኪኒኖች አንስተን ዋጥን አብዱመሊክ በቻርጅ ኃይል ተሞልታ ድምጻ ቀውጢ የሆነችው ራዲዮ ቀነስ አድርጎ ከሚሞሪው ላይ መንዙማ ከፍቶአል ሁሌም መኝታው ላይ በፀጥታ ተጋደመ መገላበጥ ናፍቆኛል የዛሬዋን ለሊት ግን ከእንቅልፍ ሠመመኔ በነቃሁ ቁጥር አንዴ በግራ ሲቀጥል በቀኝ ጎኔ ስጋደም ቆየሁ በጀርባዬ ለደቂ እንኳን መቆየት አልቻልኩም እርግጥ በግራ በኩል ስተኛ ከትንሽ ደቂቃ በኋላ ምቾት አይሰማኝም ሳል ያጣድፈኛል ሰብቆ የሚይዝ ውጋትም ቀስፎ ቶሎ አይለቀኝም በደረቴም ልሞክር ብዬ ነፍስ ውጭ ግቢ ሆኖብኛል መተንፈስ አልቻልኩም ቀጃ ግን ተመችቶኛል ወደ ክፍል አጋሮቼ ቀጥታ ወደ አብዱመሊክ ብሎም መግቢያ በሩ እፋጠጣለሁ ሁሉንም በየተራ ውጭ ድረስ መቃኘት ደስ ብሎኛል ብርቄም ሆኖአል የሽንት ነገር እረፍት ላይ ነኝ ማጠራቀሚያ ፊኛዬ ወደ ሰው ሰራሽ ላስቲክ ተተክቶ መኝታዬ ስር እንደተቀመጠ ነው ንጋት ላይ ነው ገና አስራ ሁለት ሰዓት የሞላ አይመስልም በማለዳ ማዜም ከሚገባቸው ወፎች ታጅቦ ከፍ ዝቅ እያለ የሚወጣ ዝማሬ ከጋሽ አበራ አልጋ ላይ ይሰማል ኑሮ ከጌታ ከኢየሱስ ጋራ በሸለቆ ይሁን በተራራ አመቺ ነው ደስ ያሠኛል እርካታን ይሠጣል ከአመታት በፊት እንጦጦ መካነ ኢየሱስ ሲዘመር ሰምቼዋለሁ በመሀል መዝሙሩን ገታ ያደርግና ልብ በሚሰውር ስሜት ውስጥ በገባ የተነካ ድምፅ ፀሎቱን ድምፅ እያሰማ ለቀቀው እግዚአብሔርን ሁሉንም ነገር የተደረጉለትንም ያላገኛቸውንም በመዘርዘር አመሰገነ ግቢው ውስጥ የተኛነውን በሙሉ ስም እየጠራ መዳንን መፈወስን ጠየቀልን ጌታ ኢየሱስ ሐኪሞቹን ዶር በቀለን ቢረጋን ሌሎች ነርሶችን በየስማቸው እየጠራ ጥበባቸውን እንዲያበዛላቸው በነሱ እንዲሰራ ለመነ አዲስ ክፍላችን የተቀላቀለውን ስሙን የማላውቀውን ታካሚ እግዚአብሔር እርዳው አድነው ሲል አሜን አልኩ ድምፅ ቀንሼ ዛሬ ከአምስት ሰዎች ጋር ተቀላቅዬ ነው መርፌ የተወጋሁት እንደ ክብደታችን ብሎም ተጓዳኝ ያለብን ችግር ታይቶ የተለያየ ግራም ነው እንጂ የምንወጋው አንድ አይነት ካፕሮማይሲን የተባለ የመድኃኒት ዓይነት ነው እንደ አጀማመራችን ያሳለፍነው ጊዜ ቢለያይም የክፍሉ ሰዎች በሙሉ ተቀራራቢ የህክምና ጊዜ ላይ ነው ያለነው ሐኪሞች በጉብኝታቸው ሰዓት አሁን እየተመገብኩ ያለሁት እንደሚያንስና ማሻሻል እንዳለብኝ ተነግሮኝ እጄ ላይ ተሰክቶ በደም ስሬ ሲሰጠኝ የነበረው የምግብ ጉሉኮስ ተነስቶልኛል ክብደታችን ሲጨምር አልያም ሲቀንስ የምንውጣቸው ኪኒኖስ ቁጥራቸው በሐኪሞቻችን ይስተካከላል የጎንዮኙሽ ጉዳታቸውም በተለየ መልኩ ሲታይብንም ማስተካከያ ይደረግልናል እኔ አሁን ባለሁበት ደረጃ መድኃኒቶቻችንን በተለመደው እኩል ሰዓት ከወሰድን በኋላ ያለው የድበታና የመጨናነቅ መነጫነጭ ማስመለስ ተስፋ የመቁረጥ ስሜቶች በከፊል ተደራርበው ሁላችንንም ይሠሙናል ስለዚህ ሁሉም ይተኛል ብዙ እንቅስቃሴ አይታይም ወተታችን መቶ ሁሉም በሚችለው አቅም ከጠጣ በኋላ እንቅስቃሴዎች ይበረክታሉ ታከለ ተሾመ እግርጌ ፊት ለፊት መግቢያ በሬ አጠገብ ሲገባ በስተቀኝ በኩል መስኮቱ ስር የሚተኛው ትውልደ ሶዶ ጉራጌው ስሙ የጠጣውን ወተት ታሽጎት የነበረውን ላስቲክ በር ላይ ያለው የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ውስጥ ጥሎ ተመለሰ አጠገቤ የተኛው ጋር ጠጋ ብሎ አብዱመሊክ ዛሬ ያንተ ተራ ነው ሻማ ግዛ እጁን እየዘረጋለት ጣሬ ደግሞ ምንድን ይበራል ሻማ ልደት ነው አንተ ሁለት ቀን ነው አንተ ገብርኤል ብሉ እኔ የገዛኝ ተረኛ ነው እኔ። እየተውረገረገ ጠየቀው ዘፈን ተው አንተ ታስሮአል ነበር ምክንያት ንገር ሠረቀ ነው የታሠረ አብዱመሊክ ሲናገር ይሥሃል እዮብ ወማርያም ታስሮ እንደነበረ አውርቶአል ተፈርዶበት እስር ቤት እያለ በዘፈን አዘፋፈኑ ተማርከው በወቅቱ ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን ቴዲ አፍሮ ከእስር የተፈታበት ጊዜ ስለነበር የሚተካው ባለ መረዋ ድምፅ ባለቤት መጣ ብለው የቲዲን ቦታና አልጋ እንደሰጡትና እንክብካቤ እንደበዛለት ደጋግሞ ይናገራል በምን እንደታሰረ ግን አያወራም ገና አሁን ተጠየቀ አንዱ ነው የተጫወተብኝ ለተወሰኑ ቀናት በደንብ ተግባብቶኝ ሲጋብዘኝ ብሎም ብር እየሰጠ ተንከባክቦ ምርጥ ጓደኛው ካደረገኝ በኋላ የሆነ የሀብታም ትቤት በር ላይ ወስዶ አንድ የሚያምር ታዳጊ ህፃን አሳየኝና ልጄ ነው ብሎ ራቅ ብሎ ላዳ ታክሲ ውስጥ ቁጭ ብሎ አምጣልኝ አለኝ እኔም ልጁን አፈፍ አድርጌ ትንሸ እንደተጓዝኩ በፖሊስ ተያዝኩ ሁሄታውን አስረድቼ ሰውዬውን ከታክሲው ከቦታው አጣሁት ከዚያ በኋላም እስካሁን አላገኘሁትም እኔ ግን ልጅ ልታፍን ነበር ተብዬ ታሰርኩ እዮባ ባጭሩ አስረዳ ሰውዬ የት ሄደ መቼ ነው ጠፋ አብዱመሊክ አፍጥጦ እያየ ይጠይቃል እሱማ በፖሊስ ሳልያዝ ባመጣለት ሊያፍነው ነበር መሠለኝ መያዜን ሲያይ ጠፋ እኮ ነው የምልህ እኔ ደግሞ ሰው አምናለሁ አንተ ሌባ ኖ የልጅ ሌባ ጥሩ ሰው አይደለም አሁን የሚጠጣ ውሃ ምጣ ሻይ ፍላ አሰር ብር ይሰጣል ሁለት ቋንቋዎች ተቀላቅለው በፈጠሩት የአማርኛ ቅላፄ እኔ ለገንዘቡ አይደለም አመጣልሃለሁ አፈላልሃለው የሶስት ቀን ሰላሳ ብር ዛሬ ትሰጠኛለህ ባለ አምስት ሊትሩን ውሃ ማምጫ ጀሪካን ይዞ ወጣ አብዱመሊክ በሶማሊያ ክልል ጅግጅጋ ከተማ የኛ ክፍል የፊዚክስ መምህር ነው የእንግሊዘኛ ቋንቋን የአፍ መፍቻው ያህል ስለሚናገር ከሐኪሞቹ ጋር ለመግባባት እጅጉን ጠቅሞታል አማርኛ በደንብ ይሠማል ሲናገር ተኮለታትፎ ከማጣፈጡ በስተቀር ማለት ነው ሆስፒታሉ ውስጥ ከእኔ በአስራ ዘጠኝ ቀን ብቻ ነው የሚቀድመው በወቅቱ መድኃኒቱን የተለማመደ ቲቢ ህክምና በክልሉ ስላልነበር ነው ወደ አዲስ አበባ የመጣሁ የሚያሳዝነው ነገር አገሩ ታሞ ስታስታምመው የነበረው ወላጅ እናቱም በዚሁ በሽታ ተይዛ ከሱ በመከተል እዚሁ ዋርድ ውስጥ የሴቶች ክልል ለሁለት ወራት ህክምና ተከታትለው አጥጋቢ ለውጥ በማምጣታቸውና የህክምና ክትትሉም ድሬዳዋ ሲቀጥል ጅግጅጋ በመጀመሩ እሳቸው ብሎም ሌሎች ሁለት የሶማሊያ ክልል ተወላጆች ወደ ቀያቸው ተመልሰው በአቅራቢያቸው ህክምናቸውን መከታተል ቀጥለዋል አብዱሜሊክ መሄድ አልቻለም ሰውነቱ መክሳት አልፎ ገርጥቶ አጥንቶቹ ብቻ ቀርተዋል ከአንገቱ በላይ ግን ጠይም የሚያምር የሶማሌ ቀለሙ ተጨምሮበት ከሰልካካ አፍንጫው ጋር ሸጋ መልኩ እንዳለ ሲሆን ምግብ በመጠኑ ይመገባል ከእኔ በባሰ መልኩ የሰው ሰራሽ ኦክስጂኑ ከአፍንጫው ላይ ከተነቀለ በደቂቃዎች ውስጥ ነፍስ ውጭ ነፍስ ግቢ ነው በራሱ ትንሽም እንኳን ቢሆን መተንፈስ አይችልም ሲያወራ ሲናገር ሲጫወትም ድምፅ ከየት እንደሚያመጣ ባላውቅም በጣም ይጮሃል ቁጣ ይቀናዋል መረጋጋት አልፈጠረበትም ሀኪም ታካሜ አስታማሚ ማንንም አይመርጥም መሳደብ ሲፈልግ የስድብ አይነት እንኳን ሳይመርጥ ይሳደባል በየሳምንቱ በፅዳት ታጥበው ያማሩ አንሶላ ለሁሉም ታካሚ ይቀየርልናል ቀኑ ሳይደርስ ቆሸሸ ካልንም ሌላ ይመጣልናል አበራ በየእለቱ የምትመጣው ባለቤቱ ከተቀጠረለት አስታማሚ ጋር በመሆን መኝታው ይነጠፍለታል የሠሙም እንደዛው ታከለ ተሾመ የራሱን ያመቻቻል የእኔና የአብዱመሊክን ግን የተካኑ ነርሶች እንደተኛን ሳያንገላቱን በስልጡን እጆቸው እያሽለኮለኩ ፏ አድርገው ያነጥፉልናል በሚያምር ምቾቱ በተደላደለ መኝታ እፎይ ብዬ አድሬያለሁ የምመገበው ምግብ ፍጆታ ስለጨመርኩ እንዲሁም ትንሽ እንኳን ጠብ የማደርጋትን አይነምድር ስለተውኩኝ የተጠራቀመ ሰገራ ይመስላል አልወጣ ብሎኝ በተኛሁበት እየታገልኩ ሰላሜን አሳጥቶኝ በመሀል እየተጨነኩ ነው ያደርኩት ጠዋት ገና በማለዳ እንቅልፍ ሰመመን ውስጥ ሆፔጄ አጠገቤ ከተኛው ከአብዱመሊክ አልጋ ላይ መለስተኛ የዝማሬ ቅላፄ ባለው ሁኔታ ድምፅን ከፍ አድርጎ ጆሮዬን ሳበው አልሐምዱሊልላሂ ረብቢል ዓለሚን አርረሐማኒር ረሒም ማለኪ የውድዲን አይያክ ነዕቡዲ ወኢይያከ ነሥተቂም ሲሯጠልለዚነ አንሀምተ ዐለይሂም ገይሪል መግዱቢ ዐለይሂም ወለዱዷልሊን ሳይታሰበኝ አሚን አልኩ የማለዳ የፈጅር ሶላት ሱረቱል ፋቲሐ የመክፈቻ ምዕራፍ እየቀራ ነበር በዚህ ሰአት ሁልጊዜ ድምፁን ከፍ ያደርጋል በአጠቃላይ ሌሎቹንም ቀሪ የየእለት የ ፈርድ ወይም ግዴታ ሶላት የሚሰግድ ይመስለኛል ድምፅ የሚያሰማው በዚህ ጊዜ ብቻ ነው ከመኝታው ላይ መንቀሳቀስ ስለማይችል ረከዐ አይቆምም ሱጁድ ግንባር ከመሬት ላይ ማሳረፍ ጀልሳ በሁለት ስጅዳዎች መካከል መቀመጥ አይነት ተግባሮችን አይከውንም በተኛበት ግን ሶላት ያደርጋል በመጀመሪያ ወደ ቀኝ ዞረና ከዚያም ወደ ግራው ወደ እኔ መኝታ ከአንገቱ በመዞር አሥሠላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱላህ ሲል ከልቤ አሜን አልኩ ትርጉሙ የአላህ ሠላምና ራሕመት በእናንተ ላይ ይሁን ሠላምና ራመት ተገኝቶ ነው ደገምኩት አሜን የዕለቱ የሱቢህ ሶላት አከተመ ወደ እኔ ሙሉ ለሙሉ ዞሬ አንተ ጥሩ ሰው ነው አሥሠላሙ ዐለይኩም አለኝ ዋለይኩም ሠላም አልኩ ፈገግ ለማለት እየሞከርኩ ብርድ ልብሱን ከፍ አድርጎ ተሸፋፍኖ ተኛ ዶር በቀለ አባታዊ ስሜት የሚሰጥ እና እርጋታ የተሞላባቸው ብዙ እስከመጨረሻው የሚያዳምጡ ብሎም ትንሽ የሚናገሩ ለህክምና በተፈጥሮአዊ ቅባት የተቀቡ መሆናቸውን ነግሬያችኋለሁ ዛሬ በማለዳ ከነርሶቻችን ጋር አጠገቤ ቆመዋል ቅጣው አዳር እንዴት ነበር የህክምና መዝገቤን እያገላበጡ ጠየቁኝ ዶር ጥሩ ነኝ ግን ድርቀት ይዞኛል ሠገራ እንቢ አለኝ ወደ ወገቤ በታች መልከት እያልኩ ስንት ቀን ሆነህ ማለት ነው ከተፀዳዳህ ፊት ትንሽ ታግዬም ቢሆን ጠብ አደርግ ነበር አሁን ግን አራተኛ ቀኔ መጣ እስቲ ልብስህን ሰብሰብ አድርግ ብለውኝ በጀርባዬ ተኛሁና የመኝታ ልብሶቹን ተጋግዘን ዝቅ አደረግን መላ ሆዴን እስከ ደረቴ ገለጥ አድርገው ሁለት ጣቶቻቸውን በታችኛው የተለያየ የሆዴ ክፍልላይ እያፈራረቁ በማዘዋወር በሌላኛው የእጅ ጣቶቻቸው መታ መታ በማድረግ እንደማዳመጥ ብለው እለት በእለት ምግብ አመጋገብህ በመጠኑ እየጨመርክ ስለሆነ ያጋጥማል የተገፈፉትን ልብሶች እያለበሱኝ ምን ማድረግ ይቻላል አይን አይናቸውን እያየሁ የምትወስዷቸው መድኃኒቶች በርካታ ስለሆኑ ተጨማሪ ማዘዝ አንቸኩልም መጀመሪያ በምግብ ለማስተካከል እንሞክራን የሚያለሰልሱልህ ምግቦች እንደ ጎመን ተመገብ በእንደዚህ አይነት እንሞክርና ፈፅሞ የማይስተካከል ከሆነ ነገ ሌላ አማራጭ እንወስዳለን ወደ አንደኛው ነርስ ጠጋ አሉና በጆሮው ዛሬውኑ ለምግብ ቤቶቹ ነግረህ እንደተለመደው በተለየ መልክ ያዘጋጁለት ሲሉ በደምሳሳው ሰማሁ ዶር አሁን ብዙ ለውጦች እየታዩ እና ደህና እየሆንኩ ይመስለኛል የላብራቶሪ ውጤቶችህም ጥሩ ነው የሚያሳዩት ለማንኛውም ዛሬ ደም ትሰጣለህ የተለየ ምርመራ ያስፈልገኛል። ዝብርቅርቅ ያለ ነገር ማውራት ጀምሬያለሁ በጣም አዝናለሁ እንደዚህ የምትሆን ስላልመሰለች ነው የጠየኩህ አለባብሶኝ ጨርሷል ለስላወራሽኝ ደስ ብሎኛል ትንሽ ሳይቀለኝ አይቀርም ፊቴን ለማፍታታት እያሰብኩ ነበር በምንችለው አቅም ሁሉ እንተጋገዛለን በየሁለት ቀኑ እየመጣሁ እጎበኛችኋለሁ አመሰግናለሁ ወንድሜ እውነትም ወንድም ያገኘሁ ያህል ተሰምቶኛል እጁ ላይ ያለውን ጓንት ቀየረ ጭንቅላቴን ደበስበስ አድርጎ ወደ አብዱሜሊክ አልጋ አመራ በጠራ የእንግሊዘኛ ቋንቋ ሰላምታ ተለዋውጠው ከእኔ ጋር ተመሳሳይ የሆነ አገልግት መስጠት ጀመረ አብዲ የሚያዋራው ሲያገኝ ደስተኛ የሆነ ይመስላል እየጮኸ ከማውራቱ ባሻገር በኃይለኛው ይስቃል የማህበራዊ አገልግሎት የምትሰጠው አይናለም አነሰ ቢባል በሳምንት ሁለቴ በየመኝታችን እየመጣች ችግሮቻችንን ትጠይቃለች መፍትሄ ትሰጣለች ካልሆነም ወደ ሚመለከተው ክፍል ታስተላልፋለች ከእጅ ስራ ስዕል ቅርፃ ቅርፅ ብሎም ሌሎች ማንኛውም ታካሚ መስራት እችላለሁ የሚለውን የፈጠራ ስራ እንዲሰራ ቁሳቆሶች ታቀርባለች ታበረታታለች ከሁሉ በላይ ግን በየመኝታችን ላይ ሆነን የምናመነበው ማንኛውንም አይነት በአገራችን ደራሲዎች የተፃፉ መፃህፍት ትርጉም ስራዎች አልያም በእንግሊዘኛው እንደወረዱ የተፃፉ መጻህፍቶችን እንደየፍላጎታችን ታመጣልናለች አሁን ወቅቱ የዶር ምህረት ደበበ መጽሐፍ ሌላ ሰው የሚለውን ከተቆለፈበት ቁልፍ ለጥቆ የደረሰውን በየተራ አንብበን በተረዳነው መጠን ተወያይተንበታል ያለከልካይ ተችተናል አድንቀናል ከሁሉ በላይ ግን የየግል አማካሪ መጽሐፋችን እንደነበር ሁላችንም አስምረን ተስማምተንበታል አንድነት የሚፈጠረው በማንበብ ብቻ አይደለም እየታከምነው ባለው መድኃኒቱን በተለማመደ ቲቢ የመድኃኒቶቹ አይነት ብዛት እና የግዜ እርዝማኔ እንመሳሰላለን ይባስ ብሎ ደግሞ የተለያየ ሀይማኖት ያላቸው የግቢው ታካሚዎች ያለምንም አድሎ ሙስሊሙ ለክርስቲያኑ በአል ክርስቲያኑም እንደዛው በተቃራኒው እኩል ያለውን አቅም በፈቀደ ገንዘብ ይጣና በጎደለው የዋርዱ የህክምና ባለሞያዎች አክለውበት ዳቦ ተቆርሶ ፈንዲሻው ተፈንድቶ ቡናው ተፈልቶ ለስላሳዎች ታድለው መነሳት ለማንችለው መኝታ ድረስ ሌሎች ለዚህ ተብሎ የተዘጋጀች የምትመስለው ግቢው መሀል ላይ ያለች ባለግማሽ ግድግዳ ነፋሻማ ጎጆ ውስጥ ሙዚቃ ተከፍቶ አልያም መንፈሳዊ መዝሙር መንዙማ ተለቆ ሲከበር አንድነትን መተሳሰብና መከባበርን በከፍተኛ ደረጃ ፈጥሮ የማይረሳ ትዝታዎችን ይሰጣል ቀን ላይ ፊዝዮቴራፒስት ታምራት ሐሪፍ አድርጎ ሰውነቴን ስላፍታታልኝ በጣሙን ቀሎኝ ሰመመን የሌለበት ሀይለኛ እንቅልፍ ወስዶኛል የተገላበጥኩ እንኳን አይመስለኝም በቀኝ ጎኔ እንደተኛሁ የሆነ ነገር እላዬ ላይ ዘፍ ብሎ ወደቀብኝ እንደመንሳቀስ ስል መላ አካሌ ላይ የሚከብድ የሚያቃስት ድምፅ ያለው ነገር ነበር የተሸከምኩት ደነገጥኩ ከመሸበሬ የተነሳ የገረጣ ሳንቃ ደረቴን በርጥቃ ለማውጣት ይመስል ልቤ በሀይል መታች አይኔን ብገልጥ ተሸፋፍኛለሁ እንደምንም ብርድ ልብሴን ከመግለጫ እላዬ ላይ የተኛው አብዱመሊክ የሰለለ እጁን ሰነዘረና ከአፍንጫዬ ላይ የኦክስጂን መተንፈሻውን በፍጥነት ነቀለ የሞት ሞቱን በሚታገል የታፈነ አተነፋፈስ በአነስተኛው የሚተነፍሰው አፍንጫው ውስጥ ከተተው አይን አይኔን ያያል መናገር አልቻለም እግሮቹ ወደ መሬት ተንጠልጥያለሁ በጀርባው በልብሶቼ በላይ እላዬ ላይ የመውደቅ ያህል ተኝቷል አይዞህ አብዱመሊክ ጠጋ አልኩለትና እጆቼን ሰንዝሬ የኃይል መቆጣጠሪያውን ወደ ቀኝ አዞርኩት ስድስት ቁጥር ላይ ተውኩት በሰከንዶች ውስጥ ወደ ቀድሞ አተነፋፈሱ ተመለሰ አንተ ወንድም ነው እኔ አለቀ አለኝ የእሱን ኦክስጂን በርሜል እያሳየኝ ገርሞኛል እኛም እንሁን ባለሙያዎቹ ጠንቃቆች ነበርን መቆጣጠርያ ጌጁን አይተን ከማለቁ በፊት እናስቀይራለን በተለይ ለሊት እንዳንጨርስ እንጠነቀቃለን ለነገሩ አጋጣሚው አስደነገጠን እንጂ ባለሞያዎች ሃያ አራት ሰዓት በተጠንቀቅ ይሰራሉ የሚገኙበት ዋርድ ግን እኛ ካለንበት ትንሽ ይርቃል አብዲን ካረጋጋሁት በኋላ ስልኬን አውጥቼ ለአንዱ ባለሙያ ደወልኩ አሁኑ እንመጣለን ተባልን ለተወሰኑ ደቂቃዎች እኔ መቆየት ችያለሁ አሁን ግን የሆነ ሰው አፍኖ አፍንጫዬን በእጁ ይዞ አልፎ አልፎ ለቀቅ ያዝ እያደረገ የሚያፍነኝ ስሜት አይነት ትንፋሼ ረዘም አጠር እያለ ተጨናነኩ ከጎኔ የተኛውን አብዲን መልከት አድርጌ ከአፍንጫው ነቀልኩና ለራሴ ሰካሁት እንደዚህ እንደዚህ እያደረግን ስንቀባበል የለሊት ተረኛው ሙሉ በአየር የተሞላ በርሜል እያንከባለለ ደረሰልኝ አሁንም ድረስ ሳስበው የመጀመሪያዎቹ መተንፈሻ የተቀባበልን ወዳጆች እኛ ነን ብዬ አምናለሁ የሚገርመው ሌላ ነገር አብዱመሊክ መኝታው ጋር መተንፈሻው ከተመቻቸለት በኋላ ከእኔ መኝታ ላይ ተነስቶ መሄድ ስላልቻለ የመጣው ባለሙያ አቅፎ ደግፎ ነበር የወሰደው መጀመሪያ ግን እኔ ላይ መቶ ሲወድቅብኝ የሞት ሞቱን ጉልበት አግኝቶ መራመድ ችሎ ነበር ከዚያች ሰዓት በኋላ ግን ልሞክር ቢል እንኳን አልቻለም ነበር ያቺ ጉልበት የት እንደጠፋች አልገባኝም በሰላሳዎቹ መግቢያ ላይ ይመስላል እድሜው የሆስፒታሉ ፊዝዮቴራፒስት ታምራት ቀጠን ያለ ሰውነት አጭር ከመባል ያለፈ ቁመት እስከ አሁን ሙሉ መልኩን ያላየሁት ሁሉም የሚያደርጉት አይነት ባክቴሪያውን አጣርቶ አየር ወደ ውስጥ የሚያስገባ ነጭ የአፍና የአፍንጫ መከላከያ ማስክ ያደርጋል እኛ ጋር ሲመጣ ማለት ነው ግንባሩና አይኑ አካባቢ ጠይም ቆዳውን በግልፅ ይታያል ጥርሱን ማየት ባይቻልም አይኑ ብቻ ማዘኑን መሳቁን ብሉም ማፅናናቱን ይችሉበታል ዛሬ የተለመደ አገልግሎቱን ሊሰጠን ሲመጣ ሶስተኛ ጊዜው ነው ይባስ ብሎ እንደ ጠያቂ ዘመድ የታሸገ የማንጎ ጭማቂ መኝታዬ አጠገብ አስቀምጦ ከወደድከው እጨምርልሃለሁ ብሎኝ ተመልሶ ወጣ ከደቂቃ በኋላ የነርሶች አስተባባሪ የነበረው ቢረጋ ወጻዲቅ ለስልጠና ላልተወሰነ ጊዜ ሌላ ቦታ በመሄዱ በጊዜያዊነት ተክቶት እየሰራ የነበረውን እዮብ ቀጠን ብሎ አጠር ያ የጤና ባለሙያ ይዞ ተመለሰ አመሰግናለሁ ተመችቶኛል ያመጣልኝን ጭማቂ እየተጎነጨሁ ነበር ጥሩ ነገ ሌላ ተጨማሪ አመጣልሃለሁ ለሙከራ ነው አንድ ብቻ ያመጣሁት ቅጣው በጣም ደስ ይላል እያዳንክ ነው ትንሹ የዋርዱ ኃላፊ እዮባ እያየኝ መነሳት አልተቻለም እንጂ ጥሩ ነው ያለሁት ለመራመድ ቸኩያለሁ አሁን ስለ አንተ አንድ አንድ ነገር ተነጋግረን ነበር ስለ ልጅህ ትቤትም አስበንበታል ዝም ብሎ አየኝ ታምራት ጭንቅላቴን ነቀነኩና ፊቴን ወደ መስኮቱ አዞርኩ ለማንኛውም ከስራ ባልደረቦቼ ባይጠቅምህም ትንሸ ገንዘብ አሰባስቤልሃለሁ ብሉ ከኪሱ እጁን ጨብጦ አወጣ ወደ እዮብ እየተመለከተ እዮባ እንግዲህ አንተም የቻልከውን ያህል አምጣ ብሎ እጁን ዘረጋለት ይቻላል ከራስህ ሙላና በኋላ ልስጥህ ካለው በኋላ ቆይ እንዲያውም ያዝ ብሎ ድፍን ባለ ብር ኖት እጁ ላይ አስቀመጠለት ል ቅጣው የተረጂነት ስሜት እንዳይሰማህ እኔም ሴት ልጅ አለችኝ ማድረግ ስለሚሜገኝ ብቻ ነው ያደረግነው የጨበጠው እጁ ላይ ብሩን አከለና ትራሴ ስር ከተተልኝ አመሰግናለሁ ወንድሞቼ አመሰግናለሁ ከባለፈው በበለጠ መንታ መንታ ሆኖ እንባዬ ተዘረገፈ ማልቀስ ምን አመጣው ተው ተው እባክህ ቅጣው እዮባ ጭንቅላቴን ማሻሸት ጀምሮአል አዝሄጃ እኮ አይደለም በቃ ደነቃችሁኝ አመሰግናለሁ ፈገግ ለማለት እየሞከርኩ የተደበላለቀ ስሜት ተሰምቶኝ እንባዬ ይረግፋል ለማንኛውም እራስህን በምግብ ገንባ በየቀኑ እከታተልሃለሁ በአጭር ጊዜ ለውጥህን ማየት እሻለሁ እዮባ ሲያወራ ጭንቅላቴን መዳበስ አላቆመም በየቀኑ እግሮችህን ከፍ ዝቅ እያደረክ አነስተኛ እንቅስቃሴ አስለምዳቸው ቀስ እያልክ ደግሞ ተነስተህ መቆም ተለማመድ ዛሬ ከቆምከው ደቂቃዎች በላይ ነገ እያሻሻልክ ቀጥል ጡንቻዎችህ እየዳበሩ ይሄዳሉ ለጊዜው በየጊዜው የኔ እርዳታ ላያስፈልግህ ይችላል ከአሁን በኋላ የማይመጣ መስሎኝ ከፋኝ እየተመላለስኩ አይሃለሁ ፊቴን ያነበው መሰለኝና ዘና ለማድረግ ሞከርኩ ነገሮች እስኪስተካከሉ ድረስ እኔና አንድ የስራ ባልደረባዬ በየወሩ በአንድነት ሶስት መቶ ብር ልንሰጥህ ቃል ገብተንልሃል ጉንጩን በፍቅር በመወደድ አይነት ቆንጠጥ አደረገኝ ከሚገባኝ በላይ ነው ያደረጋችሁት ይበዛብኛል በመልካምነታቸው አሸማቀውኛል ነገርንህን ቃል እንጠብቃለን አንተ ደግሞ እራስህን ለመንከባከብ አትቦዝን በርታ ጠንክር ያላሉኝ ነገር የለም ግዳጁን እንደተወጣ መንፈሱ የታደሰ ደስተኛ የሆነ መሰለኝ ተያይዘው ወደ ውጭ ሲወጡ ጀርባቸውን እያየሁ ያላብሰለሰልኩት ነገር የለም ከአይኔ ተሰወሩ ስጋ የናፈቀው ቀጥኖ የሠለለ ባለ አጥንት ግራ እጄን ወደ ትራሴ ስር ሰደድኩና ታምራት ያስቀመጠልኝ ገንዘብ ጨምደድ አድርጌ ይዢ ወጣሁ በሁለተኛው ቀኝ እጄ በመታገዝ ስንት እንደሆነ አየሁት ደነገጥኩ አይኖቼ ተከፍተው ቀሩ ፈጠጥኩ አለማመን መብታችሁ ነው እውነቱ ግን አስራ ሁለት ባለ አንድ መቶ ብሮች አንድ ሺህ ሁለት መቶ ብር አካባቢዬን ግራና ቀኝ ቃኘሁ አንድም ሰው እያየኝ አይደለም የትም የማንተዋወቅ ላለፉት ሶስት ቀናት ብቻ ያየሁት ታምራት አስደመመኝ ሲሰጡኝ ማንም እንዲያውቅላቸው አልፈለገም ያየም የለም በዘር በሃይማኖ ብሎም በማንነቴ ላይ ያነጣጠር ትብብር አልነበረም አስቀድሞ አላውቃቸው አያውቁኝም እንድድን መፈለጋቸው ተጨማሪ ትልቅ ጉልበት ሆነኝ ስላወኳቸው የታደልኩ መሰለች የልጄን እናት ለምለምን በተደጋጋሚ ደውዬ ብጠራት ልትመጣ አልቻለችም ስልክ ከምታነሳልኝ የማታነሳው ጊዜ ይበልጣል ልጄ ግን ትምህርቷን እንደቀጠለች አረጋግጫለሁ የትራስ ልብሴ ውስጥ የከተትኩትን ብር እየመዘዝኩ ያሻኝን ሞርተዴላ ቺዝ የዶሮ አሮስቶ ስላይስ ዳቦ እንዳትረሱ እያልኩ መላክ ጀመርኩ አመጋገቤ መረን የለቀቀ መሠለኝ አሻምደዋለሁ የታሸገ የፕላስቲክ ውሃ ሚሪንዳ ቪምቶ ጭማቂዎች አጠገቤ ደርድሬ ድራሻቸው እስኪጠፋ መጠጣት ተያያዝኩ ለሚላላኩልኝ ጉርሻ መስጠት ችያለሁ ሠገራዬ ለስላሳ ሆኖ በቀን አንዴ በርከት አድርጌ እፀዳዳለሁ ፈሳሽም ስለማበዛ ሽንቴ መጠኑ ጨምሮአል ቢሆንም ግን የሚደፋና ፖፖዬን አለቅልቆ የሚያመጣልኝ አላጣም የምከፍለው በርካታ ባለ አስር ብር ኖቶች ምስጋና ይድረሳቸው የወቅቱ የነርሶች ኃላፊ ትንሹ እዮብ በቀን ሶስት ጊዜ ያየኛል በየእለቱ ተጨማሪ አጋዥ ምግብ የለውዝ ቅቤ ፕላንፕኔት ይዞልኝ ይመጣል በቀን አራት መመገቤን ያረጋግጣል በየእለቱ ምሽት ላይ የኛ ክፍል ትደምቃለች ሜሮን ገበየሁ እኔ መኝታ ላይ ራህማ ዝናብ ሠሙ ጋር እና ሌሎችም በርከት ብለው ለሁለት ይከፍሉና የሜሪ ክፍል ለእኔ የራህማ ደግሞ ለአብዱመሊክ በመወገን አንደተኛን ታምራት የሰጠንን ስፖርት በውድድር እናቀርባለን ሁለቱን እግሮቻችንን በመጀመሪያ በየተራ ሲቀጥል በጥንድ ወደ ላይ በአየር ላይ ማቆየት አንድ ሁለት ሶስት የቆጠርልንና እኩል እናነሳለን ሰሙ ሁልጊዜ ዳኛ ነው በአየር ላይ የምናቆየውን ጊዜ ሰዓት ይይዝልናል የየእለት ለውጣችንን እናመዛዝናለን አብዛኛውን ጊዜ እኔ ነበርኩ የማሸንፈው ሞራልና ጭብጨባው ግን ለሁለታችንም እኩል ነበር ሲቀጥል ረዥም ጊዜ መቆም መወዳደር ጀመርን እዮብ ወማርያም በዘፈን ሌሎች ደግሞ ስም በመጥራት ቅጣው ቅጣው በሌላኛው ፅንፍ አብዲ አብዲ አሸነፈ አሸነፈ እያሉ ያጨበጭባሉ በሞራልና በእልህ እኔም አብዲ አልጋ ድረስ መሄድ ጀመርኩ እሱም እኔ ድረስ ይራመድና ተቃቅፈን ትከሻ ለትከሻ መገጫጨት ጀመርን እኩል እየተጠራራን ያለንን እየተካፈልን መመገብ ጀመርን ፍቅራችን ከጣራው በላይ ሆነ ከእንቅልፉ እንደነቃሁ አይኔ መጀመሪያ እሱን ነው የሚፈልጉት አብዱመሊክም እንደዛው በመተያየት ብቻ በጥልቀት እንግባባለን መጫወትም ሲያስፈልግ የሆድ የሆዳችንን እናወራለን አብዱመሊክ የወደፊት አላማው ሰፊ ነው ቢሆንም ግን አሁን ለጊዜው እያሰበ ያለው እየተሸለው በመሆኑና በቅርቡ በአውሮፕላን ወደ ልጆቹና እናቱ ጋር ጅግጅጋ እንደሚሄድ ብሎም ህክምናውን እዛው እንደሚጨርስ እያለመ ነው ቤተሰቡን እንደሚያስተዋውቀኝ የእኔንም ልጅ ማየት እንደሚፈልግ መቼም እንደማንለያይ እየተማማልን በመተሳሰብና በደስታ ነበር ቀናቶችን የምናሳልፈው አብዱመሊክ ያለፉትን ሁለት ቀናት ከመተያየት በዘለለ ሊያናግረኝ አልሞከረም በፀጥታ ነው ያሳለፈው የሚወደውን ሻሂ ሳይቀምስ ውሎ አድሮአል ምግብ በአፉ አልዞረም ስፖርቱንም ትቶታል የፖታሺየም እጥረት አጋጥሞሃል የኤሌክትሮላይት የላብራቶሪ ውጤትህ የሚያሳየው ይኹው ነው ተብሎ በደም ስሩ ጉሉኮስ ተደርጎለታል በውስጡ የተደረገለት እጥረቱን የሚሜተካለት መድኃኒት ከዚህ በፊት የወሰዱት እንደሚናገሩት በደም ውስጥ ሲገባ የማቃጠል ያህል ይቆጠቁጣል አብዲም ይኹን ስሜት ማስተናገድ ስላልፈለገ ይበቃኛል ብሎ ከእጁ ላይ ገንጥሉ ጥሎታል ቢመከር ቢለመን አልሰማም ብሎአል የጠዋቱን መርፌ እየተነጫነጨ ይወጋል ቀኑን ሙሉ ተጠቅልሎ ማሳለፍ ጀምሮአል ሁለተኛ ለሊቱንም እንደዛው እኔ ጥሩ የጤንነት ስሜት እየተሰማኝ ይመስላል ምሽት ላይ የሞቀ ውሃ አስመጥቼ በፎጣ መአዛው የሚያምር መታጠቢያ ሳሙና በመጠቀም ፀጉሬን ፊቴን ብሎም እጅና እግሬ ታጥቤያለሁ እንዳትጠራጠሩ ሌላ አካሌን ቀርቶ ፊቴን አልያም እጄን ውሃ ከነካው ስድስት ወራት አስቆጥሬያለሁ እጅግ በጣም ቀሉኛል ታምራት ያመጣልኝን ፈሳሽ ቅባት ያልተቀባሁት ቦታ የለም መላ አካሌ ያብረቀርቃል የጎፈረ ፀጉሬን በብሩሽ ማበጠሪያ ወደኋላ ልጌ አስተኝቼዋለሁ ደሜንም እንደዛው በዚህ ወቅት ህክምናችንን የሚከታተለው ዶር ሙሪድ በሰላሳዎቹ መጀመሪያ አካባቢ ይገመታል ታካሚውን ሊያናግርና ሊያፅናና ሲፈልግ በጉብኝት ሰዓት ሊሆን ይችላል አንድ እግሩን ጠልጠል ያደርግና በእግርጌ በኩል ጎን የታካሚው መኝታ ላይ ተቀምጦ እግሮቻችንን ተደግፎ የቅርብ የቤተሰብ ያህል ስሜት ፈጥሮብህ ነው የሚያዋራው ቅጣው ተውት በቃ አትቀስቅሱት ብሎ ፊቱን አዙሮ ወደ ቀጣይ አልጋ ሊሄድ ሲል አቤት ዶር ከተሸፋፈንኩበት ተገለጥኩ እኔ አላምንም ኑ ተመልከቱ ቅጣው ዳነ በቃ እዩት እንዴት እንዳማረበት እጁን ቡጢ ጨብጦ ግባልኝ አለኝ እየተፍነከነኩ ቦክስ ጨብጩ ከእጁ አጋጨሁ ዘረጋልኝ ዘረጋሁለት አፈፍ አድርጎ ትከሻውን ከትከሻዬ አጋጩጨ ፀጉርህ ደግሞ እንደዚህ ያምራል ለካ በቃ አንተ ድነሃል አምልጠሃል ጮቤ የመርገጥ ያህል እየተደሰተ ወጣ ላለፉት ረዥም አመታት ሊቆጠሩ ቀርቶ ለማስታወስ እንኳን የሚበዙ አያሌ መልካም ነገሮችን አብሬያቸው ያሳለፍኩ ሰዎች የቤሰቤን አባላት ጨምሮ ሁሉም ታምመሜ ስተኛ አብዛኛዎቹ የቲቢ በትንፋሽ መተላለፍ አስፈርቶአቸው ሲርቁኝ ሲሸሹኝ የራሴ ሰው የምለው በናፈቀኝ ጊዜ በህክምና ባለሞያዎቹ እንዲህ ሲበዛ በማላውቀው የስሜት አይነት ልሰክር ተቃርቤያለሁ የዶር ሙራድ ሁኔታ አቅበዝብዞኛል ሲደነቅ ሲደሰት የነበረው ለለበጣ ከአንደበቱ ብቻ እንዳልነበር መላ አካላቱ ይመሰክር ነበር ዘለል ዘለል ካለ አረማመዱ ጀምሮ ግራ ቀኝ መወራጨቱ እጄን መግጨቱ አስተቃቀፉ ደስታ ከተላበሱ አይኖቹ ጋር ተደምሮ የምይዘው የምጨብጠው አጥቼያለሁ አሁን የምነግራችሁን ያለ ማመን መፍትሄው ማመን ብቻ ነው ተስፈንጥሬ ከመኝታዬ ተነሳሁ ባለ አራት እግር መደገፍያ መንቀሳቀሻ ክራንች አስመጣሁና ቆምኩ መራመጃዬን ወደፊት እየገፋሁ ገሰገስኩ በአንድ ሜትር ከሰባ ስምንት ቁመቴ በቀጭን ሰውነቴ እየተንጎማለልኩ ወደ ውጭ መተላለፊያ በረንዳው ላይ ወጣሁ ግቢው ውስጥ በተለያየ ስፍራ ጥንድ ጥንድ ሆነው የየግል ወሬያቸውን የያዙ በቲቪ ክፍል ውስጥ ፊልም እያዩ የነበሩ በሙሉ በጭብጨባ አቀለጡት አንድ እጄን ወደ ላይ አንስቼ ከአንገቴ በመጠኑ ዝቅ አልኩ ውስጤ ግን በእድሜዬ ውስጥ ተሰምቶኝ የማያውቅ የሚፍለቀለቅ ደስታ ተረጭቶአል በየክፍላቸው ያሉት ምን እንደተፈጠረ ለማረጋገጥ ወጡ እዮብ ወማርያም ያለፉትን ሁለት ቀናት ታሞአል እግሩና እጁ አልታዘዝ እያለሁ እንደሆነ ሰምቼያለሁ ዛሬ ግን ቀኝ እጁን አጥፎ ደረቱ ላይ ለጥፎታል ማንቀሳቀስ እንደማይችል ያስታውቃል የቀኝ እግሩም ወጥሮ ተገታትሮአል በዘገምተኛ ሁኔታ እየጎተተው በመራመድ እኔ ጋር ለመድረስ ስድስት ሜትር ሲቀረው ቆመ ግራ እጁን አፍ ላይ ደቀነና ማንጎራጎር ጀመረ የሚያደርግም ሆነ ወይ የሚረዳህ እ እያለህ ካልሆነ ከሌለህ የለህም ሁሉም ወዳለው ነው ወደድክም ጠላህም ያንተ ነገር ሞቷል ከሌለህ የለህም አጭሩ ይረዝማል ቅርቡ ይርቃሀል እወቀው ከሌለህ ሳያምህ ያምሀል መቼም ሙዚቃና ዜማ ስሜት አይሰጡኝም እጠላለሁ ማለቴ አይደለም አንድ ዘፈን መልዕክቱ ከገባኝ በኃላ በመደጋገም ስፍር ቁጥር ለሌለው ጊዜና ዘመናት ማደመጥ ብሎም አብሮ መለፍለፍ ለኔ ሞኝነት ነው የሆነ የሙዚቃ ክሊፕ በስክሪን ላይ ስመለከት ግራ ቀኝ እየተወራጩ የሚያጅቡትንም ይሁን ድምፃዊው ሲውረገረግ የሙዚቃውን ድምፅ አጥፍቼ በዝምታ ማየት ስሜት ይሰጠኛል ጤና አተው የሚወራጪ ነው የሚመስለኝ ስለዳንስ ምንም እውቀት ስለሌለኝ ይሆናል ከአመታት በፊት በወጣትነቴ ማሳደጊያ ውስጥ እያለው በዘፈን ምርጫ የራድዮ ፕሮግራም አንድ ጋዜጠኛ ሙዚቃ ስሜት የማይሰጠውን ሰው ከዝንጀሮ ለይተን አናየውም ያላት አረፍተ ነገር እንድታዘበው አድርጎኛል በወቅቱ እራሴን ተጠራጥሬ ነበር መልሴ ግን ያው ነበር ሙዚቃ ለኔ ትርጉም አልባ ነው አሁን ግን የእዮብ ወ ማርያምን ድምፅ ስሰማ መነቃቃት ጀምሬያለሁ በጣም እየወደድኩት እንደሆነ ተሰምቶኛል ለወደፊቱ የሱ ኮንሰርት የመጀመሪያዬ መድረክ ይሆናል ብዬ አልሜያለው ድገምልኝ አልኩት እዮባ ማንጎራጎሩን ቀጠለ ሁሉም በታላቅ አክብሮት አጨበጨቡ ሴቶቹ መጡ ደስታቸውን ገለፁልኝ ወደነሱ ክፍል እንድመጣ ቡናም ተፈላ ጋበዙኝ እኔ ግን ደስታው አሰከረኝ እንጂ እየደከመኝ ነበር መንቀሳቀሻዬን እየገፋሁ ወደ መኝታዬ አመራሁ አምሮብሃል አምሮብሃል ስለበዛብኝ የመልክ መስታወት አስመጥቼ ፊቴን ከስምንት ወራት በኋላ አየሁት ቢያንስ በቀን አንዴ ሳየው የነበረው ቅጣው ናፍቆኝ ነበር ፀጉር አበጣጠሬና የሜ ማደግ ተመቸኝ አዲሱ ስታይሌ እንደሆነ ተሰማ የፀሐይ ብርሃን ቀርቶ ውጭውን ካየሁ ጊዜያት ስላሳለፍኩ ቀዮ የመባል ደረጃ ላይ ደርሻለሁ ቢጫ ነጭ ነገር ሆኖአል ፊቴ የፈለጋችሁት ብትሉ ማመን ግን ግዴታችሁ ነው ከወራት በኋላ እየተራመድኩ ወደ ውጭ ወጣሁ አልኳችሁ እውነት ነው የምሽት ተረኛው ዶር ተጠርቶ መቷል ሁለት ወንድ ነርሶች አጠገቡ አሉ እንስቷ ወደ ውጭ ወደ ውስጥ ትሯሯጣለች አብዱመሊክ የማጓራት ያህል በከፍተኛ ዕጩኸት ያሰማል መንፈራገጡ ከባድ ነበር ኦክስጂኑን እየነቀለ ነው እባካችሁ ገመድ አምጦልኝ ዶር እየተቻኮለ ያወራል ይቻላል በፍጥነት እመጣለሁ ሴቷ ነርስ ወጣች እግሮቹን ጠበቅ አድርገህ ያዝልኝ ሁለቱ ነርሶች በመተባበር እንዳይንቀሳቀስ ያዙት አምጣ ካኖላውን አቀብለኝ ዶሩ እራሱ የአብዱመሊክ እጅ ላይ መታ መታ በማድረግ የጉሉኮስ ማስተላለፊያ ካኖላውን በትክክለኛ ቦታ ካስገባ በኋላ ግራና ቀኝ ነጫጭ ፕላስተሮችን ከለጠፉ በኋላ ሲለቁት ባለ በሌለ ኃይሉ መወራጨት ጀመረ እንደገና ተረባርበው ያዙት ነርሷ ይዞ በመጣችው የተጠቀለለ ፋሻ እየተረተሩ ሁለት እጆቹን ግራና ቀኝ እግሩን ከእግርጌው ጋር ዘረጋግተው ከአልጋው ጋር አሰሩት የተጨመረበትን ጉሉኮስ አንጠልጥለው በከፍተኛ ፍጥነት ሰጡት ዶር ባዘዘው መሰረት ወንዱ ነርስ አንድ መርፌ በታፋው ላይ ሰጠው ታከለ ተሾመ ያለወትሮው የሰሙ አልጋ ላይ ጎን ለጎን ተቀምጠው ፈዘዋል አበራ ፀሐዬ አይኖቹን ጨፍኖ ሁለት እጆቹን ወደ ሰማይ ዘርግቷል አምላኩን በፀሎት እየለመነ እንደሆነ ገመትኩ እኔ በተኛሁበት ፈጥቻለሁ ፀጥታው ከመጠን ባለፈ ክፍላችን ነግሶአል አብዲ አንገቱን ብቻ ግራ ቀኝ ያወዛውዛል ሁለት ጊዜ አይን ለአይን ተጋጭተን ትኩር ብሎ ሲያየኝ ስሜቴ ተደበላልቆብኝ ወደ እሱ ማየት አቁሜያለሁ መርፌውን ከተወጋ በትንሽ ደቂቃዎች ውስጥ ማጓራት መጮህ አቁሟአል ነገሮች ግን እንዳሉ አልቀጠሉም ሁላችንም በየመኝታችን ላይ ተጋደምን ቢሆንም የህክምና ባለሞያዎቹ ለደቂቃ እንኳ ሳያርፉ እየተመላለሱ ያዩታል ሰአቶች እየነጎዱ ከሄዱ በኋላ ግን ቁጥራቸውን በርከት አድርገው ሶስቱም ነርሶች ተሰበሰቡ በፍጥነት ዶሩ እንዲጠራ ተደረገ አንደኛው ደረቱ ላይ በሁለት እጆቹ የያዛቸውን ነገሮች እያስነካ የአብዱመሊክ ሰውነት እንደመንጠር ብሎ ሲመለስ እየቆጠረ በመደጋገም ሌላኛው ነርስ በአየር የተሞላ የሚመስል ጠጣር ፊኛ መሳይ ነገር የአብዲ አፍና አፍንጫ ላይ እየገጠመ እየነፋ በመመላለስ ያላለሰለሰ ጥረት አደረጉ ተሯሯጡ ታገሉ ግን አልተቻለም አብዱሜልክ ሞተ ቤተሰቡ ጋር ሊመለስ እኔንም ሊያስተዋውቀኝ ልንለያይ ላንከዳዳ ቃል ስንግባባ የነበረው ጓዴ ከዳኝ መልሶ ላያናግረኝ ጨክኖ አጠገቤ ሆኖ ሳይሰናበተኝ ለዘላለሙ ተለየኝ ያን ሁሉ መርፌ መወጋቱ የኪኒኖቹ ብዛት ዋጋ ሳይኖራቸው እሩቅ ሲያስብ የነበረው የሶስት ቋንቋ ተናጋሪው የፊዚክስ ሊቁ አብዱመሊክ ሞተ የጤና ባለሞያዎቹ በየክፍሉ በጋራም ይሁን በየአልጋችን በየግል በተናጥል ሲያፅናኑን እንዳንረበሸሽ ሲሞክሩ ተስፋ አንዳንቆርጥ ሲሞክሩ ነው የዋሉት የአንዳቸውንም ቃል ግን አልሰማሁም ቅስሜ ተሰብሮአል ለደቂቃዎች አይደለም ለሰከንድ እንኳን ለሽንትም ቢሆን ሳይየኝ በእንቅልፍ ሰዓት ብቻ ሳንተያይ ለረዥም ወራት አብሮኝ ያሳለፈው ጓዴን ነው ያጣሁት ምሽት ላይ ሴቶቹ እኛ ክፍል ተሰብስበው ቡና ተፈልቶ እርስ በእርሳችን መፅናናት ጀምረናል እዚህ ግቢ ከገባሁ ሠሞኑን ሞት በዛ ምንድን ነው ጉዱ ራህማ ዝናብ ነች መሬት እያየች ባለፈው የ ዓመት ሽማግሌው የወሰኔ አባት ሞቱ እሳቸውስ እሺ እድሜም አለ መድኃኒቱ ደግሞ መቋቋም አይችሉም በዛ ላይ ስኳር ነበረባቸው እነኝህ ከወህኒ ቤት የመቱት ሁለቱ ጎልማሶችስ በተከታታይ አይደል የሞቱት የቲቢ ባክቴርያ ከሚተላለፍባቸው ቦታዎች ዋንኛው ሰዎች ንፁህ አየር እንደልብ የማይዘዋወርበት ቦታ ተሰብስበው ሲገኙ ነው ከዚህም ውስጥ የማህበራዊ አገልግሎት በአንድነት የሚሰጥባቸው የህፃናት ማሳደጊያ አዳሪ ትምህርት ቤቶች አረጋውያን ሰብስቦ ማቆያ ስፍራ የዕምነት ቦታዎች ከአነስተኛ እስከ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እንዲሁም እስር ቤቶች ነው በቅርብ ጊዜ በግቢያችን የሞቱት በርካታ ሰዎች ከሚታሰሩበት አንድ ክፍል የነበሩ ናቸው ሌላኛው የስምንት አመት ፍርደኛ የነበረው ታምራት አብሮአቸው አንድ ቤት ነበር የታሰረው እዚያው እያለ በዚሁ በሽታ ታሞ ህክምናውን በጀመረ በሰባተኛ ወሩ ፍርዱን ጨርሶ ቀጣይ የሚታከምበትን ጊዜ ለመጨረስ እዚህ ሆስፒታል መጥቶ እኔ አጠገብ ያለው ባለ ስድስት አልጋ ክፍል ውስጥ አንዱ አልጋ ላይ ተኝቶአል ለአመታት አብረውት የነበሩት የእስር ቤት ጓደኞቹ ግን በቅርቡ ሞተዋል መቼም ጉድና መከራ ሲመጣ አከታትሎ ነው ለዚህ መፅናኛ አንዳንዶች ሊነጋ ሲል ይጨልማል ሲባባሉ ለዘመናት ሰምቻለሁ እንዲያውም ነገር ሁሉ ለበጎ ነው ይላሉ እንዲህም አርጎ መልካም ብሎም በጎ ያለ አልመሰለኝም እስቲ እናንተው ፍረዱ ዝምተኛው ታከለ ተሾመ በጠና ታሞአል በእኔ እና በእሱ መሀል ይተኛል የነበረው አብዱመሊክ ከሞተ ቀናት ነው የተቆጠሩት መኝታው ቦታ ነው ተሻግሮ ሌላኛው ጥግ ላይ ታከለ ተሾመ እግሮቹን ዘረጋግቶ ተወጣጥሮአል አንድ እጁን እጥፍ አድርጎ በጀርባው እንደተኛ ደርቆአል አፉ በመጠኑ እንደተከፈተ ቀርቶአል የአይኑ ብሌን ብቻ ከግራ ወደ ቀኝ ይንቀዋለላሉ ለሜጠየቀው ጥያቄ አንገቱን ብቻ በአዎንታና በአሉታ እየወዘወዘ መልስ ይሰጣል የትኛውም ሰውነቱ መንቀሳቀስ አይችልም በቃ አበቃለት አልኩ ደንግጦናል ሐኪሞቹ ከበውታል በሀያዎቹ መጨረሻ አካባቢ ይሆናል ሴቷ ዶክተር ከሁለት ነርሶች ጋር ታከለ የምልህ ይሰማሃል የህክምና መዝገቡን እየገለጠች ታከለ ተሾመ አፉን ከፈት አድርጎ እንደደረቀ የአይኑን ሸፋሽፍት ብቻ ቀና ቀና በማድረግ አዎ እየሰማሁሽ ነው በሚል አይነት መልስ ሠጠ የዕለቱን በወቅቱ የተመዘገቡትን የምርመራ ውጤቶች ማየት ቀጥላለች የደም ግፊት ፐልስ የሠውነት ሙቀት ኦክስጂን በጥሩ ደረጃ ላይ ነው ያለው የሲቢሲ ውጤቶቹም የተስተካከሉ እንደሆኑ በደም ምርመራ የላብራቶሪ መልሶች ያሳያሌ የኤሌክትሮላይት የደም ናሙናው ውጤት ፖታሽየም ማግፒዥየም ካልሽየም ጠዐሀ አሁን እጥረት አለ መሆን የነበረበት ነው ትክክል ብዙውን ጊዜ መድኃኒቱን በተለማመደ ቲቢ ህክምና ላይ ያሉ ህሙማን ከሚወስዷቸው መድኃሂቶች በተለይ ካፕሮማይሲን የተባለው መርፌ ይኹን እጥረት ያስከትላል ዶር አሁን እርግጠኛ ሆናለች ስለሆነም በተከታታይ መድኃኒ ሊሰጠው ይገባል ብላለች መዝገቡ ላይ ጫር ጫር አድረገች በደም ስር በሚሰጥ ጉሉኮስ ውስጥ በየ ሰዓቱ የሚጨመርለትን መድኃኒት መጠን ከተበች ለዛሬው ግን በአስቸኳይ ግማሽ የሚሆን አምስት መቶ ሚሊ ጉሉኮስ አስመጣችና መጥና ቀምራ የወሰነችውን ያህል መድኃኒት በመርፌ ወግታ ከተተችበት ቀመመችው አሁን ይሻልሃል በርታ ተከታተሉት ካስፈለኳችሁ ጥሩኝ ብላ ወደ ኋላ እኛን እንኳን ሳታይ ውልቅ ብላ ወጣች በጣም ተረብሸናል አብዲን አጣነው አሁን ደግሞ ታከለ ተሾመ በአስደንጋጭ ደረጃ ላይ ነው እኔ እንደሆንኩ ከባዶ አልጋ አሻግሬ የተገታተረውን አይኑ ፈጦ አፉን ከፈት ያደረገውን የወራት የአይኔን ጓደኛ ማየት አልቻልኩም እንዳፈጠጥኩ ጣራ ጣራውን እያየሁ ነው ሰሙ ከፊት ለፊት ሠበር አድርጎ እያየው ፊቱን ያዞራል አበራ ፀኸዬ በየእለቱ የስኳር መጠኑ እየታየ የኩላሊቱም ሁኔታ በየጊዜው እየተመረመረ ስለሆነ መድኃኒቶቹ የሚስተካከሉበት የግድ ሆስፒታሉ ውስጥ መቆየት አለበት እንጂ ከእስር ቤት የመጡት ብሎም አብዱመሊክ ሲሞቱ ወደ ቤቱ ለመሄድ አሰፍስፏል ተቁነጥንጧልም ግን ሌላም ችግር አለ በሀኪሞች እስካልተወሰነ ድረስ ቤት ላሉት ቤተሰቦቹም ቲቢውን ሊያስተላልፍባቸው ይችላል ሰከንዱ ደቂቃ ደቂቃው ሰአት እየሆኑ የኤሊን ያህል እየተንቀራፈፉ በዝግታ ጊዜዎች መሄድ ይዘዋል ከአንድ ሰዓት ተኩል ቆይታ በኋላ ይመስላል ሐይለኛ ትንፋሽ ኡፍ ፍ እና የመንኳኳት ድምፅ ከታከለ ተሾመ አልጋ አካባቢ ሰማሁና ዞር ስል አይኔን ማመን አልቻልኩም ታኬ ቆሞአል እያለቀ ያለውን የጉሉኮስ እቃ ከተንጠለጠለበት ብረት ሲያወርድ ነበር የተንኳኳው ታኬ እንዴት ነህ ራህማ ዝናብ በር ላይ ቆማ እያየችው ነበር ሞቼ ነበር አይደል የታከለዬን ድምፅ ሰማን አሁን ወዴት ነው እረፍት አድርግ እንጂ ራህማ እየተጠጋችው ጣም ደህና ነኝ ሽንት ቤት መሄድ አለብኝ ጉሉኮሱን ዘግቶ በአንድ እጁ ይዞታል ቆይ ትንሽ ተረጋጋ እንዲቀመጥ እየጋበዘችው ተአምር ነው ይኸው እጄም እግሬም ተፍታታ እኮ መገረሙ ያስታውቅበታል እንዴት ነበር ያደረገህ። ውሸታሞች ናቸው አንድ ሁለት ቢራ እንጂ ጠጅ አልጠጣም ለዚህ ነዋ ሜንት ከረሜላ ሁልጊዜ ኪስህ የማይጠፋው አንድ አንድ ይሰጠኝ እንደነበር በውስጤ እያሰብኩ ነበር ከረሜላና ቢራ ምን አገናኘው አፍህ እንዳይሸተን ነዋ አፍና አፍንጫችንን በማስክ ሸፍነን ሀኪሞቹ ለዛውም በወፍራሙ ተሸፋፍነው ማነው እስቲ እዚህ ግቢ አፍንጫውንና አፉን ገልጦ ያየኸው ማሽተት እኮ ማንም አይችልም የጎጎዳህ መድኃኒቱ ከመጠጥ ጋር የማይሆን ነገር ነው የሠራኸው አሁንም ትጠጣ ይሆናል አሁንማ መውጣትም እግሬን እየጎተትኩ አልሄድም በቃኝ ደግሞ እንደምታየው በጣም ተጎዳሁ አይዞህ አሁንም አልረፈደም ሐኪሞችህን ለማ የምትባለውን አድርግ አሁንማ ተወው ገና ስንት አላማ እንዳኝ ማንም ያቃል እሱን አሳካለሁ እኔ የወማርያም ልጅ እሺ ነገ ለእንግዶቹ የማቀርበው ወሬ እያዘጋጀሁ ስለሆነ ምን ልበልልህ እኔ እዘፍንላቸዋለሁ ተዘጋጅቻለሁ አመሰግናለሁ በርታ እዮባ ተሰናብቼው ወደ መኝታዬ አመራሁ ሌሎቹም ያሉኝ ተመሳሳይ ነገር ስሆነ ሀሳቦቹን ቀምሬ የራሴንም አክዬበት አንድ ገፅ ፃፍኩኝ የኦክስጂኔን መቆጣጠርያ ሁለት ቁጥር ላይ አድርጌ ለሽ የሰላም እንቅልፍ የድካም ድካሜን ተኛሁ የአስራ ሁለት አመቷ ታዳጊ ታካሚ ብሶቷን በግጥም ልታቀርብ ተሰናድታለች ተፈጥሮ ለስዕል ያደለችው የአምቦ ዩኒቨርስቲ ሁለተኛ ዓመት ተማሪ የሆነው ዳዊት ድባቡ የፊት መሸፈኛ ማስክ ያደረጉ ሶስት ሰዎችን በተናጥል አሳምሮ ስሎ ማስክ ሳያደርጉ መግባት ክልክል ነው የሚል መመርያን ፅፎባቸው የዋርዳችን መግቢያ በር ላይ ሰቅሏል ሌሎች ታካሚዎች ከህክምና ባለሞያዎቹ ጋር በመሆን በተለያዩ ቀለማት ያሸበረቁ ባለሶስት ማዕዘን ጨርቆችን በየቦታው በገመድ ወጥረው አሸብርቀውታል አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ አላማችን በሚገባቸው ቦታ ላይ ቀልብን በሚስብ ግርማ ሞገሳቸው ይውለበለባሉ በመጠናቸው ትላልቅ በቀለማቸው የተለያዩ በርካታ ፊኛዎች ተሰቅለዋል በተለየ መልኩ እምር ድምቅ ብሎአል ጊቢያችን ልነግራችሁ ሳልችል ባልፍ የሚቆጨኝ ምን መሰላችሁ በህይወት ዘመኔ የተለያዩ የአገራችን አካባቢና ተቋም እንደሚደረገው የበላዮቻችን አልያም ኃላፊዎቻችን ይመጣሉ በሚሜል ሠበብ ከወትሮ የተለየ ምንም አይነት ፅዳት አልተደረገም ግድግዳና ኮርኒስ ሳይቀር መጥረግ ሙሉ ግቢውን ማንፃት የየእለት ተግባር ስለሆነ ማንም በማንኛውም ጊዜ ቢመጣ የሚማረክበት ከቆሻሻ የፀዳ ቦታ ነው አዲስ የመጣ ታካሚ በስህተት ያገኘበት ቦታ ሲተፋ ከታየ ቤተ ክርስቲያን የገባች ውሻ ነው የሚያደርጉት አፍና አፍንጫውን በማስክ አልያም በክንዱ ሸፍኖ ካላሰላ ወይ ካላስነጠነሰ እንደዛው ይጮህበታል በየአቅጫው ቁጣዎች ይፈሱበታል ባክቴሪያህን የትም አትትፋ በየቦታው እያሳሉ ነው ጉድ የሠሩን አፍህን ሸፍን ሌላም ሌላም ይባላል በንጋታው ይኸው ሰው ይቀላቀላቸውና እሱም ሌሎቹን መከልከል ይጀምራል በቃ የማይተፋበት በየቦታው ቆሻሻ የማይጣልበት ጠንካራ ፅዳት ሠራተኞች ያሉበት ንፁህ ክልል ነው ወተታችንን ጨልጠን ከተረጋጋን በኋላ ምሳችንን አስተናግደን እኔም ትንሽ ደካክሞኝ ስለነበር ከመኝታዬ ሳልነሳ እንደተንጋለልኩ እንግዶች ገብተው የተዘጋጀላቸው የላይኛው መኝታ ክፍሎች በረንዳ ላይ በተደረደረላቸው ወንበር ላይ ተቀምጠዋል ታካሚሜዎች በተለያየ ቦታ ተሰባጥረው አረንጓዴ መተንፈሻ ማስካቸው አድርገው ተቀምጠዋል በሁለቱ መካከል ሰባት የሚሆኑ ሌሎች አይቻቸው የማላውቅ እንግዶች እንደሆኑ በነጩ ማስካቸው የገመትኩት በተለያየ እድሜ ላይ የሚገኙ ሁለት ሴቶችና አምስት ወንዶች ተቀምጠዋል ሲስተር አይናም የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ካስተላለፈች በኋላ ስለሚቀርቡት ዝግጅቶች በመጠኑ ከገለፀች በኋላ ከዚህ በፊት በዚህ ቦታ ህክምናቸውን ሲከታተሉ የነበሩ ወገኖች የሰሯቸውን ጌጣ ጌጥ የእንጨት ቅርፃ ቅርፅ ስራዎች በእጅ የተሳሉ ስራዎች ለአይን በሚማርክ መልኩ መልኩ በእጅ ሥራ ዳንቴል የተበጃጁ ነጫጭ እርግቦች በተፋጩ ወረቀት በኮነ ተቦክቶ ለሞዴልነት የሚሆን አምሮ የተገነባ ቪላ ቤት ከነሙሉ ግቢው አረንጓዴ ስፍራን ጨምሮ ጣራው ላይ የሳተላይት መቀበያ ሳህን ዲሽ የተገጠመለት ኢንጂነር እያልን የምንጠራው በአሁኑ ሰዓት በመልካም ጤንነት ላይ የሚገኘው የግንባታ ምህንድስና ትምህርቱን አቋርጦ በህክምና ላይ በነበረበት ጊዜ የሠራው እንዲሁም ያለፉትን አመታት ዝግጅቶች የሚያሳይ የፎቶ ግራፍ አውደ ርዕይ የክብር እንግዶቹ በቂ ማብራሪያ እየተደረገላቸው ለሚጠይቁት ጥያቄ መልስ ከተሰጣቸው በኋላ በታላቅ አክብሮት በጭብጨባ ወደ ቦታቸው ተመልሰው ተቀምጠዋል ሲስተር አይኒ በመቀጠል መሀል የተቀመጡትን ሰባት የማላውቃቸው ሰዎች እየጠቆመች አሁን እነፒህ ከዚህ በፊት በዚህ ቦታ ለረዥም ጊዜ ህክምና ሲከታተሉ የነበሩ አሁን ግን የዳኑ ወገኖቻችን እዚህ ላላችሁት መዳን እንደሚቻልና ሞራል ጉልበት ይሆናችሁ ዘንድ ያለፈ የህይወት ተሞክሮአቸውን ያቀርቡልናል ቢሆንም ግን ወደ እነሱ ከመሄዳችን በፊት ከዚህ በፊት በቲቢ ምክንያት ህይወታቸውን ላጡ ወገኖች የህሊና ፀሎት እናደርጋለን ስትል ሁሉም ከተቀመጠበት ተነሳ እንደተለመደው ግራና ቀኝ እጆቻችን በማቆላለፍ አልያም ደረቶቻችን ላይ ለጥፈን አንገት ዘንበል አድርገን ዝም ተባባልን እኔ ግን አይኔን በልጥጩ ከፍቼ አካባቢዬ እያየሁ ነበር ምንም የማታውቅ ጨቅላ ሀፃን እናቷ ጀርባ ላይ ሆና ቢገባትም ባይገባትም ለታላቅ እህቷ ሞት እሪ ብላ ከእናቷ ጋር ስታለቅስ አይቻለሁ ከወህሂ ቤት የመጡ ሁለት ወገኖች በተከታታይ ሲሞቱ አስታውሳለሁ ሌሎች መኝታዬ ላይ ሆሄ መውጣት በማልችልበት ጊዜ ህይወታቸውን አጥተው ቤተሰቦች ሲጪጪሁ በለቅሶ ሲተቃቀፉ ባል ሚስቱን ሚስት ባሏን ወላጆች ልጆቻቸውን ልጆች ወላጆቻቸው በቲቢ ምክንያት በሞት ሲያጡ በአይኔ በብረቱ አይቻለሁ በሌሎች የህክምና ቦታዎችም እንደዚሁ እንደሆነ ይገባኛል ከሁሉ ከሁሉ የሚያሳዝነው ደግሞ ቁጥር ስፍር የሌላቸው ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ በቲቢ ተይዘው ወደ ህክምና ከመምጣት ይልቅ ባህላዊ መድኃኒት አልያም አዋቂ ቤት በመመላለስ አልያም የእምነት ቦታ ለምሳሌ ጠበል ገዳማት ህክምናን የሚከለክሉ እየመሰላቸው ቲቢን የሚያክል በከፍተኛ ደረጃ ሊተላለፍ የሚችል የትንፋሽ ማዕበል ይዘው ከሌሎች የእምነት ሰዎች ጋር ተቀላቅለው ለሌሎችም የጤና ጠንቅ ሆነው እነሱም ሳይድኑ ለሞት የተዳረጉትን ሳስብ ወደ ህክምና እንዲመጡ ባላደረጓቸው የቅርብ ሰዎቻቸው ላይ ነደድ አልኩባቸው ቁጭት ነገር ጫረብኝ የቆምኩት የክፍላችን መግቢያ ላይ ስለነበር ወደ ኋላ ዞር ስል ባዶውን ያለው የወዳጄን የአብዱመሊክን አልጋ አየሁና ነፍስህን በገነት ያኑረው አብዲ የባጥ የቆጡን እያብሰለሰልኩ አንተን እረሳሁህ ይቅርታ አድርግልኝ ሞት ይርሳኝ ለራሴው አሜን አልኩኝ ሞት እንደረሳኝ ሳስብ ምን እንደተሰማኝ አላውቅም ቃሉን ደገምኩት ሞት ይርሳኝ የህይወት ተሞክሮአቸውን እያካፈሉን ነው ከሰባቱ አራቱ አውተውናል የአንድ የሁለቱን በወፍ በረር ነካ ነካ ላድርግላችሁ መሀል የግንባሩ ፀጉር ወደ ኋላ መሸሼ የጀመረ ሆዱ ገፋ ብሎ ቦርጭ ቢጤ ጣል ያደረገበት በአለባበሱ ሽክ ያለ በእኔ እድሜ ላይ ነው የሚገኘው ፈገግ እያለ እንደሆነ ጥርሶቹን ቀርቶ አፉን እንኳን ማየት አይቻልም በነጭ ማስክ ተሸፍኖአል ሲናገር ግን ልብ በሜነካ ስሜት ነው ሳጂን ኤፍሬም እባላለሁ ቀና ብሎ አየን የትራፊክ ፖሊስ ነኝ ከዛሬ አራት ዓመት በፊት በጣም ታምሜ ነበር ይሁንና መድኃኒቱን የተለማመደ ቲቢ እንደሆነ ከታወቀልኝ በኋላ ወደዚህ ሆስፒታል ስመጣ ይኹ ከዚህ ፊት ለፊት ያለው ወደዚህ መግቢያው ዳገት አፍ ቢኖረው ይመሰክር ነበር ከሰውነት ጎዳና ወጥቼ በአጥንቴ ብቻ ቀርቼ በመንሳቀሻ ወንበር ዊልቸር እየተገፋሁ ነው እዚህ ዋርድ የገባሁት ለተከታታይ ወራት መንቀሳቀስ አልችልም ነበር በመሆኑም ሐኪሞች ባዘዘልኝ መሰረት መድኃኒቴን በአግባቡ በመውሰድ ከ ወራት መርፌ ብሎም ከሃያ ወራት በቀን አስራ ሁለት ኪኒኖች መዋጥ በኋላ ይኹው ጤንነቴ ከተመለሰ ሁለት ዓመታት ሆኖኛል አሁን የስራ መደቤ ላይ በመመለስ የሳጅን ማዕረግ ድረስ ደርሻለሁ ሰውነቴንም እንደምታዩት ነው ሁለት ልጆቼን እያሳደኩ ከምርጥ ባለቤቴ ጋር አለሜን እየቀጨሁ እገኛለሁ በማለት ለሆስፒታሉ ሠራተኞች በሙሉ በፍቅርና በእንክብካቤ ስላከማችሁኝ በታዳጊ ልጆቼ ስም አመሰግናለሁ ለታካሚዎችም ማበረታታትና ምክርን ሰጥቶ ለእንስቷ እንግዳ ቦታውን ለቀቁ መምህርት ነኝ በወቅቱ ስራን አቋርጩ የተሻለ ቀጣይ ህይወት እንዲኖረኝ በማሰብ ወደ አረብ አገር ጅዳ ሄጄ በመስራት ላይ እያለሁ ወላጅ እናቴ በጠና ታማብኝ ወደ ሀገሬ ተጠራሁና ስመጣ እማዬ ከሰውነት ጎዳና ወጥታ እዚያችኛዋ ክፍል ውስጥ ተኝታ ነበር በማለት አሁን እዮብ ወማርያም የሚተኛበትን አሳየችን በወቅቱ አጠገቧ ሆሄ ለመንከባከብና ለማስታመም ብዙም እድል ሳላገኝ በአስራ ሁለት ቀናት ቆይታ ውስጥ እምዬ አጠገቧ ተቀምጩ እንደምትወደኝ እያወራችኝ አረፈች እናቴን አይኔ እያየ ሀኪሞች የቻሉትን ሁሉ ቢጥሩ ማትረፍ ሳይችሉ ሞተች ሲቃ ተናነቃት መሬት መሬት እያየች ከለቅሶዋ ጋር ታገለች በቃ ሞተች ባህር አቋርጩ የመጣሁላት እናቴ አረፈች አስክሬኗ ከወጣ በኋላ መኝታዋ ፍራሽ ስር አያሌ መድኃኒቶች ተገኙ ለካ በየቀኑ ይጠጣት የነበረውን መድኃኒት ዋጥኩ ትላለች እንጂ እየሰበሰበች ትጥለው ነበር አስቀድሜ ስላልመጣሁላት ብሎም ከደረስኩ በኋላም ከልቤ ስላልተከታተልኳት ቆጨኝ ተናደድኩ ምን ያደርጋል ያደረ ውሃ አይታፈስ ይሁንና በቀጣይ ትንሽ ወራት ደህና የነበርኩት ሰው ጤና አጣሁ ያስለኝ ጀመር ከእለት ወደ እለት እየጨመረ አንድ ወር አሳልኩ የምግብ ፍላጎቴ እያሳነሰ መጥቶ ድራሹ ጠፋ ለሊት ያልበኝ ደረቴ አካባቢ ውጋት ያድፈኝ ጀመር ጉልበቴ እየከዳኝ አቅም በማጣቴ ተጠራጥሬያለሁ ግን ስለፈራሁ ወደ እዚህ ሆስፒል አልመጣሁም ነበር ይሁንና ግን ሁኔታዎች እየተባባሱ ሲመጡ ግዴታ ሲሆንብኝ መጣሁ አስፈላጊው ምርመራ ከተደረገልኝ በኋላ መድኃኒቱን የተለማመደ ቲቢ መሆኑ ተነግሮኝ እዚሁ ግቢ እናቴ ያረፈችበት አልጋ ላይ ተኛሁ ቢሆንም ለቀጣይ ሁለት አመታት መድኃኒቴን በአግባቡ ተከታትዬ ለመዳን በቅቻለሁ አሁን ህክምናዬን ከጨረስኩ አንድ ዓመት ከአስር ወር ይሆነኛል ወደ ቀድሞ የመምህርት ሙያ ተመልሼያለሁ ለሚቀጥለው ዓመት እሞሽራለሁ ላገባ ነው እባካችሁ መድኃኒታችሁን በአግባቡ ውሰዱ እናቴ እኮ ያኔ ሲቃ ያዛት እንባ በተናነቀው ስሜት በቃ አልቻልኩም አመሰግናለሁ ብላ ወደ ወንበሯ አመራች ሌሎቹም በተለያየ መሳጭ ታሪካቸው ይዘውን ወደ ጓዳ ጎድጓዳቸው አስገቡን የሚኒ ባስ ታክሲ ሾፌሩም ተረከልን መድኃኒቱን እንደጨረሱ ቢሆንም በመድኃኒቶቹ የጎንዮሽ ጉዳት ጆሮው እምብዛም እንደማይሰማ ነግሮን በዚህም የተነሳ የስራውን አይነት ቀይሮ በደላላነት እንደሚተዳደርና አሁን በቲቢ የደረሰበትን ስቃይ ሲያስታውሰው እረፍት እንደሚነሳው በማውሳት አውርቶናል ሁሉም አመስጋኞች በሆስፒታሉ አገልግሎት ረክተው ለእኛም መካሪዎች ነበሩ አሁን የእኔ ተራ ነው እንደቆምኩ ነኝ ምንም አይነት ድካም አልተሰማኝም በቀርፋፋ የሚጎተቱ እግሮቼ እየተሳብኩ መሀል ላይ ለመግባት ከፊቴ ያለችውን አነስተኛ የውሃ መውረደጃ ቦይ ራመድ ብዩ ዘለልኩ ገድ ገድ ገድ ተወለካከፍኩ ቆምኩ አይዞህ አይዞህ ደግፋት እንጂ ብዙ ሰዎች የተለያየ ነገር አጉተመተሙ ሰማያዊ የሹራብ ኮፍያ ያላትን ቱታ ሹራብ ለብሼ በሸንበቆ እግሮቼ ቀጥ ብዬ ተገተርኩ ኮፍያዋን ወደኋላ ጣል አደረኩና ግራ ቀወኘን አማትሬ ካየሁ በኋላ ማንበቤን ቀጠልኩ ሣበዝ ልፈራ ነው መሰለኝ አልኩና ቀና ብዬ አየኋቸው አይኖች በሙሉ ሁለት ሁለት ሆነው ተተክለውብኛል ምን አለበት ሌላ ቦታ እያዩ ቢያዳምጡኝ አንድ እንኳን የሚሰማኝ ልጣ ሁሉም አፍጥጠውብኛል ምንም ማድረግ አልቻልኩም በሚያስገመግም ድምፅ ጀመርኩት የተከበሩ የሆስፒታላችን ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ያዕቆብ ሰማን ከፀሐፊዋ ወሮ ራሄል ሜዲካል ዳይሬክተር ዶር ሠለሞን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ንዋይ ይመር መድኃኒቱን የተለማመደ ቲቢ ዋና አስተባባሪ ዶር ዳንኤል መረሳ የነርሶች ዋና ኃላፊ ስስተር አለምፀሐይ የዚህ የዋርዳችን አስተባባሪ ቢረጋ ወፃዲቅ ሀኪማችን ዶር በቀለ የአስተኝቶ ማከም ክፍል ኃላፊ ዶር እንዲሁም ከሆስፒታሉ ጀርባ በመሆን እየደገፋችሁ ያላችሁ የግሎባል ሔልዝ ኮሚቴ የስራ አስፈጻሚዎች በስተግራዬ የምትግኙት የቀድሞ የቲቢ ታካሚዎች ዛሬ ተሞክሮአችሁን ልታካፍሉን የመጣችሁ ወገኖች በአጠቃላይ ክቡርና ክቡራት እንኳን በደህና መጣችሁ ስላየናችሁ ደስ ብሎናል ሑብጨባ ነበር ብሎ መናገር አያስፈልገኝም ክቡራንና ክቡራት በአንድ ቀን የ ሰዓት ጊዜያችሁ ውስጥ አብዛኛውን ማለትም የስምንት ሰዓትና ከዚያ በላይ የምታሳልፋት ሆስፒታላችሁ ውስጥ እዚህ የተሰበሰብነውን በተለያ ጊዜ አስገብታችሁ ስታስተናግዱን ከርማችኋል ይሁንና ግን በተደረገል መልካም አቀባበል ፍቅር እንክብካቤ አክብሮት አጥብቀን ከመዋሃዳችን ብሎም ከእናንተ ጋር በመቆራኘታችን ምክንያት ቤተኛ ሆንና ይኸው ዛሬ ነገሮች ተገልብጠው በቤታችሁ እንግዳ አድርገው በመጋበዛችን ታላቅ አክብሮት እና ኩራት ተሰምቶናል የተደረጉልንን መልካም ነገሮች ከህከክምና ሙያቸው አንስቶ ስለ ምግቡ ወተቱ በማከል ከፅዳት ሠራተኞች አንስቶ እስከበላይ ያሉትን በተለያየ ውብ ማራኪ ስሜት ከልቤ ካመሰገንኩ በኋላ አሁን በግቢያችን ያሉ ችግሮች ንገሩን ካላችሁ በመጀመሪያ ቤቶቹ በሙሉ አርጅተዋል አልጋችን አጠገብ ያሉት ኮመድኖዎች ቀለማቸው ለቆ መዛግ ጀምረዋል ሌላ መፀዳጃ ቤቶቹ ዝቅ ብለን ካልተቀመጥን መጠቀም አንችልም ለምሳሌ እኔ ከረዥም ጊዜ በኋላ ከአልጋዬ መንቀሳቀስ ወደ ሽንት ቤት ስሄድ ወርጄ ከተቀመጥኩበት መነሳት አልቻልኩም በመሆኑም ከፍ ብሎ ተረጋግተን ከተነፋፈስን በኋላ ለመነሳት የሚያመች መቀመጫ ያለው ሸንት ቤት ያስፈልገናል ከተቻለ መለስተኛ ካፌ ቢኖረን ደስ ይለናል ብዙም አስገዳጅ አይደለም ሌላው መድኃኒቶቹ በዝተዋል የህክምና ጊዜያችንም አሰልቺ ነው የበላይ ኃላፊዎች ለዚህ ምላሽ ቢሰጡን ደስተኞች ነን ከሁሉ በላይ ግን አጋጣሚ ሆኖ በቦታው ዶር በቀለ የነበሩ ባይሆን የአባትነት የህክምና አሰጣጣቸውን በማውሳት የዋርዱ የነርሶች አስተባባሪ ቢረጋ ወፃዲቅንም ከስራ ባልደረቦቹ ጋር በሙሉ ከልብ በመነጨ እውነተኛ ስሜት አመስግፔሄ ጨረስኩ ጭብጨባው ወደር አልነበረውም በመቀጠል ከአንቦ ዩኒቨርስቲ የሁለተኛ ዓመት ትምህርቱን አቋርጦ በህክምና ላይ የነበረው ዳዊት ድባቡ ግጥሙን አነበነበ በስተመጨረሻ የሆስፒታሉ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ያዕቆብ ሰማን መልዕክት እንዲያስተላልፍ መድረኩ ተሰጣቸው መቼም ብዙ ጊዜ የስራ ኃላፊዎች ንግግር ሲያደርጉ እያሰቡ የሚያወሩ ይመስል እኤአ ከማለታቸው ባሻገር ነገሮችን የሚያንዛዙ ይመስለኛል በስተመጨረሻ ዝግጅቶች ሲያልቁ መዝግያ ከሆነ የሚናገሩት ቢያጥር ባያንዛዙት እመኛለሁ ዛሬ ፀሎቴ የተሰማ መሰለኝ አቶ ያዕቆብ ሰማን በወጣትነት እድሜ ላይ የሚገኝ ሲሆን ቀልጣፋ ያለ ያልተንዛዛ ወሬ አወራልን የተናገረውን ከተሰማኝ ስሜት ጋር ሳዋዛላችሁ እንዲህ ነበር አቶ ያዕቆብ ሰማን እበላለሁ የሆስፒታሉ ሥራ አስያጅ ነኝ በነበረን ቆይታ ደስተኞችና አመስጋኞች ነን ቢሆንም ግን አሁን ቅጣው ነው መሰለኝ ስምህን ያልከው ስሜን በትክክል በመጥራቱ ራሴን ነቀነኩለት በትክክል ስላዳመጠኝም ደስ ያለኝ መሰለኝ በመጀመሪያ ደረጃ የክፍሎቹ መታደስ ሰምተናል በቅርቡ አምነንበታል የበጀት ችግር የለብንም ተግባራዊ ይሆናል ብዙ ጊዜ እዚህ ክልል ገብቶ ለመስራት ብዙ ድርጅቶች ስለሜፈሩ ነው ይሁንና አስፈላጊውን ሁሉ አድርገን እናሳድሳለን የሞቀ ጭብጨባ ነበር አብዛኛውን ጊዜ እንደዚህ አይነት ጥያቄዎች በጀት ያንሳል የለንም በማለት ገንዘብ መጠየቂያ ሲደረጉ በምሰማበት ዘመን በሙሉ አፋቸው በጀት ችግር የለም አሉን የመፀዳጃ ቤቶቹን ችግሮች ተቀብለናል ከእኛ በበለጠ የደረሰባችሁን ስትነግሩን ማስተካከል ያለብን ገብቶናል ስለዚህ ከእድሳቱ ጎን ለጎን መፀዳጃ ቤቶቹም አመቺ ተደርገውላችሁ ይዘጋጃሉ በመቀጠል ሻይ ቡና የምትሉበት ቦታ እናመቻቻለን መድኃኒቱ ቁጥሩ በዝቶአል የህክምና ጊዜውም ረዥም ነው ለተባለው የመድኃኒቶቹን ቁጥር ለመቀነስ ጊዜውንም ከ ወራት ወደ ዘጠኝ ወራት ለማሳጠር ምርምርና ጥናት እየተካሄደ ሙከራዎችም እየተካሄዱ እንደሆነ እንድታውቁ እንፈልጋለን ውጤቱም አጥጋቢ ሆኖ ተገኝቷአል በቅርቡ ሁኔታዎች እንደሚሜስተካከሉ እናምናለን የምንደርስበትን ሁሉ በቅርብ እናሳውቃችኋለን በአገልግሎታችን በመርካታችሁና በማመስገናችሁ እናመሰግናለን በስተመጨረሻ ይኹ ክልል ለብቻው መታጠሩ አድሎና መገለል ለመሰላችሁ ተሳስታችኋል ቦታውን ለመለየት ብቻ ነው የተደረገው ለምሳሌ እኔ እንደምታዩት አፍና አፍንጫዬን የሚሸፍን ማስክ አላደረኩም አለማመን መብታችሁ ነው መተንፈሻው እንዳልተከለለ አሁን ገና ነው ያየሁት ከገባ ጀምሮ ክፍቱን ነበር ባለፉት አርባና ሀምሳ አመታት በሆስፒታላችን የሚሰራ አንድም ሰው በቲቢ አልተያዘም ያም የሆነው ሁሉም በእውቀት የዳበረ ሲሆን መቼና የት የቲቢ ባክቴሪያ እንደሚተላለፍ እናውቃለን አስፈላጊውን ጥንቃቄን መከላከልም እናደርጋለን በመሆኑም ንፁህ አየር እንደልብ የሚዘዋወርበት ቦታ እንደዚህ ክፍት አየር ፀከአ ባለበት ቦታ ላይ ቲቢ የመተላለፍ እድሉ አነስተኛ ነው እንዲያውም አይተላለፍም ማለት እንችላለን ስለዚህ በጥንቃቄ እንቀርባችኋለን በፍቅርና በአክብሮት እናገለግላችኋለን አመሰግናለሁ በስተመጨረሻ በክልላችን ቤተ መጻሕፍት አደራጅቶ ለመክፈት በፈቃደኝነት ሁሉም ሊያበረክት የሚችለውን የመጻሕፍት ብዛት በአደባባይ ቃል ገቡ ስማቸውን ብሎም ስንት እንደሚያመጡ ከአፋቸው እየቀለብኩ ፊት ለፊታቸው በመቆም የምፅፈው እኔ ነበርኩ በአጠቃላይ አስራ ሁለት ስም ዝርዝር በድምሩ አርባ ሶስት መጻሕፍት ቃል ተገቡ በደፈናው የቻልኩትን ያህል ያሉም አልጠፉም አቶ ያዕቆብ አጠገባቸው ለተቀመጠው ዶር ስለ ሌላ ሰው ስለተባለው መጨረሻ አካባቢ ስላነበብነው የዶር ምህረት ደበበ ልብወለድ የሆነ ነገር ሹክ ሲለው አይቸዋለሁ ሁሉም ነገር ከጠበኩት በተሻለ መልኩ መንፈሴን አድሶ በአሪፍ ሁኔታ ተጠናቀቀ ለስላሳዎች ታድለውን እየተጎነጨን ነበር የዕለቱ የክብር እንግዶቻችን በመሀላችን ሰንጥቀው በሰልፍ ጥንድ ጥንድ በመሆን ወጥተው ሄዱ የዚችኛዋ ቀን ምሽት በየአመቱ ላከብራት የሚገባኝ የተለየች ነበር ታከለ ተሾመ ደስ የሚል ጊዜ ነበር ሲለኝ ጋሽ አበራ ፀሐይ ንግግርህ የዲፕሎማት አይነት ነው ሌሎችም አድናቆትና ክብር ሰጡኝ በፍፁም ወደ መኝታዬ አልሄድኩም ሴቶች ክፍላቸው ወሰዱኝ ቡና ተፈላ አደነቁኝ አኮራኸን እስከ ዛሬ አፍህን ዘግተህ ለካ እንደዚህ ተናጋሪ ነን ተባልኩ የተቃራኒ ፆታን ትኩረት በማግኘቴ የሆነ ተፅእኖ ሳያሳድርብኝ አልቀረም ስራ አስኪያጁ አቶ ያዕቆብ ሰማን እና የስራ ባልደረቦቹ የፈጠረብንን ስሜት ብገልፀው ከንቱ ውዳሴ ስለሚመስልብኝ እንዳይባክን አልነግራችሁም በቃ እውነቱን ማወቅ ከፈለጋችሁ የዛን ምሽት ከክፍል ክፍል እያልኩ ግቢው ውስጥ ስንጎማለል ስስተናገድ ወሬያችን በሙሉ ሲለቀን እንግዶቻችን በተለይ የህይወት ተሞክሯቸውን ስላካፈሉን ወገኖቻችንን ብቻ ነበር ምን አለፋችሁ ከዚህች ቀን በኋላ ቀን ቀን ላይ እምብዛም መኝታዬ ላይ አልገኝም ሰው ሰራሽ መተንፈሻ ኦክስጂኑንም ለአንድ ደቂቃ እንኳን ሳልጠቀም ተውኩት በቃ አቆምኩ በራሴ በሳንባዬ መተንፈስ ጀመርኩ የኦክስጅን በርሜሉ ሶስት መቶ ይላል ውስጡ ያለውን የአየር መጠን የሚገልፀው ጠቋሚ ሰዓት ለማንኛውም በማለት ከአጠገቤ ሳይነሳ ለረዥም ቀናት አሳልፏል በየእለቱ በሰውነቴ ውስጥ ያለው ኦክስጂን የመረጥኩት አንዷ ጣቴ ላይ በመሰካት ይለካል ዘጠና እና ዘጠና ሁለት በየእለቱ አይቀንስም በጣም ሐሪፍ ነበር ከአጠገቤ እንዲነሳ ተደረገ ለካ ግኡዝ ነገርም ቢሆን መልመድ እንዴት ይከብዳል መሰላችሁ ለተከታታይ ሰባት ወራት ቀን ከለሊት ሳይለየኝ አጠገቤ ተገትሮ አየው የነበረ የድራፍት ማሽን ኤን የሚቆመው አይነት የኦክስጂን በርሜል ከአጠገቤ ሲነሳ የሆነ ነገር የጎደለብኝ መሰለኝ ቅር ቅር ሳይለኝ አልቀረም ማንኛውም ታካሜ እዚህ ሥፍራ ላይ ሐኪሞች መሄድ እስኪፈቅዱ ፊት መቆየት ግድ ይለዋል ፍቃዳቸው ሲሆን እንደ ህክምና ውጤቱ ታሪክ በመነሳት ወደ ቤቱ ይሄዳል ቀጣይ ህክምናውን አቅራቢያው የሚገኝ ጤና ጣቢያ መድኃኒቶቹ ይወስዱለትና በየእለቱ እየተመላለሰ መርፌውን እስኪጨርስ ይወጋል የሚዋጡትንም ኪኒኖች እስከ መጨረሻዋ ወይም ወራት በየእለቱ ጠዋት ጤና ጣቢያው ድረስ በመሄድ ይውጣል በየወሩ እዚህ ሆስፒታል እየመጣ አስፈላጊውን ምርመራና ክትትል ያደርጋል ታከለ ተሾመን ወደ ሰንዳፋ አበራ ፀሐዬ ሰሜን ሆቴል አካባቢ ሚቱና ልጁ ጋር ተቀላቅሏል ሰሙ ስድስት ኪሎ ሲስተር ቤት ከሄደ ሁለተኛ ቀኑ ነው እኔም የስምንት ወር መርፌዬን አጠናቅቄ የሚጡ ኪኒኖቼን አስራ አንደኛ ወሬ ላይ ደርሻለሁ አንድ ድፍን አመት ሊሞላኝ የቀረኝ አንድ ወር ብቻ ነው እንደምታዩኝ ከገባሁበት ጊዜ ከነበርኩበት ደረጃ ፍፁም ተቃራኒ በሆነ መልኩ ጥሩ አቋም ላይ ነኝ አልፎ አልፎ የሚያስለኝን በአጋዥ መድኃኒቶች ቀጥ ይላል ደረቴ አካባቢ የሚሰማኝ ውጋትና ቁስለት በጊዜ ሂደት እንደሚስተካከል አምኛለሁ አልፎ አልፎም ቢሆን የምመገበው ምግብ ይከብደኛል አልያም ተናንቆኝ ወደ ላይ ይለኛል እተፋዋለሁ ሀኪሞቼ ከመድኃኒቶቹ ብዛት የተነሳ ጨጓራዬ ተጎድቶ ሊሆን ይችላል በማለት ኦምፕራዞል የተባለ የሚዋጥ ኪኒን ተጨምሮልኛል በመንቀሳቀስ ብሎም በመተንፈስ ችግር ስላልነበረብኝ ወደ ቤት መሄድ ትችላለህ ተብዬ ወጥቻለሁ እዮብ ወማርያም ሊሻለው አልቻለም እለት ከእለት እየባሰበት ነው ሁለተኛው እግርና እጁም መንቀሳቀስ አቁመው ስልል ብለዋል መኝታው ላይ እንደተዘረጋጋ ይተኛል ሆስፒታሉ በቀጠረለት የግል አስታማሚው እርዳታ ካልሆነ መገላበጥ አይችልም በመረዋ ድምጽ ሲዘፍንበት የነበረው አንደበቱ መናገር አቁሞአል አጠገቡ ቆሜ የሚናገረውን በሙሉ እንደሚሰማ ላጽናናው ስሞክር የአይኑን ቅንድቦች ብቻ ከማነቃነቅ ብሎም ከንፈሮቹን ግራና ቀኝ አንሸራቶ ፈገግ ከማለት ውጭ ድምፅ እንኳን አያሰማም መልካሙን ተመኝቼለት ነበር የወጣሁት ጤነኛ በነበርኩት ጊዜ ስሰራበት የነበረው መካከለኛ የኤሌክትሮኒክስ መጠገኛ የግል የስራ ቦታዬ የሚሠራበት ስላልነበር ተዘግቷል ተከራይቼው የነበረው ቤት በከፊል እንደተዘረፉ የልጄ እናት ለምለም አርድታኛለች እሷም ሶስት ዓት ያለፉትን ልጃችንን ይዛ ከአክስቷ ጋር እንደምትኖር ነግራኝ በናፍቆት ሆስፒታል እያለሁ ከአንድ ወር በፊት ያሉበት ድረስ በመሄድ ጠይቄያቸዋለሁ ልጄ ፈፅሞ አልዘነጋችኝም ልትዘጋኝም አትችልም አገላብጩ አየኋት ዳበስኳት ዳበስኳት ዳሰስኳት አጫወትኳት ትንፋሼን ከትንፋጂ ለማዋሀድ አልያም የራበችኝን ያህል ከልብ ልስማት አልደፈርኩም ሲያሰቃየኝ የነበረው የቲቢ ባክቴርያ አሁንም ስጋት ውስጥ ከቶኛል ይሁንና ግን በቁመት በአነጋገር ብሎም በእድሜ አድጋ ስላገኘኋት በጣሙን ደስ ብሎኛል ቢሆንም ለጊዜውም ቢሆን በቀጣይ አብረን የማንሆንበት አያሌ ምክንያቶች ነበሩ በመሆኑም ሌላ የምገባበት ቤት አልያም የምሰራውን ስራ እንደአዲስ ማዘጋጀት እጅጉን ፈታኝ ነበር ብላችሁ መቼም ይገባችኋል ስላሳለፍኩት ፈታኝ አስቸጋሪ የመቋቋሚያ ብቻ ሳይሆን ጊዜያዊ ማረፍያ ቦታ መዘጋጀት ጊዜ ልተርክላችሁ አልሻም ይሁንና ግን በመጀመሪያ የማርፍባትን አንድ ክፍል ዋና ዋና ከሚባሉት የመኝታና የምግብ ማብሰያ ብሎም መመገቢያ እቃዎች ጋር በአንድ ነጠላ የቅርቤ ሰው ተዘጋጀልኝ ሲቀጥል ከሁለት ወራት ቆይታ በኋላ በመገናኛ ወደ ካራ በሚወስደው መንገድ ወሰን ሰፋሪ መንገድ ዳር የኤሌክትሮኒክስ መጠገኛ ቤት ከሚያስፈልጉኝ ወሳኝ መስሪያ እቃዎች ጋር በቅርቤ ሰው አማካይነት ተሟላልኝና ኑሮዬን እንደ አዲስ አንድ ብዬ መኖር ጀመርኩ ሆስፒታል ውስጥ በነበርኩ ጊዜ ከተተዋወኳቸው ድንቅ ከሚባሉ ታካሚዎች ውስጥ አለሙ ብናልፍ የሀያዎቹ አጋማሽ እድሜ ላይ የሚገኝ በሀይማኖቱ አጥባቂ የሚባል በኦርቶዶክስ ሐይማኖት ተከታይ ነው በጣም ከመግባባታችን የተነሳ ስንድን አብረን እንደምንሰራ አውግተን ነበር ከጎጃም መጥቶ አዲስ አበባ ለስድስት አመታት በተለያዩ ቦታዎች አብዛኛውን ንቁ የኾል ማምረቻ ውስጥ በታማኝነት በሙያና በኃላፊነት ሲያገለግል ቆይቶ የተወሰኑ ገንዘብ ማጠራቀወሙን ሲያረጋግጥ ጉለሌ ክፍለ ከተማ አዲሱ ገበያ አካባቢ አንድ ሙሉ ግቢ ተከራይቶ ሶስት ሠራተኞችን ቀጥሮ የእንጀራ መጋገርና መሸጥ ስራ ይሰራ ጀመር ስራው አተናክሮ ሠራተኞቹን ወደ አምስት አድርሶ ባለ በሌለ ኃይሉ አቅሙን ሁሉ አሟጦ በሚሰራበት ወቅት ነው በህመም የወደቀው ይሁንና ጠንካራ ሳሉ እየተፈታተነው ከሰማንያ እስከ መቶ እንጀራ በጭንቅላቱ እየተሸከመ ይዞራል ገበያ ያፈላልጋል ሰራተኛ ሲያቋርጥ ሌላ ጋጋሪ አልያም ሻጭ ከደላላ ቤት ያፈላልጋል ይቀጥራል ቀን ቀንን እየተካ ጊዜው ሲነጉድ ግን ጤናውም ሙሉ ለሙሉ ጠፋና መስራትም አልቻለም በየቀኑ የህክምና ቦታና ቤቱ ማሳለፍ ጀመረ በስተመጨረሻ መድኃኒቱን የተለማመደ ቲቢ መሆኑ ተረጋግጦለት እኔ የነበርኩበት ሆስፒታል የገባው ህክምናችን አንድ አይነት በመሆኑ እኔ በወድኩባት ጎዳና አልፎ የተሻለ ደረጃ ሲደርስ ነው የተለያየነው ቀሪ የህክምና ጊዜውን ቤተሰቡ ጋር ሊያሳልፍ ወደ ጎጃም ደብረ ማርቆስ ከተማ አካባቢ ጎዛመን ወረዳ አመራ አዲስ አበባማ ምን ቀረው ድርጅቱ ተዘግቷአል በሰራተኞቹ አጠቃቀም ጉድለት ሊወጣው የማይችለው ኪሳራ ውስጥ ገብቶአል ከወፍጮ ቤት የመጣ የጤፍ እዳ ከውዝፍ ቤት ኪራይ ጋር እዳ ውስጥ ገብቶአል አሁን የኔን የኤሌክትሮኒክስጥገና ቤት መክፈትና ስራ መጀመር አብስሬው ኑሮን አብረን ልንገፋ ሙያውንም ላስተምረው ተነጋግረን ወደ አዲስ አበባ ተመልሶ በአንድ ጤና ጣቢያ መድኃኒታችንን እየወሰድን በአንድ ጣራ ስር መኖር ጀምረናል መስሪያችንም መኖሪያችንም አንድ ቦታ ላይ ስለነበር ጠዋት መድኃኒታችንን ለመውሰድ ጤና ጣቢያ ከመሄዳችን በዘለለ የትም አልወጣም ከሆስፒታል ስወጣ የነበሩት የህመም ስሜቶች እንዳሉ ናቸው የሚያስመልሰኝ በተለየ መልኩ ጨምሮአል በቀን አንዴ የማይቀር ሆኖአል በየወሩ ሆሰጅፒታላችን በመሄድ ምርመራ እናደርጋለን ክትትላችንም ቀጥሷል ዛሬ ግን በአስቸኳይ እንድመጣ በወቅቱ ሲከታተለኝ ከነበረው የጤና ባለሙያ ቃሲም አባቶ በተደረገልኝ የስልክ ጥሪ በቦታው ላይ ተገኝቻለሁ መድኃኒቱን የተለማመደ ቲቢ ህክምና አስተባባሪ ሆነው ዶር ዳንኤል መረሳ ሊያናግረኝ እንደሚፈልግ ተነግሮኝ ከትንሽ ደቂቃዎች በኋላ አንደኛው የምርመራ ክፍል ውስጥ እንድገባ ተደረገ ከመርመራ ጠረሌሴዛው ጀርባ ሁለቱ ባለሙያዎች ጎን ለጎን ተቀምጠዋል ሌላኛው የጤና ባለሙያ ዮሐንስ የተከፈተው መስኮት ጎን ቆሞአል በክብር ጨብጠው እንድቀመጥ ከጋበዙኝ በኋላ ቅጣው መድኃኒት ከጀመርክ ስንተኛ ወርህ ነው ዶር ዳንኤል የህክምና መዝገቤን እያገላበጠ አስራ ሰባተኛዬ ጀምሬያለሁ ለመጨረስ የቀረችኝን በጣት የሚቆጠሩ ወራት እያሰብኩ ነበር ሁለት አልያም ሶስት መድኃኒትህን በአግባቡ እየወሰድክ ነው አዎ በሚገባ አሁን ምን ይሰማሃል ዶር አይን አይኔን እያየ ደረቴ አካባቢ ውጋት ቁስለት ያህል ነው በየቀኑ ያስመልሰኛል ክብደትህስ እስቲ ሚዛኑ ላይ ውጣ ተመዘንኩ አርባ ዘጠኝ ኪግ ከባለፈው ወር አንድ ኪሎ ቀንሻለሁ ኪሎህ ብዙም አይጨምርም ሀምሳ ሁለት ደርሼ ነበር አሁን ትንሽ ቀንሻለሁ ቅጣው አንድ እውነት ማወቅ እንፈልጋለን መድኃኒትህን አቋርጠሃል ጸረ እንዲያውም ሌሎች እየመከርኩ እንዴት አቋርጣለሁ ሲያስመልስህ መድኃኒቱን ከዋጥክ በኋላ ነው ዶር ተረጋግቶ ነው የሚያወራው እርግጥ ከወሰድኩ ከአንድ ሰዓት በኋላ ነው የሚያስመልሰኝ ግን ሲወጣ በሚታይ እቃ ላይ ስለሆነ አየዋለሁ አጋጣሚ መድኃኒቱ ከወጣ ተክቼ እወጥበታለሁ ከአንድ ሁለት ጊዜ በሳይ ግን አልተከሰተም ይኸውልህ ሁለት የካልቸር ውጤትህ ፖዘቲቭ መቶአል ብሎ ሁለት ወረቀቶች ጠረጴዛው ላይ አሳየኝ በሆስፒታል እያለንም ይሁን ቤታችን ከገባን በኋላ ህክምናችንን እስክናጠናቅቅ በየወሩ በሁለት እቃዎች የአክታ ናሙና እንሰጣለን በትንጽ እቃ የምንሰጠው እዚሁ ሆስፒታል ውስጥ የሚመረመር ሲሆን በትልቁ እቃ የምንሠጠው የአክታ ናሙና ግን ፓስተር ድረስ በመሄድ ምርመራ እንደሚደረግበትና ውጤቱም በሰጠን ሶስት ወር ውስጥ ክትትል በማድረግ ባክቴርያውን በማሳደግ ይታያል በቅሎ አድጎ የሚያዩ ከሆነ በቀጣይ እንደሚሜራባ በማን አልዳነም ጤነኛ አይደለም በማለት ፖዘቲቭ የሚል መልስን ይሰጣሉ አሁን እኔም ባለቀ ሰዓት የተባልኩት ይኹን ነው ደነገጥኩ ግራ ቀኝ ተዘዋውሬ ሶስቱንም ባለሙያዎች ግራ በገባው ስሜት አየኋቸው ቅጣው ብዙ እያሳሰብህ አሁን መድኃኒቶችህ ይቀየሩልሃል በግዜ መታወቁ ጥሩ ነው ትንሽ ተስፋ ታየኝ ማለት አልገባኝም እንዲብራራልኝ ጠየኩ አሁን የምትወስዳቸው መድኃኒቶች ከባክቴሪያው ጋር ተለማምደዋል ከዚህ የተሻሉ ሌሎች መድኃኒቶች አሉ እነሱን በፍጥነት መጀመር አለብህ መልካም ይቻላል አሁን ዛሬ መጀመር እችላለሁ አልኩ መሬት እያየሁ መድኃኒቱ እዚህ የለም ቢሾፍቱ ትሄድና እዚያ ትጀምራለህ ተመልሼ ሆስፒታል ልተኛ የሆነ ነገር ሰውነቴን ውርር አደረገኝ አሁን እንልክልሃለን ብዙም አትቆይም ወደ እዚሁ ይመልሱሃል ምን ያህል ጊዜ እቆያለሁ ማፋ ቢል ሶስት ወር አሁን እንባዬ ግጥም አለ ፈራርሶ የነበረው ኑሮዬን እንደ አዲስ መገንባት ስጀምር መልሼ ልተወው በየወሩ የስራ ቦታዬ የቤት ኪራይ አለ ብድን እንኳን መልሼ ለመቋቋም አልችልም አሁንስ ተስፋ ቆረጥኩ በቃ ተውት ልሙት እንጂ አልሄድም አልኩኝ አንተ ጠንካራ ሰው ነህ ቅጣው ያለፉትን ግዜያት ብርቱ ሰው ሆነህ ነው ያሳለፍከው በፊት እንኳን መንቀሳቀስ እንኳን ሳትችል ተቋቁመኸዋል አሁን ደግሞ እራስህን መንከባከብ ትችላለህ ብዙም አይከብድህም ዶር ዳንኤል አይኑን ሳይነቅልብኝ እያቀለለው አወራኝ ከሶስት ወር በኋላስ እንዴት እሆናለሁ ያን ያህልም ላትቆይ ትችላለህ ስላለው ሁኔታ ቀጣይ ህይወትህን ጨምር እዚያ ለሚከታተሉህ ሐኪሞች እናስረዳቸዋለን እስክትመለስም የስራ ቦታህን የቤት ኪራይ እንከፍልልሃለን አሉኝ በሹክሹክታ ከተነጋገሩ በኋላ እሺ እሺ ይሁን አልኩ እንባ እየተናነቀኝ ቀና ብዬ ለማየት እንደተቸገርኩ ከቀናት በኋላ በተቀጠርኩበት ቀን ከቢሾፍቱ እንስት የጤና ባለሙያ የጫነች አንቡላንስ አዲስ አበባ ቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል ድረስ መታለች ከዚህ ቢረጋ ወፃዲቅን ከሾፌሩ እና ከነርሷ መሀል ተቀምጦ እኔ አለሙ ብናልፍና አንድ ወዳጄ ከኋላ ተጭነን አልፎ አልፎ በምታሰማው ድምጽ መንገድ እያስለቀቀች በክብርና በምቾት በአዲሱ ፈጣን መንገድ ወደ ምስራቅ መስመር ይዛን ከነፋች ደንበኛዬ አንቡላንሷ ከአዲስ አበባ አርባ ሁለት ኪሜ ቢሾፍቱ ከተማ የሚገኘው ቢሾፍቱ ሆስፒታል ጊቢ ውስጥ ወደሚገኝ ለብቻው ተነጥሎ የታጠረ ስፍራ አውርደውኝ ቢረጋ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሆነ በሚያሳብቅ ሁኔታ ግቢውን ዞር ዞር ብሎ ካየ በኋላ እጅግ በጣም ንፁህ ቤተ መንግስት የሚመስል ቦታ ነው የመጣኸው በቅርቡ ትመለሳለህ በማለት መልካሙን ተመኝቶልኝ አስረክቦኝ ወጥቶ ሄደ አለሙ ብናልፍና ወዳጄም የሚያስፈልጉኝን ነገሮች አሟልተውልኝ ተሰናብተውኝ ሄዱ ቦታው እውነት ነው በጣም ያምራል በቅርቡ ከፍተኛ እድሳት እንደተደረገለት ያስታውቃል ሶስት የተለያዩ ባለ አንድ አንድ መኝታ ክፍሎች የየግላቸው በውስጣቸው በጥቃቴ የተሰራ ሙቅ ውሃ ያለው ገላ መታጠቢያ ብሎም መፀዳጃ አላቸው ሌሎች ሁለት ክፍሎች ደግሞ አንድ ለሴቶች ሌላኛው ደግሞ ለእኛ የሚሆኑ እያንዳንዳቸው ሶስት አልጋዎች ሲኖራቸው በይዘታቸውም ሰፋፊ ሲሆኑ ለብቻው ገንጠል ብዬ የተሰራ ምቶች የማይነሳ በጋራ የምንጠቀምበት ሀሪፍ የገላ መታጠቢያ ብሎም መፀዳጃ ቤት አለ በገባሁ ቀን ተሲያት በኋላ በየክፍሉ ያሉትን ቀድመውኝ የገቡ ታካሚዎችን ተዋውቄያለሁ አዲስ አበባ ሆስፒል ከታዘብኩት የተለየ ነገር የለም በፆታ የተለያዩ እድሜያቸውም እንደዛው የማይገናኝ ሃይማኖት ያላቸው በብሄር በእውቀት በኑሮ ደረጃ ሁሉ ልዩነት የሚታይባቸው ወገኖቼ ለአንድ አይነት ህክምና አንድ ቦታ ላይ ተገናኝተዋል የግቢው ህጎች ተነገሩኝ ህክምናው የሚሰጠኝ በውስጥ ደዌ ስፔሻሊስቶች በመታገዝ እንደሆነ ተነግሮኝ የመጀመሪያ ቀን አጠቃላይ ደቂቃ የፈጀ ምርመራ በግቢው ሐኪም ዶር አህመድና ወጣት ዶር ተደርጎልኝ አድሬያለሁ በክልሉ ሁለት ወንድና ሁለት ሴት ነርሶች እንዳሉ ታዝቤያለሁ በተዋወቀህ በደቂቃዎች ውስጥ ወዳጅህ ማድረግ የሚችልበት የህክምና ባለሞያ ጠዋት ሶስት ሰዓት ሳይሞላ በፊት እያናገረኝ ነው አቶ ቅጣው እንዴት አደረክ እየለመድክ ነው ጥሩ እንቅልፍ ወስዶኛል ምንም እንግድነት አልተሰማኝም ረና እባላለሁ እዚህ እስካለህ በየእለቱ መገናኘታችን አይቀርም አመሰግናለሁ ስላወኩህ ደስ ብሎኛል ይኸውልህ ቅጣው እዚህ ህክምና ለመጀመር የምትሞላው ፎርም ይኖርሃል መጀመሪያ አስረዳህና አንብበህ ትፈርማለህ አንዱን ግልባጭ መውሰድ ትችላለህ አንደኛው እኛ ጋር ይቀመጣል ምን ነበር ልታስረዳኝ ትችላለህ እዚህ ያሉ ታካሚዎች የምትወስዱት አንድ አይነት አይደለም ሐኪሞቹ ያላችሁበትን ደረጃ በማየት ሁለት የተለያዩ መድኃኒቶችን ከሌሎች ኪኒኖች ጋር በማዋሀድ ነው የሚሰጡት አንዳንዶች ሚላማይዲን ሲሰጣቸው ለከፊሎች ደግሞ ፔዳኩሊን ይሠጣቸዋል ይህ ካልሆነ ሁለቱም የመድኃኒት አይነቶች በአንድ ላይ ይሰጣሉ ለማንኛውም አንተ ፔዳኩሊን ከሌሎች ውህድ መድኃኒቶች ጋር ነው የምትወስደው በማለት ስለመድኃኒቶቹ አጠቃላይ ሁኔታ አብራራልኝ መልካም ምን ያህል ጊዜ ነው የምወስደው ለሚቀጥሉት ስምንት ወራት መርፌ ትወጋለህ ተሳስተሃል ወንድሜ ቦረና ስምንት ወር ተወግቼ ነው እኮ የመጣሁት አውቃለሁ የምርመራህ ውጤት የሚያሳየው ባክቴሪያው መርፌውን ጨምሮ ነው የተለማመደው እና ድጋሚ ይኹን ያህል ግዜ ልወጋ አልዋሻችሁም ድንጋጤዬ ወደር አልነበረውም ከዚህ በፊት ካፕሮማይሲን ነው የተወጋኸው አሁን በቀጣይ ካናማይሲን ነው የምትወጋው እንደገና ስምንት ወር ብዙዎች እዚህ ያሉ እንደተውናቸው ሁለተኛ ዙር ነው እየተወጉ ያሉት ይሁን እሺ ኪኒኑስ ስንት ጊዜ ነው የምውጠው ዛሬ ትጀምራለህ ከ እስከ ወራት ትወስዳለህ ድጋሚ ሁለት አመት ወሸመጤ ቁርጥ አለ የሚሆነው ሆኖ ከብዙ መነታረክ በኋላ ግድ መሆኑን ተረድቼ እንደገና ጨረስኩ ያልኩትን መድኃኒቶች አሀዱ ብዬ ጀመርኩ ከነመርፌው በተለይ መርፌው እንዴት ሊለምድ እንደቻለ አበክሬ ተከራክሬያለሁ ምክንያት ከተባለ ኪኒኖቹ ያልዋጥከው ቀን አለ ብባል እንኳን መወጊያ ታፋዬን ከሆስፒታል ሰውሬው አላውቅ ሙሉ ወር የተወጋሁት እዚያው ነው ቢሆንም ግን በተለያዩ ምክንያቶች የምወጋው የመድኃኒት መጠን የተስተካከለ ሳይሆን አሊያም መድኃኒቶች በተለያየ ምክንያት አቅማቸው ያነሰ ሲሆን በባክቴሪያው ተቀያያሪ ባህሪም ሊሆን ይችላል በሚለው የማግባቢያ ቃላት ተነጋግረን ህክምናዬን ጀመርኩ መቼም ካለፉት አስራ ሰባት ወራት ተጨማሪ እጥፍ ጊዜያትን እንደገና በቀን አስራ ሁለት ኪኒኖችን መዋጥ ከስምንት ወር መርፌዬ ጋር ለማሰብ የሚከብድ ብሎም የማይገፋ ይመስላል ይሁንና ግን ከብሶቱ እና አስከፊ ገፅታው ባሻገር ያለውን ባጭሩ ላውጋችሁ የመጀመሪያውን አንድ ወር በጥንቃቄ ብሎም በየእለቱ በሚደረግ የሐኪሞች ክትትል በተለይ ፔዳሊን የሚለው መድኃኒት በልብ ላይ የሚያደርሰውን የጎንዮሽ ጉዳት ግምት ውስጥ በመክተት በስፔሻሊስቶቹ የሰኢሲጂ የልብ ምርማ በማድረግ ያላሰለሰ ጥንቃቄና ትኩረት የተሰጠበት የህክምና ጊዜ በዚሁ ግቢ ውስጥ አሳለፍኩ አልፎ አልፎ የሚሜያስለኝ ሳል ቀኝ አለ የሚያስመልሰኝ ነገር ድራሹ ጠፋ ደረቴ አካባቢ የነበረው የህመም ስሜት የት እንደገባ አላውቅም ክብደቴ ሽቅብ ጨመረ በመልካም የጤንነት ስሜት በሰላሳ ሁለተኛ ቀኔ ወደ ቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒል አዲስ አበባ መጣሁ ሆስፒታሉ መድኃኒቱን የተለማመደ ቲቢ ህክምና በተለመደው መልኩ እያከናወነ ይገኛል ከእኔ ጋር የነበሩት በሙሉ ወደየቤታቸው ሄደዋል ሌሎች ሁሉም ማለት ይቻላል አዳዲሶች ነበሩ እዮብ ወማርያም መድኃኒቱን ጨርሶ በተደጋጋሚ በተደረገለት የአክታ ካልቸር ምርመራ ከባክተሬያሉ ነፃ መሆኑን ተረጋግጧል ቢሆንም ግን እጅና እግሩን ጨምሮ መላ አካላቱን እንዲንቀሳቀሱ ማድረግ አልተቻለም በወቅቱ መድኃኒቶቹን እየወሰደ አልኮል መቀማመሱ ሳይሆን እንዳለቀረ ችግሩን የፈጠረው ይወራል ይሁንና ግን ከቲቢ ታካሚዎች ጋር አብሮ መቆየቱ ለሱም ጥሩ ባለመሆኑ ቀጣይ በሆስፒታሉ የሚደረግለት ህክምና እንብዛም ስላልነበር ይኖርበት ቤት እንዳይሄድ ከዚህ በፊት ኪራይ እንዳይቆጥርበት በማሰብ እቃዎቹን ሸክፎ እንዳስቀመጠ ሲናገር ሰምቼዋለሁ አንድ ባለ አራት እግር ጎማ ያላት ሻንጣውን ብቻ በልብስ ወጥሮ ነበር ሆስፒታል ውስጥ የተኛው ወፍ ዘራሽ ይመስላል መቶ የሚጠይቀው ሰው አይቼ አላውቅም በመሆኑም የሚወስደው አልያም የሚሄድበት ስላልነበረ መቄዶንያ የአረጋውያን ብሎም የአዕምሮ በሽተኞች መርጃ ማዕከል በሆስፒታሉ ጥሪ መሰረት ተልኳላ ከሳምንት ቆይታ በኋላ ግን መቆየት እንዳልቻለ ሰማን እዮብ ወማርያም ሞተ የሩቅ ራዕይና አላማ ይዞ ድምፃዊ ሊሆን የነበረው እዩካ ልሳኑ ተዘጋ ሞተ መሪር ሀዘን ነው የተሰማኝ እርግጠኛ ሆጃ ነው የምነግራችሁ ድምፃዊ የምታደንቁ በሙሉ አንድም ስራው ሳይሰጣችሁ በማረፉ ከስራችኋል በቢረጋ ወጻዲቅ አጃቢነት በደንበኛዬ አራት ቁጥር ታርጋ በለጠፈች አንቡላንስ ተጭኘሄ የአንድ ወር መድኃኒቶቼን በመሸከፍ ኮተቤ ጤና ጣቢያ አስረክቦኝ ወደ ቤቴ ገብቻለሁ በየእለቱ ጤና ጣቢያው ድረስ በመሄድ መርፌዬን መወጋት አስራ ሁለት ኪኒኖችን መዋጥ ጀምሬያለሁ ምሽት ላይ ሁተል በውሃ በጥብሙጨ የምጠጣው ተጨማሪ መድኃኒት ይዢ ቀን ስሰራ እውላለሁ ሌሊቱን እንደእናንተው እተኛለሁ አንድ ወር ተመርቆልኝ ዘጠኝ ወራት ካፕሮማይሲን ተወጋሁ ተከታታይ ወር የሚዋጡ ኪኒኖችን ሰለቀጥኩ በወር አንድ ጊዜ ያለማቋረጥ ሆስፒታል በመሄድ አጠቃላይ ምርመራ አደርግ ነበር በእነኝህ ሁሉ የህክምና ወቅት የወሰድኳቸውን መድኃኒቶች በአጋዥነት የተሰጡኝ ትቼ ሒሳብ መስራት ጀመርኩ በ ወራት ጊዜ ውስጥ መርፌ ተወጋሁ ለ ወራት የሚዋጡ ኪኒኖችን የሚበጠበጡ ዱቄቶችን ለተከታታይ ወራት ያለማቋረጥ ሰው ሰራሽ ኦክስጂን ወራት ከአልጋ ላይ አለመነሳትን አልፌ አሁን በመልካም ጤንነት ላይ አገኛለሁ በተደጋጋሜ የውስጥ አካላቶቼን ልብ ኩላሊት ጉበት ጨጓራ ሳንባ ሌሎች ሌሎችንም ምርመራ አድርጌያለሁ ፍፁም ፍፁም ምንም የህመም አይነት የሌለኝ ጤነኛ ነኝ መድሀኒቶቹ የተለያዩ የጎንዮሽ ጉዳት ይዘው የሚመጡ ቢሆንም በሀኪሞቻችን ያላሰለሰ ጥረት አብዛኛዎቻችን በተሳካና በሰላማዊ ሁኔታ አጠናቀናል ይሁንና ግን አንዳንዶች የጆሮ መስማት አልያም የአይን ዕይታ መቀነስ እልያም ቀለሞችን መለየት ከፊሎች ደግሞ የጨጓራ ካልሆነም አንዱ የሰውነት ክፍል ተጎድቶ አይተናል እኔ በአሪፍ ጤንነት ላይ ብሆንም ያለፉትን የዕድሜ ዘመኔን ስኖርበት የነበረውን የቆዳዬን ቀለም ጥቁር ሆኖአል በመስታወት መልኬን ማየት ከረሳሁ ሰንብቻለሁ ፀጉር ቤት ስጠቀም ብቻ ነው የማስተውለው ቢሆንም ግን በረዥም ጊዜ መለያየት በኋላ የማገኛቸው የጥንት ወዳጆቼ መጥቆሬን ሲነግሩኝ አዲስ ይሆንብኛል የሆነ ቀን ለአንድ ጉዳይ ኢሚግሬሽን ሄጄ ከምሳ መልስ ወደ ግቢው ለመዝለቅ ትርምስ በመፈጠሩ ከአንድ ረድፍ ሰልፍ እንድንይዝ ታዘዝንና የተምታታ መስመር ሰራን ስርዓት ሲያስጠብቅ የነበረው ፌደራል ፖሊስ ተስተካከሉ ከጥቁሩ ሰውዬ በኃላ ተሰለፉ ብሎ ሲናገር የተባለውን ሰው ለማረጋገጥና ለማስተካከል ዞር ብል ሁሌም ከኔ በኃላ ለመሰለፍ መረባረብ ጀመሩ ለካ ጥቁሩ ሰው እኔ ነበርኩ ምድርን ቀለም ቀይሬ በጥቁሩ መኖር ቀጥያለሁ።

  • N.B. This Summary is Very Experimental!! based on the following scripts from:
    • https://github.com/millzon/textSummarizer-am
    • https://github.com/icoxfog417/awesome-text-summarization#motivation
Download Searchable PDF Download PDF

Comments:


memezon

Download options | Convert to Pdf | Book of the day

© dirzon | Terms of Service | Privacy | About | Services | Contact