Detecting...

Please whitelist dirzon to continue.

or subscribe for ad-free contenct.

dirzon
  • تحويل إلى قوات الدفاع الشعبي
  • قائمة القراءة
  • مختصر
  • كتاب مسموع
  • بحث
  • تحميل
  • myzon
  • تسجيل الدخول
  • تسجيل
English  አማርኛ  Français  العربية
كتاب اليوم

የራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ አዋጅ.pdf


  • word cloud

የራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ አዋጅ.pdf
  • Extraction Summary

አዋጅ ቁጥር ነው። ወርድ ማለት የራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲውን ፕሬዝዳንት ማማከር ነው። የመሸጋገሪያ ድንጋጌዎች ማንኛውም ዩኒቨርሲቲ ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲው ይተላለፋል።

  • Cosine Similarity

አዋጅ ቁጥር የራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ አዋጅ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ነጻ ሆነው እንዲሰሩ ማድረግና በሁሉም ስራዎቻቸው ላይ በራሳቸው እንዲወስኑ ማድረግ ለተቋማቱ ውጤታማነትና ብቃት መሻሻቫል ለአገር እድገት ብቃት ያለው የሰለጠነ የሰው ሀብት ለማፍራት በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪነትን ለመገንባት ያላቸውን ትልቅ አስተዋጽኦ በመረዳት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ጥልቅ በሆነ የመማር ማስተማር እና የምርምር ሥራ የዳበረ ዕውቀት የሚገኝባቸው የፈጠራ ሀሳብና ሥራ የሚስፋፋባቸው በማኅበረሰብ ጉድኝት ለሕብረተሰቡ ተገቢውን የጤናና ሌሎች አገልግሎቶች ጥራቱን ጠብቆ በሰፊው የሚሰጥባቸው ይሆኑ ዘንድ ለሰው ልጆች ዕድገትና ልማት የተሰለፉና ሥራቸውንም በሙሉ ነፃነት የሚያከናውኑ ተመራማሪዎችን መምህራንን ሠራተኞችንና ተማሪዎችን ያቀፉ ተቋማት አድርጎ እንደገና ማደራጀት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የራሳቸውን የገቢ ምጮችን በማስፋፋት ገቢያቸው እንዲያሳድጉ ማድረግ በመንግስት ላይ ያለውን የፋይናንስ ጫና ቀስ በቀስ እንደሚቀንስ በመታመኑ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ከላይ የተዘረዘሩትን ዓላማዎች ለማሳካት እንዲያስችላቸው ለተሻለ የአካዳሚሟያዊ የፋይናንስና የአስተዳደር ነፃነቶች የራስገዝ እንዲሆኑ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ እና አዲስ ራስ ገዝ ዩሂቨርሲቲ ሊቋቋም የሚችልበትን ሥርዓት መዘርጋት በማስፈለጉ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪኾብሊክ ሕገመንግሥት አንቀጽ መሠረት የሚከተለው ታውጄጀል ክፍል አንድ ጠቅላላ ድንጋጌዎች አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ ስለራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ ለመደንገግ የወጣ አዋጅ ቁጥር ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ትርጓሜ የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚሰያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ አዋጅ ውሰጥ የአካዳሚያዊ ማኅበረሰብ ማለት ሁሉም የራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎችና የአካዳሚክ ሠራተኞች ማለት ነው ሚኒስቴር ወይም ሚኒስትር ማለት እንደቅደም ተከተሉ የትምህርት ሚኒስቴር ወይም ሚኒስትር ነው የአካዳሚያዊ ኃላፊ ማለት በራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲው የውስጥ መመሪያ መሠረት የተሰየመ የአካዳሚክ ሥራ መሪ ማለት ሲሆን የዩኒቨርሲቲውን ሬጂስትራር እና ላይብረሪያን ይጨምራል አካዳሚያዊ ሠራተኛ ማለት በማስተማር በምርምር እና በማኅበረሰብ ጉድኝት የተሰማራ የራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲው ሠራተኛ ማለት ነው አካዳሚያዊ ነፃነት ማለት የአካዳሚክ ሠራተኞችና ተማሪዎችራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲውና የትምህርት ክፍሎች የመማርማስተማር የምርምርና የማኅበረሰብ ጉድኝት ሥራቸውን በሚያከናውኑበት ጊዜ ከማንኛውም መንግስታዊ ፖለቲካዊ ማህበራዊና አስተዳደራዊ ተፅዕኖ ጣልቃ ገብነት ነፃ ሆነው መሥራት የሚያስችላቸው ሁኔታ ማለት ነው የአስተዳደር ሠራተኛ ማለት ከአካዳሚያዊ ከቴክኒካልና ክሊኒካል ሠራተኛ ውጭ የተቀጠረ የራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲው ሠራተኛ ማለት ነው ራተኛ ማለት የአካዳሚያዊ ሰራተኛ የአስተዳደር ሰራተኛ እና ሌላ የራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲው ሰራተኛ ተብለው የማሜለይ ሰራተኛ ነው። በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ መሰረት የሚቋቋም ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ በከፍተኛ ትምህርት አዋጁ መሰረት የተቋቋመ የመንግስት ዩኒቨርሲቲ ወይም አዲስ ዩኒቨርሲቲ ሊሆን ይችላል። ትምህርትና ስልጠና ጥናትና ምርምር የማህበራዊ ጉድኝት ስራዎችን ማከናወን የከፍተኛ ትምህርት ዓላማዎችና መሪ እሴቶችን የሚያከብር የትምህርትና ምርምር ተቋም መሆኑን ማረጋገጥ የትምህርት ፕሮግራሞችን የመቅረጽ የከፍተኛ ትምህርትን የመስጠት በአገሪቱ ፍላጎት ላይ በበመመስረት በእውቀት በክህሎት እና በአመለካከት የታነፁ ምሩቃንን የማፍራት እና የተለያዩ የትምህርት ማስረጃዎችን የመስጠት በማስተማሪያ ሆስፒታሎች የጤና አገልግሎት መስጠት መዋቅሩን እንደስፈላጊነቱ እንደገና ማደረጀት የአካዳሚ አሀዶችን መመሥረት ማዋሀድና ማፍረስ በዚህ አዋጅ መሰረት በሚያወጡት መስፈርት መሰረት ተማሪዎችን መቀበል የአዎንታዊ እርምጃ ፖሊሲ መቅረጽና ተግባራዊ ማድረግ ለየት ያለ ተሰጥዖና የላቀ ውጤት ሳላቸው ተማሪዎች ነጻ የትምህርት ዕድል መስጠት የአካዳሚያዊ ሰራተኛን አለምአቀፍ የሰራተኛ መብቶች ስታንዳርድ እና አሰራርን መነሻ በማድረግ ቦርዱ በሚያወጣው መመሪያ መሰረት መቅጠር ማሰናበት ማስተዳደር አካዳሚያዊ ያልሆነ ሰራተኛን በአሰሪና ሰራተኛ ህጉ መሰረት መቅጠር ማሰናበት ማስተዳደር በዚህ አዋጅ መሰረት የግዢ የንብረት አስተዳደር እና የፋይናንስ ስርዓት በሚወጣው መመሪያ መሰረት መዘርጋት አካዳጓሚያዊ መጽሔቶችን የዜና መጽሔቶች እና የመጽሐፍት ማዕከላትን ማቋቋም መንግሥታዊም ሆኑ መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር ትብብር መፍጠር የስፖርት መዝናኛና ሥነጥበብ ማዕከላትን ማቋቋምና ማጎልበት የተቋቋመበትን ዓላማ ለማሳካት የሚያስችለውን የገቢ ማስገኛ ስራዎች በዚህ አዋጅ እና አግባብ ባላቸው ህጎች መሰረት መስራት ገቢውን ለተቋቋመለት ዓላማ ማዋል ለሚሰጠው አገልግሎት በቦርድ በሚወጣ መመሪያ መሰረት የአገልግሎት ክፍያ ማስከፈል ገቢውን ማስተዳደር እና ለተቋቋመለት ዓላማ ማዋል የስራ እቅድ እና በጀት ማዘጋጀት እና በቦርዱ ሲፀድቅ ተግባራዊ ማድረግ ከመንግሥት የሚያገኘውን ማንኛውንም ድጋፍ ለተደረገለት ዓላማ ማዋል ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ወይም ለህብረተሰቡ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ግለሰቦች ዕውቅና ሽልማት ወይም የክብር ዲግሪ መስጠት የተማሪዎች የሥነምግባር ደንብ ማውጣት የዲሲፕሊን እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችል የአሰራር ሥርዓት መዘርጋት የተቋቋመበትን ዓላማ ከግብ ለማድረስ የሚያሰችሉትን ሌሎች አስፈላጊ ተግባሮች ማከናወን ክፍል ሁለት መዋቅራዊ አደረጃጀትና አስተዳደር የራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ አደረጃጀት ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ የሚከተሉት አካላት ይኖሩታል ቻንስለር የሥራ አመራር ቦርድ ፕሬዚዳንት እና ምክትል ፕሬዚዳንቶች ሴኔት የራስ ገዝ ዩሂቨርሲቲ ካውንስል የማኔጅንግ ካውንስልና ኤግዚክዩቲቭ ኮሚቴ ተጠሪነታቸው ለቦርድ የሆኑ የጥራት ማረጋገጫ ክፍል እና የውስጥ ኦዲት ክፍል ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲው እንደአስፈላጊነቱ የሚያደራጃቸው ሌሎች ክፍሎች ቻንስለር ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲው በውስጥ አስተዳደሩ ውስጥ ሳይገባ በአገር ውስጥም ሆነ በአለምዐቀፍ ደረጃ የራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲውን ስራና መልካም ስም የሚያጎላ እንደ ከፍተኛ አምባሳደር የሚሜያገለግል ሀብት የሚያፈላልግ እና ሌሎች በጎ ተግባራትን የሚያከናውን ቻንስለር ይኖረዋል። በቦርድና በሴኔት የሚፀድቁና የሚወሰኑ መመሪያዎችንፖሊሲዎችን እና ሌሎች አስፈላጊ ሰነዶችን አዘጋጅቶ ማቅረብ ይሆናል ኤግዚክዩቲቭ ኮሚቴ የራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንትምክትል ፕሬዝዳንቶች በምክትል ፕሬዝዳንትነት ማዕረግ የተለዩ የኮሌጅና የኢሂስቲትዩት ኃላፊዎች አባላት ያሉት ኤግዚክዩቲቭ ኮሚቴ ይቋቋማል የኮሚቴው ተግባርና ኃላፊነት በቦርድ ይወሰናል ምክትል ፕሬዝዳንቶች ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲው ተጠሪነታቸው ለፕሬዝዳንቱ የሆነ ምክትል ፕሬዝዳንቶች እና በምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ የሚለዩ ኃላፊዎች ይኖሩታል ምክትል ፕሬዚዳንቶች ከአካዳሚያዊ ሰራተኞች በውድድር የሚመረጡ ይሆናል ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲው የሚኖሩት የምክትል ፕሬዝዳንቶች ብዛትና ተግባር እና ኃላፊነታቸው በቦርዱ ይወሰናል ምክትል ፕሬዝዳንቶች ኮሌጆችና ትምህርት ክፍሎች በተሳተፉበት ምልመላና ምርጫ የሜሾሙ ሲሆን ዝርዝሩ ቦርዱ በሚያወጣው መመሪያ ይወሰናል የምክትል ፕሬዝዳንት የስራ ዘመን አራት አመት ሆኖ ለተጨማሪ አንድ የሥራ ዘመን ብቻ ሊወዳደር ይችላል ሌሎች ኃላፊዎች ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲው እንደአስፈላጊነቱ የኮሌጅ ኃላፊዎች ኦፊሰሮች ዳይሬክተሮች ሬጅስትራር እና የተለያዩ የትምህርት የምርምር የማህበረሰብ ጉድኝት እና የአስተዳደር ክፍል ኃላፊዎች ይኖሩታል በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ የተጠቀሱት ኃላፊዎች የአመራረጥ ሥርዓት ተግባርና ኃላፊነት የስራ ዘመንና ጥቅማ ጥቅም ቦርድ በሚያወጣው መመሪያ ይወሰናል ክፍል ሦስት አካዳሚያዊ እና ተቋማዊ ነጻነት አካዳሚያዊ ነጻነት ማንኛውም ራስገዝ ዩኒቨርሲቲ በተልዕኮውና በዓለም አቀፍ መልካም ልምድ መሰረት አካዳሚያዊ ነፃነት ይኖረዋል ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲው አካዳሚያዊ ነጻነቱን ከዚህ አዋጅ ድንጋጌዎች ወይም ከዓለም አቀፍ በጎ ልምድ ጋር በተጣጣመ መልኩ መተግበር አለበት። የራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲው ነፃነት በዚህ አዋጅ አንቀጽ የተጠቀሱትን ተግባርና ኃላፊነቶች ያለምንም ጣልቃ ገብነት ማከናወንን ይጨምራል ራስገዝ ዩኒቨርሲቲው ነጻነቱን የሚተገብረው ህጋዊነትን ውጤታማነትን ቅልጥፍናን ግልጸኝነትን ፍትሃዊነትንና ተጠያቂነትን ባረጋገጠ መልኩ መሆን ይኖርበታል የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ እና ድንጋጌዎች በዚህ አዋጅ መሰረት በራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲው ሳይ የሚደረግ ክትትልና ቁጥጥርን የሚያስቀር አይሆንም። በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ መሰረት ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲው የሚያገኘው ገቢ ለራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲው ተልዕኮ ማስፈፀሚያ የሚውል መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ አጠቃቀሙ እና አስተዳደሩ መሰረታዊ የፋይናንስ መርሆዎችን መሰረት በማድረግ ቦርዱ በሚያወጣው መመሪያ ይወሰናል። የመሸጋገሪያ ድንጋጌዎች ማንኛውም ዩኒቨርሲቲ ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ ሆኖ ከተቋቋመ ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ ሆኖ ከመቋቋሙ በፊት በመንግስት የተመደበለት በጀት እና ሌላ ማንኛውም ቋሚ ሀብት ወደራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲው ይተላለፋል። ማንኛውም ዩኒቨርሲቲ ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ ሆኖ ከተቋቋመ ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ ሆኖ ከመቋቋሙ በፊት ዩኒቨርሲቲው ያለበት እዳ ወይም ግዴታ ወደራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲው ይተላለፋል።

  • N.B. This Summary is Very Experimental!! based on the following scripts from:
    • https://github.com/millzon/textSummarizer-am
    • https://github.com/icoxfog417/awesome-text-summarization#motivation
Download Searchable PDF Download PDF

تعليقات:


memezon

خيارات التنزيل | تحويل إلى قوات الدفاع الشعبي | كتاب اليوم

© dirzon | شروط الخدمة | خصوصية | حول | خدمات | اتصال