Detecting...

Please whitelist dirzon to continue.

or subscribe for ad-free contenct.

dirzon
  • Convertir en PDF
  • Liste de lecture
  • Abrégé
  • Livre audio
  • Chercher
  • Télécharger
  • myzon
  • S'identifier
  • registre
English  አማርኛ  Français  العربية
Livre du jour

የመንግስታት_ግንኙነቶች_የፖሊሲ_ማዕቀፍ.pdf


  • word cloud

የመንግስታት_ግንኙነቶች_የፖሊሲ_ማዕቀፍ.pdf
  • Extraction Summary

ጠፀ ያላቸውን ጉዳዮች የመንግስታቱ የትኩረት አጀንዳ እንዲሆኑ ማድረግ ሠ በመንግስታት መካከል የመረጃ ልውውጦች ሳይቋረጡ እንዲሳለጡ እንደ ድልድይ ሆኖ በማገልገል ግልፅነትና ተጠያቂነት እንዲሰፍን ማድረግ ረ በተመሳሳይ ጉዳዮች ዙሪያ የሌሎች ፌደሬሽኖች ልምዶችን በመቀመርና ከሀገሪቱ ነባራዊ ሁኔታዎች ጋር በማጣጣም ጥቅም ላይ እንዲውሉ ሃሳብ ማቅረብ ሰ በግንኙነቶች ዙሪያ ቀጣይነት ያለው የጥናትና ምርምር ስራዎችን የሚያካሂዱ ግንኙነቶችን የሚመለከቱ የህትመትና የሰነዶች ስርጭት ስራዎችን የሚያከናውኑ የግንኙነቶችን አፈፃፀምና ውጤታማነትን በተመለከተ ለሚዲያና ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ወቅታዊ መረጃዎችንና ማብራሪያዎችን የሚሰጡ እንዲሁም የፎሮሞችን ስብሰባዎች አመቻች በመሆን የሚያገለግሉ ይሆናሉ በመሆኑም በክልል ፕሬዚዳንት ጽቤት ስር እነዚህ ቋሚ የግንኙነት ሴክረታሪያት የመድረኮችን ውጤታማነት በመከታተል ግንኙነቶችን የተመለከቱ የዳሰሳ ጥናቶችን በማካሄድ የአፈፃፀም ሪፖረቶችን በማዘጋጀትና የማሻሻያ ሃሳቦችን በማከል ለሀገር አቀፍ የሕግ ተርጓሚ ሠ አካላት ፎረም እንዲደርስ ያደርጋል በዚህም መልኩ የሶስቱ የመንግስት አካላት የግንኙነት ፎረሞች መስተጋብር እንዲጠናከር ይደረጋል ማዕቀፉ የሚፀድቅበት አግባብ ይህ የመንግሥታት ግንኙነት የፖሊሲ ማዕቀፍ በስራ ላይ የሚውለው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ተላልፎ ሲፀድቅ ይሆናል አፈፃፀም ይህ ማዕቀፍ ከፍ ብሎ በተጠቀሳ አግባብ የግንኙነት ማዕቀፍ ሆኖ እንዲያገለግል በፌዴራልና በክልል መንግስታት አማካኝነት ሰፊ የግንዛቤ ማስፋፊያ ስራዎች ሊካሄዱ ይገባል።

  • Cosine Similarity

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የመንግስታት ግንኙነቶች የፖሊሲ ማዕቀፍ ሐምሌ ዓም አዲስ አበባ መግቢያ አገራችን ፌዴራላዊ የመንግስት አወቃቀር መከተል ከጀመረች ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ አስቆጥራለች በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ኢፌዲሪ ሕገመንግስት አንቀፅ እና መሰረት የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ በፌዴራል መንግስትና በክልሎች የተዋቀረ መሆኑን ስልጣናቸውም በሕገመንግስቱ መወሰኑ የፌዴራል መንግስትና ክልሎች የተናጠል እና የጋራ ስልጣንና ሃላፊነቶች የተሰጧቸው መሆናቸውን በግልፅ ተደንግገው ይገኛሉ እነዚህ ስልጣንና ሃላፊነቶች ተዘርዝረው የተቀመጡ ቢሆኑም በርካታ መወራረስና መደራረብ የሚታይባቸው በዚህ ምክንያትም ተቀራርቦና ተናብቦ መስራትን እንዲሁም የጋራ ፖሊሲና ስትራተጂዎችን በመንደፍ ቅንጅታዊ አሰራርንና አፈፃፀምን የሚጠይቁ ናቸው በሃገራችን ዘላቂ ሰላም ማስፈን ዋስትና ያለው ዴሞክራሲን ማረጋገጥ ፈጣን ኢኮኖሚያዊ ልማትን ማስቀጠል እና አንድ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማህበረሰብን መገንባት የሚሉ ዓላማዎችና ራዕዮች በኢፌዴሪ ሕገመንግስት መግቢያ ላይ በግልፅ ሰፍረዋል ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ስርዓታችን እነዚህን ዓላማዎች ለማሳካት የሚገነባ መሆኑን የኢትዮጵያ ህዝቦች ያለ አንዳች ተፅዕኖ በራሳቸው ፈቃድ እንደ አንድ ማህበረሰብ አብረው ለመቀጠልና ለመበልፀግ መወሰናቸውን ያመለክታል ከዚህ በተጨማሪ ሁሉም ክልሎችና የኢትዮጵያ ህዝቦች በጋራ ማደግና መጠቀም እንደሚገባቸው እንዲሁም በተለየ አጋጣሚ በዕድገት ወደ ኋላ የቀሩትን ክልሎችና ማህበረሰቦች የተቀናጀ ድጋፍ በመስጠት ከስርዓቱ የሚገባቸውን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ማግኘት እንዳለባቸው በሕገ መንግስታችን ተደንግጓል እነዚህ ዓላማዎች ተግባርና ሃላፊነቶች በተናጠል ጥረት የሚሳኩ ሳይሆኑ የፌዴራልና የክልል መንግስታት ዓቅሞቻቸውን በማስተባበርና በማቀናጀት ለመፈፀም የሚያስችሏቸውን ግንኙነቶች ማካሄድ ሲችሉ ነው ፌዴሬሽኑ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ የተጠቀሱትን የጋራ ዓላማዎች ለማሳካት እንዲሁም ለጋራ የተሰጡትን ስልጣንና ሃላፊነቶች በብቃት ለመወጣት በፌዴራል እና በክልል መንግስታት መካከል እንዲሁም በክልል መንግስታት ጋር በርካታ ግንኙነቶችን ሲካሄዱ ቆይተዋል በእነዚህ መንግስታት መካከል የርስ በርስ ምክክሮች ስምምነቶችና ትብብሮች መካሄዳቸው ከስርዓቱ ባህሪ የሚመነጭና ለስርዓቱ ጤናማነት የሚፈለግ ትስስር ነው በግንኙነቶቹ አማካኝነት በርካታ የጋራ ፕሮግራሞች ተቀርፀው ተግባራዊ ተደርገዋል ለስርዓቱ ቀጣይነት ተፈላጊ የሆኑ የጋራ አስተሳሰቦች እየተያዙ እንዲመጡ የግንኙነቶቹ አስፈላጊነትና ፋይዳም እያደገ እንዲመጣ የነበራቸው አስተዋፅኦ የሚናቅ አይደለም ሆኖም እስከ አሁን ሲካሄዱ የነበሩ የግንኙነት ልምዶች በርካታ ክፍተቶችና ተግዳሮቶች ነበሯቸው በሂደቱ የታዩትን ተግዳሮቶች ለማረምና ክፍተቶችን መሟ ለመሙላት እንዲሁም ጥንካሬዎችን ለማስቀጠል የሚያስችል ጠንካራ የግንኙነት ተቋማዊ ስርዓት መፍጠርና መዘርጋት ያስፈልጋል በመሆኑም የሃገራችንን የግንኙነት ስርዓት የሚመራበት ማዕቀፍ ማዘጋጀት በማስፈለጉ ካለፈው የራሳችን ልምድ ጠንካራና ደካማ ጎኖች በመማር እና ከሌሎች ፌዴራል ሃገሮች ልምዶች በመቅሰም በኢፌዴሪ የመንግሥታት ግንኙነት የፖሊሲ ማዕቀፍ መነሻ ሰነድ እንደሚከተለው ቀርቧል የመንግሥታት ግንኙነት ፅንሰሃሳብ ፌዴራላዊ አወቃቀር በስልጣን ክፍፍል ላይ የተመሰረተ የራስ አስተዳደርና የጋራ አስተዳደርን ያጣመረ ስርዓት ነው የመንግስታት ግንኙነት ፌዴራላዊ ስርዓተ መንግስት ከሚገለፅባቸው መሰረታዊ ባህሪያት አንዱ ነው ይህ ግንኙነት በፌዴራል ስርዓት ውስጥ ሕግ የማውጣት የመፈፀም የመተርጎምና ገቢን የመሰብሰብ ስልጣን የተሰጣቸው የፌዴራልና የክልል መንግስታት እንዲሁም ተቋሞቻቸው በጋራ ወይም በጣምራ በተሰጣቸው ስልጣንና በሚያገናኙዋቸው ጉዳዮች ላይ የሚመሰርቱት መደበኛና መደበኛ ያልሆነ የግንኙነት ስርዓት ነው በመንግስታቱ መካከል ያለውን የማይወገድ ነገር ግን ውስብስብና መረዳዳትን የሚሻ የጋራ ስልጣንና ሃላፊነት በአጋርነት ላይ በመመስረት የፖሊሲ የስትራቴጂና የዕቅድ ቀረፃና ትግበራ ቅንጅትንና የአፈፃፀም ትብብርን ተቋማዊ በሆነ መንገድ ለመምራት የሚሜፈጠር የግንኙነት ማዕቀፍ ነው ይህ የግንኙነት ማዕቀፍ ውጤታማ ለማድረግ በሚያስችሉ የተለያዩ ተቋማት እና የግንኙነት ፎረሞች የተዋቀረ እንዲሁም የግንኙነቶቹ ዓላማዎች መርህዎችና አሰራሮች ስትራተጂዎች እና ሂደቶች ያካተተ ስርዓት ነው በአጭሩ የመንግስታት ግንኙነት በፌደራላዊስርዓተ መንግስት ውስጥ የሚኖሩ ሃገራዊ እና ከባቢያዊ ዓላማዎች ሚዛናቸውን ጠብቀው እንዲፈፀሙና ስርዓቱ ጤናማ ሆኖ እንዲቀጥል የሚያደርግ ማዕቀፍ ነው የግንኙነት ተቋማዊ ስርዓትን ስንመለከት በሶስት መንገዶች እያደገ እንደመጣ ከሌሎች ፌዴራል ሃገሮች ልምዶች መረዳት ይቻላል አንደኛው ሕገመንግስታዊ የግንኙነት ድንጋጌ እንዲኖር ማድረግ ነው ይህ ሲባል የግንኙነቶች ዓላማዎች ስትራተጂዎች መርህዎችና ሂደቶች እንዲሁም የግንኙነት ስርዓትን የሚያሳልጡ የሚከታተሉና የሚቆጣጠሩ አደረጃጀቶችና ፎረሞችን በተመለከተ በሕገመንግስት በግልፅ በማመላከት ከፌዴራላዊ ስርዓቱ ምስረታ ጊዜ ጀምሮ በማዕቀፉ መሰረት እንዲመራ ይደረጋል ሁለተኛው መንገድ የግንኙነት ስርዓትን በመደበኛ ሕግ ማጠናከር ነው በሕገመንግስት የሚሰጡ የጋራ ስልጣኖችንና በሂደት የሚከሰቱ ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ይዘት ያላቸው ለውጦችንና የጋራ አጀንዳዎችን ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመምራት መደበኛ የግንኙነት ተቋማዊ ስርዓትን መፍጠርና ማጠናከር አስፈላጊነት በጉልህ እያደገ ይመጣል ከዚህ በመነሳት የግንኙነት ስርዓቱ በመደበኛ ህግአዋጅ አማካኝነት ወደ መደበኛ ተቋማዊ ስርዓት ነ ከፍ እንዲል ይደረጋል ሶስተኛው ደግሞ በዕለት ተዕለት አፈፃፀም በተገኘ ልምድ ግንኙነቱ ተቋማዊ የማድረግ አስፈላጊነት እየጎላ ሲመጣ ቀላል በሆነ አሰራር ማለትም በመግባቢያ ሰነድ የጋራ ዕቅድ በመንደፍ እና የማስፈፀሚያ ሰነድ በመፈራረም ግንኙነቱ መደበኛ ሆኖ በቋሚነት እንዲቀጥል ይደረጋል በፌዴራላዊ ስርዓተመንግስት ውስጥ የመንግስታት ግንኙነትን ተቋማዊ የማድረግ አስፈላጊነት ከበርካታ ምክንያቶች የሚመነጭ ሲሆን ጥቂቶቹ የሚከተሉት ናቸው አንደኛው ውጤታማነትን ይመለከታል ፌዴራል ስርዓት የመንግስትን ስልጣን በፌዴራልና በክልሎች መካከል የሚከፋፈልበት አወቃቀር በመሆኑ እነዚህ መንግስታት ለጋራ በተሰጣቸው ስልጣን ላይ ውጤታማ አፈፃፀም ሊከተሉ ይገባል በመሆኑም የተናጠል ፍላጎታቸውን የሚያቀራርቡ ፖሊሲዎች ስትራቴጂዎች ፕሮግራሞችና ዕቅዶች እንዲያወጡና የተቀናጀ አፈፃፀም እንዲኖራቸው የግንኙነት ስርዓት ተቋማዊ ማድረግ አስፈላጊ ያደርገዋል ሁለተኛው ሃገራዊ ዓላማዎችና ፕሮግራሞች ከክልሎችና ከባቢያዊ አስተዳደሮች ፍላጎቶችና ዕቅዶች ጋር በማጣጣም ለማስፈፀም የሚያስችል መደበኛ የግንኙነት ተቋማዊ ስርዓት መፍጠር አስፈላጊ ያደርገዋል ሶስተኛው መነሻ አለመግባባቶችን በዴሞክራሲያዊ የድርድርና መተሳሰብ መንገድ ለመፍታት ነው በስልጣን መደራረብና መነካካት ምክንያት እና በስርዓቱ ባህሪ በሚፈጠሩ አዳዲስ እድገቶችና ክስተቶች ምክንያት በመንግስታቱ መካከል ቀድሞ ያልነበሩ የዓላማና ፍላጎት ለውጦች በማስከተል አለመግባባትና የይገባኛል ጥያቄዎች መከሰታቸው የማይቀር ነው በመሆኑም እነዚህን በጋራ ተወያይቶ ለመፍታት እንዲሁም ስርዓቱ ለአዳዲስ ለውጦች በሚመጥን መንገድ በትብብር ለመምራት እና ጥራትና ውጤታማ የፖሊሲ ስትራተጂና ዕቅድ አፈፃፀም ልምዶችን ለመለዋወጥ መንግስታቱን የሚያገናኝ መደበኛ ስርዓት መዘርጋት አስፈላጊ ይሆናል አራተኛው ጉዳይ የመቻቻል የመተባበርና የመተጋገዝ ባህል በማጎልበት በልዩነት ውስጥ ያለውን አንድነት ለማጠናከር የግንኙነት ስርዓቱን ተቋማዊ ማድረግ አስፈላጊነት ጉሊህ ያደርገዋል የማዕቀፉ ስያሜ አገራችን ፌዴራላዊ የመንግስት አወቃቀር የምትከተል በመሆኗ የመንግስታት ግንኙነት የፌዴራል ስርዓቱ አንዱ ገፅታ ሆኖ እየተሰራበት ይገኛል በፌዴራልና በክልል መንግስታት ባለስልጣናት እንዲሁም በባለሙያዎች መካከል በተለያዩ የጋራ ርዕሰጉዳዮች ላይ ውይይቶችና ምክክሮች ይካሄዳሌ እንዲሁም የጋራ ፕሮግራሞችና ዕቅዶች በጋራ እየተነደፉ ተግባራዊ ይደረጋሉ እነዚህ ግንኙነቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተበራከቱ በመምጣታቸው የሃገሪቱን ዕድገትና የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ለማጎልበት የተጫወቱት ሚና የሚበረታታ ነው ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ የሃገራችን የግንኙነት ስርዓት በርካታ ክፍተቶች ያሉበት እንደሆነም በተለያየ ጊዜ በተካሄዱ የዳሰሳ ጥናቶች ተረጋግጧል በመሆኑም የሃገራችን የግንኙነት ስርዓት እስከአሁን የነበሩትን የግንኙነት ጠንካራ ጎኖችን አጎልብቶ ለማስቀጠልና ውስንነቶቹንና ጉድለቶቹን ለማስተካከል ካለፈው ልምድ በተለየ መንገድ ተቋማዊ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ ይህ ተቋማዊ የግንኙነት ማዕቀፍ ተዘጋጅቷል በመሆኑም የግንኙነት ማዕቀፍ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የመንግስታት ግንኙነት የፖሊሲ ማዕቀፍ በሚል ስያሜ ይጠራል በኢትዮጵያ የመንግስታት ግንኙነት ማዕቀፍ አስፈላጊነት በሀገራችን ፌዴራል ስርዓት ውስጥ የመንሰግስታት ግንኙነት ተቋማዊ አስፈላጊ የሚያደርጉ ምክንያቶች ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው አንድ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማህበረሰብን የመገንባት የጋራ ዓላማ ለማሳካት በኢፌዴሪ ሕጉመንግስት መግቢያ የሰፈረው የፌዴራል ስርዓቱ ዓላማ በሀገሪቱ ውስጥ አንድ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማህበረሰብን መገንባት የሚል ነው ይህ ዓላማ እውን የሚሆነው በክልሎች አስተዳደር ውስጥ ሀገራዊ ራዕይና ዓላማዎች በማሳካት ዘላቂ ሰላም ፈጣን እድገትና ዋስትና ያለው ዴሞክራሲያዊ ስርዓት መገንባት ሲቻል ነው ይህ ሲባል ሃገር አቀፍ ስታንዳርዶችና የፖሊሲ ማዕቀፎች በሁሉም ክልሎች ተፈፃሚ መሆን ይኖርባቸዋል በክልሎች መካከል ተመጣጣኝ ዕድገት ማረጋገጥ ይገባል የሕግ ልዕልና መልካም አስተዳደርና የመንግስት አካላት ተጠያቂነት በፌደራል ደረጃና በሁሉም ክልሎች ተቀራራቢ አፈፃፀም ሊኖራቸው ይገባል በየጊዜው የሚከሰቱ የኪራይ ሰብሳቢነትና ሌሎች የስርዓቱ አደጋዎች በጋራ አቋምና የፖለቲካ ቁርጠኝነት መታገል ያስፈልጋል እንዲሁም የብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቃል ኪዳን ሳይዛነፍ ወንድማዊ ትስስራቸውና የጋራ ተጠቃሚነታቸው ማደግ ይኖርበታል ማለት ነው በመሆኑም ይህንን ዓላማ ለማሳካት የሚያስችል የጋራ የፖለቲካ ቁርጠኝነትና የአመራር ብቃት ለመገንባት በመንግስታቱ መካከል የሚካሄዱ ግንኙነቶች ይበልጥ ተቋማዊ ማድረግ ያስፈልጋል አለመግባባቶችና ግጭቶችን ለመፍታት የመንግስታት ግንኙነት ተቋማዊነትን ማጠናከር የፌዴራል ስርዓቱ የተመሰረተበት እምነትና የስርዓቱ መሰረታዊ መርሆች ተጠብቀው እንዲቀጥሉ ለማድረግ ያለው ፋይዳ የጎላ ነው ይሁን እንጅ ፌዴራል ስርዓቱ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ የስርዓቱን መሰረታዊ መርሆችንና እምነቶችን ያልተከተሉ አፈፃፀሞችንና አለመግባባቶች ተስተውለዋል እንዲሁም አልፎ አልፎ በተጎራባች ክልሎች ማህበረሰቦች መካከል ኢፌዴሪ ማለት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ማለት ነው ኢ ግጭቶች ሲከሰቱ ታይተዋል እስከ አሁን የነበረው ልምድ እንደሚያሳየው የሚከሰቱ ግጭቶችንና አለመግባባቶችን የመፍታት ጉዳይ የግጭቱ ተካፋይ ወገኖች ሃላፊነት እንደሆነ ከዚህ ካለፈ ደግሞ ለፌዴራል መንግስት የሚቀርብበት እንጂ ሌሎችን ክልሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው አድርጎ ያለመገንዘብ ችግር ይታያል ይልቁንም በሌላው ስልጣን ላይ ጣልቃ እንደመግባት የሚቆጠርበት ሂደት ነበር ስለሆነም እነዚህን የተሳሳቱ አመለካከቶች በማስተካከል የስርዓቱን መሰረታዊ መርሆችንና እምነቶች አስጠብቆ ለመቀጠል እንዲሁም አለመግባባቶችን የመፍታትና ዘላቂ ሰላምን የማስጠበቅ ዓላማ የሁሉንም መንግስታት የጋራ ዓቅምና የተቀናጀ አፈፃፀም የሚጠይቅ መሆኑን በማመን የፌዴራል ስርዓቱን የትብብር መርህ ወደ ላቀ ደረጃ ከፍ ለማድረግ ተቋማዊ የግንኙነት ስርዓትን መዘርጋት አስፈላጊ ይሆናል የማዕቀፍ ስልጣንና የጋራ ሃላፊነቶችን በብቃት ለመወጣት በዚህ ሰነድ መሰረት የማዕቀፍ ስልጣን የሚባለው በአንዳንድ የስልጣን ዘርፎች ተመሳሳይ ስልጣንና ሃላፊነት ለሁለቱም መንግስታት የተሰጠበት የስልጣን ክፍፍል ሆኖ ክልሎች በዘርፉ የሚያወጡዋቸውን ፖሊሲዎችና ሕጎች ከፌደራሉ ፖሊሲዎችና ሕጎች ጋር የተጣጣሙ እንዲሆኑ እንደ ማዕቀፍ ሆኖ የሚያገለግል ስልጣን ነው በዚህ መሰረት የኢፌዴሪ ሕገ መንግስት አንቀፅ የሀገሪቱን አጠቃላይ የኢኮኖሚ የማህበራዊና የልማት ፖሊሲ ስትራቴጂና ዕቅድ የማውጣትና የማስፈፀም ስልጣን ለፌዴራል መንግስት ሰጥቷል በተመሳሳይ መልኩ ክልሎችም በአስተዳደራዊ የስልጣን ወሰናቸው ውስጥ የማህበራዊና የልማት ፖሊሲዎች ስትራቴጂዎችና ዕቅዶች የማውጣትና የማስፈፀም ስልጣን ያላቸው መሆኑን በአንቀፅ ሐ ተደንግጓል በሕገመንግስቱ አንቀፅ መሰረት የፌደራል መንግስት የጤና የትምህርት የባህልና ታሪካዊ ቅርስ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሃገራዊ መመዘኛዎችንና መሰረታዊ የፖሊሲ መለኪያዎችን የማውጣት ስልጣን አለው የጋራ ስልጣንን በተመለከተ የፌደራል መንግስትና ክልሎች በጋራ በሚያቋቁሟቸው የልማት ድርጅቶች ላይ የንግድ ትርፍ ግብር የስራና የሽያጭ ታክስ የመጣልና የመሰብሰብ በከፍተኛ የማአድን ስራዎችና በማናቸውም የፔትሮሊየምና የጋዝ ስራዎች የገቢ ግብርና የሮያሊቲ ክፍያዎች በጋራ የመጣልና የመሰብሰብ እንዲሁም በድርጅቶች የንግድ ትርፍና በባለ አክስዮኖች የትርፍ ድርሻ ላይ ግብርና ሽያጭ ታክስ በጋራ የመጣልና የመሰብሰብ ስልጣን ያላቸው መሆኑን በአንቀፅ ተደንግጎ ይገኛል በመሆኑም የማዕቀፍ ስልጣኖች ከክልሎች ነባራዊ ሁኔታ ጋር ተጣጥመው እንዲፈፀሙ ማድረግ ያስፈልጋል የጋራ ስልጣኖች የእያንዳንዱን መንግስት ዓላማና ፍላጎት በሚያቀራርብ መንገድ በምክክርና ስምምነት መፈፀም አለባቸው የመንግስታት ግንኙነት እነዚህን ሃላፊነቶች መግባባት በሰፈነበትና ውጤታማ በሆነ መንገድ እንዲመሩና እንዲፈፀሙ ለማድረግ ተፈላጊ መሳሪያ ነው የዕቅዶች አፈፃፀምና የአገልግሎት አሰጣጥ ውጤታማነትና ቅልጥፍና ለማረጋገጥ እያንዳንዱ መንግስት የተሰጠውን ስልጣንና ሃላፊነት ለመወጣት የራሱን ዕቅድ በመንደፍ ይፈፅማል እንዲሁም በዘረጋው የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓት መሰረት የመንግስትን አገልግሎት ለህዝብ ያቀርባል ሆኖም አንዳንድ የስልጣን ዘርፎች በተናጠል በመስራት ምክንያት የወጪ መደራረብና የጊዜ ብክነት ያስከትላሌሉሌ ይህንን ኪሳራ ለማስወገድ በጋራ ተወያይቶ የተቀናጀ ዕቅድ መንደፍና መፈፀም ያስፈልጋል በአገልግሎት አሰጣጥ በኩልም ከኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዕድገት የሚመነጭ የተገልጋዮች ፍላጎት መለዋወጥና ማደግ የአገልግሎት አሰጣጥ ውስብስብነትን ስለሚያስከትል ከእነዚህ ለውጦችና ፍላጎቶች ጋር ተጣጥሞ የሚሄድ የአገልግሎት አሰጣጥ ስታንዳርድ በጋራ ተወያይቶ መንደፍና አዳዲስ አሰራሮችን መዘርጋት ያስፈልጋል በተጨማሪ ማንኛውም ተገልጋይ ከአንዱ አከባቢ ወደ ሌላ አከባቢ በመንቀሳቀስ አገልግሎት በሚጠይቅበት ወቅት በጊዜ በወጪና በጥራት ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት እንዲያገኝ ማድረግ ያስፈልጋል በመሆኑም ክልላዊ ሁኔታን በሚገባ ያገናዘበ ሆኖ ነገር ግን ዜጎች እና የውጭ ባለሃብቶች በሁሉም የሃገሪቱ አከባቢዎች በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት እንዲያገኙ ለማድረግ መንግስታት በመካከላቸው ያለውን የአገልግሎት አሰጣጥ ወውጡገባነት እና የጥራት ልዩነት ተስማምተው እንዲያስተካክሉ እንዲሁም ለአዳዲስ ለውጦች የሚመጥን የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓት እንዲዘረጉ ተቋማዊ የግንኙነት ስርዓት ሊኖራቸው ይገባል ምርጥ የአፈፃፀም ልምዶችን ለመለዋወጥ የፌዴራልና የክልል መንግስታት እስከ አሁን በነበረው ሂደት በየራሳቸው የስልጣን ወሰን የመንግስትን ስልጣንና ሃላፊነት ሲወጡ እና ሲያደርጉዋቸዉ በነበሩ ግንኙነቶችም ያካበቷቸው በርካታ ልምዶች አሌ ሆኖም አሁንም ስልጣንና ሃላፊነትን ከመወጣት አኳያ በፌዴራል መንግስትና በክልልች እንዲሁም በክልሎች መካከል በርካታ የአፈፃፀም ልዩነቶች ይታያሉ ከማስፈፀም ዓቅም አኳያ የፌዴራል ሀ መንግስት የተሻለ ጥንካሬ ያለው ሲሆን በክልሎቹ መካከልም ሰፊ ልዩነት ይታያል ስለሆነም እያንዳንዱ መንግስት የማስፈፀም ዓቅሙን ለማሻሻል በተናጠል ጥናቶችንና ስልጠናዎችን ማካሄድ ሳያስፈልገው አንዱ ያካበተው ልምድ በቀላሉ ወደ ሌላው ለማሸጋገር የሚያስችል ቀጣይነት ያለው የልምድ ልውውጥ መድረክ ሊኖር ይገባል ዖፇፇሃሦራ ዕናፍሪፇ ውጨታግሃያቅ ማረጋዎ ፌዴሬሽኑ ከተመሰረተ ጊዜ ጀምሮ መንግስታቱን የሚያገናኙ ጉዳዮች በጉልህ እየበዙና የግንኙነት ፍላጎቶች እየጨመሩ በመምጣታቸው በፌዴራል መንግስትና በክልሎች መካከል እንዲሁም ክልል ከክልል ጋር በተለያዩ የጋራ ርዕሰጉዳዮች ውይይቶችና ትብብሮች እየተካሄዱ ቆይተዋል በከፍተኛ ባለስልጣናት እንዲሁም በባለሙያዎች መካከል መደበኛና መደበኛ ያልሆኑ ግንኙነቶች እንዲበራከቱ የሚያስገድዱ ሁኔታዎች እየበዙና ጥልቀት እየጨመሩ መምጣታቸው የስርዓቱ መሰረታዊ ባህሪ የሚገልፅበት ነው ሆኖም የእነዚህ ግንኙቶች ውጤት ፌዴራላዊ ስርዓቱን ከማጠናከር አኳያ ያላቸው ፋይዳ እየተገመገመ ሊመራ ይገባል አንደኛ ግንኙነቶቹ በመሰረታዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መሆናቸውን ማረጋገጥ ያስፈልጋል ሁለተኛ የግንኙነቱ ሂደትና አፈፃፀም ከወጪና ከጊዜ አንፃር ውጤታማ መሆኑ ሊረጋገጥ ይገባል ሶስተኛ የግንኙነት ስርዓቱ በየጊዜው ለሚከሰቱ አዳዲስ ለውጦች ቀድሞ ለመተንበይ ፈጣን የመረጃ ልውውጥ ለማካሄድና መፍትሄ ለመቀየስ የሚያስችል መሆን አለበት አራተኛ በየደረጃው የተቋቋሙ የግንኙነት መዋቅሮች ግንኙነቱ የሚመራባቸውን መርህዎችና የአሰራር ስርዓቶች በጥብቅ እየተከተሉ መሆናቸውን ማረጋገጥ ያስፈልጋል በአጠቃላይ የግንኙነት ስርዓቱን ውጤታማነት ለማረጋገጥና በየጊዜው ለማሻሻል ተቋማዊ ማድረግ አስፈላጊ ያደርገዋል የግንኙነት ማዕቀፉ ሕገመንግስታዊ መሰረት የፌዴራል መንግስት ከክልሎችና ክልሎች እርስ በርሳቸው እየተገናኙ በጋራ አጀንዳዎች እንዲመክሩ ሕጋዊ መሰረት የሚሰጡ እና እየተካሄደ ያለውን ግንኙነት ወደተሻለ ደረጃ ከፍ እንዲል የሚያስችሉ ሕጋዊ መሰረቶች በሕገመንግስቱና በሌሎች የሃገሪቱ ፖሊሲዎችና ስትራተጂዎች ሰፍረው ይገኛሉ አንደኛውና ዋናው የመንግስታት ግንኙነት መሰረት የኢፌዴሪ ሕጉመንግስት ነው በመሆኑም ግንኙነቶች ተፈላጊ መሆናቸውን የሚያመላክቱና በፖሊሲ የተደገፈ የግንኙነት ስርዓት እንዲኖር የሚያስችሉ የሕጉመንግስቱ ድንጋጌዎች ጥቂቶቹ የሚከተሉት ናቸው መ የሕገመንግስቱ መግቢያ የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦች ህዝቦች በፊት የነበራቸውን የተዛባ ግንኙነት በማረም በተለያዩ መስኮችና የግንኙነት ደረጃዎች የጋራ ጥቅሞቻቸውን ለማሳደግና ዘላቂ ልማትና ዲሞክራሲን ለማረጋገጥ የሚያስችል አንድ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ማህበረሰብ ለመመስረት ቃል መግባታቸውን ይገልፃል በሕገመንግስቱ አንቀፅ የክልሎችን ወሰን በሚመለከት ጥያቄ የተነሳ እንደሆነ ጉዳዩ በሚመለከታቸው ክልሎች ስምምነት እንደሚፈታ የሚመለከታቸው ክልሎች መስማማት ካልቻሉ የፌዴሬሽን ምክር ቤት የህዝቡን አሰፋፈርና ፍላጎት መሰረት በማድረግ እንደሚወስን ይደነግጋል የኢትየጵያ ፌደራላዊ ዴሞክረሲያዊ ስርዓት በፌዴራል መንግስትና በክልሎች የተዋቀረ መሆኑን እያንዳንዱ መንግስት በአስተዳደራዊ ክልሉ ውስጥ የሕግ አውጪነት የሕግ አስፈፃሚነትና የዳኝነት ስልጣን ያለው መሆኑን ለፌዴራል መንግስት የተሰጠ ስልጣን በክልሎች መከበር እንዳለበት እና ለክልሎች የተሰጠ ስልጣንም በፌዴራል መንግስት መከበር ያለበት መሆኑን እንዲሁም የፌዴራል መንግስት ከተሰጠው ስልጣንና ተግባራት ውስጥ እንደ አስፈላጊነቱ ለክልሎች በውክልና ሊሰጥ እንደሚችል በሕገመንግስቱ አንቀፅ ንኡስ አንቀፅ ተደንግጓል የፌዴራል መንግስት የጤና የትምህርት የባህልና ታሪካዊ ቅርስ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሃገራዊ መመዘኛዎችንና መሰረታዊ የፖሊሲ መለኪያዎችን የሚያወጣ መሆኑን በክልሎች መካከል የሚካሄዱትን የንግድ ልውውጦችና ግንኙነቶች እንደሚመረምርና እንደሚቆጣጠር የህጉመንግስቱ አንቀፅ እና ይደነግጋል ከዚህ በተጨማሪ ፌዴራል መንግስትና ክልሎች ታክስና ግብር በሚጥሉበት ጊዜ በጎ ግንኙነታቸውን የማይጎዳ መሆኑን ማረጋገጥ እንዳለባቸው በአንቀፅ ተደንግጎ ይገኛል የፌዴራል መንግስት ለክልሎች የተመጣጠነ እድገት እንቅፋት ካልሆነ በስተቀር ለአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ ለመልሶ ማቋቋምና ለልማት ማስፋፊያ ብድርም ሆነ እርዳታ ለክልሎች ሊሰጥ እንደሚችል እንደዚሁም የፌዴራሉ መንግስት ክልሎች ለሚያስፈልጋቸው ወጪዎች የሚሰጠውን ድጎማ የመቆጣጠርና ኦዲት የማድረግ ሃላፊነት ያለው መሆኑን በአንቀፅ ተደንግጓል የፌዴራል መንግስትና ክልሎች በጋራ በሚያቋቁምዋቸው የልማት ድርጅቶች ላይ የንግድ ትርፍ ግብር የስራና የሸያጭ ታክስ እንደሚጥሉና እንደሚሰበስቡ በከፍተኛ የማአድን ስራዎችና በማናቸውም የፔትሮሊየምና የጋዝ ስራዎች የገቢ ግብርና የሮያሊቲ ክፍያዎች በጋራ እንደሚጥሉና እንደሚሰበስቡ እና በድርጅቶች የንግድ ትርፍና በባለ አክስዮኖች የትርፍ ድርሻ ላይ በጋራ ግብርና ሽያጭ ታክስ እንደሚጥሉና እንደሚሰበስቡ በአንቀፅ እንዲሁም በአንቀጽ ሆ ክልሎችና የፌደራሉ ጋ መንግስት የጋራ ተብለዉ የተመደቡ ገቢዎች በሁለቱ መካከል የሚከፋፈሉበትን ቀመር እንደሚወስን ተደንግጓል እነዚህ ድንጋጌዎች በፌዴራልና በክልል መንግስታት መካከል ከስርዓቱ መሰረታዊ ባህሪ የሚመነጩና የማይወገዱ ትስስሮች እንዳሉ የሚያሳዩ ለመንግስታቱ በሕገ መንግስት የተሰጠ የጋራ ስልጣን ብቻ ሳይሆን የተናጠል ስልጣኖቻቸውም አርስ በርስ የተወራረሱ በመሆናቸው በትብብርና በምክክር መስራት እንደሚገባቸው የሚያመሳክቱ ናቸው ሁለተኛው የመንግስታት ግንኙነት ፖሊሲ መነሻ የኢትዮጵያ የሰላም የዴሞክራሲ የልማትና የዓቅም ግንባታ የፖሊሲ ሰነዶች ናቸው ፖሊሲዎቹ በተሟላ መንገድ ተፈፃሚ የሚሆኑት ሁሉም መንግስታት እየተደጋገፉ የተቀናጀ አፈፃፀም ሲከተሉ እንደሆነም በሰነዶቹ በግልፅ ተጠቅሶ ይገኛል እነዚህ ድንጋጌዎች በመንግስታት መካከል እንዲሁም የህዝቦችን መቀራረብና መደጋገፍ በማጎልበት አንድ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማህበረሰብን ለመገንባት የሚረዳ ተቋማዊ የግንኙነት ማዕቀፍ የመኖር አስፈላጊነትን የሚያመላክቱ ናቸው ሶስተኛ በኢፌዴሪ ሕጉመንግስት አንቀፅ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት የተሰጡ ስልጣንና ተግባራት እንዲሁም በአዋጅ ቁጥር ላይ የተዘረዘሩት የምቤቱ ስልጣንና ተግባራት የግንኙነት መነሻ ድንጋጌዎች ተደርገው የሚወሰዱ ናቸው ከዚህ በተጨማሪ የፌዴራል መንግስት ለመጀመሪያ ጊዜ ለፌዴራል ጉዳዮች ሜኒስቴር በ ዓም በአዋጅ ቁጥር እና በድጋሚ በ ዓም በአዋጅ ቁጥር ዓም የፌዴራልና የክልሎች የመልካም ግንኙነት ማእከል በመሆን እንዲሰራ ስልጣን ሰጥቶታል ይህ አዋጅም የህጉመንግስቱን መሰረታዊ ዓላማዎችና የፌዴራል ስርዓቱን መሰረታዊ ባህሪ መነሻ ያደረገና ግንኙነቶች እስከ አሁን በተለምዶ ሲካሄዱበት የነበረውን መንገድ በማስተካከልና በማጠናከር ወደ ተሻለ ተቋማዊ ስርዓት ለማሸጋገር የሚረዳ ተጨማሪ ሕጋዊ መነሻ ነው ዓላማ የመንግስታት ግንኙነት ማዕቀፍ አጠቃላይ ዓላማ የሕጉመንግስቱን ድንጋጌ በማስጠበቅ አገርን መገንባት ኢትዮጵያዊ አንድነትንና የፌዴራል ስርዓቱን ማጠናከር ጠንካራ የሕዝቦችን ግንኙነትና ትስስር መፍጠር ሃገራዊ እና ክልላዊ ዕቅዶችና ፕሮግራሞች ሚዛናቸውን ጠብቀው እንዲፈፀሙ ማድረግ እንዲሁም በመንግስታት መካከል ያሉ የጋራ ጉዳዮችን በአጋርነት ላይ የተመሰረተ የአመራር መርሆ በማስፈን በጋራ የሚመሩበትና የሚመክሩበት በዚህም የስርዓቱን ቀጣይነት ለማረጋገጥ የሚያስችል ተቋማዊ ስርዓት መፍጠር ነው ይህ አጠቃላይ ዓላማ የሚከተሉትን ዝርዝር ዓላማዎች ያካተተ ነው በፌዴራልና በክልል መንግስታት መካከል እንዲሁም በክልል መንግስታት መካከል የጋራ ጉዳዩችን በተመለከተ ተቋማዊ የምክክርና የትብብር ማዕቀፍ እንዲኖር ማድረግ በፌዴራል መንግስትና በክልሎች መካከል እንዲሁም በክልሎች እርስ በርስ የሚከሰቱ አለመግባባቶችና ግጭቶች የሚፈቱበትን የግንኙነት ተቋማዊ ስርዓት መዘርጋትና ማጠናከር ዑ በየደረጃው የግንኙነት ስርዓቱን አፈፃፀምና ውጤታማነት ለማረጋገጥና ለመከታተል የሚያስችል አደረጃጀቶችን አሰራሮችን መርሆችን መፍጠርና ማቋቋም የሚሉ ናቸው የማዕቀፉ ተፈፃሚነት ወሰን የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የመንግስታት ግንኙነት የፖሊሲ ማዕቀፍ የጋራ ጉዳዩችን በተመለከተ በፌዴራል መንግስት በአባል ክልሎች በአዲስ አበባና በድሬደዋ ከተሞች ላይ ተፈጻሚ ይሆናል ይህ ግንኙነት የፌዴራልና የክልል መንግስታት የሕግ አውጪ የሕግ አስፈፃሚ እና የሕግ ተርጓሚ አካላት በየዘርፋቸው በተናጠል የሚያካሂዷቸውን ግንኙነቶች እና ሁሉም ክልሎች በጋራ የሚያገናኝ እንዲሁም እንደ አጀንዳዎች ስፋትና ጥልቀት ሁለት ወይም ከዛ በላይ ተጎራባች ክልሎች የሚገናኙበት የጎንዮሽ የግንኙነት ስርዓትን ያጠቃልላል ይህ ማዕቀፍ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገመንግስትን መሰረት ያደረገና በህገመንግስቱ የተደነገጉ የህዝቦች የአብሮነትና የጋራ ተጠቃሚሜነት ስምምነት እንዲሁም የሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ጥበቃና የማህበረኢኮኖሚ ዓላማዎች በተሻለ ደረጃ ለማስፈፀም መግባባት የሜደረስበትና የተባበረ አመራር የሚሰጥበት ማዕቀፍ ነው በዚህ ማዕቀፍ መሰረት የሚቋቋመ የግንኙነት አደረጃጀቶች ተግባርና ሃላፊነታቸውን ሲወጡ የህገመንግስቱን ልዕልና በማስጠበቅ ይሆናል በኢፌዴሪ ሕጉመንግስት ለፌዴራል መንግስትና ለክልሎች ተዘርዝረው የተሰጡ ስልጣንና ሃላፊነቶች የተጠበቁ ናቸው ስለሆነም በዚህ ማዕቀፍ መሰረት የሚካሄዱ ግንኙነቶች የሚቋቋሙ የጋራ ፎረሞች እና በተናጠልም ሆነ በጋራ የሚደራጁ የግንኙነት አሳላጭ አደረጃጀቶች ለጋራ በተሰጡ ስልጣንና ሃላፊነቶች እና መንግስታቱን በሚሜያገናኙ የሰላም የልማትና የዴሞክራሲ አጀንዳዎች ላይ የተመሰረቱ መሆን አለባቸው መሰረታዊ መርሆዎች በዚህ ማዕቀፍ መሰረት የፌዴራልና የክልል መንግስታት እንዲሁም የክልሎች የእርስ በእርስ ግንኙነቶች የሚከተሉትን መርሆዎች በጥብቅ በማክበርና በመከተል የሚካሄዱ ይሆናለሌ የሕገ መንግስትን የበላይነት ማክበር በዚህ የፖሊሲ ማዕቀፍ መሰረት የሚካሄዱ ግንኙነቶች የሕገመንግት የበላይነትን በማክበር ብቻ መመራት አለባቸው እኩልነት እና አሳታፊነት በዚህ የፖሊሲ ማዕቀፍ መሰረት የሚካሄዱ ግንኙነቶች የእኩልነት መርህን በማክበር የሚከናወኑ መሆን አለባቸው የፌዴራል መንግስትም ሆነ ክልሎች በሕጉመንግስት የተቋቋሙ እና አንዱ የሌላውን ስልጣን ማክበር ያለበት መሆኑን በማመን የግንኙነቱ ባለድርሻ አካላት በዚህ የአቻነት መንፈስ ግንኙነታቸውን ማካሄድ ይኖርባቸዋል የእኩልነቱ አንዱ መገለጫ አሳታፊነት በመሆኑ በመንግሥታት መካካል የሚካሄዱ ግንኙነቶች የሁሉንም አካላት እኩል ተሳትፎ ማረጋገጥ ይኖርበታል አሳታፊነቱ የትብብር ፎረሞችን በጋራ ተሳትፎ ከመመሥረት ጀምሮ መድረኮችን በጋራ የመምራት የትብብር መድረኮችን የትኩረት አቅጣጫዎች እና የወቅቱን የዉይይት አጀንዳዎችን በመቅረጽ በሚሰጡ ዉሳኔዎች የዉሳኔዎች አተገባባርና የአተገባበር ግምገማ ላይ የሁሉን አካላት እኩል ተሳትፎን የሚያጠይቅ ነዉ የመንግሥታት ግንኙነት በግንኙነቱ ተሳታፊ ከሆኑ አካላት እኩል ተሳትፎ ዉጭ የሚታሰብ መሆኑ የለበትም አጋርነት በበፀከቼ ወንድማማችነት ርከዩዘሃ ክዩከበ ፌዴራልና ክልሎች እንዲሁም ክልሎች እርስ በርሳቸው የሚያካሂዱት ግንኙነት በአጋርነት መርህ ላይ የተመሰረተ መሆን ይኖርበታል የግንኘነት ስርዓቱን ከመፍጠር ጀምሮ በአጋርነት መንፈስ ለመስራት ስምምነት የተደረሰበት መሆን ይኖርበታል በአፈፃፀም ሂደትም ተደጋግፎ የመስራት ተነሳሽነትና እምነትን የሚያዳብር በመንግስታቱ መካከል የመረዳዳትና የመተሳሰብ ባህልን የሚገነባ አንዱ ያጋጠመውን ተግዳሮት ለመፍታት በሚያደርገው ጥረት ሌላውም ከጎኑ እንዲቆምለት የሚያስችል የመተሳሰብ እሴት የሚያሰፍን መሆን አለበት በዚህ ማዕቀፍ መሰረት የሚካሄዱ ግንኙነቶች ወንድማማችነትን የሚያጠናክሩ መሆን አለባቸው እያንዳንዱ የግንኙነቱ ባለድርሻ አካል ወንድማዊ ትስስርን ማጠናከር አንዱ የግንኙነቶች ፋይዳ መሆኑን በማመን በዚሁ መንፈስ መንቀሳቀስ ይህንን መርህ የሚሸረሽሩ አፈፃፀሞችን ዝንባሌዎችንና ሂደቶችን ማስወገድ ሌሎችም እንዲያስወግዱ በጎ ተፅእኖ ማሳደርና ማስተካከል እንዲሁም ተደጋግፎ የመስራት ተነሳሽነትን ማዳበር ይኖርበታል የርስ በርስ መከባበር አሀከህ ክሀ እና መተማመን ከህህ ጠ በዚህ ማዕቀፍ መሰረት ግንኙነቶች በሚካሄዱበት ጊዜ የርስ በርስ መከባበር መርህን የተከተሉ መሆን ይኖርባቸዋል በዚህ መርህ መሰረት እያንዳንዱ የግንኙነቱ ባለ ድርሻ አካል ተወካይ በግሉ እና የወከለውን መንግስት ወይም ተቋም ማክበርን ያካተተ ነው በውይይትና ምክክር ወቅት እያንዳንዱ የግንኙነቱ ባለ ድርሻ አካል ተወካይ የሚያነሳቸው ሃሳቦች የሚያንፀባርቃቸው አመለካከቶችም ሆነ የሚወስዳቸው አቋሞች ማክበር እንዲሁም የአቋሞቹና አመለካከቶቹ ጎጂና ጠቃሚ ገፅታን ተንትኖ በማስረዳት ብቻ ተፈላጊ አቋም እንዲይዝ ወይም ወደ ተቀራራቢ አስተሳሰብ እንዲመጣ ማድረግ ይገባል ምክክር ርርበህዚቨክ እና ድርድር ክከዐክ በዚህ ማዕቀፍ መሰረት የፌዴራልና የክልል አካላት እንዲሁም ክልሎች እርስ በርሳቸው የሚያካሂዷቸው ግንኙነቶች የርስ በርስ የምክክርና የድርድር መርህዎችን የተከተሉ መሆን አለባቸው የግንኙነቱ አካላት ያገባናል በሚሏቸው ጉዳዮች ላይ እርስ በርሳቸው ሲወያያዩ የምክክር መንፈስ በመላበስ አንዱ ለሌላው ምክር ለመስጠትና ለራሱም ምክር ለመቀበል ዝግጁ ሊሆኑ ይገባል እያንዳንዱ የግንኙነቱ ባለ ድርሻ አካል በተሰጠው ሕጉ መንግስታዊ የስልጣን ወሰን መሰረት የተናጠል ፍሎጎትና ዓላማ ለማሳካት ፖሊሲዎችን ሕጎችንና ዕቅዶችን የመፈፀም ስልጣኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ነገር ግን እነዚህ ፖሊሲዎችንና ሕጎችን ተግባራዊ ለማድረግ የሚወስደው እርምጃ የሌሎችን የስልጣን ወሰን ወይም ፍላጎት ሊነካ እንደሚችል በመገንዘብ እርምጃ ከመውሰዱ በፊት በሌላው ላይ የሚያሳድሩትን አሉታዊ ተፅእኖ ለመቀነስ ወይም የሚያስከትሉትን ጉዳት ለማስወገድ ተነኪውን አካል ማማከርና የሃሳብ ልውውጥ ማካሄድ ይኖርበታል የፌዴራልና የክልል አካላት እንዲሁም ክልሎች እርስ በርሳቸው ያገባናል በሚሉት ጉዳይ ላይ ሲወያዩ የድርድር መርህን በመከተል መሆን አለበት የድርድሩ ባለድርሻ አካላት የሚያካሂዱት ድርድር የተናጠል ፍላጎትም ሆነ የጋራ ዓላማን ከማሳካት አኳያ የሚያስከትለውን ጥቅምና ጉዳት በሰከነ መንፈስ በማጤን ፍላጎታቸውን የሚያቀራርብ እንዲሁም ሃገራዊ ራዕይና የአብሮነት ዓላማን የሚያሳካ መሆን አለበት በመሆኑም ድርድሩ እያንዳንዱ ተደራራሪ አካል ተጠቃሚ የሚሆኑበት ወይም ተጎጂ የማይሆኑበት ውጤት የሚያስገኝ መሆን ይኖርበታል መተባበር ርዐዐፀፀበ እና የጋራ መግባባት የፌዴራልና የክልል አካላት እንዲሁም ክልሎች እርስ በርሳቸው የሚያካሂዱዋቸው ግንኙነቶች የትብብር መርህን መሰረት በማድረግ መፈፀም አለባቸው የተናጠል ሃላፊነትን ከመወጣት ባሻገር ሌላውን የህብረቱ አባል ለማገዝ መተባበር ይገባል የግንኙነቱ አካላት ያገባናል የሚሏቸውን የጋራ ጉዳዮች እና ትብብርን ለማጠናከር የሚረዱ ፕሮግራሞችና አጀንዳዎች ተባብረው መለየትና የጋራ ፕሮግራም በመንደፍ በጋራ መፈፀም የጋራ ከሚባሉ ጉዳዮች ውስጥ በተናጠል የሚፈፀሙ ፕሮግራሞችና እቅዶች በጋራ መለየት እያንዳንዱ ባለድርሻ አካል በአፈፃፀም ሂደት ያጋጠመውን ችግርና የዓቅም ውስንነት ለማቃለል መተባበር ይኖርባቸዋል ትብብሩ መነሻዉ የጋራ መግባባት በመሆኑ በዚህ ማዕቀፍ መሰረት የሚካሄዱ ግንኙነቶች በጋራ መግባባት ላይ የተመሰረቱ መሆን አለባቸው የግንኙነቱ ባለድረሻ አካላት በሚወያዩባቸው ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት ይደረሳል የሚል መንፈስ በመያዝ በሂደቱ መሳተፍ ይኖርባቸዋል በተለያዩ ርእሰጉዳዮች ላይ ሰፊ ክርክርና ድርድር የሚካሄድባቸው እንዲሁም የተለያዩ አቋሞች የሚንፀባረቁባቸው መሆናቸውን እንደተጠበቀ ሆኖ ነገር ግን አለመተማመን እና ግትርነት የተወገደባቸው በመጨረሻም የሚያግባባ አቋም ላይ የሚደረስባቸው ግንኙነቶች መሆን ይኖርባቸዋል ግልፅነትና ተጠያቂነት የመንግስታት ግንኙነት የግልፅነት መርህን አጥብቆ በመከተል መካሄድ ይኖርበታል ለውይይት ለድርድርና ለውሳኔ የሚቀርቡ አጀንዳዎች አስፈላጊነት መነሻና መደረስ የተፈለገውን ዓላማግብ ለግንኙነቱ ባለድርሻ አካላት በግልፅ መቅረብ አለባቸው በግንኙነት ስርዓቱ ላይ የሚታዩ ችግሮች የግንኙነት ሂደቱ ውጤታማነት የግንኙነቱ ባለድርሻ አካላት የግንኙነት ስርዓቱን ተከትሎ ከመፈፀም አንፃር ያላቸውን ጠንካራና ደካማ ጎኖች ግንኙነቱን ሊጎዱ የሚችሉ የተለዩ ፍላጎቶችና አለመግባባቶች እየተለዩ ለግንኙነቱ ባለድረሻ አካላት በተናጠልም ሆነ ለጋራ መድረክ በግልፅ ማቅረብ ይገባል በተጨማሪ ግልፅነትን ሊያሰፍን የሚችል ፈጣን የመረጃ ልውውጥ መንገድን መዘርጋት ያስፈልጋል የግንኙነቱ ባለ ድረሻ አካላት በጋራ ለሚያስተላልፉት ውሳኔ ተገዥ መሆን አለባቸው በጋራ ተስማምተው በጋራ ለፈፀሙትም ሆነ በተናጠል ለሚፈፅሙት የጋራ ጉዳይ ሃላፊነትን መውሰድ ይኖርባቸዋል በግንኙነቱ ውስጥ ተሳትፎ የሚያደርጉ አካላት በጋራ በተስማሙበት መንገድ ለማይሄድና ለተስማሙበት ውሳኔ ተገዥ የማይሆንን አካል ተጠያቂ ማድረግ ይገባቸዋል ውጨታግሪዕታፖ የመንግስታት ግንኙነት ስርዓት የውጤታማነት መርህ የሚረጋገጥበት ሂደት መሆን አለበት የግንኙነት ሂደቱ በመሰረታዊ አጀንዳዎች ላይ በማተኮር ጊዜንና ወጪን የሚቀንስ መሆን አለበት ግንኙቱ ተጨባጭ ፋይዳ ያለውና በውጤት የሚለካ መሆን ይኖርበታል ስምምነት የተደረሰባቸው ፕሮግራሞች ዕቅዶችና ሌሎችም አጀንዳዎች በስምምነቱ መሰረት ውጤት የተመዘገበባቸው መሆናቸውን እንዲሁም ውጤቶች ባስከተሉት ወጪና ጊዜ ወይም በፈጠሩት ፖለቲካዊ እንድምታ እየተመዘኑ ሊገመገሙ ይገባቸዋል ሀገርአቀፍ ራዕዮችንና ዕሴቶችን ማጎልበት በመንግስታት መካከል የሚካሄዱ ግንኙነቶች ሃገራዊ ራዕዮችንና የጋራ እሴቶችን ማጎልበት የሚያስችሉ መሆን አለባቸው እያንዳንዱ የግንኙነቱ ባለድርሻ አካል የራስ ሃላፊነትን ከመወጣት ባሻገር ዴሞክራሲያዊ አንድነትን ለመገንባት በሚያስችል መንገድ መንቀሳቀስ አለበት በግንኙነቱ ሂደት የሚወሰኑ ውሳኔዎች የሚነደፉ ፕሮግራሞችና ዕቅዶች መንግስታት ራሳቸው እንዲሁም የሚያስተዳድሯቸውን ህዝቦች በሃገራዊ ራዕይና ዓላማዎች ዙሪያ በጋራ እንዲቆሙ እና የጋራ እሴቶችን እንዲገነቡ የሚያስችሉ መሆን አለባቸው አንዱ ስለ ሌላው እንዲገደውና እርስ በርስ እንዲደጋገፉ በሂደትም በልዩነት ውስጥ ያለውን አንድነት ለማጠናከር የሚያስችል መስተጋብር ሆኖ ማገልገል አለበት ተቋማዊ አደረጃጀቶችና አሠራሮች መነሻ ግምገማ በሃገራችን ፌዴራል ስርዓት በፌዴራል መንግስትና በክልሎች መካከል እንዲሁም ክልሎችን እርስ በርሳቸው የሚያገናኙ የጋራ ጉዳዮች በጉልህ እየበዙ የግንኙነት ፍላጎቶች እየሰፉና ጥልቀት እየጨመሩ መጥተዋል የግንኙነቶቹ ገፅታዎች የተዋረድና የጎንዮሽ ሆነው ወሳኝ ቦታ የያዘው የመጀመሪያው ገፅታ በተለይ ደግሞ በፌደራልና በክልሎች ዘርፍተኮር አስፈፃሟ አካላት መካከል የሚደረግ ግንኙነት ነው በእነዚህ መድረኮች ውይይት የሚደረግባቸው ጉዳዮች ሀ የጋራ ፕሮግራሞችንና ዕቅዶችን መቅረፅ መተግበርና መገምገም የሃገራዊ ስታንዳርዶች ፕሮግራሞችንና ዕቅዶች አተገባበር ከክልሎች ተጨባጭ ሁኔታዎች ጋር ማጣጣምና ማስተሳሰር ለ ውጤታማ የሃብት አጠቃቀም ላይ መስማማት ሐ አለመግባባቶችንና ግጭቶችን መፍታት መጧ መልካም ተሞክሮዎችና ልምዶችን መለዋወጥ ሰ የሙያ ቁሳቁስና ዓቅም ግንባታ ድጋፎችን ማድረግ ረ እንዲሁም የመረጃ ልውውጥን ማካሄድ የሚሉትን ያካትታሉ እነዚህ አጀንዳዎች በስምምነት የሚወሰኑ በመሆናቸው በምክክሩ ሂደት ተቀራራቢ አመለካከትና አፈፃፀም እንዲፈጠርና እየተሻሻለ እንዲሄድ በማድረግ ረገድ ጥሩ ሜና ተጫውቷል ከዚህ በተጨማሪ የስብሰባ ስነ ስርዓቶችና አመራር በስምምነት በመንደፍ የሚመሩ በመሆናቸው የጋራነት መንፈስና ተቆርቋሪነት እያደገ እንዲሄድ አስተዋፅኦ አበርክተዋል ሆኖም የግንኙነት ስርዓቱ በርካታ ክፍተቶች ያሉበት በመሆኑ የፌዴራልና የክልሎች እንዲሁም የክልልክልል መንግስታት ግንኙነት የሚመራበት ፖሊሲ ማዕቀፍ ሊኖር ይገባል የፌዴራል ስርዓታችንን ፖለቲካዊ አመራር በበላይነት የሚመራ የጠቅላይ ሚኒስትሩና የክልል ፕሬዚዳንቶች የሚሳተፉበት የግንኙነት ፎረም ማደራጀት ያስፈልጋል የዚሁ ፎረም ውሳኔዎችን የሚያስፈፅምና የዕለትተዕለት ስራዎችንም የሚከታተል ሴክረታሪያት ማቋቋም ያስፈልጋል ፎረሞች የሚመሩባቸው ዓላማዎች መርህችና የአሰራር ስርዓት ወይም ደንብ ሊኖር ይገባል የተዋረድና የጎንዮሽ ግንኙነቶችን የሚያጠናክሩ አደረጃጀቶች በፌዴራልና በክልሎች ደረጃ ሊቋቋሙ ይገባል በዚህ መሰረት የሚከተሉትን መዋቅሮችና አሰራሮች በማደራጀት የግንኙነት ስርዓቱን ማጠናከር ያስፈልጋል የግንኙነት የጋራ መድረኮች ፎረሞች ሀ ሀገርአቀፍ የሕግ አውጭ አካላት መድረክ ሀ የመድረኩ አባላት ይህ መድረክ የኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤና ምክትል አፈጉባኤ የክልል ምክር ቤቶች አፈ ጉባኤዎችንና ምክትል አፈጉባኤዎችን የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈገባኤና ምክትል አፈጉባኤ እንዲሁም የአዲስ አበባና የድሬዳዋ ከተማ ምክር ቤቶች አፈጉባኤዎችንና ምክትል አፈ ጉባኤዎችን እንዲሁም ቋሚ ኮሚቴዎችን የሚያካትት ነው መድረኩ አስፈላጊ ናቸው ብሎ ያመነባቸውን የፌዴራልና የክልል ምክር ቤቶች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎችን እና ሌሎች አካላትን በአስረጂነት ወይም በተሳታፊነት ሊጋብዝ ይችላል መድረኩ ምክክር የሚያካሂድባቸው ጉዳዮች ይህ መድረክ ሀ በሕገመንግስቱ ለፌዴራል መንግስትና ለክልሎች በጋራ የተሰጡ ስልጣንና ኃላፊነቶችን ተፈፃሚ ለማድረግ የሚያስችሉ የተጣጣሙ ሕጎች ለማውጣት ለ ሐ መ ሥ ሰ ሸ የሚመከርበት አፈፃፀማቸው ክትትል የሚደረግበትና ግምገማ የሜካሄድበት በተናጠል ህግ የማውጣት ስልጣንን ከመተግበር በፊት ሌላኛውን የስልጣን እርከን በአሉታ የማይጎዳ መሆኑን ለማረጋገጥ የሚመከርበትና የጋራ መግባባት የሚደረስበት ሃገራዊ አንደምታ ባላቸው ጉዳዮች ላይ በመምከር የጋራ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥና ሃገራዊ ራዕይን ለመገንባት የሚስችሉ ሕጎችን ለማውጣት አብሮነትን ለማጣናከርና የሃገር ግንባታን ለማሳካት የተደነገጉ ሕጎች አፈፃፀም ላይ የሚታዩ ችግሮችን በጋራ በመምከር ለማስተካከል ውይይት የሚደረግበት እንዲሁም በፌዴራልና በክልል መንግስታት የወጡ ህጎችን ተቃርኖ በማስተካከል የሚጣጣሙበትን ዘዴ ለመፈለግና ለማጣጣም የጋራ መግባባት የሚደረስበት የፌዴራል ሕጎች ፖሊሲዎችና ስትራተጂዎች ላይ ተቀራራቢ አፈፃፀም እንዲኖር የጋራ መግባባት የሚደረስበት የአስፈፃሚዎች የጋራ ስምምነቶች ተግባራዊነትና አፈፃፀም ላይ ክትትል በማድረግ የማስተካከያ እርምጃዎች ለማውሰድ ክትትል የሚደረግበትና ድጋፍ የሚሰጥበት በአስፈፃሟ አካላት መካከል የተደረሱ ስምምነቶች ሕገ መንግስታዊ ድንጋጌዎችን የተከተሉ መሆናቸውን የሚመከርበት የክልሎችን ስልጣን የሚነኩ የፌዴራል ስልጣንና ኃላፊነቶች አፈፃፀምን አስመልክቶ ክልሎች የሚማከሩበትና ሃሳባቸው የሚደመጥበት የሕዝብ ተወካዬች ምቤት አባላትና የክልል ምክር ቤት አባላት የህዝብ ዉክልና ተግባራቸዉን ለመወጣት ወደ መረጣቸዉ ህዝብ ወርደዉ በየአከባቢያቸዉ በመከናወን ላይ ባሉ ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ እና ሌሎች ተግባራት ላይ ሕብረተሰቡን በጋራ የሚያወያዩበት እና ችግሮች ካሉ ችግሮቹ በጋራ ተለይተዉ በየደረጃዉ ለሚመለከታቸዉ አስፈጻሚ ለ አካላት በማቅረብ ምላሽ የሚያገኙበትና የተገኘዉን ምላሽ ለመረጣቸዉ ሕብረተሰቡ የሚያስረዱበት አግባብን የሚስተባብርና የሚያሳልጥ ያጋራ መድረክ ነዉ ሀገር አቀፍ የሕግ አስፈጻሚዎች መድረክ ሥ የመድረኩ አባላት ይህ መድረክ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትርን የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ሚኒስትርን የብሔራዊ ፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነርን የዘጠኙን ክልል ፕሬዚዳንቶች የፌዴራልና አርብቶ አደር ልማት ጉዳዩች ሜኒስቴር ሚኒስትርን የአዲስ አበባና ድሬዳዋ ከተሞች ከንቲባዎችን እና የየክልሉን የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ኃላፊዎችን የሚያካትት ነው መድረኩ አስፈላጊ ነው ብሎ ያመነበትን የፌዴራል ወይም የክልል ተቋም ኃላፊ በአስረጂነት ወይም በተሳታፊነት ሊጋብዝ ይችላል መድረኩ ምክክር የሚያካሂድባቸው ጉዳዮች ይህ መድረክ የፌዴራል መንግስትና የክልል አስፈፃሚ አካላት ግንኙነቶች የበላይ አካል ሲሆን ሁለቱንም የመንግስት እርከን የሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ውይይትና ምክክር የሚደረግበትና ሀገር አቀፍ የፖሊሲ ሀሳቦች እና አጠቃላይ ሀገራዊ የሆኑ ጉዳዩች ለዉይይትና ምክክር የሚቀርብበት መድረክ ነው መድረኩ ሀ የፌዴራል መንግስትና ክልሎች ሀገርአቀፍ ፖሊሲዎች ስትራቴጂዎች ፕሮግራሞችና ዕቅዶች ላይ ውይይት የሚካሄድበት የሚመከርበትና በወሳኝ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት የሚፈጠርበት አፈፃፀማቸውም የሚቀናጅበት በጋራ የሚመራበት ክትትል የሚደረግበትና የሚገመገምበት ለ ሀገርአቀፍ አንድምታ ያላቸው የዘላቂ ሰላም የተመጣጠነ ዕፅድገት የዴሞክራሲ የመልካም አስተዳደር እንዲሁም የፈጣንና ፍትሃዊ ማሀበረ ኢኮኖሚ ልማት ጉዳዮች የሚመከሩበትና መፍትሄ የሚነደፍበት ሐጧ ብሔሮች ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ለዘመናት የገነቡዋቸዉን የጋራ እሴቶች ከፀሃሀ የሚያስተሳስራቸዉ ጉዳዩች የሚጠናከርበት አቅጣጫ የሚነደፍበትና በአገር አቀፍ ደረጃ አፈጻጸሙ ክትትል የሚደረግበት ነዉ ሐ መ በሕጉመንግስቱ ለፌዴራል መንግስትና ለክልሎች በጋራ የተሰጡ ስልጣንና ኃላፊነቶችን ተፈፃሚ ለማድረግ የጋራ አፈፃፀም የሚነደፍበት የሚመራበትና የሚገመገምበት ሥ የክልሎችን ስልጣን የሚነኩ የፌዴራል ስልጣንና ኃላፊነቶች አፈፃፀምን አስመልክቶ ከክልሎች ጋር የሚመከርበትና ሃሳባቸው የሚደመጥበት ረ በዘርፋዊ ፎረሞች ዕልባት ያላገኙ እና ዘርፍ ተሻጋሪ ጉዳዮች የሚመከሩበት አቅጣጫዎች የሚሰጥበትና ክትትልና ድጋፍ የሚደረግበት ሰ ሃገር አቀፍ አገልግሎት በሚሰጡ ተቋማት የሥራ አፈጻጸም ላይ ምክክር የሚደረግበት እንዲሁም ክልሎች በዉክልና በሚሰሩዋቸዉ የፌዴራል መንግስት ስራዎች ላይ የወጪ አሸፋፈንን በተመለከተ ዉይይትና ምክክር የሚደረግበት ነዉ የመንግሥታት ግንኙነት የፖሊሲ አፈጻጸምና ስትራቴጅክ አቅጣጫዎች ላይ ዉይይት የሚደረግበት የምክክር መድረክ ነዉ ሀገር አቀፍ የዳኝነት አካላት ግንኙነት መድረክ የመድረኩ አባላት ይህ መድረክ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንትንና ምክትል ፕሬዚዳንትን የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንትንና ምክትል ፕሬዚዳንትን የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግን ያለ ድምፅ የሚሜያካትት ነዉ መድረኩ አስፈላጊ ናቸው ብሎ ያመነባቸውን የፌዴራልና የክልል የዳኝነት አካል ወይም ተቋም በአስረጅነት ወይም በተሳታፊነት ሊጋብዝ ይችላል መድረኩ ምክክር የሚያካሂድባቸው ጉዳዮች በኢፌዴሪ ሕገመንግስት አንቀፅ የፍርድ ቤቶች ጣምራ ስልጣን ተደንግጓል የፌዴራል የዳኝነት አካል ሃላፊነቱን ለክልል የዳኝነት አካል መወከል እንደሚችልም ተደንግጓል እነዚህን ድንጋጌዎች መነሻ በማድረግ የፌዴራልና የክልል ፍርድ ቤቶች የጋራ ፎረሞችን በማቋቋም ሲሰሩ ቆይተዋል ስለሆነም ከዚህ በፊት የተቋቋሙት የፍርድ ቤቶች የጋራ ፎረሞች በዚህ ማዕቀፍ መሰረት የተጠበቁ ይሆናሉ ሆኖም እስከአሁን ካገኙት ልምድ በመነሳት ስልጣንና ሃላፊነታቸውን ማሻሻልና ፎረሞቹን ማጠናከር ይችላሉሌ በመሆኑም መ ሠ በሕገመንግሥቱ በግልጽ የተቀመጠዉ የዉክልናና የይግባኝ ሥርዓት እንደተጠበቀ ሆኖ መድረኩ የዳኝነት አካሉ በቴክኖሎጂ የታገዘ ተደራሽ ቀልጣፋና የተገልጋዩን የአገልግሎት አሰጣጥ እርካታ በየጊዜዉ እየፈተሸ እና እያሳደገ በሚሄድበት አግባብ የሚመክርበት ለ የሕግ የበላይነት እና ፍትሃዊነት በሚረጋገጥበት አግባብ ዉይይት የሚደረግበት ሐ የፌደራል ሕጎች በክልል የተቀራረበ አተረጓጎም እንዲኖራቸዉ ምክክር የሚደረግበት መ ነፃ ገለልተኛ የሆነና የሕዝብ አመኔታን እያጎለበተ የሚሄድ የዳኝነት ሥርዓት እየተገነባ በሚሄድበት አግባብ ዉይይት የሚደረግበት ሥ በዉክልና በሚሰጥ የፌዴራል የዳኝነት ስልጣን እና ሌሎች ተያያዥነት ባላቸዉ አስተዳዳራዊ ጉዳዩች ላይ ዉይይት የሚደረግበት ረ የአቅም ግንባታ ሥራዎችንና ሌሎችንም በጋራ የሚያቀናጁበት መድረክ ነዉ ሀገርአቀፍ የአስፈፃሚዎች ዘርፋዊ መድረኮች ማንኛውም የፌዴራልና የክልሎች አቻ የዘርፍ አስፈፃሚ መስሪያ ቤቶች ለምሳሌ የትምህርት ጤና ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር የገቢዎችና ጉሙሩክ የህግ አስከባሪ እና ሌሎችም የዘርፍ አስፈፃሚ አካላት በጋራና በሚያገናኙዋቸው ጉዳዮች ላይ የርስ በርስ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ዘርፋዊ የአፈፃፀም ውጤታማነትን ለማሻሻልና በስምምነት ላይ የተመሰረተ የአፈፃፀም ስታንዳርድ ያለዉ የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓትን ለመከተል የተቀናጀና የተናበበ ስትራቴጅክ እና ዓመታዊ ዕቅድ ለማቀድና ለመፈጸም ዘርፋዊ የአስፈፃሚዎች የግንኙነት መድረክ ሊያቋቁሙ ይችላሉ ቀደም ሲል ተቋቁመው የነበሩ ዘርፋዊ የአስፈፃሚ አካላት መድረኮች በዚህ ማዕቀፍ መሰረት እንደተቋቋሙ ይወሰዳሉ ሆኖም የነበሩዋቸውን የአሰራር የአደረጃጀትና የአፈፃፀም ክፍተቶች በዚህ ማዕቀፍ መሰረት በማሻሻል ግንኙነታቸውን አጠናክረው መቀጠል ይኖርባቸዋል የመድረኩ አባላት ዘርፋዊ የአስፈፃሚ አካላት የግንኙነት መድረኮች የየዘርፉን የፌዴራል መንግስት ሚኒስትሮች እና የዘጠኙን ክልሎችና የሁለቱን ከተማ ሰ መስተዳድሮች የየዘርፉን መስሪያ ቤት ኃላፊዎች በአባልነት ይይዛሉ መድረኩ አስፈላጊ ነው ብሎ ያመነባቸውን ማንኛውም አካላት በስብሰባው ላይ በአስረጅነት ወይም በተሳታፊነት ሊጋብዝ ይችላል ሁለት እና ከሁለት በላይ የሆኑ ዘርፋዊ የአስፈፃሚ አካላት መድረኮች አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኙት የጋራ መድረክጉባኤ ሊያቋቁሙ ይችላሉ መድረኩ ምክክር የሚያካሂድባቸው ጉዳዮች ዘርፋዊ የአስፈፃሚዎች የግንኙነት መድረኮች በየዘርፉ ሀገርአቀፍ ጥቅምን የሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ በጋራ የሚመከሩበት የክልሎችን ስልጣን ጥቅምና ፍላጎት የሚመለከቱ የፌዴራል መንግስት ዘርፋዊ ፖሊሲዎች ስትራቴጂዎችና ዕቅዶች ዝግጅትና አፈፃፀም የሚመከርበትና በነዚህ ጉዳዮች ዙሪያ የክልሎች ሃሳብ የሚደመጥበት በጋራ ተደራራቢና የማዕቀፍ ስልጣኖች ዙሪያ በሚዘጋጁ የረዥም የመካከለኛና የአጭር ጊዜ ዕቅዶችንና ፕሮግራሞችን የሚያቀናጁበትና የሚያስተሳስሩበት በየዘርፎቹ የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራትና የአፈፃፀም ደረጃ ዙሪያ ውይይት የሜካሄዱባቸው በክልል የሜተገበሩ ሃገራዊ ዘርፋዊ ዕቅዶችና ፕሮግራሞች ዕቅድ ዝግጅት አፈጻፀም ክትትልና ግምገማ ላይ የሚመክሩበት ምርጥ ተሞክሮዎችን የሚለዋወጡበትና ወደ ተቀራራቢ የሆነ አፈጻጸም ደረጃ የሚደርሱበትን መንገድ የሚመክሩበት በየክልሉ ያሉ ስራ አፈጻጸሞች ወደ ተመሳሳይ ደረጃ ለማድረስ የሚስችል የአቻ የግምገማ ሥርዓት ሀየ ጸልርነ እፎርከበበበ ተግባራዊ የሚሆንባቸዉ የምክክር መድረኮች ናቸዉ የፌዴሬሽን ምክር ቤት እና የክልሎች መድረክ በኢፌዴሪ ሕጉመንግስት ለፌዴሬሽን ምክር ቤት የተሰጠውን ሕጉ መንግስታዊ ስልጣንና ኃላፊነቶች በዚህ የግንኙነት ማዕቀፍ የተጠበቀ ሆኖ ኃላፊነቱን ለመወጣት ይበልጥ አጋዥ የሆነ የፌደሬሽን ምክር ቤትና የክልሎች የምክክር መድረክ ተቋቁሟል ወ ሸ የመድረኩ አባላት ይህ የምክክር መድረክ የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤን የክልል ርዕሳነመስተዳድሮችን የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር የፌደራል እና አርብቶ አደር ልማት ጉዳዩች ሚኒስቴር እና ገቢዎች ባለስልጣን በአባልነት ይይዛል መድረኩ አስፈላጊ ናቸው ብሎ ያመነባቸውን አካላት በስብሰባው ላይ በአስረጅነት ወይም በተሳታፊነት ሊጋብዝ ይችላል መድረኩ ምክክር የሚያካሂድባቸው ጉዳዮች ይህ መድረክ ሀ የፌዴራል መንግስት ለክልሎች በሚሰጠው ድጎማ ቋትና ክፍፍል እንዲሁም በሕገ መንግስቱ ለፌዴራል መንግስትና ለክልሎች የተሰጡ የጋራ ገቢዎች ክፍፍል ላይ ውይይት የሚሜካሄድበት የሚመከርበትና የጋራ መግባባት የሚፈጠርበት እና ለሚመለከተዉ አካል ምክረሃሳብ የሚቀርብበት ነዉ ለ የብሄሮች ብሄረሰቦች ህዝቦች አብሮነትና የጋራ ተጠቃሚነት ለማጎልበት የሚያስችሉ መሰረታዊ አቅጣጫዎችን የሚመከርበት እንዲሁም በብሄሮች ብሄረሰቦች ህዝቦች መካከል የሚታዩ የግንኙነት አዝማሚያዎች ላይ አስቀድሞ በመወያየት ለአስፈፃሚዎች የሚጠቅሙ ምክረሃሳቦች የሚቀርቡበት ሐ በብሄሮች ብሄረሰቦች ህዝቦች እና በተለይ በአናሳ ማህበረሰቦች አያያዝ ላይ ውይይት የሚደረግበት ምርጥ ልምዶችን የሚስፋፉበትና በአያያዝ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችሉ አቅጣጫዎችን የሚቀየሱበት መ በክልሎች እና በተለያዩ ማህበረሰቦች መካከል ለግጭት መንስኤ የሚሆኑ ጉዳዮች እና አፈታት ላይ ምክክር የሚደረግበት የተከሰቱና የተፈቱ ግጭቶችና አለመግባባቶች ቀጣይነት ያለው ቅራኔ በማይፈጥር እና ወንድማዊ ትስስርን በሚያጎለብት መልክ ለማስተካከል የሚያስችል አቅጣጫዎች የሚነደፉበት መድረክ ነው የክልል መንግስታት የግንኙነት መድረኮች መ የመድረኩ አባላት የክልል መንግስታት የግንኙነት መድረክ የሁሉንም ክልሎች ርዕሳነመስተዳድሮችና የሁለቱን ከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች በአባልነት ያቀፈ መድረክ ይሆናል መድረኩ አስፈላጊ ናቸው ብሎ ያመነባቸውን የፌዴራልም ሆነ የክልል አካላት በስብሰባው ላይ በአስረጅነት ወይም በተሳታፊነት ሊጋብዝ ይችላል መድረኩ ምክክር የሚያካሂድባቸው ጉዳዮች ይህ መድረክ ሀገር አቀፍ ፖሊሲዎች ስትራተጂዎችና ዕቅዶች አፈፃፀም በክልሎች ያሳደሩትን በጎና አሉታዊ ተፅእኖዎችን በመገምገም የማሻሻያ ሃሳቦችን ለፌዴራል መንግስት ለማቅረብ የሚመከርበት ለ በአንድ ክልል ውሳኔ ያገኘ ጉዳይ በሌሎች ክልሎች ተፈፃሚነት እንዲኖረው የጋራ መግባባት የሚደረስበትና አሰራር የሚሜሚዘረጋበት ሐ በልማት በመልካም አስተዳደርና በሰብዓዊ መብቶች አያያዝ ላይ ተቀራራቢ አፈፃፀም እንዲኖር የሚመከርበትና የተሞክሮ ልውውጥ የሚደረግበት መ የፌዴራል መንግስትን ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ላይ የሚመከርበትና የጋራ አቋም የሚያዝበት መድረክ ነው ሠ ክልሎችን በጋራ ማስተሳሰር የሚችሉና ድንበር ተሻጋሪ የሆኑ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችሉ ፕሮግራሞችና ፐሮጀክቶች አስፈላጊነት እና ልዩነት የሚመክር መድረክ ነዉ ከዚህ በተጨማሪ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ሁሉንም ክልላዊ ዘርፋዊ አስፈጻሚ አካላት ሁለት ወይም ከሁለት በላይ ተጎራባች ክልሎች ርእሳነመስተዳድሮች እና ዘርፋዊ አስፈፃሚዎችን ያቀፉ እንዲሁም ሁለት ወይም ከሁለት በላይ የሚጎራበቱ ክልሎች የጋራ መድረኮችን ማቋቋም ይችላሌ የሁሉም ክልሎች ሆነ የተጎራባች ክልሎች የጋራ መድረኮች ሲቋቋሙ ይህንን የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የመንግስታት ግንኙነት የፖሊሲ ማዕቀፍ መሰረት በማድረግ ይሆናል መ ሀገርአቀፍ የግንኙነት ፅቤት ሴክረታሪያት የክልሎች እና የፎረሞች ፅቤቶች ስለማቋቋም ሀገርአቀፍ የግንኙነት ፅቤት ሴክረታሪያት ስለማቋቋም በሀገር ደረጃ ግንኙነትን የሚመለከቱ የማስተባበርና የማሳለጥ ሙያዊና ቴክኒካዊ ስራዎችን በመስራት ማዕከል ሆኖ የሚያገለግል ፅቤት ሴክረታሪያት ማደራጀት አስፈላጊ ይሆናል ይህንን ኃላፊነት የሚወጣ አካል በፌዴራልና በክልል መንግስታት በጋራ ይቋቋማል የፌዴራልና የክልል መንግስታት በጋራ ተስማምተው ተቋሙን የሚመሩ ተሺጂሚዎች ይመድባሉ ለተቋሙ የሚያስፈልጉ ባለሙያዎች በውድድር ይቀጠራሉ የግንኙነት ጽቤት ተጠሪነቱ ለሀገር አቀፍ የሕግአስፈፃሚዎች መድረክ ይሆናል የሴክረታሪያቱ ተግባርና ሃላፊነት የሚከተሉትን ያጠቃለለ ይሆናል ሀ መንግስታቱ በጋራ የነደፏቸውን ፕሮገራሞች ዕቅዶችና ስምምነት የተደረሰባቸውን የጋራ ጉዳዮች አፈፃፀምን መከታተል ለ ግንኙነቶች ለስርዓቱ መጎልበት ለህብረቱ መጠናከርና ለህዝቦች ወዳጃዊ ትስስር ያስገኙትን ፋይዳ ማጥናት ፎረሞች በወጪና በጥራት ውጤታማ እንዲሆኑ አሳላጭ በመሆን ማገልገል ሐ በግንኙነቶች ዙሪያ የሚታዩ ክፍተቶችና ችግሮች በጥናት ላይ በመመስረት መለየትና የመፍትሄ ሃሳቦችን ለሀገር አቀፍ የአስፈፃሚዎች መድረክ ማቅረብ መ አለመግባባቶችንና ግጭቶችን ሊፈጥሩ የሚችሉ ጉዳዮችን አስቀድሞ በመለየት እንዲሁም ግዙፍ ተፅእኖ በቨበ። ጠፀ ያላቸውን ጉዳዮች የመንግስታቱ የትኩረት አጀንዳ እንዲሆኑ ማድረግ ሠ በመንግስታት መካከል የመረጃ ልውውጦች ሳይቋረጡ እንዲሳለጡ እንደ ድልድይ ሆኖ በማገልገል ግልፅነትና ተጠያቂነት እንዲሰፍን ማድረግ ረ በተመሳሳይ ጉዳዮች ዙሪያ የሌሎች ፌደሬሽኖች ልምዶችን በመቀመርና ከሀገሪቱ ነባራዊ ሁኔታዎች ጋር በማጣጣም ጥቅም ላይ እንዲውሉ ሃሳብ ማቅረብ ሰ በግንኙነቶች ዙሪያ የሚታዩ የግንዛቤ ክፍተቶች እንዲቀረፉ ትምህርታዊ ማብራሪያዎችን መስጠትና በፅሁፍ ማሰራጨት ሸበ አደረጃጀቶችና ፎረሞች እንዲቋቋሙና እንዲጠናከሩ ሙያዊ ድጋፍ መስጠት ይሆናል የበጀት አሸፋፈን ለጽህፈት ቤቱ የስራ ማስፈፀሚያ የሚሆን በጀት ቱ በፌዴራል መንግስት የሚሸፈን ሲሆን ቀሪዉ ደግሞ ክልሎች ከድጎማ ክፍፍል ከሚያገኙት በጀት በተመጣጠነ መልኩ እንዲሸፈን ይደረጋል የበጀት አፈፃፀሙን ኦዲት በተመለከተ ክልሎች ለፌዴራል መንግስት ውክልና በመስጠት እንዲከናወን ሊያደርጉ ይችላሌ ሌሎች ፎረሞችና ማስተባበሪያ ጽቤቶች የየራሳቸን የበጀት አሸፋፈን በተመለከተ በየፎሮሞቹ ይወስናሉሌ የክልሎች እና የፎረሞች ጽቤቶች ስለማቋቋም የግንኙነት ስርዓቱን አጠቃላይ ጤናማነትና ውጤታማነት የሚከታተሉ በግንኙነቶች ዙሪያ ቀጣይነት ያለው የጥናትና ምርምር ስራዎችን የሚያካሂዱ ግንኙነቶችን የሚመለከቱ የአፈፃፀም ሪፖርቶች ለጋራ መድረኮች የሚያቀርቡ ግንኙነቶችን የሚመለከቱ የህትመትና የሰነዶች ስርጭት ስራዎችን የሚያከናውኑ የግንኙነቶችን አፈፃፀምና ውጤታማነትን በተመለከተ ለሚዲያና ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ወቅታዊ መረጃዎችንና ማብራሪያዎችን የሚሰጡ እንዲሁም የፎሮሞችን ስብሰባዎች አመቻች በመሆን የሚያገለግሉ ቋሚና ጊዜያዊ አደረጃጀቶች በፌዴራል ደረጃ እና በየክልሎች ሊቋቋሙ ይችላሉ እነዚህ መዋቅሮች የግንኙነቶች ማስተባበሪያ ጽቤቶች ሴክራታሪያት በመሆን የሚያገለግሉ ይሆናሉ በመሆኑም በክልል ፕሬዚዳንት ጽቤት ስር እነዚህ ቋሚ የግንኙነት ሴክረታሪያት ሊቋቋሙ ይገባል የተዋረድም ሆነ የጎንዮሽ ፎረሞች እንደ አስፈላጊነቱ ቋሚ ወይም ጊዜአዊ አድሇክ ኮሚቴዎችን ማቋቋም ይችላሉ የእነዚህ ኮሚቴዎች ተጠሪነት ለያቋቋሟቸው ፎረሞች ወይም አካላት ይሆናል አሠራሮች የስብሰባ ሥነሥርዓት የስብሰባ አመራር ማናቸውም የፎረሞች ስብሰባ በጋራ አመራር መካሄድ ይኖርበታልሆኖም ከአገር አቀፉ የአስፈፃሚ አካላት ምክክር መድረክ በስተቀር የፌዴራል መንግስትና ክልሎች በተዋረድ የሚካሄዱ ውይይቶችጉባኤዎች አግባብ ባላቸው የፌዴራል መንግስት የስራ ኃላፊዎችና በክልሎች አቻዎቻቸው በዙር ሰብሳቢነት መመራት ይገባቸዋል የመወያያ አጀንዳ አቀራረፅ መ በግንኙነት መድረኮቹ ውይይት የሚደረግባቸው ርዕሰጉዳዮች የሚቀረጹት የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ የተወያዩባቸውና ስምምነት ላይ የተደረሱባቸው ጉዳዮች ይሆናሌ የፌዴራልም ይሁን የክልል አካላት በአጀንዳ አቀራረፅ ወቅት እኩል የመሳተፍ ዕድል እንዲኖራቸው ማድረግ ይገባል አጀንዳ የመቅረፅ ሂደቱ የመድረኮቹ ፅሕፈት ቤቶች ሴክረታሪያት ወይም ጊዜያዊ አድሆክ ኮሚቴዎች ያስተባብሩታል ውሳኔ አሰጣጥ ለግንኙነት መድረኮች ቀርበው ውይይት የተደረገባቸውና ውሳኔ የሚሹ ጉዳዮች ሲኖሩ በተቻለ መጠን በስምምነት እልባት እንዲያገኙ ማድረግ ያስፈልጋል በውሳኔ ሃሳቡ ላይ ስምምነት መፍጠር ካልተቻለ ግን የመጨረሻው አማራጭ ውሳኔዎችን በድምጽ ብልጫ ማሳለፍ ይሆናል ስለ ግጭቶችና አለመግባባቶች አፈታት በፌዴራል መንግስትና ክልልች እንዲሁም በክልሎች መካከል ሊፈጠር የሚችል ማናቸውንም ዓይነት አለመግባባት ወይም ግጭት በተቻለ መጠን በስምምነት ለመፍታት ጥረት መደረግ አለበት ስለሆነም ከፌዴራል መንግስት ወይም ከክልል ጋር የሚያወዛግብ ጉዳይ አለኝ ብሎ የሚያምን ወገን ሲኖር ጉዳዩን ለሌላው ወገን ማሳወቅ ይኖርበታል ይህ ጉዳይ የቀረበለት አካልም ጉዳዩን በቅን ልቦና ተመልክቶ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለውይይት ራሱን ዝግጁ ማድረግ ይጠበቅበታል ሁለቱ አካላት ጉዳያቸውን በውይይት ለመፍታት የተቻላቸውን ጥረት ማድረግ አለባቸው ይህንን ለማድረግም በዚህ ማዕቀፍ የተመሰረቱትንም ሆነ ሌሎች የግንኙነት አደረጃጀቶችና አሰራሮች መጠቀም ይኖርባቸዋል ጉዳያቸውን በስምምነት መፍታት ካልቻሉ በራሳቸዉ ፈቃድ በተሰየመ ሶስተኛ ወገን አደራዳሪነት ጉዳያቸውን በሰላማዊ መንገድ የሚፈቱበት ሁኔታን እንዲያመቻች ማድረግ ይገባቸዋል እነዚህ አለመግባባቶችና ግጭቶች በስምምነት ሊፈቱ ካልቻሉ ግን ይህን ዓይነት የመንግስታት ግጭቶችን የመዳኘት ስልጣን ለተሰጠው የፌዴሬሽን ምክር ቤት መቅረብ ይኖርበታል የግልፅነትና የተጠያቂነት አሰራር መንግስታቶቹ የሚያካሂዷቸው ግንኙነቶች የግልፅነትና የተጠያቂነት አሰራሮችን የተከተሉ መሆን አለባቸው የግልፅነትና የተጠያቂነት አሰራርን ለማስፈን የሚከተሉትን ዘዴዎች ተግባራዊ ማድረግ ይኖርባቸዋል አንደኛ የፌዴራልና የክልሎች የግንኙነት አካላት የእርስ በርስ ምክክሮችን ካካሄዱ በኋላ ወሳኝ በሆኑ የጋራ ጉዳዮች ላይ የሚደርሱባቸውን ስምምነቶች ያሳለፏቸውን ውሳኔዎችና የነዚህኑ አፈፃፀሞች የሚያሳዩ የመግባቢያ ሰነዶች በመፈራረም ለየራሳቸው ምክር ቤቶች በማቅረብ የተጠያቂነትን አሰራር ይዘረጋሉ በተመሳሳይ የሁሉም ክልሎች እንዲሁም የሁለት ወይም ከሁለት በላይ የሆኑ ተጎራባች ክልሎች ለየራሳቸው ምቤቶች በማቅረብ ተጠያቂነትን ማረጋገጥ ይገባቸዋል የፌዴራልም ሆነ የክልሎች ምክር ቤቶች ይህን ጉዳይ የሚከታተሉ የተለያዩ ኮሚቴዎችን በማደራጀት የግንኙነቱን አፈፃፀምና ውጤታማነት በተመለከተ ተገቢውን ክትትልና ቁጥጥጥር ማድረግ ይኖርባቸዋል በዚህ መንገድ የግንኙነቱ ተዋናዮች በምክር ቤቶች አማካኝነት ለመረጣቸው ሕዝብ ተጠያቂ የሚሆኑበት አሰራር ሊያረጋግጡ ይገባል ሁለተኛ የተጠያቂነት መንገድ የግንኙነት ጉዳዮችን በብዙሃን መገናኛ ዘዴዎች ለህዝብ ይፋዊ መግለጫ በመስጠት ለብዙሃን ማኅበራት ማብራሪያዎችን በመስጠት እና የፅሁፍ ውጤቶች በማሰራጨት የግንኙነቱ ተዋናዮች ለመረጣቸው ሕዝብ ተጠያቂ የሚሆኑበት የተጠያቂነት አሰራር ሊያረጋግጡ ይገባል ሦሥተኛ የአስፈፃሚዎች ዘርፋዊዋ የግንኙነት መድረኮች አፈፃፀማቸውን በተመለከተ ለሀገር አቀፍ የአስፈፃሚዎች መድረክ የፌዴራል ጠቅላይ ሚኒስትር የክልሎች ርእሳነመስተዳደሮች የሁለቱ ከተሞች ከንቲባዎች መድረክ ሪፖርት የሚያቀርቡበትና ተጠያቂ የሜሆኑበት አሰራር መከተል ያስፈልጋል የግንኙነት መስተጋብር የመንግስታት ግንኙነት ስራዎች በጋራ የሚቀናጁበት እና ስትራቴጂያዊ በሆነ አግባበብ የሚመሩበት ተቋም ሀገር አቀፍ የሕግ አስፈፃማች መድረክ ፎረም ነዉ ምንም እንኳን የሕግ አውጪ የሕግ አስፈፃሚና የሕግ ተርጓሚ አካላት ሕገጉ መንግስታዊ የስልጣን ክፍፍል መሰረት በማድረግ የየራሳቸውን የግንኙነት መድረኮች ያቋቋሙ ቢሆንም በመካከላቸው ትስስርና ግንኙነት መኖሩ የማይቀር በመሆኑ ስራዎቻቸዉን በመናበብ ሊያከናዉኑ ይገባል በመሆኑም ሀገር አቀፍ የሕግ አስፈፃሚውና የሕግ ተርጓሚው አካላት የግንኙነት መድረኮች አፈፃፀማቸውን ያጋጠማቸውን ችግሮችና ሕግ እንዲወጣላቸው የሚፈልጓቸውን ጉዳዮች አስመልክተው ለሕግ አውጪው የመንግስታት ግንኙነት ፎረም ሪፖርት ያደርጋሉ ሀገር አቀፍ የግንኙነት ሴክረታሪያት የመድረኮችን ውጤታማነት በመከታተል ግንኙነቶችን የተመለከቱ የዳሰሳ ጥናቶችን በማካሄድ የአፈፃፀም ሪፖረቶችን በማዘጋጀትና የማሻሻያ ሃሳቦችን በማከል ለሀገር አቀፍ የአስፈፃሚዎች መድረክ ያቀርባል ሀገር አቀፍ የአስፈፃሚዎች መድረክ በሴክሬታሪያቱ ሪፖረት በመወያየት ለሀገር አቀፍ የሕግአውጪ አካላት ፎረም ያስተላልፋል ሀገር አቀፍ የሕግአውጪ አካላት ፎረም በበኩሉ ከሀገር አቀፍ የአስፈፃሚዎች መድረክ የቀረበለትን ሪፖርት ለሀገር አቀፍ የሕግ ተርጓሚ ሠ አካላት ፎረም እንዲደርስ ያደርጋል በዚህም መልኩ የሶስቱ የመንግስት አካላት የግንኙነት ፎረሞች መስተጋብር እንዲጠናከር ይደረጋል ማዕቀፉ የሚፀድቅበት አግባብና አፈፃፀም ማዕቀፉ የሚፀድቅበት አግባብ ይህ የመንግሥታት ግንኙነት የፖሊሲ ማዕቀፍ በስራ ላይ የሚውለው የፌዴሬሽን ምክር ቤት የክልል መንግስታትን በአግባቡ አማክሮ ይሁንታ ካገኘ በኋላ ወደ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተላልፎ ሲፀድቅ ይሆናል አፈፃፀም ይህ ማዕቀፍ ከፍ ብሎ በተጠቀሳ አግባብ የግንኙነት ማዕቀፍ ሆኖ እንዲያገለግል ከፀደቀ በኋላ የማዕቀፉን መንፈስ ዓላማዎችና መርሆችን በተከተለ መልኩ የግንኙነቶች የዕለትተዕለት የተግባር መመሪያ ሆኖ እንዲያገለግል በፌዴራልና በክልል መንግስታት አማካኝነት ሰፊ የግንዛቤ ማስፋፊያ ስራዎች ሊካሄዱ ይገባል።

  • N.B. This Summary is Very Experimental!! based on the following scripts from:
    • https://github.com/millzon/textSummarizer-am
    • https://github.com/icoxfog417/awesome-text-summarization#motivation
Download Searchable PDF Download PDF

Commentaires:


memezon

Options de téléchargement | Convertir en PDF | Livre du jour

© dirzon | Conditions d'utilisation | Intimité | Sur | Services | Contact