Detecting...

Please whitelist dirzon to continue.

or subscribe for ad-free contenct.

dirzon
  • Convertir en PDF
  • Liste de lecture
  • Abrégé
  • Livre audio
  • Chercher
  • Télécharger
  • myzon
  • S'identifier
  • registre
English  አማርኛ  Français  العربية
Livre du jour

የመለስ ትሩፋቶች፤ ኤርሚያስ ለገሰ.pdf


  • word cloud

የመለስ ትሩፋቶች፤ ኤርሚያስ ለገሰ.pdf
  • Extraction Summary

ክር ጄቫዝበ ፎ የደራሲው መብት በህግ የተጠበቀ ነው ነጻነት አሳታሚ ድርጅት በአዳማው ስልጠና ሰፊ ሰኣት ያገኘው የህዝብ ጥያቄ ኢህአዴግ ይቅርታ ያድርግልን አጥፍተናል የሚለው ነበር። ከተቆጠሩ አንድ መቶ ወረቀቶች ውስጥ ከሀምሳ በላይ ድምፅ አልባው ተቃዉሞ ድርጅቱን አደጋ ውስጥ ከቶታል። አናም አክራሪነት ሌላ ቦታ ሳይሆን በውስጣችን የመሸገ መሆኑ የማይታበል ሀቅ ነው በኢህአዴግ የስልጣን ማማ በታቸኛው አርከን ያለው ካድሬ የሚራገፈው እንደ የኢትዮጵያ ድረቅ ነው። ጠንከር ያለ ከሆነ ደግሞ የቀበሌ መታወቂያ ሰጥተሀል ደሀ ያልሆነውን ደሀ ብለህ ለጤና ጣቢያ የነፃ ህከምና ወረቀት ጽፈሀል የቀበሌ ቤት ይሰጠኝ ብለህ ጠይቀሀል አጥርህን ገፉ አድርገህ አጥረሀል ይሆናሉ በተቃራኒው የላይኛው የኢህአዴግ የስልጣን አርከን ፓርቲው ላይ ስጋት እስካልተፈጠረ ድረስ በስፕሪንግ ፍራሽ ላይ ተደላድሎ አንደመተኛት ነው። እነ አባይ በረከት አዲሱ ዛሬም በስልጣን ላይ አሉ አባዱላ የሸንጐውን መዶሻ እየደበደበ ነው። የአማራ ክልሉ ገዱ አውነትም ገደኛ ነው። ሀይሌ ፍስሀ በአሁን ሰአት የአዲሳአባ ስራ አስኪያጅ ሆኘ አሰራ በነበረበት ጊዜ አብረውኝ ይሰሩ ከነበሩት ምክትል ስራ አስኪያጆች አንዱ ነበር። አንደኛው የአቶ አርከበ ሀሰት ይህ ነበር። እኔ አስከማውቀው ድረስ ትራንስ ኢትዮጵያ በገዛበት ዋጋና በዚያ ውል ተጠቃሚ የነበረው ይህ ጥቁር አባይ የተባለ ድርጅት ነው።

  • Cosine Similarity

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የኢህአዴግ ከፍተኛ ካድሬዎች ድርጅቱ ብለው ሲጠሩ አቶ መለስ ማለታቸው ሀሆኗል የአቶ መለስ የወል ስም ድርጅቱ ነው። በእንቅርት ላይ እንዲሉ በምርጫ ማግስት በአቶ መለስ ቀጭን ትአዛዝ ቁልፍ የገቢ ማስገኛ ዘርፎች የከተማዋ ውልና ማስረጃ አንዲሁም የአንድ ከተማ የደም ስር ተደርገው ከሚቆጠሩት አንዱ የሆነው ትራንስፓርት ክፍል ተቀምቷል ከሁሉም አሳዛኙ ከከተማዋ ታሪክ ጋር ልዩ ቁርኝት ያለው አንበሳ አውቶብስ ሳይቀር ተጠሪነት ሰፌደራል መንግስት ሆኗል ይህንን በተመለከተ ከአቶ መለስ ጋር በነበረን ሳምንታዊ ስብሰባ የመዲናይቱ ነዋሪ ቅሬታ አንዳለው ስንነግረው ባልጠበቅነው ሁኔታ የአንድ አጁን መዳፍ በሴላ እየጠበጠበ የቅንጅት ፈረሶች የሆኑትን የከተማ ታክሲዎች ከጨዋታ ውጭ ሳናደርግ ውሳኔው አይቀለበስም የሚል ምላሽ ሰጠን በአቶ መለስ ካፈርኩበት ቀናት አንዱ ሆኖ ተመዘገበ። ከዛን ቀን በኃላ ይህንን ጥያቄ ህዝቡ ምን ይላል ከሚለው ሳምንታዊ ሪፓርት ሰረዝነው አቶ መለስ እንደዛተው ታክሲዎችን ለመተካት ያላሰለሰ ጥረት ቢያደርግም አልተሳካም ከቅን ልቦና ያልመነጨ በመሆኑነ በአጠቃላይ መልኩ እነ አርከበ ባቀረቡት ጥናት መሰረት ቅንጅት አዲሳባን በተረከበ በሁለት አመት ውስጥ መዲናይቱ ከተማ አቀፍ ኪሳራ ሕፐዩርርነ በማወጅ የድሬደዋ ተከታይ ትሆናለች ይህንንም ተከትሎ የእነ አርከበ ቡድን አዲሳባን እንደ ነውጥ መሳሪያ በመጠቀም መሬት አንቀጥቅጥ ተቃዉሞዎችና አመፆች በጥቅም ላይ ይውላሉ ግጭቶች በህዝቡና አስተዳደሩ በማይቆጣጠረው ፓሊስና ፀጥታ ሀይሉ መካከል ይሆናል። ፀቡ የተገለፀበት አግባብ ለየቅል ሆነ የአርከበ ቡድን የተንኮል አቅዱን በሁለት መሰረታዊ ጉዳዮች ላይ አደረገ የኢትዮኤርትራ ጦርነትና ህውሀት በአቶ መለስና በረከት እየተገፉ ነው በማለት በመጋቢት ወር ዓም የህዉሀት መሰንጠቅ ምክንያቱ የኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ላይ የተነሳው ልዮነት እንደሆነ የአልጀርሱ ስምምነትና እሱን ተከትሎ የተሰጠው የፍርድ ቤት ውሳኔ ትግራይን ለመጉዳት የታሰበ መሆኑ መለስ የትግራይን መሬት ለኤርትራ አሳልፎ መስጠቱ የባድመ ጉዳይ አንዳለቀለት ውስጥ ለውስጥ አሰራጩ አብዛኛው የህውሀት ካድሬ አቶ መለስ በኤርትራ ጉዳይ ላይ በያዘው አቋም ደስተኛ ስላልነበረ በአርከበ መስመር ተሰለፈ በሰውየው ላይ ያለው እምነት አየተሸረሸረ ሄደ። በዚህ ጉብዝናው ምከንያት በአሊ አብዶ የጨለማ ወቅት የዞን አራት ሊቀመንበር በዘመነ አርከበ ደግሞ በልዩ ምደባ የአዲስ ከተማ ከንቲባ ሆነ ቀጥሎም የአዲሳባ ኢህአዴግ ከንፍ ስራ አስፈፃሚ ተሹሞ እኛን ተቀላቀለን አባይ ሰነዱን በድጋሚ ቃል በቃል አብራራ። እቅድ ኢህአዴግ ቢሮ በእነ ተወልደ ተዘጋጅቶ በመመሪያ መልኩ ለእነ መለስ ይወርዳል የእዝ ሰንሰለቱ ከድርጅት ወደ መንግስት ይፈሳል በዚህ መሰረት ተወልደ መለስን ሰለሞን ጢሞ ኩማ ደመቅሳንቢተው በላይ አባተ ኪሾን ተስፈማሪያም ደግሞ አሊ አብዶን የስራ ስምሪት ይሰጣሉ አቶ መለስም ሆነ ሌሎች ካድሬዎች ድርጅቱ ካስቀመጠው ውጭ ዝንፍ አይሉም ለሀገሬውና መዲናይቱ ህዝብ መግለጫ አንኳን ሲሰጡ የተቀመጠውን አቅጣጫ አይለቁም ድርጅቱን የሚመሩት ለጋዜጠኛው ጥያቄ አውጥተው ይሰጡታል ከአቶ መለስ ጋር ደግሞ በጋራ አቅጣጫ ያስቀምጣሉ በድምጽ ብልጫ ከተወሰነው ውጨ አላመንኩበትም የሚባል ነገር አይሰራም የተጻፈውን የራስ አድርጐ ከማነብነብ ውጭ። ይህ የተሳሳተ ነው ኢህአዴግ ላይ የመዲናይቱ ህዝብ የወሰነው በሁለተኛው አገር አቀፍ ምርጫ ዓም ነበር በዚህ ምርጫ ኢህአዴግ አሳፉሪ ሸንፈት ተከናንቧል። ርግጥም ፓርቲው አንደሚለው በዲሞከራሲ ግንባታ አስከ አሁን የሚታወቁት የምርጫ ስርአቶች የብዙሀን ድጋፍ የተመጣጠነ ውክልና አና የአብላጫ ድምፅ ሲሆኑ ኢህአዴግ የሚጠቀመው በመጨረሻ የቀረበውን ነው ይህ የምርጫ ስርአት ከተወዳዳሪዎች መካከል አብላጫውን ድምፅ ያገኘ አሸናፊ የሚሆንበት ሲሆን በመሰረቱ ዲሞክራሲያዊ ገፅታ ያለውና ምርጫውን ለማስፈፀም ቀላልና ወጪ ቆጣቢ ነው የኢህአዴግ ሁለተኛ መከራከሪያ በአለማችን የዲሞክራሲያዊ ግንባታ ቁንጮ ላይ የተቀመጡት አነ አንግሊዝና አሜሪካ የሚጠቀሙት የአብላጫ ስርአት እንደሆነ በመግለፅ የዲሞክራሲያዊነቱን መተማመኛ አማኝ እንደሆኑ ማሳየት ነው የኮረጅነው ከአነዚህ ሀገሮች ነው በማለት አቶ በረከትና ኢህአዴግ ይህንን አመክንዮ ሲያቀርቡ አንድም ጊዜ ከጀርባ በታኮነት ያስቀመጡትን በምርጫ ጣቢያዎች የሚወዳደሩ እጩዎችን ብዛት የሚያሳየውን የምርጫ ህግ አይጠቅሱም። የቄራና ጐፉ ህዝብ ኢህአዴግ ያቀረበለትን ዶክተር ኢንጂነር ጋዜጠኛና ከፍተኛ ነጋዴ ወደ ጐን ትቶ መቃብራቸው የተማሰ በምርኩዝ የሚሄዱ ማንበብና መጻፍ የማይቸሉ የመኢአድ አባላትን መረጠ ይህም ህዝቡ እንደ ወረዳ ሁሉ ኢህአዴግ ላይ ያለውን የመረረ ጥላቻ ፍንትው አድርጐ የሚያሳይ ሆነ እንደ አውነቱ ከሆነ የስምኦን ልጅም ሆነ አቶ መለስ ወረዳ መጥተው ቢወዳደሩ ኖሮ ወይ ለክብራቸው ሲባል ኮሮጆ አስቀድሞ ይገለበጣል አሊያም የሽንፈት ጽዋቸውን ይጐነጫሉ ጽጃ የወረዳ ነዋሪም ተመሳሳይ አርምጃ የወሰደ ቢሆንም በቆጠራው ወቅት በተሰራ ማጭበርበር ኢህአዴግ ተረፈች በወረዳው የትግራይ ተወላጅ ይበዛል በማለት የትግራይ ህዝብ በወረዳ ኢህአዴግን ታደገ የሚል ማጭበርበሪያ እንዲናፈስ ተደረገ የወረዳ ምርጫ አንዲመራ የተመደበው ነባር የህውሀት ታጋይ ገእግዚአብሔር አግዜሩ ይባላል። መመሪያ ቁጥር አንድ በከተማዋ የሚገኙ ህገ ወጥ ይዞታዎችን ወደ ህጋዊ ለመለወጥ በሚል ሽፉን ተዘጋ በተቃራኒው መመሪያውን ለማፅደቅ አንድ ሳምንት ሲቀረው የተዘረፈው መሬት ብዛት በሁለት አመት ውስጥ ያለው በአጠቃላይ ተደምሮ በእጥፍ ይበልጥ እንደነበር በወቅቱ የካቢኔ አባል የነበረው አበበ ዘልኡል ያቀረበው ጥናት አመላከተ አበበ በቁጭት ተሞልቶ መመሪያውን ማውጣት አልነበረብንም በዚህ መመሪያ ምክንያት የተዘረፈው የህዝብ ንብረት ከሁለት ቢሊዮን ብር በላይ ሲሆን ይህም ከመቶ በላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ቢያንስ በቀበሴ አንድን እና አስር ደረጃውን የጠበቁ መለስተኛ ሆስፒታሎችን ይሰራ ነበር ብሎ መመሪያው በፀደቀ አንድ ወር ሳይሞላው አጋለጠ። ከዚህ አኳያ መመሪያ ቁጥር አንድ አግባብ አንዳልሆነ የሚያረጋግጠው የምክር ቤቱን ማቋቋሚያ ሆን ተብሎ ወደ ጐን በመተው በካቢኔ ደረጃ በቆረጣ መመሪያ አንዲሆን መደረጉ ነበር በወቅቱ በፍትህና ፀጥታ ቢሮ ውስጥ የህግ ነከ ጉዳዮች ሀላፊ የነበረው ወልደሰንበት በመመሪያ መልከ መውጣቱን በመቃወም የጉዳዩ ባለቤት የሆነው የአዲሳባ ህዝብ መምከር ይኖርበታል ከሁለት ቢሊዮን ብር በላይ የሆነ የህዝብ ሀብት ለህገወጦች እየሰጠን መሆኑን ነዋሪው አውቆ መነጋገር አለበት ይህ ካልተቻለና ጉዳዩ ህግ ሆኖ መውጣት አለበት ከተባለ ቢያንስ የህዝብ ውከልና ያላቸው የምክር ቤት አባላት ተወያይተውበት በአዋጅ መልኩ መዘጋጀት ያስፈልጋል በማለት አጥብቆ ተከራከረ። በዚህም ምክንያት ከደረጃው ዝቅ እንዲል የተደረገ ሲሆን በምርጫ የቅንጅት ቀንደኛ ደጋፊ ሆኖ አስተባብሯል በሚል መረጃ ቀርቦ ለረጅም ጊዜ እንዲንሳፈፍ ተደርጓል በመመሪያ ቁጥር አንድ ላይ ቀጥሎ የተነሳዉ ለምን ቁጥር አንድ ተባለ የሚለው ነበር። አጀንዳው በሙሉ መመሪያ ቁጥር ሁለት በአስቸኳይ መውጣት አለበት ሆነ አማራጭ የለም አርከበ የተጠየቀው መስዋእትነት ተከፍሎ መሸጥ አለበት ይህ ካልሆነ አቶ መለስ ከአድማስ ባሻገር የተመለከተው ምርጫ ግቡን አይመታም እናም አርከበ ተሸጠ። ርግጥም አቶ መለስ እንዳለው የአዲሳባ ስራ አስኪያጅነት ስልጣን ከከንቲባው በላይ ነው የከተማዋ የዝርፊያ ማእከል የሆኑት አንደ ማዘጋጃ ቤት መሬት መንገድ ውሀ በቁጥጥር ስር የሚውሉት በስራ አስኪያጁ ነው ኢህአዴግ ቢሮ ከንቲባ ማን ይሁን ከሚለው በላይ የሚያጨቃጭቀው ስራ አስከከያጅ መምረጥ ላይ ነበር አቶ አርከበ በለስ ቀንቶት በአሱ ዘመን የህውሀት ካድሬውንና የመንገዶች ባለስልጣኑን አስመደበ ቀጥሎ መኩሪያ ሀይሌን በመጨረሻም የቅርብ ዘመዱን ሀይሌ ፍስሀ። በዳግም ምርጫ ዓም ኢህአዴግ መዲናይቱን በተቆጣጠረ ወቅት አቶ በረከት ቢሮ ውስጥ እኔ ህላዌ ካሚል ፀጋዮና ፍሬህይወት ተሰብስበን ከንቲባ ስራ አስኪያጅ የካቢኔ አባል አየመለመልን ነበር። ያልተጠየቀውን ዘባረቀ ወይዘሮ ገነት ጋር ምንም ግንኙነት የለንምች ባይሆን ተፈራ ዋልዋን ጠይቁት አለ ግምገማውን የሚመራው አባይ ፀሀዬ ባልተጠበቀ ሁኔታ ፊቱ ተለዋወጠ ሴትየዋ የኢህአዴግ አባል ስላልነበረች በግምገማው አልተገኘችም ስጋዋ ከመቦጫጨቅ ግን አልዳነም የከተማውን ፉይናንስ በተለይም የበጀት ዝግጅትና ገቢ መቀመቅ የከተተችው አሷ መሆኗ መግባባት ላይ ተደረሰ ግን ደግሞ አንደዚህ ከፍተኛ የብቃት ማነስ ችግር አንዳለባት አየታወቀ አንዴት ከተፈራ ዘመን አስከ አሊ አብዶ በካቢኔ አባልነት አገለገለች የሚለው የካድሬው ያልተገለፀ ሀሜት ሆነ በተለይ አርከበ አቁባይ የአንድ ከተማ የደም ስር የሆነውን ገቢ ገነት አበራን ለሚመስሉ ደካማ ሰዎች የሰጠው አካል ተጠያቂ ነው በማለት ደጋግሞ ተናገረ። አባይ ፀሀዬ ተወራጨ በኢህአዴግ ቤት መኖር ሁሌም ከኋላ አንደ ጅራት የሚጐተት ጉድ አለውና ቀኑን ጠብቆ ሌላ ተአምር ተሰማ ወይዘሮ ገነት አበራ የአዲሱ ከንቲባ አርከበ አቁባይ የፉይናንስና ኢኮኖሚ ቢሮ ሀላፊ ሆና ካቢኔውን ተቀላቀለች ከፊት መስመርም ተሰለፈች ታሪክም ራሱን ደገመ መጀመሪያ አሳዛኝ ቀጥሎ ቧልት በሚመስል መንገድ ብዙዎች በአርከበ ጊዜ የነበረውን ማዘጋጃ ቤት ባለ ሶስት በር ያለው አዳራሽ ስያሜው ተቀይሯል አድርገው ይቆጥሩት ነበር ታዲያ ወደ እልፍኙ ለመግባት የበሩን ቁልፎች የያዙት ሰዎች ሶስት ነበሩ። ከንቲባ ባልሆኑባቸው ክፍለከተሞች ደግሞ ምክትል ነበሩ ኮልፌ ነጋ በርሄ በአሁን ሰአት የኢህአዴግ ስልጠና ማእከል ካድሬአራዳ መውጫ ስራና ከተማ ልማት አዲስ ከተማ ታደለ ፓስታ ድርጅት ስራ አስኪያጅ ቦሌ ገተንሳይ ስራና ከተማ ልማት ጉለሌ ከበደ ብሩስራና ከተማ ልማትን ልደታ ዘሩ የገቢዎች የሰው ሀይል ዳሬክተር በፊት መስመር ላይ የህውሀት ካድሬዎች አንዲሰለፉ የተደረገው በታቀደ መልኩ በአቶ መለስ አባይ ፀሀዮና አርከበ መቀናጆ ነበር። ከጉራጌ ተወላጆች ጋር ተያይዞ የነበረው ውሳኔ በተቻለ መጠን በፓርቲ አመራር ደረጃ እንዳይመጡ መከላከል ነበር ርግጥ በዚህ ጉዳይ የመጀመሪያው ተጠያቂ አቶ መለስ ሲሆን አርከበ የማስፈፀም ሚና ነበረው በዚህ ምከንያት በአርከበ የከተማ ካቢኔ ውስጥ የጉራጌ ተወላጅ የሆነ ካድሬ አልነበረም ከፍለ ከተማ ከነበረው ስራ አሰፈጻሚ ውስጥ ሁለት ካድሬዎች ብቻ የጉራጌ ተወላጆች ነበሩ የላፍቶው ሚፍታህ አብዶና የጉለሌው ዳንኤላ አርጋው የሁለቱ ካድሬዎች መጨረሻም አሳዛኝ ነበር ሚፍታህ ወደ ቃሊቲ ሲወረወር ዳንኤል ከስራና ድርጅት ተባሯል ወራት ከፈጀ ዝጉብኝ በኃላ የለውጥ ኮሚቴ አባላት ስራቸውን ማጠናቀቃቸው ታወቀ ይህንን በማስመልከት አርከበ በቴሌቪዥን ቀርቦ መግለጫ ሰጠ። የአዲሳባ ኢህአዴግ መዋቅር እንኳን የመሪነት ሚና ሲጫወት ቀርቶ ለህዝብ ጭራነት ብቁ አልነበረም ካድሬውና አባላቱ በተግባር ኢህአዴግ አልነበሩም ዘባተሎውን አሊ አብዶ ጨምሮ የአብዮታዊ ዲሞከራሲ ምንነትና ግብ ምን እንደሆነ የማያውቁ ነበሩ አቶ መለስ ይሄንን ክፍተት በማየት ነበር የተማረ ሰው ፈልጉ ያለው በዚህ ምክንያት ለነባሩ ካድሬ በስራ መቀጠልና መባረር ትልቁ መመዘኛ የትምህርት ደረጃ ሆኖ ብቅ አለ። ኢህአዴግ ከፍተኛ የአርሶ አደር ፍቅርና ድጋፍ ያተረፈ ድርጅት ነው በረከት ስምኦን ሁለት ምርጫዎች ወግ ኢህአዴግ በምርጫ አሸናፊ ሆኖ የሚወጣባቸው ምክንያቶች በዝርዝር የቀረቡት በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ የድርጅቱ ካድሬዎችና አባላት በስነ ምግባር መመሪያው ላይ በፕላዝም ሁለትዮሽ ኮንፍረንስ በተካሄደ ወቅት ነበር። በዚህ ምክንያት የአብዮታዊ ዲሞክራሲ ትክክለኛነት ይረጋገጣል የሚል ማሳመኛ ቀረበ ከዚህ በተቃራኒው የመታፈን አድል ካጋጠማቸው ግን የአብዮታዊ ዲሞክራሲ የተሻለ አማራጭነት አብሮ ይታፈናል ተቃዋሚዎችንም አርቃናቸውን ማስቀረት አይቻልም የተተነተነ የፓሊሲ አማራጭ አንደሌላቸው ህዝቡ መገንዘብ አንደማይቸል ተገለፀ ይህ ሳይሆን ቀርቶ የመታፈን አድል ካጋጠማቸውና አመለካከታቸው ወደ አደባባይ ካልወጣ አብዮታዊ ዲሞክራሲ የአስተሳሰብ ልአልናውን ማረጋገጥ ስለማይቻል የተቃዋሚ አስተሳሰብ ውስጥ ውስጡን የመፉፉት አድል ያገኛል የሚል ነበር ይህን ሀሳብ ለማጠናከር በኢህአዴግ ቢሮ ሁለት ሰነዶች ተዘጋጅተው ካድሬው አንዲሰለጥንበት ተደረገ የመጀመሪያው ሰነድ የህዝብ ግንኙነት መርሆዎች በሚሜል ርአስ የተዘጋጀ ሲሆን ስለ ህዝብ ግንኙነት ምንነት ብሄራዊ መግባባት የኢህአዴግ የህዝብ ግንኙነት አላማና ማግቦች የዲሞክራሲና አስተምህሮ ተቋማት ፓለቲካ ፓርቲዎች ወዘተ የሚያነሳ ነበር። የአዲሳባ መንገዶች ባለስልጣን ለመምራት ከፌደራሉ መንገዶች ባለስልጣን ቀጥተኛ ዝውውር ተደረገ በመሆኑም የሚካሄዱት ግንባታዎች በመሰረቱ የህብረተሰብ መፈናቀል ሳያመጡ በባዶ ቦታዎች ላይ በመከናወናቸው ለልማቱ ማስኬጃ ከፌደራል መንግስት የሚመደበው ገንዘብ የተትረፈረፈ በመሆኑ ሁሉም ተቋማት በአቶ መለስ ማስጠንቀቂያ ቅድሚያ ለአዲሳባ በመስጠታቸውና በመቀናጀታቸው ከፍተኛ ሙያተኞች ከፌደራል መንግስትና ከነባሩ መዋቅር በመመደባቸው ምክንያት በመዲናይቱ ታይቶ የማይታወቅ ለውጥ ሊመጣ ቻለ ስለዚህም በአዲሳባ የተመዘገበው ልማት በአቶ መለስ መልካም ፍቃደኝነት ላይ የተመሰረተ አንደ ሰጐን አንቁላል በተደረገ ክትትል ሲሆን ምንጩ ደግሞ መለወጥን ከአምነት የወሰደ ሳይሆን ምርጫ የፈጠረው ፍራቻና መረበሽ ነበር በመሆኑም በኢህአዴግ ግንዛቤ ወደ ምርጫ ሲገባ አንደ ማሸነፊያ ምክንያት የተወሰደው አዲሳባ የሚታይ ለውጥ አምጥታለች የከተማዋን አድገት ህዝቡ መመስከር ጀምሯል የስራ እድል ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ተፈጥሯል የሚል ነበር ይህ በመሆኑ ለኢህአዴግ ማሸነፍ ምቹ ኢኮኖሚያዊና ፓለቲካዊ ምህዳር ተፈጥሯል የሚል ድምዳሜ ተይዞ ነበር። ታፁታ ምእራፍ አስራ አምስት የምርጫ ዋዜማ ፕሮፌሰር መራራ በአይናችን ስር ቁጭ ባሉበት ወንበር ወደታች ሲሰምጡ ተመለከትን በረከት ስምኦን የሁለት ምርጫዎች ወግ ከመስከረም በፊት ኢህአዴግ ምርጫ አመራበታለሁ ብሎ ባወጣው እቅድም ሆነ የተቃዋሚዎች የሀይል አሰላለፍ ትንታኔ ላይ ቅንጅት የሚባል ፓርቲ አልነበረም ቅንጅት ለኢህአዴግም ሆነ ለሴሎች ተቃዋሚ ድርጅቶች ብራ መብረቁ ነበር በህብረተሰቡ ዘንድ ታዋቂ የሆኑት እነ ፕሮፌሰር መስፍን ዶክተር ብርሀኑ ዶከተር ያቆብ ዶከተር በፍቃዱ ይሳተፉሉ ብሎ የገመተ አልነበረም እንኳን አኛ አቶ መለስም ሆነ የደህንነቱ መስሪያ ቤት የሚያውቀው ነገር አልነበረም ከዓመታት በኋላ ከበረከት አንዳረጋገጥኩት እነዚህ ምሁራን ለተቃዋሚዎች የኋላ ደጀን አንደሚሆኑ የተጠበቀ ቢሆንም በግላጭ የተቃዋሚ ፓርቲ ይመሰርታሉ ሌላውንም ያቀናጃሉ የሚል ግምት አልነበረም። በሁለተኛ ደረጃ የኢትዮጵያ ህዝብ ለተማረ ሰው ያለው ከበሬታ አጅግ በጣም ትልቅ እንደሆነ ኢህአዴግ ይገነዘባል። ኢዴአፓ አና መኢአድ በገነቡት አጥር ላይ ቆሞ የነበረው ህዝብ እንደ በርሊን ግንብ አጥሩን አፈራረሰው ልክ አቶ መለስ በድህረ ምርጫ ግርግሩ ወቅት እነ ዶክተር ብርሀኑ ነጋን ቤተመንግስት ጠርቶ ያስቸገራችሁን አጥር ላይ ቆማችሁ ነው አንዳለው በመሆኑም በአንድ በኩል ኢህአዴግ ባልገመተውና ባላቀደው ሁኔታ ቅንጅት መፈጠሩ በሌላ በኩል ቅንጅትን የመሰረቱት ሰዎች ተከለሰሰውነት ከኢህአዴግ ካድሬዎች ገዝፎ መታየቱ አንግበውት የነበረው ኢትዮጵያዊነት አጀንዳ በምርጫ ክርክሩ ወቅት በአግባቡ ራሳቸውን መሸጣቸውና አማራጭ ፓሊሲ መያዛቸው የምርጫ የፓለቲካ ምህዳር በሀገር ደረጃ ግልብጥብጡን አወጣው መስከረም ሳይጠባ የምናሸንፍባቸው ምክንያቶች ተብለው በኢህአዴግ የቀረቡት ቁምነገሮች በዜሮ ተባዙ ኢህአዴግ ተደናገጠ። ብዙ የተለፉበት ሰላማዊ ሰልፍ ምርጫ አንድ ወር ሲቀረው ከተፈጠሩት ስራዎች ሌላኛው በመስቀል አደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ ነበር የሰላማዊ ሰልፉ ምከንያት ኢህአዴግ በምርጫ ከርከክሩ ወቅት የደረሰበትን ከፍተኛ ሽንፈት ለመቀልበስ እንደ አንድ አማራጭ በመወሰዱ ነበር በየአለቱ ማታ ኢህአዴግ ቢሮ በምናደርገው ግምገማ መሬት አንቀጥቅጥ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ አንደምንቸል መግባባት ላይ ተደረሰ ይህን ማድረግ የምንቸልባቸው ምክንያቶች በዝርዝር ቀረቡ እነዚህም በየምርጫ ክልሉ ከመራጩ ብዛት በአጥፍ ከሁለት ሚሊዮን በላይ የተደራጁት ኔትወርኮች ከኔቶርኮቹ ውስጥ ከ በሳይ በ ኤ ደረጃ የሚታይ በመሆኑ ኢህአዴግን ከመምረጥ አልፎ ኢህአዴግን ምረጡ በሚል ቅስቀሳ አየተሳተፈ መሆኑ የከተማዋ የልማት ትንሳኤ በኢህአዴግ አማካኝነት መበሰሩ የኢህአዴግ ልማታዊ አቅጣጫ በመላ ሀገሪቱ ያስመዘገበው ባለሁለት አሀዝ አድገት የፈጠረው መነቃቃት ዋና ዋናዎቹ ነበሩ ከሰላማዊ ሰልፉ ጋር ተያይዞ አከራካሪ ከነበሩት ቁምነገሮች መካከል መቼ ይካሄድ የሚለው ነበር በአማራጭነት የቀረቡት ቀኖች በምርጫው የመጨረሻ ሳምንት የሚውሉት ቅዳሜአእሁድ እና ሀሙስ ነበሩ። ከፀጋዬ ጋር ምርጫ ጣቢያዎችን አና የኢህአዴግ ምርጫ መከታተያ ጊዜያዊ ቢሮዎችን እየዞርን መከታተል የጀመርነው ከለሊቱ ዘጠኝ ሰአት ነበር የቄራ ጐፉ ጐተራ መንገዶች ጭር ያሉ ሲሆን አልፎ አልፎ ጥንድ ጥንድ ሆነው በፍጥነት የሚሄዱ ወጣቶችን አንመለከት ነበር ሁኔታው ቀልቤን ስለሳበው ለሶስት ያህል ጊዜ መኪናችንን አቁመንና ማንነታችንን ገልፀን ወጣቶቹን ጠየቅናቸው ከስድስት ኪሎ እና አራት ኪሎ ዩንቨርስቲ በአግራቸው እንደመጡ እና የቅንጅት ምርጫ ታዛቢዎች እንደሆኑ ገለጹልን ሁለቱ ወጣቶች ሀና ማሪያም አካባቢ ወደሚገኘው ምርጫ ጣቢያ እየሄዱ አንደሆነ ስሰማ ማመን አቃተኝ ርግጥም ገና ከአንድ ሰአት በላይ በእግራቸው አንደሚጓዙ መገመት ሳስበው ደከመኝ የሚለውን የአቶ መለስ የዘወትር አባባል ያስታውሳል ለሊት አስራአንድ ሰአት ላይ ሁሉንም ጣቢያዎች ዞረን ተመለከትን የኢህአዴግ ታዛቢዎች አና ምርጫውን የሚከታተሉ ቡድኖች ቦታ ቦታቸውን ይዘዋል በቡድኑ አባላት ዘንድ ተስፉ ማጣት የሚነበብ ቢሆንም የተሰጣቸውን ተልአኮ ሳያንጠባጥቡ ለመፈፀም የሚሰስቱት ጉልበት የላቸውም በዚህ አደገኛ ሰአት በምንም መልኩ ተጠያቂነት የሚያስከትል ጥፉት ላለመስራት መወሰናቸው ያስታውቃል። አዲሳአባ በሰባት ማዘዣ ጣቢያ ተከፈለች ክፍለ ከተማ እና ቀበሌ ባልተገለፀ አዋጅ እንዲፈርሱ ተደረገች ነባሩ መዋቅር ከስራ ውጪ ተደረገ አርከበን ከትግራይ አጅበውት የመጡት ካድሬዎች የሰባቱ ማዘዣ ጣቢያ ሀላፊዎች ተደረጉ አርከበ እቁባይ ፊት አውራሪያቸው ሆነ እያንዳንዱ ውሳኔ በአነሱ ስር ማለፍ ግዴታ ሆነ ከየትኛውም የኢህአዴግ ካድሬዎች በላይ ቄም የቋጠሩት እነዚህ የህውሀት ካድሬዎች ከተማዋን ራቁቷን ለማስቀረት ዘመቻ ጀመሩ በአስተዳደሩ ቋት ውስጥ ያለው ገንዘብ ሙሉ በሙሉ እንዲወጣ ተደረገ ለዓመታት ተቋርጦ የነበረው የመደበኛ ደሞዝ ጭማሪ ተፈቀደ። የዚህ ግምገማ ይዘቶች ኢህአዴግ የህብረተሰቡን ችግር ለማዳመጥ የሚያስችል ጆሮ አልነበረውም አሳምኖ ከማሰራት ይልቅ በአስተዳደራዊ ጫናዎችና የተለያዩ አስገዳጅ ተጽእኖዎችን አንጠቀም ነበር ፀረዲሞክራሲያዊ አካሄዳችን ህብረተሰቡ አእንዲያማርርና ተስፉ አንዲቆርጥ አድርጐታል ለመልካም አስተዳደር እጦት ምክንያት የሆኑ ችግሮችን ተቋማዊ በሆነ መንገድ አልፈታንም የሚል ነበር ፐፅፀ ሬረይ ፐዐዐ ሂፎ በሁለተኛ ደረጃ ኢህአዴግ ሽንፈት ያጋጠመው የተጀመሩት ተስፉ ሰጪ የልማት ስራዎች አጅግ በጣም ትንሽ አና ዘግይተው የተጀመሩ በመሆናቸው አንደሆነ ተገለፀ በተለይም በከተሞች ኢህአዴግ ስራ የጀመረው ዘግይቶና በቁጥቁጥ በመሆኑ የስራ አጥነት ቁጥር በተለይም በወጣቱ አደገኛ ደረጃ ላይ መድረሱ ለምርጫው መሸነፍ አበይት ምክንያት እንደሆነ ተነገረ። ዶከተር ካሱ ኢላላን የኮሚቴው ጠርናፊ አደረገ ከአባላቱ መካከል ካሚል ኢህአዴግ ቢሮ ትአግስቱ የጉራጌ ዞን ሊቀመንበር ሺሰማ የአዲሳባ ኢህአዴግ ዞን አንድ ሊቀመንበርን ፈለቀ የዞን ሶስት ድርጅት ጉዳይ ሚፍታህ ስራና ከተማ ልማትዳንኤል የጉለሌ ካድሬና በመሀል ከድርጅት የተባረረነ ሰለሞን ኢትዮጵያ ሬድዮ ስራ አስኪያጅ ይገኙበታል። በመጀመሪያ የተከናወነው አራቱ የብሄር ድርጅቶች አሉኝ ከሚሏቸው ካድሬዎች አንድ አንድ ሺህ በድምሩ አራት ሺህ መልምለው ሲቪሺል ሰርቪስ ኮሌጅ አንዲያስገቡ ተደረገ በረከት ስምኦን ለሁለት ወር የፓርቲውን የህዝብ ግንኙነት መርሆዎች አሰለጠነ ይህን ተከትሎ በሁሉም የፌደራል ተቋማት የልማት ድርጅቶች የፓርላማ ጽህፈት ቤት ምርጫ ቦርድ የአዲሳባ መስተዳድር ውስጥ ከ ካድሬዎች የህዝብ ግንኙነት ሀላፊና ኮሙዩኒኬተር የሚል ስያሜ በመስጠት ተመደቡ በኪራይ ቤቶች ባለቤትነት የተያዙት የመንግስት ቤቶች ተለይተው በነፃ ታደላቸው። የበረከት አስተያየት ያልተዋጠለት ተፈራ በድጋሚ እጁን ቢያወጣም መለስ ነፈገው በቀጥታም ሰስራ አስፈፃሚው ውክልና ይሰጥአይሰጥ የሚለው ላይ ድምፅ አንዲሰጥበት አደረገ ከዋልዋ ውጭ ጥናቱን ሰርተንና ሴራ ጠንስሰን የገባነው ህላዌሬድዋንካሚል ፀጋይ ሀይለማርያም አና በአጠቃላይ ጉባኤተኛው መለስን በመደገፍ ለፓሊት ቢሮው በውክልና እንዲሰጥ ወሰን የተፌ አጅ ለብቻዋ ተቀሰረች በንጋታው የወጣው ሪፓርተር ጋዜጣ የፊት ገዱ ሙሉ ሽፉን የተፈራ ዋልዋ ፎቶ ሆነ በማስታወሻነት በማህደሬ አስቀመጥኩት በፎቶ ግራፉ ወይዘሮ አዜብ ዋልዋን በአግርሞት ትመለከታለች ኩማ ደመቅሳ ሙክታር ከድርና ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ይስቃሉ ጉባኤው በተካሄደ በሳምንቱ ስራ አስፈፃሚው ሳይጠራ የኢህአዴግ ፕሮግራምና ህገ ደንብ ተሻሻለ የአዲሳባ ወጣት ከሴላው አካባቢ በተለየ የኢህአዴግ አባል መሆን ከፈለገ በብሄር ድርጅት መታቀፍ ሳያስፈልገው በግለሰብ ደረጃ መሆን አንደሚችል ይፉ ሆነ ይህም ኢህአዴግ የግለሰብ አባል የለውም የሚለውን ህግ አንዲሻሻል አደረገ ከመዲናይቱ ኢህአዴግን በራሱ ጉባኤ አባረርነው ርግጥም ክስተቱ ታሪካዊ ነበር ኢህአዴግ የመኖርና ያለመኖር ጥያቄ ሲያጋጥመው ፕሮግራሙንና ህገ ደንቡን ያሻሻለበት ወቅት። ይህ የከተማዋ አይን ቦታ ላይ የተቋቋመ ትምህርት ቤት ከ አመት በላይ ያስቆጠረ ሲሆን ባለቤቱ የአካባቢው ህዝብ ነው ነዋሪው አንደ ማንኛውም የህዝብ ትምህርት ቤት ከመንግስት ድጋፍ አየተደረገለት ልጆቹን ያስተምርበታል። እስቲ ቦሌ ላይ የተደረገውን ጆሮአችንን ደፍነን እናንብብ የቦሌን የመሬት ዝርፊያ የመሩት ሶስት የህውሀት ካድሬዎች ናቸው የከንቲባ ጽቤት ሀላፊው ዶክተር አብርሀም የቦሌ ከንቲባው ሀስላሴና ትምህርት ቢሮን ያገላበጠው ገተንሳይ ሶስቱ ጓዶች በመጀመሪያ ያደረጉት በፌዴራል ተቋማትና አዲሳባ ተመድበው ለሚሰሩ ካድሬዎችና ባለስልጣናት መሬት መስጠት ነበር የሀገሪቱ ደህንነት ሚኒስትሮች የፌዴራል ፓሊስ ኢህአዴግ ቢሮ አጋዚ ክፍለ ጦር የመከላከያ ጀነራሎች የትግል ዘመናቸው ከ በፊት የነበሩና ከኮረኔል ማዕረግ በላይ የሆኑ ወታደሮች የከልል ካቢኔ አባላት ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ኤፈርት ዋልታ ሬዲዮ ፉና የአዲሳባና ከፍለከተማ ካድሬዎችና ባለስልጣናት ሙሉ ለሙሉ በሚባል መልኩ መሬት የወሰዱት በዚህ ክፍለ ከተማ ነው ሶስቱ ካድሬዎች ወሳኝ የሆኑ አካላትን አፍ የማዘጋት ስራ በዚህ መልኩ ካከናወኑ በኃላ ፊታቸውን ወደራሳቸው አዞሩ። አንድ ሀሙስ የቀራት ነፍሱ ተበሳጨች ህላዌ ነብሴ አያለ የሚጠራው የድርጅቱ እስትራቴጂስት መሸነፉን በውስጡ አመነ ጁ ምአራፍ ሃያ አንድ የህዝብ መድረኮች ኢህአዴግ ከምንም ነገር በላይ ህዝቡን ያከብራልይፈራልም ሁሌም እንደሚለው ከህዝብ ውጭ ሌላ ጌታ የለውም በረከት ስምኦን የሁለት ምርጫዎች ወግ የመዲናይቱ ወኪሎች ከምርጫ ግርግር ረገብ ማለት በኋላ የአዲሳባን ህዝብ ሙቀት መለካት ያስችላሉ የተባሉ ውይይቶች እንዲጀመሩ ከአቶ መለስ ጋር በሚኖረን ሳምንታዊ ስብሰባ ተወሰነ ውይይቱ ነዋሪዎች ሴቶችና ወጣቶች በሚል አንዲከፉፈልና ሶስት መድረኮች አንዲሆኑ አቶ መለስ አሳሰበን የተወያዮች ዋነኛ መመዘኛ በግልፅ ተመዝግበው ከሚንቀሳቀሱ የተቃዋሚ አባላት ውጪ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል የሚወከሉና ነዋሪው ወኪሎቼ ናቸውብሎ ከሚሜያምንባቸው ጋር ብቻ አንዲሆን አቅጣጫ ተቀመጠ። ይህም ከዚህ በፊት ሲሰራበት የነበረው ሰዎችን በብሔር ማንነታቸው የመከፉፈልና ማወያየት ስራ አዲሳባ ላይ አንዲቋረጥ በምትኩ በማህበራዊና አድሜ አደረጃጀታቸው ብቻ እንዲሆን ተደረገ ከአቶ መለስ ጋር በተሰበሰብን ወቅት የብሄር አዘል ስብሰባ ይሻላል የሚል አስተያየት በአርከበ አቁባይና በረከት ስምኦን ቀርቦ የነበረ ሲሆን አቶ መለስ ንዴት በተቀላቀለበት ሁኔታ ወደድንም ጠላንም የብሔር ፓለቲካ አዲሳባ ላይ አፈር ልሶ የማይነሳበት ደረጃ ላይ ደርሷል የሚል አስገራሚና ያልተጠበቀ አስተያየት ሰጠ። የአዲሳአባ ህዝብ የመጀመሪያው እና በሁሉም መድረኮች ልዩ ትኩረት ያገኘው የህዝብ ጥያቄ ኢህአዴግ ይቅርታ ያድርግልን አጥፍተናል የሚለው ነበር። ክፍል ስድስት ምርጫ ምእራፍ ሃያ ሁለት የ ምርጫ አቅጣጫሜዎች በኢትዮጵያ የመድብለ ፓርቲ ዴሞክራሲ ተስፉ የለውም ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ በ ዓም በአዲሳባ ዳግም ምርጫ አንደሚካሄድ ከመታወጁ አንድ አመት በፊት በኢህአዴግ ቢሮ ምርጫውን ለማሸነፍ የሚያስቸሉ ዝግጅቶች ተደረጉ አነዚህ ቅድመ ዝግጅቶች ሁለት የተሳሰሩ አላማ ነበራቸውበምርጫ ሰምን ተሸነፍን እንደዛ አይነት መጥፎ ታሪክ አንዳይደገም ምን ማድረግ ይኖርብናል የሚል አና ቀጣዩን ምርጫ በመቶ ፐርሰንት ለማሸነፍ ምን ማድረግ ይጠበቅብናል። በምርጫ ክርክር ወቅት ኢህአዴግ ባልተዘጋጀበት ሁኔታ በሩን መበርገድ አልነበረበትም ግንቦት ለሚካሄድ ምርጫ መስከረም ጀምሮ የሚዲያ ከርከር መካሄዱ ጥፉት ነበር በክርክሩ ወቅት ኢህአዴግን ወክለው የቀረቡ ካድሬዎች ደካማ የፓለቲካ ብቃት ማሳየታቸው ሳያንስ ሲጠቀሙባቸው የነበሩት አደገኛ ቃላት ኢንተርሀምዌይ ልብ ይሷሏል የምርጫው ውጤት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ አሳድረዋል በምረጡኝ ዘመቻ ወቅት ኢህአዴግን ምረጡ ብሎ በሙሉ ወኔና ፍላጐት የተንቀሳቀሰ አጩና አባል አልነበረም በምርጫው ዋዜማ ሚያዝያ የተካሄደው የተቃዋሚዎች የድጋፍ ሰልፍ መፈቀድ አልነበረበትም የሚሉ ቁምነገሮች ላይ መነሻ ሀሳብ አቀረብን አቶ በረከት ጥናቱ ትክክል መሆኑን ለማሳየት በአያንዳንዱ ጉዳይ ላይ አሰደማሚ መገለጫዎችን አቀረበ አፉችንን አስከፈተን። ጭ ሌላው በቡድኑ ጥናትም ሆነ በአቶ በረከት አስተያየት የቀረበው የኢህአዴግ ከፍተኛ ካድሬዎች በምርጫ ክርክር ወቅት ያሳዬት ደካማ ብቃት ነበርቋ በሚዲያ ከርክር ወቅት ኢህአዴግን ወክለው የቀረቡ ባለስልጣናት ያሳዬት አሳፉሪ የፓለቲካ ብቃት ምርጫውን በዝረራ እንድንወጣ አስተዋጽኦ አበርክቷል የሚል ነበር አቶ በረከት ካድሬዎች የብቃት ማነስ ብቻ ሳይሆን በአቀራረብ ደረጃ በጣም አሰልቺና የህዝብን ፍላጐት ማአከል ያላደረጉ በመሆኑ መራጩ ህዝብ ፊቱን ከኢህአዴግ እንዲያዞር አስተዋጽኦ አድርጓል በማለት የወቅቱን ሁኔታ በሰፊው አብራርቷል። በቡድኑ ጥናት መሰረት እነዚህ ውድድሮች በተመሳሳይ ጊዜ በመካሄዳቸው ምክንያት የአዲሳባ ምርጫ በፓርላማው ላይ አሉታዊ ተጽእኖ አሳድሯል የሜል ነበር የፌደራሉን አስቀድሞ በሁለት አመቱ የአዲሳባ ቢሆን የከተማው ህዝብ በፌዴራል ደረጃ ኢህአዴግ መንግስት ሆኖ አያየ ከተማዋን እንዲያስተዳድሩ ተቃዋሚዎችን የመምረጥ ፍላጐት አያድርበትም ተባለ። መነሻችን አዲሳባ በመሆኑ በመዲናይቱ ስለሚገኙት ከ ሺህ በላይ የቀበሌ ምከር ቤት አባላት ስልጣንና ተልእኮዎች በማንሳት እንጀምር እነዚህ የዝቅተኛ ምክር ቤት አባላት የአንድ ፓርቲ የበላይነት በሰፈነበት ሁኔታ የዲሞክራሲ ማፈኛ ተቋማት ሆነው በማገልገል ደረጃ የጐላ ሚና ይጫወታሉ ዋነኛ ስራቸውም የአካባቢያቸውን ፀጥታ በመጠበቅ ስም የነዋሪውን ኮቴ መከታተል ነው በአንዲት ቀበሌ ውስጥ ከ ያላነሱ የምክር ቤት ህጋዊ ካባ ያጠለቁ አባላትና ካድሬዎችን ማሰማራት ነዋሪው ውስጥ ምን ያህል መረበሽና በነፃነት ያለመናገር ሁኔታ ሊፈጥር አንደሚችል መገመት አያዳግትም በእንቅርት ላይ አንዲሉ በአነዚህ አርከኖች በብዛት የሚሰማራው ካድሬ ህገ መንግስቱን እንኳን በአግባቡ ያላነበበና የንቃተ ህሊና ችማሣር ያለበት በመሆኑ እያንዳንዷን የተቃውሞ ቃላት በፀረ ህዝበኝነት የመፈረጅ ባህሪው የተለመደ ነው። አንድ የምከር ቤት አባል በሚኖርበት ሰፈር ውስጥ በአድር አሊያም በለቅሶ ቤት ተገኝቶ አንድ ግለሰብ ከኢህአዴግ የተለየ አቋም ይዞ ከተመለከተ መጀመሪያ ጠላት ለተከታታይ ቀናት ካራመደ ደግሞ በሸብርተኝነት ጐራ እንዲሰለፍ ያደርጋል እነዚህ የምክር ቤት እና የድርጅት አባላት ከቁጥጥር ባሻገር ለምርጫ እንቅስቃሴ ከፍተኛ ፉይዳ አላቸው የኢህአዴግ አቅድ የአራተኛውን ሀገር አቀፍ ምርጫ ኢህአዴግ የሚያሸንፍበትን አቅጣጫ አስቀምጦ ነበር። በአጠቃላይ ሲታይ ኢህአዴግ ለ ሚሊዮን ህዝብ ከሚሊዮን በላይ አባላትና የምክር ቤት ካድሬዎችን በማሰማራት በአባላት ብዛት በአለም ተወዳዳሪ የሌለው ፓርቲ ሆኗል። በተለይም የሼህ መሀመድ አልአሙዲ ሸሪክ የሆኑት አቶ አብነት ገመስቀል ለዞን ሶስት ኢህአዴግ ጽቤት ግማሸ ሚሊዮን ብር በመስጠት ከ በላይ ለሚሆኑ ካድሬዎች ለአንድ አመት ያህል ወርሀዊ ደሞዛቸውን በመቻላቸው የድርጅቱ የቁርጥ ቀን ተደርገው መወሰድ እንዳለባቸው በምሳሌነት ተነሳ አቶ አብነት ከዚህ በተጨማሪም ዞኑ በሸራተን አዲስ ባዘጋጀው ገቢ ማሰባሰቢያ ሙሉ ወጪውን በመሸፈን ከ ሺህ በላይ ኢህአዴግን መታደጋቸው ተገለፀ። በተቃራኒው በረከት ጽፎ ባስነበበን የሁለት ምርጫዎች ወግ መጽሐፍ ላይ የሚያዝያ ሰልፎች በሚለው ርአስ ስር ከላይ የተቀመጠውን ሀቅ በመገልበጥ ኢህአዴግ ከሀያ አመታት በፊት የመድብለ ፓርቲ ስርአት ግንባታን የመረጠበት ምክንያት ዲሞክራሲያዊ ምርጫ የህዝብ መብት ከመሆኑ መሰረታዊ ጉዳይ የተነሳ ብቻ አልነበረም የተቃዋሚ በተለይም ህገ መንግስቱን ተቀብሎ በፓሊሲ ልዩነት ዙሪያ ተወዳድሮ ለመመረጥ የሚሻ ጠንካራ ታማኝ ተቃዋሚ መኖር ለዲሞከራሲ ስርአት ጤንነት የራሱ የሆነ አስተዋጽኦ ስላለው ጭምር ነበር። በመጀመሪያ ደረጃ በሀገራችን የፓለቲካ ፓርቲ መመስረት የመንደር ሱቅ ከመክፈት በላይ ቀላል ሆኗል ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም እንደገለፀው በአሁን ሰአት ከዘጠና ዘጠኝ በላይ የፓለቲካ ፓርቲዎች ይገኛሉ ይህም ሆኖ ከገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ በስተቀር ጐልቶ የወጣ ይህ የሚባል የፓለቲካ ፓርቲ የለም ለሀይል ሚዛን ተስፉ ተጥሎባቸው የነበሩትም በራሳቸውና በኢህአዴግ የዜሮ ድምር ጨዋታ ምክንያት በተወለዱ ማግስት ሰላሳ ቦታ ተሰነጣጥቀዋል። በመሆኑም መድብለ ፓርቲ ስርአት ለመመስረት ከሁለት እስከ አስር የፓለቲካ ፓርቲዎች መገኘትን አንደ መሰረታዊ ነገር የተቀመጠው በኢትዮጵያ የሚሰራ አይደለም ከሁሉም በላይ ኢህአዴግ የሚመራበት አብዮታዊ ዲሞክራሲ ርአዮተ አለም የተፈጥሮ ባህሪው መድብሲ ፓርቲን የሚያበረታታና የሚፈጥር አይደለም ዜጐች ሲነሱና ሲቀመጡ ሲበሉና ሲተኙ በህልማቸው ሳይቀር ስለአንድ ነገር ብቻ እንዲያስቡ ማድረግን አንደ ግብ የሚወስድ ፍልስፍና የተለየ አማራጭን ሊቀበል የሚችል ተክለ ሰውነት ሊኖረው አይቸልም ይህ አስተሳሰብ ገዥ ሆኖ የበላይነት ካላረጋገጠ በስተቀር ሀገሪቷ የመበታተን አደጋ ሊያጋጥማት ይችላል ከዚህ በፊትም ኢትዮጵያ አጋጥሞት የነበረውን መስቀለኛ መንገድ በድል የተሸጋገረችው በአብዮታዊ ዲሞከራሲ ነው ብሎ የሚያምን ድርጅት አብዛህነትን ሊከተል የሚችል መተክል አይኖረውም ቁዝዝቫ ኢህአዴግ እንደ መድብለ ፓርቲ ሁሉ አብዮታዊ ዲሞክራሲን አስመልክቶ የሚሰጠው ትርጉምና መፃኢ አድል ከሁኔታዎች ጋር የሚለዋወጥና ከዘመን ዘመን የሚለያይ ነው ኢህአዴግ ባጋጠመው የውስጠ ድርጅት ቀውስና የአለም አቀፍ ሁኔታ መቀያየር ምከንያት አብዮታዊ ዲሞከራሲ ለሶስት ያህል ጊዜያት ሙሉ ልብሱን ቀይሯል በዚህም ምክንያት የኢህአዴግ ትርጉም መርሆዎችየጉዞ አቅጣጫና ቀጣይ አጣ ፉንታ በተመሳሳይ መልኩ ግልብጥብጡ ወጥቷል። ከ ዓም በፊት ከ እና ከ ዓም በኋላ ያለው ኢህአዴግና አብዮታዊ ዲሞክራሲ አንድ አይነት አይደሉም ከ ዓ ም በፊት በዚህ ወቅት የነበረው አብዮታዊ ዲሞክራሲ በአብዮታዊ ምሁራን የሚመራ ሆኖ ለመላው አርሶ አደርለላብአደርና ለከተማው ጭቁን ህዝብ ቆሚያለሁ የሚል ነበር። ርግጥ የአብዛኛው ኦሮሞ ህዝብ ፍላጐት ኦነግ ከሚያራምደው አቋም የተለየ ቢሆንም ቁጥሩ ቀላል በማይባሉ የኦሮሚያ ዞኖች ፓርቲው ሰፊ ተቀባይነት ነበረው ግንባሩ ይህንን ድጋፍ ተጠቅሞ የአቋም ለውጥ ሳያደርግ ቢንቀሳቀስ ኖሮ በፌደራል ፓርላማ ከፍተኛ ቁጥር በመያዝ በህግ አውጭነት የሚሳተፍበት በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ደግሞ የጥምር መንግስት አካል የሚሆንበት አድል ይፈጠር ነበር የኦሮሞ ህዝብን የኢትዮጵያዊነት ግንድ መሆንን ዛሬ ተገንዝቦ የአቋም ለውጥ ባደረገበት ሁኔታ የኢትዮጵያ ፓለቲካ መድረከ ላይ ተገኝቶ ቢሆን ኖሮ በአነ አንግሊዝ ያየነው ጥምር መንግስት በሀገራችን አውን ይሆን ነበር ምንአልባትም የኦሮሞ ወጣቶች ስደትና የእስር ቤት መታጐር ይቀንስ ነበር ከ ዓም በኃላ በኢህአዴግ ከፍተኛ ካድሬዎች ተነስቶ አከራካሪ የነበረው ተቃዋሚ ፓርቲዎች ለዲሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ አስተዋጽኦ አላቸውየላቸውም የሚለው ነበር። አቶ በረከት ቧልት የተባለውን ታሪክ ለሰመስራት ወይዘሮ አዜብ እአና አያት የነበራቸውን የጥቅም ትስስር በላቀ ደረጃ ለማሳደግ አዲስ ነገር ጋዜጣ ከውስጥ ድርጅት የተገኘ አዲስ መረጃ በመሆኑ ቅድሚያውን በመውሰድ ትኩስ ዜና ለህብረተሰብ ለማድረስ ጋዜጣዉ ፓለቲካውንና የጥቅም ትስስሩን ሚስጥር ባለመረዳት በተጐጂው ሰው ላይ ያሳረፈው በትር ግለሰቡ ከህብረተሰቡ እንዳይቀላቀል የአጅ መጠቋቆሚያ አንዲሆንና ተሸማቆ አንዲኖር አድርቱጐታል ወደዚህ የህሊና ሸከም ወደ ሆነ ታሪክ ከመግባቴ በፊት ከላይ በአቶ በረከት የምርጫ የአዲሳባ ውጤትን አስመልከቶ በቀረበው ወግ ላይ ተዛንፈው የቀረቡ ታሪኮች በትክክለኛው ገፅታው በማስቀመጥ ልጀምር አንድ ለእናቱ ምርጫ ሲካሔድ የሁለት ሳምንት እድሜ ሲቀረው አራት ኪሎ የሚገኘው የኢህአዴግ ቢሮ በሽብርና ጭንቀት ተዋጠ። የልደታ ከፍለ ከተማን የፓለቲካ ስራ በበላይነት እንዲመራ ስልጣን ተሰጠው በምርጫ ለአዲሳባ ምክር ቤት ኢህአዴግን ወክለው በልደታ ከቀረቡ አጩዎች አንዱ ተክሌ ሆነ በዚህ ሳይወሰን የከፍለ ከተማው ምርጫ ስራ በበላይነት አንዲያስተባብር ተመደበ በዚህም ምከንያት እንደሌሎቻችን ሁሉ ማታ ማታ ኢህአዴግ ቢሮ አየመጣ ለአቶ በረከት ተስፉ አስቆራጭ ሪፓርት ማቅረብ ይቀጥላል። ሌሎቻችን በዝረራ ወጣን ስም ከማውጣት ቦዝኖ የማያውቁት ካድሬዎች ተክሌን አንድ ለእናቱ አሉት ምርጫው በተጠናቀቀ በሳምንቱ ኢህአዴግ ደጃፍ አንዳይደርሰ ተብሎ ተወስኖበት የነበረው ምስኪኑ ሰው የተለየ ከብር ተሰጥቶት ሰሌላ ትልቅ ስራ ተጠራ ቅንጅት ስልጣን ከተረከበ በኋላ የሚካሔዱ ህገ ወጥ ተግባራትን እየተከታተለ በምከር ቤት ጉባኤዎች ላይ የማጋለጥ ስራ እንደሚሰራ ተነገረው ከደህንነት ቢሮ በየጊዜው ወቅታዊ መረጃዎችን የሚያገኝበት ሁኔታ ተመቻቸለት አፍታም ሳይቆይ በሚስጥር የተያዙ መረጃዎች ይቀርብለት ጀመር ከእነዚህ ውስጥ በአንባ ጠባቂ ኮሚሸን የሚመራ የአዲሳባ ህዝብ ቅሬታ ማስተናገጃ ጽቤት እንደሚቋቋምና እሱ የበላይ ሀላፊ አንደሚሆን የሚጠቀሱ ናቸው የቅሬታ ማስተናገጃው ቢሮ የህዝብ ሮሮዎችንና በተደራጀ መንገድ አንዲያስተናግድ የታሰበ ነበር። ይቸላል በአዲሳባ አስተዳደር መሬት አስተዳደር ውስጥ ከፍተኛ ሙያተኛ ነበር በስራ ትጋቱና ቅንነቱ ምከንያት በሰራተኛች ተቀባይነት በማግኘቱ ባለስልጣን ሆነ የኢህአዴግ አይን አረፈበት ለድርጅት አባልነት ቢጠየቅ በየትኛውም ፓርቲ ውስጥ ገብቼ የመንቀሳቀስ ፍላጐት የለኝም በማለት አሻፈረኝ አለ ምርጫ ሲመጣ የአዲሳባ ምክር ቤት አባል ሆኖ ህዝቡን አንዲያገለማል የቅርብ ጓደኛው በሆነው ካህሳይ የሚባል ካድሬ ተለመነ ካህሳይ የአዲሳባ ትራንስፓርት ባለስልጣን ምዴሬከተር ሲሆን የኢህአዴግ የመንግስት ተቋማት አደረጃጀት ሀላፊ ነበር ይችላል ከጓደኛው የቀረበበትን ግፊት መቋቋም አቅቶት ኢህአዴግን ወክሎ ለምክር ቤት ለመወዳደር ፍቃደኛ ሆነ ለአዲሳባ ካቢኔ አባልነትም ምርጫው ሳይካሄድ ታጨ የ የአዲሳባ ዳግም ምርጫ ኢህአዴግ ሙሉ ለሙሉ አንደሚያሸንፍ በመረጋገጡ ምክንያት ፓርቲው ያቀረባቸውን አጩዎችን ለህዝብ ለማስተቸት አቀረበከእነዚህ ውስጥ ይችላል አንዱ ነበር ይችላል በሶስት ቦታዎች ለግምገማ ቀረበ። የከተማው ኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ በረከት ቢሮ አስቸኳይ ስብሰባ ተጠራን እኔና ፀጋዬ ክርክሩን ወዳልሆነ አቅጣጫ መምራታችንን ተነገረን የመኢብኑ አቶ መሳፍንት ኢህአዴግ ቢሮ መጥቶ ቅሬታ ማቅረቡ ተነገረን የድርጅት ጉዳዮን ለሚመራው ካሚል ደውሎ የመደራደሪያ ሀሳብ አንዳቀረበ ሰማን ይህም ኢህአዴግ ከዚህ ቀደም ለአቶ በድሩ አደም አንደሚያደርገው አንድ ወንበር ከለቀቀለት ዝ ቤተሰቦቹን ከአጩነት አንደሚሰርዝ የሚገልፅ ነበር። አንደ አውነቱ ከሆነ በምርጫ የነበረው ቅንጅት ሳይሆን መንፈሱበኢትዮጵያ ህዝብ ውስጥ ያለው የለውጥ ፍላጐት ነው ይሄ መንፈስ ዛሬም በኢትዮጵያ ምድር አለ ጭጭ ምርጫው በተካሄደ በንጋታው ሰኞ የሁሉም ምርጫ ጣቢያዎች ውጤት እጃችን ገባ በ ዓም የተካሄደውን ዳግም ምርጫ አሸናፊው ድምፅ አልባ የሆነው የከተማው ነዋሪ ሆነ። ብዙዎች ካድሬዎች ርእኔን ጨምሮ አቶ መለስ የወሰደው አርምጃ መንስኤ ኦህዴድን ለማባበል የሚለው አሳማኝ አልነበረም ይልቁንስ በምርጫ የሚስጥር ድምፅ መስጫ ወረቀቱን ድምፅ አልባ ያደረገውና ኢህአደግን የሚያዋርዱ ጽሁፎችን ያሳረፈው ወጣቱ ሀይል በመሆኑ ተበሳጭቶና ተስፉ ቆርጦ አንደሆነ የሚለው ሀሳብ ሚዛን ደፍቶ ነበር በዳግም ምርጫ ዓም ኢህአዴግ መዲናይቱን በተቆጣጠረ ወቅት አቶ በረከት ቢሮ ውስጥ አኔህላዌካሚልፀጋዬና ፍሬህይወት ተሰብስበን ከንቲባ ስራ አስኪያጅ የካቢኔ አባላት እየመለመልን ነበር ስብሰባው እንደ ተጀመረ ከቤተ መንግስት የአቶ መለስ ስልከ ተንጫረረ። በሁለተኛ ደረጃ ሀይሌ ፍስሀ ቢሆን የሚል አስተያየት አለኝ የህውሀት ቢሮ ለመስጠት አንገራግረው ነበር ግን አዲሳባ ላይ ጠንካራ ሰው መመደብ ወሳኝ መሆኑን ነግሬያቸው ፍቃደኛ ሆነዋል። አኔ ደግሞ የከንቲባው አማካሪና የመንግስት ዋና ተጠሪ የሚል ሹመት ተሰጠኝ ዥፍጽ ዎሃሃቃሃ ያፇኋ አዲሱ የኩማ ደመቅሳ ካቢኔ ስራ ሲጀምር ከኢህአዴግ ማአከል የተሰጠን አቅጣጫ የከተማዋን ሲቪል ሰርቪስ ቢሮከራሲ ከስራ ውጭ ማድረግ ነበር የኢህአዴግ አዲሱ አቅጣጫ ሰራተኛ ማባረር ሳይሆን ሸባ ሆኖ አንዲኖር ማድረግ ስለነበር በአርከበ ዘመን እንደተደረገው የለውጥ ሀይል የሆነ ያልሆነ የሚል ማባረሪያ መንገድ አልተከተልንም ከዛ በተቃራኒው ሰራተኛው ወደ ስራው መጥቶ ምንም ሳይሰራ ወደ ቤቱ አንዲመለስ የሚያደርግ አቅጣጫ ነበር በመሆኑም ከከተማ አስከ ወረዳ ድረስ ቁልፍ የቢሮክራሲው የስልጣን ቦታዎች እንዲጠኑ ተደረገ ጥናቱ ያህል የስራ መደቦች ወሳኝ ቦታዎች እንደሆነ አመላከተ። ይህን ተከትሎ ፏዐዐዐ የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸው የኢህአዴግ አባላት የሆኑ ወጣት ምሩቃን በአንድ ጊዜ እንዲቀጠሩና ወሳኝ መደቦችን ከነባሩ ቢሮክራሲ አንዲቀሙ ተወሰነ አንደ እውነቱ ከሆነ የከተማው ኢህአዴግ ክንፍ አባላት በውሳኔው በጣም ደስተኛ ነበርን በተለይ እኔ ከ አመተ ምህረት ጀምሮ አስከ ምርጫ ድረስ የአዲሳባ ልጆች ሆነው በከፍተኛ ትምህርት ተቋም የሚማሩ ተማሪዎችን የማደራጀት የማሰልጠንና ስምሪት የመስጠት ሀላፊነቱን የወሰድኩት እኔ ነበርኩ። ስም ዝርዝር ማዘጋጃ ቤት የተለጠፈ አለት የመዲናይቱ ወጣቶች እንባ ፈሰሰ የአዲሳአባ ኢህአዴግና የዞን ስራ አስፈጻሚዎችን ስም አየጠሩ ልካችንን አቀመሱን ሌባና ከሀዲ የሚል ማእረግ አለበሱን አዲሳአባ የእነሱ ብቻ ሳይሆን የእኛም አይደለችምና ውርጅብኙን ተቀብለን ኖርን ሉጽሑ ክፍል ሰባት የአርማጌዶን ጦርነት ምአራፍ ሃያ አምስት የሐመሩሐ ፓለቲካ ዘርአይ አስግዶም የሚባል ቁጥር መደመርና መቀነስ የማይቸል ሰው ኢቲቪ ሀላፊ አደረጋችቸሁኛ አቡነ ሳሙኤል ሲኖዶሱና አዲሲቷ ኢትዮጵያ ሚያዝያ ሁለት ሺህ አንድ ከፀጥታው ምከር ቤት አባላት ከፊሎቻችን የፓትሪያርኩ ጽቤት ተገኝተናል። አንዳንድ ከፍተኛ ካድሬዎች ያቀረቧቸው አስተያየቶች መሬት የሚወድቁ አልነበረም የኢህአዴግ ቢሮ ሀላፊው ሙክታር ከድር እንዲህ በማለት ተናገረ በኢህአዴግ ቢሮ ባለው ስታስቲክስ መሰረት በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከሚማሩ ተማሪዎችና መምህራን ሰማንያ በመቶው የድርጅታችን አባላት ናቸው በተለይም እንደ ባህርዳር ያሉ ዩንቨርስቲዎች አስከ ዘጠና በመቶ ይደርሳል በተቃራኒው በሀይማኖት ጉዳዮች አየታመሱ ያሉት አነዚህ ተቋማት ናቸው በተቋማቱ በተፈጠረ ሁከት ምክንያት መስታወትና ወንበር የሰባበሩ ተማሪዎች በቁጥጥር ስል ውለው ማጣራት ሲካሄድ ከሀምሳ ውስጥ አርባ ሁለቱ የእኛ አባላት ናቸው። መንግስታዊ አሰራር የማያውቀው ኪራይ ቤቶች አነ በረከትን አባዱላንና አርከበን ያፉጠጠ ተቋም ነበር በአንድ ወቅት አቶ መለስ የአውራ ዶሮ ጨዋታ መጫወት ፈልጐ የኪራይ ቤቶችን ተጠሪነት ለአርከበ የቦርድ ሰብሳቢውን ለአባዱላ ቤት አከፉፉዩን ደግሞ ኢህአዴግ ጽቤት በረከት አድር» ነበር ይህን ተከትሎ ነበር በረከት ታማኙን ተፈሪ ከኢህአዴግ ፉይናንስ ወደ ኪራይ ቤቶች የሰደደው የስምኦን ልጅ በአቶ መለስ አባይ ፀሀዬና አዲሱ ለገሰ ላይ ካልመጠበት በስተቀር የአህያ ባል ነው ለዚህም ይመስላል ተፈሪን ከጅብ ማስጣል የተሳነው ተፈሪ እንዲህ በማለት ንግግሩን ጀመረ የሀይማኖት አስተማሪዎች በድርጅታችን ውስጥ አባል መሆን ቢችሉም አመራር ደረጃ መምጣት እንደሌለባቸው መመሪያው ይደነግጋል። የስልጤ ጉራጌ አይደለም መፈክር ያቀነቀነው ቡድን አመራር ነበረች አንድን ህዝብ ለሁለት የሰነጠቀው ህዝበ ውሳኔ በበላይነት ካስፈፀሙት የስልጤ ካድሬዎች አንዷ ነበረች የትምህርቱ አንዳልከው ይሁን ግን ለምንድነው በአርከበ ዘመን የምደባ ወቅት ጠብቀህ እንዳልመደብ ጥረት ያደረከው በወቅቱ ከነባሩ ካድሬ ውስጥ ተመርጦ ምደባ ሲካሄድ በቁጥር አንድ እኔ እንዳልመደብ አንድ ጊዜ የአመለካከት ችማግር አለበት ሌላ ጊዜ የብሄር ጥያቄ ላይ የጠራ አቋም የለውም ብሎ ሲከራከር የነበረው አሱ ነበር ይህ ሁሉ አላዋጣው ሲል በደፈናው ኦህዴድ አልፈቀደም ብሎ ከምደባ ውጭ አደረገኝ በሳምንቱ በ ወረዳዎች በተካሄደ ስብሰባ የአኔን በአሊ አብዶ መገፉት የሰሙ ከ ሺህ በላይ የአዲሳባ አባላት ተቃውሞ አሰሙ ወደ ካድሬነት ያመጡኝ መከላከያ መኮንኖች ጣልቃ ገቡ በወታደሮቹና በአባሉ ሣፊት የአርከበ ዘመን ካድሬ ሆንኩ። ቡምስላግ የ ዓም የአዲሳባ ዳግም ምርጫ አየተካሄደ ነው የአዲሳአባ ኢህአዴግ ክንፍ ስራ አስፈጻሚዎች ካሚል ቢሮ ተሰባስበን መርጦ የወጣውን ህዝብ በስልክ ከዞኖች አየተቀበልን ነው ትልቁ ፍራቻቸን ህዝቡ ሊወጣ አይችልም የሚለው ሆኗል። የአዲሳአባ ኢህአዴግ ክንፍ በአቢይ ኮሚቴ አንዲሳተፍ በመወሰኑ ምክንያት ፀጋዬ ሀይለማርያም በአሁን ሰአት የአዲሳአባ ፍትህ ቢሮ ሀላፊ እንዲካተት በሙሉ መስማማት ተወሰነ አስከማውቀው ድረስ ፀጋዬ የመንደርተኝነት ስሜት ያለው ቢሆንም ፀረ ሌባ ነበር በተለይም አርከበ እቁባይ የፈፀማቸውን ዝርፊያዎች በአደባባይ ከመናገር ወደ ኋላ የሚል አልነበረም በተለይ እለቱን በውል በማላስታውሰው አንዲት ቀን ከአቶ መለስ ጋር በነበረን የጋራ ስብሰባ ላይ አርከበን ፊትለፊት አየተመለከተ የአዲሳአባ ህዝብ ትናንሾቹ አሳዎች እንጂ ትላልቆቹ አእየተጠመዱ አይደለም እያለ ነው በማለት ተናግሯል። የግርጌ ማስታወሻ የሁለት ምርጫዎች ወግ በረከት ስምኦን ዓ ም የኢፌዴሪ ህገ መንግስት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቻርተር ዓ ም የማስፈፀም አቅም ግንባታ ስትራቴጂ ዓም ነፃነት እና ዳኝነት በኢትዮጵያ ስየ አብርሀ ዓም አለም ጠፍጣፉ ናት ጆን ፍሪድማን ኢኤአ የእነ ህላዌ ዮሴፍ የይቅርታ ደብዳቤ ዓም የነጋሶ መንገድ ዳንኤል ተፈራ ዓም መልካም አስተዳደር ፍራንሲስ ፉኩያማ አኤአ ሪፓርተር ጋዜጣ ዓም ዜ የደራሲው ማስታወሻ ተስፉዬ ገብረአብ ዓም ዲሞክራሲና ሁለንተናዊ ልማት በኢትዮጵያ ዶክተር ብርሀኑ ነጋ እኤ የተሻሻለው የኢትዮጵያ የምርጫ ህግ አዋጅ ቁጥር የዲሞክራሲ ግንባታ ጥያቄ በኢትዮጵያ ዓ ም ዓሞከክራሲና ዲሞክራሲያዊ አንድነት በኢትዮጵያ ዓም ሦኮ ይጅቻሯቻዮቱ።

  • N.B. This Summary is Very Experimental!! based on the following scripts from:
    • https://github.com/millzon/textSummarizer-am
    • https://github.com/icoxfog417/awesome-text-summarization#motivation
Download Searchable PDF Download PDF

Commentaires:


memezon

Options de téléchargement | Convertir en PDF | Livre du jour

© dirzon | Conditions d'utilisation | Intimité | Sur | Services | Contact