Detecting...

Please whitelist dirzon to continue.

or subscribe for ad-free contenct.

dirzon
  • ወደ ፒዲኤፍ ቀይር
  • የንባብ ዝርዝር
  • አጠሬራ
  • ኦዲዮ መጽሐፍ
  • ፍለጋ
  • ይስቀሉ
  • የኔዞን
  • ይግቡ
  • ይመዝገቡ
English  አማርኛ  Français  العربية
የዕለቱ መጽሐፍ

የአማራ_የመስኖ_መሬት_ሽንሸና_መመሪያ.pdf


  • የቃላት ደመና

የአማራ_የመስኖ_መሬት_ሽንሸና_መመሪያ.pdf
  • የማውጣት አጠሬራ

  • Cosine ማጠቃለያ

የአካባቢ ጥበቃ መሬት አስተዳድርና አጠቃቀም ባለስልጣን ጥመጎላ በዘመናዊ መንገድ በመስኖ የሚለማ መሬት ሽግሽግ መመሪያ ጥቅምት ዓም ባህርዳር በዘመናዊ መንገድ በመስኖ የሚለማ መሬት ሽግሽግ መመሪያ ክፍል አንድ ጠቅላሳ በሀገራችን ብሎም በክልላችን ያለንን የውሀ ሀብት በተገቢው መንገድ ጥቅም ላይ ባለማዋላችን የተነሳ የክልላችን አርሶ አደር የዝናብ ውሀ ተጠቅሞ የሚያመርተው ምርት አነስተኛ ከመሆኑም በላይ የዝናብ ጥገኛ አድርጐታል ዘርን ለመዝራትና ከዘራም በኋላ ሰማይ ሰማይ ማየት የክልላችን አርሶ አደር የዘወትር ተግባር ነው በሌላ በኩል ደግሞ የገጠር ልማት ራዕያችን እውን ሊሆን የሚችለው ውሀ ጉልበትንና መሬትን አቀናጅተን ወደ ምርት ተግባር ስንገባ መሆኑ ይታወቃል ውሀን በአግባቡ ጥቅም ላይ በማዋል እንዲቻል ዘመናዊና ባህላዊ የመስኖ ስራ በመንግስት በባለሀብቶችና በአርሶ አደሩ የነቃ ተሳትፎ በስፋት መካሄድ ይኖርበታል ስለዚህ ይህ የልማት ዓላማ እንዲሳካ ለመስኖ ስራው መሰረተ ልማት ግንባታ መሬታቸውን የሚያጡ አርሶ አደሮች በሽግሽግ መሬት ማግኘት እንደሚችሉ የክልሉ የገጠር መሬት አስተዳደር አጠቃቀም መወሰኛ አዋጅ ቁጥር አንቀጽ የተገለፀውን ተግባራዊ ለማድረግ የመስኖ መሬት ሸግሽግ ግልጽና ከአድሎ የነፃ እንዲሆን ለማስቻል የመስኖ መሬት ሽግሽግ በህዝቡ ቀጥተኛ ተሳታፎ እንዲተገበር ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር በመስኖ መሬት ሽግሽግ ተሳታፊ የሚሆኑ ልዩ ልዩ አካላት ተግባርና ኃላፊነት በግልጽ ለማስገንዘብና የመስኖ መሬት ባለይዞታዎች መብትና ግዴታ በግልጽ ለማሳወቅ እንዲቻል የባለስልጣኑን መቤት ለማቋቋም በወጣው አዋጅ ቁጥር በተሰጠው ኃላፊነት መሰረት እንዲሁም በአዋጅ ቁጥር አንቀጽ እና በደንብ ቁጥር አንቀጽ መሰረት ይህ መመሪያ ተዘጋጅቷል ይህ መመሪያ የመስኖ መሬት ሽግሽግን ለማስፈፀም የወጣ መመሪያ ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ክፍል ሁለት አንቀጽ የመስኖ መሬት ሽግሽግ አሠራር በአዋጅ ቁጥር አንቀጽ መሰረት በዘመናዊ መስኖ የሚለማ ማናቸውም መሬት የቀድሞ ባለይዞታ የሚገባውን ድርሻ በቅድሚያ እንዲያገኝ እየተደረገ እንዲሸጋሸግ ሊደረግ ይችላል የመስኖ መሬት ሸግሽግ ዓላማ በመስኖ አውታር ግንባታ የተወሠደውን መሬት ትክ ለመሰጠት ከሁሉም ተጠቃማሚ ተነፃፃሪፀዐርፀዐጠበ በሆነ መንገድ መሬት አውጣጥቶ ለመስኖ አውታር ግንባታ የይዞታ መሬታቸውን ለሰጡ አርሶ አደሮች ትክ መሬት ለመስጠት ነው ሽግሽግ በሚካሄድበት ወቅት በዘመናዊ መስኖ የሚለማ መሬት ጥቅም ላይ ሲውል ተጠቃሚ የማሆኑት የውሃ ገብ መሬት ባለይዞታዎችና ለመስኖ አውታርመሠረተ ልማት ማለትም ለግድብ ለዋና መስኖ ቦይ ውሃ የሚተኛበት መሬት ወዘተ ባለይዞታ የነበሩ ሁሉ በመስኖ ከሚለማው መሬት ከይዞታቸው ተነጻጻሪ በሆነ መልኩ የመጠቀም መብት ይኖራቸዋል የመስኖ ልማቱ እንዲገነባ በህዝብ ተሳትፎ ከተረጋገጠ በባለሙያ ከታመነበትና ይህም ስልጣን ባለው አካል ከተረጋገጠ በኋላ ማንኛውም ባለይዞታ መሬቱ ለመስኖ ልማት አውታር አገልግሎት እንዳይውል መከልከል ወይም እንቅፋት መፍጠር አይችልም በዘመናዊ መስኖ በሚለማ መሬት ላይ ሽግሽግ ሲካሄድ በቀበሌው ውስጥ የሚገኝንና በዝናብ የሚለማ መሬትን አያካትትም የመስኖ መሬት ሽግሽግ ቀመር ሲዘጋጅ የአቅም ውስንነትንና የይዞታን ስፋት ግምት ውስጥ አያስገባም በዘመናዊ መስኖ የሚለማ መሬት የሚያስፈልገውን ተጨማሪ ግብአት ባለይዞታው ለማቅረብ ባለመቻሉ የተነሳ የሚደርስ የምርትና የምርታማነት መቀነስ ግዴታን በአግባቡ እንዳለመወጣት ይቆጠራል የመስኖ መሬት የመጠቀም መብት ያላቸው ተጠቃማዎች በቀደሞ ይዞታቸው ተነፃፃሪ የሆነ ስሌት ተቀምሮ በመስኖ የሚለማ አዲስ የይዞታ መጠን እንዲኖራቸው ይደረጋል በዚህ ወቅት የይዞታ ማረጋገጫ ደብተራቸው አዲሱን ይዞታ መጠን በሚገልፅ መልኩ ተስተካክሎ አዲስ ደብተር ከተዘጋጀላቸው በኋላ የቀድሞ ደብተራቸውንም እንዲመልሱ ይደረጋል አዲሱን ደብተር ለማግኘት የሚኖረው ክፍያ መጠን ውሀ ገብ ባልሆኑ ቦታዎች ላይ የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ለመቀየር ከሚኖረው አሰራር ጋር ተመሳሳይ ይሆናል የመስኖ መሬት ሽግሽጉን ተከትሎ ለሚሰጠው ለአዲሱ የመስኖ መሬት ይዞታ አዲስ መለያ ቁጥር ይሰጠዋል ጠቅላላ ይዞታው በመስኖ በሚለማው ክልል ውስጥ ያረፈ እንደሆነ ለይዞታው ባጠቃላይ አዲስ መለያ ቁጥር ሊሰጥ ይችላል ለአሰራር ያመች ዘንድ የድልድሉ ስራ እስኪጠናቀቅና ለውጥ ሊያመጡ የሚችሉ ጉዳዮች የመጨረሻ እልባት እስኪያገኙ ድረስ ለመስኖ መሬቶች ጊዜያዊ መለያ ቁጥር ተሰጥቶ እንዲቆይ ይደረጋል በባህላዊ መንገድ የሚለማ አነስተኛ መስኖ መሬት ለመስኖ አውታሩ ግንባታ መሬት አስካልተወሰደ ድረስ የመሬት ሽግሽግ አይካሄድም ሆኖም ለመስኖ አውታሩ መሬት የሚያስፈልግ ሲሆንና ተጠቃሚዎች ሲያምኑበት በዚህ መመሪያ መሰረት ኮሚቴ ተቋቁሞ ሽግሽጉ ሊካሄድ ይችላል ለመስኖ አውታር መሬት የተወሰደባቸው ባለይዞታዎችም በተነፃፃሪ መጠን ተቀንሶ መሬት ያገኛሉ ሲባል ለምሳሌ ለመስኖ አውታር ግንባታ አንድ ሄር መሬት የተወሰደበት አንድ ባለይዞታ ቢኖርና እራሱን ጨምሮ የመስኖ ተጠቃሚዎች አምስት ቢሆኑ ከሁሉም እኩል ዐዐ ካሬ ሜትር መሬት ይቀነሳል በዚህ መሠረት አንድ ሄር ይዞታ የነበረው ከአዲሱ ሽግሽግ በኃላ ዐዐዐ ካሬ ሜትር ይኖረዋል ማለት ነው ይህም በቅየሣ ሥራ በመስኖ የሚለማው መሬት እንዲመዘገብ ተደርጐ የሽግሽግ ሥራው ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት አሁን ያለውና ከሽግሽጉ በኋላ የሚኖረው ይዞታ በካርታ ላይ ሰፍሮ በባለሙያዎችና በኮሚቴው አማካይነት ለሕዝብ ቀርቦ አስተያየት እንዲሠጥበት ይደረጋል ለመስኖ መሰረተ ልማቱ አመቺ ሲሆን ወይም መሬትንና ውሀን በቁጠባ ለመጠቀም አመቺ መሆኑ በባለስልጣኑ የወረዳ ተጠሪ ጽቤት ከተረጋገጠ በኋላ ተራፊው መሬት ከዝቅተኛው የማሳ ስፋት በታች ከመሆኑ በተጨማሪ የብሎኮችን ቅርጽና መጠን በማስተካከል ወይም አጎራባች ብሎክ ውስጥ ለሚገኙ ባለይዞታዎች በማሸጋሸግ መሬቱን ጥቅም ላይ ማዋል በማይቻልበት ወቅት ሰፊ ይዞታ ያላቸው የተራፊው መሬት አዋሳኝ ባለይዞታዎች ተገቢውን ካሳ መሬቱ ለሚቀነስባቸው አርሶ አደሮች በቅድሚያ በመክፈል መሬቱን እንዲያጠቃልሉ ሊወሰን ይችላል የመስኖ መሬት ሽግሽግ ግልፅና ሚዛናዊ በሆነ መንገድ እንዲካሄድ ጥረት መደረግ አለበት ነባር ባለይዞታዎች ቤትና ቋሚ ሰብል በመሬቱ ላይ ካላቸው በዚህ መመሪያ በአንቀጽ ንዑስ አንቀጽ በንኡስ አንቀጽ መሰረት ድርሻቸውን ከወሰዱ በኋላ የሚቀረውን መሬት ለመስኖ አውታር ግንባታ መሬታቸው ለተወሰደባቸው ባለይዞታዎች ይሸጋሸጋል የመስኖ መሬት ሽግሽግ ሲካሄድ ለመስኖው ውኃ ስርጭት አመች ያልሆነ ቅርጽ ያላቸው ማሳዎች የተስተካከለ ቅርጽ እንዲኖራቸውና የተበታተኑ ማሳዎች በተቻለ መጠን ወደ አንድ ቦታ እንዲሰባሰቡ ይደረጋል የመስኖ መሬት ሽግሽግ ከተጠናቀቀ በኋላ በማንኛውም ጊዜ በባለይዞታዎች ፈቃደኝነትና በወረዳው ተጠሪ ጽቤት ሙያዊ ውሳኔ መሰረት የመሬት ልውውጥ ማድረግ ይቻላል የመስኖ መሬት ሽግሽግ ከተካሄደና ቋሚ የድንበር ምልክት እንዲቀመጥ ከተደረገ በኋላ በአያንዳንዱ ባለይዞታ የአዲሱን መሬት መጠንና አቀማመጥ የሚያሳይ ካርታ ተዘጋጅቶ ከይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ጋር ለባለይዞታው እንዲሰጠው ይደረጋል የመሬት ሽግሽጉ ከግድቡ አቅራቢያ ከሚገኘው ቀበሌ ጀምሮ የመስኖውን ዋና ቦይ ተከትሎና በቅድሚያ የመስኖ ውሀ የሚያገኘውን መሬት ግምት ውስጥ በማስገባት ተግባራዊ ይደረጋል በቀበሌው ውስጥ የሚገኙ የመስኖ መሬት ባለይዞታዎች በመስኖ በሚለማው መሬት ውስጥ በጋራ የሚጠቀሙበት ቦታ ተከልሎ ይቀመጣል በዚህ ቦታ ላይ ከይዞታቸው ስፋት ጋር ተነጻጻሪ በሆነ መልኩ እኩል መብትና ግዴታ ይኖርባቸዋል ልበመስኖው ከሚለማው መሬት የይዞታቸው መጠን ከ ሄር በታች የሚሆንባቸው አርሶ አደሮች አዲሱን ይዞታቸውን በቡድን እንዲያገኙ ይደረጋል በቡድን ይዞታው ውስጥ ድርሻ ያላቸው የባለይዞታዎች በሙሉ በይዞታ ማረጋገጫ ደብተሩ ላይ ማስፈር በማይቻልበት ጊዜ የባለይዞታዎች ዝርዝርና በቡድን ይዞታው ውስጥ የሚኖራቸው ድርሻ ለብቻው ተመዝግቦ ይቀመጣል የመስኖ ግንባታው ከአንድ ቀበሌ በላይ የሚያለማ ሆኖ የመስኖ መሬት ሸግሽጉ ሲካሄድ ለመስኖው ግንባታ መሬት የተወሰደባቸው በቀበሌው ውስጥ የሚለማው መሬት በቂ በማይሆንበት ጊዜ በሚወጣው ቅደም ተከተል መሰረት ቅድሚሜያ የሚያገኙት በቀበሌያቸው ሌሎቹ ደግሞ በአጎራባች ቀበሌዎች ውስጥ እንዲሸጋሸጉ ደረጋል የመስኖ መሬት ሽግሽግ አስገዳጅ ሁኔታ ካላጋጠመው በስተቀር በቀበሌ ደረጃ በየመስኖ ብሎኩ እንዲካሄድ ጥረት ይደረጋል በሽግሽጉ ወቅት በመስኖ በሚለማው መሬት ላይ ማሳ ያላቸው ባለይዞታዎች ቅድሚያ ያገኛሉ በመቀጠልም ለመስኖ አውታር ግንባታ ማሳቸውን ያጡ የቀበሌው ነዋሪዎች እንዲሸጋሸጉ ይደረጋል በመጨረሻም የመስኖ መሬት የማግኘት መብት ያላቸውና ከቀበሌው ውጪ ነዋሪ የሆኑ ባለመብቶች እርቀታቸውን ግምት ውስጥ በማስገባት እንደቅደም ተከተላቸው እንዲሸጋሸጉ ይደረጋል በአንቀጽ ንዑስ አንቀጽ የተመለከተው እንደተጠበቀ ሆኖ የመሬት ሽግሽግ በሚካሄድበት ጊዜ ሁሉንም ባለይዞታዎች በአንድ የሰብል ዘመን ማሸጋሸግ በማይቻልበት ጊዜና በቀበሌው ውስጥ የሚገኘው በመስኖ የሚለማ መሬት ለሁሉም ባለመብቶች በቂ በማይሆንበት ጊዜ በሚከተለው ቅደም ተከተል መሰረት ይከናወናል ሀ በመስኖ በሚለማው ክልል ውስጥ የመኖሪያ ቤት ላላቸው ለ በመስኖ በሚለማው ክልል ውስጥ ቋሚ ሰብል ላላቸው ሐ መሬታቸው በሙሉ ለመስኖ መሰረተ ግንባታ በመዋሉ ምክንያት የግብርና ስራ ለማከናወን ለተቸገሩ መ ከፍተኛ መሬት ለተወሰደባቸው ሠ መሬታቸው ለመስኖ መሰረተ ልማት በመወሰዱ ምክንያት ካሳ ተከፍሏቸው ካሳ የተከፈለበት የጊዜ ገደብ ለተጠናቀቀ ባለይዞታዎች የጊዜ ገደቡ ከተጠናቀቀ በኋላ እንዲቆዩ የተገደዱበትን የጊዜ ብዛት ግምት ውስጥ በማስገባት ለመስኖ መሰረተ ልማት ግንባታው ይዞታቸውን ያጡ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የተወሠደባቸው መሬት በመስኖ ከሚለማው መሬት በቅርብ ርቀት በሚገኝ በዝናብ በሚለማና ለስራቸው ተስማሚ በሆነ አካባቢ ትክ መሬት እንዲያገኙ ይደረጋል ትክ ለመስጠት ከይዞታ ነጻ የሆነና ተስማሚ መሬት ባመገኘቱ ምክንያት ከሌሎች ባለይዞዎች መሬት ከተወሰደ ለተወሰደው መሬት በቀመሩ መሰረት ተመጣጣኝ የሆነ ትክ መሬት በመስኖ ከሜለማው አካባቢ በሽግሽግ እንዲያገኙ ይደረጋል የወል መሬት በመስኖ እንዲለማ ከተደረገ በወል መሬቱ ተጠቃሚ የሆነው በህዝብ ውሳኔ መሰረት መሬታቸው ለተወሰዳባቸው እንዲተካ ወይም በቀበሌው ውስጥ ለሚገኙ አዲስ መሬት ጠያቂዎች በህጉ መሰረት ሊሸጋሸግ ይችላል ለምርምር ለሠርቶ ማሣያና እና ለመሳሰሉት የጋራ አገልግሎቶች የሚውልን መሬት ከሁሉም ተጠቃሚዎች በተነጻጻሪ ለመቀነስ የሚያስችል አሰራር በሽግሽግ ቀመሩ ውስጥ እንዲካተት በማድረግ መሬቱ በእያንዳንዱ የመስኖ ብሎክ ውስጥ ከግል ይዞታ ውጪ ሆኖ እንዲቆይ ይደረጋል አንቀጽ የመስኖ መሬት ኩታ ገጠም ስለማድረግ አንድ ባለይዞታ በተለያዩ ቦታ በመስኖ የሚለማ መሬት ያለው እንደሆነ ወደ አንድ ማቀራረብ የሚሰጠውን ጠቀሜታ ግምት ውስጥ በማስገባት በተለያየ ቦታ ያለው ማሣ ወደ አንድ እንዲጠቃለል ይደረጋል ማሳዎችን ኩታ ገጠም በማድረግ ረገድ የመስኖ ፕሮጀክት እቅድ በተጠቃሚው ህብረተሰብ ከመጽደቁ በፊት በውሀ ገብ መሬት ላይ የተገነቡ ቤቶች ካሉ በቤቶች ዙሪያ እንዲሆን ይደረጋል ለቋሚ ሰብሎችም በተቻለ መጠን ቅድሚያ ይሰጣል የልማት እቅዱ ከጸደቀ በኋላ የተሰራ ቤትና የለማ ሰብል ማሳን ኩታ ገጠም በማድረግ ሂደት ውስጥ ግምት ውስጥ እንዲገባ አይደረግም ማሳዎች ወደ አንድ ቦታ በሽግሽግ ወቅት እንዲሰባሰቡ ከተደረገ በኋላ በሚደረግ የይዞታ ለውጥና ክፍፍል ምክንያት ማሳዎች እንደገና ከተበታተኑ ማሣዎችን የማጠጋጋት ተግባር በባለይዞታዎች ፈቃድ ሊከናወን ይችላል በማሳ ማጠጋጋት ወቅት ቋሚ ሰብል ያለበት መሬት የሚደርሰው የመስኖ ተጠቃሟ በዚህ መመሪያ አንቀጽ መሰረት ካሳ እንዲከፍል ይደረጋል በአንድ አካባቢ ተጠጋግተው የተሰሩ መኖሪያ ቤቶች በሚኖሩበት ጊዜና ይዞታን ኩታ ገጠም ለማድረግ አስቸጋሪ ሆኖ ሲገኝ ለአንድ የመስኖ መሬት ባለይዞታ ከአንድ በላይ በሆኑ ቦታዎች ላይ ማሳዎች እንዲኖሩት ሊደረግ ይችላል አንቀጽ ካሣ አከፋፈል ለመስኖ መሠረተ ልማት የሚወሰደው መሬት ለአመታዊ ሰብል ምርት የዋለ ከሆነ ሽግሽግ ተከሂዶ ትክ መሬት እስከሚያገኝ ድረስ በየዓመቱ ከመሬቱ ይገኝ ለነበረው ምርት ግምት በካሣ መልክ እንዲከፈል ይደረጋል የካሳው ጊዜም መሬቱ ከተወሰደበት ዓመት ጀምሮ ትክ መሬት እስከሚያገኝበት ጊዜ ድረስ ይሆናል ትክ የውሀ ገብ መሬት መስኖው በሚጀምርበት ዓመት ሊሰጥ ይችላል በመሬቱ ላይ ቋሚ ሰብል ያለበት ከሆነም ሰብሉ የሚሰጠው ጥቅም እንዳይቋረጥ የዓመታዊ ገቢውንና አዲስ የሚለማው ሰብል ምርት ለመስጠት የሚፈጅበትን ጊዜ ባገናዘበ ሁኔታ ካሣ ይከፈለዋል ቋሚ ሰብሉ ምርት ለመስጠት ያልደረሰ ከሆነ ባለንብረቱ ያወጣውን ወጭ ሊተካ የሚችል ካሳ በባለሙያ ተገምቶ እንዲከፈለው ይደረጋል የመስኖው መሠረተ ልማት ተጠናቆ የመሬት ሽግሽግ እስከሚደረግ ድረስ መሬት ለግንባታው ለተወፉሠደባቸው ባለይዞታዎች የመስኖ ልማቱ የሚሠራው በተጠቃሚዎች የገንዘብ መዋጮ ከሆነ ካሳውን ሕዝቡ የሚከፍል ሲሆን በመንግሥት ድጋፍ ዋጋ በመተካት አሰራር የሚገነባ ከሆነ ደግሞ ካሣውን መንግሥት በቅድሚያ ከፍሎ ከሕዝቡ በብድር መልክ እንዲሰበሰብ ይደረጋል መስኖው በእርዳታ ወይም በመንግስት ድጋፍ የሚከናወን ከሆነ በውል ስምምነቱ ውስጥ ህዝቡ ካሳውን እንደሚሸፍን ካልተገለጸ በስተቀር የካሳውን ወጪ የመሸፈን ሀላፊነት ለልማቱ የገንዘብ ድጋፍ ያደረገው አካል ይሆናል ወደ ማሣ ውሀ የሚያስገባውን ቦይ ለመስራት ጥቅም ላይ የሚውል መሬት ምንም አይነት ካሣ አይከፈልበትም በመስኖ መሬት ሽግሽግ ምክንያት ቋሚ ንብረታቸውን የሚያጡ ባለይዞታዎች የንብረታቸው መጠን በባለሙያዎች ኮሚቴ ተገምቶ መሬቱን በሽግሽግ ከሚያገኙ ሰዎች እንዲከፈላቸው ይደረጋል ባለግዴታው በአንድ ጊዜና በቅድሚያ መክፈል እንደማይችል በጽሁፍ ከጠየቀና የባለስልጣኑ የወረዳ ጽቤት ይህንኑ ካረጋገጠ ካሳው በቅድሚያ ከመንግስት እንዲከፈል ተደርጎ ባለግዴታው የባንክ ወለድን ሳይጨምር በመንግስት የተከፈለውን የገንዘብ መጠን ለመንግስት ለመተካት ግዴታ ይገባልክፍያውንም እጅግ ቢዘገይ በአስር ዓመት ጊዜ ውስጥ ለወረዳው ፋይናንስ ከፍሎ ማጠናቀቅ ይኖርበታል የመስኖ መሬት ሽግሽግ ሲካሄድ ቋሚ ሰብልና ንብረት ያለበት መሬት ከሆነ ለባለይዞታው ቅድሚያ እንዲሰጥ ጥረት ይደረጋል ከቀድሞው ባለይዞታው ላይ ቋሚ ንብረት ያለበት መሬት እንዲቀነስ ከተወሰነ ሀ ሊነሱ የሚችሉት ምርቶችን የመስኖ ልማት ከመጀመሩ በፊት እንዲያነሳ ይደረጋል ለ ንብረቱ ለማንሳት የሚያስፈልገውን የማጓጓዣ ወጪና የሚደርሰውን ጉዳት በሽግሽጉ መሬቱ የሚሰጠው ባለይዞታ እንዲከፈል ይደረጋል የካሣው መጠንም በባለሙያዎች ኮሚቴ ይወሰናል ለማይነሱ ነገር ግን አላባቸውን ማንሳት ለሚቻልና ቀጣይነት ለሌላቸው ቋሚ ሰብሎች ለምርት የደረሱ ከሆነ ቆርጦ እንዲያነሳ ይደረጋል ለምርት ካልደረሱም ለምርት ሲደርሱ ቆርጦ እንዲወስድ ይደረጋል ቋሚ ሰብሉ በተከታታይ ምርት የመስጠት ባህሪ ካለው መሬቱን የሚረከበው አዲሱ ባለይዞታ በአዲስ መልክ ሰብሉን አልምቶ ምርት እንዲሰጥ ለማድረግ የሚያስፈልጉትን አመታትና አመታዊ የሰብሉን ገቢ ባገናዘበ መልኩ በባለሙያዎች ኮሜቴ ተገምቶ እንዲከፈል ይደረጋል ቋሚ ሰብሉ ምርት ለመስጠት ያልደረሰ ከሆነ ለባለንብረቱ መሬቱን የሚረከበው አዲስ ባለይዞታ አትክልቱን ለማሣደግ ያወጣውን ወጭ በባለሙያዎች ኮሚቴ ተገምቶ እንዲከፈለው ይደረጋል አንቀጽ የመስኖ መሬት ባለይዞታዎች መብት ለሌሎች የገጠር መሬት ባለይዞታዎች በህግ ከተሰጡ መብቶች በተጨማሪ የመስኖ መሬት ባለይዞታ የሚከተሉት መብቶች ይኖሩታል በመስኖ መሬት የመጠቀምና በመስኖ ማህበሩ ደንብ መሠረት ውሃ የማግኘት በመስኖ ባለይዞታዎች ስብሰባ የመገኘት የመምረጥና የመመረጥ የሙያ ምክርና ድጋፍ የማግኘት መብቶች ይኖሩታል አንቀጽ የመስኖ መሬት ባለይዘታዎች ግዴታ ለሌሎች የገጠር መሬት ባለይዞታዎች በህግ ከተጣሉ ገደቦች በተጨማሪ የመስኖ መሬት ባለይዞታ የሚከተሉት ግዴታዎች ይኖሩበታል የመስኖ ውሃን በአግባቡና በቁጠባ የመጠቀም አዳዲስ የመስኖ ቴክኖሎጂዎችን በባለሙያዎች በሚሰጠው ምክር መሠረት ተግባራዊ የማድረግ የመስኖውን መሬት በተገቢው መንገድ የመንከባከብ በሽግሸግ የተገኘውን መሬት ድንበር አለመግፋትና የድንበር ምልክቶችን ያለማጥፋት የመስኖ ቦይ መጠበቅ የማፅዳትና የመጠገን በተፋሰስ ልማት እንቅስቃሴው ውስጥ ንቁ ተሳትፎ የማድረግ በመስኖ ውሃ አጠቃቀም ወይም በአጎራባች መስኖ ተጠቃሚዎች ላይ ጉዳት እንደሚያመጡ በመታመኑ ምክንያት በባለሙያዎች የተከለከሉ ሰብሎችን ያለማልማት መሬትን በተፈጥሮ መንገድ እንዲያገግም ለማድረግ ካልሆነ በስተቀር የመስኖ መሬትን ጦም አለማሳደር በስምምነቱ ላይ የተገለጹትን የመስኖ ኘሮጀክቱን ግንባታ ወጪ የመጋራት ኃላፊነቶችን የመወጣት በዘመናዊ መስኖ የሚለማ መሬት የሚያስፈልገውን ተጨማሪ ግብአት በማቅረብ የሚደርስ የምርትና የምርታማነት መቀነስ እንዳይከሰት የመከላከል አንቀጽ የመስኖ መሬት ሽግሽግ ኮሚቴ ስለማቋቋም የመስኖ መሬት ሽግሽግ ኮሚቴ አባላት በተጠቃሚዎች ሙሉ ተሳትፎ ይመረጣሉ በዚህ ስብሰባ ላይ ሁሉም ወንድና ሴት ባለይዞታዎች ባለትዳር ሴቶችን ጨምሮ እንዲሳተፉ ጥረት ይደረጋል በኮሚቴ ምርጫ ወቅት ሴቶች ተመጣጣኝ ውክልና እንዲኖራቸው ይደረጋል የኮሚቴ አባላት ምርጫ በወረዳው ጽቤት ተወካይ ሰብሳቢነትና የቀበሌው አስተዳደርና የቀበሌው የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ኮሚቴ አባላት በተገኙበት ይከናወናል የመስኖ መሬት ሸግሽግ የኮሚቴ አባላት ብዛት ከ ሲሆን የቅሬታ አጣሪና ቁጥጥር ኮሚቴ አባላት ብዛት ደግሞ ከ ይሆናል የኮሚቴው አባላት ምርጫ ከተጠናቀቀ በኋላ ለአባላቱ በባለሥለጣኑ የወረዳ ተጠሪ ጽቤት አማካይነት ሥራውን ለማከናወን የሚያስችል ሥልጠና ይሰጣቸዋል የኮሚቴው የአገልግሎት ዘመን የመስኖ መሬት ሽግሽግ እንደተጠናቀቀ የመስኖ መሬት ሽግሽግ መረጃ ለቀበሌው የመአስአአጠኮሚቴ በማስረከብ ይጠናቀቃል የኮሚቴው አባላት ተጠሪነት እንደጉዳዮቹ አግባብነት ለመረጣቸው ሕዝብ ለቀበሌው የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ኮሚቴና ለወረዳው ተጠሪ ጽቤት ይሆናል የመስኖ ልማቱ ከአንድ ቀበሌ በላይ የሚካሄድ ከሆነ አብይ የመሬት ሸግሸሽሸግና ቅሬታ አጣሪ አብይ ኮሜቴ ይቋቋማል የአብይ የሽግሽግና ቅሬታ አጣሪ የኮሚቴው አባላት ከእያንዳንዱ ቀበሌ ኮሚቴዎች የሚወከሉ አንድ አንድ ሰዎች ይሆናለሉ አብይ ኮሚቴውም ሆነ የቀበሌ ኮሚቴዎች የራሳቸውን ሊቀመንበርና ጸሀፊ ይመርጣሉ አንቀጽ የኮሚቴዎች ተግባርና ኃላፊነት የቀበሌ የመስኖ መሬት ሸግሽግ ኮሚቴ ኮሚቴው ለመስኖ አውታር ከባለይዞታዎች የተወሰደውን መሬት መጠን ያጣራል ዝርዝሩንም ለሕዝብ አቅርቦ ያፀድቃል የመስኖ ተጠቃሚዎች ዝርዝርና የመስኖ መሬት ስፋት በዝርዝር ይመዘግባል ለሕዝብ አቅርቦ ያስፀድቃል የዘመናዊ መስኖ መሬት የሽግሽግ መመሪያን ለተጠቃሚዎች ያሳውቃል የመስኖው መሬት ሽግሽግ ሲካሄድ በቀበሌው ውስጥ ከመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ኮሜቴ ጋር በቅንጅት ይሠራል በምዝገባ ወቅት ከይዞታ ነፃ የሆነ መሬት መዝግቦ ለቀበሌው መአስተአጠኮ ያቀርባልከይዞታ ነፃ የሆነው መሬት የቀበሌው ሕዝብ በሚያስቀምጠው ቅደም ተከተል መሠረት ከመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ኮሚቴዎች ጋር በመሆን ለአዲስ መሬት ጠያቂዎች ይሰጣል ስለመስኖ መሬት ሽግሽጉ በየጊዜው ለመስኖ መሬት ተጠቃሚዎችና ለወረዳው የአካጥመአአ ተጠሪ ጽቤት ሪፖርት ያቀርባል የቅሬታ አጣሪና ቁጥጥር ኮሚቴ ተግባርና ኃላፊነት ለመስኖ አውታር የዋለውም ይሁን በመስኖ የሚለማው መሬት በትክክል መመዝገቡን ያረጋግጣል የመስኖ መሬት ልኬታ ምዝገባና ሽግሸግን በመመሪያው መሠረት መካሄዱን ይከታተላል ከተጠቃሚዎች የሚቀርበውን ቅሬታ ይቀበላል ያጣራል በመመሪያው መሠረት እንዲፈፀም ያደርጋል ስለ መሬት ምዝገባና ሽግሽግ ሂደቱም ለመረጠው ሕዝብ ሪፖርት ያደርጋል የአብይ ኮሚቴ ተግባርና ሀላፊነት የመስኖ መሬት ሽግሽግ በቀመሩና በመመሪያው መሠረት መከናወኑን ይከታተላል ከቅሬታ አጣሪና ቁጥጥር ኮሚቴ አቅም በላይ የሆኑ ቅሬታዎችን ያጣራል ከመመሪያ ውጭ የተሠራ ካለ እንዲስተካከል ያደርጋል በመስኖ መሬት ሽግሽግ ሴቶች አረጋዊያን አሳዳጊ የሌላቸው ሕፃናት በአካባቢ የሌሉ ባለይዞታዎች ወዘተ መብታቸው መከበሩን ይከታተላል ከአንድ ቀበሌ በላይ የሚደረግን የመሬት ሽግሽግ በመመሪያው መሰረት ተግባራዊ ያደርጋል አንቀጽ የሌሎች አካላት ተግባርና ኃላፊነት የወረዳ አከጠመአአ ተጠሪ ጽቤት ቀ ቀ ቀ ኮሚቴዎችን በሕዝብ ያስመርጣል ሥልጠናና ትምህርት ይሰጣል በመስኖ አውታር የተዘረጋበትንና በመስኖ የሚለማውን መሬት በመሳሪያ ይለካል የመስኖ መሬቱንን ሸግሽጉን የሚያሳይ ካርታ አዘጋጅቶ በኮሚቴዎችና በባለይዞታዎች እንዲተች ያደርጋል በኮሚቴዎች በመታገዝ የመሬት ሽግሽጉን በበላይነት ይመራል አስተዳደራዊ ውሳኔ በሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ላይ ከወረዳው አስተዳደር ጋር በትብብር ይሰራል የቀበሌ አስተዳደር ተግባርና ኃላፊነት ቀ ቀ ቀ ለኮሚቴው ተገቢውን ድጋፍ ያደርጋል የመሬት ሸግሽጉ ሲካሄድ በታዛቢነት ይገኛልያስተባብራል ኮሚቴዎችን ስራ በቢሮና በቁሳቁስ ያግዛል የህግ ማስከበርና የማስፈጸም ስራ የሚፈልጉ ውሳኔዎችን ተግባራዊ ያደርጋል ኮሚቶዎቹ ከህግና ከመመሪያ ውጪ እንዳይሰሩ ክትትልና ቁጥጥር ያደርጋል።

  • N.B. This Summary is Very Experimental!! based on the following scripts from:
    • https://github.com/millzon/textSummarizer-am
    • https://github.com/icoxfog417/awesome-text-summarization#motivation
Download Searchable PDF Download PDF

አስተያየቶች:


memezon

የማውረድ አማራጮች | ወደ ፒዲኤፍ ቀይር | የዕለቱ መጽሐፍ

© dirzon | የአገልግሎት ደንቦች | የግላዊነት መምሪያ | ስለ | አገልግሎቶች | መልእክት