Detecting...
Please whitelist dirzon to continue.
እያለች ቤት ያከራየቻት ሴት ስትለፈልፍባትና ከቤት ለማስወጣት ስትዝትባት ነበር ስለዚህ ሚስስ ማርሜላዶቭ ግን በጄ አላለችም ትንፋጂ ቁርጥ ቁርጥ እያለና እያሳለች እንዲህ ስትል በመጮህ ተናገረች ሶንያ እረፊ። ጌታው ምንም ነገር አያውቁም። ቢያንስ በሰላም ልሙት እንደገና ትራስ አስደግፈው አስተኙአት ዋምን ቄስ ነው የምትሉት። እግራችሁን አንቀሳቅሱና እንዝፈን እንዲያውም በጠራራ ፀሀይ ሸለቆ ውስጥ ሆነን የሚለውን ዘፈን አባታችሁ ይወደው ነበር ስንቱ ደግ ጊዜ አለፈ መዝፈን ያለብን ይሄን ዘፈን ነው ግን አስታውሱኝ እንዴት ነበር። አንጀት በሚበላ ሁኔታ አይኖቿ እንባ እያመነጩ የሟቹ ባሌ ትብብር ያልተለየዎት እንደመሆኑ መጠን ክቡርነትዎ ለእነዚህ ለሙት ልጆቼ አንድ ነገር ያድርጉላቸው። በቅሎዋን ወደሞት እየጋለቧት ነው። በአሁኑ ሰአት ግን ህሊናዋን ስታ ለረጅም ጊዜ አልቆየችም።
ለእንግዶች ቦታ እንዳይጠብ ታስቦ ሕፃናቱ አብዛኛውን ክፍሉን ያዳረሰው ጠረጴዛ ሳይ አልቀረቡም ሁለቱ ሕፃናት ከአግዳሚ ወንበር ተቀምጠው ትልቋ ፖልያ አፍንጫቸውን እያበሰች በጥግ በኩል ካለው ሳጥን ላይ የቀረበውን ምግብ ልታጎርሳቸው ተዘጋጅታለች ሚስስ ማርሜላዶቭ ወደደችም ጠላችም ኮራ ብላ እንግዶቿን መቀበል ነበረባት አንዳንዶቹንማ እንደባለስልጣን ከፍና ዝቅ አድርጋ እየተመለከተች መቀመጫቸውን እንዲይዙ በበሳይነት ስሜት ትጋብዛቸዋለች በግብዣው ላይ ሳልተገኙት ሰዎች ተጠያቂው የቤቱ ባለቤት ሚስስ ሊፕቬል ነች ብላ ስለገመተች በንቀት ትመለከታት ገባች ይሄን ደግሞ የቤቱ ባለቤት ወዲያውኑ አስተዋለችና በጣም ተቀየመች ግብዣው በጣም ቀዝቀዝ ብሎ ተጀመፈና ሁሉም ቦታውን ያዘ ራስኮልኒኮቭ የደረሰው ከቀብር እንደተመለሱ ነበር ከእንግዶቿ መካከል ብቸኛው የተማረሰው እርሱ በመሆኑና ሁሉም እንደሚረዳው ለሁለት አመት በዩኒቨርስቲ በመቆየቱ ሚስስ ማርሜላዶቭ ገና እንዳየችው ደስ አላት በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ እንደፍላጎቱ ሳይሆን ቀርቶ ለቀብር ባለመድረሱ ይቅርታ እንዲደረግለት ወዲያውኑ በትሕትና ይቅርታ ስለጠየቀ ልቧ በደስታ ስሜት ተሞላ ይዛ በግራ በኩል ከነኗ እንዲቀመጥ አደረገችው ሚስስ ሊፕሼቬል ከቀጂ በኩል ተቀምጣለች እያንዳንዱ ሰው በሚገባ መጋበዙንና በቂ ምግብ ማግኘቱን ጉራ ከተቀላቀለበት አካሄድ ጋር ለመቆጣጠር ብትሞክርም ቅሉ ባለፉት ሁለት ቀናት እየተባባሰባት ሄዶ በየደቂቃው ንግግሯን ደረቅ ሳል ቢያቋርጠውም ቅሉ የተጠራቀመውን ስሜቷንና በድግሱ አለመሳካት የተሰማትን ንዴት ለራስኮልኒኮቭ ያለማቋረጥ በሽክሹክታ ነገረችው ይሁንና እንግዶቿ በተለይም የቤቱ ባለቤት በሚያሳዩት ደማቅ ሳቅ ንዴቷ ። ሶንያ ግን የት ነች። ከዚያም ራስኮልኒኮቭን እጅ ነስታና በጨረፍታ ተመልክታ ከአጠገቡ ተቀመጠች ብዙውን ጊዜ ግን እርሱን ላለማየትና ላለማነጋገር የምትሞክር ይመስሳል ሚስስ ማርሜላዶቭን ለማስደሰት ብላ ትኩረቷን ሁሉ ወደ እርሷ ብታደርግም በሀሳብ የተመሰጠች መስላ ትታያለች እርሳም ሆነች ሚስስ ማርሜላዶቭ የሀዘን ልብስ ስላልነበራቸው አለበሱም ሶንያ ቡናማ ቀሚስ ሚስስ ማርሜላዶቭ ደግሞ ጥቁር ሰረዝ ጣል ያለበትን ብቸኛውን የሐር ቀሚሷን ለብሳለች የሚስተር ለዚን የይቅርታ መልእክት በሚስስ ማርሜላዶቭ ዘንድ የኩራት ስሜት አሳደረ ለቤተሰቧ ፍቅር ከአባቷም ጋር የቆየ ወዳጅነት ቢኖረውም በሕብረተሰቡ ውስጥ አቢይ ቦታ ያለውና በጣም የተከበረ ሚስተር ለዚንን የመሰለ ሰው ከእንዲህ አይነት መናኛዎች መካከል ቢገኝ ኖሮ የሚያስገርም ነበር ስትል ለራስኮልኒኮቭ በጎላ ድምፅ ተናገረች ተወዳጁ ሚስተር ራስኮልኒኮቭ በእንዲህ አይነቱ ሁኔታ ውስጥ እንኳን ጥሪዬን አክብረህ በመገኘትህ አመሰግናለሁ ቃልህን እንድታከብር ያደረገህ ለምስኪኑ ባሌ ያለህ ታላቅ ወዳጅነት እንደሆነ እርግጠኛ ነኝ ስትል ንግግሯን አዳበረችው ከዚያም እንግዶቿን በድጋሚ በኩራት ተመለከተችና አሻግራ የምታየው መስማት የተሳነው ሰው የስጋ ጥብስ በድጋሚ እንዲወስድና የሊስበን ወይን ጠጅ ተቀድቶለት እንደሆን ጠየቀች ሰውየው ግን ከአጠገቡ ያሉት ለጨዋታ ያህል አጁን እየያዙ ቢጨብጡትም የተጠየቀው ምን እንደሆነ ለብዙ ጊዜ አልተረዳም እንዲያውም አፉን ከፍቶ ይመለከት ስለነበር ሳቅና ሁካታው ቀጠለ እስቲ ይታይህ። ፈረንሳዊ ሽማግሌ አወራች በመዋቅሯ ውስጥ ሶንያም ስለታቀፈች ረዳቷ እንደምትሆን አበሰረች ይሄን ከማለቷ ከማዶ ያለ ሰው የሆነ የሽሙጥ ድምፅ አሰማ እርሳም በተራዋ አሽሟጣጩን ለማሳፈር የሚቻላትን ሁሉ እያደረገች ሶንያ ረዳቷ ለመሆን ያላትን የማይካድ ችሎታጨዋነቷን ታጋሽነቷን ታማኝነቷንና በትምህርት መታነጺን ጎላ አድርጋ ተናገረች ይሄን ያለችው የሶንያን ጉንጭ ይዛ እየሳመች ነበር ሶንያ ሀፍረት ተሰማት ቂስስ ማርሜሳዶቭ ደግሞ በራሷ ሞኝነት ተገርማ አለቀሰች እንግዶች መብላት ስላቆሙ ሻይ ተሰጥቷቸው ግብዣው የሜጠናቀቅበት ሰአት ሳይ እንደደረሱ ሚስስ ሊፕሼል አድማጭ ባለማግኘቷ ተቀይማ ስለነበር ሚስስ ማርሜላዶቭን ለማናደድ ብላ በአዳሪ ትቤቱ ውስጥ የሚሠሩት ወጣት ሴቶች ልብስ ንፁህ እንዲሆን አሳሰበች ለዚህ ስራ ሀላፊነት የምትወስደው የላውንድሪ ክፍሷ እንጂ የትቤቱ ዲሬክተር እንዳልሆነች በመናገር እየተሰሳቸች ሚስስ ማርሜላዶቭ አፀፋውን መለሰች የቤቱ ባለቤት ሚስስ ሊፕሼል ደግ አስባላት የተናገረች መሆኑን ብታሳውቅም ሚስስ ማርሜላዶቭ በትናንትናው እለት የባሏ አስከሬን ተዘርግቶ እያለ የቤት ኪራይ የጠየቀች ሴት ደግ ልታስብሳት እንደማትችል ገለፀች። ሚስስ ማርሜላዴዶቭ ከመቀመጫዋ ተነስታና ኮስተር ብሳ ተወዳጅ አባቷን ከእርሷ አባት ጋር ለማነፃፀር ከእንግዲህ ብትሞክር ያደረገችውን ባርኔጣ ቀዳዳ አእንደምትጥልባት በደከመ ድምጺ ተናገረች በዚህን ጊዜ ሚስስ ሊፕቬል በክፍሉ ውስጥ እየተንጎራደደችና የቤቱ ባለቤት እርሷ መሆኗን አጉልታ እየገለፀች ከአሁኑ ሰአት አንስቶ ሚስስ ማርሜላዶቭ ቤቱን እንድትለቅ ቀጭን ትእዛዚን አስተላለፈች ከዚያም ከጠረጴዛው ላይ የነበሩትን ከብር የተሠሩ ማንኪያዎቿን መሰብሰብ ጀመረች ከፍተኛ ጫጫታ ተከተለና ሕፃናቱ ያለቅሱ ገባ ሶንያ የእንጀራ እናቷን ለማረጋጋት በማሰብ ወደ ሚስስ ማርሜላዶቭ ፈጥና ስትሄድ ሚስስ ማርሜላዶቭ ሶንያጊ መነጨቀቻትና ቤቱን ባለቤት ባርፄጣ ቀዶ ለመጣል ተፍጨረጨረች በዚህ ቅፅበት ላይ በሩ ተከፈተና ሚስተር ሉዚን ከደጃፉ መቆሙ ታወቀ በክፍሉ ውስጥ የነበሩትን ሰዎች በጥሞና አማተረ ሚስስ ማርሜሳዶቭ ፈጥና ወደ እርሱ አመራች ሚስተር ሉዚንቢያንስ አንተ ከለላ እንደምትሆነኝ ተስፋ አለኝ ሀዘንተኛን ሴት እንዲህ ማድረግ እንደማይቻል ለዚህች ደደብ አስረዳት ይሄን የሚመለከት ሕግ ስላለ ወደሀገረ ገዢው ሄጄ አቤት አላለሁ በሀሳፊነት ትጠየቅበታለች የአባቴን ውለታ አስታውሰህ እነዚህን ምስኪን የሙት ልጆች አትርፍልኝ እያለች በማሳዘን ገለጠችለት ሴትዮ እባክሽን እንደምታውቂው ሀሉ ከአባትሽ ጋር አግባብነት ኖርኝ አያውቅም በዚሀን ጊዜ የሆነ ሰው ከት ብሉ ሳቀ ከሚስስ ሊፕሼል ጋር በየጊዜው የምታደርጉት ጭቅጭቅ እንዲመለከተኝ አልፈልግም ወደዚህ የመጣሁት ለራሴ የግል ጉዳይ ነው የእንጀራ ልጅሽ ስም ሶንያ ይመስለኛል አይደለም እንዴ። ከእርሷ ጋር ጉዳይ ስላለኝ አሳልፊኝ በማለት አመናጨቃት ሚስተር ሉሌዚን ሚስስ ማርሜሳዶቭን አልፎ ሶንያ ወዳለችበት ጥግ አመራ ሚስስ ማርሜላዶቭ በመብረቅ የተመታች ይመስል ከቆመችበት ክው ብላ ቀረች ሚስተር ሉዚን አባቷን ውለታቢስ አድርጎ ለምን እንደተናገረ ሊዝባት አልቻለም የሚስተር ሌዚን ለዛ ቢስ የአንገት በላይ ንግግር ግራ አጋባት የሰውየው መገኝት አስገርሞት በክፍሉ ውስጥ ያለው ሁሉ በዝምታ ተዋጠ እንዲህ አይነት ኮስታራ የስራ ሰው ከተሰበሰቡት መካከል የሚመጥነውን አለማግኘቱ ብቻ ሳይሆን ወደዚያም የመጣው አንድ ከፍተኛ ጉዳይ ገጥሞት እንደሆነ ግልፅ ነበር ሚስተር ሌዚን ባያስተውለውም ከሶንያ አጠገብ የቆመው ራስኮልኒኮቭ ስፍራ ለቀቀለትና አለፈ። ከዚህ ሁሉ ሰው ሶንያ ሌባ ነች። በማለት ሌቤዚያትኒኮቭ ጮሽኸ በመጨረሻም ራስኮልኒኮቭ ወደፊት ራመድ ብሎ በመቆም ምክንያቱን ማስረዳት እችላለሁ አስፈላጊ ከሆነም በመሀላ የተደገፈ የምስክርነት ቃል ለመስጠት ዝግጁ ነኝ ሲል ረጋ ባለ ድምዕ ተናገረ ከአቋሙ ዝንፍ የማይል መሆኑ በገሀድ ይታይ ስለነበር ሁሉም ነገር ግልጥልጥ እንደሚል እያንዳንዱ ሰው ገመተ በአሁኑ ሰአት ሁኔታውን በግልፅ እረዳለሁ ገና ከመጀመሪያው በነገሩ ላይ ተንኮል እንዳለበት ጠርጥሬአለሁ ለመጠርጠር የበቃሁትም የምገልዕላችሁና እኔ የማውቀው ጉዳይ ስላለ ነው ሚስተር ሌቤዚያትኒኮቭ ያቀረብከው ጠቃሚ ማስረጃ ደግሞ ሁሉንም ነገር በቀላሉ እንድረዳው አድርጎኛል በማለት ራስኮልኒኮቭ ከተናገረ በኋላ ማብራራቱን ቀጠለ ይህ ሉዚን የተባለ ሰው በቅርቡ ከእህቴ ጋር ተጫጭቶ ነበር ፒተርስቡርግ ደርሶ ከሁለት ቀናት በፊት ከእኔ ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ እንደተገናኘን ግን ጠብ ፈጥረን ከቤቴ አባርሬዋለሁ ለዚህም ሁለት ምስክሮች አሉኝ ይህ ሰው ፍፁም ከይሲ ነው ከሁለት ቀናት በፊት ከአንተ ከሚስተር ሌቤዚያትኒኮቭ ጋር መኖሩን አላውቅም ነበር ልክ በተጣላንበት ቀን ከትናንት በስቲያ የሟቹ ሚስተር ማርሜላዶቭ ጓደኛ በመሆኔ ለባለቤቱ ለቀብር የሚሆናትን ገንዘብ ስሰጣት አይቶኛል ወዲያውኑም ለእናቴ ማስታውሻ ይፅፍና ገንዘቤን ሁሉ ለሚስስ ማርሜላዶቭ ሳይሆን ለሶንያ እንደሰጠሁ ያሳውቃል። ለምን። ሶንያ የምትናገረው ጠፍቷት ቆመች ግን ወዲያውኑ ተርባችሁ ነበር ይሄን ያደረግኸው እናትህን ለመርዳት ብለህ ነው አይደለም እንዴ። እንዴ። እያለች ሶንያ የሰቆቃ ጩኸት አሰማች ሶንያ ኽረ የፈጣሪ ያለህ ብሎ በመበሳጨት ተናገረ የሆነ መልስ ሊሰጣት ቢፈልግም ቅር ተሰኝቶ በዝምታ ተዋጠ ሶንያ ንግግሬን አታቋርጪ። ሶንያን ተመለከታትና ለእርሱ ያላት ፍቅር የቱን ያህል ታላቅ እንደሆነ ተዝዘበ ክፉኛ ስለተሰቃየ መፈቀር እንዳለበት ተሰማው ወደ ሶንያ ባቀናበት ጊዜ ተስፋው ሁሉ ወሳኙ ሁሉ እርሷ እንደሆነች ተሰምቶት ነበር ከፊል ስቃዩን እንኳን ያላቀቀ መስሎት ነበር አሁን ግን ደግሞ ልቧን ከፍታ ስትሰጠው ከበፊቱ የባሰ የመከፋት ስሜት በድንገት ሰረፀበት ሶንያ በምታሰርበት ጊዜ መጥተሽ ባትጠይቂኝ ይሻላል ሶንያ መልስ አልሰጠችም እያነባች አያሌ ደቂቃዎች አለፉ በድንገት ሀሳብ የመጣላት ይመስል መስቀል ታደርጋለህ። ወዲያውኑ ዞር ብላ ወደበሩ አቀናች ራስኮልኒኮቭ ተነስቶ ሄዶ አስቆማትና ዳንያ ራዙምኪን በጣም ጥሩ ሰው ነው አላት ዳንያ በመጠኑ አፈረችና ትንሽ ቆየት ብላ ምን ማለቱ እንደሆን ጠየቀችው ከፍተኛ ስሜትና ፍቅር ያለው ሐቀኛ የስራ ሰው ነው እስከ ወዲያኛው ደህና ሁሺፒ ዳንያ ዳንያ ፊቷ ፍም ከመሰለ በኋላ ወዲያውኑ ደግሞ ተከፋችፅ ሮዲ ለመጨረሻ ጊዜ ነው እንዴ ሰላም የምንባባለው። ሶንያ ሚስስ ማርሜላዶቭ ወደቤት እንድትመለስ እየተማፀነችና እያለቀሰች እንደጥሳ ትከተላታለች ሚስስ ማርሜላዶቭ ግን በጄ አላለችም ትንፋጂ ቁርጥ ቁርጥ እያለና እያሳለች እንዲህ ስትል በመጮህ ተናገረች ሶንያ እረፊ። ራስኮልኒኮቭ አንተ ነህ እንዴ። አለች በእርግጥም አንድ ፖሊስ በተኮለኮለው ሕዝብ መሀል እየተጋፋ ይመጣ ነበር በሌላ በኩል ግን የመንግስት ሠራተኛ ልብስ የለበሰ ማእረግ ያለው ኮስታራ ሰው በሚስስ ማርሜላዶቭም ሆነ በፖሊሱ አይን ውስጥ ገብቶአል ጠጋ ብሎ ሶስት ሩብል ለሚስስ ማርሜላዶቭ ሰጣት በፊቱ ላይ ቅን ስሜት ይነበብበታል ሚስስ ማርሜላዶቭ ገንዘቡን ተቀበለችና በጨዋ ደንብ እጅ ነሳችው ኮራ ብላ እንዲህ ስትል ተናገረች በጣም አመሰግናለሁ ጌታው ስቃይ የደረሰባትን ድሀና ጨዋ ሴት ለመርዳት የተሰለፉ የተከበሩ ደጋግ ሰዎች አሉ ጌታው የሚያዩአቸው ከደህና ቤተሰብ የተፈሩ የሙት ልጆች ናቸው። ሶንያ ሶንያ። ሚስስ ማርሜላዶቭን በደንብ በተመለከቷት ጊዜ መንገዱን ያለበሰው ደሟ ይፈልቅ የነበረው ሶንያ እንደገመተችው ራሷን በስለት ቆርጣ ሳይሆን ከአፏ እንደሆነ ተገነዘቡ እንዲህ አይነት ነገር ከዚህ በፊት አጋጥሞኛል የሳንባ ነቀርሳ ውጤት ነውፅ ደም እያስተፋ ይገድላል የእኔ ዘመድ የሆነች ሴት እንዲህ ስትሞት በቅርቡ አይቻለሁ ምን ማድረግ ነው ያለብን። ደሙ መፍሰሱን ባያቋርጥም ህሊናዋን እያወቀች የሄደች መሰለች ፖሊሱ ከበው ይመለከቱ የነበሩና እስከበሩ ድረስ ተከትለው የመጡ አንዳንድ ሰዎችን ከአባረረ በኋላ በሶንያ መሪነት ራስኮልኒኮቭን ሌቤዚያትኒኮቭንና የመንግስት ሠራተኛውን ተከትሎ ወደክፍሉ ገባ ፖልያ ያለቅሱና ይንቀጠቀጡ የነበሩትን ኮልያንና ሊዳን እየመራች ተከተለች የካፔርናሞቭ ቤተሰቦችም ደረሱ አንካሳውና አንድ አይናማው ሜስተር ካፔርናሞቭ ዊሙን አንዣርግነ ሁልጊዜ በፍርሀት የምትናወጥ ከምትመስለው ሚስቱ ጋር አፋቸውን ከፍተው የመገረም ገፅታ በሚታይባቸው ልጆቹ ታጅቦ ከተፍ አለ ስቪድሪጋሎቭም ሳይታሰብ ደረሰ ከየት እንደመጣ ለማወቅ አቅቶትና ከተሰበሰበው ሕዝብ መካከል አይቶት እንደሆነ ለማስታወስ ተስኖት ራስኮልኒኮቭ በመገረም ተመለከተው ሐኪምና ቄስ እንዲመጡ ትጠየቀ በአሁኑ ደረጃ የሐኪም መምጣት ዋጋ እንደሌለው የመንግስት ሠራተኛው ለራስኮልኒኮቭ ቢያንሾካሹክለትም ሰው መላኩን ተገነዘበ ካፔርናሞቭ ፈልጎ ሊያመጣ ሄሷል ሚስስ ማርሜላዶቭ ትንፋጂ መለስ ብሎላታል ለጊዜውም ቢሆን ደሙ ከመፍሰስ አቁሞአል ገርጥታ እየተንቀጠቀጠች ከግንባሯ ላይ የነበረውን ላብ በመሀረብ የምትጠርግላትን ሶንያን ትክ ብላ ተመለከተቻት ብድግ እንዲያደርጓት ጠየቀች ከግራና ከቀኝ ተደገፈችና አልጋው ሳይ ተቀመጠች ልጆቹ የት አሉ። ስትል በደከመ ድምፅ ጠየቀች ፖልያ አመጣሻቸው። ሲል ጠየቀ ከቁጥጥር ውጭ ሆናለች ሶንያ ሳትሆን ሚስስ ማርሜሳዶቭ ማለቴ ነው ሶንያም ብዙ አትርቅም ሚስስ ማርሜላዶቭ ግን አእምሮዋን ስታለች አብዳለች ነው የምልህ ወደፖሊስ ጣቢያ ይወሰዳሉ ይሄ ደግሞ ጣጣ ያመጣባቸዋል በአሁኑ ሰኣት ከሶንያ ቤት አካባቢ ከሚገኘው ድልድይ አጠገብ ናቸው ሶንያ ከምትኖርበት አካባቢ ሁለት የሚሆኑ ሕንፃዎችን አልፎ ከሚገኘው ድልድይ ስር ካለው የወንዝ ዳርቻ ላይ ሰዎች ተኮልኩለዋል ገና ከድልድዩ ላይ የሚስስ ማርሜሳዶቭ የጎረናና የተሰባበረ ድምፅ ይሰማል ሁኔታው ያልተለመደና እይታ የሚጋብዝ ነው ሚስስ ማርሜላዶቭ ያረጀ ቀሚስ አረንጓዴ ነጠላና የተቀደደ ባርኔጣ አድርጋ ከቁጥጥር ውጭ ሆናለች ቁርቁዝ ብላ ቁና ቁና ትተነፍሳለች። የመከፋቷ መጠን በየደቂቃው ይጨምራል ወደልጆቿ እየሮጠች ትጮህባቸዋለች ታግባባቸዋለች እንዴት መጨፈርና ምን መዝፈን እንደሚኖርባቸው በተሰበሰበው ሕዝብ ፊት ትነግራቸዋለች አስፈላጊነቱን ትገልዕሳቸዋለች ሳይገባቸው ሲቀር ደግሞ ትደበድባቸዋለች ወዲያውኑ ደግሞ የጀመረችውን ትተውና ወደተሰበሰበው ሕዝብ ትሮጣለች ደህና የለበሰ ሰው ካየች ከጨዋ ቤተሰብ የወጡ እነዚህ ሕፃናት ምን አይነት አስከፊ እጣ እንደዝጠማቸው ታስረዳዋለች የሚስቁ ወይም የሚተነኩሱ ሰዎች ካሉ ወዲያውኑ ታባርራቸውና አፍ መካፈት ትጀምራለች ከፊሉ ይስቃል ሌላው ጭንቅላቱን ይነቀንቃል ሁሉም ደግሞ እብሷን ሴት በፍርሀት ከተዋጡ ሕፃናት ጋር ማየቱ ያስገርመዋል ሌቤዚያትኒኮቭ የጠቀሰው የብረት መጥበሻ የለም ቢያንስ ራስኮልኒኮቭ አላየውም ሚስስ ማርሜላዶቭ መጥበሻውን ከመደብደብ ይልቅ ልጆቿ እንዲዘፍኑና እንዲጨፍሩ ለማድረግ ስትፈልግ እጆቿን ታጨበጭባለች እርሷ ራሷ መዝፈን ትጀምራለች ወዲያው መዝፈን ከመጀመሯ የሳል በሽታዋ ይቀሰቀስና ያደናቅፋታል ታማርርና እንባዋን ታጎርፈዋለች ከሁሉም በላይ ያበሳጫት የኮልያና የሊዳ ማልቀስና መሸበር ነው በእርግጥም ሕፃናቱን እንደ ጎዳና ዘፋኞች ለማልበስ ከፍተኛ ጥረት አድርጋለች። ሶንያ ሚስስ ማርሜላዶቭሸ ወደቤት እንድትመለስ እየተማፀነችና እያለቀሰች እንደጥላ ትከተላታለች ሚስስ ማርሜላዶቭ ግን በጄ አላለችም ትንፋጂ ቁርጥ ቁርጥ እያለና እያሳለች እንዲህ ስትል በመጮህ ተናገረች ሶንያ እረፊ። አለች በእርግጥም አንድ ፖሊስ በተኮለኮለው ሕዝብ መሀል እየተጋፋ ይመጣ ነበር በሌላ በኩል ግን የመንግስት ሠራተኛ ልብስ የለበሰ ማእረግ ያለው ኮስታራ ሰው በሚስስ ማርሜላዶቭም ሆነ በፖሊሱ አይን ውስጥ ገብቶአል ጠጋ ብሎ ሶስት ሩብል ለሚስስ ማርሜላዶቭ ሰጣት በፊቱ ላይ ቅን ስሜት ይነበብበታል ሚስስ ማርሜላዶቭ ገንዘቡን ተቀበለችና በጨዋ ደንብ እጅ ነሳችው ኮራ ብላ እንዲህ ስትል ተናገረች በጣም አመሰግናለሁ ጌታው ስቃይ የደረሰባትን ድህና ጨዋ ሴት ለመርዳት የተሰለፉ የተከበሩ ደጋግ ሰዎች አሉ ጌታው የሚያዩአቸው ከደህና ቤተሰብ የተፈሩ የሙት ልጆች ናቸው ያ ከይሲ ጀኔራል ተቀምጦ ዶሮ እየበላ አትረብቪኝ አለኝ «ክቡርነትዎ ሟቹ ባሌን ስለሚያወቁ ለእነዚህ የሙት ልጆች አንድ ነገር ያድርጉላቸው» ነበር ያልኩት። ሲል ተናገረ ስቪድሪጋሎቭ ወደእነርሱ እየሄደ ሚስተር ራስኮልኒኮቭ ትንሽ ላነጋግርህ እፈልጋለሁ አለው ሌቤዚያትኒኮቭ ዘወር እንዳለላቸው ስቪድሪጋሎቭ ራስኮልኒኮቭን ወደ አንዱ ጥግ ወስዶ ማነጋገር ቀጠለ ይሄን ሁሉ ጣጣ ማለትም ቀብሩንና የመሳሰለውን ለእኔ ተውት የሚያስፈልገው ገንዘብ ብቻ ነው እንደነገርኩህ ደግሞ ሳጠፋው የምችል ገንዘብ አለኝ እነዚህን ሁለት ሕፃናትና ፖልያን በተመለከተ ደግሞ ለእያንዳንዳቸው እድሜአቸው ሲደርስ የሚቀበሉት አንድ ሺህ አምስት መቶ ሩብል ከፍዬ ወደእጓለ ማውታ ስለማስገባቸው ሶንያን ጭራሽ አያሳስባትም ደህና ልጅ ስለሆነች ከዚህ ቀውጢ ሁኔታ አወጣታለሁ አስር ቪህ ሩብሉን በዚህ አይነት እንዳጠፋሁት ለእህትህ መንገር ትችላለህ በአንድ ጊዜ እንዲህ አይነት ደግነት ከዬት አመጣህ።