Detecting...
Please whitelist dirzon to continue.
ፈረሶቹ በልጓም ተይዘዋል ብዙ ሰው ተሽከርካሪውን ከበል አያሌ ፖሊሶች ደግሞ ከፊት ለፊት ቆመዋል አንዱ ፖሊስ ፋኖስ ይዞ ጎንበስ በማለት ተሰናበተ ከክፍሉ ሲወጣም ምርቃት ምስጋናና ጨዋነት የተመላበት ጥያቄ ተዥጎደጎዱለት የዳንያ ውብ እጅ እንኳን ሳይቀር ይጨብጠው ዘንድ ተዘረጋለት ወደዚያ በመሄዱም ሆነ በሰራው ስራ በጣም ተደስቶ ከክፍሉ ወጣ ራዙምፖኪን ዞሲሞቭን እየተከተለ ገ እንወያይበታለን አሁን መተኛት አለባችሁፁ ነገ በተቻለ ፍጥነት ቀደም ብዬ ሪፖርቴን አቀርባለሁ በማለት ቀርቦ ሊነሱ የነበሩትን ጥያቄዎች በአጭሩ ቀጫቸው ሁለቴም ከመንገድ እንደደረሱ የሚዢም ነው። በጣም ታፍራለች ለደቂቃሥ ቢሆን ብቻዋን የማትተዋት መሆኑ እንዲሰማት ከአደረግህ ራሱ በቂ ነው ቤት ውስጥ ልጅዎን በአይኔ በብረቱ ከማየቴም እኔን በጣም እስኪያስገርመኝ ድረስ እርስዎ በቀላሉ የማያገኙትን ሃያ አምስት ሩብል ለቀብር የሚውል በሚል ሰበብ ለአንዲት ወጣት ጋጠወጥ ሲሰጥ መመልከቴ ቀደም ሲል የተጠቀሰውን እውነት የሚያረጋግጥ ነው። በመጨረሻም ለሴት ልጅዎ ያለኝን ልዩ ከበሬታ ለመግለፅና ታማኝነቴን ለማረጋገጥ ይፈቀድልኝ ሽ ር ታዛዥዎ ፒ ሌዚን ሜስተር ራዙምኪን አሁን ምን ማድረግ ነው ያለብኝ። ወሬውን እንደሰማ ሆን ብሎ እንደሚመጣ ርግጠኛ ነኝከዚያ በኋላ ምን ይውጠናል። ትናንት አእምሮው ትክክል አይመስለኝም ምንም እንኳን ጥሩ ቢሆንም ከምግብ ቤት ያደረገውን ብትሰሙ የሚገርም ነው።ስትል የራስኮልኒኮቭ እናት ከመቅፅበት ተናገረች ይሄን ያለችው በጥድፊያ ባርኔጣዋንና ካባዋን እያደረገች ነበር ዳንያም እንዲህ የዳንያ የእጅ ጓንቲዎች መናኛ መሆናቸውን ብቻ ሳይሆን መበሳሳታቸውን ራዙምኪን አስተዋለ እንዲያም ሆኖ ግን የልብሶቻቸው አልባሌነት መናኛ ልብሶችን እንዴት መልበስ እንደሚገባ በሚያውቁ ሴቶች ዘንድ እንደሚያጋጥመው ሁሉ ለእናትና ለልጅ ልዩ ክብር አጎናጽፎአቸዋል ራዙምኪን ዳንያን በአድናቆት ተመለከታት ሊሸኛት በመነሳቱም ኩራት ተሰማው በየመንገዱ የምትታየው ንግስት በኦፊሴሊያዊ የመንግስት ግብዣ ላይ ከምትገኘው ንግስት በውበት ትበልጣለች ብሎ አሰበ ከራሴ ልጅ ከውዱ ሮዲ ጋር ስገናኝ እንደዚህ ፍርሀት ይውጠኛል ብዬ አስቤም አላውቅ በጣም ነው የደነገጥኩት ሚስተር ራዙምኪን። ማመንማ አምናለሁ ሌሊቱን ሙሉ ግን እንቅልፍ በአይኔ ሳይዞር ነው ያደርኩት። ይቅርታ አድርግልኝ እኔማ የምታውቃት መስሎኝ ነበር አሁንማ የምናገረውንና የምሰራውን አላውቅም እንድትጠብቀን ከአምላክ እንደተላክህ አድርጌ ስለምቆጥርህ ሁሉንም ነገር የምቷውቅ ይመስለኛል እንደዘመዳችን ስለማይህ ይሄን በማለቴ ቅር አይበልህ ቀኝ እጅህን ምን ሆነህ ነው። ጉዳት አድርሰህበት ነው። አየህ እኔ ሳልሆን በድኔ ነው የሚሂደው።
ስትል ሚስስ ማርሜሳዶቭ ተስፋ በቆረጠ ስሜት ጮኸችና ወደባሏ ተጠጋች በቀላሉ ህሊናዋን የምትስት ሴት አለመሆኗን ለማወቅ ራስኮልኒኮቭ ጊዜ አልወሰደበትም። ሚስስ ማርሜሳዶቭ ፈጥና ወደመስኮቱ አመራች የልጆቿንና የባሏን ልብሶች ለማጠቢያ የሚውል ውህ የሚቀመጥበት ትልቅ ጋን ከጥግ በኩል ተቀምጦአል የምሽቱን አጠባ ቢያንስ በሳምንት ሁለት ጊዜ የምትከውነው ራሷ ሚስስ ማርሜላዶቭ ነች እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል የሚቀይረው ጨርቅ የሚያጣበት ደረጃ ሳይ ይደርሳል ያለውም የውስጥ ልብስ አንድ ብቻ ነው ሚስስ ማርሜላዶቭ የቆሸሸ ነገር ማየት ስለማትወድ ሁሉም ሲተኛ አጠባዋን ትከውንና ገመድ ላይ አስጥታ ለጥዋት እንዲደርቅ ታደርጋለች ለራስኮልኒኮቭ ለማድረስ ጋኑን አነሳች ክብደቱ አመዝኖባት ቢያንገዳግዳትም ራስኮልኒኮቭ ፎጣ ለማግኘት በቃ ፎጣውን አርጥቦ በማርሜላዶቭ ፊት ላይ የተጋገረውን ደም መክላት ጀመረ ሚስስ ማርሜላዶቭ ጡቶቿን በእጂ ይዛ በስቃይ እየተነፈሰች ከአጠገቡ ቆማ ነበር እርሷ ራሷ ርዳታ ፈላጊ ሆነች የተገጨው ሰው ወደቤቱ እንዲደርስ ማድረጉ ስህተት እንደሆነ ራስኮልኒኮቭ እየተገነዘበ ሄደ ፖሊሱም ቢሆን ግራ ተጋባ ሚስስ ማርሜላዶቭ ወደፖልያ እየተመለከተች በፍጥነት ሂጂ ወደሶንያ። ስትል ሚስስ ማርሜላዶቭ በንዴት ጮኸችበት። አለች ራስኮልኒኮቭ ወደ ሚስስ ማርሜላዶቭ ተጠግቶ እንዲህ አለ ሟቹ ባለቤትሽ ኑሮውን አስመልክቶ ሁሉንም ነገር ባለፈው ሳምንት አጫውቶኛል ስለአንቺ የተናገረው በአድናቆትና በአክብሮት ነበር ምንም እንኳን የራሱ ድክመት ቢኖርበትም ለእናንተ ሁሉ የቱን ያህል ታማኝ በተለይ ሚስቱን የቱን ያሀል አክባሪ መሆኑን ከተረዳሁበት ያ ምሽት አንስቶ ጓደኛሞች ሆንን ሟቹ ጓደኛዬን ለመጨረሻ ጊዜ ስሰናበተው አንድ ነገር እንዳደርግ ፍቀዱልኝ ሀያ ሩብል ይኸው ይህ ገንዘብ የሚጠቅማችሁ ከሆነ ደስታውን አልችለውም ተመልሼ እመጣለሁ ምናልባትም ነገ ይሆናል የምመጣው ደህና ሁኑ። ሲል ጨመረበትና ይህ የተማሪ ትችቱ ጦሽ አድርጎ አሳቀው ግሩም የሚያሰኝ ሞራል ነበረው ራዙምኪንን በቀላሉ አገኘው አዲሱ ተከራይ ስለታወቀ ዘበኛው ወዲያውኑ ቤቱን አመላከተው ገና ደረጃውን እንዳጋመሰ የተሰባሰቡትን ሰዎች ጩኸትና ሞቅ ያለ ውይይት ሰማ የፊት ለፊቱ በር በስፋት ተከፍቷል ጩኸትና ክርክር ይደመጣል የራዙምኪን ክፍል ሰፋ ያለ ነው የተሰባሰቡትም ሰዎች ወደአስራ አምስት ይጠጋሉ ራስኮልኒኮቭ ከደጃፉ ላይ ቆም ብሎ ተመለከለተ በአቅራቢያው ካለው መጋረጃ በስተጀርባ ሁለት ትላልቅ የሻይ ማፍያ ጀበናዎች ጠርሙሶች ሰሀኖችና ከቤት አከራዩዋ ወጥቤት የመጡ ቀላል ምግቦች የሁለት ሴት ሰራተኞችን እጆች ፋታ ነስተዋል ራስኮልኒኮቭ ገና እንዳስጠራው ራዙምኪን ሸግ ብሎት ወጣ ራዙምኪን ራሱን እስኪስት ሰክሮ ባያውቅም ገና ሲያዩት ብዙ እንደጠጣ ግልፅ ነበር በአሁኑ ሰአት ከመጠኑ ማለፉ በገህድ ይታያል ስማውርርዱን ማሸነፍህን ልነግርህ ነው የመጣሁት እንደእውነቱ ከሆነ ነገ ምን እንደሚያጋጥምህ በርግጠኝነት መናገር አትችልም ወደ ውስጥ አልገባም በጣም ከመዳከሜ የተነሳ በእግሬ የቆምኩት በመከራ ነው በል ደህና ሁን። ስትል ጠየቀች እናትየዋ ፈጥና ወደ ዳንያ በመጠጋት አንቺም ቢሆን በቀላሉ ነው የምትገነፍይው አሁን መናገር አያስፈልግም እያየሽው አይደለም እንዴ እንዲያውም ብንሄድ የተቫለ ነው አለች ሞቅታ ያልተለየው ራዙምኪን ስለታመመ ነው እንዲህ የሚናገረው ባያመው ኖሮ እንዲህ አይልም ነበር በነገው እለት ይሄን ሁሉ እንደሚረሳው እርግጠኛ ነኝ በርግጥ ዛሬ አባርሮታል ትክክል ነው ያደረገው ሰወየው ለመበሳጨት በቃ በመማሩ እየተኮፈሰ ነበር የተናገረው ሀፍረቱን ተከናንቦ ተመልሷል እውነት ነዋ። እያለ ራዙምኪን ጮኸበት ራስኮልኒኮቭ ግን መልስ አልሰጠም ምናልባትም መልስ ለመስጠት አቅመ አልነበረውም ራስኮልኒኮቭ ጭራሽ ስለተዳከመ ፊቱን ወደግድግዳው አዙሮ ፎቴው ላይ ተኛ ዳንያ ራዙምኪንን በስሜት ተመለከተችው ጥቁሮቹ አይኖቿ አበሩ መልኳን አይቶ ራዙምኪን ቀልቡ አረፈባት የራስኮልኒኮቭ እናት በሁኔታው ተገርማ ክው ብላ ቀረች። ናስታስያ ከፍ ብላ ከደረጃው ላይ ፋኖስ ይዛላቸው ቤት ከአከራየችው ባልቴት ደጃፍ ላይ ቆመው ነበር የሚያወሩት ራዙምኪን በጣም ሞቅ ብሎታል ከግማሽ ሰአት በፊት ራስኮልኒኮቭን ወደቤቱ ሲሸኘው ያለማቋረጥ መለፍለፉ ይታወቀው ነበር በዚያን ምሽት የጠጣው የአልኮል መጠን ብዙ ቢሆንም ራሱን ተቆጣጥሮ የሚሰራውን ሁሉ ያውቅ ነበር አሁን ግን ጫን ብሎታል የጠጣው ሁሉ አረቄ በአንድ ጊዜ አናቱ ላይ ወጥቶ ስራውን የጀመረ ይመስላል ሁለቱንም ሴቶች ለማሳመን የሚቻለውን ሀሉ እያደረገ ምክንያቶቹን በሚያስገርም ግልፅነት እየደረደረ በእጃቸው ውስጥ ካቴና የገባ ይመስል እስኪያማቸው ድረስ ግጥም አድርጎ እየያዘና ያለኦንዳች ሀፍረት ዳንያን በአይኖቹ እየጎበኘ ከአጠገባቸው ቆሟል አንዳንድ ጊዜ ሕመሙን መቋቋም አቅቷቸው እጆቻቸውን ከጠፍር እጆቹ ለማላቀቅ ቢሞክሩም እርሱ ግንየሚያደርገውንየሚያውቅ አይመስልም ይባስ ብሎ ወደራሱ ያስጠጋቸዋል ከደረጃው ላይ ተፈጥፈጥ ቢሉት ሳያስብና ሳያወላውል ወዲያውኑ ይፈዕም ነበር የልጂ ሁኔታ ክፉኛ ያሳሰባት እናት ከአጠገቧ ያለው ወጣት ከስርዓቱ የወጣ መሆኑና እጆቿም አላግባብ መጠፍነጋቸው ቢሰማትም እነርሱን ለመርዳት መቆሙን ተገንዝባ ሁሉንም በትዕግሥት ተቋቋመች የወንድሟ ሁኔታ የዚያኑ ያህል ያሳሰባትና በተፈጥሮዋ ፈሪ ያልሆነችው ዳንያም የወንድሟ ጓደኛ እርሷን አፍጥጦ ማየቱ ከማስገረምም አልፎ አስደንግጧታል ናስታስያ ስለዚህ የሚገርም ሰው ያደረገችው ገለፃ ያሳደረባት ወደር የለሽ አመኔታ መንጭቃው ከመሮጥም ሆነ እናቷም እንድትከተላት ከማድረግ እንድትቆጠብ አስቻላት በተጨማሪም በአሁኑ ሰአት ከመሸ ወዲህ ለማምለጥ መሞከሩ እንደማያዋጣትም ተሰምቷታል ከአስር ደቂቃ በኋላ ግን እየተረጋጋች ሄደች ራዙምኪን ወዲያውኑ እስኪዝዘቡለት ድረስ እውነተኛ ባህሪው ጎልቶ ወጣ ወደ ቤት አከራይዋ መሄዱ አያዋጣም። በማለት ራዙምኪን በስሜት ተፈነቀለ በሉ እንሂድ ናስታሲይወደ እርሱ ተመልሰሽ ፋኖስ ይዘሸ ተቀመጪ እኔ ከሩብ ሰአት በኋላ እመለሳለሁ የራስኮልኒኮሸቭ እናት ሙሉ በሙሉ ባታምንበትም እምቢተኛ አልሆነችም ራዙምኪን እጆቻቸውን ይዞ ደረጃውን ወረዱ ያም ሆኖ ግን የእርሱ ሁኔታ ይሄን ያህል አላስደሰታትም ነበር ብቁና ጥሩ ባህሪ ያለው ወጣት ሊሆን ይችላል አሁን በሚገኝበት ሁኔታ ግን ቃሉን ለመጠበቅ ይችላል ወይ። ስትል የራስኮልኒኮቭ እናት በመደናገጥ ጮኸች ዳንያ የመደናገጥ ፊት ቢታይባትም ተነስ አባክህ። ካለች በኋላ በነገው እለት ስለጉዳዩ በተሻለ ሁኔታ እንደሚያስብበት እርግጠኛ ነኝ ብላ ደመደመች ስለዚያ ጉዳይ በነገው እለት ያንኑ እንደሚል እርግጠኛ ነኝ በማለት ዳንያ እቅጩን ተናገረች የራስኮልኒኮቭ እናት በአሁኑ ሰአት ልትነጋገርበት ያስፈራት ነጥብ በመሆኑ ውይይቱ በዚሁ አበቃ ዳንያ ጠጋ ብላ እናቷን ሳመቻት አናቷም ምንም ሳትተነፍስ አቀፈቻት ከዚያን በኋላ ቁጭ ብላ ልጄን ፍርሀት በተቀላቀለበት ስሜት እየተመለከተች የራዙምኪንን መመለስ በጉጉት ትጠባበቅ ገባች ዳንያ የራዙምኪንን መምጣት እየተጠባበቀች እጆቿን አጣጥፋና በሀሳብ ተውጣ በክፍሉ ውስጥ ትንጎራደዳለች ዳንያ አንድ ነገር ስታስብ በክፍል ውስጥ መንጎራደድ ስለሚቀናት በእንዲህ አይነት ጊዜ ከማሰብ እንዳታሰናክላት እናቷ ትጠነቀቃለች ራዙምኪን ሰክሮ ለዳንያ ያሳየው ጥልቅ ስሜት የማይገባ ነው በዚያን ሰአት ዳንያ እጆቿን አጣጥፋ ተክዛና በሀሳብ ተመስጣ በክፍሉ ውስጥ ሳይና ታች ስትል የሚመለከቷት ሰዎች ቢኖሩ ግን ለራዙምኪን ባዘኑ ነበር ዳንያ ረጅም ቅርጺ ያማረ ጠንካራና በራሷ የምትተማመን ውብ ሴት ነች በራስ መተማመኗ ከገፅታዋ ቢነበብም የአረማመጳን ማራኪነት ጭራሽ አያሳንሰውም ውብ ተብላ ከመጠራቷ በስተቀር የፊቷ ገፅታ ከወንድሟ ጋር ይመሳሰላል ከወንድሟ ትንሽ ፈካ ያለ ቡናማ ፀጉር አላት የኮሩ የሚያበሩና ብዙውን ጊዜ ደግነትን የተላበሱ ጥቋቁር አይኖች ባለቤት ነች የገረጣች ሳትሆን መጠጥ ያለች ነች። የራስኮልኒኮቭ ቤት አከራይ የሆነችው ቀውስ ባልቴት በዳንያ ብቻ ሳይሆን በራሷ በራስኮልኒኮቭ እናት ጭምር ልትቀና እንደምትችል በመግለፅ ከደረጃው ላይ ሆኖ መናገሩ ሆድ ያባውን ብቅል ያወጣዋል ቢሆንም የማይታበል ሐቅ ነው የራስኮልኒኮቭ እናት እድሜዋ አርባ ሶስት ቢሆንም ወርቁ ቢጠፋ ሚዛኑ መች ጠፋ እንዲሉ ፊቷ የቀድሞ ውበቷን ርዝራዥ አሁንም እንደያዘ ነው ከዚህም በተጨማሪ ያያት ሁሉ የሚገምታት ከእድሜዋ በታች ነው ይህ ደግሞ የአእምሮ ሰላም አዲስ አስተሳሰብ ንፀህና ቅን ልብ ይዘው እስከመጨረሻው ከሚጓዙ ሴቶች ላይ ምንጊዜም የማይነጥፍ ነው በስተርጅናም ቢሆን አንድ ሴት ውበቷን መጠበቅ የምትችለው እነዚህን ሁሉ ባህርያት ስታሟላ መሆኑን በተጨማሪ ኋጡ ጠኋኋ ኋጮብጠ ማብራሪያ መልክ መግለፅ እንችሳለን ፀጉሯ መሸበትና ብን ማለት ጀምሯል በአይኖቿ ዙሪያ ያለው ቆዳ ተጨማቋል ከችግርና ከሀዘን የተነሳ ጉንጪ ምጥጥ ብሎ ተሸብሸሽባል እንዲያ ሆኖ ግን ፊቷ ወብ ነው ለዳንያ የበላይነት ስሜት ያጎናፀፋት ጣል ያለው የታችኛው ከንፈር ከአለመኖሩ በስተቀር ከሀያ አመት በኋላ የሚኖረውን የዳንያ ፊት የሚመሰል ነው የራስኮልኒኮቭ እናት በብዛትም ባይሆን ስሜቷን የምትጠብቅ አይን አፋርና ሌሎች የሚሉትን የምችሰማ ነች ከእምነቷ ውጭ የምትስማማባቸው ነገሮች ቢኖሩም በአለም ላይ ምንም ሀይል የማይገፋቸው ታማኝነት ስነምግባርና የአላማ ፅናት አሏት ራዙምኪን በሄደ ልክ በሀያ ደቂቃ በሩ በትንሹም ቢሆን በፍጥነት ለሁለት ጊዜ ተንክከኳ ራዙምኪን ተመልሶ መጣ በሩ እንደተከፈተ በጣም ስለምቸኩል አልገባም። አለች ጥሩ ሰው ይመስሳል በማለት ዳንያ ከመለሰች በኋላ በድጋሚ መንጎራደድ ጀመረቹ ከአንድ ሰአት በኋላ ከደጃፉ የሚመጣ የኮቴ ድምፅ ተሰማና በሩ ተንኳካ ሁለቱም ሴቶች ራዙምኪን ቃሉን እንደሚጠብቅ ርግጠኛ ሆነው ይጠባበቁ ነበር እንዳለውም ዞሲሞቭን ይዞ መጣ ዞሲሞቭ ግብዣውን አቋርጦ ራስኮልኒኮቭን ለማየት ምንም አላመነታም ነበር ራዙምኪን ሰክሮ ስለሴቶቹ ያቀረበለትን ገለፃ በመጠራጠሩ ግን ያለፍላጎት ነበር ወደሴቶቹ የሄደው እንደአምላክ ቆጥረውት ይጠባበቁት እንደነበር ሲገነዘብ ደግሞ ተረጋጋ በቆየባቸው የአስር ደቂቃ ጊዜ ውስጥ የራስኮልኒኮቭ እናት እንዳትረበሽ ለማድረግ በቃ ከአላማው ሳያፈነግጥና ከሁለቱ ሴቶች ጋር የግል ግንኙነት ለመመስረት ፍላጎት እንዳለው ሳያሳይ ከሀያ ሰባት አመት ሐኪም በሚጠበቅ ሁኔታ ተጨንቆና ተጠቦ ተናሀዝረ ገና ከመግባቱ ዳንያ እጅግ ውብ መሆኗን ስላስተዋለ ወዲያውኑ እርሷን ላለማየት በመሞከር ሁኔታውን ለእናቷ አስረዳ ይህን በማድረጉም ውስጣዊ ርካታ ተሰማው ሕመምተኛውን በሚመለከት የሚገኝበት ሁኔታ ፈፅሞ አስተማማኝ ነው ብሎ ገመተ ሕመሙ የተቀሰቀሰው ባለፉት ጥቂት ወራት ውስጥ ባጋጠመው ችግር የተነሳ ሳይሆን ከአእምሮ ጋር በተያያዘ ምክንያት እንደሆነ ተናገረ የማቴሪያልና የሞራል ተፅእኖዎች ጭንቀቶች ስጋቶች አስተሳሰቦችና የመሳሰሉት ድምር ውጤት እንደሆነ አስረዳ ይህ አባባሉ በተለይ የዳንያን ቀልብ እንደሳበ በመረዳቱ ዘርዘር አደረገው ከአእምሮ ቀውስ ጋር የተያያዘ እንደሆን በመስጋት እናትየዋ ላቀረበችው ጥያቄ ፈገገ እያለ በሰጠው መልስ አባባሉ እንዲህ ለማለት እንዳልሆነና እነደተጋነነ ገለፀ። የራስኮልኒኮቭ እህት ውብ ነች እያለ ዞሲሞቭ በመቋመጥ ተናገረ ውብ። አለው ቅር በመሰኝት እኔ ቂል አይደለሁም ለእንዲህ አይነት አልባሌ ነገር ቦታ አልሰጠውም ሳይነጋገሩ ገዞኮአቸውን ቀጠሉ ከራስኮልኒኮቭ ቤት አጠገብ በደረሱ ጊዜ ብቻ ተክዞ የነበረው ራዙምኪን ዝምታን አሸንፎ መናገር ጀመረ ጥሩ ሰው ነህ ከሌሎች ድክመቶችህ በተጨማሪ ግን ርካሽ ነህ የለየልህ ርካሽ ደካማ ቄጡ መናኛ ሰው ነህ በወረት የታጀልክ ነህ ስለወፈርክና ስጋ ስለተሸከምክ እፖቢ የምትለው ነገር የለህም ጥንቡን ሁሉ ታጋብሳለህ እስከዚህ ደረጃ በመድረስህ መልካምና ራሱን ለመሰዋት የተዘጋጀ ሐኪም እንዴት ልትሆን እንደምትችል ግራ ገብቶኛል ከዶሮ ላባ በተሰራ ፍራሽ ላይ ተኝተህ ሌሊት ሕመምተኛ ለማከም ትነሳለህ። ሚስስ ዛርኒሲንን ስላደረገችልኝ መስተንግዶ አመስግንልኝ ክፍሏን ቆልፋ ነበር ለማለዳ ሰሳምታዬ መልስ አልሰጠችም እንዲያም ሆኖ ግን ከጥዋቱ በአንድ ሰአት ተነስታ ምድጃውን ከወጥቤት ወደክፍሏ ወስዳለች ልሰናበታት አልቻልኩም ራዙምኪን ልክ ከጥዋቱ በሶስት ሰአት በጉጉት ይጠብቁት የነበሩትን ሁለት ሴቶች አገኘ እነርሱ በአንድ ሰአት ወይም ከዚያ ቀደም ብለው ነቅተው ነበር እንደ ድቅድቅ ጨለማ ጠቁሮ የማይሆን አይነት ሰላምታ ሰጣቸው ይህን በማድረጉም ወዲያውኑ ተበሳጨ እርሱ ግን ጥሩ አቀባበል አልጠበቀም ነበር የራስኮልኒኮቭ እናት ፈጥና ከአጠገቡ ደርሳ እጆቹን ያዘች ልትስማቸውም ምንም ያሀል አልቀራት ሲፈራ ሲቸር ዳንያን ተመለከታት ያ የተከፋ ፊት እንኳን የትካዜና የቅሬታ ሳይሆን የምስጋናና የወዳጅነት እርሱ ያልጠበቀው የከበሬታ ስሜት ስለተላበሰ ግራ ተጋባ እንዳገኙት ቢወቅሱት ኖሮ በቀለለው ነበር እንደ አጋጣሚ ሆኖ የመነጋገሪያ ርእስ በመኖሩ በእድሉ ለመጠቀም ተጣደፈ። የራስኮልኒኮቭ እናት በመጀመሪያ ከራዙምኪን ጋር ለመነጋገር ጓግታ ስለነበር ከእንቅልፉ ባይነቃም ሁሉም ነገር ደህና መሆኑ እንደተነገራት ቸር ወሬ በመስማቷ ደስታዋን ገለፀች ቁርስ ሳይበሉ ስለጠበቁት አብሯቸው ሻይ እንዲጠጣ ጠየቁት የራስኮልኒኮቭ እናት መጥሪያውን እንደደወለች የተቀደደ ኮት የለበሰ ብሽቅጥ ያለ አስተናጋጅ መጣ ሻይ እንዲያመጣላቸውም ጠየቁት ሻይው እንደመጣ ሁሉም ነገር የከረፋና አስተናጋጁም ጋጠወጥ በመሆኑ ሁለቱ ሴቶች በሀፍረት ተዋጡራዙምኪን ስለፔንሲዮኑ ለመናገር ዳዳውና የለዚንን ጉዳይ ሲያስታውስ ግራ ተጋብቶ ከመናገር ተቆጠበ የራስኮልኒኮቭ እናት ማለቂያ በሌላቸው ጥያቄዎች ስሳጣደፈችውም ተደሰተ ጥያቄዎቻቸውን ባለማቋረጥ እየመለሰ ለአርባ አምስት ደቂቃ ያህል ተናገረ ባለፈው አመት ራስኮልኒኮቭ ካሳለፈው ሕይወት ጋር አያይዞ ሕመሙን በመግለዕ አበይት የሆኑ ማስረጃዎችን ገለፀላቸው በፖሊስ ጣቢያ የነበረውን ሁኔታ ጨምሮ ሊነሱ የማይገባቸውን ብዙ ነገሮች ዘለላቸው ያሳቸውን ሁሉ በጥሞና አዳመጡት ይሁንና ሁሉንም ነገር አጫውቷቸው የተረጋጉ እንደሆኑ አድርጎ በመቁጠሩ መሳሳቱን ተገነዘበ በእነርሱ ዘንድ ገና ወሬውን እንደተጀመረ አድርገው ነበርና የቆጠሩት እባክህ ምን ይመስልሀል ሚስተርይቅርታ እስካሁን ድረስ ስምህን አላውቀውም አለች የራስኮልኒኮቭ እናት በመጣደፍ ራዙምኪን እባላለሁ እየህ ሚስተር ራዙምኪን ነገሮችን እንዴት እንደሚያይ ለማወቅ በጣም እፈልጋለሁ እንዴት እንደምገልፀው እንጃየሚወዳቸውና የሚጠሳቸው ነገሮች ምንድናቸው። አየሽ ዳንያብሁሉም ነገር ከወንድምሽ ጋር በጣም ትመሳሰያለሽ በማለት ራዙምኪን በስጨት ብሎ ከተናገረ በኋላ ከደቂቃ በፊት ስለወንድሟ የነገራትን አስታውሶ ሀፍረት ተሰማው ግራ በመጋባቱም ዳንያ ሳቀች የራስኮልኒኮቭ እናት ጣልቃ ገባችና እንዲህ ስትል በመቀየም ተናገረች ሮዲን በሚመለከት ሀለታችሁም ተሳስታችኋል ለማለት እደፍራለሁ አሁን ስለተፈጠረው አይደለም የማወራው ሚስተር ሉዚን በደብዳቤው ላይ የገለፀውና አንተና እኔም የምናስበው ትክክል ላይሆን ይችላል ጠባዩን በድንገት መለወጡ ሳይሆን ምክንያተ ቢስ መሆኑ ነው የሚገርመው ገና የአስራ አምስት አመት ልጅ እያለ ያሳይ የነበረው ጠባይ ተለዋዋጭ ነበር ማንም ለማድረግ ጭራሽ ያላሰበውን ነገር ሳይታሰብ በድንገት ያደርግ እንደነበረ ይታወሰኛል በቅርቡ እንኳን ያጋጠመውን እስቲ እናስተውል። እግዚአብሔር ብቻ ይቅር ይበለኝ እርሷ እርሱን ትጉዳው ወይም እርሱ እርሷን ይጉዳት ባላውቅም መሞቷን እንደሰማሁ ተደስቼ ነበር አለች የራስኮልኒኮቭ እናት ከዚያን በኋላ በየመሀሉ እያቋረጠችና በወሬው ቅር የተሰኘችውን ልጂን ያለማቋረጥ እየተመለከተች በትናንትናው እለት በሮዲና በሚስተር ሉዚን መካከል ስለነበረው ሁኔታ በጥንቃቄ መጠየቅ ጀመረች ሁኔታው ከምንም ነገር ይበልጥ ስለከነከናት ለማወቅ እንደጓጓች ግልፅ ነበር ራዙምኪን ሁሉንም ነገር በዝርዝር ተናገረ የራሱንም መደምደሚያ ጭምር ራስኮልኒኮቭ ሚስተር ሉዚንን ሆን ብሎ በመሳደቡ በግልዕ እንደወቀሰው ይሃን ማድረጉም ከሕመሙ ጋር በተያያዘ አይደለም ብሎ እንደሚገምት ገለፀ ከመታመሙ በፊት ያሰበበት ይመስለኛል አለ እኔም እንደዚያው እገምታለሁ አለች የራስኮልኒኮቭ እናት በመከፋት። የሮዲን ጠባይ ከማንም ይበልጥ የምታውቀው አንተ ነህ ከማንም ይበልጥ ደግሞ ምክር ልትለግሰን እንደምትችል እርግጠኛ ነኝ ዳንያ ወዲያውኑ ወስና የራሷን አቋም ብትወስድም ስለሁኔታው ልነግርህ ተገደድኩ መጥተህ ሀሳብህን እንድትሰጠን እየተጠባባቅሁ ነበር ቄ ሥሥሙጮ ጻጸ ና በኽ ራዙምኪን በትናንትናው ምሽት የተፃፈውን ማስታወሻ ከፍቶ እንደሚከተለው አነበበው ውድ ማዳም በጣም አንገብጋቢ በሆኑ የቢዝነስ ቀጠሮዎች የተነሳ ከባቡር ጣቢያ መጥቼ ልቀበልዎት አለመቻሌንና የሚረዳ ቀልጣፋ ሰው የላኩልዎት መሆኑን እገልፅልዎታለሁ በከፍተኛው ፍርድ ቤት ባጋጠመኝ አጣዳፊ የቢዝነስ ስራና እርስዎና ዳንያ ከሮዲ ጋር የሚደረገውን ውይይት ላለማደናቀፍ ስል በነገው ጥዋት ቀጠሮ ላይ አለመገኘቴን ስገልፅልዎ እያዘንኩ ነው ይሁንና ከነገ ምሽት ሳይዘገይ ልክ ከምሽቱ ሁለት ሰአት ሳይ ወደአረፉበት ክፍል መጥቼ እንደምጠይቅዎት ተስፋ አደርጋለሁ ቀደም ሲል የተጠቀሰው ወንድ ልጅዎ ሮድዮን ሮማኖቪች ራስኮልኒኮቭ ትናንት አሞት በነበረ ጊዜ ሳነጋግረው ብልግና በተሞላበት ሁኔታ ስለሰደበኝ እኔ በምጠይቅዎ ጊዜ እንዳይገኝ አሳስባለሁ የተወሰነ ነጥብን በሚመለከት አፋጣኝና ዝርዝር ማብራሪያ እንዲሰጡኝ እጠይቃለሁ ያላሰብኩት ሳይሆን ቀርቶ እርሱን የማገኝ ከሆነ ወዲያውኑ ተመልሼ እሄዳለሁ የሚወቀሱትም እርስዎ ብቻ ነዎት። እያለች የራስኮልኒኮቭ እናት እንባ እየተናነቃት በመከፋት ተናገረች ዳንያ የምትልዎትን ያድርጉ በማለት ራዙምኪን ረጋ ብሎ መለሰ ወይ ጉድ እርስዋማ የምትለውን ብላለች ምክንያቷንም አትነግረኝ ሮዲ በሁለት ሰአት ወደዚህ እንዲመጣ ቢነገረውና ቢገናኙ ይመረጣል እንዲያውም በጣም ያስፈልጋል ትላለች እኔ ደብዳቤውን ላሳየው እንኳን አልፈልግም በጣም ብስጩ ስለሆነ እርሱ የማይኖርበትን ዘዴ ለመፍጠር እንድትረዳኝ የጠየቅሁህ መሆኔን ተስፋ አደርጋለሁ ከዚህም በተጨማሪ ስለሞተው ሰካራም ስለሴት ልጁና እንዴት ገንዘቡን ሁሉ እንደሰጣት የማውቀው ነገር የለም። አዎ ጉዳት አድርሼበት ነውሲል ራዙምኪን በፈገግታ መለሰ አንዳንድ ጊዜ በጣም ግልፅ ሆይ ስለምናገር ዳንያ ትወቅሰኛለች ይገርማል ለመሆኑ ልጄ በእንዴት አይነት ጠባብ ክፍል ነው የሚኖረው።