Detecting...

Please whitelist dirzon to continue.

or subscribe for ad-free contenct.

dirzon
  • Convert to Pdf
  • Reading List
  • Summary
  • Audiobook
  • Search
  • Upload
  • myzon
  • Log in
  • Register
English  አማርኛ  Français  العربية
Book of the day

ወንጀልና ቅጣት 4.pdf


  • word cloud

ወንጀልና ቅጣት 4.pdf
  • Extraction Summary

ሲል ራዙምኪን ጠየቀ ሚስተር ሉዚን ቢቀየምም ቅሉ ክብሩን እንደጠበቀ በእንዲህ አይነት የግልቢያ አነጋገር መሰረት እኔም ጭምር እንዲያነኝ ማለትህ ነው። ወኔ የሚባል ነገር የለህም። የምትሞክሩት ሁሉ ከሰው የተለየ ለመሆን ነው። ምን ታውቃለሀ። ይሄ አባባልህ አፍንጫህን ያስመታሀል ራስኮልኒኮቭ ራዙምኪንአልመጣም። ራስኮልኒኮቭ መንገዱን ይዞ ከተጓዘ በኋላ ታጠፈ ራዙምኪን በጥሞና በአይኑ ይከተለው ነበር በመጨረሻ ግን ላለመከተል ወስኖ ወደምግብ ቤቴ ገበ ደረጃውን እንዳጋመሰ ግን ቆም አለ የሚያሳዝን ነው ሲል ከሞላ ጎደል በጎላ ድምፅ ተናገረና እንዲህ ሲል ቀጠለ ብቁምነገር ነው የተናገረው እንዲያም ሆኖ ግን ሞኝ ነው የሆንኩት። ዞሲሞቭን ያሰጋው ይህ ነው እንዲሆን የፈለግሁት በዚህ መልኩ ስለሆነ ሁሉ ነገር ያክትም። ምን ልዩነት ግን ያመጣል። የሚያሳዝነው ሁሉም ነገር ፌዝ መሆኑ ነው። ግን መርሳት ነው። አለባበሷ ሁሉ ልክ በፋሽን መፅሔት ላይ ያለውን የተከተለ ነው። በዚያን እለት የተሰማው በጣም የሚሰቀጥጥ አስፈሪ ስሜት በአሁኑ ሰኣት ግልጥልጥ ብሉ ተቀሰቀሰበት ደወሉን ባንቃጨለ ቁጥር ጀርባውን የሙቀት ስሜት ወረረው ምን ፈልዝህ ነው። ዋምን ደም ነው። እስከአሁን ድረስ ክፍት ነው ረዳት ሹሙ ከዚያ ነው። ለትንሽ ጊዜ ከዚያ ነበር ምን ፈልገህ ነው። ዋዛ አይደለም ጮሌ ነው።

  • Cosine Similarity

ይውጣልኝ ስለቀለም ቀቢው ለመስማት እኔም በጉጉት እየተጠባበቅሁ ነው ቀጥል እንግዲህ ስማ ታሪኩ ይኸውልህ እነርሱ ከኮችና ከፔስትርያኮቭ ጋር ጊዜያቸውን ሲያባክኑ በነበረ ጊዜ ማለትም ግድያው በተፈፀመ በሶስተኛው ቀን ጭራሽ ያልተጠበቀ መረጃ ተገኘ ሁለቱ ሴቶች ከተገደለብት ቤት ፊት ለፊት የሚገኝ የመሸታ ቤት ባለቤት የሆነ ዱሸኪን የሚባል አርሶ አደር የወርቅ ጉትቻ ከእነ ማስቀመጫው ይይዝና ወደ ፖሊስ ጣቢያ ሂዶ ረጅም ታሪክ ይዘከዝካል «ከትናንት በስቲያ ሁለት ሰአት ከምሽቱ እንዳለፈ አንድ ቀለም ቀቢ ሰራተኛ ወደመሸታ ቤቴ ይመጣል ቀኑና ሰአቱ ግድያው የተፈፀመበት ነወ ከዚህ በፊትም ይመጣጣ ነበር ስሙ ኒኮላይ ነው ይሄን የወርቅ ጉትቻ ይዢ ሁለት ሩብል እንዳበድረው ጠየቀኝ ከየት አገኘክው ብለው ከመንገድ ወድቆ አለኝ ልክ እርሱ እንዳለኝ ነው የምነግራችሁ በተጨማሪ ሳልጠይቀው አንድ ሩብል ሰጠሁት ከእኔ ጋ ባያስይዘው እንኳን ከሌላ ጋ ማስያዙ አይቀርም ብዬ ተቀበልኩት ሁኔታው ተለውጦ የሆነ ሹክሹክታ ከሰማሁ በኋላ ግን ለፖሊስ አመልክቼ ልሰጥ ወሰንኩ ይህ ውሸት ነው ዱሽኪንን በሚገባ አውቀዋለሁ አራጣ አበዳሪና የሌባ ተቀባይ ስለሆነ ሰላሳ ሩብል የሚያወጣ ነገር ከኒኮላይ ተቀብሎ ለፖሊስ አያስረክብም በፍርሀት ብቻ ያደረገው ነው ብቻ ያለውን አድምጥ «ኒኮላይን ከልጅነቱ ጀምሮ ነው የማውቀው የአንድ አካባቢ ሰዎች ነን። ይሄ እንኳን ተረጋግጣል ኮች ያውቀው ስለነበር የንብረቱ ባለቤት ማን እንደሆነ ገልፆአል በዚያ መሰረት ባለቤቱ በተጠየቀ ጊዜ የጉትቻ ማስቀመጫው የእርሱ እንደሆነ በማያሻማ መልኩ አረጋግጧልበማለት ራዙምኪን ያለውዴታው በቅሬታ መልክ መለሰ ይሄ መጥፎ ነው ሌላ ጥያቄ አለኝ ኮችና ፔስትርያኮቭ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደአሮጊቷ ቤት ሲያቀኑ ኒኮላይን ያየው ሰው ነበር ወይ። ሲል ጠየቀ ። ለሚስተር ሉዚን መልስ ይሰጥ በነበረ ጊዜ ፊቱን በመጠኑ ብቻ ያዞረው ራስኮልኒኮቭ ከደቂቃ በፊት ሰውየውን በሚገባ ለመመልከት ጊዜ ያጠረው ይመስል ወይም ደግሞ በሰውየው ላይ ባየው አዲስ ነገር ስሜቱ የተነካ ይመስል በድንገት ያፈጥበት ጀመር ለአንድ እጮኛ የሚመጥነው የሚስተር ሉዚን አቋም የማንንም ትኩረት የሚስብ ነው በሰርጉ መዳረስ የተነሳ በመዲናው ውስጥ በሚቆይባቸው ጥቂት ቀናት ሽቅርቅር የማለቱ እድል እንዳያልፈው ለመጣደፉ በገሀድ ይታያል ይህ ደግሞ ክፋት የሌለው በጎ ነገር ነው ሚስተር ሉዚን እጮኝነቱን በደስታ የተቀበለው ስለሆነ አለባበሱን በመለወጥ በመጠኑ መኩራራቱ የሚጠበቅ ወግ ነውሱ ልብሶቹ ሁሉ ገና ከልብስ ሰፊ ቤት መውጣታቸው ነው ሀሉም ነገር ሽክ ያለ ነው ሲበዛ አዲስ ከመሆኑና የተለበሰበትን ምክንያት በግልዕ ከማሳወቁ በስተቀር ፋሽን የጠበቀው አዲሱ ባርኔጣው እንኳን ይሄንኑ ያንፀባርቃል ሚስተር ሉዚን በከፍተኛ ከበሬታ የሚመለከተውና በከፍተኛ ጥንቃቄ በእጁ የያዘው ባርኔጣ ሳያጠልቃቸው ለእይታ ብቻ በእጁ የያዛቸውና የወይን ጠጅ ቀለም ያሳቸው ጓንቲዎቹ ሳይቀሩ ይሄንኑ ያረጋግጣሉ ሚስተር ሉዚን የለበሳቸውን ልብሶች በሚመለከት ደማቅ ቀለማት ይበዙባቸዋል ቡናማ ቀለም ያለው በጣም የሚስማማ የበጋ ጃኬት ቀለል ያለ የበጋ ሱሪ ተመሳሳይ የሆነ ሰደርያ ገና ከመደብር የወጣ የላይኖን ሸሚዝ ቀይ ሰረዝ ጣል ያለበት ነጭ ከረባት ሽክ አድርገውታል ብሩህና ሸጋ ፊቱ ከአርባ አምስት አመት ዝቅ ያለ አስመስሉሎታል ጥቁር የሪዝ ቂሙ ከግራና ከቀኝ ልቅም ብሎ እስከአገጩ ወርዶ ቀልብ ይስባል ፀጉሩን የጎነጎነ ሰው የተሞቨረ ጀርመናዊ ቢመስልም በፀጉር አስተካካይ ቤት የተከረከመው ገብስማ ፀጉሩ እንኳን አላሳጣውም በዚህ ሸጋ ቁመና ላይ እንከን ይወጣለታል ቢባል ምክንያቱ የተለየ መሆን አለበት ራስኮልኒኮቭ ሚስተር ለዚንን በንቀት እየተመለከተ የጥላቻ ፈገግታ አሳየ ተመልሶ በጀርባው ተኛና ወደኮርኒሱ አንጋጠጠ ሚስተር ለዚን ግን ስሜቱን ተቆጣጠረ ለጊዜውም ቢሆን እነዚህን ያልተለመዱ ባህሪዎች አይቶ እንዳላየ ለማለፍ ወሰነ ኦንተን በእንዲህ አይነት ሁኔታ በማግኘቴ በጣም አዝናለሁ መታመምህን ባውቅ ኖሮ ቀደም ብዬ አመጣ ነበር ግን የቢዝነስ ጉዳይ ሆነብኝ። ሲል ራስኮልኒኮቭ በደከመ ድምፅ ጠየቀ ከዚህ ብዙ አይርቅም። አለ ራስኮልኒኮቭ ከመቅፅበት ራስኮልኒኮቭ ያለውን በቅጡ ያልተገነዘበው ሚስተር ሉዚን ምን ማለትህ ነው። ሲል ጠየቀ። እንደዚያ አትገምት ያም ሆነ ይህ በዚሁ ይብቃ በማለት በአጭር ቀጨውና ወዲያውኑ አቋርጠውት የነበረውን ውይይት ለመቀጠል ፊቱን ወደዞሲሞቭ መለሰ ሜስተር ሉዚን የራዙምኪንን ማብራሪያ ወዲያውኑ ተቀበለ በተጨማሪም ያንን ቤት ለቅቆ በአንድ ወይም በሁለት ደቂቃ ውስጥ ለመውጣት ወስኖ ነበር ወደራስኮልኒኮቭ እያመለከተም አሁን የተጀመረው ትውውቃችን ከሕመምህ በምትድንበት ጊዜ እንደሚቀጥልና ከምታውቀው ጉዳይ አንፃርም እንደሚጎለብት ተስፋ አደርጋለሁ ጤናህ ተመልሶ ለማየት ምን ያህል እንደጓጓሁ ለመግለፅ ይፈቀድልኝ አለ ራስኮልኒኮቭ ፊቱን እንኳን አሳዞረም ሚስተር ሉዚን ከተቀመጠበት ወንበር መነሳት ጀመረ እነርሱ ግን ደንታ ሳይሰጡት ወዲያውኑ ወደተቋረጠው ንግግራችው ተመለሱ ወደ በራፉ ራመድ አለና ለመሰናበት ቆም አለ ማድያው የተፈፀመው በአሮጊቷ ደንበኛ መሆን አለበትሲል ዞሲሞቭ ረገጥ አድርጎ አሰመረበት ራዙምኪን ጭራሽ አያጠራጥርም በማለት መስማማቱን ከገለፀ በኋላ ፖርፊሪ የራሱን ግምት የወሰደ ቢሆንም በአሁኑ ሰኣት የአሮጊቷን ደንበኞች ቃል እየተቀበለ ነው አለ የደንበኞችን ቃል ነው ወይ የሚቀበለው። ሲል ራስኮልኒኮቭ በጎላ ድምፅ ጠየቀ። ራስኮልኒኮቭ አስራ አምስት ሳንቲም ከኪሱ አውጥቶ ሰጣት ግሩም ሰው ነህ። ብሎ ጠየቀ ሁለት ወይም ሶስት ሰዎች ሻይ ይጠጣሉ ራቅ ካለው ክፍል ደግሞ አራት ሰዎች ሻምፓኝ ይጎነጫሉ ራስኮልኒኮቭ እርግጠኛም ባይሆን አንደኛው ዛምያቶቭ ሳይሆን አይቀርም ብሎ ገመተ እርሱስ ቢሆን ምን ያመጣል። እዚህ ነህ እንዴ። እንዴት አይነት አስደሳች ሰው ነህ። ሲል ዛምያቶቭ መለሰ ራስኮልኒኮቭ ፊቱን ቅጭም አድርጎ ዛምያቶቭን ተመለከተ አፍህን ከፍተህ እያዳመጥክ እንደሆነ ይገባኛል እንዲህ አይነቱ ሁኔታ ቢገጥመኝ ምን እንደማደርግ ለማወቅ የምትፈልግ ይመስለኛል አይደለም እንዴ። ሳንቲም እንዳልነበረኝ ታውቃለህ እስካሁን ድረስ ቤት ያከራየችኝን ሴት መጠየቅ ነበረባችሁ በዚሁ ይብቃ ደህና ሁን አንተን በማግኘቴ ደስተኛ ነኝ መጠነኛ ደስታ በተቀላቀለበት ከቁጥጥር ውጭ በሆነ ስሜት እየተፈነቀለ ምግብ ቤቱን ለቀቀ በአጠቃላይ ግን ሀዘንና ድካም ጎድተውታል ፊቱ አገገሞ ከአልጋ የተነሳ ሰው ፊት መሰለ ድካሙ በአፋጣኝ እየጨመረ ሄደ ትንሺ የመቆጥቆጥ ስሜት ሀይል ብትለግሰውም ሰውነቱ በተዳከመ መጠን ሀይሌም በዚያው ልክ ተመናመነ ዛምያቶቭ ብቻውን ሆኖ እያሰላሰለ ከዚያው ስፍራ ለረጅም ጊዜ ተቀመጠ በተወሰነ ነጥብ ሳይ የያዘውን አቋም ራስኮልኒኮቭ አቅዶት ሳይሆን ሳያስበው እንዲለውጥ ስላደረገው ረዳት የፖሊስ ሹሙ ቂል ነው። ሲል ራዙምኪን ጮኸ ህላችሁም ስላንዝገሻችሁኝ ብቻዬን መሆን ፈለግሁ ማለት ነው እያለ ራስኮልኒኮቭ በርጋታ መለሰ ብቻውን መሆን ፈለገ። ፖሊስ ጣቢያ ዛምያቶቭ ለምን ከፖሊስ ጣቢያ አይሆንም። እያለ አሰላሰለ ከፖሊስ ጣቢያው ለመድረስ በቀጥታ ተጉዞ መታጠፍ ነበረበት ብዙ የሚርቅ አልነበረም ከመታጠፉ በፊት ግን ቆም ብሎ አሰበና አንዲት ቀጭን መንገድ ያዘ ያለምንም ምክንያት ይሆን ወይም ደግ ሀሳቡን ለመለወጥ የሚያስችለው ጊዜ ለማግኘት ሲል ውስጥ ለውስጥ ወደፖሊስ ጣቢያው አመራ ቀና ሲል ግን ያልተጠበቀ የዚያን ቤት በር ተመለከተ ከዚያ ምሸት በፊት ያንን ሰፈር ያልደረሰበት አካባቢ ነበር ሊገልፁትና ሊቋቋሙት በማይቻል ግፊት ተማረከ ደጃፉን አልፎ ከመግቢያው በር ደረሰና ወደአራተኛ ፎቅ የሚወስደውን የተለመደ ደረጃ መውጣት ያዘ ደረጃውን በጨረሰ ቁጥር ቆም ብሎ ዙሪያውን በጥሞና ይመለከታል ከመጀመሪያው ፎቅ የሚያደርሰውን ደረጃ ወጥቶ እንደጨረሰ የመስኮቱ ክፈፍ ሙሉ በሙሉ መነሳቱን ተገነዘበ ተዚያ ወዲህ የሆነ ነውብሎ አሰበ ኒኮላይና ድሚትሪ ያድሱት የነበረው ቤት ከሚገኝበት ከሁለተኛ ፎቅ ደረሰ ቤቱ ተዘግቷል በሩ በቅርቡ ቀለም እንደተቀባ ያስታውቃልየሚከራይ ነው ከዚያም ሶስተኛውን ፎቅ አልፎ ወደአራተኛው ፎቅ ዘለቀ ከዚያ። በማለት ሰራተኛው ተከትሎ ሄዶ ጠየቀው ራስኮልኒኮቭ ተመልሶ ገባ ዙሪያውን እየተመለከተ ቤት መከራየት እፈልጋለሁ አለ ከመሸ ቤት መከራየት የሚባል ነገር የለም ከዚህም በሳይ ደግሞ ከዘበኛው ጋር መምጣት ይኖርብሃል ራስኮልኒኮቭ በመቀጠል ወለሉ ንፁህ ነው ሊቀቡት ነው እንዴ። ከዚህ ስፍራ አንድ አሮጊት ከእነእህቷ ተገድላለች ከዚህ ስፍራ የደም ኩሬ ነበር ምን አይነት ሰው ነህ። ራስኮልኒኮቭ መልስ ሳይሰጥ ከአጠገባቸው ቆሞ በሀሳብ ተዋጠ ተለቅ ያለው ሰራተኛ ወደእነርሱ እየተጠጋ ቤት ለማየት ነበር የመጣው አለ ምን አይነት ቤት። ብሎ ጠየቀ እኔ ሮድዮን ሮማኖቪች ራስኮልኒኮቭ እባላለሁ የቀድሞ የዩኒቨርስቲ ተማሪ ነኝ ከዚሁ አካባቢ በሚቀጥለው መንገድ ላይ ካለው ቤት ነው የምኖረው የግቢውን ዘበኛ ብትጠይቀው ያውቀኛል ራስኮልኒኮቭ ዞር ሳይል የጨለመውን መንገድ እየተመለከተ በተፍታታና በተቀናጀ ሁኔታ ነበር የተናገረው ለምን ወደዚያ ቤት ሄድክ። እያለ ጮኸበት የራስኮልኒኮቭን ትከሻ ይዞ ወደመንገድ አሽቀነጠረው ራስኮልኒኮቭ እየተንገዳገደ ሳይወድቅ ቀረ ቆም ብሎ ዘበኛውንና ሌሎቹን ሰዎች ከተመለከተ በኋላ ገዞውን ቀጠለ የሚዢም ሰው ነውሲል ሰራተኛው ተናገረ በአሁኑ ጊዜ ብዙ የሚገርሙ ሰዎች አሉበማለት ሴትየዋ ሀሳቧን ገለፀች ባለእጁ ግን ያም ሆነ ይህ ወደፖሊስ ጣቢያ ልትወስዱት በተገባ ነበር አለ ከእንዲህ አይነት ሰው ጋር አለመነካካቴ ይሻላል ጮሌ መሆኑ ግልፅ ነው ወደዚያ እንድንወስደው የፈለገው ሆን ብሉ ነው ብንወስደው ኑሮ ማለቂያ የሌለው ነገር ይገጥመን ነበር እንደነዚህ አይነቶቹን እናውቃቸዋለን። በማለት ዋናው ዘበኛ አስረግጦ ተናገረ ራስኮልኒኮቭ ከሆነ ሰው መልስ የሚጠብቅ ይመስል ከመንታ መንገድ ላይ ቆሞ ዙሪያውን እየተመለከተ ልሂድ ወይስ ይቅርብኝ።

  • N.B. This Summary is Very Experimental!! based on the following scripts from:
    • https://github.com/millzon/textSummarizer-am
    • https://github.com/icoxfog417/awesome-text-summarization#motivation
Download Searchable PDF Download PDF

Comments:


memezon

Download options | Convert to Pdf | Book of the day

© dirzon | Terms of Service | Privacy | About | Services | Contact