Detecting...

Please whitelist dirzon to continue.

or subscribe for ad-free contenct.

dirzon
  • Convert to Pdf
  • Reading List
  • Summary
  • Audiobook
  • Search
  • Upload
  • myzon
  • Log in
  • Register
English  አማርኛ  Français  العربية
Book of the day

ወንጀልና ቅጣት 10.pdf


  • word cloud

ወንጀልና ቅጣት 10.pdf
  • Extraction Summary

ካለ በኋላ ወዴት ነው የምትሄጂው። እኔ አድነዋለሁ ገንዘብና ጓደኞች አሉኝ እንቺም ሆንሽ እናትሸ ፓስፖርት ከፈለጋችሁ አስወጣላችኋለሁ ራዙምኪን ምን ያደርግልቫል። የማይቻለውን ሁሉ አደርጋለሁ እምነትሽ እምነቴ ነው። ቁልፉን ጥዬዋለሁ ላገኘው አልችልም ዳንያ በአንድ ጊዜ ገርጥታ ወደጥግ እየሮጠችና ያገኘችውን ትንሽ ጠረጴዛ እየተከለለች አስገድደሀ ልትደፍረኝ ነው። አንቺው ራስሽ እያሳካሽልኝ ነው። ራዙምኪን ነው የሰጠሽ። የእኔው ሽጉጥ ነው ለካ። እውነት ነው ቢባል እንኳን ለአንቺ ስል ያደረግሁት ነው ምክንያቱ አንቺው ነሽ የምትናገረው ሐሰት ነው። ስም ማጥፋት ነው። የሆነ ነገር ለማለት ቢፈልግም ከንፈሮቹን ከማጣመም በስተቀር አንድም ቃል ለመተንፈስ አልቻለም ዳንያ በተኮሳተረ ድምጺ እባክህ ልሂድብላ ጠየቀች ስቪድሪጋሎቭ ተርበተበተ ድምጺ ከዚህ በፊት ያልነበረ ያልተጠበቀ ወዳጅነት የተንፀባረቀበት ነበር አትወጂኝም ማለት ነው።

  • Cosine Similarity

ክፍል ስድስት ራስኮልኒኮቭ አዲስና ያልተለመደ የሆነበትን ጊዜ መግፋት ጀመረ ጭጋግ በላዩ ላይ ወርዶበት ከአሰቃቂና ተስፋ ቢስ የብቸኝነት አረንቋ ውስጥ የከተተው ይመስል ነበር ያን ጊዜ ከረጅም ጊዜ በኋላ ሲያስታውሰው ሕዋሳቱ ጭራሽ አስኪያበቃላቸው ድረስ እየተመናመኑ መሄዳቸውን አይረሳውም ስለብዙ ነገሮች ለምሳሌ ያህል ድርጊቶች ስለተካሄዱበት ቀንና ስለፈጀባቸው ጊዜ ይሳሳት እንደነበር ያምናል ከጊዜ በኋላ አስታውሶ ሊገልፃቸው ሲሞክር ከሌሎች ሰዎች ያገኘውን መረጃ እያሰባሰበ ስለራሱ የማያውቃቸውን ብዙ ነገሮች አወቀ ለምሳሌ ያህል አንዱን ድርጊት ከሌሳ ጋር ያምታታል ሌላውን ድርጊት የአእምሮው ምናባዊ ፈጠራ ውጤት አድርጎ ይቆጥራል አንዳንድ ጊዜ የሚያምና የሚያሳዝን ስሜት ስር ይሰድበትና ያስጨንቀዋል በተቃራኒው ደግሞ ለሞት የተቃረቡ ሰዎች ከሚያሳዩት ያልተለየ ግዴለሽነት ሰርፀውበት የነበሩትን ደቂቃዎች ሰአታትና ቀናት ያስታውሳል ባለፉት ቀናት ውስጥ ራሱን ከማወቅ ለመሸሸ የፈለገ ይመስሳል አፋጣኝ መግለጫ የሚፈልጉ አንገብጋቢ ነጥቦች ክፉኛ ተጭነውታል። ይሁንና ከጭንቀቱ መሸሸ የቱን ያህል ቢያስደስተውም ጭንቀቱን እንዳለ ከጭንቅላቱ አውጥቶ መጣሉ ለእንደርሱ አይነት ሰው አጣዳፊ ሞት ማለት ነበር የስቪድሪጋሎቭ ሁኔታ በተለይ ያስጨንቀዋል አስተሳሰቡ ያተኮረው በስቪድሪጋሎቭ ዙሪያ ነበር ለማለት ይቻላል ሚስስ ማርሜሳዶቭ እንደሞተች ስቪድሪጋሎቭ በሶንያ ክፍል ውስጥ ሆኖ የሰነዘራቸው አስፈሪና ተገቢ ቃላት አስተሳሰቡን ያፋለሱት ይመስላሉ ግን ይህ አዲስ ሁኔታ ራስኮልኒኮቭን ክፉኛ ቢያስጨንቀውም ስለሁኔታው ማብራሪያ ለማግኘት የተጣደፈ አይመስልም አንዳንድ ጊዜ ራቅና ገለል ወዳለ የከተማው ክፍል ከአንድ አስቀያሚ የመሸታ ቤት ውስጥ ሳይታሰብ በድንገት ተቀምጦ ራሱን ያገኝና ስለስቪድሪጋሉቭ ያስባል ከዚያ ሰወዬ ጋር በተቻለ ፍጥነት መግባባትና ከስምምነት ደረጃ ላይ መድረስ እንዳለበት ይገነዘባል። ክፉኛም ተከዘ በዚያች ቅፅበት ወደሌላ ቦታ ሄዶ ቀሪውን ሕይወቱን ብቻውን መኖር ቢችል ኑሮ እራሱን የተባረከ አድርጎ ራሱን በቆጠረ ነበር ችግሩ ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ብቻውን ቢሆንም ብቻውን እንደሆነ ጭራሽ ሊሰማው አለመቻሉ ነው አንዳንድ ጊዜ አውራ ጎዳናውን ይዞ ይጓዝና ወደገጠር ያቀናል አንድ ቂንማ ጫካ ውስጥ ራሱን ያገኛል ቦታው ጭር ባለ ቁጥር በባዶነት ፋንታ የሆነ አስፈሪ ነገር ይሰማውና ፈጥኖ ወደከተማ በመመለስ ከሰዎች ጋር ይቀላቀላል ወደ ምግብ ቤትና መሸታ ቤት ይሄዳል ወደደራ ገበያ ያመራል ከዚያ ሲሆን ይረጋጋና ብቻውን የሆነ ይመስለዋል በአንድ ምሽት ላይ ከመሸታ ቤት ዘፈን ይዘፈናል ለአንድ ሰአት ያሀል በዚያው ተቀምጦ ዘፈኑን በማዳመጥ መዝናናቱን ያስታውሳል በመጨረሻ ላይ ግን ህሊናው ይኮረኩረውና እንደገና ይረበሻል ከዚህ ተቀምጩ ዘፈን እሰማለሁ ማድረግ ያለብኝ ግን ይሄን አይደለም እያለ ያሰሳላስሳል ወዲያውኑም በዚህ ብቻ እንዳልተጨነቀ ይገነዘባል አጣዳፊ መፍትሔ የሚጠይቅ ነገር አለ ምን እንደሆነ ግን በግልፅ አይረዳውም ወይም ደግሞ ይህ ነው ብሉ በቃላት አይናገረውም ሁሉም ነገር ቀውጢ የሆነበት ይመስላል አይደለም መታገሉ ይሻላል። አእምሮው ከመታደሱም በላይ ከአለፉት ሶስት ቀናት ጋር ሲነፃፀር እንደዛሬ ተረጋግቶ አያውቅም ቀደም ሲል የነበረበትን ድንጋጤና ሽብር አስታውሶ እስከመገረም ደረሰ በዚህ ሁኔታ ላይ እንዳለ ነበር በሩ ተከፍቶ ራዙምኪን የገባው ራዙምኪን ወንበር ስቦ ከራስኮልኒኮቭ ፊት ለፊት ተቀመጠና እየበላህ ነውሉ እንዲህ ከሆነማ እንዳልታመምክ እገምታለሁ አለው መቀየሙን ለመደበቅ አልሞከረም ቅር ቢሰኝም ሳይጣደፍና ሳይጮህ ተናገረ ልዩ ተልእኮ አንግቦ እንደመጣ ግልፅ ነበር በእኔ በኩል ዝነም ብትገባ ደንታ የለኝም በአሁኑ ሰአት ምንም ነገር ሊገባኝ አልቻለም ከሚል ደረጃ ሳይ ደርሻለሁ የመጣሁት አንተን በጥያቄ ለማፋጠጥ መስሉህ አትስ ጋ ያን የመሰለ ፍላጎት የለኝም አንተ ራስህ ሚስጥሮችህን ዘክዝከህ ልትነግረኝ ብትሞክር እንኳን ቁጭ ብዬ ስለማላዳምጥህ በከንቱ እንዳትለፋ የመጣሁት እብድ መሆንህን ወይም አለመሆንህን ለማወቅ ነው አንተን የሚመለከት አንድ አስተሳሰብ አለ አንድም ቀውሰሀል አሊያም ለመቀወስ እየተዘጋጀህ ነው በምታሳየው የቂልና በተወሰነ ደረጃም የሚያንገሸግሽ ባህሪ የተነሳ እንዲሁም ለእናትህና ለእህትህ በቅርቡ ባሳየኸው ጠባይ የተነሳ ይሄን አስተሳሰብ ለመቀበል እንደተገፋፋሁ በግልፅ እነግርሀለሁ ለእነርሱ እንዲህ አይነት ጠባይ ማሳየት ያለበት ጭራቅና ከይሲ የሆነ ወይም ያበደ ሰው ብቻ ነው ስለዚህ እብድ መሆን አለብህ በቅርቡ ተገናኝታችኋል። አንተ አቋረጥከኝ እንጂ ምስጢሩን ሁሉ የራሴ ጉዳይ አድርገ ለራሴ መተውዝን ከአንድ ደቂቃ በፊት ስትናገር በመስማቴ መደሰቴን ልገልዕልህ ነበር ለጊዜው ለእኔ ተውልኝ ጥሩ ሰው ስላገኘሁ አትጨነቅበት ሁሉንም ነገር ጊዜው ሲደርስ ታውቀዋለህ ነ እንድታውቀው የሚያደርግህ ጊዜ ሲመጣ ማለቴ ነው በትናንትናው እለት ሰው የሚፈልገው አየር እንደሆነ አንድ ግለሰብ ነግሮኛል። ይሄን ሲል ምን ማለቱ እንደሆነ ለማወቅ አሁኑኑ ሄጄ ላነጋግረው እፈልጋለሁ ራዙምኪን ኮስተር ብሎና ስሜት ውስጥ ገብቶ የሆነ ነገር አሰሳሰለ ያ ግለሰብ የፖለቲካ ሴረኛ መሆኑ አያጠራጥርም ወሳኝ የሆነ እርምጃ እንደሚወስድም አያጠራጥርም ሌላ ሊሆን አይችልም ዳንያም ስለዚህ ጉዳይ ታውቃለች ብሎ አሰበ እያንዳንዱን ፊደል ረገጥ እያደረገ እህትሁ ልትጠይቅህ መጥታ ነበር አንተም ደግሞ አየር ያስፈልገናል የሚል ሰው ለማነጋገር ጓጉተሀል ያ ደብዳቤ ከዚሁ ጋር ተመሳሳይ ይመስለኛል እያለ ለራሱ እንደሚናገር ሰው አወራ። ሁሉም ነገር የመጣልኝ በድንገት ሳላስበው ነው ዘበኞቹን ለመላክ ጊዜው አልነበረኝም ዘበኞቹን ስትወጣ እንዳየሀቸው እገምታለሁ በዚያን ሰአት አንድ ሀሳብ በአእምሮዬ ብልጭ አለብኝ አንተ ራስህ እንደምትገነዘበው ሁሉ በዚያን ጊዜ ፅኑ አቋም ወስጃለሁ እስቲ እንሞክረው ብዬ አሰብኩ አንድ ነዢ ለጊዜው ከአጄ እንዲያመልጠኝ ባደርግም ሌላ ነዢ በእጄ ውስጥ እንደማስገባ እርግጠኛ ነኝ የምፈልገው ነገር ደግሞ እንዲያመልጠኝ አልፈቅድም ይቅርታ አድርግልኝና በተፈጥሮህ በጣም ብስጩ ትመስለኛለህ በዚያን ሰአት አንድ ሰው ዝም ብሉ ተነስቶ ስለራሱ ዘክዝኮ እንደማይናገር መገዝዘብ ነበረብኝ ሰውዬው ፈፅሞ እንዲበሳጭ ከአደረግኸው ግን አልፎ አልፎ ያጋጥማል ትንሽ ማስረጃ ያስፈልገኛል ብዬ አሰብኩ ይዝ መነሳት ያለብኝ ተጨባጭ የሆነ ነገርን እንጂ የሳይኮሎጂ መላ ምትን አይደለም አንድ ሰው ጥፋተኛ ከሆነ በወቅቱ ከሰውዬው ተጨባጭ የሆነ ነገር ለማግኘት መቻል አለብህ ያልተጠበቀ ውጤት አገኛለሁ ብለህ እንከን መተማመን ትችላለህ ከሁሉም በላይ እኔ መሠረት ያደረግሁት የአንተን ጠባይ ነው በወቅቱ በአንተ ላይ ከፍተኛ አመኔታ ነበረኝ ራስኮልኒኮቭ ምን እንደሚጠይቅ ባለመገንዘብ በአሁኑ ሰአት ለምንድነው እንዲህ የምትናገረው። ይሄን ማድረግ ክቡር ግዴታዬ ነው ሁሉንም ነገር እንዳለ ከእነታሪኩና በወቅቱ የወሰድኩትን የአቋም ለውጥ ልገልፅልህ አፈልጋለሁ ወዳጄ ልቤ ብዙ ያስጨነቅሁህ መሰለኝ እኔ ጭራቅ አይደለሁም ተስፋ ቢቆርጥም ኩሩ ስሙኝ ባይና ብስጩ የሆነ ሰው በዚህ ሁሉ ሂደት ሲያልፍ ምን ማለት እንደሆነ በሚገባ እገነዘባለሁ አንተን ማታለል ስለማልፈልግ በግልፅነትና በቅንነት መንገር ያለብኝ ነገር አስተሳሰብህን ሁሉ የምቀበል እንዳልሆነ ቢታወቅም በባህሪህ ለጋስ የሆንክ የተከበረ ሰው አድርጌ እቆጥርሀለሁ ምን አይነት ሰው እንደሆንክ ከተረዳሁ በኋላ አንተን የማቅረብ ስሜት እንዳለኝ መደበቅ አልችልም። በዚህ ላይ መወያየት አስፈላጊ አይመስለኝም ወሬውና አጋጣሚው ተዳምረው በአእምሮዬ ውስጥ ሀሳብ ጫሩብኝ ማመን እስካለብኝ ድረስ ሁሉንም ነገር ማመን አለብኝና አንተን ለመጠርጠር የመጀመሪያው ሰው እኔ ነበርኩ አሮጊቷ በእዳ የያዘቻቸው እቃዎችና የመሳሰሉት ምንም አይፈይዱም በመቶዎች የሚቆጠሩ እንዲህ አይነት ፍንጮች ማግኘት ይቻላል በወቅቱ ከፖሊስ ጣቢያ የነበረውን ዝርዝር ሁኔታ በአጋጣሚ ተረድቻለሁ የተረዳሁት ግን እንዲህ አይነቱን ትርኢት ሪፖርት ለማድረግ ልዩ ስጦታ አለውና እርሱ ራሱ ሳያውቀው በግሩም ሁኔታ ከተረከልኝ ሰው ነው ወዳጄ ልቤ አንዱ ሁኔታ ወደ ሌላ እያመራ ሁሉም ነገር በአፋጣኝ ሲቀነባበር ወደ ተወሰነ አቅጣጫ ለማተኮር ተገደድኩ እንግሊዞች እንደሚሉት ሁሉ መቶ ጥንቸሎች ቢደራረቡ አንድ ፈረስ አይወጣቸውም መቶ ጥርጣሬም አንድ ማስረጃ አይሆንም መቼም ይሄ ግልፅ ነው ሰውን ግን ስሜቱ ይገዛዋል መርማሪም ደግሞ ሰው ነው። አስደንጋጭ አባባሉን ጭራሽ አላመንኩበትም ነበር አንተ ራስህ አይተሀል አንተ ከሄድክ በኋላ እንኪን ለአንዳንድ ጥያቄዎቼ አጥጋቢ መልስ በመስጠቱ እኔ ራሴ ብገረምም የተናገረውን አንድም ቃል አላመንኩትም ባመኑት መፅናት ይሷል ይሄ ነው ኒኮላይ ከደሙ ንፁህ ነው ኒኮላይን ጥፋተኛ አድርገህ መገመትህንና ይሄንንም እንዳረጋገጥክለት ራዙምኪን አሁን ነግሮኝ ሄጸጻልየምትለውን ብቻ ራስኮሊንኮቭ ጣልቃ በመግባት ተነፈሰች ትንፋሽ ስላጠረው ያሰበውን እንኳን ተናግሮ አልጨረሰም ይህን ዘዴኛ ሰው ስስ ዝዝ ይ ዓ ሪኤ ና ሊገልፁት በማይቻል ሁኔታ ተመስጦ ያዳምጠው ነበር ሊያምነው አልደፈረም አላመነውም ግን አሁንም በጥቅሉ ከሚሰነዝራቸው ቃላት መካከል ተጨባጭ የሆነ ነገር ፈልቅቆ ለማውጣት ጥረቱን ቀጠለ ፖርፊሪ በዝምታ ተውጦ የነበረው ራስኮልኒኮቭ በሰነዘረው ጥያቄ የተደሰተ ይመስል ፈንድቆ እንዲህ ሲል ተናገረ ህለት ከሆንክ ባልንጀራ ነህ ሶስት ከሆንክ ብዙነህ እንደሚባለው ሁሉ ራዙምኪን ከገዳዩ ውጪ እንዲሆን ማድረግ ነበረብኝ ምንም አይመለከተውም ከጨዋታው ውጪ ነው ግርጥት ብሎ ወደ እኔ እየሮጠ ይመጣል እርሱን ግን ብንረሳው ይሻላል ለምን እዚህ ውስጥ እናስገባዋለን። ኒኮላይ ምን አይነት ሰው እንደሆነ ማወቅ ትፈልጋለህ። ራስኮልኒኮቭ በመገረም አንተ ማን ነህ። እንድትወደኝ የምሞክር መስሉ እንደታየህ እርግጠኛ ነኝ ምናልባትም ዝም ብለህ ቃሌን እንዳለ ባትወስድ ይሻሳል ምናልባትም መቼም ላታምነኝ ትችላለህ እንዲህ አይነት ሰው መሆኔን አልክድም እኔ ሐቀኛ ሰው መሆኔን ወይም አለመሆኔን ግን አንተ ራስህ ፍረደው ግንመቼ ነው ልታስረኝ ያሰብከው። በዚህ ረገድ ኒኮላይ ትክክል ነው ስለዚህ ወዳጄ ልቤ ጥለህ አትጠፋም ራስኮልኒኮቭ ብድግ ብሎ ባርኔጣውን እንደያዘ ፖርፊሪ ከመቀመጫው ተነሳ በዛሬው እለት የእምነት ቃሌን እንደሰጠሁ ቆጥረህ አትሂድ የምትገርም ሰው ስለሆንክ ያዳመጥኩህ ተገርሜ ነው ያመንኩልህ ነገር እንደሌለ አስታውስ በማለት ራስኮልኒኮቭ ፈርጠም አድርጎ ተናገረ በሚገባ አውቃለሁም አስታውሳለሁም መንቀጥቀጥህ ያስገርማል ወዳጄ ልቤ አይዞህ። በተቻለ ፍጥነት ስቪድሪጋሎቭን ለማግኘት ጓግቷል እርሱ ራሱ ከማያውቀው ሰው ምን ማግኘት እንደሚችል ባይገባውም ያ ሰው እርሱን የመቆጣጠር ሀይል ያለው ይመስሳል ይሄን ከተዝነዘበ በኋላ አደብ ሊገዛ ካለመቻሉም በሳይ ጊዜው እየደረሰ ነው በዝዞው ላይ እያለ ስቪድሪጋሎቭ ፖርፊሪን ለማነጋገር ሄዶ ነበር ወይ የሚለው ጥያቄ አስጨነቀውፅ ከፖርፊሪ ጋር ያደረገውን ግንኙነት በዝርዝር አስታውሶና ጥያቄውን በጥንቃቄ አሰላስሎ አልሄደም ከሚል ድምዳሜ ላይ ደረሰ እስካሁን ባይሄድም ወደፊት ይሄድ ይሆን የሚል ጥያቄ ተቀረፀበትና ለጊዜው እንደማይሄድ እርግጠኛ ሆነ ለምን የሚለውን ጥያቄ ግን መመለስ አልቻለም መመለስ ቢችልም እንኳን በአሁኑ ደረጃ ጊዜ ማባከን ሆኖ ተሰማው ይሄ ሁሉ እያስጨነቀው ግን ያልተጨነቀ ይመስላል የሚርመው ነገርና ማንም ሊያምነው የማይችለው የአሁኑም ሆነ የወደፊቱ ሁኔታው ብዙም ያስጨነቀው አለመምሰሉ ነው ያስጨነቀው ሌላ ጉዳይ ነው በይበልጥ አንገብጋቢ የሆነ ነገር በቅፅበት ሊያሟሳው የሚገባና እርሱን ብቻ የሚመለከት ጉዳይ በቅርቡ ከነበሩት ቀናት ጋር ሲነፃፀር ዛሬ አእምሮው በተሻለ ሁኔታ ቢሠራም ሞራሉ ክፉኛ እንደወደቀ ተሰማው ያ ሁሉ ነገር ከደረሰበት በኋላ እነዚህን ጥቃቅን ጉዳዮች ለመወጣት መሞከሩ ፋይዳ ይኖረዋል። ከተነሳበት የገበያ ስፍራ አጠገብ ከሚገኘው አደባባይ አልራቀም ከአደባባዩ በግራ በኩል ያለው ሕንፃ ሁለተኛው ፎቅ ምግብ ቤት ነው የምግብ ቤቱ መስኮቶች ተከፍተዋል የሚተላለፉትን ሰዎች በመስኮቶቹ በኩል በማየት መገመት እንደሚቻለው ምግብ ቤቱ ተጨናንቋል በሙዚቃ መሣሪያዎች የታጀበ ዘፈንና የሴቶች ድምፅ ጎላ ብሎ ይሰማል ወደዚህ አደባባይ ለምን እንደመጣ ተገርሞ ለመመለስ ሲል ስቪድሪጋሎቭ ፒፓ ለጉሞ በጥግ በኩል መቀመጡን በአንደኛው መስኮት በኩል በአጋጣሚ ተመለከተ አጋጣሚው ከማስገረም አልፎ አስደነገጠው ስቪድሪጋሎቭ አድፍጦ ተከታተለው ከመታየቱ በፊት ተነስቶ ቦታ ለመለወጥ መሞከሩ ራስኮልኒኮቭን ትዝብት እንዲወስድ አደረገው ወዲያውኑም በአንድ በኩል በቆረጣ እይታ እየተከታተለው በሌላ በኩል ደግሞ ሌሳ ነገር በመመልከት ላይ ያተኮረ በማስመሰል ሰውዬውን እንዳላየ ሆነ ልቡ ክፉኛ ይመታ ገባ በእርግጥም ደግሞ ትክክለኛ ነበር ስቪድሪጋሎቭ ሳለመታየት ሞክሮአል ፒፓውን ከአፉ አውጥቶ ብድግ በማለት ራሱን ሊደብቅ ሲል ራስኮልኒኮቭ አይቶ እንደሚከታተለው ተገነዘበ የአሁኑ ሁኔታ ራስኮልኒኮቭ በክፍሉ ውስጥ ተኝቶ እያለ ለመጀመሪያ በተያዩ ጊዜ ከነበረው ጋር ይመሳሰሳል እየጎላ የሄደ ምስጢራዊ ፈገግታ በስቪድሪጋሎቭ ፊት ላይ ተነበበ አንዱ ሌላውን አይቶ እንደሚከታተለው ሁለቱም ተነቃቁና ስቪድሪጋሎቭ ከት ብሎ ሳቀ ከፈለግህ ና እዚህ ነኝ ሲል በመስኮት በኩል ጮኸ ራስኮልኒኮቭ ወደምግብ ቤቱ አመራ ነጋዴዎች የመንግስት ሰራተኞችና ሌሎች ሰዎች ወንድ አዝማሪ እያዝናናቸው ሻይ ከሚጠጠበት ሰፊ የምግብ አዳራሽ ጎን ካለች ጠባብ ክፍል ውስጥ ስቪድሪጋሎቭን አገኘው ከሆነ ቦታ የሚወጣ የከረንቦሳ ድምፅ ይሰማል ከስቪድሪጋሎቭ ጠረጴዛ ሳይ የተከፈተ የወይን ጠጅ ጠርሙስና የተጋመሰለት ብርጭቆ ጉብ ብለዋል በክፍሉ ውስጥ አነስተኛ የሙዚቃ ሙሣሪያ የያዘ ልጅ ሰረዝ ያለበት ቀሚስ ለብሳና ባለ ሪበን ባርኔጣ አድርጋ በሙዚቃው እየታጀበች ባልተገራ ድምጺ የባሕል ዘፈኑን የምታስነካው ጉንጮቿ ፍም የመሰሉ የአስራ ስምንት አመት ልጃገረድ ይታያሌ ራስኮልኒኮቭ ወደክፍሉ እንደገባ ይበቃሻል። አለ ወደ አዝማሪዋ እየተመለከተ አንድ ብርጭቆ ቀዳላትና ቢጫ ኖት አወጣ ሴቶች ብዙውን ጊዜ እንደሚያደርጉት ሁሉ ጊዜ ሳታባክን በአንድ ትንፋሽ ጭልጥ አደረገችና ገንዘቡን ወሰደች ስቪድሪጋሎቭ በመኮሳተር የሰጣትን እጁን ሳመችና የሙዚቃ መሳሪያ የያዘው ልጅ እየተከተላት ከክፍሉ ወጣች ሁለቱም ቢሆን ከመንገድ ተጠርተው የመጡ ነበሩ ስቪድሪጋሎቭ ፒተርስቡርግ ውስጥ ገና ሳምንት ባይሞላውም ከበሬታ እያተረፈ ነው አስተናጋጁ ፊሊኘ አቤት ወዴት የሚል ጥሩ ጓደኛ ሆኖለታል ወደምግብ አዳራሹ የሚያመራው በር ስለሚቆለፍ ስቪድሪጋሎቭ በዚህ ክፍል ውስጥ እየተዝናና ሙሉ ቀን ይውሳላል ምግብ ቤቱ ከርካሽነቱ ብዛት ይከረፋል ወደአንተ ክፍል እየተጓዝኩ ነበር ግን በሆነ ምክንያት ገበያውን ትቼ ወደአደባባዩ አመራሁ ለምን እንዳመራሁም አሳውቅም ብዙውን ጊዜ ከዝበያው ስፍራ ወደቀኝ እታጠፋለሁ የአንተ ቤት ያለው ደግሞ በዚህ አቅጣጫ አይደለም አደባባዩን ትቼ ለመመለስ ስል አየሁህ የሚገርም ነው። በማለት ራስኮልኒኮቭ ተናገረ ተአምር ነው ብለህ ለምን በግልፅ አትናገርም። ስቪድሪጋሎሉቭ በግማሽ ብርጭቆ ወይን ጠጅ ለብ ብሎታል የራሴ አቋም ያለኝ ሰው መሆኔን ከማወቅህ በፊት ልታነጋግረኝ መጥተህ የነበረ «ይመስለኛል አለ ራስኮልኒኮቭ ዚያን ጊዜው ጉዳይ ለየት ያለ ነው እያንዳንዱ ሰው የራሱ አሠራር አለው ተአምርን በተመለከተ ላለፉት ሁለትና ሶስት ቀናት እንቅልፍ ላይ እንደነበርክ ልነግርህ እችላለሁ ስለዚህ ምግብ ቤት ግን እኔ ራሴ የነገርኩህ ስለሆነ ወደዚህ መምጣትህ ተአምር መ ጫጫ ዴዴ ። በማለት ራስኮልኒኮቭ ትክ ብሎ እየተመለከተው ጠየቀ ስቪድሪጋሉቭ ደግሞ በአባባሉ የተገረመ ይመስል የማውቀው ነገር የለም ብሎ መለሰ ራስኮልኒኮቭ ግንባሩን ቋጠረና እንደሱ ከሆነ ብቻዬን ተውኝ ሲል አጉረመረመ ጥሩ ብቻህን እንተውህለን ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ከመንገዱ ላይ ሆጄ በመስኮቱ በኩል ስመለከት ከእኔ ለምን ለመደበቅ እንደሞከርክ ብትነግረኝ ይሻሳል ለመጠጣት አዘውትረህ ወደዚህ የምትመጣ ከሆነና ከአንዴም ሁለቴ ወደዚህ መጥቼ እንድንገናኝ ከጠየቅኸኝ እኔ ሳላይህ ቦታ ለመቀየር ለምን ፈለግህ። በማለት ራስኮልኒኮቭ በድንገት ተነስቶ በንዴት እየተንጎራደደ ተናገረና እንዲህ ሲል ቀጠለ ሰውን ችግር ላይ ለመጣል ከፈለግህ አደገኛ ልትሆን ብትችልም በአንተ የተነሳ ሕይወቴን አላመሰቃቅልም አንተ እንደምታስበው ሳይሆን ስለእራሴ የማልጨነቅ መሆኔን ግልፅ ሳደርግልህ እወዳለሁ አሁንም ቢሆን እህቴን ለቀቅ የማታደርጋት ከሆነ በቅርቡ የደረስክበትን ምስጢር መጠቀሚያ በማድረግ ግቤን እመታለሁ ብለህ የምትገምት ከሆነ እኔን ከማሳሰርህ በፊት እንደምገድልህ ለመንገር ወደዚህ መምጣቴን እንድታውቅልኝ እፈልጋለሁ በከንቱ የምዝት አይደለሁም ቃሌንም እንደማሳጥፍ የምታውቅ ይመስለኛል ጊዜ ወርቅ ስለሆነና አሁን ካልተናገርክ ትንሽ ቆይቶ ሊዘገይ ስለሚችል ልትነግረኝ የምትፈልገው ነገር ካለ አሁኑኑ እንድትነግረኝ በሁለተኛ ደረጃ እጠይቅሀለሁ ልትነግረኝ የቋጠርከው ነገር መኖሩ ሁልጊዜ ይሰማኛል ስቪድሪጋሎቭ በመገረም እየተመለከተው ጥድፊያው ምንድነው። ሲል ጠየቀው ሁሉም ሰው ጥሩ የመሰለውን ያደርጋል በማለት ራስኮልኒኮቭ ተክዞና ተበሳጭቶ መለሰ ስቪድሪጋሎቭ ፈገገ አለና እንዲህ ሲል ተናገረ በግልፅ ለመናገር በአሁኑ ሰአት እንኳን አንተ ራስህ ከተፈታተንከኝ በኋላ የመጀመሪያ ጥያቄዬን ለመመለስ እምቢተኛ ሆንክ ሁልጊዜ በአእምሮዬ የቋጠርኩት ነገር ያለ ይመስልሀል በአንተ ደረጃ ሲታይ ይሄን ለምን እንዳሰብክ ለመረዳት አያዳግትም ግን ከአንተ ጋር መወዳጀት ስለምፈልግ መሳሳትህን እመንልኝ ብዬ አላስቸግርህም በማሳመን የሚገኝ ጥቅም ከአለመኖሩም በላይ በተለየ አርእስት ላይ ከአንተ ጋር ለመወያየት እቅዱ ጭራሽ የለኝም ታዲያ ከጥቂት ቀናት በፊት ለምን ፈለግኸኝ። ለሚስስ ማርሜላዶቭ ልጆች እርዳታ አድርዝሀል አሁን እንደምረዳው ግን ያደረግህበት የራስህ ምክንያት የሚኖርህ ይመስለኛል ስቪድሪጋሎቭ ሳቁ ቀደመውና የሚከተለውን ተናረ በአጠቃላይ ልጆችን እወዳለሁ ከዚህ ጋር በተያያዘ እስካሁን ድረስ ያላበቃለት አንድ አስደናቂ ታሪክ ልነግርህ እችላለሁ ከሰባት አመት በኋላ ናፍቆቱና ስሜቱ ስላጠቃኝ ገና ከዚህ እንደደረስኩ በየምሽት ክለቡ ዞርኩ ከቀድሞ ጓደኞቼ ጋር የነበረኝን ግንኙነት ለማደስ ሳልጣደፍ እስከተቻለ ደረጃ ድረስ ብቻዬን ለመሆን ተስፋ አደረግሁ ከውሷ ባለቤቴ ጋር በገጠር ስኖር የማውቃቸው ሁሉ የምወዳቸው ትናንሽ የመደሰቻ ቤቶች ከአእአምርዬ አይጠፉም ነበር ተራው ሕዝብ ይሰክርባቸዋል ምንም ስራ የሌለው የተማረው ወጣት በማይሆን ራእይ ሲበዛ እየተፈላሰፈ ይሰናከልባቸዋል አይሁዶች ከሆነ ቦታ መጥተው እኛ ላይ ሰፈሩና ገንዘብ ያዙ የተቀረው ሕዝብ ደግሞ ርካሽ ሕይወት ይገፋል ወዲያውኑ ከተማ እንደደረስኩ ወልፉ ስለነበረብኝ በዳንስ ክለብ ስም ርካሽ ድርጊት ወደሚፈፀምበት አንድ ቦታ ሄድኩ በእኔ ጊዜ የሌለና ከየትም ቦታ የተሻለ ዳንስ ይጨፈርበታል በአጋጣሚ ሆነና በደንብ የለበሰች የአስራ ሶስት አመት ልጅ ዳንስን ሙያው ከአደረገ ሰው ጋር ስትደንስ ተመለከትኩ እናትዬዋ ከግድግዳ ጥግ ተቀምጣለች ምን አይነት ጭፈራ ሊሆን እንደሚችል መቼም ትገምታለህ ልጅቷ ግራ ግብት ይላትና ሀፍረት ይዚት እንባዋን ትለቀዋለች። ለደቂቃ ያሀል እንደገና ተፋጥጠው ቆሙ በመጨረሻ ግን ራስኮልኒኮቭ እንዳልተበገረ ሲዝዘብ ስቪድሪጋሉቭ ተለውጦ ተለሳለሰ ምን አይነት ሰው ነህ። ለመዝነብ የሚከጅል መሰለኝ ግን ግዴለም ዝናብ መከለያ አይጠፋም ስቪድሪጋሎሉቭ ከጋሪው ላይ ተሳፈረ ራስኮልኒኮቭ ለጊዜውም ቢሆን ያደረበት ጥርጣሬ መሰረተቢስ እንደሆነ ገመተ አንድም ቃል ሳይተነፍስ ፊቱን አዞረና ወደገበያው አቅጣጫ ተመልሶ ሄደ አንድ ጊዜ ፊቱን መለስ ቢያደርግ ኖሮ መቶ ሜትር ያህል በጋሪ ከተሣዘ በኋላ ሂሳቡን ከፍሉ በእግረኛ መንገድ ላይ ይሄድ የነበረውን ስቪድሪጋሉቭን ሊመለከት በቻለ ነበር እርሱ ግን ታጥፎ ስለሄደ ምንም ነገር ለማየት አልቻለም መጥፎ የጥላቻ ስሜት ከስቪድሪጋሎቭ ያርቀው ገባ ከዚያ ቆሻሻ ወንጀለኛ ሴሰኛና ርካሽ ሰው ምን ጠብቄ ነበር።

  • N.B. This Summary is Very Experimental!! based on the following scripts from:
    • https://github.com/millzon/textSummarizer-am
    • https://github.com/icoxfog417/awesome-text-summarization#motivation
Download Searchable PDF Download PDF

Comments:


memezon

Download options | Convert to Pdf | Book of the day

© dirzon | Terms of Service | Privacy | About | Services | Contact