Detecting...
Please whitelist dirzon to continue.
አንዳንዴማ መቋቋም የማይችሉት ነገር ይሆንብኛል።ትሰማኛለሀህ በማለት እያንባረቀ ጣቱን ቀሰረበት ወጣቱም ቆም ብሎ ባርኔጣውን በስሜት ጨምድዶ ያዘ ባርኔጣው ረጅምና ክብ ሆኖ በጊዜው ከአንድ የታወቀ ዘመናዊ ሱቅ የተገዛ ነበር አሁን ግን ከመቅዕበት ተለወጠ እንደእኔ አይነቱ የተማረ ሰው ከእንዲች አይነት ልጃገረድ ጋር በአንድ ሕንፃ ውስጥ አንዴት ይኖራል እያለ በተናገረ ቁጥር ሚስቴ በዝምታ አታልፈውም በአሁኑ ጊዜ ሶንያ ወደእኛ የምትመጣው ከመሸ ነው ከመሸ መጥታ ልጆቹን በመያዝና የሣጀቱን ስራ በመከወን ሚስቴን ታግዛታለችሱ የምትኖረውም በድኩቻነቴና በተብታባነቴ ከሚታወቀው ልብስ ሰፊ ማለትም ከካፔርኑሞቭ መኖሪያ ቤት ውስጥ አንድ ክፍል ይዛለች ሁሉም ድሆች ናቸው ሁሉም ደግሞ ይንተባተባሉ የዚያን እለት ጥዋት ከእንቅልፌ እንደተነሳሁ ልብሴን ደራርቤና ፀዐሱቴን አድርሼ ከተከበሩ ኢቫን አፋናሴቪች ዘንድ ሄደድከኩ እንዴት አይነት የተባረኩ ሰው መሰለህ ትህትና ባልተለየው ሁኔታ እስከመጨረሻ ካዳመጡኝ በኋላ ማርሜላዶቭ ከዚህ በፊት አስቀይመኽኛል አሁን ግን በራሴ ሃላፊነት አንድ አድል እሰጥሀለሁ ወደ ስራህ መመለስ ትችላለህ ብለው አሰናበቱኝ እኔም ጎንበስ ብዬ መሬቱን ሳምኩ ስል በምፀት መናገሬ ነው ዘመናዊ አስተሳሰብ ያላቸው ባለስልጣን እንደመሆናቸው መጠን የረገጡትን መሬት እንድስም ጨርሶ አይፈትዱም ወደቤት ተመልሼም ወደመንግስት ስራ በቋሟ ደመወዝተኛነት መመለሴን ሳበስር የተሰሣኝ ደስታ ይህ ነው።
በእንዲህ አይነቱ ጊዜ በተቻለ መጠን አይን ውስጥ ላለመግባት መሞከር ያስፈልጋል ጥቃቅኑን ነገር ሁሉ መዘንጋት አኢያስፈልግም ነገሩን ሁሉ የሚያበላሸው ጥቃቅኑ ነገር ነው እኮበማለት ለብቻው እንደ መቆጨት አለ ይህ ሁኔታ ያጋጠመው ብዙ ሳይጓዝ ነበር ከቤቱ ደጃፍ የራቀው በትክክል በሰባት መቶ ሰላሳ እርምጃ ነው ይሄን ርቀት ቆጥሮ የደረሰበት አንድ ቀን በሕልም አለም ውስጥ ገብቶ በተጓዘበት ሌሊት ነበር በወቅቱ በሕልሙ ላይ አመኔታ አለማሳደር ቢያስደስትም እንኪን ድፍረትን በተላበሰው ሕልሙ ተመሰጠ አሁን ወር ከአለፈ በኋላ ግን ህልሙን ከሌላ አቅጣጫ ማየት ጀመረ ስለራሱ ደካማነትና ወላዋይነት ቢያነበንብም ሆነ ሕልሙን መተግበሩን ባያምንበት እንኳን የማያስደስት ሕልሙ ፍፃሜ እንደሚያገኝ አድርጎ መቄጠሩን ተያያዘው እቅዱን ለማስፈፀም ቀስ በቀስ መለማመድጀመረ አንድ ድርጊት በፈፀመ ቁጥርም ደስታው አጥፍ ድርብ እየሆነ ሄደለት ልቡ እየተጨማደደና እየተንቀጠቀጠ በአንድ ጎኑ ከዬካቴሪንስኪ ቦይ በሌላ ጎኑ ደግሞ ከሳዳሾያ ጎዳና ጋር ትይዩ ወደሆነ ትልቅ ሕንፃ አመራ በዚህ ሕንፃ ውስጥ የተለያዩ ሙያተኞች ማለትም ልብስ ሰፊዎች ፀጉር አስተካካዮች ምግብ አብሳዮች በተገኘው መን ኑሯቸውን ሞምሂገፉ ኮበሌዎች ወይም ልጃገረዶች በዝቅተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞችና የጀርመን ዝርያዎች ጭምር ሰፍረዋል ወደ ሕንፃው የሚዘልቁፋም ሆነ ከሕንፃው የሚወጡ ሰዎች ያለማቋጥ ወደ ሕንፃው ሀለት በሮችና ሁለት ደጃፎች ሲያመሩ ማየት የተለመደ ትርኢት ነበር በዚህ ሕንፃ ውስጥ ሶስት ወይም አራት ዘበኞች ተቀጥረው ይሰራሉ ወጣቱ ከአንድም ሰው ጋር ባለመገናኘቱ እየተደሰተ በሩን ከፍቶ ተፍ ተፍ በማለት ደረጃዎችን ከወጣ በኋላ ወደቀኝ ታጠፈ ቀደም ሲል አስተውሉት እንደነበረው ሁሉ ደረጃዎቹ ደብዛዛና ጠባብ በመሆናቸው በሁኔታው ተደሰተ በእንዲህ አይነት ብዥታ ውስጥ ትክ ብሎ የሚመለከት አይን ቢያጋጥም እንኳን ጉዳት አያመጣምና ወደ አራተኛ ፎቅ እየወጣ ሳለም አሁን እንዲህ የፈራሁ ፍጥረት ድርጊቱን ስፈፅምማ እንዴት ልሆን ነውየሚል ሀሳብ ሳያውቀው በአእምሮው ተመላለሰበት አራተኛ ፎቅ ላይ እንደደረሰም ከአንዱ ቤት ዕቃ የሚያግዙ ተሸካሚዎች መንገዱን እደናቀፉበት። ምን አይነት አሰቃቂ ነገር ነው መከረኛው ልቤ የተሸከመው አዎ ነገሩ አስቀያሚም አስነዋሪም ነው በማለት ጮክ ብሎ ተናገረ ግና ስሜቱን ለሌላ ሰው ደፍሮ መግለፅ አልቻለም ከአሮጊቷ ቤት ወጥቶ በማቅናት ላይ እንደነበረ እንኳን አእምሮውን ማስጨነቅና ማሸበር የጀመረው አስቀያሚ ስሜት ተጠናክሮና ገህድ ወጥቶ በመታየቱ ምን ማድረግ እንዳለበት ግራ ገብቶት ነበረ የሰከረ ይመስል አልፎ ሂያጁን ሳያስተውልና ከእነርሱም ጋር እየተላተመ በእግረኞች መንገድ ላይ መጓዙን ቀጠለ ቀልቡን ያወቀው ከሚቀጥለው ጎዳና ሲደርስ ነበር ዙሪያውን ሲቃኝም ከአንድ መሸታ ቤት አጠገብ እንደቆመ ተገነዘበ ወዲያውኑም ሁለት ሰካራሞች ከመሸታ ቤቱ ወጥተው እየተደጋገፉና እየተወራረፉ ወደጎዳናው ዘለቁ በዚህን ጊዜ ራስኮልኒኮቭ ሳያመነታ ወደመሸታ ቤቱ አመራ ከዚህ ቀደም መሸታ ቤት ገብቶ አያውቅም አሁን ግን ከመዳከሙም በላይ በውሃ ጥም ተቃጥሏል ለመዳከሙ ምክንያቱ ረሀቡ እንደሆን በመገመት አንድ ቀዝቃዛ ቢራ ለመቸለስ ፈለገ ጨለማን ተገን አድርጎና ከተዝረከረከ ጥግ ሆኖ አንዲት የ ጫጻዔዌሯፔክ ቨ ዘ የእንጨት ጠረጴዛ በመያዝ ቢራ ከአዘዘ በኋላ የመጀመሪያውን ብርጭቆ በአንድ ትንፋሽ ጨለጠው ወዲያውኑም እየተሻለውና አእምሮው እየሰከነ ሄደ ሁሉም ነገር ከንቱ ነው። በራሱ ቢበሳጭም አንድ አይነት ሸክም የወረደለት ያህል የደስታ ስሜት ተነበበበት በመሸታ ቤቱ ውስጥ ያሉትንም ሰዎች በወዳጅነት አይን መቃኘት ጀመረ ነገሮችን ሁሉ በበጎ አይን መመልከቱ ግን ትክክል እንዳልሆነ ተሰማው በመሸታ ቤቱ የቀሩት ጥቂት ሰዎች ብቻ ነበሩ ሲወጡ ከተመለከታቸው ሁለት ሰካራሞች ሌላ አምስት ሰዎች ከአኮርድዮንና ከልጃገረድ ጋር እርሱ እንደገባ መሸታ ቤቱን ለቀዋል እነርሱ ከሄዱ በኋላም መሸታ ቤቱ ባዶ በመቅረቱ ፀጥ ረጭ አለ ከቀሩት ሰዎች መካከል አንድ ባለሙያ የሚመስል ሰው ጠረጴዛ ይዞ ቢራ ይጠጣል በመጠኑ ለብ ብሎታል ሽበት ጣል ጣል ያለበትን ጢሙን አንርግነጎ ውብ ባለሰረዝ ኮት የለበሰው ወፍራሙ ጓደኛው ግን በጣም ሰክሯል ለይቶለታል እተቀመጠበት እንቅልፍ ይዞት ሄዶአል በእንቅልፍ አለምም ሆኖ አንዳንዴ ከመቅዕበት ወደ ህይወት ይመለስና እጆቹን ዘርግቶ ጣቶቹን እያፍታታ ከተቀመጠበት ሆኖ ይንጠራራል እንዲህ ሲያደርግ ደግሞ ዘፈን አይሉት ቁምነገር «አመት ሙሉ ያቀፍኩሽ ሚስቴ አመት ሙሉ ያቀፍኩሽ ሚስቴ በጎዳናው ወርጄ ስሄድ ያጋጠምሸኝ የመጀመሪያ ፍቅሬ» እያለ ይቀባጥራል የሚያዳምጠው ግን ማንም ሰው አልነበረም ለዝምተኛ ጓደኛው እንዲህ አይነቱ ልፍለፋና መለፋደድ ክፉኛ ቸኮታል ጡረታ የወጣ የመንግስት ሰራተኛ የሚመስል ሌላ ሰው ደግሞ በአካባቢው ነበር የተቀመጠው ከሌሎቹ ፈንጠር ብሉ ነው አረቄውን እየጨለጠ ዙሪያውን ይቃኛል እርሱም ዝም አይነቅዝም ሆኖ ነው እንጂ ሞቅ ያለው ይመስላል። በባንኮኒው ላይ በቀጭኑ የተቆራረጠ ኪዩኩምበር ደረቅ ጥቁር ብስኩትና የተቆራረጠ አሳ ተደርድረው ይከረፋሉ ቤቱ ከመታፈኑ የተነሳ በዚያ መቀመጥ ያዳግታል የአልኮሉ ሽታ እጅግ በመሰራጨቱ የገባ ሰው ሁሉ አየሩን በመሳብ ብቻ በአምስት ደቂቃ ውስጥ የሚሰክር ይመስሳል የማይተዋወቁ ሰዎች ቃላት እንኳን ባይለዋወጡ ገና ከመተያየታቸው የመቀራረብ ፍላጎት የሚያድርባቸው ሁኔታ ያጋጥመናል በዚሁ በተመሳሳይ መንገድ ጡረታ የወጣ የመንግስት ሰራተኛ ይመስል የነበረውና ትንሽ ፈንጠር ብሎ የተቀመጠው ሰውዬ ከራስኮልኒኮቭ ጋር መጫወት ፈለገ ከጊዜም በኋላ ይህ አይነቱ ፍላጎት የለከፋ ይሆን እንዴ በማለት መገመቱን ወጣቱ አዘውትሮ ያስታውስ ነበር ሰውዬው ትክ ብሎ ያየው ስለነበርና ጨዋታ መፈለጉም ግልፅ ስለነበር እርሱም ያለማቋረጥ የመንግስት ሰራተኛውን ተመለከተ የመንግስት ሰራተኛው በቤቱ ውስጥ ያሉት ሌሎች ሰዎች ከእነባለቤቱ ጭምር ደብረውታል የእርሱን ያህል ያልተማሩ ዝቅተኛ ሰዎች አድርጎ በመቁጠር ከእነርሱ ጋር ማውራት ፋይዳ ቢስ እንደሆነ ገምቷል እድሜው ከአርባ በላይ ሲሆን ቁመቱ መካከለኛ ሆኖ ሰውነቱ የተደላደለ ነው ራሰ በራና ሽበት ጣል ጣል ያደረገበት ነው የሐቀኛ ጠጪ ፊት ያለውና አበጥ አበጥ ካሉት የአይን ቆቦቹ ውስጥ የሚወጡት አይኖቹ ፍም የመሰሉ ናቸው ሌላው ያልተለመደ ነገር ደግሞ አይኖቹ ከደስታ ብዛት የሚያበሩ መምሰላቸው ነው ማብራታቸው ግን አንድም የአዋቂነት ነው አለዚያም የእብደት ነው ያረጀና የነተበ ረጅም ጥቁር ኮት ለብሷል የኮቱ አንድ ቁልፍ ብቻ እንጂ የተቀሩት ሁሉ ረግፈዋል ከኮቱ ላይ እንደነገሩ የተቀመጠው ይህ ቁልፍ ቁመናውን ላለማሳጣት ሲባል የተተከለ ነው ከሰደሪያው ስር የለበሰው ሸሚዝ ደግሞ ከመጨማደዱም በላይ ያደፈና የቆሸሸ ነው ቂሙን በመንግስት ሰራተኛ ደንብ ተላጭቷል ጨጎጊት ስለወረሰው ግን ከተላጨው የሰነበተ ለመሆኑ ያስታውቃል የሚያሳየው አለመረጋጋት አንድ የተከበረ የመንግስት ሰራተኛ ከሚያሳየው ባህሪ መካከል የጎደለ ነገር እንዳለው ያመለክታል ፀጉሩን ያሻሻል አልፎ አልፎ ደግሞ እጆቹን ከረጠበው ጠረጴዛ ላይ አድርጎ ጭንቅላቱን ይይዛል በመጨረሻም ወደራስኮልኒኮቭ አነጣጥሮ ተመለከተ አንድ ወንድ ልጅ ከመሰሉ ጋር እንደሚያደርገው ሁሉ ላነጋግርህ እችላለሁን። እያለ ፎለለ ግንባሩን በጣቱ ተምተም በማድረግ ግምቱ ትክክለኛ በመሆኑ መደሰቱን ገለፀ የዩኒቨርስቲ ተማሪ ነህ ወይም የተወሰነ የዩኒቨርስቲ ትምህርት ተከታትለሀል ካለ በኋላ ለመቀመጥ ትፈቅድልኛለህ ሲል ተናገረ ቀና ካለ በኋላ እየተንገዳገደ ጠርሙስ አረቄውንና ብርጭቆውን ይዞ ከወጣቱ ጠረጴዛ በመድረስ ወጣቱን በስላሹ በሚያይበት ሁኔታ ተመቻችቶ ተቀመጠ ቢሰክርም እንኳን በብዛትና በተፍታታ ሁኔታ መናገር አልተሳነውም ነበር ከመዘበራረቁና የአነጋገር ፍጥነቱን ከመቀነሱ በስተቀር ወሩን ሙሉ ሳይናገር የተቀመጠ ይመስል ራስኮልኒኮቭን በተመስጦ ያስተውል ገባ ኮስተር ብሎ እንዲህ በማለት ንግግሩን ቀጠለ ድህነት ወንጀል አይደለም የማወራው ሐቅ ነው ስካርም በጎ እንዳልሆነ በእርግጥ አውቃለሁ ይህ ደግሞ ከምንም የበለጠ ሐቅ ነው እጦት ግን ወንጀል ነው ድሀ ሆነህ ሰብአዊ ክብርህን መጠበቅ ትችሳላለህ ከአጣህ ከነጣህ ግን ክብርህን መጠበቅ ጭራሽ ይሳንሀል አንድ ሰው ከአጣና ከነጣ ክብሩን ስለሚያስነጥቅ በአርጩሜ አይደለም የማሚባረረው እጅግ አሳፋሪ በሆነ ሁኔታ ከጨዋዎች መካከል በመጥረጊያ ታፍሶ ነው የሚጣለው ቤትና ገንዘብ በሌለኝ ጊዜም ራሴን ለማዋረድ የመጀመሪያው ሰው ለመሆን መዘጋጀቴ መሆኑ ትክክል ነው አየህ ጌታው ከአንድ ወር በፊት ሚስተር ሌቤዚያትኒኮቭ ሜስቴን እስክትበልዝ ድረስ ደበደባት ሚስቴ ደግሞ ከእኔ የተለየች ነች ተረዳኸኝ አይደል። ያሳለፍኩት ጊዜ ያለ አይመስለኝምበማለት መለሰ አምስት ቀን ቆይቼ ገና አሁን ከዛ መመለሴ ነው ብርጭቆው ላይ አረቄ ቀድቶ ከጩለጠ በኋላ በዝምታ እንደተዋጠ በሀሳብ ወደ ሌላ አለም ነጎደ እንደ እውነቱ ከሆነ በልብሱና በፀጉሩ ላይ የሳር ብናኝ ይታያል ላለፉት አምስት ቀናት ልብሱን እንዳልቀየረና ሰውነቴን ውሃ እንዳልነካው ይገመታል በተለይ ጠቋቁር ጥፍሮችን ያዘሉት ደንዳና እጆቹ ቆሽሸዋል የሰውየው ንግግር በመሸታ ቤቱ የነበሩ ሰዎችን ትኩረት የሳበ መሰለ ይሄን ያህል የተመሰጠ ሰው ግን አልነበረም ከባልኮኒው በስተጀርባ የነበሩ ወጣቶችም ቀስ አያሉ ማሽካካት ጀመሩ የመሸታ ቤቱ ባለቤት ቀልደኛውን ሰውዬለማዳመጥ ሲል ከላይ ካለው ክፍል ወርዶ በመምጣት በተዳከመ መንፈስ ፈንጠር ብሉ ተቀመጠ ማርሜላዶቭ ነባር ደንበኛ መሆኑ በገዝህቄድ ይታይ ነበር ወደ መሸታ ቤቱ የሄመጡ እንግዶችን አዘውትሮ በማጫወት ጉራ የተመላበት አንደበት እንደተላበሰ አያጠራጥርም በተለይ በቤታቸው ውስጥ ፈላጭ ቆራጭ ለሆኑ ለአንዳንድ ጠጪዎች ይህ አይነቱ ባህሪ የማይለቅ ነው ስለሆነም ከሌሉች ጠጪዎች ጋር በሚቀላቀለብት ጊዜ ትክክለኛነታቸውን ለማሳየት ከዚያም አልፎ ለመከበርም ይከጅላሉ የመሸታ ቤቱ ባለቤትም ምን አይነቱ ቀልደኛ ነህ። በሣሣለት ራስኮልኒኮቭ አጥብቆ ጠየቀው የምታውቀው ሰው ባይኖርህ እንኳ የምትሄድበት ቦታ ይኖርሃል የምትሄደው ደግሞ ወድደህ ሳይሆን ጊዜው አስገድዶህ ነው የገ ሴት ልጄ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደጎዳና እንደወጣች እኔም መውጣት ነበረብኝብሉ ወጣቱን በስጋት አይን እየተመለከተም ልጄ ወደጎዳና በመውጣት የታወቀች ስለሆነች ነዋ ሲል አጠናክሮ ተናገረ በባንኮኒው ውስጥ ያሉት ሁለት ልጆች እየሳቁበትና የመሸታ ቤቱ ባለቤትም ፈገግ ባለበት ሁኔታ ምንም አይነት ሀፍረት ሳያሳይ ይህ አንኳን የሚያሳስብ ጉዳይ አይደለምበማለት ንግግሩን ቀጠለ ሰዎች ራሳቸውን ነቀነቁና እኔ ደግሞ የምደነግጥ አይደለሁም ይህ ሁሉ ከመታወቁም በላይ የተደበቀው ሁሉ እየተገለጠ ይገኛል ሁኔነታውን የምመለከተው በቅሬታ ሳይሆን ከንፁህና ፀፀትን ካዘለ ልብ በመነሳት ነው እባክህ አንድ ጥያቄ ልጠይዓህ በዚህች ደቂቃ ውስጥ ። ዘ ወጣቱ ለጥያቄው ምንም መልስ አልሰጠም ነበር በመጨረሻ ላይ የተናገረው ቃል ያስከተለው ሳቅ ከበረደ በኋላ ተናጋሪው እየፎለለ ንግግሩን እንዲህ ሲል ቀጠለ ጌታው አኔ እቪ ግዴለም ደባሪ ልሁን ሚስቴ ግን እመቤት ነች እኔ ከብት ልሆን እችላለሁ ውጳ ባለቤቴ ካተሪና ኢቫኖቭና ግን በጣም የተማረችና ከጦር መኮንን የተወለደች ነች ግሩም ጠባይና ክቡር ስሜት ያላት ምሁር ነች እንዲያም ሆኖ እንኳን እሰቲ ብታዝንልኝ ምናለበት። አንዳንዴ እንኳን ሚስቴ ብታዝንልኝ ምነው መክረ የማይሆን ነው መናገርም አያስፈልግ ፀሎቴ ቢሰምርማ ኖሮ ሰዎች ያዝኑልኝ ነበር እንዲህ አይነት ሰው ነኝ ጌታው ርካሽ ሆ የተፈጠርኩ ሰው። ቦዝ አልተረዳህልኝም መሰለኝ ለአንድ ሙሉ አመት መጠጥ የሚባል ሳልቀምስ ግዴታዬን በሚገባ ተወጣሁ እንዲያም ሆኖ እንኳን ደስተኛ አልነበረችም ከዚያ በኋላ እኔ አጥፍቼ ሳይሆን በመስሪያ ቤት ውስጥ በተደረገው የሰራተኛ ሽግሽግ የተነሳ ከስራዬ ተሰናበትኩ ወደመጠጥ ያዘነበልኩትም በዚያን ጊዜ ነበር እንግዲህ ብዙ መንከራተትና ሁልቁ መሳፍርት የሌለው ስቃይ አልፎ በበርካታ ሕንፃዎች በተዋበው በዚህ ደማቅ መዲና ውስጥ የተገናኘነው ከአስራ ስድስት ወራት በኋላ ነው እዚህም ቢሆን ስራ አግኝቼ ነበር ከስራዬ ግን እንደገና ተፈናቀልኩ የተፈናቀልኩትም ድክመቴ አሸንፎኝ በራሴ ጥፋት ነበር በአሁኑ ጊዜ ወደ መ አንዱ ጥግ ቤት ተከራይተን እንኖራለን እንዴት እንደምንኖርና የቤት ኪራያችንን ከዬት አምጥተን እንደምንከፍል ግን አላውቀውም ከእኛ በተጨማሪ ሌሎች ሰዎች በአካባቢው ይኖራሉ አስከፊ ቦታ ሲበዛ ችምችም ያለ ነው ከዚሁ ጎን ለጎን ደግሞ ከመጀመሪያው ጋብቻዬ ያፈራኋት ሴት ልጄ እያደገች ሄደች ስታድግ ግን በእንጀራ እናት እጅ ስላየችው ስቃይ ባላነሳው ይሻሳል ሚስቴ የተከበረ ጠባይ ቢኖራትም ቅሉ ቁጡ ቅብጥብጥና ሰዎችን ልክ ልካቸው ድረስ የምትናገር ነች ስለዚህ ጉዳይም ባሳወራው ይመረጣል እንደምትገምተው ሀሉ ልጄ ሶንያ አልተማረችም ጂኦግራፊና የአለም ታሪክ ላስተምራት ከአራት አመት በፊት ሞክሬ ነበር እኔ ራሴ ግን ትምህርቱን በደንብ ካለማወቄም በላይ ተገቢው መቁዌህፍት አልነበሩንም እስከጥንታዊው የፋርስ ሥርወ መንግሥት ድረስ ብቻ ነበረ ዘልቀን የተማርነው እያደገች ከሄደች በኋላ ግን አያሌ የፍቅር መፃሕፍት አንብባለች ከቅርብ ጊዜ ወዲህም ጆርጅ ሉዊ የፃፈውን ፊዚዮሎጂ የተሰኘ መፅሐፍ ሚስተር ሌቤዚያትኒኮቭ ሰጥቷት በከፍተኛ ስሜት አንብባለች አንተም በአጋጣሚ አንብበኸዋል። ከዚያ በኋላ ሚስቴም ቃል ሳትተነፍስ ወደሶንያ አልጋ ሄዳ ከአልጋው አጠገብ በርከክ በማለት የሶንያን እግር ስትስም ተመለከትኩ ምሽቱን በሙሉ ተንበርክካ የሶንያን እግር እየሳመች ለመነሳት ፈቃደኛ አልነበረችም በመጨረሻም ሁለቱም እንደተቃቀፉ እንቅልፍ ይዚቸው ሄደ ማርሜላዶቭ ድምፁ የከዳው ይመስል በዝምታ ከተዋጠ በኋላ ብርጭቆውን ሞልቶ ጉሮሮውን አራሰ ትንሽ እንደቆየም ንግግሩን እንዲህ እያለ ቀጠለ በአንድ አጋጣሚ የተነሳ ዳርያ ፍራንዞቭናም የናቅናት ስለመሰሳት ከአንዳንድ ርኩስ ሰዎች ጋር ግንባር ቀደም በመሆን መረጃውን ለፖሊስ ስላቀበለች ልጄ ሶንያ በሴትኛ አዳሪነት ተመዝግባ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ከእኛ ጋር አትኖርም ቤት የአከራየችን ሴትና ሚስተር ሌቤዚያትኒኮቭ እንዲህ አይነቱን ነገሯ አይፈቅዱም መጀመሪያ ላይ ግን ራሱ ሚስተር ሌቤዚያትኒኮቭ አባብሉ ሶንያን ለመድፈር የሣቻለውን ሁሉ ዋኖክሮ ነበር አሁን ግን ከመቅዕበት ተለወጠ እንደእኔ አይነቱ የተማረ ሰው ከእንዲች አይነት ልጃገረድ ጋር በአንድ ሕንፃ ውስጥ አንዴት ይኖራል እያለ በተናገረ ቁጥር ሚስቴ በዝምታ አታልፈውም በአሁኑ ጊዜ ሶንያ ወደእኛ የምትመጣው ከመሸ ነው ከመሸ መጥታ ልጆቹን በመያዝና የሣጀቱን ስራ በመከወን ሚስቴን ታግዛታለችሱ የምትኖረውም በድኩቻነቴና በተብታባነቴ ከሚታወቀው ልብስ ሰፊ ማለትም ከካፔርኑሞቭ መኖሪያ ቤት ውስጥ አንድ ክፍል ተከራይታ ነው የሰውየው ጪስትም የምትንተባተብ ስትሆን ምሄኖሩት በአንድ ክፍል ነው ሶንያ የተሸነሸነ አንድ ክፍል ይዛለች ሁሉም ድሆች ናቸው ሁሉም ደግሞ ይንተባተባሉ የዚያን እለት ጥዋት ከእንቅልፌ እንደተነሳሁ ልብሴን ደራርቤና ፀዐሱቴን አድርሼ ከተከበሩ ኢቫን አፋናሴቪች ዘንድ ሄደድከኩ እንዴት አይነት የተባረኩ ሰው መሰለህ ትህትና ባልተለየው ሁኔታ እስከመጨረሻ ካዳመጡኝ በኋላ ማርሜላዶቭ ከዚህ በፊት አስቀይመኽኛል አሁን ግን በራሴ ሃላፊነት አንድ አድል እሰጥሀለሁ ወደ ስራህ መመለስ ትችላለህ ብለው አሰናበቱኝ እኔም ጎንበስ ብዬ መሬቱን ሳምኩ መሬቱን ሳምኩ ስል በምፀት መናገሬ ነው ዘመናዊ አስተሳሰብ ያላቸው ባለስልጣን እንደመሆናቸው መጠን የረገጡትን መሬት እንድስም ጨርሶ አይፈትዱም ወደቤት ተመልሼም ወደመንግስት ስራ በቋሟ ደመወዝተኛነት መመለሴን ሳበስር የተሰሣኝ ደስታ ይህ ነው ልልህ አልችልም ማርሜላዶቭሸ በጣም ተሟሙቆ እንደገና በዝምታ ተዋጠ ወዲያውኑም በስካር ያበቃላቸው ሳዎች ወደመሸታ ቤቱ ዘለቁ ከደጃፉም ላይ አንድ የሰባት አመት ልጅ በቃጭል ድምፁ የሀገረሰብ ዘፈን ይዘፍን ነበር የመሸታ ቤቱ ባለቤትና ሁለቱ ልጆች ጠጪዎቹን ማስተናገድ ጀመሩ ማርሜላዶቭ ግን ስለአዲሶቹ መጤዎች ደንታቢስ በመሆን ታሪኩን መዘክዘኩን ቀጠለ የተዳከመ ቢመስልም በይበልጥ በጠጣ ቁጥር በይበልጥ መለፍለፉን ተያያዘው ወደቀድሞው ስራ ለመመለስ የመብቃቱ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ጥንካሬ እየሰጠው ከመሄዱም በላይ እየፈካ በመምጣቱ ስሜቱ በፈቱ ሳይ ተንፀባረቀ ራስኮልኒኮቭም በጥሞና ይሰማው ጀመር ከአምስት ሳምንታት በፊት ነበር ወደስራ ስለመመለሴ ሂስቴና ሶንያ እንደሰሙ ያደረብኝ ስሜት መንግስተ ሰማያት የገባሁ ያህል ነበር ከዚህ ቀደም እንደሣንኛውም ሰካራም የባጥ የቆጡን እየቀባጠርኩ እዋሽ ነበር የምሰማውም ስድብና ዘለፋ ብቻ ነበር። ይሄን ሁሉ ለሣቅረብ ገንዘቡን ከዬት አንዳገኙት አምላክ ይወቀው ምርጥ ጫማና ሽሚዝ ከመንግስት ሰራተኛ የደንብ ልብስ ጋር በአስራ አንድ ሩብል ተኩል ተገዘልኝ ከእኩለ ቀን በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከቢርዬ ወደቤት እንደተመለስኩ ከዚህ ቀደም አይተነው የማናውቀውን ሾርባና ግሩም ጥብስ አዘጋጅታ ጠበቀችኝ እንደእውነቱ ከሆነ አንድም የረባ ልብስ አልነበራትም አሁን ግን ሰው ለመጠየቅ እንደሚወጣ ሰው ለባብሳ ብቅ አለች አዲስ ልብስ ኖሯት ሳይሆን ከምንም ተነስታ አንድ ነገር ፈጠረች ንፁህ ሻርፕና ጃኬት ደርባ ሌላ ሰው ሆና ቀረበች ወጣት ሆነች ውብ ህነች ከእንግዲህ ወዲህ አዘውትሬ እየመጣሁ የማይህ አይመስለኝም ምናልባት ምሽት ላይ ማንም ሳያይ እመጣለሁበማለት ተናገረች ታዳምጠኛለህ። ምንም የቀላቀለችውም ወቭት አልነበረም ፍላጎቷን በመግለፅ እየተዝናናች ነበር ይሄን በማድረባም ጭራሽ አልወቅሳትም ከስድስት ቀን በፊት የመጀመሪያ ደመሀዚዜ የሆነውን ሀያ ሶስት ሩብል ከአርባ ሳንቲም እንዳለ ስሰጣት የእኔ ማር የእኔ አካል ብላ ጠራችኘኙ ብቻችንን ስንሆን ደግሞ ሌላ ጉዳይ ነው ተረዳኸኝ አይደል ለማንኛውም አንዴት አይነት ባል መሰልኩህ ከመውደጂ የተነሳ የእኔ ማር እየለች ጉንጩን ዳብሳዋለች ማርሜላዶቭ ትንሽ ጋብ ብሉ ፈገግ ለፃለት ከሞከረ በኋላ መዝረብረብ ቢጀምርም ራሱን ተቆጣጠረ የመሸታ ቤቱ ሁኔታ የሰውዬጦ ስካር አረቄው ሰወዬው ከሚስቱና ከቤተሰቡ ጋር ያለው ይህ አይነቱ ግንኙነት ተዳክሞም ቢሆን በተመስጦ ይሰማ የነበረውን ራስኮልሂኮቭ ግራ አጋቡት ወደመሸታ ቤቱ በመሄዱም አዘነ ማርሜላዶቭ ሀሊናውን እንደገዛም የእኒ ጌታ የእኔ ጌታበማለት ከኸ በኋላ ንግግሩን እንዲህ ሲል ቀጠለ ይህ ሁሉ ጨዋታ ሌሉችን እንዳስገረመ ሁሉ አንተንም ሊያስገርምህ ይችሳል የቤተሰቤን ሁኔታም በመዘርዘር ረብሼህ ሊሆን ይችላል እመነኝ ነው የምልህ ለእኔ ግን የሚያስገርም ሳይሆን የልቤን ቁስል የማነካ ነው በሕይወቴ ባጋጠመኝ በዚያች አስደሳች ቀን በማይጨበጥ የሕልም አለም ውስጥ ገባሁ ለልጆቻችን ጨርቅ የመግዛት የሚስቴን ኑሮ ትንሽ የማደሳደል ሴት ልጄን ከርካሽ ሕይወት አላቅቆ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ህልምማርሜላዶቭ ቀና ብሉ ወጣቱን አድማጭ ካየ በኋላ ንግግሩን በአዲስ መልክ ጀመረ በማግስቱ ማለትም ከአምስት ቀናት በፊት ይሄ ሁሉ ሕልም ከታየ በኋላ ከሚስቴ ሳጥን በዘዴ ያገኘሁትን ቁልፍ በመያዝ ከደመወዜ የተረፈውን ሁሉ ወሰድኩ ምን ያሀል እንደሆነ ግን አላስታውስም እስቲ አሁን ተመልከቱኝ ለአምስት ቀን ቤት አልነበርኩም ከቤት እየፈለጉኝ ነው ከስራዬ ተፈናቅዬአለሁ የስራ ልብሴን በመሸታ ቤቱ ውስጥ በእዳ አስይዝፔው የለበስኩት ይሄን ጨርቅ ነው ሁሉም ነእር አከተመለት። ለምን ሰው አያዝንልኝም።