Detecting...
Please whitelist dirzon to continue.
ወደራስኮልኒኮቭ ክፍል እንደገቡ በጣም ደህና ነው። እያለ ዞሲሞቭ ጎላ አድርጎ ደስታ በተመላበት ስሜት ገለፀላቸው ዞሲሞቭ ከአስር ደቂቃ በፊት ደርሶ ከተለመደ ስፍራው ከሶፋው ሳላይ ተቀምጧጣል ራስኮልኒኮቭ ተጣጥቦ ፀጉሩን አበጣጥሮና ለባብሶ ከፊት ለፊቱ ተቀምጣል ክፍሉ በአንድ ጊዜ በጣም የተደሰተ ይመስል ነበር ከትናንቱ ማታ ግብዣህ በኋላ ከባድ የዞረ ድምር ይዞኛል በአጠቃላይ የሳትኩ ይመስለኛልሲል እየሳቀ ለየት ባለ ስልት ለራዙምኪን ነገረው ጥሩ ውይይት ነበር። ተራ የማህበራዊ ጥያቄ ነው በማለት መለሰ ጥያቄው እንኳን እንደዚህ አልቀረበምአለ ፖርፊሪ ራዙምኪን ወዲያውኑ ተስማምቶና እንደተለመደው ስሜት ወስጥ ገብቶ ልክ ነው እንደዚያ አይደለምካለ በኋላ እንዲህ ሲል ተናገረ አየህ ሮዲ አዳምጥና የምታስበውን ንገረኝ አስተሳሰብህን ማወቅ እፈልጋለሁ ትናንት አንተን እየጠበቅሁ ላሳምናቸው የሚቻለኝን ሁሉ አድርጌአለሁ እንደምትመጣ ነግሬአቸው ነበር ከሶሻሊስቶች አመለካከት አንፃር የተጀመረ ውይይት ነው። የእነርሱ አመለካከት በግልፅ ይታወቃል ወንጀል እኩይና ጤናማ ያልሆኑ ማህበራዊ ሁኔታዎች ላይ የተቃጣ ተቃውሞ ነው እንጂ ሌላ አይደለም ከዚህ የተለዩ መንስኤዎች የሉትም እዚያ ላይ ነው ስህተትህ።» ሁሉንም ነገር የሚገልፁት ከደደብነት አንፃር ብቻ ነው ስለሆነም የሕይወትን ሕያው ሂደት በጣም ይጠሉታል። ሕያው ነፍስ ጥያቄዎችን ያቀርባል በሜካኒክስ ላይ ያሾፋል ተጠራጣሪ ነው የሚዘቅጥ ነው። እነርሱ የሚፈልጉት ነፍስ እንደቋንጣ ሊሸት ይችላል ከላስቲክም ሊሰራ ይችሳላል ቢያንስ ግን ሕያው አይደለም አላማ የለውም አጎብዳጅና ለአመዕ የማይነሳሳ ነው። ሎጂክ ሊያያቸው የሚችል ሶስት እድሎች ቢኖሩም ቁጥራቸው ግን ሚሊዮን ነው። ሚሊዮኑን ወደጎን ትተው ጥያቄውን የምቾት ጥያቄ አድርገው ያቀርቡታል ለችግሩ የቀረበ አቋራጭ መፍትሔ ነው። እንዴት የነበር ይመስልሀልሲል ወደራስኮልኒኮቭ ከዞረ በኋላ ትናንት ማታ እርሱ የመጠጥ አቅርቦት ሳያጓድል በአንድ ክፍል ውስጥ ያሉት ስድስቴም እንደዚያ ሲለፈልፉ ነበር። ወዳጄ ለመሆኑ ለድርሰትህ ገንዘብ ይሰጡህ ነበር። እኔም ስሊዚህ አስተዋፅኦህ አላውቅም ነበር። ቀኑ መቼ ነበር።በማለት ፖርፊሪ መለሰ እንዲህ አይነት ነገር አይፅፍም። ግልፅ እንዳደርግልህ ትፈልጋለህ ብል ምናልባት የተሳሳትኩ አይመስለኝም ለምሳሌ ያህል ግድያና ዝርፊያ ለመፈፀም ማለቴ ነው። ድርሰትህን መረዳቴን ለማረጋገጥ ስል ከዕሁፉ ይዘት አኳያ ያነሳሁት ነጥብ ነው ግልዕና ብልግና ያልተለየው ነውእያለ ራስኮልኒኮቭ አሰሳሰለ ግልፅ ሳደርግልህ እፈልጋለሁ ራሴን ማሆሜት ወይም ናፖሊኦን ወይም እንደዚያ አይነት ሰው አድርጌ አልቆጥርም የምቆጥር ቢሆን ግን እወስደው የነበረው እርምጃ ይህ ነው ራስኮልኒኮቭ በጣም እያሰላሰለና ፖርፊሪ ያጠመደለትን ወጥመድ አውቆ ለማምለጥ እየተጨነቀና እየተጠበበ የምን ቀለም ቀቢ ነው። ይህ ስራ ነገሩን አመሰቃቀለብኝ አለ አየህ በቤቱ ውስጥ ወደሁለት ሰአት ገደማ ሰው አይቷቸው እንደሆን ማወቁ በጣም አስፈላጊ ነው ስለዚያ ልትነግረኝ የምትችል መስሎኝ ነበር ተምታቶብኛል።
አይደለም እንዴ። ቤታችንም እያለን ዳንያና እኔ ከዚያን በፊት ተኝተን አናውቅም እኔም ራሴ እንዴት እንደማመሰግነው አላውቅም ይቅርታ አድርጉልኝና የገንዘብ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር እንዲህ አይነት ልዩ ክትትል ለማግኘት እንዴት እንደበቃሁ ላውቀውም ሆነ ሊገባኝ አልቻለም ከዚሀም የተነሳ ስለሁኔታው ጥሩ ስሜት እንደማይሰማኝ መግለፅ አለብኝ ይሄን የምልህ ሳልደብቅህ ነው ሲል ራስኮልኒኮቭ ግንባሩን ቋጥሮና አቀርቅሮ ተናገረ ዞሲሞቭ ከአንገት በሳይ እየሳቀ ይሄ እንኳን ሊያሳስብህ አይገባም። ሲል ራዙምኪን ጮኸ ራዙምኪን የሰውን ጠባይ የሚያስተውል ዳኛ ቢሆን ኖሮ ጉዳዩ የስሜት ሳይሆን ተቃራኒው እንደሆነ በተገነዘበ ነበር ዳንያ ግን ተገንዝባዋለች ወንድሟንም በጥሞና ትመለከተው ነበር እናቴን በሚመለከት ምን እንደምል ቃላት ያጥሩኛልእያለ በቃል ያጠናውን ትምሀርት የሚደጋግም ይመስል ከተናገረ በኋላ ትናንት ከቤት ስትጠብቂኝ የቱን ያህል ልትጨነቂ እንደምትችይ በመጠኑም ቢሆን የተረዳሁት ዛሬ ነው አለ ይሄን ከተናገረ በኋላ ከዝምታ ጋር ፈገግ በማለት እጁን ወደእህቱ ዘረጋ ግን በአሁኑ ፈገግታ ውስጥ የቅን ስሜት ነፀብራቅ ይታያል ዳንያ ወዲያውኑ እጁን ይዛ ከደስታና ከምስጋና ጋር በስሜት ጨበጠችው ትናንት ከተጣሉ ወዲህ የእርሷን ርዳታ ሲፈልግ የአሁኑ የመጀመሪያ ጊዜ ነበር በሁለቱ ልጆቿ መካከል በቃላት ሊገለፅ በማይቻል ሁኔታ የወረደው እርቅ የእናትየዋን ፊት በደስታ ብዛት እንዲበራ አደረገ ሁሉንም ነገር ማጋነን የሚወደው ራዙምኪን ከርሱ ጠባይ የሚያስደስተኝ ይህ ነው። ደህና አደርሽ ናስታስያ አእምርህ እንደተረበሸ ሐኪሙ ሳያይህ ተደብቀህ እንዳመለጥክና ወደመንገድ ወጥተው እየፈለጉህ እንደሆነ በድንገት ነገረችን ምን አይነት ስሜት እንደተሰማን ልትረዳው አትችልም አንተ ባታስታውሰውም እኛ በሚገባ የምናውቀውና የአባትህ ጓደኛ የነበረው መቶ አለቃ ፖታንቺኮቭ አእምሮው ተረብሾ በተመሳሳይ መንገድ ካመለጠ በኋላ ጉድጓድ ገብቶ በአሰቃቂ ሁኔታ ሞቶ በማግስቱ መገኘቱን አስታወስኩ የአንተን ሁኔታ ደግሞ ከዚህም መቶ ጊዜ የከፋ አድርገን ነበር የቆጠርነው ሊረዳን ይችላል በማለት ሚስተር ሉዚንን ፍለጋ ልንወጣ ነበር ምክንያቱም አየህ የእኔ ልጅ አሁን እንደገና ለመደሰት ብንበቃም በዚያን ጊዜ ግን ብቻችንን ስለነበርን ነው ሰወየውን ፍለጋ የተነሳሳነው ስለሚስተር ሉዚን ማውሳት ጊዜው ገና እንደሆነ በመገመት ሳይታሰብ ንግግሯን አቋረጠች አዎ ይህ ሁሉ በጣም የሚያሳዝን ነው በማለት ራስኮልኒኮቭ እያጉረመረመ መለሰ ሀሳቡ ተሰርቆ በቸልተኝነት የሰጠው መልስ ስለነበር ዳንያ በመገረም ተመለከተችው ሌላ ለማለት የፈለግሁት ምን ነበር። እያለ ራስኮልኒኮቭ በጥንቃቄ መለሰ ይህ የሚታወቅ ክስተት ነው አንዳንድ ጊዜ አንድ እቅድ በረቀቀ ዘዴ ገቢራዊ ይሆንና ድርጊቱን የመቆጣጠር ጉዳይ ግን በተለይ መጀመሪያ ላይ አጠራጣሪና ምትሀታዊ ይሆናል ልክ እንደህልምበማለት ዞሲሞቭ ተናገረ ግሩም ነው ከሞላ ጎደል አብዶአል ብሎ ይገምታልሲል ራስኮልኒኮቭ አለበ ዳንያ ዞሲሞቭን በመረበሽ አይን እየተመለከተች ጤነኛ የሆኑ ብዙ ሰዎችም ተመሳሳይ ደርጊት ይፈፅማሉ አለች ዞሲሞቭ እንዲህ ሲል መለሰ ትክክለኛ ግምት ነው ከዚህ አንፃር ሲታይ አብዛኛውን ጊዜ ብዙዎቻችን የምቆፈፅመው ድርጊት እንደ አብደት የሚቆጠር ነው ልዩነት ቢኖር «እብዶች» ከእኛ እብደታቸው ትንሽ መብለጡ ነው በርግጥ ጤነኛ ሰው አይኖርም ከአስር ሺህ ወይም ከመቶ ሺህ አንድ ቢገኝ ነው እንዲህ አይነቱንም ያልተለመደ ሰው ጆ ብዬ ብጠራው ይሻላል ዞሲሞቭ በንግግሩ ላይ እንደቀልድ ያስገባው «እብድ» የሚለው ቃል በክፍሉ ውስጥ ያለው ሀሉ ግንባሩን እንዲቋጥር አደረገ ራስኮልኒኮቭ ውይይቱን ሳያዳምጥ በሀሳብ ተመስጦና ከንፈሮቹ ያልተለመደ ፈገግታ እያሳዩ ተቀምጦ ነበር የሚያሰላስለው ሌላ ነር ነበረው ሸበክ የዚያ የተገጨው ሰው ጉዳይ ከምን ደረሰ። አለች ዳንያ። ሲል ጠየቀ ዳንያ ወንድሟን በትኩረት ትክ ብላ እየተመለከተች አዎ ደረጃውን ስንወጣ እማዬ ከመረበሺ የተነሳ ታማትብ ነበር እኮ አለች ፊቱ ወዲያውኑ ተለዋወጠ የራስኮልኒኮቭ እናት በጣም ግራ ተጋብታ እንዲህ አለች ዳንያ እንዲህ ማለት የለብሽም ሮዲ እባክህ አትበሳጭ ዳንያ ለምንድነው እንዲህ ያልሽው። ሲል ከመለሰ በኋላ ክፍሌ ዋናው ምክንያት ይመስለኛል እማዬ አሁን ያልሽው የቱን ያህል እንደሚያስገርም ብታውቂ ኖሮበማለት ካልተለመደ ፈገግታ ጋር ተናገረ የሚቀርቡትና ውድ የሆኑ ለሶስት አመት ያላያቸው ሰዎች ስለምንም መናገር አቅቶት በነበረ ጊዜ ከአጠገቡ ሆነው እርሱን ከልብ ማወያየታቸውን ሊቋቋመው አልቻለም ወጣም ወረደ ደግሞ መቋጨት ያለበት አንድ አቢይ ጉዳይ አለ ጥዋት ከአንቅልፉ እንደተነሳ ውሳኔ የሰጠበት ጉዳይ ነው ከዚህ ከማይቋቋመው ሁኔታ የመውጫ ስልት ሆኖ ስላገኘውም ተደሰተ ኮስተርና ነቃ ብሎ እንዲህ ሲል ተናገረ ዳንያ ትናንት በተፈጠረው ሁኔታ ባዝንም ዋናውን ጉዳይ በሚመለከት አቋሜን ያለወጥኩ መሆኔን ለአንቺ የማስታወስ ግዴታ አለብኝ ወይ ሉዚንን ወይ እኔን ምረጪ። አለ ለራሱ የተናገረ ቢመስለውም ድምፁን ጎላ አድርጎ ነበር የተናገረው ግራ እንደተጋባ ሰው ለተወሰነ ጊዜ ያህል እህቱን ማየት ቀጠለ በመጨረሻም የመገረም ስሜት እየተነበበበት ፖስታውን ከፈተ ቀስ ብሎ በጥሞና ማንበብ ጀመረ ሁለት ጊዜ አነበበው እናትየው በጣም ተጨነቀች ሁሉም የተለየ ውጤት ይኖራል ብለው ጠበቁ ጊ ደብዳቤውን ለእናቱ እየመለሰ ማንንም ሳይመለከት የሚያስገርመኝ እኮ ጠበቃ መሆኑ ነው በተለየ ዘይቤ እያስመሰለ ያወራል የሚፅፈው ደግሞ እንደመሃይም ነው አለ ሁሉም እየተቀባበሉ ወቀሳቸውን ኦሰሙ እንዲህ ይላል ብለው ጭራሽ አልጠበቁም ሁሉም እኮ እንደዚያ ነው የሚፅፉትበማለት ራዙምኪን በድንገት ተናገረ አንብበኸዋል እንዴ። የምነግርሽ አለኝ የምትቸኩይ ቢሆን እንኳን ለእኔ ስትይ ጥቂት ደቂቃ መስዋእት አድርጊልኝ አላት ወንበሩን አመቻቸላትና ሶንያ ፍርሀቱና ጭንቀቱ ሳይለቃት እንደገና ተቀመጠች ሁለቱን ሴቶች ፍርሀት ባልተለየው ሁኔታ ፈጥና ተመለከተችና አንገቷን ደፋች የራስኮልኒኮቭ የገረጣ ፊት ፈካ ከመቅፅበት አይኖቹ እሳት እየተፉ አበሩ እማዬ ይህች ልጃገረድ ትናንት በአይኔ ስር በተሽከርካሪ የተገጨውና እኔም አሁን ስነግራችሁ የነበረው ሰው ልጅ ነች በማለት ግልጥ አድርጎ ተናገረ የራስኮልኒኮቭ እናት ሶንያን በሀዘን አይን ተመለከተቻት ዳንያ በወንድሟ የተለየ እይታ ግራ ብትጋባም ምስኪኗን ልጅ በአትኩሮት ገመገመቻት ሶንያ ስለርሷ ሲነገር ቀና አለችና ወዲያውኑ ደግሞ ሀፍረት ይዚት አንገቷን ደፋች ዛሬ ሁሉን ነገር እንዴት እንዳስተካከላችሁት ልጠይቅሽ እፈልጋለሁ ለምሳሌ ያህል ፖሊስ ችግር አልፈጠረባችሁም። እያለ ከመለሰ በኋላ መጀመሪያ ግን አንድ የምሰራው ነገር ይኖራል አለ ራዙምኪን ራስኮልኒኮቭን በመደነቅ እየተመለከተ መቼም እራት ብቻቓህን አትበላም አይደለም እንዴ ሲል ጮኸ። እንዳትቀር እባክህ አለች ዳንያ ራዙምኪን ደስ ብሎት ፈገግ እያለ ጎንበስ ብሎ ግብዣውን ተቀበለ ለትንሽ ጊዜ ሁሉም ዝም አሉ ሮዲ ደህና ሁን። ታዲያ ጊዜ ለምን ይባክናል። የጥቂት ደቂቃ መንገድ ነው እርግጠኛ ነኝ እናገኘዋለንፓሲል ራዙምኪን ባልተለመደ ስሜት ተመስጦ ተናገረ ጥሩ ነው እንሂድ አንተን ማነጋገር በጣም ያስደስተዋል በተለያየ ጊዜ ስለአንተ ብዙ አጫውቼዋለሁ ትናንት እንኳን ሳይቀር እንሂድ። ሲል ራዙምኪን በፍጥነት መለሰ ግን እኔን ለማግኘት ለምን በጣም ይፈልጋል። እያለ ፊቱን አገርጥቶ አሰላሰለ ከዚህ ከግራጫ ቤት ነውሲል ራዙምኪን ተናገረ ዋናው ነጥብ ትናንት ከአሮጊቷ ቤት ሆቬ ስለደሙ መጠየቄን ፖርፊሪ ያውቅ ። እያለ አሰበ በጣም ያፈረ በመምሰል በጣም አዝናለሁሲል ራስኮልኒኮቭ መናገር ጀመረ ፖርፊሪ ሽረ ምንም አይደል አንተን በማግኘቴ በጣም ተደስቻለሁ ወደክፍሉ የገባኸውም ደስ በሚል ሁኔታ ነውካለ በኋላ ወደራዙምኪን እያመለከተ ደህና ነህ እንኳን አይለኝም እንዴ። ሲል ራስኮልኒኮቭ ራሱን ጠየቀ ፖርይሪ እናትህ መጡ እንዴ። እያለ ራዙምኪን ጮኸ ጥሩ ሀሳብ ነው። ተራ የማህበራዊ ጥያቄ ነው በማለት መለሰ ጥያቄው እንኳን እንደዚህ አልቀረበምአለ ፖርፊሪ ራዙምኪን ወዲያውኑ ተስማምቶና እንደተለመደው ስሜት ወስጥ ገብቶ ልክ ነው እንደዚያ አይደለምካለ በኋላ እንዲህ ሲል ተናገረ አየህ ሮዲ አዳምጥና የምታስበውን ንገረኝ አስተሳሰብህን ማወቅ እፈልጋለሁ ትናንት አንተን እየጠበቅሁ ላሳምናቸው የሚቻለኝን ሁሉ አድርጌአለሁ እንደምትመጣ ነግሬአቸው ነበር ከሶሻሊስቶች አመለካከት አንፃር የተጀመረ ውይይት ነው። ሲል ራስኮልኒኮቭ እንደዋዛ ጠየቀው ለምን። እያለ ራዙምኪን በስሜት ተናገረ ድርሰቱ የእኔ መሆኑን እንዴት አወቅህ። ሮዲ ከልብህ አይደለም ነው እንዴ። እያለ ራዙምኪን ጮኸ ። በማለት ከያዘው ጥግ ላይ ሆኖ ዛምያቶቭ ሳይታሰብ አምባረቀ ራስኮልኒኮቭ ቃል አልተነፈሰም ፈርጠምና ኮስተር ብሎ ፖርፊሪን ተመለከተው ራዙምኪን እየተከዘ ተበሳጨ የሆነ ነገር መጠራጠር ከጀመረም ጥቂት ጊዜ አለፈ ትካዜ የተመላበት ዝምታ ለደቂቃ ያህል ሰፈነ ራስኮልኒኮቨ ለመሄድ ሲል ፊቱን አዞረ ፖርፊሪ እጁን በጋለ ስሜት ይዞ በወዳጅነት መንፈስ መሄድህ ነው እንዴ።