Detecting...
Please whitelist dirzon to continue.
ምላሷም ተሳሰረ ምን ጉድ ነው። ምን ፈልጎ ነው። እንዳይሰርቁት ፈርቶ ነው።ሲል ራዙምኪን ኮስተር አድርጎ ተናገረ ራስኮልኒኮቭ ባይፈልግም ሸሚዙን ለወጠለት ራስኮልኒኮቭ ትራሱን ተደግፎ ለደቂቃ ያህል ቃል ሳይተነፍስ ቆዩየ መቼ ነው የሚተውኝ።
ልብሶቹን ገና ማገለባበጥ ከመጀመሩ ከቆዳ ኮቱ ውስጥ የወርቅ ሰአት ዱብ አለ ሁሉንም ነገር መበርበር ጀመረ በርግጥም ከልብሶቹ ውስጥ ይህ ነው የማይባሉ የወርቅ አይነቶች ተዥጎደጎዱ አገዳንዶቹ የመያዣ እቃዎች ገና ተበዳሪዎቹ የተበደሩትን እንደመለሱ ተመላሽ የሚሆኑ ሲሆኑ ሌሎቹ ደግሞ ተበዳሪዎቹ መክፈል አቅቶአቸው የተወረሱ ናቸው የወርቅ አምባሮችቪ ቀለበቶች ጉትቻዎች ሀብሎችና የመሳሰሉት አንዳንዶቹ በማስቀመጫ ሳጥኖች ውስጥ ናቸው ሌሎቹ ደግሞ በጥንቃቄ በጥንድ ጋዜጣ ተጠቅለው የተቋጠሩ ናቸው ጊዜውን ሳያባክን በሱሪውና በኮቱ ኪሶች ውስጥ እንደመጡለት አሮጊቷ ከነበረችበት ክፍል የኮቴ ድምፅ በድንገት ተሰማው ቆሞ ክው ብሎ ቀረ ሀሉም ነገር ግን እረጭ እንዳለ ነበር እርሱ ራሱ የገመተው መሆን አለበት ወዲያውኑ ደግሞ እንደማቃሰት የመሰለ የደከመ ድምፅ ከሰማ በኋላ ለሁለትና ለሶስት ደቂቃ እረጭ አለ መተንፈስ አቅቶት ሳጥኑ ላይ ተንበርክኮ አደፈጠ ከመቅፅበት ግን ዘሎ በእግሩ ቆመና መጥረቢያውን ይዞ ከመኝታ ቤቱ ወጣ በክፍሉ መሀል ለመሀል ሊሳቬታ ቆማለች የሆነ ጥቅል ነገር ይዛ የእህቷን አስከሬን እያየች ደርቃለች እንደበረዶ ከመንጣቷም በላይ ድምፅ ለማሰማት እንኳን አቅም አጥታለች ከመኝታ ቤቱ በጥድፊያ ሲወጣ ባየችው ጊዜ መላ ሰውነቷን ብርክ ያዘው ተንዘፈዘፈች እንደሚረግፍ ቅጠል ተንቀጠቀጠች ፊቷ ተለዋወጠ እጂን በትንሹ ዘርግታ አፏን ከፈተች ድምፅ ግን አላወጣችም አይኗን ከእርሱ ላይ ሳትነቅል ለመጮህ ትንፋሽ ያጣች ይመስል ድምጺን አጥፍታ የኋልዮሽ እያፈገፈገች ወደክፍሉ ጥግ መሄድ ጀመረች መጥረቢያውን እንደያዘ ደረሰባት የሆነ ነገር ሲያስፈራቸው የሚያስፈራቸውን ነገር እያዩ ለማልቀስ እንደሚዘጋጁ ሕፃናት ከንፈሮቿ ተርበተበቱ መጥረቢያውን ከፊቷ ላይ ሲያነጣጥር እጆቿን አንስታ ፊቷን መከላከል በወቅቱ ማድረግ የነበረባት ጉዳይ ቢሆንም ክው ብላ ቀረች ምንም ያልያዘውን ግራ እጂን ትንሽ ብድግ አደረገችና መጥረቢያውን እንዲከላከልላት በቀስታ ዘረጋችው መጥረቢያው በቀጥታ በራስ ቅሏ ላይ አረፈ። ሰንሰለቱን አሳቅቆ በሩን ከፈተና ማዳመጥ ያዘ ቆሞ ለረጅም ጊዜ አዳመጠ ከታች በኩል ምናልባትም ከዋናው በር አጠገብ ሁለት ሰዎች እየተወቃቀሱ ይንጫጫሉ ጉዳዩ ምንድነው። ብሎ አሰበ እንደገና በሩን ዘጋና ድምፁ እስኪያቆም ድረስ ጠበቀ በመጨረሻ ሁሉ ነገ እረጭ አለ ደረጃውን ቁልቁል ሊወርድ ሲል የኮቴ ድምፅ በብዛት ሰማ ይህ ኮቴ ከእርሱ ዘንድ ለመድረስ ገና ብዙ መጓዝ ቢቀረውም የኮቴውን ድምፅ በሰማበት ወቅት የሆነ ሰው ወደ አራተኛ ፎቅ ማለትም ወደ አሮጊቷ ቤት እየመጣ መሇኑን በአንድ አይነት ምክንያት እንደጠረጠረ ከጊዜ በኋላ ሁሉ ያስታውስ ነበር ለምን። ወዲያውኑም ግኡዝ አካል የሆነ መሰለው ከነፍሰ ገዳይ ጋር ተፋጠህ እያለህም ቢሆን መንቀሳቀስ አቅቶህ ከመሬት ላይ ተተክለህና ክንድህን እንኳን ማንሳት ተስኖህ በቀረህበት የህልም አለም ውስጥ የሚደረግ ሆኖ ታየው ሰውየው ወደአራተኛ ፎቅ እንደተቃረበም በሚገርም ፍጥነት ወደአሮጊቷ ቤት ገብቶ በሩን ዘጋና ድምፅ ሳያሰማ በሩን ከብረት ሰንሰለቱ ጋር አያያዘ በደመ ነፍስ ያደረገው እንቅስቃሴ አዝው ከዚህ በኋላ ትንፋሹን ዋጥ አድርጎ ከበሩ ስር አጎነበሰ ከጥቂት ጊዜ በፊት እርሱንና አሮጊቷን በር ለያይቷቸው አድፍጦ ያዳምጥ የነበረበት ሁኔታ ተደገመ በሩ ። በማለት ወጣቱ ተናግሮ በደረጃው ቁልቁል ወረደ ኮች ከበሩ አጠገብ እንደቆመ ነበር መጥሪያውን በዝግታ ተጭኖ ለአንድ ጊዜ የደወል ድምፅ አሰማ ከዚያም እየተመራመረ የበሩን እጀታ መነካካት ጀመረ በሩ በሰንሰለት ብቻ መያያዙን ለማመን ሲል እጄታውን ሳብ አደረገና ለቀቀው ቁና ቁና እየተነፈሰ ጎንበስ ካለ በኋላ በቁልፍ መክተቻው ቀዳዳ በኩል አጮልቆ ማየት ጀመረ ቁልፉ ከውስጥ ተንጠልጥሎ ስለነበር ግን ምንም ማየት አልቻለም ራስኮልኒኮቭ መጥረቢያውን እንደያዘ ተረብሾ ቆሟል ወደውስጥ የሚገቡ ከሆነ ጥቃት ሊሰነዘርባቸው እስከ መዘጋጀት ደርሷል በሩን ኢያንገጫዝጩ ያወሩ በነበረበት ወቅትም ከውስጥ ሆኖ በመጮህ እስፈራርቶ ሊያባርራቸው ፈልጎ ነበር በሩን ለመክፈት በታገለብትም ጊዜ የስድብ ቃላት ሊሰነዝርባቸው ዳድቶት ነበር ከዚህ ሁሉ ቶሎ የመገሳገል ሀሳብ ብልጭ አለበት ህዳቆቋ። አለ ራስኮልኒኮቭ ሰንሰለቱን አላቆ በሩን ገርበብ አደረገ ድምፅ የለም ወዲያውኑም ያለማወላወል ከቤት ወጣ በሩን አጥብቆ ከዘጋ በኋላ ቁልቁል ወረደ ደረጃውን እንዳጋመሰም ከስሩ ካለው ፎቅ ሳያስበው ከፍተኛ ድምዕ ሰማ ራሱን የሚደብቅበት ቦታ ስላጣ መላ ቅጡ ጠፋው ተመልሶ ወደአሮጊቷ ቤት ለመሄድ ከጀለ ከስሩ ካለው ቤት አንተ ድሚትሪ። በማለት ራስኮልኒኮቭ በጎላ ድምፅ ከተናገረ በኋላ የደስታ ስሜት አሞቀው የመዝገብ ቤት ሹሙ ፈገግታ እያሳየ ተመለከታቸው ብስጩው ረዳት ሹም ግራ ተጋባ ን ይሄ የአንተ ጉዳይ አይደለም ስለእዳህ የምታውቀውን በፅሁፍ መልስልን አሳየው እባክህ እያለ ወደመዝገብ ሹሙ በማመልከት በጩኸት ተናገረ ገዳዩ ስለ ምንድነው። ሲል ተናገረ ራስኮልኒኮቭ ሊያስደስታቸው የሚችል የሆነ ነገር ማለት እንዳለበት ተሰማው እስቲ ፈጣሪ ያሳይዎት ሻምበል እኔ የምገኝበት ሁኔታን ለመረዳት አባክዎ ይሞክሩ በንግግሬ አስቀይሜዎ ከሆነ በእኔ በኩል ይቅርታ ለመጠየቅ ዝግጁ ነኝ ድሃ ተማሪ ነኝ ጤና የለኝም ድህነት አድቆኛል በአሁኑ ጊዜ ደግሞ ራሴን ለማኖር ስላልቻልኩ ትምህርቴን አቋርጫለሁ በቅርቡ ገንዘብ ይኖረኛል ገጠር ያሉት እናትና እህቴ ገንዘብ ሲልኩልኝ እዳዬን እከፍላለሁ ቤት ያከራየችኝ ሴት ደግ ነች። ይህ እኛን አይመለከትም ሲል የመዝገብ ቤት ሹሙ አጉረመረመ ራስኮልኒኮቭ ወደመዝገብ ቤት ሹሙ ሳይሆን ወደአዛዢ እንዲሁም ለይስሙላ ወረቀት ወደሚያገላብጠውና ቅር በመሰኘቱ አስተውሎት ወደነፈገው ረዳት ሹም እያመለከተ መናገሩን እንዲህ በማለት ቀጠለ የመዝገብ ቤት ሹሙ የሚለው ትክክል ቢሆንም ሁኔታውን እኔም ልግለፀው ቤቱን ተከራይቼ መኖር የጀመርኩት ከገጠር ከመጣሁ ጊዜ አንስቶ ነው ሶስት አመት አልፎኛል ሁሉንም ፍርጥርጥ አድርጌ ሳውጋችሁ ገና ከመነሻው ልጂን ላገባ ቃል ገብቼ ነበር በቃል ደረጃ እንጂ የገባሁት ግዴታ አልነበረም ልጃገረድ ። ሲል ጨዋነት በጎደለው መልክ ጠየቀ እኔ እየነገርኩህ ትፅፋለህ የኑዛዜ ያህል ከተናገረ በኋላ የመዝገብ ቤት ሹሙ ለእርሱ ያሳየው ዝንባሌ ቅር የሚያሰኝና ሀላፊነት የጎደለው መስሎ ታየው ወዲያውኑ ከአንድ ደቂቃ ባነሰ ጊዜ ውስጥ ማንም ለሚናገረው ቁብ ያለመስጠት ስሜት አደረበት ሁኔታውን በጥሞና ቢያስተውለው ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት እንደዚህ ለማነጋገርና ለማሳመን በቅቶ ቢሆን ኖሮ ምንኛ በተደነቀ አሁን ይህ ስሜት ከየት መጣ። በዚያን ወቅት ተቃጥሎ እንዲሞት ቢፈረድበት እንኳን ጉዳዩ አልነበረም የፍርዱን ውሳኔ እንኳን ባላዳመጠም ነበር አዲስና ቅፅበታዊ የሆነ ያልተለመደ ነገር ከዚህ በፊት ደርሶበት የማያውቀው ነገር አሁን ገጠመው ከአንድ ደቂቃ በፊት ከፖሊስ ጣቢያ የነበሩትን ሰዎች ባነጋገረበት ሁኔታ በድጋሚ እንደማያነጋግራቸው በዚያን ጊዜ እንኪን በፖሊስ መኮንኖች ፋንታ የራሱ ወንድሞችና እህቶች አነጋግረውት ቢሆን ኖሮ ቃል እንደማይተነፍስሳቸው ተሰማው እንዲህ አይነት እንግዳና አስፈሪ ነገር ከዚህ በፊት ገጥሞት አያውቅም ነበር ከሁሉም አስከፊ የሚያደርገው ደግሞ የተቀነባበረ ሀሳብ ሳይሆን በህዋሳት ውስጥ የሚሰራጭ ስሜት መሆኑ ነበር ከዚህ ቀደም በሕይወቱ የማያውቀው ስሜት የመዝገብ ቤት ሹሙ የተለመዱን የማስፈራሪያ ቃላት እንዲዕፍ ይነግረው ጀመር ። ሲል ረዳት ሹሙ በልዩ ድምዕ ተናገረ አዛዢ ንግግሩን ሊቀጥል ነበር ራስኮልኒኮቭን በአትኩሮት ይመለከት የነበረውን የመዝገብ ቤት ሹም እንዳየ ግን ከመናገር ታቀበ ሁሉም ሰው ድምፁን አጠፋ ያልተለመደ ሁኔታ ነበር ረዳት ሹሙ ከእንግዲህ ጣቢያ አናቆይህምበማለት ለጉዳዩ እልባት ሰጠ ራስኮልኒኮቭ ከቢሮው ወጣ የአዛዢዣ ድምፅ ከሌላው ጎልቶ ቢሰማውም ሁሉም በጋለ ሁኔታ ወዲያውኑ መናገር እንደጀመሩ ይሰማው ነበር መንገዱን እንደተያያዘም ሙሉ በሙሉ ነፍሱ ተመለሰ አሰሳ አሁኑኑ አሰሳ ይኖራል። ሲል አጉረመረመ ናስታስያ አሁንም በዝምታ ማየቷን ቀጠለች እመቤቴን ማንም አልደበደባትምእያለች ኮስተር ብላ እቅጩን ተናገረች ትንፋሹን ውጦ ትክ ብሎ ተመለከታት ሁሉንም ሰምቻለሁ አልተኛሁም ተቀምጩ ነበር ለረጅም ጊዜ ነው ያዳመጥኩት ረዳት የፖሊስ ሹሙ ከዚህ ነበር ሰው ሁሉ ከየቤቱ እየወጣ ደረጃው ላይ ነበርሲል ይብስ እየፈራ ተናገረ ከዚህ ማንም አልነበረም በውስጥህ ያለው ደም ሲዘዋወር ያወጣው ድምፅ ነው ደም ገፍትሮ መውጣት ሲያቅተው ሁልጊዜ ድምዕ ያወጣና ገብትህ ውስጥ መርጋት ይጀምራል። ይሁንና በሚታመምበት ጊዜ ሁሉ ህሊናውን በጠቅላሳ አይስትም እያተኮሰውና እየቃ ህሊናውን በከፊል ይስታል ከዚያ በኋላ የሚያስታውሳቸው ብዙ ነገሮች ይኖሪሉ አንዳንድ ጊዜ ክፍሉ ሊያዙትና ወደሌላ ቦታ ሊወስዱት በሚፈልጉ ሰዎች የተጨናነቀ ይመስለዋል ከዚያ በኋላ በክፍሉ ውስጥ ብቻውን ይቀራል ሁሉም ጥሎት ይሄዳል ሁሉንም ያስፈራራል አልፎ አልፎ ብቻ በሩን ከፈት እያደረጉ ያዩታል ስጋት ላይ ይጥሉታል በጋራ ሆነው ሴራ ያውጠነጥነበታል ይስቁበታል ይሳለቁበታል ብዙውን ጊዜ ናስታስያ ከአጠዝቡ እንደሆነች ያስታውሳል በጣም የሚያውቀውን ሌላ ሰው የሚያይ ይመስለዋል ሰውየው ማን እንደሆነ ግን የቱን ያህል እንኪን ቢሞክር ይጠፋበታል ይህ ሁኔታ ደግሞ ክፉኛ እያሳዘነው እስከመጮህ ይደርሳል አንዳንድ ጊዜ ወሩን ሙሉ አልጋ ሳይ የተኛ ይመስለዋል በሌላ ጊዜ ደግሞ ቀኑ ያልተለወጠ ያው ይመስለዋል። ራስኮልኒኮቭ ቀና ብሎ ወደ ወጣቱ ሰው እያመለከተ ናስታስያ ምን የሚሉት ሰው ነው። በዚያው ሰአት ግን በሩ እንደገና ተከፈተ ራዙምኪን ረጅም በመሆኑ ትንሽ ቆም አለና ከአንገቱ ጎንበስ ብሎ ወደክፍሉ ገባ እንደገባም ምን አይነት ቤት ነው። በደህናው ጊዜ እንኳን ይህ አይነቱ ሁኔታ ያጋጥመዋል አንተ የተማርክ ሰው ነህ እጁን ደረሰኙ ላይ ካደረግንለት ይፈርማል በቃ እንደዚህ እናርግ በማለት ራዙምኪን ከመስሪያ ቤት ለመጣው ሰው ተናገረ ሌላ ጊዜ ልመጣ እችላለሁ ለምን እናስቸግርሀለን። ይሁን እሺ ቅጂው ወይም እኔ ራሴ እቀዳዋለሁ ወደ ጠረጴዛው ሄደሽ ተቀመጪ ወዲያውኑም ሁሉን ነገር አቀራረበ አንድ ስኒ ቫይ ከቀዳ በኋሳ ሌላም ደገመ ምሳውን ትቶ እንደገና ከፎቴው ላይ ተቀመጠ እንደበፊቱ ሁሉ ግራ እጁን ከራስኮልኒኮቭ ትከሻ ላይ ጣል አድርጎ ቀና አደረገው በማንኪያ ሳይ ያደረገውን ሻይ በትንፋሹ እያበረደ ሰጠው ሻዩን ያለማቋረጥ በልዩ ዘዴ ነበር እንዲበርድ ያደረገው የእርሱ ትንፋሽ ጓደኛውን ከሕመም የሚፈውስ ይመስል ራስኮልኒኮቭ ያለማንም ርዳታ ከፎቴው ላይ ተቀምጦ ስኒና ማንኪያ ለመያዝ ብቻ ሳይሆን ተነስቶ በእግሩ ለመሄድ አቅሙ እንዳለው ቢሰማውም ትንፍሽ አላለም ወይም አላንገራገረም ይሁንና ያልተለመደ ብልጠት ስለያዘው ለጊዜውም ቢሆን አቅሙን በመደበቅ ድምፁን በማጥፋትና ከአስፈለገም አእምሮው ገና እንዳልተመለሰለት አድርጎ በመቅረብ ስለነበረው ሁኔታ ማሰላሰል የሚበጅ መስሎ ታየው ግን ብስክስክ የማለት ባህሪን ማስቀረት አቃተው ጥቂት ማንኪያ ሻይ ከጠጣ በኋላ በድንገት አእምሮውን ልቅ አደረገ ማንኪያውን በመንገሽገሽ ከአጠገቡ አራቀ እንደገና ትራሱን ይዞ ተኛ በአሁኑ ሰአት ጭንቅላቱን ያስደገፈው በንፁሕ ከረጢት ውስጥ ባለ ለስላሳ ትራስ እንደነበርም አስተዋለ ራዙምኪን ወደቦታው ተመልሶ ሾርባውንና ቅቅል ስጋውን እየተመገበ የሚያተኩስ ጭማቂ እንድናዘጋጅለት ጋሼቬንካ ዛሬ እንጆሪ ልትሰጠን ይገባል አለ ናስታስያ የስኒ ማስቀመጫውን በእጂ ይዛ ቫይዋን እየጠጣች እንጆሪ ከት ታመጣልሀለች። የመዝገብ ቤት ሹሙ። ለምን። እያለ ራስኮልኒኮቭ በፍጥነት ዞር ብሎ በራዙምኪን ላይ አፈጠጠ ጉዳዩ ምንድነው። ምንድነው። ይህ ምንድነው። ጭራሽ አልታመምከኩም ራዙምኪን ከአዚህ ለምን ያህል ጊዜ ነበርክ። አለች ናስታስያ ለምን ልክ አይሆንም። ራስኮልኒኮቭ ለረጅም ጊዜ በትካዜ ዝም ብሎ ከቆየ በኋላ አሁን አስታወስኩ አለ ራዙምኪን ፊቱን ቅጭም አድርጎ ተመለከተው በሩ ተከፈተና ገዕታው ለራስኮልኒኮቭ አዲስ ያልሆነ ረጅም ወፍራም ሰው ገባ ዋማታ ማታ ዞሲሞቭ መጣ።