Detecting...
Please whitelist dirzon to continue.
ስቪድሪጋሎቭ ተቀመጠና ሶንያ ከአጠገቡ እንድትቀመጥ ጠየቃት ፈራ ተባ እያለች ልታዳምጠው ተዘጋጀች ወደአሜሪካ ስለምሄድ የዛሬው ግንኙነታችን የመጨረሻ ሊሆን ይችላል የመጣሁት አንዳንድ ነገሮችን ለማስተካከል ነው ዛሬ ያቺን ሴት አግኝተሻት ነበር። አረቦን ያመጣሁልሽ መሆኑ ነው። ባልና ሚስቱ የወደፊት እቅድ እያወጡ ሁኔታዎችን አመቻችተው ወደሳይቤሪያ ለመጓዝ ወሰኑ እስከዚያው ድረስ ግን ተስፋቸውን በሶንያ ላይ ጣሉ የራስኮልኒኮቭ እናት የዳንያንና የራዙምኪንን ጋብቻ በማየቷ ብትደሰትም ከጋብቻው በኋላ ይባስ እየተከፋች ሄደች ራዙምኪን አማቱን ለማበረታታት በማሰብ ስለተማሪውና አካል ጉዳተኛ ስለሆነው አባቱ ከአንድ አመታት በፊት ሁለት ሕፃናትን ራስኮልኒኮቭ እንዴት ከእሳት ቃጠሎ እንዳዳናቸውና ራሱ በቃጠሉው እንደተጎዳ ይነግራት ነበር። የጭንቅላት ወባ ነበር በሽታዋ። እንዲያውም በስራ መድከሙ የጥቂት ሰአት የሰላም እንቅልፍ ስለሚለግሰው ተደስቶበታል የምግቡስ ሁኔታ ለእርሱ ምኑ ነው። ከማን ፊት ይቀርብና ነው የሚያሳፍረው። ሶንያ እየተሸሽቆጠቆጠችለት እንዴት ያፍራታል። ማፈር ግን እንዴት ይነሰው። ተሰቃይቶ ቢያነባ ኖሮ በእርግጥም ትክክለኛ ሕይወት መምራትጀምሯል ማለት ነበር። ወንጀል ስለሆነ ነው። ወንጀል ምን ማለት ነው። ሁሉም ነገር የፈፀመው ወንጀልና የተወሰነበት ቅጣት ሳይቀር የማያውቀው እንግዳ ነገር መስሎ ታየው ይሁንና ያለማቋረጥ ለረጅም ጊዜ ለማሰብ ወይም በተወሰነ ነገር ላይ ለማተኮር በዚያን ምሽት አልቻለም ከዚህም በተጨማሪ ረጋ ብሎ ችግሮቹን በሚፈታበት ደረጃ ላይ ሳይሆን ስሜቱ ብቻ ነበር የናኘው። ሕይወት የለውጥ ሂደትን ተከትላ የተለየ ነገር በአእምርው ውስጥ በሕሊናው ነበረች ከትራሱ ስር የተቀመጠውን የአዲስ ኪዳን መፅሐፉን እንዲያነብ ጠይቃው አታውቅም ይሁን እንጂ ከመታመሙ በፊት እንድታመጣለት የጠየቃት እርሱ ራሱ ነበር። የሚል ሀሳብ በአእምሮው ተመላለሰ በዚያን እለት እርሷም ቢሆን ተረብሻ ከዋለች በኋላ ምሽት ላይ እንደገና ታመመች ይሁንና ከልክ በላይ ተደሰተች የቀራት ሰባት አመት ብቻ ነው።
አረቦን ያመጣሁልሽ መሆኑ ነው ወስደሽ እንደፈለግሽ ተጠቀሚበት ማንም ማወቅ ስለሊለበት የሁለታችን ብቻ ምስጢር ነው ተወዳ ሶንያ አሁን በያዝሽው አስቀያሚ ኑሮ ለመቀጠል ከእንግዲህ ምክንያት ስለማይኖርሽ ገንዘቡ ያስፈልግሻል ለእኔ ለሕፃናቱና ለእንጀራ እናቴ ብዙ አድርዝልናል በሚገባ ላመሰግንህ እንኳን እድሉን አላገኘሁም ነበር ይሄን ገንዘብ ለእኔ ለመስጠት በመፍቀድህ ምስጋናዬ የላቀ ቢሆንም ለጊዜው አያስፈልገኝም ምንጊዜም በራሴ መኖር ስለምችል የአንተን እርዳታ መናቅ አድርገዝሀ ጭራሽ እንዳትቆጥርብኝ ለጋስ እስከሆንክ ድርስ ገንዘቡን ይሄ ገንዘብ ለአንቺ ነው ጥድፊያ ላይ ስለሆንኩ ጊዜ አናባክን ያስፈልግሻል ራስኮልኒኮቭ ወይ ራሱን በሽጉጥ ይገድሳል አሊያም ወደሳይቤርያ ይጓዛል ሶንያ አፍጥጣ ተመለከተችውና ተርበተበተች አይዞሽ ሁሉንም ነገር አውቀዋለሁ እርሱ ራሱ ነው የነገረኝ እኔ ወንፊት አይደለሁም ለማንም አልናገር እጁን እንዲሰጥና ራሱን እንዲያጋልጥ በዚያን ምሽት የነገርሽው ትክክል ነው። በነገራችን ላይ ይህች ሴት በቀጥታ መጠየቅ ያዳግታታል ፈገገ እያለችና እጆቿን እያሻሸች ትጀምርና ለየት ያለ ዘዴ ትጠቀማለች ለምሳሌ ያህል ስቪድሪጋሎሉቭ ጋብቻውን መቼ ለመፈፀም እንዳሰበ ለማወቅ ከፈለገች ስለፓሪስና ስለፈረንሳይ ቤተመንግስት የሚያጓጉ ጥያቄዎችን ከአቀረበች በኋላ ወደራሷ ጉዳይ ትሸጋገራለች ይህ አቀራረቧ በሌላ ጊዜ ከበሬታን ያተረፈላት ቢሆንም በዚያን እለት ግን ገና እንደገባ እጮኛው መተኛቷ ሲነገረው ስቪድሪጋሎቭ ባልተለመደ ሁኔታ ተበሳጨና እጮኛውን ማነጋገር እንዳለበት አጥብቆ ጠየቀ ወጣቷም ብቅ አለች ለከፍተኛ ስራ ጉዳይ ለጊዜው ፒተርስቡግን ስለሚለቅ አስራ አምስት ሺህ ሩብል እንዳመጣላት ነገራት ከሠርጋቸው በፊት እንዲህ አይነት አነስተኛ ገንዘብ ሊሰጣት ቀደም ብሎ ማሰቡን በመግለፅ ስጦታውን እንድትቀበለው ጠየቃት ስጦታው የእርሱ ፒተርስቡርግን መልቀቅና በዝናብ እየበሰበሰ በእኩለ ሌሊት መምጣት እርስ በርስ የሚያገናኛቸው ነገር ባይኖርም ድርጊቱ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቀ በሁኔታው የመገረሙ ገፅታ ወዲያውኑ ተለወጠና በእናትየዋ እንባ የተጠናከረ ምስጋና ተዥጎደጎደለት ስቪድሪጋሎቭ ከመቀመጫው ተነስቶ ሳቀና አጮኛውን ሳመ ጉንጪን አሻሸ በቶሎ እንደሚመለስ በድጋሚ ገለፀ የልጅነት ጉጉት ብቻ ሳይሆን ቅዝዝ ብሎ የመመራመር ሁኔታ ከአይኗ ላይ አነበበና ትንሽ አሰብ አድርጎ በድጋሚ ሳማት ወዲያውኑ ደግሞ ያበረከተው ስጦታ በጠንቃቃዋ እናት እጅ ገብቶ በሳጥን ይቆለፍበታል የሚል ስሜት መጣበትና ተከዘ በልዩ ስሜት ውስጥ ከተታቸውና ሄደ እናትየዋ ግን ስቪድሪጋሎቭ ትልቅ ቦታ ያለው ታዋቂ የስራ ሰውና በጣም ሀብታም እንደሆነ በአእምሮው የሚያስበውን ማንም እንደማያውቅ በከፊል ሹክሹክታ ፈጥና ተናገረችና የጉብኝቱን አንቆቅልሽ ፈታችው ፒተርስቡርግን የመልቀቅ ሀሳብ በአእምሮው መጣና ፒተርስቡርግን ይኸው ለቀቀ ለሆነ ሰው ገንዘብ ለመስጠት አሰበና ይኸው ሰጠ ስለዚህ ምንም አያስገርምም በዝናብ መበስበሱ ቢያስገርምም ለምሳሌ ያህል እንግሊዞች ከዚህ የበለጠ ያልተለመደ ነገር ይፈፅማሉ ከዚህ በላይ ደግሞ ብዙ ያዩ ሰዎች ለሰው ደንታም የላቸው ወግም አያጠብቁ ምናልባትም እንዲህ ያደረገው ማንንም እንደማይፈራ ለማሳየት ሆነ ብሎ ይሆናል ሆኖምየአሁኑ አድራጎቱ መዘዝ ማስከተል አለማስከተሉ ስለማይታወቅ ለማንም መናገር እንደሌለባቸው አስታወሱና ሌላ ሰው ባለመኖሩ አምላካቸውን አመሰገኑ እስከ ሌሊቱ ስምንት ሰአት ድረስ ሲያንሾካሽኩ ቆዩ። ዝናቡ ቢያባራም የሌሊቱ ንፋስ ይጋረፋል መንቀጥቀጥ ጀመረና የኔቫን ወንዝ ለደቂቃ ያህል በመገረም ተመለከተ ከድልድዩ ሳይ ብርዱን ስሳልቻለው ተመልሶ ወደአደባባዩ አቀና ረጅሙን አደባባይ ይዞ በጨለማው እየተደናበረ ለግማሽ ሰአት ያህል ተጓዘና ከሰሞኑ በጋሪ ተሳፍሮ ሲሄድ አስተውሎት ከነበረው ሆቴል ደረሰ ከከተማ ርቆ በሚገኝ ስፍራ ሳይ ጉብ ያለው ሆቴል በጨለማ እንኳን የማያሳስት ነበር ፅዳቱን ያልጠበቀና ከእንጨት የተሰራ ረጅም ሕንፃ ነው በዚያን ሰአት እንኳን ጭልጭል የሚል ብርሀንና አንዳንድ ሰዎች ይታዩበታል ወደሆቴሉ ገባና ልብሱ የነተበውን አስተናጋጅ ክፍል ይኖር እንደሆን ጠየቀ አስተናጋጁም ስቪድሪጋሎቭን ከተመለከተ በኋላ ራሱን በመነቅነቅ የአዎንታ መልስ ሰጥቶ በጥግ በኩል ወዳለች ጠባብና የታመቀች ክፍል ወሰደው ሁሉም ክፍል በመያዙ ሌላ አልነበረም አስተናጋጁ ለመታዘዝ ዝግጁ ሆኖ ተመለከተው ሻይ ይኖራል። ዝናብ የጠገበ ትልቅ ዛፍ መርጩ ገና ደገፍ እንዳልኩት ጭንቅላቴን ሻማውን እንደያዘ ልብሱ የነተበውንና ይሄን ጊዜ በአንዱ ጥግ ተኝቶ የሚሆነውን አስተናጋጅ ፍለጋ ወደኮሪደሩ አቀና ሂሳቡን ከፍሎ ለመሄድ ከዚህ የተሻለ አመቺ ጊዜ እንደሌለ ገመተ በጠባቡ ኮሪዶር ላይ ማንንም ሳያገኝ በብዛት ስለተመሳለሰ አስተናጋጁን ለመጥራት ገና ከማሰቡ በቁምሳጥንና በበር መካከል ሕይወት ያለው የሚመስል ነገር ሲንቀሳቀስ ተመለከተ ሻማውን እንደያዘ ጎንበስ ሲል እየተንቀጠቀጠች የምታለቅስና ልብሷ በዝናብ የራሰ የአምስት አመት ሕፃን አገኘ ስቪድሪጋሎቭን የፈራች አትመስልም እንዲያውም ተገርማ በትላልቅ ጥቁር አይኖቿ ትክ ብሳ ተመለከተችው ሕፃናት ለረጅም ጊዜ በልቅሶ ከተንፈቀፈቁ በኋላ እንደሚያደርጉት ሁሉ ዝም ብላ ትቆይና እንደገና ለቅሶዋን ታቀልጠዋለች ፊቷ ገርጥቷል ብርዱ ያዳከማት ይመስላል እንዴት ከዚህ ተገኘች። የምፈልገው ስፍራ ነው ቢያንስ ከዚህ ስፍራ እማኝ ይኖራል እያለ አሰላሰሰ እንደዚያ በማሰቡ ፈገግ እንደማለት አለና ወደማማው ተቃረበ ግራጫ የወታደር ኮት የለበሰና የብረት ቆብ ያጠለቀ አጭር ሰው የተዘጉትን የግቢውን በሮች ተደግፎ ቆሟል ስቪድሪጋሎቭን በቸልታ ተመለከተው ሰውየው የመላው አይሁዶች መለያ ባህሪ የሆነ ቁጠና ኮስታራ ፊት ያለው ነው ሁለቴም ለተወሰነ ጊዜ በዝምታ ተያዩ በመጨረሻም ያልሰከረ ሰው ቃል ሳይተነፍስ ከአጠዝቡ ያን ያህል ጊዜ መቆሙ አግባብ ስላልመሰለው ከቦታው ሳይነቃነቅ ምን ፈልዝህ ነው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ብቻዬን ትታኝ ትወጣለች ይባርከውና ራዙምኪን እየመጣ ያጫውተኛል ስለሚወድህና ስለሚያከብርሁ ሁልጊዜ ስለአንተ ያወራል እንዲያም ሆኖ እህትህ ጣል ጣል ያደረገችኝ መስሎ እንዲታይህ አልፈልግም የእራሷ መንገድ አላት እኔም የራሴ መንገድ አለኝ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የያዘችው ምስጢር ያለ ይመስላል እኔ ግን ከሁለታችሁ የምሸሸገው ምስጢር የለኝም ዳንያ በጣም ጎበዝ ከመሆኗም በላይ አንተንም ሆነ እኔን እንደምትወደን እርግጠኛ ነኝ ውጤቱ ግን ምን እንደሚሆን አላውቅም ሮዲ እኔን ለመጠየቅ በመምጣትህ አስደስተኸኛል ይሁንና እህትህ ናፍቃሃለች በምትመጣ ጊዜ እርሷ እየዞረች ከተማውን ስታካልል ወንድሟ ከዚህ እንደነበር እነግራታለሁ ለእኔ በጣም አታስብ በቻልክ ጊዜ ብቅ በል ካልቻልክ ደግሞ ምንም ማድረግ እንደማይቻል እገምታለሁ እንደምትወደኝ ስለማውቅ ባትመጣም እጠባበቅሀለሁ ፅሀፎችህን አነባለሁ ስለአንተ ወሬ ከየሰው እሰማለሁ አልፎ አልፎም አንተ ራስህ እኔን ለመጠየቅ ትመጣለህ ሌላ ምን የተሻለ አማራጭ ይኖራል። የፈለገው ሰው ቢሆን እኔ አላምነውም ከቤቴ ውጣልኝ ነው የምለው ቅላፄውን ሳይቀይር ንግግሩን ቀጠለ ምንጊዜም እወድሽ እንደነበር ልገልዕልሸ ነው የመጣሁት ብቻችንን መሆናችንና ዳንያ እንኳን አለመኖሯ አስደስቶኛል አንቺን ላያስደስትሽ ቢችልም በአሁኑ ሰአት ልጅሽ ከራሱ በሳይ እንደሚወድሽ በግልፅ ልነግርሽ ስለፈለግሁ ነው የመጣሁት እኔ ጨካኝና አንቺን የማልወድ አድርገሽ የገመትሽው ሁሉ ትክክል አይደለም እስከመጨረሻው ድረስ እንደምወድሽ መንገር አለብኝ የራስኮልኒኮቭ እናት ድምጺን አጥፍታ በመጠኑ እያለቀሰች ወደ ደረቷ አስጠግታ እቅፍ አደረገችው ሮዲ ምን እንደነካህ አላውቅም እኛ ያስቀየምንህ አድርጌ ነበር እስከዛሬ የማስበው አሁን ግን ከፍተኛ ችግር ላይ እንደወደቅህና ደስተኛም ያልሆንከው በዚሀ ምክንያት እንደሆነ እገነዘባለሁ ከታየኝ እኮ ቆይቿል ልጄ ይሄን በማለቴ አዝናለሁ ቢሆንም ግን ሁል ጊዜ እያሰብኩ እንቅልፍ በአይኔ ሳይዞር ነው የማድረው ትናንት ሌሊት እህትህ እንቅልፍ ሳታይ እንዲሁ ስትገላበጥ ነው ያነጋችው አተኩሷት ያለማቋረጥ ስለአንተ ታወራ ነበር ባይገባኝም ቅሉ የሆነ ነገር ሰምቻለሁ ልጄ የዛሬውን ጧት ያሳለፍኩት በከፍተኛ ስቃይ ነው የሆነ ነገር እንደሚገጥመኝ እየተሰማኝ ነው ያሳለፍኩት ይኸውና ደረሰ ሮዲ ወዴት ነው የምትሄደው። እቅፍ አድርገህ ሳምከኝ አባትህ በሕይወት በነበረ ጊዜ እንዲህ አይነቱ ቀውጢ ጊዜ ሲገጥመን ከእኛ ጋር ሆነህ ታዕናናን ነበር አባትህ ከሞተ በኋላም እንደአሁኑ ተቃቅፈን ከመቃብሩ ላይ ስንት ጊዜ አልቅሰናል አሁን የማለቅሰው ችግር እንደደረሰብህ የእናትነት ልቤ ስላመላከተኝ ነው ታስታውስ እንደሆን ከዚህ ከተማ እንደደረስን ገና በዚያን ምሽት ለመጀመሪያ ጊዜ እንዳየሁህ ገፅታህን አይቼ ሁሉንም ነገር ስለገመትኩ ልቤ በፍርሀት ተጨማደደ ዛሬ በሩን ከፍቼልህ ገና እንደተመለከትኩህ የማለቅስበት ሰአት እንደተቃረበ ወዲያውኑ ገመትኩ ሮዲ አሁኑኑ መሄድህ ነው። ምን አይነት ወንጀል። ከትናንት ምሸት ጀምሮ ይሄን ጥያቄ አንስቶ ምናልባት ለመቶ ጊዜ ያህል ራሱን ቢጠይቅም ጉዞውን ቀጠለ ከሶንያ ክፍል ሲደርስ ጨልሞ ነበር ሁሉንም ነገር ስቪድሪጋሎቭ የነገራትን አስታውሳ ሶንያ ታውቀዋለች በማለት ገና በጧቱ ከመጣችው ዳንያ ጋር ሆና ሶንያ ትጠብቀው ነበር የሁለቱን ልጃገረዶች ውይይት ያፈሰሱትን እንባ የመወዳጀታቸውን ደረጃ ባናነሳው ይሻሳል። ዳንያ ከዚያን እለት ውይይታቸው ወንድሟ ብቻውን እንደማይሆን ቢያንስ አንድ ማዕናኛ አግኝታለች ራሱን ለመጀመሪያ ጊዜ ያጋለጠው ለሶንያ ነው አብሮ የሚሆን ሰው ባስፈለገው ጊዜ ያገኘው የሶንያን ሰብእና ነው ስለሆነም በሄደበት ቦታ ሁሉ ትከተለዋለች ዳንያ ይሄን ለማወቅ መጠየቅም አላስፈለጋት የሀፍረት ስሜት እስኪሰማት ድረስ ሶንያን ከከፍተኛ ከበሬታ ጋር ቀረበቻት ሶንያ ደግሞ በአንፃሩ ሌላው ቀርቶ ዳንያን ለማየት እንኳን የማትበቃ አድርጋ ራሷን ስለቆጠረች በዳንያ አድራጎት አንጀቷ ተንሰፈሰፈ በራስኮልኒኮቭ ክፍል ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ በተገናኙ እለት ዳንያ በአክብሮት የሰጠቻት ሰላምታ ውብና ድንቅ ትዝታ ሆኖ መቼም ላይጠፋ በአእምሮዋ ውስጥ ተቀርጸል። አንድ ላይ በነበሩ ጊዜ ግን የየራሳቸውን ምክንያት እየደረደሩ አያደርገውም ብለው ገመቱ ይሁንና ወዲያውኑ እንደተለያዩ ሁለቱም ስጋት ሳይ ወደቁ ራስኮልኒኮቭ ያለው ምርጫ ሁለት ነው ወደሳይቤሪያ መጋዝ ወይም ደግሞ ራሱን ማጥፋት በማለት ስቪድሪጋሉቭ የነገራትን አስታውሳ ወኔ ቢስነትና ሞትን መፍራት ብቻ ናቸው ራሱን እንዳይገድል የሚያደርጉት ብላ አሰላሰለች ዞሮ ዞሮ ጀንበሯ እየጠለቀች ሄደች ከመስኮቱ አጠገብ በትካዜ ቆማ ውጭውን በትኩረት ተመለከተች ግን ከፊት ለፊቷ ካለው ኖራ ካልተቀባ ግድግዳ በስተቀር ምንም ነገር አላየችም በመጨረሻም ይህ የተከፋ ሰው ራሱን ገድሏል ከሚል እምነት ላይ እንደደረሰች ወደክፍሏ ዘልቆ ገባ የደስታ ጩኸት ብታሰማም ትክ ብላ ተመለከተችውና በአንድ ጊዜ ገረጣች ሶንያ መስቀልሽን ፈልጌ ነው የመጣሁት ወደመስቀልኛ መንገድ እንድሄድ አንቺው ራስሽ ከነገርሽኝ በኋላ አሁን ጊዜው ሲደርስ ምን ያስፈራሻል። በዚያች ቅፅበት ሶንያ በሄደበት ቦታ ሁሉ እስከመቃብር ድረስ እንደማትለየው ተረዳ ስሜቱ ቢነካም ከአሰበው ቦታ ደረሰ ተፍ ተፍ እያለ ወደቅጥር ግቢው ዘለቀ ከሶስተኛው ፎቅ መድረስ ነበረበት ፎቁን መውጣቱ ጉዳት የለውም ብሎ አሰበ የሞትን ፅዋ የመጨለጫው ሰአት እንዳልደረሰና በቂ ጊዜ እንዳለው በመካከሉም አውጥቶና አውርዶ ሀሳቡን ሊለውጥ እንደሚችል ገመተ አሁንም ያው ቆሻሻ በየደረጃው የተዝረከረከው ያው የእንቁላል ቅርፊት ክፍታቸውን የዋሉት እነዚያው በሮች እነዚያው በጭስ የታፈኑትና የሚከረፉት ወጥ ቤቶች እንዳሉ ናቸው ራስኮልኒኮቭ ከዚያን እለት ወዲህ ከዚህ ስፍራ አልደረሰም እግሮቹ ቢሽመደመዱም ገዞውን ቀጠለ ትንፋሹ እንዲመለስለት እንዲረጋጋና ሰው መስሎ ወደቢሮ እንዲገባ በማሰብ ለትንሽ ጊዜ ቆመ ለምን እንደቆመ ተገነዘበና ለምንድነው የቆምኩት። ሌላው ደግሞ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተበራከቱት ራሳቸውን የሚገድሉ ሰዎች ጉዳይ ነው ጎረምሳው ልጃገረዷና ሽማግሌው ሀሉ ገንዘቡን እየረጨ ይጨርስና ሽጉጡን ጠጥቶ ይሞታል ዛሬ ጧት እንኳን አጋጥሞናል በቅርቡ ወደዚህ ከተማ የመጣ ነው አለና ከሚቀጥለው ክፍል ያለውን ሰራተኛ በፒተርስቡርግ ዙሪያ ዛሬ ጧት ራሱን በሽጉጥ የገደለው ሰው ስም ማን ነው ሲል ጠየቀ ደንታ ቢስ በሆነ በሻከረ ድምፅ ስቪድሪጋሎቭ የሚል መልስ አገኝ ራስኮልኒኮቭ በታላቅ ድንጋጤ ስቪድሪጋሎቭ ራሱን ገደለ። ራስኮልኒኮቭ ወንበሩ ላይ ዘፍ አለ የመገረም ፊት የሚታይበት ከሚመስለው ረዳት የፖሊስ ሹም ላይ ግን አይኑን አልነቀለም ሁለቱም ለጥቂት ጊዜ በዝምታ እየተያዩ ተጠባበቁ ውሀውም መጣ እኔ ነኝ በማለት ራስኮልኒኮቭ ጀመረ ውሀ ጠጣ አለው ራስኮልኒኮቭ ውህ የተሞላውን ብርጭቆው አንስቶ ወደጎን በማስቀመጥ እያንዳንዱን ቃል በዝግታ እያፍታታ እንዲህ ሲል ተናገረ አሮጊቷን አራጣ አበዳሪና እህቷን ሊሳቬታን በመጥረቢያ ፈርክሼ የገደልኳቸውና የዘረፍኳቸው እኔ ነኝ ከድንጋጤው የተነሳ ረዳት የፖሊስ ሹሙ የጩኸት ድምዕ አሰማ ሰዎች ከየአቅጣጫው እየሮጡ ተሰባሰቡ ራስኮልኒኮቭ አባባሉን ደገመው ፍፃሜው ሰው ዝር ከማይልበት ትልቅ ወንዝ ዳርቻ ላይ ከተማ ተቆርቁሯል በከተማው ውስጥ ምሽግ በምሽጉ ውስጥ ደግሞ እስር ቤት አለ በእስር ቤቱ ውስጥ ሁለተኛ ደረጃ እስረኛ የሆነው ራስኮልኒኮቭ ከተቀፈደደ ዘጠኝ ወር ሞላው ወንጀሉ ከተፈፀመ ወደ አስራ ስምንት ወር ይጠጋዋል የፍርድ ሂደቱ የተካሄደው ያለችግር ነበር እስረኛው ሁኔታዎችን ሳያምታታ ለራሱ በሚጠቅም መንገድ ሳይጠመዝዛቸው ሐቁን ሳያውገረግርና እያንዳንዷን ዝርዝር ነገር ሳይስት ቃሉን በግልፅና በማያሻማ ሁኔታ ሰጠ። ራስኮልኒኮቭ የዩኒቨርስቲ ተማሪ በነበረበት ወቅት ደሀና የቲቢ በሽተኛ የነበረውን ተማሪ ከመርዳቱም በላይ ከአነስተኛ ገቢው ላይ ቀንሶ ለስድስት ወር እንዳኖረው የሚያረጋግጥ ማስረጃ የቀድሞው ተማሪ ራዙምኪን ፈልጎ አገሽ ይህ ተማሪ ለህልፈተ ሕይወት ከተዳረገ በኋላም ቢሆን የአካል ጉዳተኛ የነበሩትን ሽማግሌ አባቱን ሆስፒታል እስካስገባበት እለት ድረስ ክትትል ያደርግላቸው እንደነበርና በሞቱ ጊዜም ለቀብሩ የሚያስፈልገውን ወጪ እንደከፈለ ተረጋገጠ እነዚህ ሁሉ ሁኔታዎች ቅጣቱን ለማቅለል አስተዋፅኦ ከማድረጋቸውም እንደዚሁም ቀደም ሲል ለራስኮልኒኮቭ ቤት አከራይታው የነበረችው ሴት በሌሊት ቤት ተቃጥሎ በነበረበት ወቅት ራስኮልኒኮቭ ከስፍራው በመገኘት ሁለት ሕፃናትን ከቃጠሎ አድኖ እርሱ ራሱ በቃጠሎው መነዳቱን መሰከረች ሁኔታው በጥልቀት ሲመረመርም ብዙ ምስክሮች ይሄንኑ የሴትየዋን ቃል አረጋገጡ ለማጠቃለል ያህል ፍርድ ቤቱ የእስረኛውን የእምነት ቃልና ሌሎች ቅጣትን የሚያቀሉ ሁኔታዎችን አገናዝቦ በወንጀለኛው ሳይ የስምንት አመት ብቻ እስራት ፈረደበት ጉዳዩ በፍርድ ቤት መታየት እንደጀመረ የራስኮልኒኮቭ እናት ታመመች የፍርዱ ሂደት እስኪያበቃ ድረስ ከፒተርስቡርግ ውጭ እንድትኖር ለማድረግ ዳንያና ራዘዙምኪን በቅተው ነበር ራዙምኪን ከፒተርስቡርግ አጠገብ በተዘረጋ የባቡር መስመር እየተጓጓዘ የፍርዱን ሂደት በመላ ይከታተልና በአመቸው ቁጥር ዳንያን ይጠይቅ ነበር የራስኮልኒኮቭ እናት በሽታ ከአእምሮ መታወክ ጋር የተያያዘ የነርቭ መዛባት መሆኑ ታወቀ ዳንያ ለመጨረሻ ጊዜ ከወንድሟ ጋር ተገናኝታ እንደተመለሰች እናቷን በጣም ታማ አገኘቻት በዚያኑ ምሽት ስለራስኮልኒኮቭ ሁኔታ እናቷ ለምታቀርባቸው ጥያቄዎች የምትሰጠውን መልስ ከራዙምኪን ጋር ሆና በፈጠራ መልክ አቀነባበረች ራስኮልኒኮቭ ለቢዝነስ ራቅ ወዳለ ወደሩስያ ግዛት እንደሄደና ስራውን አጠናቆ ሲመለስ ሀብትና ዝና እንደሚያተርፍ ነገረቻት ዳንያንም ሆነ ራዙምኪንን ያስገረማቸው ግን የራስኮልኒኮቭ እናት ምንም ጥያቄ ያላቀረበችላቸው መሆኑ ነው። የወደፊት ሁኔታውን አስመልክታም አንዳንድ ነጂ ተፅእኖዎች ሲወገዱ ብሩህ እድል እንደሚገጥመው ያለመጠራጠር ገለፀቹላቸው ለሕትመት በበቃው መጣጥፍና የስነፀሁፍ ችሎታው አማካይነት እንደተመሰከረው ሁሉ አንድ ቀን ልጂ ታዋቂ ባለስልጣን እንደሚሆን ለራዙምኪን አረጋገጠችለት የልጂን መጣጥፍ ከመኝታዋ ላይ ሁሉ ሆና እያነበበች ልጂ የት እንዳለ ግን አትጠይቃቸውም ነበር የራስኮልኒኮቭ እናት በተወሰኑ ነጥቦች ሳይ ዝምታን መምረጧ ስጋት ሳይ እንዲወድቁ አደረጋቸው ለምሳሌ ያህል ገጠር በነበሩበት ወቅት ኑሮዋን የገፋችው ከተወዳጁ ልጂ ደብዳቤ ይደርሰኛል በሜል ተስፋ ሲሆን አሁን ግን ደብዳቤ ባለማግኘቷ ስሞታ አታሰማም በልጂ ላይ መጥፎ አጋጣሚ እንደደረሰ ብታውቅም የጠየቅሁ እንደሆን የባሰ የከፋ ወሬ እሰማለሁ በሚል ፍርሀት ዝምታን መርጣ እንደሆን በመገመት ዳንያ ተጨነቀች ወጣም ወረደ የእናቷ አእምሮ ትክክል እንዳልነበረ ዳንያ ተገነዘበች ይሁንና ከአንዴም ሁለቴ የራስኮልኒኮቭ እናት የውይይቱን አቅጣጫ በመቀየሯ ልጂ የት እንዳለ ሳይገልፁ ማለፍ አስቸጋሪ ነበር ወደዱም ጠሉም የሚሰጡአት መልሶች አጥጋቢ ሳይሆኑ ሲቀሩ ለረጅም ጊዜ ይከፋትና ፊቷን ጨፍግጋ ዝም ትሳለች በመጨረሻም ሁልጊዜ መዋሸት አዳጋች እንደሆነ ዳንያ ተገንዝባ በተወሰነ ነጥብ ሳይ ምንም አለማለቱ እንደሚሻል ገመተች ምስኪኗ እናት ግን አስከፊና አስደንጋጭ ነገር ይደርሳል ብሳ እንደጠረጠረች ግልፅ እየሆነ ሄደ። የእስር ቤቱ ሀሳፊዎችን አግባብታቸው ራስኮልኒኮቭ ቀለል ያለ ስራ እንዲሰጠውና አንዳንድ ጥቅማጥቅሞች እንዲያገኝ ማድረጓን ግን አላወሳችላቸውም በመጨረሻም ራስኮልኒኮቭ ሁሉንም ሰው ማግለሉ በፍርደኞች ዘንድም መጠላቱ ለቀናት ያህል በዝምታ መዋጡና በጣም መገርጣቱ ተሰማ ውሎ አድሮም በጣም መታመሙንና ፍርደኞች በሚታከሙበት ሆስፒታል ውስጥ መግባቱን ሶንያ በመጨረሻው ደብዳቤዋ ላይ ገለፀች ለረጅም ጊዜ ታመመ ቅስሙን የሰበሩት ግን የአስር ቤት ሕይወት ሰቆቃ አድካሚው ስራ አስቀያሚው ምግብ ፀጉሩን መላጨቱ ወይም ልብሱ መንተቡ አልነበሩም ስቃዩና መከራው ሁሉ ለእርሱ ምንም አልነበረም። እያሉ ጮሁበት ስለ እግዚአብሔር ወይም ስለሀይማኖት አንስቶላቸው ጭራሽ ባያውቅም አማኝ አይደለም በሚል ሊሉት ፈለጉ እርሱ ግን በዝምታ ተውጦ መልስ ሳይሰጣቸው ቀረ አንዱ እስረኛ በንዴት ጦፎ ገብ ሊልበት ነበር ራስኮልኒኮቭ በርጋታና በዝምታ ጠበቀው በፊቱ ሳይ ምንም ለወጥ ሳያሳይና ዝንፍ ሳይል ተመለከተው ወዲያውኑ ጠባቂ በመካከላቸው ባይገባ ኑሮ ደም ይፈስ ነበር ሌሳው ግራ ያጋባው ነጥብ በዚያ ያለው ሁሉ በሶንያ ላይ ያሳየው ትኩረት ነበር ከእነርሱ ውለታ ለማግኘት አልሞከረችም የሚያጋጥሟትም በአብዛኛውበስራ ላይ ሆነው ወይም ደግሞ እርሱን ለመጠየቅ ስትመጣ አልፎ አልፎ ነው እንዲያም ሆኖ ግን ሁሉም ያውቋታል እርሱን ብላ እንደምትመጣና የትና እንዴት እንደምትኖር ያውቃሉ ገንዘብ አትሰጣቸውም ወይም የተለየ ነገር አታደርግላቸውም አንድ ጊዜ ብቻ ለገና በዐል ምግብ ይዛላቸው መጥታለች ቀስ በቀስ ግን በእነርሱና በሶንያ መካከል ግንኙነቱ ተጠናከረ ለቤተሰቦቻቸው ደብዳቤ ሳይቀር እየፃፈች በፖስታ ቤት ትልክሳቸዋለች እነርሱን ለመጠየቅ የሚመጡ ዘመዶቻቸው አድርጉ እየተባሉ እቃም ሆነ ገዝዘብ የሚተውት ከሶንያ ዘንድ ነው ሚስቶቻቸውና ቁባቶቻቸው ስለሚያውቋት እየሄዱ ይጠይቋታል ራስኮልኒኮቭን ለመጠየቅ ወደስራ ቦታ ስትመጣ ወይም ደግሞ ለስራ በተንቀሳቀሱ ጊዜ ከተገናኙ እስረኞቹ ባርኔጣቸውን ከፍ አድርገው ምስጋና እየደረደሩ ለዚህች ድንቢጥ ለምታክል ሴት ሰላምታ ያቀርቡላታል የአፀፋ ሰላምታዋን ከፈገግታ ጋር ስትመልስ ሁሉም ይደሰታል በአረማመጳ ሳይቀር ይደሰቱና ዞር ብለው እያዩ ያመሰግኗታል እጥር ምጥን ማለቷን እያደነቁ ያሞካሸታል ለምን እንደሚያመሰግኗት ግን አያውቁትም ትንሸ ሲያማቸው እንከን እርዳታ ለማግኘት ወደ እርሷ ይሄዳሌ በሀዳዴ የመጨረሻዎቹ ሳምንታትና በፋሲካ የመጀመሪያዎቹ ቀናት ራስኮልኒኮቭ በሆስፒታል ተኛ ከሕመሙ እንዳገገመ ሲያተኩሰውና ሲያቃዣው በነበረ ጊዜ የታየውን ሕልም አስታወሰ በሕልሙ መሠረት ከእስያ ተነስቶ አውሮፓን ባዳረሰ ወረርሽኝ መላው እለም ይንኮታኮታል ከጥቂቱ በስተቀር ሀሉም ለውድመት ይዳረጋሉ በአዳዲስ አይነት ጀርሞች የሚለከፉት ሁሉ ወዲያውኑ እብድና አመፀኛ ይሆናሉ በወረርሸኙ የተጠቁትን ሰዎች ያህል እውነትን በመፈለግ ረገድ ብልህና ጠንካራ አድርገው ራሳቸውን የቆጠሩ ከዚህ ቀደም አልነበሩም ውሳኔዎቻቸውን የሳይንቲፊክ መደምደሚያዎቻቸውንና የሞራል አቋማቸውን የማይናወፁና የማይለወጡ አድርገው ይቆጥራሉ መንደሩ ከተማውና ሕዝቡ በወረርሸኙ ተለክፈው ተናወጡ በስጋት ተዋጡ እርስ በርስ ሳይግባቡ ቀሩ እውነት ያለችው በእርሱ ውስጥ ብቻ እንደሆነች አድርጎ እያንዳንዱ ስለሚቆጥር መሰሉን በተመለከተ ጊዜ ይከፋና ደረቱን ይደቃል እጆቹን አጣጥፎ ያለቅሳል ማንን እንደሚከሱ ወይም ውሳኔ እንዴት እንደሚያስተላልፉ አያውቁም ሰናዩንና እኩዩን በመለየት ረገድ አንድ አይነት አቋም አይዙም ማንን እንደሚወነጅሉ ወይም ከወንጀሉ ነፃ እንደሚያደርጉ አያውቁም ውሀ ቀጠነ ብሎ አንዱ ሌላውን ይገድሳል ጦር ሠራዊት ቢደራጅም ይህ ጦር ግስጋሴውን ሲጀምር ሳይታሰብ እርስ በርሱ ይፋለምና ይበታተናል። ቀኑ ደማቅና ብሩህ ነው በእስርቤቱ ውስጥ በየክፍሉ ያሉት የብረት መስኮቶች ተከፍተው ከስራቸው ያሉ ወታደሮች ወደፊትና ወደኋላ በሰልፍ ይጓዛሉ ሶንያ ወደ ሆስፒታል ሄዳ የጠየቀችው ለሁለት ጊዜ ብቻ ነው ለመጠየቅ ልዩ ፈቃድ በማስፈለጉ ተቸገረች ይሁንና ሊመሻሸ ሲል ወደ ሆስፒታሉ ቅጥር ግቢ እየሄደች ራስኮልኒኮቭ የተኛበትን ክፍል መስኮት ለደቂቃ ያህል ከርቀት ትመለከታለች ታዲያ ከሕመሙ ቀስ በቀስ እያገገመ ራስኮልኒኮቭ አንድ ቀን ምሽት ላይ ከእንቅልፉ እንደነቃ ወደ መስኮቱ እየሄደ ሲንሸራሸር ሶንያን ከሆስፒታሉ በር ላይ ሆና በርቀት ተመለከታት የሆነ ነገር የምትጠብቅ መስላ ቆማለች የሆነ ነገር ልቡን የወጋው መሰለውና ወዲያውኑ ፊቱን ከመስኮቱ መለሰ በማግስቱ ሶንያ ሳትመጣ ቀረች በሚቀጥለውም ቀን እንዲህ በጉጉት ይጠብቃት እንደነበር አስተዋለ በመጨረሻም ከሆስፒታል ወጥቶ ወደ እስር ቤት ሲመለስ ሶንያ መታመሟንና ከቤት መውጣት አለመቻሏን እስረኞች ነገሩት በጣም ስለተጨነቀ ሰው ላከባት ወዲያውኑም ሕመሟ ለአደጋ እንደማይሰጣት ሰማ ሶንያ የራስኮልኒኮቨን መጨነቅና መጠበብ ተገንዝባ እንደተሻላትና በቅርቡ ወደስራ ቦታው መጥታ ልትጠይቀው ተስፋ እንዳሳት የሚገልፅ በእርሳስ የተፃፈ ማስታወሻ ላከችለት ማስታወሻውን እንዳነበበ የልቡ ትርታ ጨመረ ዕለቱ ሞቃትና ብሩህ ስለነበረ ከወንዝ ዳርቻ ወዳለውና ሸክሳ ወደሚመረትበት ቤት ሄዶ ለመስራት ከጧቱ አስራ ሀለት ሰአት ገዞውን ጀመረ አብረውት የተሰማሩት ሶስት እስረኞች ብቻ ነበሩ።