Detecting...
Please whitelist dirzon to continue.
ነ ብረት ከባህር እንዲያወጣ ነቢዩ ኤልሳዕ የተጠቀመበት ቁራጭ እንጨት ነገ የቅዱስ ጳውሎስ የልብስ እራፊ ጮሥራ የቅዱስ ጴጥሮስ ጥላ ሁጮሥራ እግዚአብሔር የፈውስና የተአምራት መግለጫው አድርጓቸዋልና በሥጋዌ ዓይን እየመዘንን የተፈጥሮ ባህርያቸውን በመዘርዘር ጥርጣሬንና ክህደትን የምንፈጥርባቸው አይደሉም ይልቁንም ከነዚህ ማስረጃ ምሳሌዎች የምንረዳው ቅዱሳን የነፍሳቸው ቅድስና ለሥጋቸው የሥጋቸው ቅድስና ለምርኩዛቸው ለአልባሳታቸውና ጥላቸው ተርፎ ድንቅ ተአምራትን ማድረጉን ነው ። ዋናው እምነት ነው። ይህች መልክ ሲል ለጊዜው የቄሳርን ለቄሳር የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር ስጡ ሲል ለፍጻሜው ግን ይህች ስዕል ሲል የቄሳርን መልክ ለማለት ነው ቄሳር ምንድን ነው። ሰው ነው ። ሰው የማን መልክ ነው። ስለዚህም ፕሮቴስታንት ወገኖችን ጣዖትና ቅዱሳት ንዋያትን የመለየት እምነቱና ድፍረቱ ይኖራችሁ ዘንድ እንመክራለን ስዕልና የፕሮቴስታንት መንትያ አቋም ዐሀክፀ ጳበበጩ ነው እነርሱ ለሌላ ሰው እየጸለዩ የቅዱሳንን ጸሎት እንደሚቃወሙት ዓይነት ማለት ነው። በግድግዳ ፊት። በዓለም ዙሪያ ያሉ ክርስቲያኖች ኦርቶዶክስ ካቶሊክ እና ከፊል ፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮችን ስዕልን ለትምህርት ለጸሎትና ለስርዓተ አምልኮ ይጠቀማሉ ነገር ግን አንዳቸውም በስዕሉ በኩል የስዕሉን ባለቤት ለይተው አያዩም ስዕሉን ከባለቤቱ ለይቶ የሚያመልክ ክርስቲያን በዓለም አንድ እንኳን አይገኝም እንግዲህ የሁለት ዓለም ሰዎች የሆነው በዓለም ላይ ያለን በቢሊዮን ምንቆጠር ክርሰቲያኖች ስለተሳሳትን ነው። ወይስ ፕሮቴስታንተት ስለስዕል የተሳሳተ አመለካከት በመያዛችሁ ነው። በስዕል ፊት መስገድ ለስዕሉ ባለቤት የአክብሮት ስግደት እንሰግዳልን ለማን እንደምንሰግድና ምን ዓይነት ስግደት እንደምናቀርብ የምናውቀው እኛው ነን አንድ ሰው በቅዱሳን ስዕል ፊት ስሰግድ እያመለካቸው ነው ቢለኝ ከባለቤቱ ያወቀ ቡዳ ነው እለዋለው። ስዕል በኦሪቱም በሐዲስ ኪዳንም የነበረን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ክስተት የሚገልጽ ብቻ አይደለም የእግዚአብሔርን ቃልና ሰማያዊው ስርዓትም በዓይነ ህሊናችን እንዲሳል የሚረዳን ጭምር አንጂ በክስርትናው ዓለም ስዕል እንደ እንግዳ ደራሽ እንደ ውሀ ፈሳሽ ድንገቴ የሆነ ክስተት አይደለም ክርስትናን ከራሱ ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ እግር ስር ቁጭ ብለው የአንደበቱቱ ትምህርት ከሰሙት የእጁን ተዓምራት በአይናቸው ካዩት ከሐዋርያት ዘመን ጀምሮ ስነጽሑፍ እስከ ተስፋፋበት ወርቃማው ዘመን ድረስ ወንጌል ለመስበክ እንደ ድልድይ የነበረም ነው የጽሑፍ እውቀት ያልነበራቸው በቃል ሰዎች በቃል ከመማራቸው በተጨማሪ ወንጌልን የተማሩበት የተረዱበት በስዕል አማካኝነት ነበር። እመቤታችን ልጂን ታቅፋ የምናያትን ስዕል ለመጀመሪያ ጊዜ የሳለው ወንጌላዊው እና ሰዓሊው ሉቃስ ነው።
ስለ ስዕል በአዲስ ኪዳን ገላሩ የማታስተውሉ የገላትያ ሰዎች ሆይ በዓይናችሁ ፊት ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ተሰቀለ ሆኖ ተሥሎ ነበር ለእውነት እንዳትታዘዙ አዚም ያደረገባችሁ ማን ነው። ነገር ግን ለቅዱሳት ስዕላት ክብርና እንክብካቤ እንዲሁም ለስዕሉ ባለቤት ስግደት እንደሚገባ ቀኖና ሰራ ልብ ልንለውና ልናስተውለው የሚገባን አንድ እውነት ቢኖር በሥዕል ፊት ቆሞ መፀለይ ከባለ ስዕሉ ረድኤት በረከትና ምልጃ ለማግኘት እንጂ ወረቀቱን ማክበራችን ወይም መለመናችን አይደለም ለምሳሌ በጌታ ስዕል ፊት መፀለያችን ለባለ ስዕሉ ለጌታ መጸለያችን ነው እንጂ ለወረቀቱ አይደለም ደግሞም በፍቅርና በእምነት የሚሆን ነገር ሁሉ በመጽሐፍ ቅዱስ ባይጻፍ እንኳን ያጸድቃል እንጂ አያስኮንንም። አንዳንድ ጊዜ ብርሃናዊ መልኩና ረዘም ብሎ የሚታየው ጽህሙ የሚሰጠው ፍፁም ውበት በማንም ው ብ ልጅ ላይ ታይቶ የማይታወቅ ነው መልአካውያን አይኖቹና የጥቁር ወርቃማ ጠጉሮቹም አወራረድ በሚሰጡት የተንጸባረቀ ውበት ማንም ሰው ቢሆን ለረጅም ጊዜ አተኩሮ ሊመለከተው አይችልም የሚመስለው ፍጹም እናቱን ነው እርሷም ደግሞ በዚህ ክፍለ አገር በማንም ያልታየ ውበትና የትህትና መልክ ያላት ልዩ ሴት ናት ቆራጥ ከባድና የሚያከራክሩ ንግግሮቹም በውስጣቸው የሚገኘው ፍጹም የሆነ የመንፈስ ልዕልናና የዕውቀት መጠናቸው ከታላላቅ አዋቂዎች ተብለው ከሚገመቱት ሰዎች እጅግ አድርጐ የራቀና የጠለቀ ምስጢር አላቸው በተግሳፅና በእዝናት ጊዜም በጣም ኃይለኛ ነው በማስተማርና በማጽናናት ጊዜ ደግሞ በጣም ትሁት ተወዳጅና ልብ የሚመስጥ ነው ራሱን ሳይከናነብና መጫሚያ ሳይጫማ በእግሩ ይሄዳል በሩቅ የሚያዩት አንዳንዶቹ ይሳለቁበታል ወደ ፊቱ ሲቀርቡና ሲያዩት ግን በመንቀጥቀጥና በመፍራት ይሰግዱለታል ማንም ቢሆን ሲስቅ አየሁት የሚል የለም ነገር ግን ብዙዎች በተደጋጋሚ ሲያለቅስ አይተውታል የቀረቡት ሁሉ ብዙ ፈውስና ተአምራት ማግኘታቸውን ይናገራሉ አይሁድ ግን ገዢና ተገዢ ሁሉም በእኔና በአባቴ ፊት እኩል ናቸው ምንም ልዩነት የላቸውም ብሎ ስለሚያስተምር የግርማዊነትህ አጥፊ ሳይሆን አይቀርም በማለት እየመጡ ይነግሩኛል ስለዚህ ጉዳይ አጢነህ የወሰንከውን ውሳኔ ብታዘኝ ድኣ ወዲያውኑ ትዕዛዝህ የሚፈጸም ይሆናል ጤና ሁን ጺላጦስ ጴንጤናዊ ነኝ ፒሎንቱሌ በማለት ጸፏል ይህም ደብዳቤ ዛሬ ድረስ በታሪክ አጥፒዎችና ጠበብቶች እጅ ይገኛል ይህ ከላይ ያነበብነው የጌታ ዝርዝር መልክ ከታች ከምትመለከቱት የጌታ እውነተኛ ስዕል ጋር ፍጹም ተመሳሳይ ነው እጅግ ይደንቃል ዛሬ የሚሳሉ የጌታችን ቅዱሳት ስዕላትም ካነበብነው እውነት የሚወስዱ ናቸው የጌታን ስዕል የሳለው ዮሐንስ ወንጌላዊ ሲሆን የእመቤታችንን ምስለ ፍቁር ወልዳን የሳለው ደግሞ ቅዱስ ሉቃስ ነው ይህ ስዕልውቅዱስ ሉቃስ የሣላት ምስለ ፍቁር ወልዳን ዛሬ ድረስ በጥንታዊቷ ተድባበ ማርያም ቤተ ክርስቲያን ይገኛል ሌላውና ዋናው የቬሮኒካ ታሪክ ለስዕል ጥሩ መነሻ ነው። ይህ ቅዱስ ለረጅም ዘመናት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተከርስቲያን ሥዕላቸው ያለመቋረጥ ተሥሎ ከሚገኙት ቅዱሳን መካከል ነው ሥዕሉም በብራና በግድግዳ እንዲሁም በገበታ ሥዕሎች ላይ ተሥሎ ይገኛል ለምሳሌ በጥንታዊነታቸው ከሚታወቁት አብያተክርስቲያናት መካከል በገነተ ማርያም ቤተከርስቲያን በ መክዘ የግድግዳ ሥዕል በአባ ገብረመስቀል እና ጊዮርጊስ ቤተከርስቲያን ግድግዳ ላይ በኛው መክዚን በጉንዳጉንዶ የሚገኝ የብራና ሥዕል በኛው መኳክን ኛው መክዘ ተአምረ ማርያም ብራና ላይ ኛው መክ ዘ መዝሙረ ዳዊት እና በፎ በፎፍ ከሚገኙት ገበታ ሥዕል በገና እየደረደረ የሚታዩት ሥዕሎች ለዚህ ማሳያ ናቸው ቅዱስ ዳዊት በቤተክርስቲያናችንም በስፋት በገና ሲደረድር ይሣላል በዚህ የአሣሣል ጭብጥም ቅዱስ ዳዊት ለረጅም ዘመናት በቤተክርስቲያናችን የእርሱን ቅዱስ ሥዕል ለአገልግሎት ከቅዱስ መዝሙር በተጨማሪ ለአገልግሎት ስትጠቀምበት ኖራለች በገና ሲደረድር እንዳለው በብዛት የሚገኙ ባይሆንም ሌሎች ግ ቅዱስ ዳዊትን ጭብጦች ተሥለው ለአገልግሎት ውለዋል ዳዊት ጎሊያድን በእግዚአብሔር ሲያሸንፈው በዓለ እረፍታ ለማርያም ሥዕል ላይ እያረጋጋት በበገናው የሚታየው ሥዕል ለምሳሌ በተአምረማርያም እና በሴቶች ወገን ባሉ ግድግዳዎች ላይ ይታያል ዳዊት በጎችን እየጠበቀ እና ነቢዩ ሳሙኤል ቅዱስ ዳዊትን ሲቀባው በቅዱስ ሚካኤል ድርሳን ላይ ደግሞ ቅዱስ ዳዊትን እንዲቀባው ቅዱስ ሚካኤል የእግዚአብሔርን ቤተመቅደስ ልታንጽ አይገባም ተብሎ በነቢዩ ሲነገረው በቤተ እግዚእብሔር ሲጸልይ በመዝሙረ ዳዊት ላይ ደግሞ መዝ ዐ ላይ ያለውን ጥቅስ ተይዞ ተጸጽቶ እየሰገደ ሲጸልይ በዮርዳኖስ ባሕር አጠገብ እየሰገደ ሲጸልይ በአቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ገድል ላይ ነፍሳቸውን በበገና መዝሙር እያረጋጋ ተሥሏል ከላይ የተጠቀሱት እንደምሳሌ ከብዙ በጥቂቱ ቅዱስ ዳዊት በሥዕል የተገለጠባቸው ጭብጦች ናቸው ከቅዱስ ዳዊት እና ከወላዲተ አምላክ በረከት ረድኤት ፈጣሪያችን ይክፈለን ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር የካቲት በዓሏ የሚታሰብላት ከጉንጧሟ ደም የሚፈስሳት ተአምር አድራጊዋ የእመቤታችን ሥዕል እጅግ አስደናቂ ታሪክ መነበብ የሚገባው በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ የዚኽች አስደናቂ ሥዕልን ድንቅ ታሪክ ከመጻፌ በፊት ለወንጌል አገልግሎት ወደ ኖርዌ በኹድጐ ጊዜ ከጐንጮቿ ላይ ደም የሚፈስሳት ሁላችንም የምናውቃት የእመቤታችንን የታተመች ሥዕሏን በአንድ ወንድም ቤት ውስጥ በክብር ባማረ መልኩ ተቀምጣ አይቼ በመደነቅ ሥዕሏን ከየት እንደገዛት ጠየቅኹት ርሱም በኖርዌ የዕቃ መሸጫ አጠገብ ወድቃ አግኝቶት ቶሎ ብሎ በገንዘቡ ገዝቷት ቤቱ ወስዶ መብራት አብርቶ ሽቱ ረጭቶ በክብር ባስቀመጣት ጊዜ ሌሊቱን ኹሉ እጅግ ዕጹብ ድንቅ የሚያሰኝ የዕጣን ሽታ ሲሸተውና የማዕጠንትና የምስጋና ድምፅ ሲሰማ እንዳደረ በነገረኝ ጊዜ ልዑል እግዚአብሔርን በማመስገንና የተቀደሰ ሥዕሏን በመሳለም የሥዕሏን ታሪክ ነገርኩት ልጁ የገዛት ሥዕል ግን ዋናዋ የጥንቷ ናት ማለቴ ሳይኾን ያው አኹን የምንጠቀምባት ፖስት ያደረግኳት ዓይነት በዚያች በዋናዋ አምሳል የታተመችውንና የምትሸጠውን ሥዕል እንደኾነች ለማስታወቅ እፈልጋለጐ ይኽን በጥንት ጊዜ የነበራትን የተቀደሰ ታሪክ ለኹሉም መጻፍ እንዳለብኝ ለራሴ ቃል ገብቼ ነበርና እነሆ ጊዜው ገጥሞልኝ በየካቲት በመላው ዓለም በዓሏ የሚታሰብላትን ታሪኳን በበዓሏ ዕለት እነሆ ብያለጎ ስለዚኽች ድንቅ ተአምር አባ ጽጌ ድንግል አስቀድሞ በማሕሌተ ጽጌ ላይ እንዲኽ ብሏት ነበር ሥዕልኪ ማርያም ጸገየት ሥጋዌ ከመ ዕፀ ገነት ትጸጊ ጽጌያተ ለሥርጋዌ ሣሕለ ተአምርኪ እኩን ለትውልደ ትውልድ ዜናዌ ቅብዕኒ ሐፈ ሥዕልኪ ወፈውስኒ እምደዌ እስመ በኅምዙ አቀሰለኒ አርዌ የገነት ዛፍ አበቦችን ለሽልማት እንደምታብብ ማርያም ሥዕልሽ ግዘፍን አበበች ሥጋን የለበሰች መስላ ታየችን የተአምርሽን ዜና ለልጅ ልጅ የምነግር እኾን ዘንድ የሥዕልሽን ወዝ ቀቢኝ ከበሽታም አድፒኝ አባብ አውሬ በመርዙ በኀጢአት አቀስሎኛልናን በማለት ተማፅኗታል ይኸውም ከ ዓም በቤዛንታይን የነገሠው ንጉሥ ቴዎፍሎስ በቅዱሳት ሥዕላት ላይ በክፋት ተነሳሥቶ ዐዋጅ በማወጁ ወታደሮቹ በርሱ ትእዛዝ በእያንዳንዱ ቤት እየዞሩ ቅዱሳት ሥዕላትን ለማጥፋት ፍተሻ ያደርጉ ነበር በኒቅያ ከተማ አቅራቢያ አንዲት የተቀደሰች ሴት ነበረች ቅዱስ ሉቃስ የሣላት የአምላክ እናት የቅድስት ድንግል ማርያም ውብ ሥዕሏን በቤቷ ውስጥ ደብቃ በማኖር በሥዕሏ ፊት መብራትን እያበራች ከልጂ እንድታማልዳት ትማፀን ነበር የከሓዲው ንጉሥ ወታደሮቹም የአምላክ እናት ሥዕል በቤቷ እንዳለች በማወቃቸው ወደ ቤቷ በድንገት ዘልቀው ገቡ ከመካላቸውም አንዱ ወታደር የእመቤታችንን ሥዕሏን በያዘው ጦር ጉንሟ ላይ ወጋት ኾኖም ግን በእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ ይኽ ክፉ ሥራው በተአምር ተተክቶ ከተወጋው ከአምላክ እናት ፊት ላይ ደም ይፈስስ ጀመር ይኽን ግሩምና ድንቅ ተአምር ባዩ ጊዜ ወታደሮቹ ደንግጠው ሸሽተዋል ሴቲቱም ይኽነን ድንቅ ተአምር ባየች ጊዜ ሌሊቱን ሙሉ በሥዕሏ ፊት መብራትን አብርታ በአምላክ እናት በቅድስት ድንግል ማርያም ሥዕል ፊት ስትጸልይ ዐደረች በነጋጋውም በእግዚአብሔር ፈቃድ ከጉንጮቿ ደም የፈሰሳትን የአምላክ እናት ሥዕሏን በባሕሩ ላይ እንድታስቀምጥ ታዘዘችና አስቀመጠቻት ሥዕሏም በባሕሩ ላይ በመንሳፈፍ በማዕበሉ እየተነዳች ያለምንም መስጠምና መርጠብ ወደ ምዕራብ አቅጣጫ ጉዞዋን አድርጋ ወደ አቶስ ደረሰች ጊዜያቶች ካለፉ በኋላ ከዕለታት በአንዳቸው ምሽት በአቶስ ተራራ የአይቬሮን ገዳም መነኮሳት የብርሃን ምሰሶ በባሕሩ ላይ ተተክሎ እንደ ፀሓይ ሲያበራ ተመለከቱ ይኽም የ ተአምር ለተካታታይ ቀናቶች በመቀጠላቸው በዚያ የተቀደሰ ተራራ በምናኔ ያሉ አባቶች ኹሉ በአንድ ላይ ተሰባስበው በማድነቅ የብርሃን ምሰሶ ወደተተከለበት የአምላክ እናት ሥዕል በላዩ ላይ ወደ ተንሳፈፈበት ወደ ባሕሩ በመውረድ ወደ ሥዕሏ ለመጠጋት ቢሞክሩም ሥዕሏ ወደ ኋላዋ እየተመለሰች ሊያነሷት አልተቻላቸውም በዚያው የአይሾሪዮን ገዳም ረድእ የጉልበት አገልጋይን ኾኖ የሚኖር አባ ገብርኤል የተባለው መነኩሴ ብቻ ሥዕሏን ከባሕር ውስጥ ማንሣት የሚችል እንደኾነ የአምላክ እናት ለመነኮሳቱ ገለጠችላቸው በተመሳሳይም ለአባ ገብርኤል እመቤታችን ተገልጣለት ወደ ባሕሩ ኺድ ማዕበሉንም ሳትፈራ በባሕሩ ውስጥ በእምነት ተጓዝ እናም ኹሉም ለዚኽ አንተ ላለኽበት ገዳም ያለችን ፍቅርና ርኅራቴ ምስክር እንዲኾኑ ሥዕሌን ከባሕር አውጣ በማለት ነገረችው ከዚያም በአቶስ ተራራ ያሉት መናንያን ኹሉ አባ ገብርኤልን ይዘው ልብሰ ተክህኖ ለብሰው እያመሰገኑ በማዕጠንታቸው ዕጣን እያጠኑ የብርሃን ምሰሶ ወደተተከለበት የአምላክ እናት ሥዕል ወዳለበት ወደ ባሕሩ ኹዱ አባ ገብርኤልም በደረቅ መሬት እንደሚጓዝ ያለምንም ፍርሃት ወደ ባሕሩ ውስጥ በመግባት በናፍቆት ኾኖ የአምላክ እናት የቅድስት ድንግል ማርያምን ሥዕሏን በደረቱ ታቅፎ ተሳለማትና ወደ ባሕር ዳርቻ ይዚት ወጣ እነርሱም በደስታ ኾነው እጅ ካል ከዚያም ማግሰኞ በጠዋቱ ሥዕሏ ባረፈበት ቦታ ላይ በሚያመሰግኑበት ጊዜ ቀዝቃዛና ጣፋጭ ውሃ ከምድር ላይ ፈለቀላቸው ከዚያም የእመቤታችንን ሥዕሏን በታላቅ ክብር በምስጋና ይዘው በመኹድ ወደ ቤተ መቅደስ አግብተው በመንበሩ ላይ አስቀመጧት ነገር ግን በነጋታው መነኮሳቱ ወደ ቤተ መቅደስ ገብተው መብራት ሲያበሩ የእመቤታችን ሥዕሏን ባስቀመጡበት ቦታ አላገኗትም ይልቁኑ በመግቢያው በር ባለው ግድግዳ ላይ ተሰቅላ አገጄት እነርሱም መልሰው በቦታዋ ላይ ቢያኖሯትም ተመልሳ በገዳሙ መግቢያ ላይ ተሰቅላ ያገሂት ነበር ከዚያም እመቤታችን ለአባ ገብርኤል ተገልጻለት ለወንድሞች እንዲኽ ብለኽ ንገራቸው ከዚኽ በኋላ ሥዕሌን ማግባት የለባቸውም የእኔስ ፈቃድ በእናንተ ልጠበቅ ሳይኾን እኔን በምልጃዬ ጥላ በዚኽም ዓለም በወዲያኛውም ዓለም ልጋርዳችጐ እንጂ ሥዕሌን በገዳሙ በምታዩበት ጊዜ ኹሉ የልጄ ምሕረትና ጸጋ ከእናንተ አይቋረጥም አለችው መነኮሳቱም ይኽነን ሰምተው በእጅጉ በመደሰት ለአምላክ እናት ለእመቤታችን ክብር በገዳሙ በር አጠገብ አነስ ያለች ቤተ ክርስቲያን ሠርተው ገባሪተ ተአምራት ወመንክራት ድንቅ ተአምር አድራጊዋንን የአምላክ እናት የቅድስት ድንግል ማርያምን ሥዕሏን ወደ ውስጥ አገቧት የተቀደሰች የሥዕሏ መጠሪያም የአይቬሮኗ የአምላክ እናት ስትባል በግሪክ ፓርታኢቲሳ ትባላለች ከዚያም በአይቬሮን ገዳም ያለችው የእመቤታችን ሥዕል ድንቅ ተአምር በዓለም ኹሉ ላይ ከተሰማ በኋላ በረከቷን ለማግኘት ክርስቲያኖች ወደዚያች ገዳም መኹድን ዝመሩ ይኽ የተቀደሰ ሥዕሏና ታሪኳም ኢትዮጵያን ጨምሮ በዓለሙ ኹሉ ላይ ተሰማ ዛሬም ምእመናን ይማፀኑበታል እኔ መጋቤ ሐዲስ ሮዳስም ይኽነን የተቀደሰ ታሪኳን ዛሬ የካቲት ዓም በበዓሏ ዕለት በመጻፌ እጅግ ደስታ እየተሰማኝ ለአባ ገብርኤል የተለመነች እና በረከቷን እንዳሳደረችበት ዛሬም የምልጃዋ ጥላ በዚኽም ዓለም በወዲያኛውም ዓለም እንዳይለየኝ በመማፀን አባ ጽጌ ድንግል ስለዚኽች ሥዕል በማሕሌተ ጽጌ ላይ ባመሰገናት ምስጋና ጽሑፉን አበቃለ ቦ አመ ትትረከብ ምስለ ቃለ ነገር ጥዑም ወቦ አመ ትትረአይ በለቢሰ አባል ልምሉም ሥዕልኪ ማርያም ጽጌ ተአምር አዳም ወአመ ዘበጣ በሰይፍ አይሁዳዊ ርጉም እምኔሃ አንጸፍጸፈ ደም ሥዕልሽ ቃልን ደስ ከሚያሰኝ ነገር ጋራ የምትገኝበት ጊዜ አለ የለመለመ አካልንም ለብሳ የምትታይበት ጊዜ አለ ማርያም ሥዕልሽ የተአምር አበባ ናት ርጉም አይሁዳዊ በሰይፍ በመታት ጊዜ ከርሷ ሥዕል ደም ተንጠባጠበ ይላል የአምላክ እናት ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ በምልጃሽ ሃሬ በቃል ኪዳንሽ የማይጠገበው በረከትሽን ዕጽፍ ድርብ አድርገሽ አሳድርቢን እስቲ እናንተም በተቻላችጉ መጠን በተሰማችጐ ልክ አመስግኗት ከመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ ብዙዎች እናንተ የምትሰግድት ፈረንጅ ለሳለው ስእል ነው አምላክ ነጭ ይሁን ጥቁር ያየው የለም የሚሉ አሉና ይሄን ለማወቅ ፈልጌ ነው ። ለመጀመሪያ ጊዜ የጌታን ሥዕል የሳለው ዮሐንስ ወንጌላዊ ነው ከዓንም ሮምን ገዚ ጢባርዮስ ልጁ ሞቶበት አስከሬኑን ከጌታ መቃብር ላይ አኖሩት ልጁም ተነሳ በዚሕ መክንያት ዮሐንስ ለጢባርዮስ በዕለተ ዓርብ በመስቀሉ ላይ እዳየው አድርጎ ገለሜዳ አስታጥቆ ጌታን ስሎታል ድምጽም ከሥዕሉ እንደወጣ ታሪክ ይናከራል ምንጭ አምደሃይማኖት ሌላው ሥዕል በብሉይ ኪዳን እግዚአብሔር ለሙሴ ሥዕለኪሩብን እነዲአዘጋጅ ነገረው በታቦቱ አጠገብ እንዲአስቀምጥ አዞታል ዘጸኃ ዘጐ ዘጸ በዚሕ አይነት ለሙሴ የተሰጠው ሥዕል መነሻና መሠረት ሆኖ ለሥርአተ አምልኮ መፈጸሚያ ሆኖአል ሌላው ነጉሥ ሰሎሞን ቤተመቅደሱን በሰራ ጊዜ ይሕን መነሻ አድርጎ የ ኪሩብን ሥዕሎች በቅድስተ ቅዱሣኑ ወስጥ አስቀምጦአል ኛዜና እስራኤል የባቡን ሥዕል በዕምነት ባዩጊዜ ድነዋል ዘጉ ሥዕል በአዲስ ኪዳን ለአዲስኪዳን ሥዕል መሠረቱ የብሉይ ኪዳን ሥዕል ነው ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለሥጋዌው ሥዕለ ኪሩብ ባለበት ቤተመቅደስ አልተለየም ነበር በአርባ ቀኑ ድንግል ማርያም ወደቤተ መቅደስ ወስዳዋለች ሉቃ ሪሯ ዕለት ዕለትም ሥዕለኪሩብ ካለበት ቤተመቅደስ እየተገኘ ያስተምር ነበርማቴ ዮሐ ሥዕል በቤተመቅደስ ባያስፈልግ ኖሮ ሥዕሉንም ከቤተመቅደስ ባወጣ ነበር ጥንቱንም እነሙሴ ሥዕል እንዲስሉ አያዝም ነበር ሐዋርያት ይሕንን መሠረት አድርገው ሥዕል ባለበት ቤተመቅደስ እየተገኙ ጸልየዋል ሉቃ ባጭሩ አንድ ነገር ልናገር የሙሴ በትር ታምራትን አድርጋለች ዘጸ የየልያስ መጎናጸፊያ ወንዝ ለሁለት ከፍላለች ኛ ነገየጳውሎስ ልብስ ጨርቅ ቢሆንም በሽተኛ ይፈውስ ነበር የጴጥሮስ ጥላአጋንንትን ያስወጣ ነበር የሐዋ ነበር ታዲያ የጌታ ሥዕል ሙት ቢአስነሳ የጌታ መስቀል አጋንንት ቢስወጣ ምን ይደንቃል የእመቤታችን ሥዕልም እንዲሁ ቢፈውስ ማድነቅ ነው እንጅ መተቸት ምን አስፈለገ ከብዙ በጥቂቱ ይሕን ይመስላል መልካም ቀን ይሁንላችሁ። በስመአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ አንድ አንድ አምላክ አሜን ቅዱሳት ሥዕላት ሥዕል እግዚአብሔር ጋር የተያያዘና በብሉይም ሆነ በአዲስ ኪዳን የሚሰራበት ነው ሥዕል በእግዚአብሔር ፊት የተሰጠ ህግ ነው ይኽውም ለሙሴ በታቦተ ሕጉ በፅላት ኪዳኑ ላይ ሥዕለ ኪሩብን እንዲስል ታዞ ነበር በብሉይ ኪዳን የመጀመሪያው ሰአሊ ሙሴ ነው ሰለሞንም የመጀመሪያውን ቤተ መቅደስ በሰራ ጊዜ ሥዕለ ኪሩቤልን ስሏል። ኢየሱስ ክርስቶስ ስለነበረበት በጣም ቅርብ የነበሩት የጥንት ክርስቲያኖች በጌታችን ሥዕል በቅድስት ድንግል ሥዕልና በቅዱሳን ሥዕሎች ይማፀኑ አንደ ነበር የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ይመሰክራል። አውሳብዮስ ኤጺስ ቆጳስ ዘቂሳርያና ሌሎችም የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ጸሐፊዎች አንደ መሰከሩት የጥን ትዋ ቤተ ክርስቲያን ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥዕል ስወሳዲተ አምላክ ለቅዱሳን መላአክት ለ ጻድቃንና ስሰማዕታት ሥዕሎች ከፍ ያስ ክብር አንዲደረግላቸውና የጸጋና የአክብሮት ስግደት አንዲቀር ብላቸው ስታስተምር ኖራለች። እንዴት በሆነ እምነት በምንስ ዓይነት ማስረጃና እንዴት ባለ አስተሳሰብ ስዕል ጣዖት ሊሆን ይችላል። እንኳን ዛሬ አምላክን በስጋ ተገልጦ ባየንበት በሐዲስ ኪዳን ዘመን ይቅርና እግዚአብሔር ማንነቱ በግልጥ በማይታወቀበት በኦሪቱ ዘመን ስዕል ጣዖት አልሆነም አልተባለምም እውነት ለመናገር ስዕልን ጣዖት ማለት የጣዖትን ትርጉም በቅጡ ካለማወቅ እና በጣም ተጠራጣሪ ከመሆን የሚመነጭ ነው ሰው አንድ ሲደመር አንድ ሶስት ነው ብሎ ራሱን ካሳመነ አንድ ሲደመር አንድ ሁለት መሆኑን እንደማስረዳት የሚከብድ ነገር የለም። በድንግል ማርያም ስዕል ፊት ቆመን በአይነ ህሊናችን እርሷን እየተመለከትን ለርሷ ያለንን ፍቅር በትህትናና በስግደት መግለጽ በምን ዓይነት መንገድ ጣዖት ማምለክ ሊሆን ይችላል። በስዕል ፊት መስገድ ለስዕሉ ባለቤት መስገድ ነው በስላሴ ወይም በጌታ ስዕል ፊት የአምልኮ ስግደት እንሰግዳለን በመላእክት ወይም በቅዱሳን ስዕል ፊት በትህትናና በፍቅር ሆነነ ለስዕሉ ባለቤት የአክብሮት ስግደት እንሰግዳልን ለማን እንደምንሰግድና ምን ዓይነት ስግደት እንደምናቀርብ የምናውቀው እኛው ነን አንድ ሰው በቅዱሳን ስዕል ፊት ስሰግድ እያመለካቸው ነው ቢለኝ ከባለቤቱ ያወቀ ቡዳ ነው እለዋለው። የለጥርጥር የጽሑፍ እውቀት ላለነበራቸው ክርስቲያኖች ስዕል መጽሐፍ ቅዱሳቸው ነበረ ነውም ወንጌልን በልባቸን ለመቅረጽ በአይናቸው ፊት የተሳለው ስዕል ታላቅ አስተዋጽኦ አለው የስዕል ዓላማውም ወንጌልንና የስዕሉን ባለቤት ፍቅር በልባችን እንዲሳል መርዳት ነው ዮሐንስ ደማሰከስ የተባለ አባት በቅዱሳተ ስዕላት አማካኝነተ ህሊናችን ወደ ሰማያዊው የቅዱሳን ህብረት ይነጠቃል ይገልጻል ር ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙም አብርሐም ይስሀቅን የሚሰዋበትን ስዕል ስመለከት አይኖቼ በእንባ ይሞላሉ በማለት ገልዷጺል። መር ጳውሎስ ለዚህ ነው የገላትያ ከርስትያኖችን የማታስተውሉ የገላትያ ሰዎች ሆይ በዓይናችሁ ፊት ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ተሰቀለ ሆኖ ተሥሎ ነበር ለእውነት እንዳትታዘዙ አዚም ያደረገባችሁ ማን ነው በማለት የገሰጸው ገላ በክርስትና ታሪክ ቅዱሳት ስዕላትን መጠቀም የጀመሩት የመጀመሪያዎቹ ሐዋርያት ናቸው። የጌታን የስቅለት ስዕል የሳለው ደግሞ ወንጌላዊው ዮሐንስ ነው ይህንን አውነት የታሪክና የትውፊት ማስረጃዎች ያረጋግጣሉ ይህንን ይበልጥ መመርመርና መረዳት የፈለገም ከቤተክርስቲያችን መጻህፍት በተጨማሪ ጥንታውያን የክርስትና መጻሕፍትን ም ሽና የካቶሊክ ኢንሳይክሎቲዲያዎችን እንዲሁም ዊኪፒዲያና ተመሳሳይ የመረጃ ምንጮች ላይ መመልከት ይቻላል በክርስትናው ታሪክ አብዛኛዎቹ ጥንታውያን አባቶች ስለ ሰዕል በዙ ተናግረዋል ጽፈዋልም የሐዋያው ዮሐንስ ደቀመዝሙር ሰማዕቱ ፖሊካርፐስ ዝዩ እቴሃፕዐዐኗ ዐ ኮዐቨርጳፔ ቅዱስ ሄራኒየስ ርበ ለ ታዋቂው የመጀመሪያወ መቶ ክዘ ታሪክ ጸሐፊ ቱርቱሊያን ኬ ኮህጩጠርቨ የቅዱስ ጴጥሮስ ደቀ መዝሙር ቅዱስ ቀለሜንጦስ ርዝፎከበጴፎጁ ዥዐርሠርዐቪ ኦሪገን አውሳብዮስ ህ ቪዜጄ ሂቨ ክክክፀ ቅዱስ ፓውሊኒዮስ ከህ ዐ እርዐዘ ሠ ቅዱስ ባስልዮስ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ቅዱስ ኤጺፋንዮስ ወዘተ እኒህ ሁሉ አባቶች ስለ ስዕል የጻፉልንን መዘርዘር ቅዱስ ጳውሎስ ሁሉንም እንዳልተርክ ጊዜ ያጥርብኛል እንዳለው ይሆንብናል ሰለዚህም በጥልቀት ጥናት ማድረግ ማወቅ የፈለገ ሰው የአባ ታድሮስ ማላቲን ዝጄ ርዉርዘ ዘበ መ ርዐዑ መጽሐፍቸውንና በህዳግ የተጠቀሱትን ሌሎች በርካታ መጻህፍት ከሌሎች የኢንተርኔት መረጃዎች ጋር በማጣመር አንድ መጽሐፍ ሊወጣው የሚችል ብዙ እውቀት መሸመት ይቻልል አኔ ግን ከዚ በላይ እንዳልሄድ ጌዜ ገደበኝ ወስብሐት ለእግዚአብሔር።