Detecting...
Please whitelist dirzon to continue.
ድኅነት በመጽሐፍ ቅዱስ መዳን ተብለው የተገለጹ የተለያዩ ነገሮችን እናገኛለን ከእነዚህም ለምሳሌ ያህል የሚከተሉትን መጥቀስ ይቻላል ኖኅና ቤተሰቦቹ በመርከብ አማካይነት ከጥፋት ውኃ መዳናቸው እስራኤላውያን ከግብፅ ባርነት ነጻ መውጣታቸው እና በባሕር መካከል በደረቅ መሸጋገራቸውና ሲከተሏቸው ከነበሩት ጠላቶቻቸው እጅ መዳናቸ ንዕማን ሶርያዊ ከነበረበት ለምጽ በዮርዳኖስ ውኃ ታጥቦ መዳኑ እስራኤላውያን በንጉሁው በሕዝቅያስ ዘመን ከሰናክሬም እጅ በተአምራት መዳናቸው ሆኖም እነዚህ ሁሉ መዳኖች ድኅነቶችን ለጊዜው ድኅነቱ የተደረገላቸውን ሰዎች ያስደሰቱና ከመከራ ያዳኑ ነገሮች ቢሆኑም ሁሉም ጊዜያዊና ድኅነታቸው በሥጋና በዚህ ዓለም የተወሰነ ነበር ይህም ማለት የሰውን ልጅ ሲያስፈራና ሲያስደነግጥ የኖረውን ሞት ከሥሩ ነቅሎ ያጠፋልንና ያስወግድልን ዘንድ ክብር ምስጋና ለዘለዓለሙ ለእርሱ ይሁንና ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ ያላቸው በጥምቀት ሥርየት ኃጢአትና ድኅነት የሚገኝ በመሆኑ ነው በሁለተኛው ዓለም አቀፋዊ የቤተ ክርስቲያን ጉባኤ በ ዓም በቁስጥንጥንያ የተሰበሰቡት ቅዱሳን አባቶችም በጸሎተ ሃይማኖት ላይ ወነአምን በአሐቲ ጥምቀት ለሥርየተ ኃጢአት ኃጢአት በሚሠረይባት በአንዲት ጥምቀት እናምናለን ያሉት ለዚህ ነው ከላይ እንደ ተገለጸው ሕፃናትም እንዲጠመቁ የሚደረገው ጥምቀት ለድኅነት ወሳኝ ስለ ሆነ ነው።
ሐዋርያው እርሱ ደግሞ በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን በሞት እንዲሽር ይኸውም ዲያብሎስ ነው በሕይወታቸውም ሁሉ ስለ ሞት ፍርሃት በባርነት ይታሰሩ የነበሩትን ሁሉ ነፃ እንዲያወጣ በሥጋና በደም እንዲሁ ተካፈለ አለ ዕብ ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ የቃልን ሥጋ መሆን በተናገረበት ድርሳኑ ስለዚህ ሲናገር እንዲህ አለ በመሞት ካልሆነ በቀር የሰው ሞት ሊወገድ እንደማይችል እግዚአብሔር ቃል ባየ ጊዜ እርሱ በባሕርዩ የማይሞት ስለ ሆነ ስለ ሁሉም መሞት ይችል ዘንድ የሚሞት የእኛን ባሕርይ ተዋሐደ የእኛ ባሕርይ ከተዋሐደው ቃል የተነሣ የማይሞት ይሆን ዘንድ መፍረስና መበስበስም በትሣኤ ይጠፋ ዘንድ የነሣውን ሥጋ ከበደል ንጹሕ የሆነ መሥዋዕት አድርጎ በማቅረብና ለሞት በመስጠት ሞትን ከወገኖቹ አስወገደ የሞትን ዕዳ ሞትን በመክፈል ከእኛ አስወገደው ሞትና ጥፋት የእኛን ሥጋ ከተዋሐደው ከአካላዊ ቃል የተነሣ እኛን ሊገዛና ሊይዝ አልተቻለውም የሁሉ ጌታና መድኃኒት መጥቶ ሞትን ድል ባያደርገው ኖሮ የሰው ዘር ጠፊ ነበር ስለሆነም ክርስቶስ በሞቱ ድል ካደረገው ወዲህ ሞት ኃይሉን ያጣ ደካማ የቀድሞ አስፈሪነቱ ቀርቶ በክርስቲያኖች ዘንድ መሳለቂያና ወደ ማያልፈው ዓለም መሄጃ መንገድ ሆኗል በዘመነ ክርስትና ሞት ጥፍሩ እንደ ወለቀ ጥርሱ እንደረገፈና ኃይሉ እንደ ደከመ ከዚህም የተነሣ የሕፃናት መጫወቻ እንደ ሆነ አንበሳ እንዲሁም መርዙ እንደ ወጣና ምንም ጉዳት ማድረስ እንደማይችል እባብ ሆኗል ሞት በሰው በአዳምን በኩል መጥቶ በሰው ላይ እንደ ነገሠ በዚሁ መንገድ ሰው በሆነ የእግዚአብሔር ቃል ሞት ተወገደ። ቆሮ መቃብርም ለዘለዓለም በዚያው ውስጥ ይዞ የሚያስቀረን ሳይሆን እስከ ትንሣኤ ድረስ የምንቆይበትና ከዚያም የሚበሰብሰው የማይበሰብሰውን የሚሞተው የማይሞተውን ለብሶ የሚነሣበት ነው በዚያን ጊዜም በኃጢአት ምክንያት ከሰው ተፈጥሮ በኋላ የመጣው የኋለኛው ጠላት ሞት ድል ይነሣል ቆሮ እሳት የሚኖረው የሚቃጠል ነገር እስካለ ድረስ ብቻ እንደ ሆነ ሁሉ ሞትም ከትንሣኤ በኋላ የሚሞት ሰውነት ስለማይኖር ራሱ ይሞታል ለዘለዓለም ይጠፋል ይህን ነው ሐዋርያው በመልእክቱ እንዲህ በማለት የገለጸው ሙታንም የማይበሰብሱ ሆነው ይነሣሉ እኛም እንለወጣለን ይህ የሚበሰብሰው የማይበሰብሰውን ሊለብስ ይህም የሚሞተው የማይሞተውን ሊለብስ ይገባዋልና ዳሩ ግን ይህ የሚበሰብሰው የማይበሰብሰውን ሲለብስ ይህም የሚሞተው የማይሞተውን ሲለብስ በዚያን ጊዜ ሞት ድል በመነሣት ተዋጠ ተብሎ የተጻፈው ቃል ይፈጸማል ቆሮ ወደ እግዚአብሔርና ቅዱሳን አንድነት ተመለሰ ሰላምን አገኘ ሰው ከእግዚአብሔር አንድነት ተለይቶ የተስፋ ቦታውን አጥቶ ከዓለመ መላእክት ወደ ዓለመ እንስሳት ተጥሎ ነበር ክብር ምስጋና ይግባውና አካላዊ ቃል እግዚአብሔር ወልድ በተለየ አካሉ ሰው ሆኖ ሰው ወደ ወደቀበት ወደዚህ ዓለም በመምጣትና በእንስሳት በረት በመወለድ የሰውን ልጅ ወደ ራሱ ኅብረትና አንድነት መለሰው በዚህም መላእክት ከሰዎች ጋር በአንድነት ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር ሥምረቱ ለሰብእ ክብር ለእግዚአብሔር በሰማያት ይሁን ሰላምም በምድር ለሰውም በጎ ፈቃድ በማለት ሰው ወደ እግዚአብሔር በመመለሱ ደስታቸውን ገለጹ ሉቃ በመስቀሉ ቤዛነትም በሰውና በእግዚአብሔር መካከል የነበረው የጠብ ግድግዳ ፈረሰ ቅዱስ ጳውሎስ ለኤፌሶን ክርስቲያኖች በላከው መልእክቱ ይህን እንዲህ ሲል ገልጾታል ሁለቱን ያዋሐደ በአዋጅ የተነገሩትንም የትእዛዛትን ሕግ ሽሮ በመካከል ያለውን የጥል ግድግዳ በሥጋው ያፈረሰ እርሱ ሰላማችን ነውና ይህም ከሁለታቸው አንድ አዲስን ሰው በራሱ ይፈጥር ዘንድ ሰላምንም ያደርግ ዘንድ ጥልንም በመስቀሉ ገድሎ በእርሱ ሁለታቸውን በአንድ አካል ከእግዚአብሔር ጋር ያስታርቅ ዘንድ ነው መጥቶም ርቃችሁ ለነበራችሁ ለእናንተ ሰላምን ቀርበው ለነበሩትም ሰላምን የምሥራች ብሎ ሰበከ በእርሱ ሥራ ሁላችን በአንድ መንፈስ ወደ አብ መግባት አለንና ኤፌ ክርስቶስ ስላማችን ብቻ አይደለም ይህን ሰላም ራሱን መሥዋዕት አድርጎ በመስጠት አመጣ እንጂ ሰው ከፈጣሪው ጋር ከተጣላበት ጊዜ ጀምሮ ሐዘን የከበበውና የተቅበዘበዘ ነበር ነቢዩ በትንቢት ሜጥከ ላሕየ ወአስተፍሣሕከኒ ሠጠጥከ ሠቅየ ወሐሣተ አቅነትከኒ ልቅሶዬን በደስታ ለወጥክልኝ ማቄን ቀደድህ ደስታንም አስታጠቅኸኝ ብሎ እንደ ተናገረ ሐዘኑን አስወግዶ ደስታን ሰጠው መዝ ፀዐ መድኃኒታችን ሰላሜን እተውላችኋለሁ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ አለ ዮሐ ይህንም በመስቀሉ ላይ ባደረገው መሥዋዕትነት አረጋገጠ በዚህም ከቅዱሳን አንድነት ደመረን ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ክርስቶስ በመስቀሉ ቤዛነት ጥልን ማስወገዱንና ሰላምን ማድረጉን ከገለጸ በኋላ የዚህን ተከታይ ውጤት ሲናገር እንዲህ አለ እምይእዜሰ ኢኮንክሙ ነግደ ወፈላሴ አላ አንትሙ ሰብአ ሀገሪቶሙ ለቅዱሳን ወሰብአ ቤቱ ለእግዚአብሔር እንግዲያስ ከእንግዲህ ወዲህ ከቅዱሳን ጋር ባላገሮች እና የእግዚአብሔር ቤተ ሰዎች ናችሁ እንጂ እንግዶችና መጻተኞች አይደላችሁም ኤፌ እንዲሁም በዕብራውያን መልእክቱ ይህንኑ በተመለከተ ማለትም የሰውን ወደ ቅዱሳን አንድነት መመለስ ሲናገር እንዲህ አለ ወደ ጽዮን ተራራና ወደ ሕያው እግዚአብሔር ተራራ ደርሳችኋል ወደ ሰማያዊቱም ኢየሩሳሌም በደስታም ወደ ተሰበሰቡት ወደ አእላፋት መላእክት በሰማያትም ወደ ተጻፉ ወደ በኩራት ማኅበር የሁሉም ዳኛ ወደ ሆነ ወደ እግዚአብሔር ፍጹማንም ወደ ሆኑት ወደ ጻድቃን መንፈሶች የአዲስ ኪዳንም መካከለኛ ወደሚሆን ወደ ኢየሱስ ደርሳችኋል ዕብ ጌታችንም ሰው አስቀድሞ በመብል ምክንያት ከእርሱ ተለይቶ ነበርና በፍጹም ቸርነቱና ፍቅሩ ራሱን መብልና መጠጥ አድርጎ በመስጠት ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ በእኔ ይኖራል እኔም በእርሱ እኖራለሁ ዮሐ በማለት በራሱ መሥዋዕትነት ከእርሱ ጋር ፍጹም አንድነትን ሰጠን። መዳናችን ድኅነታችንን የተገኘው በእኛ ሥራ መልካምነት አይደለም እግዚአብሔር የሰውን ልጅ ከሞት ወደ ሕይወት ያሸጋገረው እርሱን የሚያስደስትና እንዲያ እንዲያደርግለት የሚያበቃው የተቀደሰ ሕይወት ስለነበረው አይደለም በኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ ሰው የዳነው በእግዚአብሔር ቸርነት ጸጋን ነው የሰው ድኅነት የእግዚአብሔር የቸርነቱ ስጦታና ለሰው ያለው የማይለወጥ ፍቅር ውጤትና መገለጫ ነው የእኛን የቀደመ ሁኔታና እግዚአብሔር እንዴት እንዳዳነን ሐዋርያው ግልጽ በሆነ ሁኔታ እንዲህ ሲል ያስተምረናል እኛ ሁላችን ደግሞ የሥጋችንንና የልቡናችንን ፈቃድ እያደረግን በሥጋችን ምኞት በፊት እንኖር ነበርን እንደ ሌሎችም ደግሞ ከፍጥረታችን የቁጣ ልጆች ነበርን ነገር ግን እግዚአብሔር በምሕረቱ ባለጸጋ ስለሆነ ከወደደን ከታላቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወትን ሰጠን በጸጋ ድናችኋልና በሚመጡ ዘመናትም በክርስቶስ ኢየሱስ ለእኛ ባለው ቸርነት ከሁሉ የሚበልጠውን የጸጋውን ባለጠግነት ያሳይ ዘንድ ከእርሱ ጋር አስነሣን በክርስቶስ ኢየሱስም በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን ኤፌ ሰው ሁሉ በአዳም በደል ምክንያት የቁጣ ልጅ ነበር ሁሉም በኃጢአት ምክንያት የሞተ ነበር ሮሜ ። ዐ አሁንም ይኸው ሐዋርያ ስለዚሁ ጉዳይ ሲናገር ለደቀ መዝሙሩ ለቲቶ በላከው መልእክቱ እንዲህ አለ እኛ ደግሞ አስቀድመን የማናስተውል ነበርንና የማንታዘዝ የምንስት ለምኞትና ለልዩ ልዩ ተድላ እንደ ባሪያዎች የምንገዛ በክፋትና በምቀኝነት የምንኖር የምንጣላ እርስ በርሳችን የምንጠላላ ነበርን ነገር ግን የመድኃኒታችን የእግዚአብሔር ቸርነትና ሰውን መውደዱ በተገለጠ ጊዜ እንደ ምሕረቱ መጠን ለአዲስ ልደት በሚሆነው ጥምቀትና በመንፈስ መታደስ አዳነን እንጂ እኛ ስላደረግነው በጽድቅ ስለነበረው ሥራ አይደለም ቲቶ ጌታችንና መድኃኒታችንም እግዚአብሔር ሰውን የወደደውና ያዳነው እንዲሁ በአባታዊ ፍቅሩ መሆኑን ሲገልጽ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን ሰውንን እንዲሁ ወዷልና አለ ዮሐ የወደደን እንዲሁ በቸርነቱ እንጂ እንዲወደን የሚያደርግ መልካም ሥራ ስለነበረን ወይም እኛ ስለ ወደድነው አይደለም ሰውማ በራሱ ጥፋት ከአምላኩ ፊት የኮበለለ ነበር ጌታችን በጠፋው በግ ምሳሌ እንደ ተናገረው የጠፋውን አዳምን የሰውን ልጅ በሙሎ ይፈልገውና ወደ ቀደመ ክብሩ ይመልሰው ዘንድ ከሉዐላዊ መንበሩ ወርዶ ፈለገው ባገኘውም ጊዜ ለመፈለግ በደከመው ድካም ሳይቆጣው ሳይገርፈው በእግርህ ሂድ ሳይለው በማግኘቱ ተደስቶ በጫንቃው ላይ ተሸከመው በጠፋው ልጅ ምሳሌ እንደ ተናገረው ያጠፋውን ጥፋትና የበደለውን በደል ሳያሰብ አዘነለት በፍጹም ፍቅር ተቀበለው የሰባውን በማረድ የራሱን ቅዱስ ሥጋውን በመቁረስና ክቡር ደሙን በማፍሰስ በዓል አደረገለት ይህ ልጄ ሞቶ ነበርና ደግሞም ሕያው ሆኗል ጠፍቶም ነበር ተገኝቷልም ደስ እንዲለን ፍሥሐም እንድናደርግ ይገባናል አለ ሉቃ ቅዱስ ጳውሎስም ይህንኑ ሲገልጽ እናንተንም ነውርና ነቀፋ የሌላችሁና ቅዱሳን አድርጎ በእርሱ ፊት ያቀርባችሁ ዘንድ በፊት የተለያችሁትን ክፉ ሥራንም በማድረግ በአሳባችሁ ጠላቶች የነበራችሁትን አሁን በሥጋው ሰውነት በሞት በኩል አስታረቃችሁ አለ ቆላ ይህን ሁሉ አጠቃልሎ ወሶበ እንዘ ጸሩ ንሕነ ለእግዚአብሔር ተሣሃለነ በሞተ ወልዱ እግዚአብሔር ጠላቶቹ ሳለን በልጁ ሞት ታረቀን አለ ሮሜ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስም እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ በመገረፉ ቁስል ተፈወሳችሁ በማለት የዳንነው ክርስቶስ በቸርነቱ በተቀበለው ሕማምና መከራ መሆኑን ይነግረናል ጴጥ ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስም እንዲህ ይላል በዚህ የእግዚአብሔር ፍቅር በእኛ ዘንድ ተገለጠ በእርሱ በኩል በሕይወት እንኖር ዘንድ እግዚአብሔር አንድ ልጁን ወደ ዓለም ልኮታልና ፍቅርም እንደዚህ ነው እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደ ወደደን ስለ ኃጢአታችንም ማስተሥረይ ይሆን ዘንድ ልጁን አንደ ላከ እንጂ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው አይደለም። ዮሐ የወደቀውንና የሞተውን የሰው ልጅ ያዳነው የእግዚአብሔር ቸርነት እንጂ የእርሱ ሥራ አይደለም ሰው በሥራው ብቻ የሚጸድቅ ቢሆን ኖሮ በብሉይ ኪዳን የነበሩ ደጋግ አባቶች ለመዳን ክርስቶስ ባላስፈለጋቸው ነበር ነገር ግን ምንም እንኳ በደጋግ ሥራቸው በኃጥአን ላይ የሚደርሰው መከራ ሙሉ በሙሉ ባይደርስባቸውም ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋውን ቆርሶ ደሙን አፍስሶ በአዳም በደል ምክንያት የተዘጋችውን ገነት እስኪከፍታት ድረስ ከሲኦል መውጣትና ወደ ገነት መግባት አልቻሉም በኃጢአት ምክንያት ከመጣው ፍዳ አንዷንም ፈቀቅ ማድረግ አልቻሉም ስለዚህ እኛን ያዳነን የክርስቶስ ቸርነት እንጂ ሥራችን አይደለም ማለት ነው እንደ ሥራችንማ ቢሆን እግዚአብሔር ሰው ኾኖ ኃጥአን ለሆንነው ለእኛ መከራ ይቀበል ዘንድ የሚያበቃው የትኛው ሥራችን ነበርን በእኛ ሥራ ቢሆንማ ኖሮ እንኳን ይህ ሁሉ ቸርነት ሊደረግልን ቀርቶ ከተደረገልን ቸርነት አንዷንም እንኳን ባላገኘን ነበር የእግዚአብሔር ስጦታ በዋጋ የሚገዛ አይደለም በኃጢአት ድካም ሳለን በቸርነቱ የወደደንና ያዳነን መሆኑን በማድነቅ ሐዋርያው እንዲህ ይላል ግና ደካሞች ሳለን ክርስቶስ ዘመኑ ሲደርስ ስለ ኃጢአተኞች ሞቷልና ስለ ጻድቅ የሚሞት በጭንቅ ይገኛልና ስለ ቸር ሰው ግን ሊሞት እንኳ የሚደፍር ምናልባት ይገኝ ይሆናል ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቷልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል ሮሜ ቅዱስ ጳውሎስ በሚገባ እንደ ገለጸው እኛ ጻድቃን ሆነን ክርስቶስ ቢሞትልን ኖሮ ምናልባት ብዙም ላይደንቅ ይችል ይሆናል ምክንያቱም ለጻድቅ ሰው ተላልፎ የሚሞት ምናልባት ይገኝ ይሆናልና ነው ነገር ግን ኃጢአተኞች ሳለን ስለ እኛ መሞቱ እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ፍጹም ፍቅርና የቸርነቱን ገናናነት ያስረዳል ለምሳሌ ለሞት የሚያበቃ ወንጀል ሠርቶ ሞት ለተፈረደበት ኃጢአተኛ ሰው እኔ እሞትለታለሁ ብሎ ራሱን አሳልፎ የሚሰጥ ማን ነውን ክርስቶስ ለእኛ ያደረገው ይህንን ነው በኃጢአታችን ሞት የተፈረደብን የሞት ሰዎች ሳለን በፍጹም ፍቅሩ ስለ እኛ ራሱን ቤዛ አድርጎ ሰጠ ሞተልን በሞቱም ከሞት አዳነን ሕይወትን ሰጠን ይህ የእርሱ የጸጋ ስጦታ ብቻ ነው ሕይወትን ሰጠን ይህ የእርሱ የጸጋ ስጦታ ብቻ ነው ኢሳ ይህን ሁሉ ቸርነት ያደረገልን የሞት ሰዎች ሳለን በማይነገር ፍቅሩ ሕይወትን የሰጠን አምላካችን እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን አሜን ሰው ለመዳን ምን ያስፈልገዋል። ሰውን ያዳነው የእግዚአብሔር ጸጋ መሆኑ ተገልጂል ነገር ግን ይህን መዳን ለመፈጸምና በተሰጠው የመዳን አገልግሎት ተጠቃሚ ለመሆን ከእያንዳንዱ ሰው የሚጠበቅ ነገር አለ ሐዋርያው የእግዚአብሔርን የማዳን ነገር ሲገልጽ እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንሆን ዘንድ ኃጢአት ያላወቀውን እርሱን ስለ እኛ ኃጢአት አደረገው በማለት ንጹሐ ባሕርይ የሆነ ክርስቶስ ስለ እኛ ኃጢአት ኃጥእ ተብሎ መከራ በመቀበሉ የእኛ ኃጢአት መወገዱንና በእርሱ ኃጥእ መባል እኛ የእግዚአብሔር ጽድቅ መሆናችንን ገለጸ በመቀጠልም እንዲህ አለ አብረንም እየሠራን የእግዚአብሔርን ጸጋ በከንቱ እንዳትቀበሉ ደግሞ እንለምናለን ቆሮ ይህም ማለት እግዚአብሔር ያደረገልንን የማዳን ጸጋ ለመቀበል ከእኛ የሚጠበቀውን ምንም እንኳ የምናደርገው ነገር ለጸጋው ምንም የማይመጥንና እዚህ ግባ የሚባል ባይሆንም ነገር ሳናደርግ እንዳንቀር ነው ይህም እያንዳንዳችን ማድረግ ያለብን የራሳችን ድርሻ ያለ መሆኑን በግልጽ የሚያስገነዝብ ነው ከእርሱ የሚጠበቅበትን ለማይፈጽም ሰው የእግዚአብሔር ሰውን ማዳን ብቻ በራሱ ተጠቃሚ አያደርገውም አንድ ሰው ለመዳን የሚከተሉትን መፈጸም ይኖርበታል እግዚአብሔር ሰውን ለማዳን በፈቃዱ ያደረገውን ነገር ሁሉ ማመንና መቀበል እምነትን ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው ሆኖ ከመወለድ ጀምሮ ለሰው ሲል ያደረውን መጠመቁን ዞሮ ማስተማሩንና ያስተማረውን ቃልና ትእዛዝ ማመንን መከራ መቀበሉን በመጨረሻም በራሱ ፈቃድ ለእኛ ሲል መሞቱን መቀበሩንና በሦስተኛው ቀን መነሣቱን እና በአርባኛው ቀን ወደ ቀደመ ክብሩ ማረጉን በአጠቃላይ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የምታምነውን ሁሉ በፍጹም ልብ ማመን ያስፈልጋል እግዚአብሔር እኛን ለማዳን ያደረገውን ልዩ ቸርነትና እናምነው ዘንድ የገለጠውን እውነት የማያምን ሰው ሊድን አይችልዎ እግዚአብሔር ያደረገውን ቸርነትና የፈጸመውን ድኅነት ለማያምን ሰው ለእርሱ ልክ የሰው ድኅነት እንዳልተፈጸመና ገና እንዳልዳነ ይሆንበታል ይህም ማለት በኢየሱስ ክርስቶስ የማያምን ሰው አሁን እየኖረበት ያለው ዘመኑ ዘመነ ወንጌል ዓመተ ምሕረት ቢሆንም እርሱ ግን በዘመነ ኦሪት በዓመተ ፍዳ እንደ ነበሩት ሰዎች ይሆናል ማለት ነው በእርግጥ እንዲያውም በዚያ ዘመንም ወደፊት በዘመነ ወጌል የሚሆነውን በእምነት አሻግረው ያዩና በተስፋ የጠበቁ ደጋግ አበው ነበሩ ከዘመኑ ሳይደርሱ እንደ ደረሱ ሆነው ሥጋዌው ከፊታቸው ግልጽ ብሎ እየታያቸው ዕለቱን እንደ ተፈጸመ እያደረጉ ትንቢት የተናገሩ ነቢያትም ነበሩ አሁን በዘመነ ወንጌል በዓመተ ምሕረት እየኖረ የማያምን ኢአማኒ ሰው ግን ከዘመነ ብሉይ እንደ ነበሩት አሕዛብ ያለ ነው ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ በኢየሱስ ክርስቶስ ያላመነን ሰው ምን እንደሚገጥመው ሲናገር በልጁ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቁጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም ያለው ለዚህ ነው ዮሐ ጌታችን በቅዱስ ቃሉ እውነት እውነት እላችኋለሁ ቃሌን የሚሰማ የላከኝንም የሚያምን የዘለዓለም ሕይወት አለው ከሞትም ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም በማለት ማመን የሕይወት መንገድ መሆኑን አስተምሯል ዮሒ እንዲሁም በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘለዓለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር እንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዷልና በእርሱ በሚያምን አይፈረድበትም በማያምን ግን በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመነ አሁን ተፈርዶበታል በማለት በእርሱ ማመን የድኅነት መሠረት ሲሆን አለማመን ደግሞ የፍርድና የሞት መንገድ መሆኑን ግልጽ ባለ ቃል አስረዳ ዮሐ ዮሐ ዮሐ ጌታችን የሰጠኸኝን ቃል ሰጥቻቸዋለሁና እነርሱም ተቀበሉት ከአንተም ዘንድ እንደ ወጣሁ በእውነት አወቁ አንተም እንደ ላክኸኝ አመኑ በማለት እምነት እርሱ የነገረንን ቃል መቀበልና ማመን መሆኑን ተናግሮፖል ዮሐ በአጠቃላይ እግዚአብሔር እርሱን ማወቅ በምንችለው መጠን እናውቀውና እናምነው ዘንድ ወደ እውነት ይመራን ዘንድ በቅዱስ መጽሐፍ የገለጠውን እውነት መቀበልና ማመን ለድኅነት የግድ ነው ያለ እምነት እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት አይቻልም ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና እንደ ተባለ ዕብ ሃይማኖት የድኅነት መሠረት ነው ቤት ያለ መሠረት ሊቆም እንደማይችልና በአየር ላይ ሕንፃ መገንባት እንደማይቻል ሁሉ የዘለዓለማዊ ድኅነት መሠረትም ሃይማኖት ነው ለመዳን አንድ አምላክ የሆነውንና በአንድነቱ ውስጥ ልዩ ሦስትነት ያለውን የሕያወ ባሕርይ የእግዚአብሔርን ህልውናውን ፈጣነቱን አዳኝነቱን ማመን የእግዚአብሔር ወልድን ሥጋዌውን ሞቱን ተዋሕዶውን ትንሣኤውን ማመን ለመዳን ሊታለፉ የማይችሉ ቁልፎች ናቸው ያለዚህ እምነት ወይም ከዚህ የወጣ እምነት አያድንም ለድኅነት መሠረታዊ የሆኑ ምሥጢራትን መፈጸም ከማመን ቀጥሎ ለድኅነት ወሳኝና አስፈላጊ የሆኑ ምሥጢራትን መፈጸም ይገባል እነዚህም በመጀመሪያ ጥምቀት ሜሮን እና ቁርባን ሲሆኑ ከዚያ በኋላ በሕይወት ሂደት ለሚገጥሙ ነገሮች ደግሞ ንስሐ ናቸው። ጌታችን በግልጽና በአጽንኦት ደጋግሞ እንዳስተማረው የእርሱ ቅዱስ ሥጋና ክቡር ደም የዘለዓለም ሕይወትን የምናገኝበትና ከእርሱ ጋር ተዋሕደን የምንኖርበት የሕይወት ምግብ ነው እንዲሁም ሥጋውን ስንበላና ደሙን ስንጠጣ በመስቀል ላይ ስለ እኛ የተቀበለውን መከራ ሕማሙንና ሞቱን ትንሣኤውንና ዕርገቱን በአጠቃላይ ለእኛ ሲል ያደረገውን ቸርነትና የደረሰበትን መከራ ሁሉ እናስታውሳለን ቆሮ ስለዚህ ይህን በቸርነቱ የሰጠንን አማናዊ የሕይወት ምግብ እየተዘጋጀን መመገብ ይገባናል አስቀድሞ አትብሉ ተብለን ሳለ በልተን ሞትን አሁን ደግሞ ብሉ ስንባል አንበላም ብለን ብንሞት ሁል ጊዜ የተባለውን ትቶ ያልተባለውን ማድረግና ዓመፀኛነት ይሆንብናል ይህንም አንድ ጊዜ ብቻ ሳይሆን ንስሐ እየገባን ስለ ኃጢአታችን ዕለት ዕለት የሚሠዋውን የክርስቶስን ቅዱስ ሥጋ ክቡር ደም መቀበል ይገባል ምሳሌው የነበረውን መና እስራኤላውያን በምድረ በዳ ሳሉ አርባ ዓመት ሙሉ ሕፃናትም አዋቂዎችም ሴቶችም ወንዶችም ሁሉም በየዕለቱ ሲመገቡ እንደ ኖሩ ሁሉ አማናዊ የሆነውን የክርስቶስን ቅዱስ ሥጋና ክቡር ደምም የዕድሜና ሌላ ልዩነት ሳይኖር ሁሉም አንድ ጊዜ ወይም ለተወሰነ ጊዜ ብቻ ሳይሆን በዚህ ዓለም ሕይወት እሰካሉ ድረስ መቀበል ይገባል ኃጢአትን ለማሸነፍ ኃይልን መንገድ በሆነ በዚህ ዓለም ውጣ ውረድ ደክመን እንዳንዝል ጽናትን የምናገኘው በዚህ ነውና ቆሮ እነዚህን ምሥጢራት ማለትም ምሥጢረ ጥምቀትን ምሥጢረ ሜሮንን እና ምሥጢረ ቁርባንን ያልፈጸመ ድኅነት የለውም ከዚህ በኋላ ባለው ሕይወት ለሚገጥሙ ውጣ ውረዶች ደግሞ ምሥጢረ ንስሐ አስፈላጊ ነው ጥምቀትና ሜሮን የማይደገሙ ሲሆን ምሥጢረ ቁርባን ግን ከላይም አንደ ተገለጸው ሁል ጊዜ ሊፈጸም የሚገባው ነው ከዚህ በኋላ ባለው ሕይወት ለሚገጥሙ ውጣ ውረዶች ደግሞ በምሥጢረ ንስሐ አማካይነት የሚፈጸሙ ይሆናሉ ሕጉን መጠበቅ ትእዛዙን መፈጸም ምግባር ትሩፋት መሥራት አንድ ወጣት ባለጸጋ ወደ ጌታችን ቀርቦ የዘለዓለምን ሕይወት አንዳገኝ ምን ላድርግን ብሎ ሲጠይቀው ጌታችን ወደ ሕይወት መግባት ብትወድ ትአዛዛትን ጠብቅ አለው ማቴ ወደ አግዚአብሔር መንግሥት ለመግባት ማመን ብቻ ሳይሆን በተግባርም የእግዚአብሔርን ፈቃድ መፈጸም እንደሚያስፈልግ ሲናገር በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ የሚለኝ ሁሉ ወደ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም አለ ማቴ ። ማቴ በመሆኑም የሰው ልጅ ይድን ዘንድ ሥጋውን የሚጎስምባቸውና ራሱን የሰው ልጅ ይድን ዘንድ ሥጋውን የሚጎስምባቸውና ራሱን ለፈቃደ እግዚአብሔር የሚያስገዛባቸው መንፈሳዊ ተጋድሎዎች ጾም ጸሎት ስግደት ዐቂበ ሕዋሳት ምጽዋት ትዕግሥት ትሕትና ያስፈልጉታል እግዚአብሔር ዓለምን ሁሉ አድኗል ማለት ዕዳችን ተከፍሏል የድኅነት መንገዱ ተከፍቷል ማለት ነው በዚህ ነገር እሺ ብሎ ለመጠቀም አለዚያም እምቢ ብሎ ለመጎዳት ለእያንዳንዱ ሰው ነጻ ፈቃድ ተሰጥቶታል እግዚአብሔር ሰውን ወደ ዘለዓለማዊ ሕይወት ይገባ ዘንድ በፍቅሩ ይጠራዋል ይመራዋል የተለያየ የቸርነት ሥራውን ይሠራለታል እንጂ ሰውዬው ሳይፈልግ በግድ ጎትቶ አያመጣውም ይህም ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ ባለው ቅዱስ ቃሉ ግልጽ ሆኖ ይታያል ዮሐ ማንም ሰው ትእዛዙን ጠብቆ የመጠቀም ያልፈለገ ደግሞ ባለመጠበቅ ሊጎዳ ነጻ ፈቃድና ሙሉ መብት አለው ጌታችን አልዓዛርን ከመቃብር ሲያስነሣ የመቃብሩን ድንጋይ ሰዎች እንዲያሠ ሲያደርግ እርሱ ደግሞ ከሞተ አራት ቀን የሆነውን ጠርቶ አስነሣው ይህን ማድረጉ ሰው በድኅነቱ ላይ የራሱ የሆነ ድርሻ እንዳው ለማሳየት ነው ዮሐ የእያንዳንዱ ሰው ድኅነት በራሱ ላይ የተመሠረተ ስለ መሆኑ ምንም እንኳ ሰውን የሚያጸድቀው የእግዚአብሔር ቸርነት እንጂ የእርሱ ሥራ በራሱ ባይሆንም በእግዚአብሔር ቸርነት ለመጠቀምም ቢሆን ከሰው የሚጠበቅ ነገር መኖሩን አይተናል ኃጥአን የሚፈረድባቸው የእግዚአብሔርን ቸርነት ለመጠቀም የሚያስችል ሥራ ስላልሠሩና በዓመፅ ስለኖሩ ነው እንጂ እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ ስለሚጨክን አይደለም አንድ ሰው ለዘለዓለም ሕይወት የሚበቃውም ሆነ የሚፈረድበት በራሱ ሥራ እንጂ በትውልድ ሐረግ ወይንም በሌላ ሰው ሥራ አይደለም ሕዝ ዐ።