Detecting...
Please whitelist dirzon to continue.
ተጨማሪ ማብራሪያ ቢያስፈልጋችሁ የኮርስ መምህር ግሩም ጥበቡ ሀዝከፀከሀፀዐጊጠጡጠ መ ፀጠኋጂርዐበበ ሚያዚያ የእ ኮርስ መለማመጃ ፈተና መልሶች ሐ ለ ለ ሀ መ ሐ መ መ ሀ ሐ።
የኮርሱ አጠቃላይ ዓላማዎች ፅጩ ተመራቂዎቹ ይህንን ኮርስ ካጠናቀቁ በኋላ የዘገባን ምንነት አስፈላጊነትና ባህርያት ይገልፃሉ » የተለያዩ የደብዳቤ አይነቶችን በመለየት ደብዳቤ መፃፍ ይችላሉ የኢመደበኛ ዘገባን ምንነትና ዓይነቶች ይለያሉ ልዩ ልዩ ኢመደበኛ ዘገባዎችን ይጽፋሉ « የመደበኛ ዘገባን ምንነትና ባህርያት ይለያሉ የመደበኛ ዘገባን መረጃ ምንጮችና መረጃ መሰብሰቢያ መሣሪያዎች ይለያሉ ከተለያዩ የጥናታዊና የመስክ የመረጃ ምንጮች መረጃ በመሰብሰብና በማጠናቀር ጥናታዊ ዘገባ ይጽፋሉ ክፍል አንድ ልዩ ልዩ ደብዳቤዎችና ጽሁፎች የንዑስ ርዕሱ አላማ ተማሪዎች ይህን የቀረበላችሁን ማስታወሻ ካነበባችሁ በኋላ ይደቆኔጌፇ ምኔነፖ ፖናሃራጎቻታሥ ይደጋቆፍጌ ጴይዕዶቻ ፖረገራጎቻሥ ያመፅሪዖ ይፖ ደይን ሐምፇ ፅምፇ ፅማ ዳሳሚሃፃፍ ፖዕረዳጎቻሥ ያራጎቻቃሥ ደዓን ሐፈፈጋቻሥፖ ለጎማ ሦሪፉጎቻታሥ የሰው ልጅ ደብዳቤን ለረጅም አመታት የተለያዩ ተግባቦታዊ ተግባራትን ለማከናወን ሲጠቀምበት ቆይቷል አሁንም እየተገለገለበት ይገኛል ለዚህም በተለያዩ የአለም ክፍሎች የፖስታ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት ከረጅም ጊዜ በፊት ተቋቁመው ግልጋሎት በመስጠት ላይ ናቸው ምንም እንኳ የስልክ አገልግሎትና ሌሎች የመገናኛ ቴክኖሎጂዎች መበራከት በደብዳቤ መጠቀምን የቀነሱት ቢመስሉም ደብዳቤ አሁንም ቢሆን የሰው ልጆችን ተግባቦት በማሳለጡ ረገድ የማይተካ ሚና አለው በአገሮች መካከል በርካታ የዲፕሎማሲያዊና የደህንነት ጉዳኞች በደብዳቤ ልውውጥ አማካኝነት ይከናወናሉ ደብዳቤ ዘላቂነት ያለው ስለሆነ መልሶ መላልሶ ለማየትና በታሪካዊ ማህደሮች ውስጥም ሰንዶ ለማስቀመጥ ይመቻል ደብዳቤን መደበኛ አና ኢመደበኛ ደብዳቤ በማለት ልንከፍለው የምንችለው ሲሆን ሁለቱን የሚለያያቸው የሚከተሉት መንገድና የቋንቋ አጠቃቀማቸው ነው አሁን አሁን መደበኛ አና ኢመደበኛ ደብዳቤ ከሚለው አከፋፈል ይልቅ የመስሪያ የመስሪያ ቤት ደብዳቤና የግል ደብዳቤ የሚለው አጠራር እየተለመደ መጥቷል የመስሪያ ቤት ደብዳቤ አንዱ መስሪያቤት ተቋም ከሌላኛው መስሪያ ቤት ተቋም ወይም ግለሰብ ከመስሪያቤት ወይም መስሪያቤት ከግለሰብ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ለሚኖራቸው ግንኙነት የሚፃዛፉት ነው ሀ የመስሪያቤት ደብዳቤ የመስሪያቤት ደብዳቤ ሲባፍ ጥቅም ላይ የሚውለው ቋንቋ መደበኛነቱን የጠበቀና አክብሮትን የተላበሰ መሆን አለበት ስለሆነም በጥንቃቄ የሚነደፍና የሚፃፍ ነው በመስሪያቤት ደብዳቤ መተላለፍ የፈለገው ጉዳይ ወይም መልዕክት ብቻ ይቀርብበታል አህፅሮተ ዕሑፎች ጥቅም ላይ አይውሉም መደበኛ ወይም ዕውቅ ካልሆኑ በቀር ስርዓተ ነጥቦች በተገቢው መልኩ ጥቅም ላይ ይውሉበታል ተፃዛፊዎቹ በአካል ተገናኝተው ማብራሪያ የሚሰጣጡበት ሁኔታ የተገደበ በመሆኑ ማለት የተፈለገው ነገር በግልፅ ቋንቋ መቅረብ አለበት አሻሚ የሆኑ አገላለፆች ይወገዳሉ በተጨማሪም የመስሪያቤት ደብዳቤ የራሱ የሆነ ወጥ መዋቅር ወይም ንድፍ አለው በዚህ መዋቅር ውስጥም የተፃፈበት ቀን የላኪ አድራሻ የተቀባይ አድራሻ የሰላምታ ክፍል ርዕስ ዳዩ የሚተዋወቅበት መግቢያ ዋና ክፍል እና የመሰናበቻ ወይም የማጠቃለያ ክፍሎች ይኖሩታል ለ የግል ደብዳቤ የግል ወይም የቤተዘመድ ደብዳቤ በአባዛኛው በጣም ለምናውቀውና የቅርብ ግንኙነት ላለን ሰው የሚፃፍነው የግል ደብዳቤ ለምሳሌ ለጓደኛ ለወላጆች ወይም ለቤተሰብ አባል ለሆነ ሰው ይዛፋል ከግለሰቦቹ ጋር ባለን ቅርበት የተነሳም እንደዘዬቀበልኛ ያለ ኢመደበኛ ቋንቋ ጥቅም ላይ ይውላል ተቀባያችን እስከተረዳን ድረስ አህፅሮተ ጽሑፎችና በሌሎች ዘንድ የማይታወቁ ምልክቶችን ልንጠቀም እንችላለን ውል ያልያዙ በርካታ ጉዳዮችም በውስጡ ሊነካኩ ይችላሉ የግል ደብዳቤዎች ናፍቆት ለመግለጫነት ለሠላምታ ጤንነነትን ለመጠየቅ የፍቅር ወይ የገንዘብ ጥያቄ ለማቅረብ ሊፃፉ ይችላሉ ማመሳከሪያ ተቁ የተነሱ አንኳር ነጥቦች አዎ አይ ደብዳቤ ምን አንደሆነ ብጠየቅ አመልሳለሁ የደብዳቤ አይነቶችን ለይቼ አመለክታለሁ በመስሪያ ቤት ደብዳቤና በግል ደብዳቤ መካከል ያለ ተመስላሎና ልዩነት እዘረዝራለሁ ደብዳቤ በራሴ ማዘጋጀት እችላለሁ ማዕፖወሻው ያታጳያ ያ ይ ዉፀይም ሂምሥጳያታሃ ያማዕመም ያፖፇጋፇፅው ያ ይ ፇኔ መያሃ ሪመባፉሃ ለመሷሳያታ ክፍል ሁለት ኢመደበኛ ዘገባ የንዑስ ርፅሱ አላማ ሪጩ መምሥሀራሃ ይሀ ታዕ ፍጳሳ ታፖፓጎፇሥታ ያ ዕፅቋሏጴመደያኛ ምኃነፖ ፇረሃራጎቻታሥ ያሏመያያኛ ያ ያመድደያኛ ሀምሃ ዳፇያሟፈፀ ታህራራጎቻታሥ ይቃኃ ምፖባዔ ምጋታፖና ህፊዖም ፈይታቻሯሥ ታዕረዳጎቻታሥ ቃፅፖያዔ መያ ዖጄነሃሰ ልምድ መቀታማቻሥፇ ታፏቦጎቻሥራ ያመፅሰጳ ማዕፖወሻ ኋሕሄዴ መያፖ ዳጎያታ ፖናሃራጎቻታሥ ኢመደበኛ ዘገባ በይዘቱ አጠር ያለና አስፈላጊ የሚባሉ የዘገባ አካላትን ሳያሟላ የሚቀርብ ሲሆን የሚያቀርበውን ጉዳይ በጥልቀት አይተነትንም ከመደበኛ ዘገባ የሚለይበትም አንዱ መንገድም አጭር አቀራረብን የሚከተል መሆኑ ነው የኢመደበኛ ዘገባ አላማ ውሳኔ ለማሳለፍ የሚረዱ መረጃዎችን አጠናቅሮ ማቅረብ ነው መረጃን ከአንድ ወገን ወደ ሌላ ወገን በማስተላለፍ ጉዳዩን በሚመለከት በቂ ግንዛቤ በማስጨበጥ ላይ ያተኩራል ኢመደበኛ ዘገባ በስሩ በርካታ አይነቶችን ሊያካትት የሚችል ሲሆን ጥቂቶቹን ቀጥለን አንመለከታለን ሀ የማስታወሻ ዘገባ የማስታወሻ ዘገባ በአንድ መስሪያቤት ወይም ተቋም ውስጥ በሚገኙ ልዩ ልዩ የስራ ክፍሉች መካከል ለሚደረግ ውስጣዊ ግንኙነት የመልዕክትየሀሳብ መለዋወጫ ሆኖ ያገለግላል የማስታወሻ ዘገባ ጎናዊ ወይም ተዋረዳዊ ግንኙነት ባላቸው አካላት መካከል ይካሄዳል በሰራተኛች አርስበርስና በአመራሩና በሰራተኛው መካከል የማስታወሻ ዘገባ አበይት አላማዎች ማስታወስ ተጨማሪ ማብራሪያ መጠየቅ ትኩረት አንዲሰጥ ለማሳሰብ ወይም ትዕዛዝ ለማስተላለፍ ሊሆን ይችላል የማስታወሻ ዘገባ ሰላምታ ወይም ሌላ ትርፍ ነገር አያካትትም ማስታወሻ ዘገባው የተፃፈበት ክፍልግለሰብ ማስታወሻውን የፃፈው ግለሰብክፍል ቀን ጉዳዩ ዝርዝር ሀተታ የማስታወሻ ዘገባ ይዘት አንድ ነጠላ ጉዳይ ብቻ ጉዳዩን የሚመለከት መግለጫና ዋናውን ጉዳይ ብቻ የሚመለከቱ ሁለት ክፍሎች ብቻ አሉት አጭር ግልፅ ምጥንና የተጠቃለለ ሆኖ ሊቀርብ ይገባል ለ ሂደታዊ ዘገባ በሂደታዊ ዘገባ በአንድ ስራ ወይም ፕሮጄክት ውስጥ የተከናወኑ ተግባራት በቅደም ተከተል አየተብራሩ ይቀርቡበታል ሂደታዊ ዘገባ የሚዘጋጀው በአንድ በተወሰነ የጊዜ ገደብ ተከልሎ ሲሆን እንደአስፈላጊነቱ በየወሩ በየሶስት ወሩ በየስድስት ወሩ ወይም በየአመቱ ሊቀርብ ይችላል ዛሄደዊ ዘገባ በሚፃፍበት ወቅት ልክ እንደ ማስታወሻ ዘገባ ሄደታዊ ዘገባ የተፃፈለት አካልክፍል ሂደታዊ ዘገባውን የፃፈው ሰውክፍል ቀን ጉዳዩ እና ዝርዝር ሀተታ ይካተቱበታል ሄደታዊ ዘገባ የሚከተሉትን ዋና ዋና ነጥቦች በስሩ ያካትታል መግቢያ አክላማና የስራውየፕሮጀክቱ ባህሪ የተከናወኑ አበይት ተግባራት በቅደም ተከተል ያጋጠሙ ችግሮችና የመፍትሄ የተሰጡ የመፍትሄ ሀሳቦች ለወደፊት የታቀደ ዕቅድ ካለ ማጠቃለያ ሐ የጉዞ ወይም የመስክ ዘገባ አንድ ጉዞ ወይም የመስክ ምልከታጉብኝት ከተከናወነ በኋላ ተጠንቶና ተመርምሮ የሚፃፍ የዘገባ አይነት ነው የመስክ ዘገባ የሚከተሉትን ነጥቦች ማካተት ይገባዋል ዥህዢጭህዝ ዥ ዣ የዘገባው ርዕስ መግቢያ ዝርዝር መግለጫ መደምደሚያ ቀን ፊርማ ሁ ዘገባውን ያዘጋጀው ሰው ስም መ የንባብ ዘገባ የንባብ ዘገባ አንድ መፅሐፍ ወይም መጣጥፍ በትኩረት ከተነበበ በኋላ ንባቡን መሰረት በማድረግ የሚቀርብ ዘገባ ነው በአንድ የንባብ ዘገባ ውስጥ የሚከተሉት ንዑሳን ክፍሎች ይካተታሉ ሃሦ ደራሲውንፀሐፊውንና የቀረበውን ስራ የሚመለከት አጭር መግለጫ ጭምቅሀሳብ ትንተና ግምገማ ዥፔዢጭ ህዝ ዥጭ ሃ ሣጭ ሠ ቃለ ጉባኤ ምንነትና ባህርያት ቃለ ጉባዔ ኢመደበኛም ሆነ በመደበኛ የውይይት መድረኮች ወይም ስብሰባዎች በወቅቱ የቀረቡ አጀንዳዎችን ተሳታፊዎችን የተነሱ አበይትና ዝርዝር ነጥቦችን የተደረሰባቸውን ድምዳሜዎችና የወደፊት አቅጣጫዎች ወዘተ መዝግቦ የሚያስቀር ፅሑፋዊ መረጃ ነው ቃለ ጉባዔ ለታሪካዊ ሰነድነት ከማገልገሉም በላይ የተለያዩ ውሳኔዎችንም ለማሳለፍ በማጣቀሻነት ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል ቃለ ጉባዔ በስብሰባው የተነሱ ሀሳቦችን አንድም ሳያስቀር ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው የሚያትት ዝርዝር መግለጫም ተደርጎ መታየት የለበትም የሚጠበቅበት የተጨመቀ የተመጠነና በቅደም ተከተል የተቀናበረ የስብሰባ ሂደት ጠቋሚ ቀሪ መረጃ ማቅረብ ነው አለም እሼቱ ጋርትሳይድ ን ጠቅሶ እንዳቀረበው ቃለ ጉባዔ ሦስት አበይት ባህሪያት አሉት ሀቀኝነት ግልፅነትና ብሩህነት ሀ ሀቀኝነት በውስጡ የተካተቱት ነጥቦች ትክክለኛና አውነተኛ ሊሆነ ይገባል በቃለ ጉባዔ ሀቀኛ ነው ለመባል የጉባዔው አባላት በጋራ የሚያረጋግጡትን ሀሳብ ይዞ መገኘት አለበት ካልሆነ ግን አውነተኛነቱንና ተቀባይነቱን በከፍተኛ ደረጃ ይቀንሰዋል ለ ግልፅነት ቃለ ጉባዔ ተቀባይነትን ለማግኘት ግልፅ ሆኖ መገኘት አለበት ግልፅነት ያለው ነው ሲባል የተገለፁት ሀሳቦች በስብሰባው ያልነበሩ ሰዎችም ቢሆነ በቀላሉ አንብበው ሊረዲቸው ይችላሉ ማለት ነው ለግልፅነት ሲባል ቃለ ጉባዔ ያዝ በቃላት አመራረጡ በዓረፍተ ነገር አሰካኩና አጠቃላይ በሀሳብ አደረጃጀቱ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርበታል ሐ ብሩህነት ቃለ ጉባኤ የተጨመቀ የተመጠነና በቅደም ተከተል የተጠናቀረ ሀሳብን በተብራራ መንገድ ማቅረብ ይኖርበታል ቃለ ጉባዔ በስብሰባው ሂደት የተነሱ ሀሳቦችን በቅደም ተከተል ከገለፀ የተደረሰበትን ድምዳሜና የውሳኔ ሀሳብ ቁልጭ አድርጎ ካሳየ ብሩህ ነው ሊባል ይችላል ቃለ ጉባኤን መፃፍ የቃለ ጉባዔ ያዥ በተለይ በመንግስት መስሪያቤቶች አስቀድሞ የተመደበ ወይም ከሚያከናውናቸው ተግባራት ወይም የስራ ድርሻው አንዱ ይህንኑ መከወን የሚያስችለው ይሆናል መደበኛ ባልሆኑ ስብሰባዎች ግን ተወያዮች ተስማምተው የመረጡት ወይም ፊደል የቆጠረ ሰው ሊሆን ይችላል ቃለ ጉባዔ በመደበኛ አውድ ሲፃፍ የሚከተሉትን ነጥቦች ከግምት በማስገባት ሊሆን ይገባል የስብሰባውን ባህሪ መግለፅ ስብሰባው የተካሄደበትን ሰዓት ቀንና ቦታ በትክክል ማስፈር ተሳታፊ አባላትን ስም ዝርዝር ማስፈር ያልተገኙ አባላት ካሉ ስማቸውን መጥቀስ ያለፈ ስበብሰባ ቃለ ጉባዔን አቅርቦ ባስፀደቅ የተነሱ ሀሳቦችን በቅደም ተከተል ማስፈር አሰፈላጊ ሲሆን የቀጣይ ስብሰባ ቀንን መግለፅ ፍ ዴ ዒ ሏ ዒ ሏፌ ዒ ማመሳከሪያ ተቁ የተነሱ አንኳር ነጥቦች አዎ አይ ስለኢመደበኛ ዘገባ ምንነት መናገር እችላለሁ የኢመደበኛ ዘገባ አይነቶች እነማን እንደሆኑ አዘረዝራለሁ ቃለጉባኤ ከሌሎች የዘገባ አይነቶች በምን እንደሚለይ አስረዳለሁ የማስታወሻ ዘገባን ከንባብ ዘገባ ለይቼ መናገር አቅም አለኝ ማዕፖታወሻው ያፖያያ ያ ይሬ መፀም ጄ ምጳሷያፖ ያማዕፇመዎ ያፖሦጋፇፅው ጎያ ይ ሄኔ መፆ ሪመባፉሃ ለመሷሳያታ ክፍል ሦስት የመደበኛ ዘገባ አፃፃፍ የንዑስ ርዕሱ አላማ ፅጩ መምህራን ይህንን የኮርሱን ሦስተኛ ክፍል ትት ከተከታተላችሁ በኋላ በኢመደበኛና በመደበኛ ዘገባ መካከል ያለውን ልዩነት ትናገራላችሁ የመደበኛ ዘገባ ባህሪያትን ትዘረዝራላችሁ ለመደበኛ ዘገባ ሊደረጉ የሚገቡ ዝግጅቶችን ማከናወን ትችላላችሁ ሃ የምርምር ዘገባ የመረጃ ምንጮችን ትለያላችሁ ዘገባ አንድን የተከናወነ ተግባር ክስተት ወይም ሁነት በወቅቱ መዝግቦ በመያዝ የተገኘውን መረጃ መልሶ ለሌሎች ማሳወቅ ነው ስለዚህ በጊዜ ወይም በቦታ ርቀት ሁነቱን በአካል ሊመለከቱ እድል ያላገኙ አድማጮች ወይም አንባቢዎች በቀላሉ መረጃው በዘገባው አማካኝነት ይደርሳቸዋል ማለት ነው ዘገባ በቃል ወይም በፅሑፍ ቋንቋ አማካኝነት ሊቀርብ የሚችል ሲሆን ቃላዊ ወይም ፅሁፋዊ እንዲሆን የሚያደርገው የዘገባው አላማ ዘገባው የሚቀርብበት ሁኔታ ወቅታዊ ጉዳይ ዘገባው የሚቀርብለት አካልና ዘጋቢው ራሱ ሊወስኑት ይችላሉ ይሁን አንጂ ተፈላጊ እርማቶችን አድርጎ ዘላቂነት ባለው ሁኔታ ለማቅረብ የፅሁፍ ዘገባ ይመረጣል የዘገባ አይነቶችን ኢመደበኛ እና መደበኛ ብለን ልናያቸው እንችላለን እነዚህኑ መልሰን ከተግባራቸውና ከተፃፉበት አላማ አንፃር መረጃ ሰጭ ዘገባ ወይም ተንታኝ ዘገባ እና ከሚቀርቡበት ጊዜ አንፃር ደግሞ እለታዊ ሳምንታዊ ወርፃዊ ወይም አመታዊ ዘገባዎች ብለን አንከፍላቸዋለን መደበኛ ዘገባ ዝርዝር ጉዳዮችን የሚዳስስ እንደመሆኑ መጠን በደንብ በተደራጀና ዘገባ ማሚላት የሚገባቸውን አካላት በሙሉ አሟልቶ የሚገኝ ነው በዚህ ኮርስ ውሰጥ ትኩረት የተሰጠው መደበኛው ዘገባ ስለሆነ ይህንኑ ቀጥለን በዝርዝር እንመለከተዋለን ሀ የመደበኛ ዘገባ ምንነት መደበኛ ዘገባ ሰፊና ጥልቀት ያለውን ይዘት ስለሚያቀርብ በክፍል ክፍል ተከፋፍሎ ይፃፋል ስለሆነም መደበኛ ዘገባ የመግቢያ ዋና እና የመደምደሚያ ክፍሎች አሉት መግቢያው የማስዋወቅ ሚና ሲኖረው ዋናው አካል ደግሞ አብዩን ጉዳይ ያቀርባል የመደምደሚያው ክፍል ደግሞ አንኳር አንኳር ነጥቦችን በማንሳት ወይም የመፍትሔ ሀሳብ በማንሳት ዘገባው እንዲቋጭ ያደርጋል ጥናታዊ ወይም ምርምራዊ ዘገባ የመደበኛ ዘገባ ማሳያ ነው ለ የዘገባ መሠረታዊ ባህርያት ዘገባ የሚከተሉት መሠረታዊ ባህሪያት ይኖሩታል ትክክለኛነትና ሀቀኝነት ዘገባ በመረጃ የተደገፈና ሊረጋገጥ የሚችል መሆን አለበት በይሆናልና ግላዊ አስተያየት ላይ ተመስርቶ በቸልተኝነት መፃፍ የለበትም ይህ ካልሆነ ተቀባይነት አይኖረውም በህግም ያስጠይቃል ተጨባጭነትና ኢምናባዊነት ተጠየቃዊ እንጂ ስሜታዊ መሆን የለበትም ዘገባ ከፈጠራ ታሪክ መራቅ አለበት ፀሀፊው የራሱን ምናባዊ አለም እየተከተለ በስሜት መጻፍ የለበትም እውነታ መሠረቱ ሊሆን ይገባል በበሰለ ትንተናና በተጨባጭ መረጃ መደገፍ አለበት ቁጥብነት ለማለት የተፈለገውን ጉዳይ በተገቢጥቂት ቃላት በብቃት መግለፅ መቻል ጥሩ ዘገባ ከቃላት ድረታና ከድግግሞሽ የፀዳ ነው ቁጥብነት ከገፅ ማነስ ጋር መያያዝ የለበትም ኢኩ ግልፅነትና ሰዋስዋዊነት ዘገባ አሻሚነት ካላቸው አገላለፆች በፀዳ መልኩ ቀጥተኛና ግልፅ ሆኖ መፃፍ አለበት የሀሳብ ፍሰቱ የቃላት አመራረጡና የዓረፍተ ነገር አወቃቀሩ ከቋንቋው ሰዋስው ያፈነገጠ መሆን የለበትም ሃ ተነባቢነት የዘገባ የግልፅነት ባህሪ ተነባቢነቱንም እንዲጨምር ያደርገዋል አንድ ዘገባ ተነባቢ ለመሆን ከእንከን የፀዳ የወረቀት ላይ አሰፋፈሩ የተገራ ስርዓተ ነጥቦችን በአግባቡ የሚጠቀም መሆን አለበት ተገቢ ልሆኑ ቃላትን መጠቀምና የጽሁፍ አደረጃደቱን በጥንቃቄ አለመምራት ተነባቢነትን ይቀንሳል ኣላ ወቅታዊነት ዘገባ ወቅቱን የጠበቀ ካልሆነ ዋጋ አይኖረውም ዘገባ የተለያዩ ውሳኔዎችን ለመስጠትና አርምጃዎችን ለመውሰድ በመነሻነት ስለሚያገለግል በጊዜው ካልቀረበ ጠቀሜታ አይኖረውም ሐ በዘገባን ለመፃፍ የሚረዱ የቅድመ ዝግጅት ነጥቦች የዘገባውን የትኩረት ጉዳይአላማ አስቀድሞ መወሰን ዘገባው የሚሰራበትን ቦታ ተቋም መምረጥ የመረጃ ምንጮችን ማወቅ መረጃን ከተገቢው ምንጭ ዥ ዥኘ ሦጭ ሣጐሮ የመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያን መምረጥ ሁ ተግባራትን በቅደም ተከተል ለመከወን አስቀድሞ ማቀድ መ የዘገባ መረጃ ምንጮች የመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያዎች የመረጃ ምንጮችን ቀዳማይ ርቱዕ የመረጃ ምንጮችና ካልአይ ኢርቱዕ የመረጃ ምንጮች በማለት ልንከፍላቸው እንችላለን መረጃችንን በቀጥታ ከተገቢው ምንጭ ካገኘን ግለሰብ ወይም ሰነድ ይህ ቀዳማይ ምንጫችን ይሆናል መረጃ ከዋናው ምንጭ ሲገኝም አስተማማኝነቱ ይጨምራል ከዚህ ውጭ በተዘዋዋሪ ሌሎች ስለጉዳዩ ካሉት በመነሳት ወይም ስለዋናው የመረጃ ምንጭ የተወሰነ አውቂያ ካላቸው ሰዎች መረጃ ስንወስድ መረጃችን ኢርቱዕ ከሆነ ከካልዓይ ምንጭ ተገኘ ያስብለዋል ሠ የመስክ የመረጃ ምንጮች የመረጃ አሰባሰብ ከቤተ መፅሐፍትና ቤተ መዘክሮች ውጭ መረጃን ከመስክ ሰዎችን በማነጋገር በመጠየቅ ወይም ምልከታ በማካሄድ ልንሰበስብ እንችላለን ከመስክ መረጃ በሚሰበስብበት ወቅትም ተገቢ የሆነ አጋዥ መሳሪያዎች መፃፊያ መሳሪያዎች ካሜራና ቪዲዮ መቅረጫ ወዘተ አስቀድመው ሊዘጋጁ ይገባል የመስክ መረጃ በፅሑፍ መጠይቅ በቃለ መጠይቅ ሁ በምልከታና በፈተና ሊሰበሰብ ይችላል የምርምር ጥናታዊ ዘገባዎች አጭር ዳሰሳ ምርምር ሳይንሳዊ የሆነ አካሄድን በመከተል የችግሮችን ምንጭ ተጨባጭ መረጃ ላይ ተመስርቶ በመፈተሽ ጥልቅ ትንታኔ ያቀርባል የመፍትሄፄ ሀሳብም ይጠቁማል ከግላዊ አመለካትና ስሜት አንዲሁም ምናባዊነት የፀዳ መሆን አለበት ሃ ምርምር ለችግሮች መፍትሔ በመስጠት ላይ ያተኩራል ድምዳሜ ላይ ያስደርሳል ምርምር ጥልቅ ምልከታና ተጨባጭ ገለፃን ይጠይቃል መረጃን ከአስተማማኝ ምንጭ ይሰበስባል በጥንቃቄ የተመረጠ ቅደምተከተላዊ አካሂያድን ይከተላል ሦ ሦ ሦ ሃ ተጨባጭና ተጠየቃዊነትን የተላበሰ ነው ተቁ የተነሱ አንኳር ነጥቦች አዎ አይ ኋ የመደበኛ ዘገባን ምንነት ማስረዳት አችልለሁ የዘገባ ባህሪያትን ያለምንም ችግር አዘረዝራለሁ የዘገባ መረጃ ምንጭ አይነቶችን አለያለሁ ዬ ጩ ጥናትና ምርምር ለማድረግ የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎችን ተረድቻለሁ ማዕፖታወሻው ያፖያያ ያ ይነ መፀም ጄ ምጳሷያፖ ያማዕፇመምዎ ያሦጋፇፅው ጎያ ፅ ሄኔ መዖሃ ሪመባፉሃ ለመሷሳያታ በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ የዲፕሎማ ዕጩ መምህራን የብቃት መመዘኛ ፈተና ማዘጋጃ ጥያቄዎች ለእ ኮርስ የመስሪያ ቤት ደብዳቤ ሊፃፍ ከሚቻልባቸው ምክንያች መካከል ሊጠቀስ የማይችለው ሀ ቅሬታን ለማቅረብ ሐ ሠላምታን ለማቅረብ ለ የስራ ማመልከቻ ለማስገባት መ ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት የመስሪያ ቤት ደብዳቤ ሲፃፍ ሊዘነጉ የማይገባቸው ነጥቦች ሀ የመስሪያቤቱ ስምና አድራሻ ሐ ዋናው ጉዳይ ለ የመግቢያ ክፍል መ ሁሉም ምላሽ ይሆናሉ የግል ደብዳቤ ከመስሪያቤት ደብዳቤ የሚለየው ሀ መደበኛ ቋንቋ መጠቀሙ ሐ አላማው ጉዳይ ማስፈፀም መሆኑ ለ አህፅሮተ ፅሑፎችን መጠቀሙ መ የሚፃፍለት ግለሰብ አለመታወቁ ለመስሪያ ቤት ደብዳቤ የሚፅፍ ግለሰብ የደብዳቤውን ጭብጥ የሚያስረዳው ሀ በዋናሀተታ ክፍል ሐ በመደምደሚያ ክፍል ለ በመግቢያው ክፍል መ በሠላምታ ክፍል ከሚከተሉት ዓረፍተ ነገሮች መካከል አንዱ ስለደብዳቤ ልክ አይደለም ሀ በደብዳቤ የሚተላለፍ መልዕክት ጊዜና ቦታ አይወስነውም ለ የደብዳቤ አገልግሎት በታሪካዊ ሰነድነት እስከማገልገል ይደርሳል ሐ የቴክኖሎጂ መስፋፋት በደብዳቤ መጠቀምን አስቀርቷል መ የደብዳቤ ልውውጥ በሰዎች መካከል ያለ መካካድን ያስወግዳል የግል እና የስራ ደብዳቤ የሚያመሳስላቸው ሁለቱም ነው ሀ ላኪና ተቀባይ አካል ስላላቸው ሐ ቀንና ቦታን መጥቀሳቸው ለ የሚፃፉበት ምክንያት ስላላቸው መ ሁሉም ምላሽ ይሆናሉ የሚከተለውን የመስሪያ ቤት ደብዳቤ መዋቅር በመመልከት በቁጥር የተጠቆሙትን የደብዳቤ ክፍሎች ከተሰጡት አምራጭ ፊደሎች እየመረጣችሁ መልሱ በተራ ቁጥር በተጠቀሰው ቦታ ሊገባ የሚችለው ሀ የተፃፈበት ቀን ለ የላኪ አድራሻ ሐ መሰናበቻ መ ዋና ክፍል ተራቁጥር የሚወክለው የደብዳቤ ክፍል ሀ የላኪ አድራሻ ለ የተፃፈበት ቀን ጠ የተቀባይ አድራሻ መ የሠላምታ ክፍል በተራ ቁጥር ያለው ክፍት ቦታ የሚወክለው ሀ ጉዳዩ ለ ዋና ክፍል ሒሕ የተቀባይ አድራሻ መ ማጣቀሻ የደብዳቤውን ዋና ክፍል ወይም ሀተታ የሚወክለው ቁጥር ሀ ለ ሒ መጋ የባለጉዳዩ ስምና ፊርማ የሚሰፍረው ተራ ቁጥር የወከለው ቦታ ነው ሀ ለ ሒ መ ኢመደበኛ ዘገባ ከመደበኛ ዘገባ የሚለየው ሀ ሰፊ ትንታኔ የሚያቀርብ መሆኑ ሐ የመረጃ ምንጭ ሊሆን አለመቻሉ ለ አጭር አቀራረብን የሚከተል መሆኑ መ ሂደታዊ ሊሆን አለመቻሉ የማስታወሻ ዘገባ አላማዎች ተብለው ከሚታወቁት መካከል የማይጠቀሰው ሀ ትኩረት እንዲሰጥ ማሳሰብ ሐ ሰላምታ መለዋወጥ ለ ተጨማሪ ማብራሪያ መጠየቅ መ ትፅዛዝ ለመስጠት ቀጥሎ ከተዘረዘሩት ውስጥ ከአንዱ በስተቀር ሁሉም በማስታወሻ ዘገባ ውስጥ የሚያካተቱ ናቸው ሀ ማስታወሻውን የፃፈው አካል ሐ ቀንና የተፃፈበት ጉዳይ ለ የራስጌና የግርጌ ማህተም መ በጉዳይ ላይ ማብራሪያ ሂደታዊ ዘገባ ከሚታወቅባቸው መለያዎች ዋነኛው ሀ በክፍል በክፍል እየተከፈለ ሊቀርብ መቻሉ ሐ ላኪና ተቀባይ ያለው መሆኑ ለ የመግቢያ የሀተታና መደምደሚያ ክፍል ያለው መሆኑ መ የመፍፄ ሀሳብ መሰንዘሩ ዘገባው የሚቀርብበት ጉዳይን በተመለከተ በአካል ቦታው ድረስ ተገኝቶ መዘገብን የሚጠይቀው የኢመደበኛ ዘገባ አይነት ሀ የንባብ ዘገባ ሐ የማስታወሻ ዘገባ ለ የመስክ ዘገባ መ ቃለ ጉባዔ የጉባዔው አባላት በጋራ የሚያረጋግጡትን ሀሳብ ይዞ መገኘቱን የሚመለከተው የቃለ ጉባዔ ባህሪ ሀ ሀቀኝነት ለ ግልፅነት ሕ ብሩህነት መ ተነባቢነት ስብሰባ ሲካሄድ አከራካሪ ወይም የልዩነት ሀሳብ ቢነሳ ሀ የልዩነት ሀሳቡን ያነሳው ግለሰብ ይወገዛል ለ ሀሳቡ በድምፅ ብልጫ አንዲወሰን ይሆናል ሐ ሀሳቡ በልዩነት ተመዝግቦ ይያዛል መ ለ እና ሐ ምላሽ ይሆናሉ ቃለ ጉባኤን አስመልክቶ ከሚከተሉት መካካከል አንዱ ስህተት አለበት የቱ ነው። ሀ በመደበኛ ሁኔታ የሚያዝ ቃለ ጉባኤ የሚፃፈው አስቀድሞ በተመደበ ሰው ነው ለ ቃለ ጉባኤ ተቀባይነት የሚኖረው በተሳታፊዎች ፊርማ ሲረጋገጥ ነው ሐ ቃለ ጉባዔ ሲያዝ በውይይቱ ላይ ያልነበረ ሰው የውሳኔው ተገዢ አይሆንም መ የቃለ ጉባዔ ዘገባ በቀጣይ ሌላ አዲስ እቅድ ለማውጣት በመነሻነት ሊያገለግል ይችላል አንድን ዘገባ ቃላዊ ወይም ፅሁፋዊ እንዲሆን ሊያደርጉት ከሚችሉት መክከል የሚጠቀሰው ሀ የዘገባው አላማ ሐ ዘገባው የሚቀርብለት አካል ለ ዘገባው የሚቀርብበት ሁኔታ መ ሁሉም ምላሽ ይሆናሉ የመደበኛ ዘገባ ምሳሌ ከሚሆኑት መካከል በዋነኛነት የሚጠቀሰው ሀ ምርምራዊ ዘገባ ለ ቃለ ጉባኤ ሐ ጉዞ ማስታወሻ መ የንባብ ዘገባ ዘገባ ኢምናባዊ ይሁን ሲባል ማለት ነው ሀ በስሜት ይፃፍ ሐ የግል አስተያየት ይኑርበት ለ ፈጠራዊ አይሁን መ ሁሉም ምላሽ ናቸው አንድ ሰው መደበኛ ዘገባ ከመፃፉ በፊት ሊያከናውናቸው ከሚገቡ ነጥቦች መካከል የሚካተተው ሀ የዘገባውን የትኩረት ጉዳይአላማ አስቀድሞ መወሰን ለ ዘገባው የሚሰራበትን ቦታ ተቋም መምረጥ ሐ በሚሰበሰበው መረጃ የሚገኘውን ውጤት ይፋ ማድረግ መ የመረጃ ምንጮችን መምረጥና መወሰን አንድ ሰው በዘዬና በቋንቋ መካከል ያለውን ልዩነት ለማወቅ ፈልጎ ጥናት ማካሄድ ቢፈልግ የትኞቹን ተግባራት ማከናወን አለበት ሀ የየትኛውን ቋንቋ ዘዬ እንደሚያጠና መወሰን ለ ተዛማጅ ክለሳ ድርሳናትን መፈተሽ ሐ የመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያዎችን መምረጥ መ ሁሉም ምላሽ ይሆናሉ ጥናትና ምርምር ከሚደረግባቸው አላማዎች መካከል የማይጠቀሰው ሀ አዲስ ግኝት ለማግኘት ለ ቀድሞ የነበረን ግኝት መልሶ ለማረጋገጥ ሐ የሌሎችን ስራ ተቀባይነት ለማሳጣት መ ለተፈጠረ ችግር መፍትፄ ለመስጠት የፅሑፍ መጠይቅ ከቃለ መጠይቅ በተለየ ሀ መደበኛ ቋንቋን አይጠቀምም ሐ ለበርካታ ሰዎች ተደራሽ አይደለም ለ በርከት ያሉ ጥያቄዎች ይይዛል መ ፊት ለፊት የመገናኘት አድል ይፈጥራል በመምህርነት ሞያ ውስጥ የጥናትና ምርምር ስራ መታየት ያለበት ሀ የትምህርት አመራር አካልን ማስደሰቻነት ሐ የየዕለት የተማሪዎችን ችግር መፍቻ ቁልፍነት ለ የትምህርቱን ስራ ሊሻማ እንደሚችል መ በመምህራን ላይ ጫና እንደሚያሳድር አሁን ለሚደረግ ጥናታዊ ምርምር ዘገባ በመረጃ ምንጭነት የማያገለግለው ከሚከተሉት መካከል የትኛው ነው። ሀ አላማ መወሰን ርዕስ መምረጥ መረጃ መተንተን የመፍትሔ ሀሳብ መጠቆም ለ ርዕስ መምረጥ አላማ መወሰን የመፍትሔ ሀሳብ መጠቆም መረጃ መተንተን ሐ ርዕስ መምረጥ አላማ መወሰን መረጃ መተንተን የመፍትሔ ሀሳብ መጠቆም ሕ አላማ መወሰን መረጃ መተንተን ርዕስ መምረጥ የመፍትሔ ሀሳብ መጠቆም ለጥናት ውጤት የተሰበሰበ መረጃ ሲተነተን ሀ ቻርቶችንና ስዕላዊ መግለጫዎችን መጠቀም ተጨባጭነቱን ይጨምራል ለ የይመስለኛል አገላለፆች በስፋት ጥቅም ላይ መዋል የሚኖርባቸው ይሆናል ሐ ክለሳድርሳናት ስር የተጠቀሱት ንድፈ ሀሳቦችና እውነታዎች አይካተቱበትም መ በስነዘዴው ክፍል ስር ባልተጠቀሰ መተንተኛ መሳሪያ መሆን አለበት የዘገባ መሠረታዊ አላማ ከሚባሉት መካከል የማይጠቀሰው ሀ የምርምር ውጤቶችን ይፋ ማድረግ ለ ውሳኔ ለማሳለፍ የሚረዱ ዝርዝር መረጃዎች ማቅረብ ሐ ፅውቅናንና ሽልማትን ከሚመለከተው አካል ለማግኘት መ የውሳኔ ሀሳብ ለማስተላለፍ የሚያስችል ማስረጃ ለማቅረብ የፅሑፍ ዘገባ ከቃል ዘገባ ተመራጭ የሚሆነው ሀ የሀሳብ መንጠባጠብ ሳይኖር ማቅረብ ስለሚቻል ለ የተፃፈበት ቋንቋ መደበኛው ስለሆነ ለሁሉም አንባቢ የተመቸ ነው ሐ የጥናቱን ይዘት በስርዓታዊ ቅደም ተከተል ማቅረብ ስለሚያስችል መ ሦስቱም አረፍተ ነገሮች የያዙት ሀሳብ ትክክል ነው ኢመደበኛም ይሁን መደበኛ ዘገባ ሲፃፍ በብዛት ተግባር ላይ የማይውለው ተውላጠ ስም ያለበት መደብ ሀ አንደኛ ለ ሁለተኛ ሐ ሦስተኛ መ መልሱ አልተሰጠም በዘገባ ወቅት ቀጥተኛ ጥቅስ ዘዴን የምንጠቀመው ሀ የተናጋሪውን ሀሳብ እንዳለ ለማቅረብ ሐ አንባቢ እንዳይሰለች ለማድረግ ለ ያገኘነው መረጃ አጠራጣሪ ስለሆነ መ የጥናት ስራው በጋራ መሰራቱን ለማመልከት ጥናትና ምርምር ሲካሄድ የተገኘን መረጃ ምንጭ ሳይጠቅሱ ወይም የራስ አስመስሎ ማቅረብ ይባላል ሀ ማጭበርበር ሐ ማታለል ለ ፕላጃሪዝም መ ሪፖርቲንግ አንድን ፅሑፍ አንበብን ያገኘነውን መረጃ በራሳችን መንገድ አሳጥረን ካቀረብን ይህንን መረጃ የማቅረቢያ ስልት ብለን እንጠራዋለን ሀ ግለ ገለፃ ለ ቀጥታ ጥቅስ ሐ ጭምቃሳብ መ ተዘዋዋሪ ገለፃ አንድን ዘገባ ስናቀርብ ዘገባው የቀረበበትን ምክንያት የምንጠቁመው ክፍል ነው ሀ በመግቢያው ለ በመደምደሚያው ሕ በዋናው አካል መ በፍትፄ መስጫ የዘገባው እምብርት ተብሎ የሚታወቀው የዘገባ አካል ሀ መግቢያ ለ ዋና አካል ሐ የስነዘዴው ክፍል መ መደምደሚያው ዋቢ ፅሑፎችን አስመልክቶ ትክክል ያልሆነው ሀሳብ ከሚከተሉት መካከል የትኛው ነው። ሀ የተነበቡ ስራዎችን በሙሉ በዝርዝሩ ውስጥ ማካተት ለ የፅሑፍ ስራዎቹን በፊደል ቅደም ተከተል አከታትሎ መፃፍ ሐ ሁልጊዜም ቢሆን ከእንግሊዝኛ ምንጭ የተገኙትን ብቻ መጥቀስ መ የታተሙም ይሁኑ ያልታተሙ የተዘጋጁበትን ዓመተ ምህረት መጥቀስ መምህራን የሚያከናውኗቸው የምርምርና ጥናት ስራዎች በቀጥታ ከመማር ማስተማር ሂደቱ ጋር እንዲገናኙ የሚፈለገው ሀ በክፍል ውስጥ የሚያጋጥሟቸውን ተግዳሮቶች በቀላሉ እንዲፈቷቸው ለ ስራዎቹ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ማህበረሰቡን የሚጠቅሙ በመሆናቸው ሐ የመማር ማስተማሩ ጉዳይ የራሳቸው የመምህራኑ ጉዳይ ስለሆነ መ ከላይ የቀረቡት በሙሉ ትክክል ናቸው ከሚከተሉት አንዱ በቋንቋ ዙሪያ ለሚደረግ ጥናት ችግርርዕስ ምንጭ አይሆንም ሀ ቋንቋና ብዝሃነት ሐ ወረርሺኝና መፍትሔዎቹ ለ ቃላዊ ውሰትና አወንታዊ ጎኑ መ ብዝፃ ባህልና ስርዓተ ፆታ አንድ ተማሪ በትምህርት አሰጣጡ ላይ ያለውን ቅሬታ ለሚማርበት ትምህርት ክፍል በደብዳቤ ቢያሳውቅ ይህ የተማሪው ደብዳቤ አይነቱ ሀ የመስሪያቤት ደብዳቤ ሐ የቤተሰብ ደብዳቤ ለ የግል ደብዳቤ መ ኢመደበኛ ደብዳቤ የተማሪዎቻችንን ዘገባ የመፃፍ አቅም ሊያሳድጉልን ከሚችሉ መንገዶች መካከል የማይጠቀሰው ሀ ሞዴል ሆኖ መገኘት ሐ ሲፅፉ የሚፈጥሯቸው ስህተቶች ላይ ማተኮር ለ ተደጋጋሚ ሙከራ አንዲያደርጉ ማትጋት መ ግብረ መልሶችን በወቅቱ ተደራሽ ማድረግ አንድን ዘገባ መፃፍ ከመጀመራችን በፊት ቢጋር ማዘጋጀት የሚገባን ለምንድን ነው።