Detecting...
Please whitelist dirzon to continue.
ፊኛዋ ስለሞላ ለምርምር ጊዜ አልሰጣትም። «የምን እድል ነው ከየት ነው። ጥቁር አፈር አረንጓዴ ሣር በየተክሎቹ ሥርቻ ጨርሶ አይታይም። የዛሬው እለት ነፋሻማ ሆኖ ይበርዳል። እስካሁን ግን አጣዳፊ ሥራ አልገጠማቸውም። ሕዝቡ ከቦታ ቦታ በታክሲ እየተዘዋወረ ከመዝናናት አልፎ ፈነጠዘ። ያው የጨፈገገ ክረምት ነው። ሁኔታው አንደ ልደትና ሞት ዓይነት የኅብረተሰቡ የፍቅር መግለጫ ባህላዊ ልማድ ሆኖ ቆይቷል። ቦታው አሜሪካ ካሊፎርኒያ ኬኔዲ አየር ጣቢያ ነው።
ፋጡማ የነገሩን ሁኔታ በደንብ ሳትረዳ ጆኒ ከሆነ ሴት ጋር ባወራ ቁጥር በቶሎ ትቀናለች። ጆኒ እረጋ ባለድምፅ «አየሽ ፋጡማ ታሪኩን ጀመርኩልሽ እንጂ ገና አልጨረስኩም። ሁለት ወር አልፎ በሦስተኛው ገደማ እኔም እንደሷ ይገርምሻል ፋጡማ ሙች ፍቅር ያዘኝ። የሆነ ቀን እሷም ትንሽ ገንዘብ ሰጥታኝ ከኔም ጨማምሬ ጥሩ ሆቴል ይዘን አብረን አመሸን» ብሎ ጆኒ የፋጡማ ስሜት በቅናት እንዳይነካ ተጠንቅቆ የወሲቡን ጉዳይ አድበስብሶ ነገራት። ፋጡማ ። ክላውዝ በእለቱ ሥራ አልገባም። ፋጡማ ገና ሥራ እንደ ጀመረች ታክሲዋን ይዛ የሄደችው መኖሪያ ቤቷ ነበር። ሮዚ የለሊቱን ሥራ በቅልጥፍና አከናውና እረፍት ከማድረጓ በፊት አንድ ሁለት በሮች ለመሥራት ፈልጋ መኪናዋን ፈርፌልድ ከዘአ የታክሲዎች መቆሚያ ቦታ አሰልፋ ሙዚቃዋን ከፍታ ታዳምጣለች። ፋጡማና ጆኒ እረፍት አድርገው ኪስሜት ምግብ ቤት እራት በልተው ጨርሰው ሻይ ይጠጣሉ። ፋጡማ ብዙም ሳትቆይ በፉንክ አንድ በር ማለት የታክሲ አገልግሎት ሥራ ደረሳት። » «አመሰግናለሁ ሮዚ። » «ሥራ ሥራ። ፋጡማ በአባባሉ ተገርማ «ታዲያ ፍቅር ያለው መቼ ነው። «ፋጡማ ቅናት። ጆኒ ያለፈውን የለሊት የታክሲ ሥራ ጨርሶ እቤቱ የገባው ብቻውን ነበር። ጆኒ ምክንያቱ ባልታወቀ ምክንያት ብዙ ጊዜ የሆነ ነገር ጀምሮ መጨረስ አይሆንለትም። ጆኒ በበጋም ሆነ በክረምት በማናቸውም የወር መጀመሪያ አለት የታክሲ ሥራ መሥራት አይወድም። ሮዚ እንዳጋጣሚ ጥሩ የታክሲ አገልግሎት በር ደረሷት ሆላንድ ደርሶ መልስ ከሆነ ተሳፋሪ ጋር በብዙ ገንዘብ ተኮናተረች። ሁለቱም ታክሲያቸውን ይዘው ፋጡማ ቤት ደረሱ። ሮዚ ለምን እንደሄደ ምን ይዞ እንደ መጣ ጨርሶ አታውቅም። አዎ ሮዚ ገና ጀርመን እንደ ገባች የመጀመሪያ ወዳጄ የሲሪላንካ ተወላጅ ነበር። የታክሲ አገልግሎት ሥራ አልገባኝም። በእለቱ ክላውዝ ስለማይሠራ ሮዚ ትንሽ ቅር አላት። ደርቤ የታክሲ ሥራውን ከጀመረ ሰንብቶ ብዙ ጊዜ ሮዚ በሩቅ አይታ ሰላም እንኳን ሳትለው እንዳላየ ሆና በማለፏ ልቡ ቅር ብሎት ተጨንቆ ነበር። የታክሲ ሥራ ቢደራም ባለፈው ቀን ጆኒ በደንብ ስላልተኛ ደካክሟል። ሮዚ ሰሞኑን ሀገር ቤት እናቷ ጋ ስልክ ባለመደወሏ ስጋቷ ከእሷ አልፎ ኢትዮጵያ ኮበለለ። «ጆኒ ሥራ ጨርሶ ቤቱ ሄዷል። ሮዚ ምግብ ሳይሆን የሆነ ኬክ ብጤ አዛ ፋጡማ ፊት ለፊት ተቀመጠች። ፋጡማ ሥራ ጨርሳ እጆኒ ቤት ሲነጋጋ ደረሰች። ፋጡማ ጆኒ እስከሚመለስ ቁጭ ብላ አልጠበቀችውም። እረፋዱ ላይ ፋጡማና ጆኒ ከእንቅልፋቸው ነቅተው ሮዚ ቤት ስልክ ደውለው የሚያነሳው ጠፋ። ባለፈው ጊዜ ጆኒ ለፋጡማ ጨርሶ ያላወራላትን የድሮ ፍቅረኛውን ታሪክ ፋጡማ ጠይቃው ቡናውን ሩት እያለ በጀርባው ተንጋሎ ይህንኑ ታሪክ ቀጠለላት። ፋጡማ ንግግሩን አቋርጣ «እኔ እኮ ጆኒ እንደዚህ የምትቀና አይመስለኝም። ጆኒ የፋጡማ ሁኔታ አልተሰማውም። ሽ ሮዚ ባለፈው ጊዜ የመኪና አደጋ ደርሶባት እንብዛም ባትጐዳም ለታክሲ ሥራ ያላት ፍላጐት እያደር ቀዘቀዘ። ጆኒ የድርሰቱ ሥራ ውጥረት ስለመሰለው ፋጡማን ጨርሶ በሌላ አልጠረጠረም። ሮዚ «ሃሎ ጆኒ እንኳን አደረሰህ መልካም ገና። » ጆኒ በዚሁ ታላቅ በዓል ሳቢያ የሦስት ቀን እረፍት ወስዷል። የለሊቱ የታክሲዎች ሥራ ተጀምሮ ሮዚም ሆኑ ክላውዝ ፋጡማም ሆነች ጆኒ ሌሎችም ጭምር በእለቱ ሁሉም ሥራ ገብተዋል። ፋጡማና ክላውዝ ታክሲያቸውን የሆነ ቦታ አቁመው አብረው አንድ መኪና ውስጥ ተቀምጠዋል። ተንከባለሉ ፋጡማ ከላይ ሮዚ ከታች። ጥር ጥርርርር ጥርፋጡማ ስልኩን አንስታ «ሃሎ ፋጡማ ነኝ» ቀሰቀስኩሽ ይቅርታ ጆኒ ነኝ። ፋጡማ ዑስማን አዲሱ የታክሲ ድርጅት ተመዘገበች እንጂ ገና ሥራ አልጀመረችም። ጆኒ በእለቱ ሥራ ገብቶ የታክሲ አገልግሎቱን ያጣድፋል።